TG Telegram Group Link
Channel: ሃይማኖት አንድ ናት
Back to Bottom
❖●◉❖ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ መሞትን ለምን መረጠ? ❖●◉❖
አንዳንዶች እንደሚመስላቸውና እንደሚያስቡት ክብር ይግባውና ጌታችን፡-
ለምን በእሳት ተቃጥሎ አልሞተም?
ለምን ውኃ ውስጥ ሰጥሞ አልሞተም?
ለምን በሰይፍ ተወግቶ አልሞተም?
ለምን ታፍኖ ወይም በገመድ ታንቆ አልሞተም?
ለምን ታርዶ አልሞተም? ይላሉ ወይም የሚሉ በዚህ ዘመንም አይጠፉም ምክንያቱም ግን፡-

1/ ራሱ በመስቀሉ ላይ ካህንም መሥዋዕትም ሆኗል፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነፍሱን ለዓለም የሰጠ መሥዋዕት ብቻ አይደለም፤ ራሱ በተመሳሳይ ጊዜ ካህንም መሥዋዕትም ሆኗል፡፡ በምድር ላይ ታርዶ ቢሞት ኖሮ መሥዋዕት ብቻ እንጂ ካህን ሊሆን አይችልም ነበር፡፡ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ሲሞት ግን እጆቹን ወደ ሰማይ ከፍ አድርጐ ሲጸልይ መሥዋዕት የሆነ መባ ሆኖ ታይቷል፡፡የሚመለከተው ሰው የሚጸልይ አንድ ካህንና መሥዋዕት ሆኖ የቀረበ መባ አድርጐ ስለሚመለከተው እንዲህ ይላል፡- ‹‹ፋሲካችን ክርስቶስ ታርዶአል እና፤ …›› [1ኛቆሮ 5.7፡፡] መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስራሱ የእግዚአብሔር በግ በመሆኑ ራሱን መሥዋዕት አድርጎ ሲያቀርብ ስለ ሰው ልጆች መማለዱ አስፈላጊ ነገር ነበር፡፡ ፍቁረ እግዚእ ቅዱስ ዮሐንስ ክርስቶስን በራዕዩ ከተመለከተው በኋላ እንዲህ ነበር ያለው፡- ‹‹በዙፋኑና በአራቱ እንሰሶች መካከልም በሊቃናቱም መካከል እንደታረደ በግ ቆሞ ዐየሁ፤ …›› [ራእ 5.6፡፡] በመሆኑም መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መቆም ነበረበት፡፡ ራሱ እንደ ሊቀ ካህናት ሆኖ ሥራውን ሲሠራ አልተጋደመም፤ ስለሆነም ውስጣዊ መታረድ አስፈላጊ ነበር፡፡

2/ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ሳለ ሕያው ሙት ነበር፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ እየጸለየ ወይም በቁም እያለ መሥዋዕት መሆን ነበረበት፡፡ እርሱ ነፍሱን ከሰጠ በኋላ የነበረው ትዕይንት እጅግ ድንቅ ነበር! እርሱ በተመሳሳይ ጊዜ ቆሞም ሞቶም ነበር፤ የተሸከምኩት የተሰቀለ ሰው እግሮች ነበሩና፡፡ እርሱ አስቀድሞ ነፍሱን ሰጥቶ ስለነበር እግሮቹን ሲሰብሯቸው ከመጡ በኋላ ትተዋቸዋል፡፡ ስለሆነም እርሱ ነፍሱን ሲሰጥ በእግሮቹ እንደ ቆመ ነበር፡፡ ይህ የሚያሳየን እርሱ በሞቱ ጊዜ የተነሣ ሕያው ክርስቶስ መሆኑን ነው፡፡ ይህን ማለት ግን በእርግጥ አልሞተም ማለት አይደለም፤ ‹‹ በእርሱ ሕይወት ነበረች፤…›› [ዮሐ 1.4] የሚለውን ቃል ያጎላልናል እንጂ፡፡
እርሱ ነፍሱን ቢተውም የሕይወትን ኃይል በእርሱ ውስጥ ነበረ፡፡ጌታ ከሙታን መካከል ተለይቶ ሲነሣ እኛ ታርዶ መሞቱን እንድንመለከት ቁስሎቹን እንደ ነበሩ ጠብቆአቸው ነበር፡፡ በሌላ ቃላት የተነሣ ክርስቶስ ሆኖ ታርዷል፤ እንደ ታረደ መሥዋእት ሆኖም ቆሟል ማለት ነው፡፡ይህ ደግሞ ‹‹…እንደ ታረደ በግ ቆሞ አየሁ ፤ …›› [ራእ 5.6] በሚለው ቃል ተረጋግጧል፡፡ በመሆኑም ኢየሱስ ክርስቶስ ተቃጥሎ ወይም ውኃ ውስጥ ሰጥሞ መሞት አልነበረበትም፤ እነዚህ የግድያዘዴዎች እነዚህን ጥልቅ ትርጉሞች ሊሸከሙ አይችሉም ነበርና፡፡

3/ ክርስቶስ በመስቀሉ አማካኝነት ምድራዊውን ከሰማያዊው ጋር አስታርቋል፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ እግዚአብሔርን በሰው ልጆች መካከል ነው የወከለው ወይሰ የሰውልጆችን በእግዚአብሔር ፊት? እርሱ ኹለቱንም በተመሳሳይ ጊዜ ፈጽሟል፡፡ ይህም ማለት እርሱ በተመሳሳይ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅና የሰው ልጅ ሆኗል ማለት ነው፡፡ እርሱ ሥጋን ባይለብስ ኖሮ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ ይቀር ነበር፤ የሰው ልጆችም የሰው ልጆች ሆነው ይቀሩ ነበር፡፡ ሥጋን በመልበሱ ግን የእግዚአብሔር ልጅነትን ከሰው ልጅነት ጋር አንድ አደረገ፤ እርሱ ራሱ በተመሳሳይ ጊዜ የእግዚአብሔር ልጅና የሰው ልጅ ሆኗል፡፡ በሰውና በእግዚአብሔር መካከል ያለውን ግንኙነት እንደ ድልድይ አገናኝቷል ማለት ነው፡፡

4/ መስቀሉና የተሰጠን አመለካከት (ምልክት)
የመስቀሉ ምልክት የሚያሳየን የተሠዋውን ምልክትና የመታዘዝን ፍፃሜ ነው፡፡ እኛ አንድን መስመር ለመሰረዝ ወይም ለማጥፋት ስንፈልግ የተመሳቀለ ምልክት በላዩ ላይ እናደርጋለን፡፡ መስቀሉ በራሱ ለእግዚአብሔር የሚሆን እጅ የመስጠት ሕይወትን ያውጅልናል፡፡ የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ውጪያዊ ገጽታ ስንመለከተው በመስቀል ላይ ቆሞ ነው የምንመለከተው፡፡ ይሁን እንጂ ጠለቅ ብለን ስንመለከተው የሰውነቱ እያንዳንዱ ክፍል እንዳይንቀሳቀስ ተደርጐ ተቸንክሮ ነበር፡፡ በዚህም ለእኛ ሊነግረን የወደደው ሥጋችንን መስቀል እንደሚገባን ነው፡- ‹‹የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑት ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቹ ጋር ሰቀሉ፡፡›› [ገላ 5.24]፡፡ በመሆኑም እያንዳንዳችን ‹‹ከክርስቶስ ጋር ተሰቅዬአለሁ፤ እኔም አሁን ሕያው ሆኜ አልኖርም፣ ክርስቶስ ግን በእኔ ይኖራል፤… ›› [ገላ 2.20] ማለት አለብን ፡፡
በመስቀሉ ላይ የሥጋን መሻትና የግል ፍላጐትን ምኞት መቸንከር አለባቸው፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ይፈጸም ዘንድ ሥጋ መሰቀል አለበት፡፡ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሳለ ሰይጣን በሰዎች ላይ አድሮ ‹‹…የእግዚአብሔር ልጅስ ከሆንህ ከመስቀል ውረድ…›› [ማቴ 27.40] ብሎት ነበር፡፡ እኛም ሥጋን ለመስቀል ስንደክም ይህሁሉ ከባድ ልፋትና ድካም ለምን አስፈለገ? ይለናል፡፡

5/ በመስቀሉ አመካኝነት ትንቢቶች ተፈጽመዋል፡፡
ትንቢቶች በመስቀሉ አማካኝነት ስለ ተፈጸሙ መስቀሉ አስፈላጊ ነበር፡፡ ነቢዩ ዳዊት በመዝሙሩ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እጆቼን እግሮቼን ቸነከሩኝ፡፡›› [መዝ 21.16] ‹‹ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፣ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፡፡›› [መዝ 21.18] ‹‹ለመብሌ ሀሞት ሰጡኝ፣ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ፡፡›› [መዝ 68.21]፡፡ በስቅለት ካልሆነ በስተቀር እነዚህ ሁሉ ትንቢቶች በምንና እንዴት ይፈጸሙ ነበር? መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ በትንቢት ሲናገር እንዲህ ብሎ ነበር፡- ‹‹ሙሴ በምድረ በዳ እባብን እንደ ሰቀለ እንዲሁ በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ የሰው ልጅ ሊሰቀል ይገባዋል፡፡›› [ዮሐ 3.14-15፡፡]

ኢየሱስ ክርስቶስ በእባብ የተመሰሉ ኃጢአቶቻችንን ተሸክሞ ወደ መስቀሉ ከወጣ በኋላ እነዚህን ኃጢአቶቹን በመስቀሉ ላይ ቸንክሮአቸዋል፡፡ ከዚህ በኋላ እርሱ ከመስቀሉ ሲወርድ ኃጢአቶቹን በመስቀሉ ላይ እንደ ተቸነከሩ ትቷቸው ወርዷል፡፡ በመሆኑም በቅዳሴያችን ውስጥ ‹‹አቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፡- አንተ የኃጢአቶቻችንን ዝርዝር አጥፋና አድነን፡፡›› እንላለን፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም እንዲህ በማለት ጽፎልናል፡- ‹‹በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው፤ እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል፤… ›› [ቆላ 2.14፡፡]
ሌላው ምሳሌያዊ ክስተት ነቢዩ ሙሴ ቀይ ባሕርን በበትሩ በመምታት ለኹለት መክፈሉ ነው፡፡ እርሱ በኹለተኛው ምቱ የመስቀል ምልክት በመሥራት ውኃውን ወደ መጀመሪያው ሁኔታ መልሶታል፡፡ በዚህም የሰይጣን ምሳሌ የሆነውን ፈርዖን በውኃው ውስጥ ሰጥሞ እንዲሞት አድርጎታል፡፡ ከዚህ የተነሣም መስቀሉ የሰይጣንን መንግሥት ድል መንሻ ሆኗል፡፡
6/ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀሉ ላይ ነግሣል፡፡
የእርሱን ሞት ያመጣውና እርሱ በሰው ልጆች ልብ ውስጥ እንዲነግሥ ያደረገው መሣሪያ የእንጨት መስቀል መሆን ነበረበት፡፡ ክርስቶስ ‹‹…መንግሥቴ ከዚህ ዓለም አይደለችም፤›› [ዮሐ 18.36] ስላለ ይህ የእንጨት መስቀል ወደ ላይ ከፍ ማለት ነበረበት፡፡ አገረ ገዥው ጲላጦስ ራሱ ‹‹የአይሁድ ንጉሥ የናዝሬቱ ኢየሱስ… ›› [ዩሐ19.19] ብሎ በመጻሕፍት ስለ መሰከረ መስቀሉ የመድኃኒዓለም ዙፋን ነበር፡፡ ይህ ጽሑፍ በሦስት ቋንቋዎች (በላቲን፣ በግራክና በእብራይስጥ) ስለ ተጻፈ መላው ዓለም ክርስቶስ የአይሁዳ ንጉሥ እንደሆነ በይፋ መስክሯል፡፡ በመሆኑም ይህ የክስ ጽሑፍ እርሱ በመስቀል ላይ ሲነግሥ ከራሱ በላይ ስለ ተንጠለጠለ ተሰቅሎ መሞት ነበረበት፡፡ ሌላምንም ዓይነት የሞት መንገዶች እንዲህ ዓይነቱን መንገድ ለእርሱ አይፈቅዱለትም፡፡ በመሆኑም እርሱ የአይሁድ ንጉሥ ነው ዙፋኑንም መስቀሉ ነው፡፡ በሌላ ቃላት፡- እርሱን ለመስቀል ሞት ያበቃው ምክንያት ንጉሥ መሆኑ ነበር፤ እርሱ የሞተውም ለመንግሥቱ ነው፡፡ ለመሆኑ እንዴት ነው የነገሠው? የነገሠው በሞቱ ነው!

7/ ኢየሱስ ክርስቶስ ሥራውን እንዲፈጽም መስቀሉ የሦስት ሰዓታት ጊዜ ሰጥቶታል፡፡
ሦስት ሰዓት የሚወስድ ሌላ ምንም ዓይነት የግድያ ዘዴ የለም፡፡ አንድ ሰው ወደ እቶን እሳት ከተጣለ በዐምስት ደቂቃ ውስጥ ይሞታል፡፡ ልክ እንደዚሁ አንድ ሰው ውኃ ውስጥ ከሰጠመ ወይም በገመድ ከታነቀ ሞት ወዲያውኑ ነው የሚከሰተው፡፡ አንድ ሰው በገመድ ሲታነቅ በአንገቱ ዙሪያ ሸምቀቆ ይገባል፤ የቆመበትም ጣውላ ከስሩ ተስቦ ይወጣል፡፡ በዚህ ጊዜ አከርካሪው ወዲያውኑ ስለሚለያይ ከኹለት ደቂቃዎች በኋላ ነፍሱ ትወጣለች፡፡ ይህ ይሁን እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስ የሞተው በሦስት ሰዓታት ውስጥ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥም ብዛት ያላቸው ጠቃሚና እጅግ ታላላቅ ክስተቶች ተከስተዋል፡፡

8/ መስቀሉ የሕይወት ዛፍ ነው፡፡
ሶሪያዊው ቅዱስ ኤፍሬም ‹‹ ነጻ የሚወጡት የሚያቋርጡበትን ድልድይ በመስቀሉ የሠራው አናጢእርሱ ብፁዕ ነው፡፡›› በማለት ተናግሯል፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከደቀ መዛሙርቱ መካከል ብዙዎቹዓሣአጥማጆቹን መርጧል፡፡ ይሁን እንጂ የእርሱ ሥራ ዓሣ አጥማጅነት አልነበረም፡፡ እርሱ፤ ኹለት ዓይነት የሥራ ዘርፎችነበሩት፡፡ የመጀመሪያውን ተግባራዊ ያደረገው ከድኅነት ሥራው በፊት ሲሆን እርሱም የአናጢነት ሥራ ነበር፡፡ ኹለተኛው ደግሞ ከድኅነት ሥራው በኋላ ሲሆን እርሱም የሥራው ዘርፍ ባይሆንም የአትክልት ጠባቂ መስሎ ታይቷል፡፡
በመጀመሪያው የሥራ ዘርፍ አናጢነትን ተግባራዊ አድርጓል፡፡እርሱ ከአንድ የዛፍ እንጨት መስቀልን የሠራና የሰው ልጆችን በዚያ እንጨት የሰው ልጆችን ያዳነ አናጢ ነበር፡፡ እርሱ የድኅነት ሥራውን ለመፈጸም ውድቀትን ያመጣውን ተመሳሳይ መሣሪያ ተጠቅሟል፡፡ ዛፍ ለሰው ልጆች ውድቀት ምክንያት ነበር፡፡መስቀልም የሰው ልጆችን ወደ ዘላለማዊነት ከፍ ከፍ የሚያደርግ የሕይወት ዛፍ ነው፡፡ በምድር ላይ የእግዚአብሔርን ጥበብ የሚቃወም ምንም ዓይነት ነገር የለም፡፡ ለሰው ልጆች ውድቀት ሌላ ምክንያት የሆነው ደግሞ እባብ ስለነበረ የሰው ልጆች ከክፉ ነገር እንዲርቁና ኃጢአትን እንዲያጠፉ ሙሴ በምድረ በዳ ሰቅሎታል፡፡ አሁንም ቅዱስ ኤፍሬም ሶሪያዊው እንዲህ ብሎአል፡- ‹‹ ሰይጣን የሰው ልጆችን ለመጣል በፈለገ ጊዜ እራሱን በእባብ ውስጥ ሸሽጎ እንደመጣ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም አምላክነቱን ከሰይጣን የሸሸገው በሰው ልጅ ውስጥ ነበረ፡፡›› ጌታችን ክብሩን የሸሸገው በሰው ተፈጥሮ ውስጥ ነበር፡- ‹‹ሰማዮችን ዝቅ ዝቅ አደረገ ወረደም፤ጨለማ ከእግሩ በታች ነበረ፡፡ በኪሩቤልም ላይ ተቀምጦ በረረ፣ በነፋስም ክንፍ በረረ፡፡›› [መዝ 17.9-10፡፡]
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ስለ ነበር እርሱ ፍሬዎች እንደ ተንጠለጠሉበት ዛፍ ነበር፡፡ በዚህ ጊዜ ሰይጣን ፍሬው ለመብላት የሚያስጎመጅና ለጥበብም መልካም እንደ ሆነ ስለ ተመለከተ ቆርጦ በላው፡፡ ሞት የራሱን ጠላት (ተቃዋሚ) ስለ ዋጠ በሕይወት ተውጧል፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ይህን አስመልክቶ ሲጽፍ እንዲህ ብሏል፡- ‹‹እርሱ ደግሞ በሞት ላይ ሥልጣን ያለውን በሞት እንዲሽር፤ ይኸውም ዲያብሎስ ነው፣… ›› [ዕብ 2.14፡፡] ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች ላይ የሠራውን ሥራ እንዲያስታውስ ስለ ፈለገ ሌሎች ይጨልጡት ዘንድ ያዘጋጀውን ጽዋ ራሱ እራሱ እንዲጨልጥ እድርጎታል፡፡ መድኃኒያዓለም ፈጽሞ ማንንም አልጎዳም፣ ይህን እንጂ እርሱ የሞትንና የኃጢአትን ኃይል ከሰው ላይ ለማጥፋት ሲል የእነርሱን ሁሉ ጥፋት በራሱ ላይ አኑሮአል፡፡ ይህ እጅግ ድንቅ የእግዚአብሔር ጥበብ ነው፡፡ ሰይጣን አምባገነን ስለ ነበር ምንምዓይነት ምሕረት አልነበረውም፤ እርሱ በራሱ ወንጀል ሲያዝም ፍርድ ይገባዋል፡፡ በመሆኑም የኢየሱስ ክርስቶስ የመስቀል ላይ ሞት በኃጢአት እና በመጥፎ ነገሮች ላይ ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል አንዱ ደረጃ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ሰይጣን በመስቀል ተፈርዶበታል ማለት ነው፡፡
ስናጠቃልለው እንዲህ እንላለን፡- መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ድኅነትን በመስቀል ላይ የፈጸመው እርሱ መሆኑን እናውቅ ዘንድ እንደ አናጢ ሆኖ መሥራት ነበረበት፡፡ በመሆኑም በእንጨት መስቀል ላይ መሞት ነበረበት፡፡

9/ መስቀሉ እርግማንን አጥፍቷል፡፡
በኦሪት ዘዳግም መጽሐፍ ውስጥ ‹‹በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነው …›› [ዘዳ 21.23] የሚል ቃል ተጽፎአል፡፡ በመሆኑም አይሁድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተሰቅሎ እንዲሞት አጥብቀው ጠይቀዋል፡፡ ይህን ሲያደርጉም ጌታ የተቀጣው በሕጉ መሠረት መሆኑን ለማረጋገጥ ነበር ፡፡ ‹‹በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነው… ››የሚል ሕግ ስለ ነበር በእንጨት ተሰቅሎ ለሚሞት ሰው ምንም ዓይነት የጽድቅ ወይም የቅድስና ምሕረት አይደረግለትም ነበር፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ይህን በሕጉ ውስጥ እንዲገባ ያደረገው በመስቀሉ ላይ እንዲንጠለጠል፣ የኃጢያትንእርግማን እንዲሸከምና እንዲያጠፋው ነው፡፡ ይህን አሳብ ነቢዩ ኢሳይያስ እንዲህ በማለት አጠቃልሎታል፡- ‹‹በእውነት ደዌያችንንተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሟል።እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሰፈ እንደ ተቸገረም ቆጠርነው፡፡እርሱ ግን ስለመተላለፋችን ቆሰለስለበደላችንም ደቀቀ፤የደኅንነታችንም ተግሣጽበእርሱላይ ነበረ፣በእርሱም ቁስል እኛ ተፈወስን፡፡›› [ኢሳ 53.4-5፡፡] እርሱ የብዙዎችን የኃጢአት እርግማን በመሸከም ለዓመፀኞች ሲማልድ እነርሱ ግን እንደ ተቀሰፈና እንደ ተቸገረ አድርገው ነበር የቆጠሩት፡፡ የአንድን ጥቅስ የሚቀር ትርጉሙን ከሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ጋር ሳታነጻጽሩ እንዲሁ አትውሰዱት፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እርግማንን ያጠፋው ከሙታን መካከል ተለይቶ በተነሣ ጊዜ ነበር፡፡ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዲህ በማለት ተናግሮአል፡- ‹‹…እንደ ቅድስና መንፈስ ግን ከሙታን መነሣት የተነሣ የእግዚአብሔር ልጅ ሆኖ ስለ ተገለጠ ስለ ልጁ ነው፤ እርሱም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡ ›› [ሮሜ 1.4፡፡] ከዚህ በተጨማሪም‹‹…ስለእኛም ነው እንጂ ስለ በደላችን አልፎ የተሰጠውን እኛን ስለ ማጽደቅም የተነሣውን ጌታችንን ኢየሱስን ከሙታን ባስነሣው ለምናምን ለእኛ ይቆጠርልን ዘንድ አለው፡፡››[ሮሜ 4.25] ብሎናል፡፡ በዚህም መስቀሉ በዳኑት ላይ የነበረውን እርግማን የማንሻ መንገድ መሆኑን አረጋግጦልናል፡፡ ስለዚህም እንዲህ
አለን፡- «በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተጽፎአልና ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን፤ የመንፈስን ተስፋ በእምነት እንድንቀበል፤የአብርሃም በረከት ወደ አሕዛብ በኢየሱስ ክርስቶስ ይደርስላቸው ዘንድ፡፡ [ገላ 3.13-14፡፡]

10/ መስቀሉና የመለኮት ዙፋን፡፡
የመስቀሉ ምልክት አራት ቅርንጫፎች ወይም ክንፎች አሉት፡፡ ይህም የእግዚአብሔር ዙፋንን በአራት መናፍስት (መላእክት)መከበቡን በምሳሌ ይገልጥልናል፡፡ አራት ቊጥር መስቀሉን መንፈሳዊ እንጂ ቁሳዊ ዙፋን ጋር ያገናኛል ማለት ነው፡፡ አራት ቊጥር በሰማያዊው ዙፋን ውስጥም ሆነ በመስቀሉ ውስጥ በጣም ግልጽ ነው፡፡ መስቀሉ ድኅነት በዓለም ሁሉ ውስጥ መስፋፋቱን በምሳሌ ያመለክተናል፡፡ድኅነት በመስቀሉ አመካኝነት ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ከሰሜን እስከ ደቡብ ተዳርሷል፡፡ የሰው ምሳሌነቱ ሥጋን መልበስን ሲገልጥ የላም ምሳሌነት ደግሞ መሥዋዕትን ወይም ስቅለትን ይገልጣል፡፡ የአንበሳ ምሳሌነት ትንሣኤንና ብርታትን ይገለጻል (ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በትንሣኤው አማካኝነት ሞትን ድል መንሣቱን በኃይሉ ገልጦአልናል፤ እርሱ የነገሥታት ሁሉ ንጉሥ እና የጌቶች ሁሉ ጌታ ነውና)፡፡የንስር ምሳሌነት የሚገልጥልን ደግሞ ዕርገቱን ነው፤ ንስር በሰማይ ውስጥ ያንዣብባልና ፡፡ በመሆኑም እነዚህ አራት ሕያው ፍጥረታት የሥጋዌው፣ የስቅለቱ፣ የትንሣኤውና የዕርገቱ ምልክቶች ናቸው ማለት ነው፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ በመላዉ ዓለም ውስጥ የተስፋፋው በአራቱ ወንጌላውያን ማለትም በማቴዎስ፣ በማርቆስ፣ በሉቃስና በዮሐንስ ነው፡፡ አጠቃላዩ የወንጌል ቊጥር ሦስት ወይም አምስት አይደለም፤ አራት እንጂ፡፡ይህ የሆነው በአጋጣሚ አይደለም፡፡ ይህ የሆነው ወንጌላቱ ከመስቀሉ አራት ጎኖችና ከአራቱ እንስሳት ጋር ሆን ተብሎ ለማገናኘት ነው፡፡
እነዚህ የድኅነት ምሳሌዎች እና ሁሉም የድኅነት ሀሳቦች እንዲፈጸሙ ሲባል መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ እንጂ በሌሎች መንገዶች መሞት አልነበረበትም፡፡ ሌላው ቢቀር ከሞቱ በፊት ሽቱ በእርሱ ላይ እንዲፈስስ መደረጉ የሚያሳየን በሕይወት ሣለ መሞቱና ሞቶም ሕያው መሆኑን ነው፡፡ እርሱ ቆሞ የሞተው እኛ ትንሣኤን በመስቀሉ እንድንቀበል እና መስቀሉን በትንሣኤው ውስጥ እንድንመለከት ነው፡፡
@haymanotanednat
@haymanotanednat

      ✥••┈••●◉ ይቆየን ◉●••┈••✥
                        †                         
[ አቤቱ ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ! ]
▬▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬▬▬

" ጌታዬና መድሃኒቴ ኢየሱስ ክርስቶስ የደረሰበትን ጉስቁልና ሊተካከል የሚችል ጉስቁልና እንደምን ያለ ነው? ቀላያት ፊቱን በተመለከቱ ጊዜ የሚንቀጠቀጡለት ፀሐይ ብርሃኗን የምትከለክልለት : ጨረቃ የምታለቅስለት : ከዋክብት የሚረግፉለት : ክፉዎች አይሁድ ተፉበት : እጃቸውን አክርረው መቱት : ከስድብ ሁሉ የከፋ ስድብ ሰደቡት::

ስድባቸው እንዲሁ የቃላት ብቻ አልነበረምና ምራቅና ቡጢም አለበት እንጂ : ይህ ብቻ አይደለም : - ክርስቶስ ሆይ በጥፊ የመታህ ማን ነው? ትንቢት ተናገርልን ¡ የሚል ስላቅም አለበትና:: ጌታዬና ንጉሴ መከራ ያልደረሰበት አካል አልነበረውም:: ጭንቅላቱ ላይ የእሾኽ አክሊል ደፉበት : ፊቱን በጥፊ መቱት ፡ ትከሻውን መስቀል አሸከሙት : እጁን በችንካር ቸነከሩት : እግሩን በምስማር ቸነከሩት : አፉን ኮምጣጤ አጠጡት : መላ አካልቱን በጅራፍ ገረፉት :: ወዮ ! እንዲህ ያለ መውደድ እንደምን ያለ ፍቅር ነው፡፡ "

"አቤቱ፥ ነፍሴን ከሲኦል አወጣሃት ፥ ወደ ጕድጓድም እንዳልወርድ አዳንኸኝ።" [መዝ.፴፥፫]

[  ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ  ]


         †              †               †
▬▬▬▬▬ ▬▬▬ ▬▬▬▬▬
የቅዱስ ላሊበላ ፍልፍል ውቅር አብያተ ክርስቲያናት የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ስፍራና መገለጫ ብቻ አይደለም።
የሙስሊሙም ፣ የጴንጤውም ፣ የካቶሊኩም አጠቃላይ የሁሉም ህዝብ ታሪክ የሆነ ከሃገር አልፎ የአለም ቅርስ ነው።

በየትም አለም ያለን የሃገራችሁ ታሪክና ቅርስ ጥቀሱ ቢባል ያለ ማቅማማት በአንደኛ ደረጃ የምንጠራው ቅዱስ ላሊበላን ነው።
የምንኮራበት ቅርሳችንና ታሪካችን ስለሆነ።

ስለሆነም የሁላችንም ቅርስ የሆነው ቅዱስ ላሊበላ አሁን ላይ ታሪክን መፋቅ እንጂ ታሪክ መስራት በማይችለው ፣ ማፍረስ እንጂ ማልማት አላርጂኩ በሆነው የአብይ አራ ዊት መ ን ጋ ባጠመደው የከባድ መሳሪያ ድምፅ ንዝረት አደጋ ላይ ወድቋል።

ይሄ ውቅር እንደ ቤተክርስቲያን ፈርሶ ዳግም የሚሰራ ስላልሆነ ሁላችንም ለላሊበላ ድምፅ እንሁን!!

➢ትኩረት ለአለም ቅርስ ለሆነው ለማይተካው የቅዱስ ላሊበላ ውቅር አብያተ ክርስቲያን ‼️

#ትኩረት_ለቅዱስ_ላሊበላ_ውቅር_አብያተ_ክርስቲያናት
#ላሊበላ_የኢትዮጵያ_ሃብት_የአለም_ቅርስ_ነው !
#ላሊበላን_የመጠበቅና_ለትውልድ_የማስተላለፍ_ታሪካዊ_አደራ_አለብን!
🌹ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ...!🌹
🌹ናሁ ተፈጸመ ተፈጸመ ማኅሌተ ጽጌ  ስሙር  ተፈጸመ ናሁ አክሊል አክሊል  ማርያም ለጊዮርጊስ ቀጸላ መንግስቱ!
🌹እነሆ በእመቤታችን ስም ተሰባስበን አበባ ይዘን ልጅዋን  በአበባ እርስዋን በጽጌረዳ እየመሰልን የምንዘምርበት ያ የተወደደው የምስጋና የዝማሬ ወር አለፈ እመቤታችን ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ የጊዮርጊስ የክብር ዘውድ ነሽ! እያሉ በተመስጦ እንደ ቅዱስ ያሬድ የቅዱስ ያሬድ ልጆች ሊቃውንቱ  እናታቸውን ሲያመሰግኑ  የሚያሳይ ግሩም {ማኅሌተ ጽጌ}
🌹እመቤታችን ዘውድነቷ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ብቻ ሳይሆን  ውዳሴዋን ቅዳሴዋን እየደገመ ስሟን እየጠራ ለሚማጸን በአማላጅነቷ በቃል ኪዳኗ ለሚያምን ሁሉ ዘውድ ናት! 

🌹ምዕመናንም ትምክህተ ዘመድነ! እያሉ ይዘምሩላታል፤ ያመስግኗታል! ድንግል ሆይ የባህርያችን መመኪያ ነሽ! ተስፋችን ነሽ! የድህነታችን ምልክታችን ነሽ! እያሉ በእናትነቷ ጥላ ስር ያሉ ምዕመናን ይዘምሩላታል! እርስዋም እንደ ቅዱስ ኤፍሬም ትባርካቸዋለች!  ሁላችንም እናታችን ትባርከን!

✝️ለእኛም ለልጆችሽ ሞገስ ሁኝን  አማላጅነትሽ ቃልኪዳንሽ አይለየን!!
                           †                           

      [   🕊 ድንግል ሆይ ፦  🕊    ]  

🌼▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬🌼

🌹እንኳን ለበዓለ ደብረ ቁስቁዋም አደረሰን 🌹

“ ሕብረ ሐመልሚል ቀይሕ ወጸአድዒድ አርአያ ኰሰኰስ ዘብሩር ተአምርኪ ንጹሕ በአምሳለ ወርቅ ግቡር ተፈጸመ ናሁ ማሕሌተ ጽጌ ሥሙር አስምኪ ቦቱ ንግሥተ ሰማያት ወምድር ከመ በሕጽንኪ ያሰምክ ፍቁር ”

" የሚያብረቀርቅ ቀይና ነጭ ቀለም ያለው አርአያው የብር ዝንጒርጒር ጠቃጠቆ የኾነ ንጹሕ ተአምርሽ በወርቅ አምሳል የተሠራ ነው ፤ እነሆ የተወደደ [ መልካም ] ማሕሌተ ጽጌ ደረሰ ተፈጸመ ፤ የሰማይና የምድር ንግሥት ማርያም ሆይ የተወደደ ልጅሽ በጒያሽ [ በዕቅፍሽ ] እንዲጠጋ [ እንዲደገፍ ፣ እንዲንተራስ ] በርሱ ዐማጽኚ፡፡"

[ አባ ጽጌ ድንግል [ ማህሌተ ጽጌ ] ]

🕊

" ሱላማጢስ ሆይ ተመለሺ ! " [መሓ. ፯:፩]

†                       †                      †
💖                    🕊                   💖
" የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ ተላልፏል "

የጾምና የጸሎተ ምኅላ አፈጻጸም እንዴት ነው ?

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ አስተላለፈች።

ሀገራዊ ሰላምን፣ መረጋጋትንና አንድነትን ለማስፈን የታወጀው የጾምና የጸሎተ ምኅላ ዝርዝር አፈጻጸምንም ይፋ አድርጋለች።

ቤተክርስቲያን ፤ ያለፈውን በይቅርታና በምህረት ተዘግቶ ሁሉም በእውነተኛ ንሥሓ ልቅሶና በምህላ፣ በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪ እንዲቀርብ በዜጎች መካከል ፍቅርና አንድነት እንዲመጣ ጾመ ነቢያት ወይም የገና ጾም በልዩ ሁኔታ እንዲጾም መንፈሳዊ አዋጅ አስተላልፋለች።

በዚህም ቋሚ ሲኖዶስ በኅዳር ወር 2016 ዓ/ም የሚከተለውን የጾምና የጸሎተ ምኅላ ዝርዝር አፈጻጸም አውጥቷል፡፡ 

አፈፃፀም ፦

- የጾሙ የመጀመሪያ ሳምንት ከቅዳሜ ኅዳር 15 እስከ ኅዳር 21 ቀን 2016 ዓ/ም በሁሉም የሀገራችን ክፍልና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ባለችበት በመላው ዓለም የንሥሓ፣ የጾም፣ የጸሎትና የምኅላ ሳምንት እንዲሆን፤
 
- በብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ በአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ በአጥቢያ አለቆችና በገዳም አበምኔቶች መሪነት ሁሉም ዲያቆናት፣ ቀሳውስት፣ መነኰሳት፣ ሰባክያንና ሊቃውንት በሙሉ በየመዐርጋቸው ልብሰ ተክህኖና ወጣት የሰንበት ትምህርት ቤት ዩኒፎርማቸው ለብሰው፣ ሁሉም ምእመናን ጋር በአንድነት በዐውደ ምህረት ጸሎተ ምኅላውን እንዲያደርሱ፤ 

- በላው ሕዝበ ክርስቲያን ከሊቅ እስከ ደቂቅ፣ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ እናቶች አባቶች አረጋውያን ሁሉ የቻለ በቤተ ክርስቲያን፣ ያልቻለ በያለበት ሆኖ የተጣላ ታርቆ፣ በፍቅርና በአንድነት፣ በእውነተኛ ንሥሓና ጸጸት በምኅላው እንዲሳተፍ፤ በማእከል የሚደረገው ጸሎተ ምኅላ በብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት በተገኙበት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ድንግል ማርያም ገዳም ሆኖ በመገናኛ ብዙኀን የቀጥታ ሥርጭት ለመላው ዓለም እንዲተላለፍ፤

- በመጀመሪያው የሱባኤ ቀን ኅዳር 15 ቀንና፣ በሰባተኛው ቀን ኅዳር 21 ቀን በጸሎተ ምኅላው በሚደረግበት ጊዜ ታቦቱ ከመንበሩ ተነሥቶ በዐውደ ምኅረት በቀሳውስት እንዲከብር ሆኖ፤ በሁሉም የምኅላው ቀናት ሥዕለ ማርያም፣ ወንጌልና መስቀል ወጥቶ በአራቱ መዐዝን ሥርዓተ ጸሎተ ምኅላው ከጸሎተ ወንጌል ጋር በየቀኑ በነግህና በሠርክ የሥራ ሰዓትን በማይነካ ሁኔታ እንዲፈጸም፤

- በየዕለቱ የሚነበቡት የወንጌል ክፍሎችን ስለ ሰላም፣ ስለንሥሓና ጸጸት፣ ስለ ፍቅርና አንድነት፣ ስለ በጎነትና መደማመጥ፣ ስለመሰማማትና ጥላቻን ስለማራቅ እንዲሆን፤

- በሰፊህና በአንቀዓድዎ፣ በሰጊድና በአስተብርኮ፣ ምኅላው ከደረሰና፣ ጸሎተ ወንጌል ደርሶ ዕለቱ ወንጌል ከተነበበ በኋላ በአንድነት የንሥሓ መዝሙር በመዘመር፣ ሕዝበ ክርስቲያን ስለሀገራቸውና ስለሰው ልጆ ደኅንነት እያሰቡ ወደቤታቸው እንዲሄዱ፤

- ከመጀመሪው ሳምንት በኋላ እስከ በዓለ ልደት ድረስ የሰርክ ምህላ ሳይቋረጥ መደበኛው ሥርዓተ ጾምና ጸሎት እንዲቀጥል፣ የቤተ ክርስቲያንን ታላቅነት፣ የአበውን ተቀባይነት በሚገለጽ፣ በቀጣይም ሁሉም ኦርቶዶክሳውያን በመንፈሳዊ ጽናት የሰላም ልዑካን ሆነው እንዲቀጥሉ በሚያደርግ ሁኔታ እንዲፈጸም፤ 
 
- አስቀድሞ የደረሰውንና፣ እየደረሰብን ያለው ችግር የጦርነትና የግጭት ብቻ ሳይሆን የረሀብ፣ የድርቅ፣ የኑሮ ውድነት፣ የመፈናቀልና የስደት ጭምር ስለሆነ ከጸሎትና ምኅላችን ጎን ለጎን መረዳዳትና መተዛዘን፣ ርኅራሄና መደጋገፍ አብሮ እንዲፈጸም፤

@haymanotanednat
@haymanotanednat
@haymanotanednat
😍ገብርኤል አባቴ🙏​​እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል አመታዊ ክብረ በዓል በሠላም አደረሳችሁ
አደረሰን 🙏🙏

ታህሳስ 19 ቀን በዚህ ቀን ሰለስቱ ደቂቅ "የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶኑ ሊያድነን ይችላል" ያሉበት ዕለትና ቅዱስ ገብርኤል ከእሣት ያዳቸው ዕለት መታሰቢያ በዓል ነው።

ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን አባቶቻችን እንዳስተማሩን ነገሩ እንዲህ ነው። ዘመኑ ጣኦት የሚመለክበት ንጉስ ናቡከደነፆር የእግዚአብሔር ሰዎች የቅዱስ ገብርኤል ወዳጆች የነበሩት ወጣቶች ሥም አይጣላልናንያ (ሲድራቅ) ፤ አዛርያ (ሚሣቅ) ፤ ሚሣኤል (አብድናጎ) ነበሩ። ት/ዳንኤል 3፡1-30 ታሪኩ እንደሚግረን ንጉስ የጣኦት ምስል አሰራ በገሊላ አውራጃ ያለውን ሕዝብ ጠርቶ ለጣኦቴ ያልሰገደ ወደ እሣት ውስጥ ብሎ አወጀ።

በዚህ መካከል ሰልስቱ ደቂቅ ነበሩ። የንጉስ ትህዛዝ ነውና ሕዝቡ ሁሉ ለጣኦቱ ሲንበረከክ እነርሱ ግን ቆመው ያዩ ነበር። የእግዚአብሔር የሆነ ሰው ምንም ነገር አያስፈራውምና ናቡከደነፆር እርሱ ላስቆመው ጣኦት አለመስገዳቸውን ሲሰማ ተናደደ ፤ ተበሳጨም እሳቱን 7 እጥፍ እንዲነድ አስደረገ ሦስቱንም አስሮ እሣቱን እያሳየ "ከመቃጠል ወይስ ለእኔ ጣኦት መስገድ የቱ ይሻል?" ባላቸው ጊዜ የምናመልከው አምላካችን ከሚነደው ከእሳቱ እቶን ሊያድነን ይችላል ባያድነንም እንኳን አንተ ለመታመልከው ጣኦት አንሰግድም አሉት።

በዚህ ጊዜ ጉልበት ያላቸው ሠዎች ተፈልገው ሦስቱን ወጣቶች አስረው ወደ እሣት ቶን ውስጥ ጣሏቸው አስረው የጣሉቸው ወታደሮች የእሣቱ ወላፈን አቃጠላቸው ሠልስቱ ደቂቅን ግን መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ከሰማይ ወርዶ እሳቱን አበረደላቸው አጠፋላቸው።

በዚህም ጊዜ ንጉስ ናቡከደነፆር እንዲህ በማለት መሰከረ "እኛ አስረን የጣልናቸው ሦስት ነበሩ አሁን ግን አራተኛው ሰው በእሳቱ ሲመላለስ ይታየኛል እንዲያውም የአማልክትን ልጆች ይመስላል " አለ። የእግዚአብሔር የማዳኑ ስራ ሲገለጥ ቅዱስ ገብርኤል ሲታይ አዋጁ ሁሉ ተሻረ ጉልበት ሁሉ ለጣኦት ተብሎ የነበረው "ጉልበት ሁሉ ለሰልስቱ ደቂቅ አምላክ ይስገድ ይንበርከክ" ተባለ ይህን ሁሉ ታህሳስ 19 ቀን ሆነ በዚህም ምክንያት በታላቅ ደስታ እናከብረዋለን!😍🙏

ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የመላዕክት የቅዱስ ገብርኤል ጥበቃው ረድኤት በረከቱ አይለየን አሜን!
@haymanotanednat
@haymanotanednat
✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ፡፡ አሜን ፡፡ ✞✞✞

✞✞✞ እንኳን ለጻድቅ: የዋሕና ልበ አምላክ ቅዱስ #ዳዊት ንጉሥ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞✞✞


✞✞✞ ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ ✞✞✞

=>ቅዱስ መጽሐፍ እንዲህ ይላል:- "እግዚአብሔር ለዳዊት በእውነት ማለ: አይጸጸትም::" (መዝ. 131:11) አሁን በእግዚአብሔር መጸጸት ኑሮበት አይደለም:: ቅዱስ ዳዊት የማያጸጽት ፍጹም ወዳጅ መሆኑን ሲገልጥ ነው እንጂ:: ጌታ ቅዱስ ዳዊትን "እንደ ልቤ የሆነ: ፈቃዴን የሚፈጽም: ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት" (መዝ. 88:20) ብሎ ሲናገር ሰምተን እጅግ አደነቅን::

+እንደ አምላክ ልብ ሆኖ መገኘት ምን ይረቅ?! ምንስ ይደንቅ?! ለዚህ አንክሮ ይገባል !! ጌታ ይቀጥልና ደግሞ "ዳዊትን እንዳልዋሸው አንድ ጊዜ በቅዱስነቴ ማልሁ" (መዝ. 88:35) ይላል::

*አቤት አባታችን ዳዊት ክብር: የክብር ክብር: ውዳሴና ስግደትም ላንተ በጸጋ ይገባል* እንላለን::

✝️ ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ዳዊት 7 ሃብታት ሲኖሩት:-

1.ሃብተ ትንቢት
2.ሃብተ መንግስት
3.ሃብተ ክህነት
4.ሃብተ በገና (መዝሙር)
5.ሃብተ ፈውስ
6.ሃብተ መዊዕ (ድል መንሳት)
7.ሃብተ ኃይል ተብለው ይታወቃሉ::

✝️ በ7ቱ ስሞቹም:-

1.ጻድቅ
2.የዋህ
3.ንጹሕ
4.ብእሴ እግዚአብሔር
5.ነቢየ ጽድቅ
6.መዘምር እና
7.ልበ አምላክ ተብሎ ይጠራል::

✞ ልደት ✞

=>ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት ስለ ልደቱ ሲናገር "እስመ ናሁ በኃጢአት ተጸነስኩ-በኃጢአት ተጸነስኩ" ይላል (መዝ. 50:5) አበው እንደ ነገሩን የቅዱስ ዳዊት አባት ደጉ እሴይ ከነገደ ይሁዳ የኢዮቤድ ልጅ ነው::

+ሚስቱን ሰሊብን አንድ ጐልማሳ በዝሙት ዐይን ሲፈልጋት ተመልክቶ ነበር:: አንድ ቀንም መንገድ ሔድኩ ብሎ ግን ያንን ጐልማሳ መስሎ ተመልሶ አብሯት አድሯል:: በዚያች በዚያች ሌሊትም ቅዱስ ዳዊት ተጸንሷልና እንዲህ ብሏል::

✞ ዕድገት ✞

=>ቅዱስ ዳዊት ከሕጻንነቱ ጀምሮ ጸጋ መንፈስ ቅዱስ ያደረበት ነበር:: ሕጸን ሳለ በእረኝነት በጐቹን አያስነካም ነበር:: አንበሳውን በጡጫ: ድቡን በእርግጫ: ነብሩን በሩጫ የያዙትን ያስጥላቸው ነበር:: በጥቂቱ በበግ እረኝነት ስለ ታመነ ለእሥራኤል እረኛ ሊሆን ተመርጧል::

✞ መቀባት ✞

+እግዚአብሔር ሳዖልን ከናቀው በሁዋላ ከእሴይ ልጆች መካከል "እንደ ልቤ የሆነውን ቀብተህ አንግስልኝ" ቢለው ነቢዩ ሳሙኤል ቤተ ልሔም ገብቷል::

+በዚያም ከኤልያብ እስከ አሚናዳብ: 7ቱን የእሴይን ልጆች ቢፈትን አልሆነም:: በቅዱስ ሚካኤል ጠቁዋሚነት ግን ከእረኝነቱ ዳዊት ተጠራ:: ገና ከርቀት ሲመጣ የዘይት ቀርኑ ቦግ ብሎ ተከፈተ::+በቅዱስ ዳዊት ራስ ላይም እንደ እሳት ፈላ:: በአምላክ ምርጫም በ12 ዓመቱ ንጉሥ ተባለ::

✞ ዳዊትና ጐልያድ ✞

=>ኢሎፍላውያን በጠላትነት በተነሱባቸው ጊዜም ጐልያድ የሚሉት የጌት ሰው እሥራኤልን ሲያስጨንቅ ለ40 ቀናት ቆይቶ ነበር:: ለአምላኩ ስምና ክብር የሚቀና ቅዱስ ዳዊት ግን በድፍረት ገጥሞ በፈጣሪው ኃይል: በጠጠር ጥሎታል:: ከእሥራኤልም ሽሙጥን አርቁዋል:: ግን ቅዱሱ ብላቴና: ጐልያድ ደግሞ 6 ክንድ (3 ሜትር) የሚረዝም ሰው ነበር::

✞ ስደት ✞

=>ቅዱስ ዳዊት ንጉሥ እንዲሆን ተቀብቶ ዙፋን አልጠበቀውም:: ጠላታቸውን ጥሎ ስላዳናቸው ፈንታ: ሳዖልን በገና እየደረደረ ስለ ፈወሰው ፈንታም ሊገደል ተፈለገ:: ፈጣሪው ከእርሱ ጋር ባይሆንም ይገድሉት ነበር::

+እርሱ ግን ለ18 ዓመታት በትእግስት ተሰደደ:: ከአንዴም ሁለት ሦስቴ ጠላቱን ሳዖልን አሳቻ ሥፍራ ላይ አግኝቶ በምሕረት ተወው:: በዚህ የዋሕነቱም በብሉይ ሆኖ "ጠላቶቻችሁን ውደዱ" የምትለውን ሕግ ፈጸማት:: (ማቴ. 7:45, መዝ. 16:4)

✞ ንግሥና ✞

=>ቅዱስ ዳዊት የስደት ዘመኑ ሲፈጸም ሳዖል ሞተ:: ምን ጠላቱ ቢሆን 'የሳዖል ገዳይ ነኝ' ያለውን ተበቀለ:: ስለ ጠላቱም አለቀሰ:: 30 ዓመት ሲሆነው ነግሦ ለ7 ዓመታት በኬብሮን: ለ33 ዓመታት በኢየሩሳሌም (ጽዮን) ሕዝበ እግዚአብሔርን ጠብቁዋል::

+በዘመኑም ጠላቶቹን ሁሉ ድል አድርጉዋል:: በልጁ አቤሴሎም እጅ መሰደድን: በሳሚ ወልደ ጌራ መሰደብንም ታግሷል::

✞ ንስሃ ✞

=>ቅዱሱ ንጉሥ ሁሉ ነገር የተሰጠው አባት ነው:: ሁሉ ሕይወቱም ለእኛ ት/ቤት ነው:: ሰው ነውና የኦርዮን ሚስት ቀምቶ: ኦርዮን አስገድሎ ነበር:: ጉዳዩን ነቢዩ ናታን በምሳሌ ሲነግረው ፍጹም ተጸጸተ::

+ማቅ ለብሶ: አመድ ነስንሶ አለቀሰ:: መሬትንም በእንባው ክንድ አራሳት:: ሐረግ እስከ ማብቀልም ደረሰ:: እግዚአብሔርም ንስሃውን ተቀብሎ ከፍ ከፍ አደረገው:: በንስሃ ለምትገኝ ጸጋም ምሳሌ ሆነ::

✞ ነቢይነት ✞

=>በቤተ ክርስቲያን ትምሕርት ቅዱስ ዳዊትን የሚያህል ነቢይ (ምሥጢር የበዛለት) አልተገኘም:: 'ከዓለም በፊት እንዲህ ነበረ' ብሎ: ከዚያ ከስነ ፍጥረት እስከ ዳግም ምጽዓት የተናገረ እርሱ ነው::

+ስለ መላእክት: ነቢያት: ሐዋርያት: ጻድቃን: ሰማዕታት: ደናግልና መነኮሳት ሁሉ መናገሩ ይደነቃል:: ስለ ድንግል ማርያምና ስለ መድኃኒታችን ክርስቶስም አምልቶ: አስፍቶ ተናግሯል:: 150 ምዕራፎች ባሉት መጽሐፈ ትንቢቱ ኃላፍያትንና መጻዕያትን ተመልክቷል::

+ስለዚህም አበው:-
"አልቦ ምስጢር ወአልቦ ትንቢት:
ዘኢተናገረ አቡነ ዳዊት" ይላሉ::

✞ መዝሙር ✞

=>ቅዱሱ ነቢይና ንጉሥ በጣም የሚታወቀው በዝማሬው ነው:: ለራሱ ባለ 10 አውታር : ለመዘምራኑ ደግሞ ባለ 8 አውታር በገናን አዘጋጅቶ ፈጣሪውን ያመሰግን ነበር:: 24 ሰዓት ሙሉ ስብሐተ እግዚአብሔር እንዳይቁዋረጥ 288 መዘምራንን በአሳፍ መሪነት መድቦ ነበር::

+ራሱም በፍጹም ተመስጦ: ማር ማር እያለው እግዚአብሔርን ያመሰግነው ነበር:: "ቃልህ ለጉረሮየ ጣፋጭ ነው" እንዲል:: (መዝ. 118:103) የዳዊት መዝሙሩ ለአጋንንት ትልቅ ጠላት ነው:: ቅዱሳን መላእክትም በዳዊት መዝሙር ይዘምራሉ::

"በዘቦቱ ይሴብሑ ሰማያውያን ወምድራውያን" እንዲል::

#ዳዊትና ጽዮን ✞

=>ቅዱስ ዳዊት ጽዮንን አንጾ ጽላተ ኪዳኑን አመጣ:: ለአምላከ ያዕቆብ ማደሪያን ሊፈልግም ዐይኑ ከእንቅልፍ ተከለከለ:: (መዝ. 131:2) የፈጣሪውን ፈቃድ ሊጠይቅ ሱባኤ ቢገባ "አኮ አንተ ዘትነድቅ ሊተ ቤተ - አንተ ሳትሆን የሚሠራልኝ ልጅህ ነው" አለው::

*አያይዞም የምሥጢረ ሥጋዌን ነገር ቢገልጥለት "ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ - እነሆ በኤፍራታ ሰማነው" ሲል ተናግሯል:: (መዝ. 131:6) የኪዳኑ ጽላት (ጽዮን) ከአቢዳራ ቤት ስትመጣ ከዙፋኑ ወርዶ: ከተራው ሕዝብ ጋርም ተቀላቅሎ በበገናና በመሰንቆ ተጫወተ::

*ስለ ፈጣሪው ክብሩን ተወ:: ከዳን እስከ ቤርሳቤህ የሚገዛ ኃያል ንጉሥ ነበርና:: በጽዮን ፊት እየወደቀ: እየተነሳ: እየታጠቀ: እየፈታ ሲዘምርም ሚስቱ ሜልኮል ናቀችው:: እግዚአብሔር ግን ከፍ ከፍ አደረገው:: (ሳሙ. 6:16)

✞ ክብረ ዳዊት ✞

=>እግዚአብሔር ስለ ዳዊት ሲል ኢየሩሳሌምን ብዙ ጊዜ ታድጉዋል:: ሰሎሞንና ሕዝቅያስን (ነገሥታቱን) ይቅር ያላቸው ስለ ባለሟሉ ስለ ዳዊት ነው::
✝️ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ✝️

አዳም ከሕቱም ምድር የተወለደ በተፈጥሮ ነው። እኔን ግን የጠቀመኝ የለም። ሔዋንም ከአዳም ግራ ጎን ተወለደች እሷም በተፈጥሮ ነው። ለኔ ግን የጠቀመችኝ የለም።
ቃየልም እንደ ሰው ሁሉ በዘር በሩካቤ ተወለደ የጠቀመኝ የረባኝ የለም። እንኳን እኔን እራሱንም አልጠቀመም። እሊህ ሦስቱ ልደታት ለማንም ለማን አይረቡም አይጠቅሙም።
ክርስቶስ ግን ያለ ዘር ያለ ሩካቤ ከድንግል ተወለደ ለሁሉ የሚረባ የሚጠቅም ሆነ✝️
ለዚህ ልደት መስገድ መገዛት ይገባል። ክብር ምስጋና ለዚህ ልደት ይገባል ጌትነትና ገናንነት ኀያልነት አዚዝነት እልልታ ግርግታ ለዚህ ልደት ይገባል፡፡

እንኳን ለ ጌታችን ለመዳኒታችን ለ እየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳቹ✝️

         
🕊

[ ✞ እንኩዋን ለቅዱስ "አምላካችን አማኑኤል" : "ዕለተ ማርያም" እና "ዕለተ ጌና ስቡሕ" ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ✞ ]

† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን።

--------------------------------------------

🕊  †  ቅዱስ አማኑኤል  †  🕊

- የክርስትና ሃይማኖት እጅግ ብዙ ምሥጢራትን ያካትታል:: ታላቅ መዝገብ ነውና:: ሰዎች እናልፋለን:: ዓለምም ታረጃለች እንጂ ምሥጢረ ክርስትና አያረጅም:: እዚህ ቦታ ላይ ይጠናቀቃልም አይባልም::

- "አማኑኤል" የሚለውን ስም መረዳት የሚቻለው በአንድ መንገድ : እርሱም ምሥጢረ ሥላሴንና ምሥጢረ ሥጋዌን ጠንቅቆ በመማር ነው:: ምሥጢራት ደግሞ በእምነት ለማይኖር: በትሕትናም ለማይቀርብ የሚገለጡ አይደሉም::

- እግዚአብሔር አንድም ነው: ሦስትም ነው:: ጊዜ ሣይሠፈር: ዘመንም ሳይቆጠር እግዚአብሔር በስም: በአካል: በግብር ሦስትነቱ: በባሕርይ: በሕልውና: በመለኮትና በሥልጣን አንድነቱ የጸና አምላክ ነው::

- ከዓለም መፈጠር በፊት ስለ ነበረው ነገር የሚያውቅ ራሱ ሥላሴ ብቻ ነው:: ዓለምን ከፈጠረ በሁዋላም ምሥጢረ ሥላሴ [ መለኮት ] ብለን የምንማረው ትምሕርት እንድንና እንጠቀም ዘንድ እርሱ የገለጠልንን ያህል ብቻ ነው::

- ይኼውም በየጊዜው እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ቅዱሳኑ የገለጠው ምሥጢር ነው:: ከዚህ አልፈን በሥጋዊ አዕምሯችን ጌታን "እንመርምርሕ" ብንለው ግን ፍጻሜአችን ሞት: ማደሪያችንም ገሃነመ እሳት መሆኑ አይቀርም::

- ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና እግዚአብሔር በአንድነቱና ሦስትነቱ ሳለ ይህንን ዓለም ፈጠረ:: እግዚአብሔር ዓለምን ለምን ፈጠረ ቢሉ :- ስሙን ቀድሰን ክብሩን እንድንወርስ ነው:: ከዚህ የተረፈውን ምክንያት ግን ራሱ ባለቤቱ ያውቃል::

- እግዚአብሔር በሁዋለኛው ዘመን ሰው የሆነበት ምሥጢር እኛን ለማዳን ቢሆንም ይሔው ተግባሩ ዓለም ሳይፈጠር ያሰበው እንጂ በአዳም ውድቀት ምክንያት ድንገት የታሰበ አይደለም::

- እግዚአብሔር አዳምን በ፯ ሃብታት አክብሮ በገነት ቢያኖረው "አትብላ" የተባለውን ዕፀ በለስ በላ:: በዚህም ከፈጣሪው ተጣልቶ: በሞተ ሥጋ ሞተ ነፍስ: በርደተ መቃብር ርደተ ገሃነም ተፈረደበት:: በሁዋላ ግን ንስሃ ስለ ገባ "ከ፭ ቀን ተኩል ፭ ሺህ ፭ መቶ ዘመን [ 5,500 ዘመን ] በሁዋላ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ" የሚል ቃል ኪዳንን ሰጠው::

- ከዚህ በሁዋላ ለ ፭ ሺህ ፭ መቶ [ 5,500 ] ዘመናት ጊዜ ወደ ታች ይቆጠር ጀመር:: ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆንና ዓለምን ማዳንም ትንቢት ይነገር: ሱባኤ ይቆጠር: ምሳሌም ይመሰል ገባ::

- ከአዳም እስከ ሙሴ [ ዘመነ አበው ] ምሳሌያት ይበዛሉ:: ከሙሴ እስከ ዳዊት [ ዘመነ መሣፍንት ] ምሳሌያቱ እየጐሉ መጥተዋል:: ከልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እስከ ቅዱስ ሚልክያስ ድረስ [ በዘመነ ነቢያት / ነገሥት ] ግን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስና ስለ ማደሪያ እናቱ እንደ ጐርፍ ፈሰዋል::

- ነቢያትም የመሲህን መምጣት እየጠበቁ በጾም: በጸሎትና በትሕርምት ኑረዋል:: እንባቸውንም አፍሰው ቅድመ እግዚአብሔር ደርሶላቸዋል:: መድኅን ክርስቶስም ተወልዶ አድኗቸዋል::

- "አማኑኤል" የሚለው ቃል ከእብራይስጥ ልሳን [ ከጽርዕ የሚሉም አሉ ] በቀጥታ የተወረሰ ሲሆን ትርጉሙም "እግዚአብሔር ምስሌነ - እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ" እንደ ማለት ነው:: [ ኢሳ.፯፥፲፬ , ማቴ.፩፥፳፪ ] ምሥጢሩ ግን ከዚህ የሠፋ ነው::

- " አማኑኤል" ማለት "እግዚአብሔር ከሥጋችን ሥጋን: ከነፍሳችን ነፍስን ነስቶ በፍጹም ተዋሕዶ እኛን መሰለን" ማለት ነው:: በሌላ አነጋገርም "አምላክ ሰው ሆነ: ሰውም አምላክ ሆነ" እንደ ማለት ነው::

- ይሕንን ሲያደንቁ ቅዱሳን ሊቃውንት "ወዝንቱ ስም ዓቢይ: ወኢይደሉ ፈሊጦቶ-ይህ ስም ታላቅ ነው:: ወደ ሁለት ሊከፍሉት [ ሊለዩት ] አይገባም" ብለው ምሥጢረ ተዋሕዶን አስረድተዋል:: [ ሃይ. አበ. ዘሳዊሮስ ]

- ስለዚህም ከሦስቱ አካላት አንዱ ወልድ እኛን ያድን ዘንድ በተለየ አካሉና በከዊነ ቃልነቱ ፍጹም የድንግል ማርያምን ሥጋ ተዋሕዶ የሰውነትንም: የአምላክነቱንም ሥራ ሠርቶ አድኖናል::

- በማሕጸነ ድንግል ከተቀረጸባት ደቂቃ ጀምሮም ፍጹም ተዋሕዶን ፈጽሟልና መቼም መች አምላክም: ሰውም ነው እንጂ ወደ ሁለትነት: ማለትም አምላክን ለብቻ: ሰውን ለብቻ አናደርግም::

- ስለዚህም ዛሬም: ዘወትርም እግዚአብሔር ቃል የተዋሐደው ሥጋችን በዘባነ ኪሩብ ሲሠለስና ሲቀደስ ይኖራል:: እርሱ ጌታችን እስከዚህ ድረስ ወዶናልና::

- ፈጣሪያች በሦስትነቱ:- ሥላሴ [ አብ: ወልድ: መንፈስ ቅዱስ ] : በአንድነቱ :- እግዚአብሔር: ኤልሻዳይ: አልፋ: ወዖ: ቤጣ: የውጣ: ኦሜጋ . . . እያልን እንደምንጠራው ሁሉ በሥጋዌው ምክንያት:- አማኑኤል: መድኃኔ ዓለም: ኢየሱስ: ክርስቶስ እያልን እንጠራዋለን::


🕊  †   ዕለተ ጌና   †   🕊

- ከሳምንታት በፊት ጀምረን የክርስቶስን የማዳን ሥራ ለመገንዘብ እየሞከርን ቆይተናል:: በተለይ ታኅሳስ ፯ ቀን "ስብከት" በሚል ስለ እግዚአብሔር ሰው መሆን ትንቢት መነገሩን: ምሳሌ መመሰሉን: ሱባኤ መቆጠሩን ተመልክተን ነበር::

- ቀጥለን ደግሞ ታኅሳስ ፲፬ ቀን " ብርሃን " በሚል አምላካችን እንደ ምን ባለ ጥበቡ ብርሃኑን እንደ ሰጠን: አንድም ወደን ወደ ጨለማ በገባን ጌዜ ሥጋችንን ተዋሕዶ ብርሃን እንደ ሆነልን ለማየት ሞክረናል::

- ታኅሳስ ፳፩ ቀን ደግሞ በበደላችን ምክንያት የነፍሳችንን እረኛ አጥተን ነበር:: ለእኛው በደል እርሱ ክሶ ድጋሚ መልካም እረኛችን ሆኖ በሥጋ ማርያም መለገለጡን አየን:: የዛሬው በዓል ዕለተ ጌና ደግሞ ማሠሪያው ነው::

- " ጌና " ማለት በቁሙ " ዕለተ ልደት ስቡሕ: ማለትም አምላክ ሰው የሆነበት ምስጉን ቀን " እንደ ማለት ነው:: ይህ ቀን ሁሌም በየዓመቱ "አማኑኤል [ ጌና ] " እየተባለ ይከበራል:: ምክንያቱ ደግሞ ጌታ የተጸነሰ መጋቢት ፳፱ [ 29 ] ቀን በመሆኑና ከዚህ ቀን ፱ [ 9 ] ወር ከ ፭ [ 5 ] ቀናት ብንጨምር ይህ ዕለት ታሕሳስ ፳፱ [ 29 ] ቀን ይመጣል::

- ነገር ግን በ ፬ [ 4 ] ኛው ዓመት ዘመነ ዮሐንስ ዻጉሜን ፮ [ 6 ] ስትሆን ፱ [ 9 ] ወር ከ ፮ [ 6 ] ቀን ስለሚሆን ቀኑን እንዳይለቅ በዘመነ ዮሐንስ ዕለተ ልደቱ ለክርስቶስ ታሕሳስ ፳፰ [ 28 ] ቀን ይከበራል:: ያም ሆኖ በዘመነ ዮሐንስ ታኅሳስ ፳፰ [ 28 ] ን አክብረናል ብለን ፳፱ [ 29 ] ን አንተወውም:: እርሱም ይከበራል::

- በዚያው ልክ ደግሞ በ3ቱ አዝማናት [በማቴዎስ: በማርቆስና በሉቃስ] ልደቱ በ ፳፱ [ 29 ] ነው ብለን ፳፰ [ 28 ] ን አንሽረውም:: " ጌና-አማኑኤል-ዕለተ ማርያም " እያልን እናከብረዋለን እንጂ:: ብዙ ጊዜም በተለምዶ በዓለ ልደትን "ጌና" በማለት ፈንታ "ገና" የምንል ብዙዎች አለን::

- ግን አበው ባቆዩልን ትውፊት "ጌና" ልደቱን የሚመለከት ሲሆን "ገና" ግን ባሕላዊ ጨዋታውን የሚመለከት ቃል ነው::


🕊  †   ዕለተ ማርያም   †   🕊

- ዳግመኛ ይህ ቀን ዕለተ ማርያም ይባላል:: "ማርያም" የሚለው ቃል ብዙ ትርጉምን ያዘለ የእናታችንና የእመቤታችን: የተስፋችንና መመኪያችን: የድንግል እመ ብርሃን ስም ነው::
HTML Embed Code:
2024/06/10 08:28:28
Back to Top