TG Telegram Group Link
Channel: መቅረዝ
Back to Bottom
የመቅረዝ የ2016 እጩ ስራ አስፈፃሚዎች(psedo-8)

የተመረጡት ስራ አስፈፃሚዎች የ1 ወር የሙከራ ጊዜ ተሰጥቷቸው በብቃት ከተወጡ በዘላቂነት የስራ ሃላፊነቱን የሚረከቡ ይሆናል።
በምርጫውም መሰረት:

ኤፍሬም
በረከት
ቤተልሔም
ዳዊት
ትዕግሥት
አርሴማ
ናትናኤል
እየሩስ (ጄሪ)

የስራ ዘርፋቸው በቀጣይ የሚለቀቅ ይሆናል ።

⚠️ በነዚህ የስራ ዘርፍ እጩዎች ላይ ሀሳብ አስተያየት እና ቅሬታ ያላቹ መድረኩ ክፍት ነው እና በውስጥ @Yeabseraz መስመር አናግሩኝ ።

⚠️ ከላይ ያለው የስራ ዘርፍ አደራደር ምንም አይነት የሀላፊነት ብልጫ እና ማነስን አያመለክትም ለአገላለፅ ሰለተመቸ ብቻ ነው።

እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን ለማለት እንወዳለን! መልካም የስራ ዘመን!

የአብስራ ዘላለም
መ.ኪ.አ.ህ ፕሬዚዳንት
መሆን መኖር ስኬት !
መጋቢት 2015 ዓ.ም
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤው በሰላም አደረሳችሁ።
በዓሉ የሰላም እና የጤና እንዲሆን  እንመኝልዎታለን።


መቅረዝ የኪነጥበብ አፍቃሪያን ህብረት

@mekereze
@mekereze
ዒድ ሙባረክ! 🌙

እንኳን ለዒድ አል ፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

መቅረዝ የኪነጥበብ አፍቃሪያን ህብረት ለእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ መልካም በዓል ይመኛል!


መቅረዝ የኪነጥበብ አፍቃሪያን ህብረት

@mekereze
@mekereze
ለፕሬዝዳንትነት - ናትናኤል
ፀሐፊ - ዳዊት
ግንኙነት -  አርሴማ
ለተውኔት ክፍል - ትዕግሥት
ለ ሙዚቃ እና ዳንስ ክፍል - ቤተልሔም
ለስነ-ፅሁፍ ክፍል - በረከት
ለፋይናንስ - እየሩሳሌም
ለኤሌክትሮኒክ ሚዲያ እና በጎ አድራጎት - ኤፍሬም

የተመረጡት ስራ አስፈፃሚዎች የ1 ወር የሙከራ ጊዜ ተሰጥቷቸው በብቃት ከተወጡ በዘላቂነት የስራ ሃላፊነቱን የሚረከቡ ይሆናል።



⚠️ በነዚህ የስራ ዘርፍ እጩዎች ላይ ሀሳብ አስተያየት እና ቅሬታ ያላቹ መድረኩ ክፍት ነው እና በውስጥ @Yeabseraz መስመር አናግሩኝ ።

⚠️ ከላይ ያለው የስራ ዘርፍ አደራደር ምንም አይነት የሀላፊነት ብልጫ እና ማነስን አያመለክትም ለአገላለፅ ሰለተመቸ ብቻ ነው።

እንኳን ደስ አላችሁ ደስ አለን ለማለት እንወዳለን! መልካም የስራ ዘመን!

የአብስራ ዘላለም
መ.ኪ.አ.ህ ፕሬዚዳንት
መሆን መኖር ስኬት !
ሚያዝያ 2015 ዓ.ም
ተዋናይ እንቁስላሴ ወ/አገኘሁ ሆስፒታል ገብቷል።

በስርየት እና የእግር እሳቱ ተዋናይ ሁለቱ ኩላሊቶቹ በመድከሙ ነው ሆስፒታል የገባው።

ፈጣሪ ምህረቱን ይላክለት

@mekereze
⚠️ ቁምጣ ወይም ቱታ አድርጋቹ ኑ
#መቅረዛውያን_እንደምን_ቆያችሁ

አርብ ዛሬ  ሚያዝያ 27
🏟️  ስታዲየም አዳራሽ
10:00  ሰዓት ላይ Training አለ ሁላችሁም እንድትገኙ።
ነፍስ ይማር

ተማሪ ረድኤት ደረጀ እና ወላጅ አባቷ እልፈተ ህይወት የተሰማን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅን ለቤተሰቦቿቸው፣ለወዳጆቻቸው መፅናናቱን እንመኛለን።

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መቅረዝ የኪነጥበብ አፍቃሪያን ህብረት

@mekereze
Forwarded from Natty Blattena
መቅረዝ የኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን ህብረት

መቅረዝ በቅድሚያ የአክብሮት ሰላምታውን እያቀረበ ከዕረፍት ቆይታችሁ በኋላ ወደ ትምህርት ግዜያችሁ የተመለሳችሁትን ውድ ቤተሰቦቹንና ወዳጆቹን እንኳን በደህና መጣችሁ ይላል።

🔲 እንደ ቀድሞው ሁሉ መቅረዝ በመጭውም ግዜ ውድና ውብ የሆኑትን ዕንቁ የጥበብ ስራዎቹን እያዘጋጀ ለውድ ተደራሲዎቹም ያለ ስስት እያቀረበ ይቀጥላል።

🔲 ታድያ አሁንም እንደ በፊቱ መቅረዝ ነባር አባላቶቹን(ቤተሰቦቹን) እጅ ከምን እያለ እንደ አዲስ መቀላቀል ምትፈልጉትን የጥበብ ወዳጆች ደግሞ ኑልኝ እያለ እጁን ዘርግቶ ይጠብቃል።

📌 ያልመጣም በሰላም ይምጣ የመጣም ባለበት በቸር ይቆይ እያልን በቀጣይ የመገናኛችንን ግዜና ቦታ የምናሳውቃችሁ መሆኑን በአክብሮት እየገለፅን አብራቹን እንድትዘልቁ በጥበብ ስም እንጠይቃለን።

መቅረዝ ኪነ-ጥበብ አፍቃሪያን ህብረት
መሆን መኖር ስኬት!
ነሐሴ 2016 ዓ.ም
የሀዘን መግለጫ
በሀዋሳ ዩኒቨርስቲ በኤሌክትሮ ሜካኒካል ኢንጂነሪርግ የ2009 ዓ.ም ባች እና አሁን በስራ አለም ላይ የነበረው ባርክልኝ አበራ በአጋጠመው ድንገተኛ አደጋ ህይወቱ ማለፉ ሰምተናል።

በመሆኑም እኛ የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መቅረዝ የኪነጥበብ አፍቃሪያን ህብረት ለወጣት ባርክልኝ አበራ ነፍሱን ፈጣሪ ከደጋጎቹ ጎን እንዲያሳርፍል እና ለቤተሰቦቹ፣ጓደኞቹ፣ለወዳጅ ዘመዶቹ እና ለስራ ባልደረቦቹ መፅናናትን እንመኛለን።

የሀዋሳ ዩኒቨርስቲ መቅረዝ የኪነጥበብ አፍቃሪያን ህብረት
@mekereze
መስከረም 2, 1967 ዓ.ም የደርግ አባላት 13 ሆነው ወደ ቤተ-መንግሥት ሄዱና ጃንሆይ የአገዛዝ ዘመናቸው ማብቃቱን አረዷቸው፡፡ የደርግ አባላት ቤተ-መንግሥት ደርሰው ንጉሱን አስጠሯቸው፡፡

ንጉሱም በዝግታ ከፎቅ ላይ ወርደው በዙፋናቸው ላይ ሲቀመጡ የደርግ አባላት ደነገጡ፡፡ ሻምበል ደበላ ዲንሳ ደርግ የወሰነውን የውሳኔ ሃሳብ አነበቡ …

"ለሀገርና ለህዝብ ደህንነት ሲባል በዛሬው ዕለት ግርማዊ ቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከስልጣን ወርደዋል፤ ለደህንነትዎ ሲባልም አስተባባሪው ኮሚቴ ወዳዘጋጀልዎ ቦታ እንዲሄዱ ተወስኗል …" የሚል ይዘት ያለው ደብዳቤ አነበቡ፡፡

ሻምበል ደበላ ውሳኔውን አንበበው ሲጨርሱ ንባባቸውን ሲጀምሩ የሰጡትን ወታደራዊ ሰላምታ ደገሙ፡፡ ንጉሱም ዝም ብለው ቆዩና መናገር ጀመሩ፡፡

"ያነበባችሁትን ሰምተናል፤ የኢትዮጵያ ንጉሰ ነገሥት ስንሆን ስም ብቻ አይደለም፡፡ ቢሆንም በየጊዜው የሚለዋወጠው ነገር ደግሞ ላገር የሚጠቅም ነገር እስካለበት…

የኢትዮጵያን ታሪክ ጠብቃችሁ ማልማት ከቻላችሁ የእኛ ታሪክ እዚህ ላይ ያበቃል፤ ካልቻላችሁ የእናንተ ታሪክ ያበቃና የእኛ ይቀጥላል ፤ አገራችንንና ሕዝባችንን በምንችለው አገልግለናል ፤ የኢትዮጵያ ሕዝብ እድል የእኛን መወገድ የሚጠይቅ ከሆነ ስራችንን አቁመን ማንኛውንም ነገር ለመቀበል ዝግጁ ነን፤ ‹አሁን ተራው የእኛ ነው› ካላችሁ ኢትዮጵያን ጠብቁ›› በማለት ተናገሩ፡፡

… ከዚያም ንጉሱ ውብ በሆነችው ሮልስ ሮይስ መኪናቸው ሳይሆን ባረጀች ሰማያዊ ቮልስ ዋገን መኪና ተጭነው ወደ አራተኛ ክፍለ ጦር ግቢ ተወሰዱ፡፡
"ወደ ዋገን ወርደው ሲተኩ በሌላ" እንዲል ቴዲ አፍሮ

@mekereze
Forwarded from Natty Blattena
ሰላም መቅረዛውያን እንደምን አላችሁ!🙏
ነገ ማክሰኞ 15/01/2016 ውብ ልምምድና የጥበብ ግዜ ስለሚኖረን ሁላችሁም እንድትገኙ።

በአዲሱ አመት በአዲስ መንፈስ በአዲስ ሃሳብ
ቆንጆ የመድረክ ስራ መስራት ስለምንጀምር የሚቀር ወይ የሚያረፍድ ሰው ካለ እጅግ እንደሚቆጭ እርግጥ ነው።

መቅረዝ ዳግም በተወዳጅ ስራዎቹ ወዳጆቹን
ሚያስደምምበት ግዜ አሁን ነው። ሁላችንም Stadium በሚገኘው አዳራሻችን እንገናኝ።
ሰዓት: 11:30
#መቅረዝ
#መሆን_መኖር_ስኬት
#ሰላም_ይስጠን
HTML Embed Code:
2024/05/17 21:45:49
Back to Top