TG Telegram Group Link
Channel: ሃይማኖት አንድ ናት
Back to Bottom
- ክርስቶስ ተጸነሰ-ተወለደ ስንል ለዚህ ሁሉ ምሥጢር ማካተቻና የድኅነታችን መጀመሪያ: የመመኪያችን ዘውድና የንጽሕናችን መሠረት ድንግል ማርያም ናትና ከፈጣሪ ቀጥሎ ታላቅ ክብር: ምስጋና: ስግደትና ውዳሴ ለእርሷ ይገባታል:: መድኅናችን ክርስቶስ ያዳነን በእርሷ ምክንያት ነውና::

- ሠለስቱ ምዕት [ ፫ መቶ ፲፰ [318] ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት) ይህንን ምሥጢር ሲያደንቁ እንዲህ ብለዋል :-

- በሥጋ ማርያም ጌታ ተጸነሰ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ተወለደ
- በሥጋ ማርያም ጌታ አደገ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ተጠመቀ::

- በሥጋ ማርያም ጌታ አስተማረ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ተሰቀለ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ሞተ
- በሥጋማርያም ጌታ ተነሳ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ዐረገ
- በሥጋ ማርያም ጌታ በአባቱ ቀኝ ተቀመጠ
- በሥጋ ማርያም ጌታ ዳግመኛ በሕያዋንና ሙታን ላይ ይፈርድ ዘንድ ከመለኮቱ ኃይል ጋር ይመጣል:: [ መጽሐፈ ቅዳሴ ]

- በዚያውም ላይ ለዘለዓለም ድኅነት የምንመገበው የጌታ ሥጋና ደም መለኮት የተዋሐደው የድንግል ማርያም ሥጋና ደም ነው::

" ለድንግል ማርያም ክብርና ውዳሴ ከስግደት ጋር ይሁን !!! "

- የድንግል ማርያም ልጅ አማኑኤል ክርስቶስ በርሕራሔው ይማረን:: ከበረከተ ልደቱም ያሳትፈን::

🕊

[ † ታሕሳስ ፳፰ [ 28 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. አማኑኤል አምላካችን
፪. በዓለ ጌና ስቡሕ
፫. ዕለተ ማርያም ድንግል
፬. ፻፸፬ "174" ሰማዕታት [ የቅዱስ ዻውሎስ ማሕበር ]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱሳን [ አብርሃም: ይስሐቅና ያዕቆብ ]
፪. ቅዱስ እንድራኒቆስና ሚስቱ ቅድስት አትናስያ
፫. ቅድስት ዓመተ ክክርስቶስ
፬. ቅዱስ ቴዎድሮስ ሮማዊ
፭. ቅዱስ አባዲርና ቅድስት ኢራኢ

" የዳዊት ልጅ ዮሴፍ ሆይ! ከእርስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነውና እጮኛህን ማርያምን ለመውሰድ አትፍራ:: ልጅም ትወልዳለች:: እርሱ ሕዝቡን ከኃጢአታቸው ያድናቸዋልና ስሙን ኢየሱስ ትለዋለህ:: በነቢይ ከጌታ ዘንድ:-
'እነሆ ድንግል ትጸንሳለች:: ልጅም ትወልዳለች:: ስሙንም አማኑኤል ይሉታል::' የተባለው ይፈጸም ዘንድ ይህ ሁሉ ሆኗል:: ትርጉዋሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር የሚል ነው::" [ ማቴ.፩፥፳]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †

[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]

         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🛑🛑የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ የተዋህዶ ልጆች አክሊል ሚዲያ ተተኪ ዘማርያን የምናፈራበት መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ ተከፈተ አሁኑኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ለነፍስዎ ብዙ ነገር ያተርፋሉ@aklil media


https://youtu.be/-S_ZG86A9Bc?si=0HlMPv5UnuqJ9Vv4
Audio
💒 ለጥምቀቱ መልእክት ይደመጥ ❤️
ጥምቀት ምንድን ነው?

ተወዳጆች የኢትዮጲያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ልጆች እንኳን ለጌታችንና ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ጥምቀት በሰላም አደረሳችሁ እያልን ነገረ ጥምቀቱን እንዲህ መናገር እንጀምራለን

ጥምቀት በጽርዕ ቋንቋ ኤጲፋኒያ በግእዝ አስተርዮ በአማርኛ መገለጥ ይባላል።

ጥምቀት “አጥመቀ” ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ፍቺውም በገቢር መንከር፣ መድፈቅ፣ መዘፈቅ፣ በተገብሮ መነከር፣ መደፈቅ፣ መዘፈቅ፣ መላ አካልን በውኃ ውስጥ ማስገባት ማለት ነው።

በሌላ አገላለጽ ጥምቀት ማለት በተጸለየበት ወይም በተለየና በከበረ ውኃ (ማየ ገቦ ወይም ማየ ሕይወት) ውስጥ በሥላሴ (በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ) ስም ከራስ ፀጉር እስከ እግር ጥፍር መጥለቅ፣ መዘፈቅ፣ መነከር ማለት ነው። በመሆኑም የምንጠመቅበት ውኃ ተራ ውኃ አይደለም።

ጥምቀት ከሰባቱ ምሥጢራተ ቤተክርስቲያን አንዱ ነው።

💎የጥምቀት በዓል ከዘጠኙ የጌታ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ነው

💎በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እምነትና ሥርዓተ አክብሮት መሠረት በየዓመቱ ከጥር አሥር እስከ አሥራ አንድ ቀን በደማቅ ሥነ ሥርዓት በካህናት፣ በምዕመናንና በሰንበት ት/ቤት ወጣቶች አገልግሎት ይከበራል።

💎 በዓሉ የሚከበረው ጌታ በዕደ ዮሐንስ በማየ ዮርዳኖስ የተጠመቀበት ምሥጢረ ጥምቀትና ሥርዓተ ጥምቀትን የመሠረተበት ዕለት በመሆኑ ነው። ጌታ የተጠመቀው በተወለደ በሠላሳኛው ዓመት ሲሆን ያ ወራት ዮሐንስ መጥምቁ ሕዝቡን እየሰበሰበ የንስሐ ጥምቀት የሚያጠምቅበት ጊዜ ነበር:: 📗ማቴ. 3:1📗

ታሪካዊ የጥምቀት በዓል አከባበር በኢትዮጲያ

💧ታላቁ የከተራ እና የጥምቀት በዓል ሲነሳ ኢትዮጵያውያን ሩቅ ዘመንን ተሻግረን የቅዱሳን ሰማዕት አባቶችን፣ የሊቃውንት አባቶችን አስተምሮት እናዘክራለን።

💧በቅዱስ ላልይበላ ዘመነ መንግሥት በኢትዮጵያ ምድር እየተመላለሱ በብሕትውና እና በስብከተ ወንጌል ያገለግሉ የነበሩት ጻድቁ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ በአክሱም፣ በመቐለና በመርጡለ ማርያም እየተዘዋወሩ ባሕረ ጥምቀቱን ባርከዋል።

💧በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት (1260-1275 ዓ.ም) በጻድቁ አቡነ ተክለ ሃይማኖት (1203-1204 ዓ.ም) አሳሳቢነት የተጀመረው ሥርዐተ በዓል ተጠናክሮ እንዲቀጥል በዐዋጅ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

💧ታቦታቱም በሕዝብ ጥበቃና እንክብካቤ ተደርጎላቸው በየጥምቀተ ባሕሩ እንዲያድሩ ወስነዋል።

💧የበዓሉ አከባበር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየሰፋና አድማሱ ብሔራዊነትን እየያዘ መጣ።

💧ከዐፄ ገብረ መስቀል ጀምሮ የአደባባይ በዓል የሆነው የጥምቀት በዓል በ15ኛው ክ/ዘመን በደገኛው ኢትዮጵያዊው ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ (1426-1460 ዓ.ም) አማካኝነት ታቦታቱ ወደ ወንዝ ወርደው ዕለቱን እንዳይመለሱ፣ በዚያ ፈንታ በጥምቀት ዋዜማ ጥር 10 ቀን ከሰዓት በኋላ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ ወርደው እንዲያድሩ፣ አገሩን በኪደተ እግር ይባርኩም ዘንድ በሄዱበት መንገድ እንዳይመለሱ በዐዋጅ ወሰኑ።

💧ይህን ታሪክ በመከተል ዐፄ ናዖድ (1486-1500) ዓ.ም) ማንኛውም የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሃይማኖት ምእመን ታቦተ ሕጉ ወደ ባሕረ ጥምቀቱ በሚወርድበት እና ከባሕረ ጥምቀቱ ወደ ቤተ መቅደሱ በሚመለስበት ጊዜ አጅቦ አውርዶ፣ አጅቦ መመለስ እንዳለበት timqet celebration በዐዋጅ አስነግረው ነበር።

💧ሕዝቡም ታቦታተ ሕጉን በሆታና በእልልታ ከቤተ መቅደስ አጅቦ ካወጣ በኋላ በባሕረ ጥምቀት ከትሞ ማደር ጀመረ ።

💧ኢትዮጵያ ዜና ጥምቀተ ክርስቶስን ከሰማችበት ከመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን አንሥቶ በተለይም ከአጤ ገብረ መስቀል ዘመነ መንግሥት (6ኛው መ/ክ/ዘ) ወዲህ የጥምቀትን በዓል ዛሬ በሚታየው አኳኋን ስታከበር እንደ ቆየች ይታመናል።

💧በክብረ በዓሉ ከመንበረ ክብራቸው ወጥተው ወደ ባሕረ ጥምቀት የሚወርዱት ታቦታት በካህናቱ ሃሌታ፣ በምእመናኑ እልልታ እና በየአጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ በተቋቋሙ የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች መዝሙሮች ታጅበው በተመሳሳይ አኳኋን እንደሚመለሱ ይታወቃል።

እስትንፋስ ያለው ሁሉ እግዚአብሔርን ያመስግን።

መዝሙረ ዳዊት ፻፶፥፮

💎ጌታችን በተጠመቀ ጊዜ የዮርዳኖስ ወንዝ የላይኛው ሸሽቶ ወደ ላይ ተመልሶ ሽቅብ ፈሷል። የታቹም ወደ ታች ሸሽቷል። የላይኛው ፈሳሽ ተቋርጦ እንደ ክምር ተቆልሎ ቀርቷል።

💎ቅዱስ ዳዊት የተመለከተውም ይህንኑ ነው።

ከአዳም ጀምሮ እስከ ክርስቶስ ድረስ በዘር ይወርድ የነበረው ፍዳ መርገም በክርስቶስ ቤዛነት ተቋርጦ፤ የታቹም ፈጽሞ መድረቁ ኃጢአተ አዳም የመጥፋቱ ምሳሌ ነው።

እስራኤል ፈለገ ዮርዳኖስን ተሻግረው ወደ ኢያሪኮ መሔዳቸው ምእመናን በጥምቀት ከኃጢአት ቍራኝነት ተላቀው እግራቸውን ወደ ልምላሜ ገነት ወደ ዕረፍት መንግሥተ ሰማያት አቅንተው ለመሔዳቸው ምሳሌ ነው።

ኢያሱ የጌታ፣

እስራኤል የምእመናን፣

ዮርዳኖስ የጥምቀት፣

ምድረ ርስት የገነት መንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው።

ታቦቱን አክብሮ የሚሔደው ካህን የቅዱስ ዮሐንስ፣

ታቦቱ የጌታችን፣

ባሕረ ጥምቀቱ የዮርዳኖስ ወንዝ፣

ታቦታቱን አጅበው የሚሔዱትና በዓሉን የሚያከብሩት ምእመናን ወደ ቅዱስ ዮሐንስ እየመጡ የንስሐ ጥምቀት ሲጠመቁ የነበሩት ሰዎች ምሳሌዎች ናቸው።

ታቦታቱ በጥምቀት ዋዜማ ከመንበራቸው ወደ ጥምቀተ ባሕር መውረዳቸውና በዚያ ማደራቸው ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ በፈለገ ዮርዳኖስ ከማታው ጀምሮ መውረዱንና ተሰልፎ ተራውን ሲጠብቅ ማደሩን ያጠይቃል።

‹‹ጥምቀት የሞቱና የትንሣኤው ምሳሌ ነው።

👉ከኃጥአን ጋር ተቆጥሮ እንዲጠመቅና እንዲሰቀል የተጻፈውን ቃል ንስሐና ጥምቀት የማያስፈልገው ሲሆን ነገር ግን ፍጹም ኃጥእ መስሎ በዮሐንስ እጅ ጥምቀትን ለመፈጸም በማየ ዮርዳኖስ እግር ተጠመቀ።››።

💎ጌታችን የተጠመቀበት ወርኀ ጥር በእስራኤላውያን ዘንድ የዝናብ፣ የበረዶ ወራት ነው። ከወንዝ ዳር ያለ መጠለ

ያ መዋልና ማደር አይቻልም። በመኾኑም ከዮሐንስ ለመጠመቅ የሚሄዱ ሰዎች ሁሉ በዮርዳኖስ ዙሪያ ድንኳናቸውን ተክለው ያርፉ ነበር። በዚህ አንጻር ዛሬም በባሕረ ጥምቀት ዙሪያ ድንኳኖች ዳሶች ይጣላሉ።

በሀገራችን በተለያዩ አካባቢዎች በተለይ በአክሱም የንግሥት ሳባ መዋኛን ‹‹ማይ ሹም›› በጎንደር የዐፄ ፋሲል መዋኛን፣ በላስታ የላሊበላ መዋኛን፣ በሸዋ የዐፄ ዘርዐ ያዕቆብ ፍርድ መስጫ አደባባይን፣ አርባ አራት ታቦታት የሚያድሩበትን የሸንኮራ ሜዳን “ራቡቴ ወንዝ” በአዲስ አበባ ደግሞ ጃንሆይ ሜዳን /ጃንሜዳን/ ወዘተ ለአብሕርተ ምጥማቃት እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። እኒህ ቦታዎች ዛሬም ድረስ ተከብረው ይገኛሉ።

💎እኛ በዚህ ወቅት ታቦት ይዘን፣ ከወንዝ ወርደን፣ ድንኳን ተክለን በማክበራችን ይፈጸማል፡፡
“ሕዝቡም ሁሉ ከተጠመቁ በኋላ ኢየሱስ ደግሞ ተጠመቀ። ሲጸልይም ሰማይ ተከፈተ፥
መንፈስ ቅዱስም በአካል መልክ እንደ ርግብ በእርሱ ላይ ወረደ፤ የምወድህ ልጄ አንተ ነህ፥ በአንተ ደስ ይለኛል የሚል ድምፅም ከሰማይ መጣ።”

  — ሉቃስ 3፥21-22
#መድሃኒአለም ማለት የአለም ሁሉ መድሃኒት ማለት ነዉ
ስጋዉን ቆርሶ ደሙን አፍስሶ ለኛ ሲል ህይወቱን የሰጠ

፨ አሮንና ልጆቹን 🌺ለክህነት የመረጠ
፨ ኤልያስን .🌺 በአዉሎ ነፋስ የነጠቀ
፨ እዮብን 🌺በባእድ ሀገር ከፍ ከፍ ያደረገ
፨ ሎጥን 🌺ከእሳት ያወጣ
፨ ለሳምሶን 🌺ሀይልን የሰጠ
፨ አዛርያን አናንያን ሚሳኤልን🌺 ከእሳት የታደገ
፨ ጥበብና ማስተዋልን 🌺ለሰለሞን የሰጠ
፨ ያዕቆብን 🌺 በመንገዱ የጠበቀ እና የባረከ
፨ እስራኤልን 🌺ከግብፅ ባርነት ያወጣ
፨ ለሙሴ 🌺ጽላት የሰጠ
ለኪሩቤል ላይ የተቀመጠ ክብሩንም የገለጠ ስጦታዉ የማያልቅበት

#ቸሩ_መድሃኒአለም_ይክበር ይመስገን_አሜን /፫/
#መድኃኒአለም 🌺የገዢዎች ሁሉ ገዢ
#መድኃኒአለም 🌺የነገስታት ሁሉ ንጉስ
#መድኃኒአለም 🌺 የፍጥረታት ሁሉ ፈጣሪ ነዉ
ኃይሌን ጉልበቴን ታድሳለህ
ቀና ቀና እንድል ታደርጋለህ
መድኃኒአለም መድኃኒቴ

🌺 መሃሪ ይቅር ባይ አምላክ
🌺ድካሜን ተመልከት ስለዉ ተበርክኬ
🌺ኃያላት የማይችሉህ የኃያላን ኃያል
🌺ነፍሴ ትልኃለች ጌታዬ ይረዳኛል
🌺አለምን ለማዳን መስቀል ላይ የዋለ
🌺ለዘላለም ፍቅር ነህ ሁሌ የማትቀየር
🌺ምህረትህ የበዛ
የድንግል ማርያም ልጅ_ቸሩ መድኃኒአለም አንተ ነህ አባቴ !!

በችግር ተይዘን ዉስጣችን ሲያነባ
ደምህ የፈሰሰው ለሰዉ ልጅ ነዉና
በምህረት እጆችህ እንባችን አብሰዉ
የሀዘንን ሸማ ከኛ ላይ ግፈፈው

ምስጋና ይሁን ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ጥንት ለነበረ አሁንም ላለ ኋላም የሚኖር ስሙ የተመሰገን ይሁን አሜን ፫
🕊

[ † እንኩዋን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ዓመታዊ የኪዳን በዓል በሰላም አደረሳችሁ † ]

† ፯ [ 7 ] ቱ ኪዳናት †

'ተካየደ' ማለት 'ተስማማ: ተማማለ' እንደ ማለት ሲሆን 'ኪዳን' በቁሙ 'ውል: ስምምነት' እንደ ማለት ነው:: ይኸውም እግዚአብሔር ከሰዎች ጋር: ሰዎችም ከሰዎች ጋር የሚያደርጉት ሊሆን ይችላል:: ልዩነቱ የእግዚአብሔር ቃል ኪዳን ቅዱስና የማይለወጥ መሆኑ ነው::

እግዚአብሔር አምላክ ከሥነ ፍጥረት ጀምሮ በየጊዜው ከብዙ ወዳጆቹ ጋር ኪዳንን አድርጉዋል:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያንም እነዚህን ኪዳናት ጥቅልል አድርጋ ፯ [7] እንደ ሆኑ ታስተምራለች:: ስለዚህም ዛሬ ፈጣሪ ቢረዳን እነዚሁን ፯ [7] ኪዳናት በጥቂቱ እንመለከታለን::

"ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ"
"ከመረጥኩዋቸው ጋር ቃል ኪዳንን አደረግሁ" [መዝ.፹፰፥፫] [88:3]

፩. " ኪዳነ አዳም "

አዳም ማለት የእግዚአብሔር ድንቅ ፍጥረት: የፍጡራን አስተዳዳሪ: ነቢይ: ካህንና ንጉሥ ነው:: እግዚአብሔር ከአዳም ጋር አስቀድሞ በእጸ በለስ አማካኝነት ቃል ኪዳን ነበራቸው:: ነገር ግን አባታችን በዲያብሎስ ሴራ በመረታቱ ኪዳኑ ፈረሰ:: [ዘፍ.፫፥፩] [3:1]

አዳምና ሔዋን ተጸጽተው ቢያለቅሱ ግን አዲስ የኪዳን ተስፋ: "ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ኪዳንን ተቀበሉ:: [ቀሌምንጦስ: ገላ.፬፥፬]

፪. " ኪዳነ ኖኅ "

ከአዳም እስከ ኖኅ ድረስ ባሉት ፲ [10] ትውልድ ዓለም በዓመፃ ተሞላች:: ቅዱስ ኖኅ በደግነቱ መርከብ ሠርቶ ቤተሰቡን ሲያተርፍ ዓለም በማየ ሥራዌ ጠፋች:: ከመርከቡ ከወጣ በሁዋላ ኖኅና እግዚአብሔር በቀስተ ደመና ምልክትነት ቃል ኪዳን ተጋቡ:: "ኢያማስና ለምድር ዳግመ በማየ አይኅ" እንዲል:: [ዘፍ.፱፥፲፪] [9:12]

፫. " ኪዳነ መልከ ጼዴቅ "

መልከ ጼዴቅ የእግዚአብሔር ካህኑ: የክርስቶስም ምሳሌው የሆነ የሳሌም ንጉሥ ነው:: በ፲፭ [15] ዓመቱ መንኖ: አጽመ አዳምን ይዞ: በቀራንዮ በሕብስትና በወይን ያስታኩት ነበር::

እግዚአብሔር ለመልከ ጼዴቅ: በሐዲስ ኪዳን ለምትሠራው ክህነትና ምሥጢረ ቁርባን ምሳሌ አድርጐ በቃል ኪዳን አትሞታል:: በዚህም ተሰውሮ ይኖራል እንጂ ሞትን እስካሁን አልቀመሰም:: ይህም ካህኑ መልከ ጼዴቅ ከአብርሃም ጋር በተገናኙበት ጊዜ ተገልጧል:: [ዘፍ.፲፬፥፲፯ ፣ ዕብ.፯፥፩]

፬. " ኪዳነ አብርሃም "

ቅዱስ አብርሃም የሕዝብና የአሕዛብ አባት: ሥርወ ሃይማኖት: የጽድቅም አበጋዝ ነው:: ስለ ፍቅረ እግዚአብሔር ሲል ከርስቱና ከወገኖቹ ተለይቶ በቅድስና ኑሯልና እግዚአብሔር "በዘርሕ አሕዛብ ይባረካሉ" አለው:: [ዘፍ.፲፪፥፩] የቃል ኪዳን ምልክትም ይሆነው ዘንድ ግዝረትን ሰጠው:: [ዘፍ.፲፯፥፩-፲፬]

፭. " ኪዳነ ሙሴ "

ቅዱስ ሙሴ የነቢያት አለቃ: የእሥራኤል እረኛ: የእግዚአብሔር ሰው እና ፍጹም ትሑት [የዋህ] ሰው ነው:: በፈጣሪው ትዕዛዝ እሥራኤልን ከግብጽ ባርነት አውጥቶ ለ፵ [40] ዘመናት በበርሃ ሲመራቸው ከእግዚአብሔር የኪዳንን ጽላትና አሠርቱን ትዕዛዛት ተቀብሏል:: [ዘጸ.፳፥፩ 20:1, ፴፩፥፲፰ (31:18)]

፮. " ኪዳነ ዳዊት "

ቅዱስ ዳዊት ሥርወ ነገሥት: ጻድቅ: የዋህና ቡሩክ የሆነ አባት ነው:: እግዚአብሔር ከእረኝነት ጠርቶ ንጉሥ አድርጐ ሹሞት "ከሆድህ ፍሬ በዙፋንህ ላይ አኖራለሁ" [መዝ.፻፴፩፥፲፩] [131:11] ሲል ምሎለታል:: አክሎም ሰፊ ቃል ኪዳን ሰጥቶ "አልዋሰሽህም" ብሎ ሲምልለት እንመለከታለን:: [መዝ.፹፰፥፴፭]

፯. " ኪዳነ ምሕረት "

በብሉይ ኪዳን የነበሩ ፮ [6] ቱ ኪዳናት በዘመናቸው ክቡርና ሕዝቡን ከመቅሰፍት ይታደጉ የነበሩ ቢሆንም ከሲዖል ማዳን ግን አልቻሉም:: ስለዚህም አንድ ፍጹም ኪዳን ያስፈልግ ነበር:: ይህን ፍጹም ኪዳን ይፈጽም ዘንድም ከቅድስት ሥላሴ አንዱ ወልድ ከሰማያት ወርዶ በድንግል ማርያም ማሕጸን አደረ::

በፍጹም ተዋሕዶም በሕቱም ድንግልና ተወልዶ: አድጎ: ተጠምቆ: አስተምሮ: ሙቶ: ተነስቶና ዐርጐ ሥጋ ማርያምን በዘባነ ኪሩብ አስቀመጠው:: ኪዳነ ምሕረት [የምሕረት ኪዳን] የምንለው አንዱ ታዲያ ይሔው ነው::

የጌታችን መጸነሱ: መወለዱ: መሰደዱ: መጠመቁ: ማስተማሩ: ሥጋውንና ደሙን መስጠቱ: መሰቀሉ: መሞቱና መነሳቱ: ማረጉና መንፈስ ቅዱስን መላኩ በአንድ ላይ ኪዳነ ምሕረት ይባላል:: ታዲያ ይህ ሁሉ የተደረገው በሥጋ ማርያም ነውና የኪዳኑ ባለቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ናት::

የእርሷ ኪዳን ፮ [6] ቱን አበው ኪዳናት ፍጹም በማድረጉ የኪዳናት ማሕተም ይባላል:: የድንግል ማርያም ኪዳኗ ከሲዖልና ከገሃነም ሊታደገን አቅሙ አለውና:: መድኃኒታችን ክርስቶስ ለድንግል እናቱ ቃል ኪዳኑን ያጸናላት ደግሞ ካረገ ከዓመታት በሁዋላ ጐልጐታ ላይ ነው::

እመ ብርሃን በዚያ ቁማ ስለ ኃጥአን ስታለቅስ "እናቴ ሆይ! በስምሽ ያመነውን: በቃል ኪዳንሽ የተማጸነውን እምርልሻለሁ" ብሎ ደስ አሰኝቷታልና:: ይሔው በእመ ብርሃን ምልጃና ቃል ኪዳን ምዕመናን ከመቅሰፍትና ከገሃነመ እሳት ማምለጥ ከጀመሩ ፪ [2] ሺ ዓመታት ሆኑ:: ዛሬም እኛ ኃጥአን ልጆቿ ከእሳት እንደምታድነን አምነን በጥላዋ ሥር እንኖራለን::

" ኢትዝክሪ ብነ አበሳነ: ኃጢአተነ: ወጌጋየነ:
ማርያም እሙ ለእግዚእነ:
በኪዳንኪ: ወበስደትኪ ድንግል ተማሕጸነ::"

"ድንግል ሆይ! ኃጢአታችን: አበሳችንና በደላችንን አታስቢብን ዘንድ በስደትሽና በኪዳንሽ ተማጽነናል::"

የአርያም ንግሥት: የሰማያውያንና ምድራውያን ኁሉ እመቤት: የአምላክ እናት: ቅድስት: ስብሕት: ክብርት: ልዕልት: ቡርክት: ፍስሕትና ጥዕምት የሆነች ድንግል ማርያም የድኅነታችን መሠረት: ላመኑባት አንገት የማታስደፋ እውነተኛ አማላጅ ናት::

በዚህች ዕለት የካቲት ፲፮ [16] ስለ ወገኖቿ የሰው ልጆች ፍቅር በእንባ ያቀረበችውን ልመና የባሕርይ አምላክ የሆነ ልጁዋ ተቀብሎ በማይዋሽ ንጹሕ አንደበቱ ቃል ኪዳን ገብቶላታል:: በስምሽ ያመነ በቃል ኪዳንሽ የተማመነ እሳት አያይም ብሏታል::

ቸሩ ልጇ ከበረከተ ኪዳኗ አይለየን:: በዓሉንም የሰላም: የፍቅርና የበረከት ያድርግልን::

🕊

[ † የካቲት ፲፮ [ 16 ] ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት ]

፩. ኪዳነ ምሕረት [የሰባቱ ኪዳናት ማሕተም]
፪. ቅድስት ኤልሳቤጥ [የመጥምቁ ዮሐንስ እናት / የእመቤታችን አክስት / የሶፍያ ልጅ]
፫. ቅዱስ ገብረ ማርያም ጻድቅ ንጉሠ ኢትዮዽያ [የቅ/ላሊበላ ወንድም]

[ † ወርኀዊ በዓላት ]

፩. ቅዱስ አኖሬዎስ ንጉሥ ጻድቅ
፪. አባ አቡናፍር ገዳማዊ
፫. አባ ዮሐንስ ወንጌሉ ዘወርቅ
፬. አባ ዳንኤል ጻድቅ

" . . . ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምፅም ጮኻ እንዲህ አለች:- አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማኅፀንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? እነሆ የሰላምታሽ ድምፅ በጀሮየ በመጣ ጊዜ ፅንሱ በማኅፀኔ በደስታ ዘሎአልና:: ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈፀማልና ያመነች ብፅዕት ናት::" [ሉቃ.፩፥፴፱]

† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †
† ወለወላዲቱ ድንግል †
† ወለመስቀሉ ክቡር †
[ ዲ/ን ዮርዳኖስ አበበ ]
@haymanotanednat
@haymanotanednat
         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
💖                   🕊                    💖
🕊

በስመ አብ : ወወልድ : ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን።

[ " ከዮናስ የሚበልጥ እዚህ አለ " ]

[ማቴ.፲፪፥፵፩]

💖

ጌታና ዮናስ በምን ይመሳሰላሉ ?

• በየዋህነት ፤ [ማቴ.፲፩፥፳፱]

• በነቢይነት ፤ [ሉቃ.፲፫፥፴፫]

• መርከቡ ላይ በመተኛት ፤ [ማቴ.፰፥፳፬]
• ወዲህም መርከቡ የመስቀል ምሳሌ ነው ፤ ጌታ መስቀል ላይ መሞቱን የሚያመለክት ነው።
• ዕጣ የወጣበት በመሆን ፣ ዮናስ ወደ ባሕሩ ለመጣል ዕጣ እንደወጣበት ጌታም የእኛን ዕጣ ሞትን መሞቱ
• አንድም ጌታ በአካለ ነፍስ ወደሲኦል የመውረዱ ምሳሌ ነው።
• ዮናስ ወደ ባህሩ ሲጣል ማዕበሉ ጸጥ ማለቱ ጌታም በሞቱ ሞገደ ፍዳን ማዕበለ መርገምን ጸጥ ማድረጉ

• ዮናስ በዓሣ ሆድ ፫ ቀንና ሌሊት እንደቆየ ሕያውም ሆኖ እንደወጣ ፤ ጌታም በምድር ሆድ በመቃብር ፫ [ 3 ] ቀንና ሌሊት ቆይቶ ሞትን በማሸነፍ ሕያው መሆኑ ፤ [፩ቆሮ.፲፭፥፶፭]
• ዮናስ ማለት ርግብ ማለት ነው ፤ የጌታንም ጸዓዳ ርግብ ይለዋልና

---------------------------------------------

ሕዝበ ነነዌና ምእመናነ ሐዲስ ፦

• እነሱ በዮናስ ስብከት ንስሐ ገቡ ፤ እኛስ በጌታ ስብከት በወንጌል አምነን ንስሐ ገብተን ይሆንን ?

• ነነዌን ያስተማረ ፍጡር ዮናስ ነው ፤ እኛን ግን ያስተማረ የዮናስ ፈጣሪ ነው

• እነሱ በዮናስ ስብከት አምነው ንስሐ ገብተው እኛ ግን በጌታ ቃል አምነን መምህራንን ሰምተን ፤ በዓለማችን ላይ ያሉትን ጌታ የሚያደርጋቸውን ተአምራት ተመልክተን ንስሐ ካልገባን የነነዌ ሕዝብ መፈራረጃ ሆነው እንደሚመሰክሩብን የሚያጠይቅ ምሥጢር ነው።

ጾሙን ለበረከት ፤ ለሥርዬተ ኃጢአት ያድርግልን !

አሜን !!!

[ መጋቤ ሐዲስ ነቅዐጥበብ ከፍ ያለው ]


†                       †                        †
💖                    🕊                     💖
#እንኳን ለታላቁ ለአብይ ፆም በስላም በጢና አደረሳችሁ አደረሰን።
#ዐብይ ጾም ማለት ምን ማለት ነው
በመጀመሪያ ‹‹ዐቢይ›› የሚለው ቃል ‹‹አበየ›› ከሚለው የግዕዝ ግስ የተገኘ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ከፍ አለ›› ማለት ነው፡፡
2. ዐብይ ጾም ለምን ዐቢይ ተባለ
ዐብይ ጾም ዐብይ የተባለበት ሦስት አበይት ምክንያቶች እንመለከታለን
2.1. ጌታቸን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ የጾመው ሥለሆነ ማቴ
4፡2-3
2.2. በቀኑ ቁጥር ከሌሎች አጽዋማት ስለ ሚበልጥ የቀኑ ብዛትም 55
ቀን ነው፡፡
2.3. ታላላቅ የሰይጣን ፈተናዎች እንዲሁም ደግሞ ሶስቱ ርዕሰ ኃጢአት
የሚባሉት ትዕቢት፣ስስት ፍቅረ ነዋይ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ድል
የተመቱበት ስለሆነ ይህ ጾም አብይ (ታላቅ) ተብሏል፡፡ ማቴ 4፡3-11
የዐብይ ጾም የተለያየ ስያሜዎች
ዐብይ ጾም ከቀኑ ርዝማኔ በተጨማሪ ጾሙ የተለያዩ ስያሜዎች አሉት፡፡

#ጾመ ሁዳዴ፡- #ሁዳድ ማለት ሠፊ (ትልቅ) የእርሻ ቦታ ማለት ነው፡፡ ይህም ጾም ደግሞ በቀኑ ብዛት ትልቅ (ሠፊ) በመሆኑ የሁዳዴ ጾም ይባላል፡፡
@haymanotanednat
#የካሳ_ጾም፡- እንዲህ የተባለበት ምክንያቱ ደግሞ አዳምና ሔዋን በዲያቢሎስ ግዞት እያሉ ክርስቶስ ደሙን በመክፈል (በመካስ) ነጻ ስላውጣቸው የካሳ ጾም ተብሎሏል
°#የድል_ጾም ፡-ይህም ደግሞ ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ጾም ሰይጣንን ድል ያደረገበት በመሆኑ የድል ጾም ተብሏል፡፡
#የመሸጋገሪያ_ጾም
ጌታችን ከሕገ ኦሪት ወደ ሕገ ወንጌል
ሊያሸጋግረን የጾመው ጾም በመሆኑ የመሸጋገሪያ ጾም
ተብሏል።
@haymanotanednat
#ጾም_አስተምህሮ፡- ይህ ጾም ‹‹ጾም አስተምህሮ›› የተባለበት ምክንያት ደግሞ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማስተማር የጾመው በመሆኑ ነው፡፡
ከዚህም በተጨማሪ ደግሞ የተለያዪ ስያሜዎች አሉት ‹‹የመሸጋገሪያ ጾም፣ ‹‹የስራ መጀመሪያ ጾም ››
@haymanotanednat
#የዐብይ_ጾም_ሳምንታት
ዐብይ ጾም በያዘው በ55 ቀኑ ውስጥ 7 ቅዳሜና 8 እሁዶቸን ይዟል የእነዚህ የስምንቱ እሁዶች የተለያየ ስያሜ አላቸው፡፡ ስያሜአቸውንም የሰጣቸው የቤተክርስቲያናችን የዜማው ሊቅ የሆነው ቅዱስ ያሬድ ነው፡፡
1፣ ዘወረደ
2፣ ቅድስት
3፣ ምኩራብ
5፣ ደብረዘይት
6፣ ገብረ ሔር
7፣ ኒቆዲሞስ
4፣ መጻጉዕ
8፣ ሆሳዕና
ጾሙን በሰላም፣ በፍቅር፣ በትሕትና ጾመን ለበዓለ
ትንሣኤው በሰላም እንዲያደርስ ጾመን ለማበርከት እንዲያበቃን የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን
መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣
የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ
ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን አሜን
@haymanotanednat
@haymanotanednat
꧁༒꧂ ዘወረደ (ጾመ ሕርቃል) ꧁༒꧂

በዚህ ታላቅ ጾም (ጾመ ክርስቶስ) ክርስቶስ ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥርዓተ ጥምቀትን ከፈጸመ በኋላ በዕለቱም ተነሥቶ ወደ ገዳመ ቆሮንጦስ በመሄድ አርባ ቀንና አርባ ሌሊት የመጾሙን ወራትና ጊዜ የምናስብበት ሲሆን ጾሙን በሦስት ክፍሎችና በስምንት ሳምንታት የተከፈሉ ናቸዉ፡፡ እነርሱም:-
√ ዘወረደ ( ጾመ ሕርቃል )፡- ይህም ጾሙ ከሚገባበት ሰኞ ጀምሮ እስከ እሑድ ድረስ ያለዉ ቀን ነዉ፡፡
√ የጌታ ጾም፡- ይህም ከቅድስት ሰኞ እስከ ሆሣዕና ዋዜማ ዓርብ ድረስ ያለዉ 40 ቀን ነዉ፡፡
√ ሕማማት ፡- ይህም ጌታችን በአልአዛር ቤት ለማዕድ ከተቀመጠበት የሆሣዕና ቅዳሜ ጀምሮ እስከ ቅዳሜ ሥዑር ያለዉ መከራን የተቀበለበት 8 ቀን ሕማማት ነዉ፡፡ ይህም 7+40+8= 55 ቀን ማለት ነዉ፡፡

ዘወረደ ማለት እግዚአብሔር ወልድ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱን የምናስብበት፣ የምናመሰግንበት ነው፡፡ ወረደ ስንል ከላይ ወደ ታች መጣ፣ በሰው አስተያየት እግዚአብሔር በሁሉ የሚገኝ ሲሆን ከሰማይ ወደ ምድር ወረደ ያባላል፡፡ መውረድም በክርስቶስ (በእግዚአብሔር ወልድ) ብቻ ሳይሆን ምሥጢረ ጥምቀትም ሲፈጸም እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በላዩ ወርዷል [ዘፍ11:7፣ ዘጸ 19:18፣ ዘጸ 34:5፣ ሉቃ 3:22፣ ሐዋ 10:44፣ ዘጸ 4:16]፡፡ ቅዱሳን መላእክትም ከሰማይ ወደ ምድር መውረዳቸውን መጽሐፍ ያስተምረናል ዘፍ 28:12፣ ማቴ 1:52]፡፡ ወረደ ስንል ጌታችን ከሰማየ ሰማያት የመውረዱን ወርዶም የእኛን ሰው (ሥጋ) መልበሱን የምንረዳበት ትምህርት ያስረዳል [ዮሐ 3:13]፡፡ ለምን ከሰማያት ወረደ ቢሉ ድኅነት ዓለምን ሊፈጽም ስለሆነና ትኅትናውን ለማሳየት ነው፡፡ ዘወረደም ለዐብይ ጾም መጀመሪያ (አመላካች) ሲሆን ቀጥሎ ለሚመጣው ጾም መግቢያ ማጠንከሪያ መዘጋጃ ነው፡፡

እንደ ቅዱስ ያሬድ ትምህርት መጠረት በዚህ ዕለት ‹ተቀነዩ ለእግዚአብሔር በፍርሐት-እግዚአብሔርን በመፍራት አመስግኑ ተገዙለትም› በማለት ያስተምርና ይዘምር ስለነበር ቤተክርስቲያንም በዚህ ዕለት ትምህርቷ እግዚአብሔር ወልድ ክርስቶስ ከሰማያት መውረዱንና እርሱን በመፍራት እንድናከብርና እንድንገዛላት ታስተምረናለች፡፡ [ዮሐ 3:12፣ ዕብ 13:7-17፣ ያዕ 4:6-ፍጻሜ፣ መዝ 2:11]፡፡
‹ዘያከብሮሙ ለፈራህያነ እግዚአብሔር- እግዚአብሔርን የሚፈሩትን የሚያከብር ይከበራል" [መዝ 14:4] በልዑላን ይልቅ ከፍ ያለ በቅድስናው ከቅዱሳን ይልቅ ቅዱስ የሆነ በግርማውም ከአስፈሪዎች ሁሉ የሚያስፈራ በማስተዋሉም የጥበበኞች ጥበበኛ ስለእሱ መገኘቱ ከመቼ ጀምሮ ነው ወርዱም ይህን ያህል ነው ራስጌው በዚያ በኩል ነው መምጫውም በዚህ በኩል መድረሻውም እስከዚህ ድረስ ነው በማይባል በእግዚአብሔር ስም በስፍራ ሁሉ መልቶ የሚኖር በየቀኑም ድንቆችን የሚያደርግ ለዘላለሙ ህያው ነው፡፡
‹የጥበብ ሁሉ መጀመሪያ እግዚአብሔርን መፍራት ነው› [ምሳ 1:7፣ ምሳ 9:10] የጥበብ ሁሉ መጀመሪያው የተባለችበት ምክንያት ሰው እግዚአብሐየርን ከፈራ እንደ አብርሃም የታዘዘውን ሁሉ ያደርጋል፡፡ [ዘፍ 22:12-23] እግዚአብሔርን ፈርቶ የሠራው ሥርም ሞገስ ይሆነዋል፡፡ [ዘፍ 31:42] ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊትም ‹ኑ ፈሪሃ እግዚአብሔርን ላስተምራችሁ› [መዝ 33:1] ካለ በኋላ ልጆቹም በመጥራት ‹የእግዚአብሔር መልአክ እግዚአብሔርን በሚፈሩት ሰዎች በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይከባል ያድናቸውማል› በማለት እግዚአብሔርን በመላእክተ እግዚአብሔር እንደምታስጠብቀን ተናገረ፡፡ መዝ 33.7 ቅዱስ ጳውሎስም ‹በፍርሃትና በመንቀጥቀጥ የራሳችሁን መዳን ፈጽሙ› ይላል [ፊል 2:12] ቅዱስ ጴጥሮስም ‹በእንግድነታችሁ ዘመን በፍርሃትና በፍቅር ኑሩ› ይላል [ጴጥ 1:17] ወደ ዕብራውያን መልእክትም ‹የማይናወጥን መንግሥት ስለምንቀበል በማክበርና በፍርሃት እግዚአብሔርን ደስ እያሰኘን የምናመልክበትን ፀጋ እንያዝ አምላካችን በእውነት የሚያጠፋ እሳት ነውና› በማለት ይናገራል፡፡ [ዕብ 13:7-17]፡፡

በመለኮታዊ ጥበቡ (ጥባቆት) ከድፍረት ኃጢአት እግዚአብሔር እንዲያድነን እንጸልይ እንማጸነው [መዝ 18:13] ‹---ከእኔም ፈቀቅ እንዳይሉ መፍራቴንበልባቸው ውስጥ እኖራለሁ ለእነሱም መልካም በማድረግ ደስ ይለኛል› ብሎ የነገረውን ተስፋ እንዲያወርሰን [ኤር 32:40] በፍቅር የተነሣ እንፍራው እናክብረው እንገዛለት እናምልከው የአጋንንት ዓይነት፣ ፍርሃት ሳይሆን አባታችን ስለሆነ ክብርን፣ ንጉሣችን ስለሆነ ፍርሓትን ይዘን ለእርሱ በፍቅር እንገዛለት፡፡ ‹ልጅ አባቱን ያከብራል ባሪያም ጌታውን ይፈራል እኔስ አባት ከሆንሁ ክብሬ ወዴት አለ? ጌታስ ከሆንኩ መፈራቴ ወዴት አለ? እንዳንባል [ሚሊ 1:6-7፤ ምሳ 8:7፣ ሐዋ 10:20፣ ሐዋ 24:25፣ ዕብ 10:26፣ ራዕ 21:8፣ መዝ 33:14፣ ዘፍ 3:10፣ ምሳ 28:1፣ ሮሜ 8:15፣ 1ዮሐ 4:18]፡፡

ጌታችን ወደዚህች ምድር ወርዶ ለአዳም የገባለትን ቃል ኪዳን ከመፈጸሙ በፊትና ከፈጸመ በኋላ በብሉይ ኪዳንም ሆነ በሐዲስ ኪዳን የሰውን (የአዳምን) ልጆች ወደ ራሱ ሲጠራ እንዴት ነበር; ያልን እንደሆነ እግዚአብሔርን የሚወዱት፣ የሚያከብሩትና የሚፈሩት ቅዱሳን አባቶች እንደርሱ ቅዱስ ዐሳብ ጠርቶዋል፡፡ እነርሱም፡- አብርሃም፣ ሙሴ፣ ኤልሳዕ፣ ሠለስቱ ደቂቅ፣ ዳንኤል፣ ዮናስ፣ ዳዊት፣ ሰሎሞን፣ ኖኅ፣ ያዕቆብ --- ሲሆኑ በሐዲስ ኪዳንም መጥምቁ ዮሐንስ፣ ቅዱስ ጳውሎስ፣ ጴጥሮስና እንድርያስ፣ ያዕቆብና ዮሐንስ፣ ናትናኤል---ናቸው፡፡ አጠራራቸውም፡-

በብሉይ ኪዳን
➥ አብርሃምን- ከጣዖት አዟሪነት- ወደ ሕዝብና የአሕዛብ አባት- ቃልኪዳን-- [ዘፍ 12]
➥ ሙሴን- ከከብት እረኝነት- ወደ እሥራኤል ሁሉ መሪ -በብሔረ ጡታን--- [ዘጸ 3]
➥ ዳዊትን- ከበግ ጠባቂነት- ወደ ኢየሩሳሌምና የይሁዳ መሪ- እንደ ልቤ የሚሆንልኝ የተባለ--- [1ሳሙ 16:1]
➥ ኤልሳዕን- ከእርሻ ሥራ- ወደ እግዚአብሐየር ነቢይነት- በኹለት እጥፍ መንፈስ--- [1ኛነገ 19:16-21፣ 2ኛነገ 3:11፣ 2ኛነገ 2:1-14]

በሐዲስ ኪዳን
➥ መጥምቁ ዮሐንስን- ከምድረ በዳ- ወደ ንስሓ መምህርነት- በመንግሥተ ሰማያት ከሁሉ የሚበልጥ- [ዮሐ 1:5]
➥ ጴጥሮስንና እንድርያስን እንዲሁ ያዕቆብንና ዮሐንስን- ከዓሣ አስጋሪነት- ወደ ወንጌል ሰባኪነት- በዐሥራ ኹለቱ የእሥራኤል ነገድ ላይ መፍረድ - [ማቴ 4]
➥ ማቴዎስን- ከቀራጭነት- ወደ ወንጌል ሰባኪነት- ዐሥራ ኹለቱ የእስራኤል ነገድ ላይ መፍረድ- [ማቴ 9:9]
➥ ጳውሎስን- ከአሳዳጅነት- ወደ ወንጌል መምህርነት- የጽድቅ አክሊል- [ሐዋ 9:1] ጀምሮ
➥ ናትናኤልን- ከበለስ ሥር- ወደ ወንጌል መምህርነት- በዐሥራ ኹለቱ የእሥራኤል ነገድ ላይ መፍረድ- [ዮሐ 1:47] ጀምሮ
እነዚህ ሁሉ ድንቅ በሆነ ምስጢር ለእግዚአብሔር ታላቅ መምህርና አገልጋይ ይሆኑ ዘንድ ተመርጠዋል የእኛስ አጠራርና የምናገኘው ቦታ ምን ይሆን?

በሐዲስ ኪዳን ላይ የተጠሩትን ቅዱሳን ከመጠራታቸው በፊት እነርሱን ለመምረጥና ለመጥራት ወደ ጽድቅ ለማስገባት ወደ መንግሥቱ ተካፋይነት ለመምረጥ ከሰማየ ሰማያት ወረደ ከድንግል ማርያምም ተወለደ ስለ እኛ ሲል ሁሉን ተቀበለ ሁሉን ቻለ ይቅርም አለን ታዲያ ለዚህ ድንቅና ምስጢር ለሆነ አምላክ እንደምንስ በፍርሃት በመንቀጥቀጥ በንጽሕና አናከብረውም ለምን አናመሰግነውም ለምንስ አናመልከውም በዚህ ታላቅ ጾም እራሳችንን ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት በጥልቀት መርምረንና አስተውለን መፈተሸ ይገባናል፡፡
Audio
   ዐቢይ ጾም   [   ጾመ እግዚእ  ] 

" ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ "

🕊  †  [        ት ሕ ት ና         ]  †  🕊


🕊 [ በመምህራችን በቀሲስ ኅብረት የሺጥላ ]

💖          ድንቅ ትምህርት          💖


" እንዲሁም ፥ ጐበዞች ሆይ ፥ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርሳችሁ እየተዋረዳችሁ ትሕትናን እንደ ልብስ ታጠቁ ፥ እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማልና ፥ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።

እንግዲህ በጊዜው ከፍ እንዲያደርጋችሁ ከኃይለኛው ከእግዚአብሔር እጅ በታች ራሳችሁን አዋርዱ ፤ እርሱ ስለ እናንተ ያስባልና የሚያስጨንቃችሁን ሁሉ በእርሱ ላይ ጣሉት።" [ ፩ጴጥ.፭፥፭ ]

[   ትምህርቱን በማስተዋል ይከታተሉ  ]

         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
                   
            †           

✍️ የዐቢይ ጾም ሁለተኛ ሳምንት

             ቅድስት       

" ቅድስት " ማለት ‹ የተለየች ፣ የነጻች ፣ የከበረች › ማለት ነው፡፡ ይኸውም ጌታችን ጾም የጀመረባት ፣ ልዩ ፤ የተቀደሰች ፤ የከበረች ፤ ልዩ ፣ ንጹሕ ፣ ክቡር በሚኾን በጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጾመች መኾኗን ያመላክታል፡፡

ይህች ጾም በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ አራት የተገለጠችው የጌታችን ጾም ስትኾን ፣ ስያሜዋና የዕለቷ የምስጋና ሥርዓትም የቅዱስ ያሬድ ነው፡፡አምላካችን በገዳመ ቆሮንቶስ ዐርባ መዓልትና ዐርባ ሌሊት በጾመበት ጊዜያት እነዚህ ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል አድርጓል፡፡

ሦስቱ አርእስተ ኃጣውእ የሚባሉትም ፦ ትዕቢት ፣ ስስትና ፍቅረ ንዋይ ናቸው፡፡ በእነዚህ ሦስት ኃጢአቶች ጌታችን በዲያሎስ በተፈተነ ጊዜ በትዕቢት ቢመጣበት በትሕትና ፤ በስስት ቢመጣበት በትዕግሥት ፤ በፍቅረ ንዋይ ቢመጣባት በጸሊዓ ንዋይ ጌታችን ዲያሎስን ድል አድርጎታል፡፡ ለእኛም እነዚህን ድል ለማድረግ የምንችልበትን ጥበብ – ጾምን ገልጦልናል፡፡

ትዕቢት ያልተሰጠንን መሻት ፣ ስስት አልጠግብ ባይነት ስግብግብ መኾን ፣ ፍቅረ ንዋይ ለገንዘብ ሲሉ ፈጣሪን መካድ ነው፡፡ አንደ ክርስቲያን ሦስቱን አርእስተ ኃጣውእ ድል ካደረገ ሌሎችን ኃጣውእ በቀላሉ ድል ማድረግ ይቻለዋል፡፡

ለመቀላቀል👇👇
 @haymanotanednat
@haymanotanednat
  
🕊                      💖                     🕊


[        🕊     ም ኵ ራ ብ      🕊       ]

💖

የሳምንት ሦስት ምኩራብ ቻሌንጅ ከዕለታዊ የመንፈሳዊ መግባራት መከታተያ ጋር

፩ ] ብዙ ጊዜ የምናጠፋበት የእጅ ስልካችን ውስጥ ያሉ ወደ ክርስቶስ እንዳንቀርብ የሚያደርጉ አላስፈላጊ የሆኑ ገጾችን : ዘፈኖችን ሌሎችም የማይጠቅሙ ፋይሎች: መተግበሪያዎች ጠርጎ ማስወገድ

፪ ] ለአእምሮአችን እረፍት በምናገኝባት ቅድስት ቤተክርስቲያን በመገኘት የጽሞና ጊዜ ማሳለፍ

፫ ] በምኩራብ ሰንበት የሚነበበውን ወንጌል [ ዮሐ ፪፥፲፪ ] { 2:12-ፍጻሜው } እንዲሁም መልእክታቱን [ ቆላ.፪፥፲፮ ] { 2:16-ፍጻሜው }
[ ያዕ ፪፥፲፬ ] { 2:14-ፍጻሜው } ማስታወሻ በመያዝ ማጥናት

፬ . በዚህ ሳምንት ውዳሴ ዘአምላክ የተባለውን የ7ቱ ቀናትን ውብ ጸሎት መጸለይ

፭ . ወንድምን ማማትን [ ሀሜትን ] ማስወገድ]
 @haymanotanednat
@haymanotanednat
  
🕊                        💖                       🕊
HTML Embed Code:
2024/05/15 09:41:12
Back to Top