TG Telegram Group Link
Channel: ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር(Yoftahe Book Store)
Back to Bottom
ማስያስ
በዲያቆን ሚክያስ አስረስ
በደብተራ በአማን ነጸረ

#እግዚአብሔር የፍጡራን ሕሊና ከማይደርስበትና ከቶ ሊመረምረው በማይችል ፍጹም አዋቂነቱ በበዛ ቸርነቱ አዋቂ አድርጎ ከነጻ ፈቃድ ጋራ ፈጥሮናል፡፡ ለጥሪው ያንን ጠባይዐዊ ዕውቀትና ፈቃድ ተጠቅመን ምላሽ እንሰጣለን፡፡ ሃይማኖትና ዕውቀት የግድ የተፋቱ ናቸው አንልም፡፡ ሰው በጠባይዐዊ አእምሮው (ዕውቀቱ)ና በተሰጠው ነጻ ፈቃድ ወደፈጣሪው የመሳብ ፍጥረታዊ ዝንባሌ አለው እንላለን እንጂ፡፡ ያን ዝንባሌውን ከሚያሠምሩለት መንገዶች አንዱ በፍጥረታት መደመም ነው፡፡ ሰው የእግዚአብሔርን ሥራ ዐይቶ በመደነቅ ወደፈጣሪው ይሳባል፡፡ በፍጡሩ በመደመም ወደ ፈጣሪው ይደርሳል፡፡ በሥራው ተደንቆ እንዴት እንደሠራው ጠይቆ ከሕሊና በላይ ሲሆንበት ‹‹ያንተን ሥራ፡ ያንተን ግብር፡ ማን ይመራምር፤›› እያለ ይደነቃል፡፡ ሥነ ፍጥረት በተለይም ኦርቶዶክሳዊ ነገረ ሰብእ ከነገረ መለኮት ጋራ እየተሰናሰለ መነገሩ በቤተ ክርስቲያናችን የረታና የቀና አካሄድ ነው፡፡ የዘፍጥረት ‹‹አርአያ ወአምሳል›› ከብሉይ ተፈጥሮ እስከ ሐዲስ ተፈጥሮ በአያሌው ይመሠጠራል፡፡ ከጠባይዐዊ እውቀት የሚነሣው ይህ መጽሐፍ የብሉዩን መለኮታዊ የመገለጥ ትንታኔ ከቤተ አብርሃም እስከ ነገረ ማርያም ቀስ እያለ ያወርድና ነገረ መለኮትን ከሥነ ፍጥረትና የብሉያት የመገለጥ ዋዜማዎች (ጥላዎች) እያገናኘ በአንጻረ ሕገ ልቡናና ሕገ ኦሪት ተንትኖልን ሲያበቃ ምዕራፉን ለነገረ ሥጋዌ ይለቃል - ማስያስ ይመጣል፡፡

‹‹ረከብናሁ ለማስያስ›› ሐዋርያው በሲቃ የተናገረው ቃል ነው (ዮሐ.1፡41)፡፡ ባሕርያችንን ባሕርይ አድርጎ፣ ከእኛ እንደ አንዱ ሆኖ አገኘነው፡፡ ቃል ሥጋ ሆነ፡፡ ረቂቁ ገዘፈ፡፡ በሥነ ፍጥረት የምናውቀው አምላክ በሥጋ ብእሲ ታየ፤ ተዳሰሰ፡፡ ቃል ሥጋ ሆነ፡፡ በእርሱ ሥጋን መዋሐድ የሥሉስ ቅዱስ አንድነትና ሦስትነት ታወቀ፤ ተረዳ፡፡ ወደመለኮታዊ ክብሩ በቸርነቱ ሳበን፡፡ ለዚህም ምሥጢራተ ቤተ ክርስቲያንን ሠራልን፡፡ በተወደደ ሥርዓተ አምልኮ በምንሳተፍበት ቅዱስ ቍርባኑ አቀረበን፡፡ በቸርነቱ የመለኮታዊ ክብሩ ተካፋዮች አደረገን፡፡ አስቀድሞ በሰጠን አእምሮ ጠባይዕና ነጻ ፈቃድ፣ በየዘመናቱ በልዩ ልዩ አምሳል በመገለጥ፣ ኋላም ባሕርያችንን ባሕርይ በማድረግ ሥጋውን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ይኸው ምሥጢር የሚፈጸምባትን ቤተ ክርስቲያን በመመሥረት ወደራሱ አቀረበን፡፡ ቀድሞ በጥላ የምናውቀውን በአካል አገኘነው፤ ረከብናሁ ለማስያስ፡፡ የዚህ የታናሽ ወንድማችን መጽሐፍ ማጠንጠኛዋ እንደዚህ ይመስለኛል፡፡ መጽሐፏ ከብሉይ እስከ ሐዲስ፤ ከአእምሮ ጠባይዕ እስከ አእምሮ መንፈሳዊ፤ ከሃይማኖተ ሰሚዕ እስከ ሃይማኖተ ርእይ፤ ከምሳሌ እስከ ፍጻሜ ክርስቶስን ለማሳየት መሞከር፡፡ አስቀድማ በጥንተ ተፈጥሮ፤ በዕውቀትና ሃይማኖት፤ በብሉይ አምሳላት ሁሉ ጥላውን ታሳየናለች፤ ኋላ ደግሞ በኩነተ ሥጋ በአካል ‹‹ረከብናሁ ለማስያስ›› ታሰኘናለች፡፡ መጽሐፏ ረቂቅ የነገረ መለኮት ሐሳቦችን በውብ፣ ቀላልና ለዚህ ትውልድ በሚገባ ቋንቋ በምጥን ይዘት ታቀርባለች፡፡ አንብቦ ለመጠቀም ያብቃን፡፡

መልካም ንባብ!

ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore
ዚድራር

ስድስት አመታትን የወሰደዉ የዶ/ር ወሰን “ዚድራር” መፅሐፍ ሁለተኛ ዕትም ለንባብ በቅቷል!

ዚድራር የጥንታዊ ኢትዮጵያዉያንን ጥበብ እና ፍልስፍናን ያማከለ ሲሆን፣ በአንድ የኢትዮጵያን ዳግም ውልደት በሚያመጣ፣ የዓለምን ቅርጽ በቀየረ እና በሚቀይር ሚስጥራዊ ሰነድ (ቅርስ) ላይ ያተኮረ ነዉ። መጽሐፉ ከቅርሱ ጋር ተያይዞ በካፒታሊዝሙ እና ሶሻሊዝሙ ዓለም መካከል የነበረን፣ ያለን እና የሚኖርን ሽኩቻ ሲያሳይ፣ ታሪክን መሰረት ያደረገና እውነትን ያዘለ ነዉ። ዚድራር ሀገር ላይ ሳይወሰን አምስት አህጉራትን አማክሎ የተፃፈ ሲሆን ሀገር በቀል እውቀትን ጣራ ላይ የሰቀለ ሳይንሳዊ ይዘት ያለው ልብን ሰቅዞ የሚይዝ መፅሐፍ ነዉ። አለፍ ሲልም አሁን ሀገራችን ለገባችበት አረንቋ የመፍትሄ ሀሳቦችን የያዘ፣ በሀገራችን የነበሩት እና አሁን ያለዉ የፓለቲካ ዕሳቤዎች በኢትዮጵያ የስልጣኔ መስክ ላይ ያላቸዉን አንደምታ በምክንያት ይቃኛል።
በርካታ አንባቢያን ዚድራር ባለዉ ጠለቅ ያለ ዕሳቤ ከዉጭ መጻሕፍት ከታቦተ ፅዮን ፍለጋ፣ ከዘ አልኬሚስት፣ ከዳቬንቺ ኮድ ጋር፣ ከሀገር ዉስጥ ደግሞ ከዴርቶጋዳ እና ከእመጓ ጋር አነፃፅረዉታል። ይህ መፅሐፍ ወደ እንግሊዝኛ ተተርጉሞ አሜሪካ በሚገኘዉ በAFRICA WORLD PRESS አታሚነት ታትሞ አውሮፓ እና አሜሪካ ገበያዎች ላይ እንዲዉል ተቀባይነት ማግኘቱ የስራዉን ክብደት ከማሳየት አልፎ ነገ ሀገራችን በዓለም መድረክ የምትጠራበት ስራ ስለመሆኑ ማሳያ ነዉ ብለዉ ብዙዎች ተስፋ ያደርጋሉ።

የመፅሐፉ ገምጋሚ ፕሮፌሰር ባየ ይማም ዚድራር በኢትዮጵያ የስነ ፅሑፍ ዘርፍ ላይ አዲስ አሻራ እንደሚጥል ፍንጭ አስቀምጠዋል። እናንተም እንድታነብቡት ጋበዝን!
     ደራሲ (Author)፦ ዶ/ር ወሰን መኮንን

     አርታዒ እና የሽፋን ፅሑፍ፦
        1. ፕሮፌሰር ባየ ይማም (አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ)
        2. ደራሲ እና መምህር ዉቤ ታደገ

መፅሐፉን እኛ ጋር ያገኙታል።
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
የፈለጉትን መጻሕፍት በፈለጉት ጊዜና ሰዓት በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ስልክ👉 0902093535 ወይም 0918004191 ይደውሉ
ለማንኛውም ጥያቄ ሆነ አስተያየት👉 @yoftahiebot
Facebook ፔጃችን #Like ያድርጉ👇
https://www.facebook.com/yoftahiebookstore/
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04  ቋሪት ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
የፈለጉትን መጻሕፍት በፈለጉት ጊዜና ሰዓት በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ስልክ👉 0902093535 ወይም 0918004191 ይደውሉ
ለማንኛውም ጥያቄ ሆነ አስተያየት👉 @yoftahiebot
Facebook ፔጃችን #Like ያድርጉ👇
https://www.facebook.com/yoftahiebookstore/
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር

አድራሻችን👇
ባሕር ዳር ቀበሌ 04  ቋሪት ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
የፈለጉትን መጻሕፍት በፈለጉት ጊዜና ሰዓት በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
ስልክ👉 0902093535 ወይም 0918004191 ይደውሉ
ለማንኛውም ጥያቄ ሆነ አስተያየት👉 @yoftahiebot
Facebook ፔጃችን #Like ያድርጉ👇
https://www.facebook.com/yoftahiebookstore/
አድራሻችን👇
              hottg.com/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore  መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
አድራሻችን👇
              hottg.com/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore  መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
የመጽሐፉ፦ 48ቱ የኃያልነት ሕጎች
ደራሲ፦ ሮበርት ግሪን
ትርጉም ፦ ሀኒም ኤልያስ
#መጽሐፉን በልዩ ቅናሽ ከእኛ ጋር ያገኛሉ።
አድራሻችን👇
hottg.com/yoftahiebooks
ባሕር ዳር ቀበሌ 04 ቋሪት (ደንገል) ሁለገብ የገበያ ማዕከል ያገኙናል፡፡
ዮፍታሔ መጻሕፍት መደብር Yoftahie Bookstore መጻሕፍትን በተመጣጣኝ ዋጋ ያገኛሉ።
HTML Embed Code:
2024/04/27 07:32:43
Back to Top