Channel: ግጥም ብቻ 📘
ጎዳናው ይገርማል?!
ጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ ~ #በረከት_በላይነህ
#ETHIOPIA | ይገርማል መንገዱ
እግረኛው ይገርማል
፧
ሸራ ጫማ ባ'ይነት
በነጫጭ ካልሲ
በሲኪኒ ሱሪ
ከመምህሩ ጋራ
አይስክሬም ሚልስ
የሀይስኩል ተማሪ
.
ፀባይኛ ወጣት
ጃንቦ ተከልሎ
በምርቃና ሆኖ
ሀሳብ የሚፈትል
አንዲት ሙ......ደኛ እናት
በ'ድሜ ከልጆቼ አንሳለው የምትል
ፒዛውን የሚገምጥ
ጭማቂ የሚመጥ
አራዳ አባወራ
በሚስቱ ትከሻ
በልጆቹ ምላስ
ቅምጥ የሚጣራ
.
አንድ ፍሬ ሴቶች
በተገዛ ቅንድብ
በተገዛ ፀጉር በተገዛ ጥፍር
በውሰት ወዘና የተብለጨለጩ
ማኪያቶ ከበው
ለውስኪ ሚንጫጩ
ጅናም ጅንሳም ወንዶች በሴቶች ጫጫታ የሚቁለጨለጩ
.
ይገርማል ጎዳናው ይገርማል መንገዱ....
.
ድንቡሽቡሽ ህፃናት
በቶም ኤንድ ጄሪ ሱስ
ቀልባቸው የከሳ
በአይፎኑ አጮልቆ
ያንጀሊናን ከንፈር የሚስም ጎረምሳ
.
ቀውጢ ዳያስፖራ
.
የሎቲው የቁምጣው የቲሸርቱ ጥለት የተንዘረፈፈው
አማርኛ ሲሸሽ "what's happen" የጠለፈው
.
ነቄ ብላቴና
.
ከዮፍታዬ ቀዬ
ካ'ዲስ አለማየሁ
ከመዝገቡ መንደር
የአዲስ አ'ባ ጥሪ
በቁምጣ ያበረረው
ከቅኔ ተጣልቶ
ከግዕዝ ተኳርፎ ሎተሪ ሚያዞረው
.
ፀዴ ብላቴና
.
ከባላገር ዘመን
ከጨለማ ዘመን
ወደ ብርሃን ጥግ ተሸጋገርኩ ብሎ
በሸንኮራ ምርኩዝ ከተማ ሚያካልል መቋሚያውን ጥሎ
ነብሱ እየሰለለች
በከተሜነት ወግ ባ'ራዳነት ልምሻ
ሲያዘግም የሚውል
ሊስትሮውን ጭኖ በታቦት ትከሻ
.
ፎቆቹ
.
በመስታወት ቁመት በቆርቆሮ ገፆች
ባ'ልሙኒየም ጥራዝ የተብረቀረቁ
የጌቶቻቸውን እድሜ ሚያሳብቁ
ሁሉም........ ሁሉም......ሁሉም ጥግ ናቸው
ለወደቀ ወገን ይራራል ልባቸው
.
ሁሉም
...... ሁሉም
.
ከዘለለት ጥድፊያ
ከሰርክ ውጣ ውረድ በተረፈች አንጀት
ለወደቀ ወገን ምርኩዝ ማበጃጀት
ሁሉም...... ሁሉም ይችላሉ
ስለ'ግዚአር ላለ ይመፀውታሉ
.
እኔ ግን........ እኔ ግን .........ቆጥራለው
የ'ድሜ ክቡር ጀንበር
በጎዳና ፅልመት ሲዋጥ አስተውላለው
ጡረታ መንገድ ዳር ሲከፈን አያለው
.
ቆጥራለው.....ቆጥራለው
.
ቆጥራለው አዛውንት
በየአቀበቱ በየቁልቁለቱ
ማረፊያ ፍለጋ የሚንከራተቱ
ቆጥራለው አዛውንት ከልጆቻቸው ፊት
የልመና መዝገብ የገለጡ አሮጊት
ቆጥራለው በየመንገዱ ዳር
እርጅና ሙሽራው ለምፅዋት ሲዳር
ቆጥራለው በየሸንተረሩ በየተፋሰሱ
አቀርቅሮ ሲያዘግም እርጅና ሞገሱ
ቆጥራለው በ'ያደባባዩ
የሽማግሌ አይኖች የልጅ ፊት እያዩ
ቆጥራለው በየሰርጣሰርጡ
በልመና ጉልበት ከሞት ሲፋጠጡ
የ'ርጅና መዳፎች እሾህ ሲጨብጡ
.
ቆጥሬ..... ቆጥሬ.......ቆጥሬ
በለማኝ አዛውንት ብዛት ተሳክሬ
የማሰንበቻ ስንቅ ከኪሴ ቆንጥሬ
ያፅድቆቴን ዋጋ በሳንቲም መንዝሬ
ባ'ዛውንት ምርቃት ከሀገር ከቀዬው ትርፌን ሳመሳስል
በጎዳናው ቀለም ፃድቅ መልኬን ስስል
ጎልቶ ሚታየኝ ግን የሚያሳፍር ምስል
በቀላል ጥያቄ የነተበ ምስል
.
ጥያቄ
.
የዲጄ ኳኳታ የደናሽ ጋጋታ
የድራፍት እርካታ ያ'ረቄ ድንፋታ
ባጣበበው መንገድ
እንደምን ይቻካል
ላ'ያት ሳንቲም ሰጥቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለወጣት ሹክሹክታ ለገደል ዝምታ
ላስመሳይ ጫጫታ ላድርባይ እሪታ
በተሰራ መንገድ
እውነት ቀላል ነው ወይ
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለቡቲክ ሰልፈኛ ለካፌ 'ድምተኛ
ለውስኪ ጭሰኛ ለበርገር ምርኮኛ
በተሰራ መንገድ
እንደምን ይቻላል
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
አያት....አያት...አያትነት ማለት
በደማቅ አሻራ የሸመኑት ጥለት
ለተራኪ እድሜ የተሰጠ አንደበት
ባ'ባት በ'ናት ፅናት የማይደክም ጉልበት
በልጅ ልጅ መነፅር የማያረጅ ውበት
በልጅ ልጆች ጥበብ የሚታደስ እውቀት
.....................................የሚታደስ እውነት
አያት ሆኑ ማለት
ድርብ አባትነት
ድርብ እናትነት
.
በተለይ እዚህማ.......
በዚህች አይነት ሀገር
ጎጆዋን ላቆመች
በተጋድሎ ካስማ
ባርበኝነት ማገር
በዚህች አይነት ሀገር
ጥያቄና መልሷን
ባ'ዛን በቅዳሴ በምትሰራ መንደር
በዱአ በፀሎት
በምናኔ ምርኩዝ በከረመች ሰፈር
የአያትነት ዋጋው በልኩ ቢሰፈር
ለሳንቲም ምርቃት ባልተሻማን ነበር!
.
ታሪክ በመዳፉ ስላደላደለው
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጉስ አያት አለው
የልጅ ልጆች ስባት ባያመነምነው
ያያቶቻችን መልክ ሁሌም አንድ አይነት ነው
.
እላለው... እላለው....
.
የልጆች ምፅዋት ያ'ያቶች ልመና
ያ'ባቶች ግርግር በሞላው ጎዳና
መንገዱ አይልቅም
ጎዳናው አያልቅም
ይሰፋል ይረዝማል ይሄዳል ይጓዛል
እግረኛው ሞኝ ነው
ሳንቲሙን ዘርዝሮ
ከወደቁ አዛውንት ምርቃት ይገዛል
.
መንገዱ ያስፈራል
መንገዱ ይጨንቃል
ልጆች ሳቅ ሲያንቃቸው
አያት እምባ ይጨምቃል
መንገዱ ያሰጋል መንገዱ ያረጃል
ከዘናጭ ልጆች ጎን እርዛት ያዘለ አያት ይወለዳል
.
ሰጪ ካለቀሰ ተበዳሪ ስቆ
ጌታ ከለመነ አማኙ 'ግር ወድቆ
ልዑል ከዘመረ ንጉሱ ተዋርዶ
ገፁ ተመሳቅሎ ሽፋኑ ካማረ
ወለሉ ተንቆ ምንጣፍ ከከበረ
ባ'ገርኛ ስሌት ማነው ያልከሰረ?
.
እላለው........እላለው
.
ከየጎዳናው ገፅ ጥያቄ አነሳለው
ጥያቄ እጥላለው
እርጅና ለማምሻው ጎዳናን ካመነ
አያት ከልጅ ልጁ ሳንቲም ከለመነ
ባገርኛ ስሌት ማነው ያልመከነ?
.
በ'ግዚኦታ ዘመን በምዕላ ዘመን
እመንገድ ዳር ወድቆ ትራፊ መለመን
በጥሞና ዘመን የሚያስቡት ማጣት
በማውረሻ እድሜ የሚሰጡት ማጣት
በማልበሻ ዘመን በ'ርዛት መቀጣት
በለጋሽነት ወቅት በማጉረሻ ዘመን
በጥማት መገረፍ በርሀብ መመንመን
ከሆነ እጣችን
ይጠየቅ ትርጉሙ የልጅነታችን
ይፈተሽ መንገዱ የልጅ ልጆቻችን
፧
ግድ የለም እንመን
፧
እንመን
፧
በሰውኛ ስሌት ውጤቱ ሲሰራ
ትውልድ ያደኸያል ያያቶች ኪሳራ
በልጅ ልጆች ዓለም
እንደጉድ ቢደለቅ ቢዘመር ቢዘፈን
አባት ይወራጫል ባ'ያቶች መታፈን
.
አባት ሆይ
.
ለልጆችህ ርዕዮት
ትላንቱን የረሳ ተስፋ ሲደራረት
ህልሜ ነው ይልሀል ያ'ያቶቹ ቅዠት
ከልጅህ አንደበት
ቋንቋ እንደዶፍ ቢዘንብ
ትርጉም ቢንፎለፎል ሺ ቃላት ቢጎርፍም
የልጅ ልጅ አግባቢ ግማሽ ገፅ አይፅፍም
ከልጆችህ ባህር
አሳ የሚያጠግቡ ለአሳ ሚስማሙ
እፅዋት ተክሎች
እንደጉድ ቢራቡ እንደጉድ ቢያብቡ
ገበታው አይሞላም ተቀዷል መረቡ
.
ግድ የለም እንመን........እንመን
.
የስኬት ክብደቱ
የምቾት አይነቱ
የነገ ውበቱ ባሻው ቋት ቢለካ
በምንም ቢሰፈር ባሻው ቃል ቢነገር
ጀግና ልጅ አትወልድም
አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር
.
ከፎቆቹ ጥላ....
ከያስፓልቱ ገላ ሲታተም ድምቀቴ
በመስታወት አጀብ ሲጠገን ጉልበቴ
ይኸው አነበብኩት
አያቶቼ ፊት ላይ ተፅፏል ሽንፈቴ
በመኪና ብዛት
በመስታወት አይነት ሲለካ ፍጥነቴ
በግንብ አጥር መአት
በፎቆች ጋጋታ ሲሰላ ስኬቴ
ይኸው ይታየኛል
አያቴ ገፅ ላይ ተስሏል ውድቀቴ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ተስሏል ሽንፈቴ!
***
@getem
@getem
#jeko
ጋዜጠኛ፣ ገጣሚና ደራሲ ~ #በረከት_በላይነህ
#ETHIOPIA | ይገርማል መንገዱ
እግረኛው ይገርማል
፧
ሸራ ጫማ ባ'ይነት
በነጫጭ ካልሲ
በሲኪኒ ሱሪ
ከመምህሩ ጋራ
አይስክሬም ሚልስ
የሀይስኩል ተማሪ
.
ፀባይኛ ወጣት
ጃንቦ ተከልሎ
በምርቃና ሆኖ
ሀሳብ የሚፈትል
አንዲት ሙ......ደኛ እናት
በ'ድሜ ከልጆቼ አንሳለው የምትል
ፒዛውን የሚገምጥ
ጭማቂ የሚመጥ
አራዳ አባወራ
በሚስቱ ትከሻ
በልጆቹ ምላስ
ቅምጥ የሚጣራ
.
አንድ ፍሬ ሴቶች
በተገዛ ቅንድብ
በተገዛ ፀጉር በተገዛ ጥፍር
በውሰት ወዘና የተብለጨለጩ
ማኪያቶ ከበው
ለውስኪ ሚንጫጩ
ጅናም ጅንሳም ወንዶች በሴቶች ጫጫታ የሚቁለጨለጩ
.
ይገርማል ጎዳናው ይገርማል መንገዱ....
.
ድንቡሽቡሽ ህፃናት
በቶም ኤንድ ጄሪ ሱስ
ቀልባቸው የከሳ
በአይፎኑ አጮልቆ
ያንጀሊናን ከንፈር የሚስም ጎረምሳ
.
ቀውጢ ዳያስፖራ
.
የሎቲው የቁምጣው የቲሸርቱ ጥለት የተንዘረፈፈው
አማርኛ ሲሸሽ "what's happen" የጠለፈው
.
ነቄ ብላቴና
.
ከዮፍታዬ ቀዬ
ካ'ዲስ አለማየሁ
ከመዝገቡ መንደር
የአዲስ አ'ባ ጥሪ
በቁምጣ ያበረረው
ከቅኔ ተጣልቶ
ከግዕዝ ተኳርፎ ሎተሪ ሚያዞረው
.
ፀዴ ብላቴና
.
ከባላገር ዘመን
ከጨለማ ዘመን
ወደ ብርሃን ጥግ ተሸጋገርኩ ብሎ
በሸንኮራ ምርኩዝ ከተማ ሚያካልል መቋሚያውን ጥሎ
ነብሱ እየሰለለች
በከተሜነት ወግ ባ'ራዳነት ልምሻ
ሲያዘግም የሚውል
ሊስትሮውን ጭኖ በታቦት ትከሻ
.
ፎቆቹ
.
በመስታወት ቁመት በቆርቆሮ ገፆች
ባ'ልሙኒየም ጥራዝ የተብረቀረቁ
የጌቶቻቸውን እድሜ ሚያሳብቁ
ሁሉም........ ሁሉም......ሁሉም ጥግ ናቸው
ለወደቀ ወገን ይራራል ልባቸው
.
ሁሉም
...... ሁሉም
.
ከዘለለት ጥድፊያ
ከሰርክ ውጣ ውረድ በተረፈች አንጀት
ለወደቀ ወገን ምርኩዝ ማበጃጀት
ሁሉም...... ሁሉም ይችላሉ
ስለ'ግዚአር ላለ ይመፀውታሉ
.
እኔ ግን........ እኔ ግን .........ቆጥራለው
የ'ድሜ ክቡር ጀንበር
በጎዳና ፅልመት ሲዋጥ አስተውላለው
ጡረታ መንገድ ዳር ሲከፈን አያለው
.
ቆጥራለው.....ቆጥራለው
.
ቆጥራለው አዛውንት
በየአቀበቱ በየቁልቁለቱ
ማረፊያ ፍለጋ የሚንከራተቱ
ቆጥራለው አዛውንት ከልጆቻቸው ፊት
የልመና መዝገብ የገለጡ አሮጊት
ቆጥራለው በየመንገዱ ዳር
እርጅና ሙሽራው ለምፅዋት ሲዳር
ቆጥራለው በየሸንተረሩ በየተፋሰሱ
አቀርቅሮ ሲያዘግም እርጅና ሞገሱ
ቆጥራለው በ'ያደባባዩ
የሽማግሌ አይኖች የልጅ ፊት እያዩ
ቆጥራለው በየሰርጣሰርጡ
በልመና ጉልበት ከሞት ሲፋጠጡ
የ'ርጅና መዳፎች እሾህ ሲጨብጡ
.
ቆጥሬ..... ቆጥሬ.......ቆጥሬ
በለማኝ አዛውንት ብዛት ተሳክሬ
የማሰንበቻ ስንቅ ከኪሴ ቆንጥሬ
ያፅድቆቴን ዋጋ በሳንቲም መንዝሬ
ባ'ዛውንት ምርቃት ከሀገር ከቀዬው ትርፌን ሳመሳስል
በጎዳናው ቀለም ፃድቅ መልኬን ስስል
ጎልቶ ሚታየኝ ግን የሚያሳፍር ምስል
በቀላል ጥያቄ የነተበ ምስል
.
ጥያቄ
.
የዲጄ ኳኳታ የደናሽ ጋጋታ
የድራፍት እርካታ ያ'ረቄ ድንፋታ
ባጣበበው መንገድ
እንደምን ይቻካል
ላ'ያት ሳንቲም ሰጥቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለወጣት ሹክሹክታ ለገደል ዝምታ
ላስመሳይ ጫጫታ ላድርባይ እሪታ
በተሰራ መንገድ
እውነት ቀላል ነው ወይ
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
ለቡቲክ ሰልፈኛ ለካፌ 'ድምተኛ
ለውስኪ ጭሰኛ ለበርገር ምርኮኛ
በተሰራ መንገድ
እንደምን ይቻላል
ላ'ያት ሳንቲም ሰቶ በ'ርካታ መራመድ?
.
አያት....አያት...አያትነት ማለት
በደማቅ አሻራ የሸመኑት ጥለት
ለተራኪ እድሜ የተሰጠ አንደበት
ባ'ባት በ'ናት ፅናት የማይደክም ጉልበት
በልጅ ልጅ መነፅር የማያረጅ ውበት
በልጅ ልጆች ጥበብ የሚታደስ እውቀት
.....................................የሚታደስ እውነት
አያት ሆኑ ማለት
ድርብ አባትነት
ድርብ እናትነት
.
በተለይ እዚህማ.......
በዚህች አይነት ሀገር
ጎጆዋን ላቆመች
በተጋድሎ ካስማ
ባርበኝነት ማገር
በዚህች አይነት ሀገር
ጥያቄና መልሷን
ባ'ዛን በቅዳሴ በምትሰራ መንደር
በዱአ በፀሎት
በምናኔ ምርኩዝ በከረመች ሰፈር
የአያትነት ዋጋው በልኩ ቢሰፈር
ለሳንቲም ምርቃት ባልተሻማን ነበር!
.
ታሪክ በመዳፉ ስላደላደለው
ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንጉስ አያት አለው
የልጅ ልጆች ስባት ባያመነምነው
ያያቶቻችን መልክ ሁሌም አንድ አይነት ነው
.
እላለው... እላለው....
.
የልጆች ምፅዋት ያ'ያቶች ልመና
ያ'ባቶች ግርግር በሞላው ጎዳና
መንገዱ አይልቅም
ጎዳናው አያልቅም
ይሰፋል ይረዝማል ይሄዳል ይጓዛል
እግረኛው ሞኝ ነው
ሳንቲሙን ዘርዝሮ
ከወደቁ አዛውንት ምርቃት ይገዛል
.
መንገዱ ያስፈራል
መንገዱ ይጨንቃል
ልጆች ሳቅ ሲያንቃቸው
አያት እምባ ይጨምቃል
መንገዱ ያሰጋል መንገዱ ያረጃል
ከዘናጭ ልጆች ጎን እርዛት ያዘለ አያት ይወለዳል
.
ሰጪ ካለቀሰ ተበዳሪ ስቆ
ጌታ ከለመነ አማኙ 'ግር ወድቆ
ልዑል ከዘመረ ንጉሱ ተዋርዶ
ገፁ ተመሳቅሎ ሽፋኑ ካማረ
ወለሉ ተንቆ ምንጣፍ ከከበረ
ባ'ገርኛ ስሌት ማነው ያልከሰረ?
.
እላለው........እላለው
.
ከየጎዳናው ገፅ ጥያቄ አነሳለው
ጥያቄ እጥላለው
እርጅና ለማምሻው ጎዳናን ካመነ
አያት ከልጅ ልጁ ሳንቲም ከለመነ
ባገርኛ ስሌት ማነው ያልመከነ?
.
በ'ግዚኦታ ዘመን በምዕላ ዘመን
እመንገድ ዳር ወድቆ ትራፊ መለመን
በጥሞና ዘመን የሚያስቡት ማጣት
በማውረሻ እድሜ የሚሰጡት ማጣት
በማልበሻ ዘመን በ'ርዛት መቀጣት
በለጋሽነት ወቅት በማጉረሻ ዘመን
በጥማት መገረፍ በርሀብ መመንመን
ከሆነ እጣችን
ይጠየቅ ትርጉሙ የልጅነታችን
ይፈተሽ መንገዱ የልጅ ልጆቻችን
፧
ግድ የለም እንመን
፧
እንመን
፧
በሰውኛ ስሌት ውጤቱ ሲሰራ
ትውልድ ያደኸያል ያያቶች ኪሳራ
በልጅ ልጆች ዓለም
እንደጉድ ቢደለቅ ቢዘመር ቢዘፈን
አባት ይወራጫል ባ'ያቶች መታፈን
.
አባት ሆይ
.
ለልጆችህ ርዕዮት
ትላንቱን የረሳ ተስፋ ሲደራረት
ህልሜ ነው ይልሀል ያ'ያቶቹ ቅዠት
ከልጅህ አንደበት
ቋንቋ እንደዶፍ ቢዘንብ
ትርጉም ቢንፎለፎል ሺ ቃላት ቢጎርፍም
የልጅ ልጅ አግባቢ ግማሽ ገፅ አይፅፍም
ከልጆችህ ባህር
አሳ የሚያጠግቡ ለአሳ ሚስማሙ
እፅዋት ተክሎች
እንደጉድ ቢራቡ እንደጉድ ቢያብቡ
ገበታው አይሞላም ተቀዷል መረቡ
.
ግድ የለም እንመን........እንመን
.
የስኬት ክብደቱ
የምቾት አይነቱ
የነገ ውበቱ ባሻው ቋት ቢለካ
በምንም ቢሰፈር ባሻው ቃል ቢነገር
ጀግና ልጅ አትወልድም
አያቶቿን ገድላ የምትሸልል ሀገር
.
ከፎቆቹ ጥላ....
ከያስፓልቱ ገላ ሲታተም ድምቀቴ
በመስታወት አጀብ ሲጠገን ጉልበቴ
ይኸው አነበብኩት
አያቶቼ ፊት ላይ ተፅፏል ሽንፈቴ
በመኪና ብዛት
በመስታወት አይነት ሲለካ ፍጥነቴ
በግንብ አጥር መአት
በፎቆች ጋጋታ ሲሰላ ስኬቴ
ይኸው ይታየኛል
አያቴ ገፅ ላይ ተስሏል ውድቀቴ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።ተስሏል ሽንፈቴ!
***
@getem
@getem
#jeko
መድሀኒት
""""""""""""
ተስፋን እንድሰንቅ
እፎይ ብዬ እንዳድር ልቤ እንደተመኘ፤
እሰይ አሹ ልበል
አይኔም እንቅልፍ ያግኝ
እስቲ በሉኝና መድሀኒት ተገኘ!
.
"ተገኘ እኮ" በሉኝ
ለሰውም፣ ለምድሩም ፣ለሀገሩም መድሀኒት፤
ለመንደር ፣ለቀዬው፣ ለአድባሩም መድሀኒት፤
ለወፍ፣ ለአራዊቱ ፣ለእንስሳው መድሀኒት፤
ለህፃን ፣ወጣቱ ፣ ለአዋቂው መድሀኒት፤
ኑሮ ኑሮ እንዲሆን
ህይወት እንድትጥም ተስፋን እንድሰነቅ!
.
ህይወት ምን ባትጥም
ካለመሰናክል ስንክሳር ካልኖራት፤
እጥፍ ትጥማለች
ዘዴ ሲገኝላት በሰዎች ብልሀት፤
ለደዌውም ፈውስ ለህመሙም መድሀኒት!
(እናማ)
ተስፋን እንድሰንቅ
እፎይ ብዬ እንዳድር ልቤ እንደተመኘ፤
እሰይ አሹ ልበል
አይኔም እንቅልፍ ያግኝ
እስቲ በሉኝና መድሀኒት ተገኘ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
""""""""""""
ተስፋን እንድሰንቅ
እፎይ ብዬ እንዳድር ልቤ እንደተመኘ፤
እሰይ አሹ ልበል
አይኔም እንቅልፍ ያግኝ
እስቲ በሉኝና መድሀኒት ተገኘ!
.
"ተገኘ እኮ" በሉኝ
ለሰውም፣ ለምድሩም ፣ለሀገሩም መድሀኒት፤
ለመንደር ፣ለቀዬው፣ ለአድባሩም መድሀኒት፤
ለወፍ፣ ለአራዊቱ ፣ለእንስሳው መድሀኒት፤
ለህፃን ፣ወጣቱ ፣ ለአዋቂው መድሀኒት፤
ኑሮ ኑሮ እንዲሆን
ህይወት እንድትጥም ተስፋን እንድሰነቅ!
.
ህይወት ምን ባትጥም
ካለመሰናክል ስንክሳር ካልኖራት፤
እጥፍ ትጥማለች
ዘዴ ሲገኝላት በሰዎች ብልሀት፤
ለደዌውም ፈውስ ለህመሙም መድሀኒት!
(እናማ)
ተስፋን እንድሰንቅ
እፎይ ብዬ እንዳድር ልቤ እንደተመኘ፤
እሰይ አሹ ልበል
አይኔም እንቅልፍ ያግኝ
እስቲ በሉኝና መድሀኒት ተገኘ!
አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)
@getem
@getem
@getem
#ዘመንኛ_ዘማች ❤️❤️❤️
በፊት ድሮ....ድሮ..
ከወንዶች ለይቶ ...ሀሞቱ ኮስትሮ...
ድግን መትረየሱን ..
በዝናር ሸልሞ...ከፈፉ ወድሮ
ባላንጣውን ለቅሞ ...በጥይት የቆላ
የዱር የገደሉ...የሀገሬው ጥላ
ሞት አልያ ጡረታ ...እስኪገላግለው
ግዳጁ... ግንባር ነው
ግንባሩን ...አይነሳም...ግንባር ለለመነው
ክብሩ ለሌላንጂ...
በሱ ደም ጠብታ...ለሚንዘባነነው
ብለን #እያመመን ...ስለሱ ሲነሳ
የተገላቢጦሽ
በኔና ባንች አገር...
ቅቤ ጠባሹ ነው ...የሚያገኘው ምሳ
የሞተልሽ እማ....
ሲሞት ኖሮ ኖሮ...
እንደቀደሙቱ ፥ አያገኝም ካሳ
ብንል ስናወጋ.... ከቀናቶች ቀድሞ
#ግዳጅ...
የወቶ አደር...የሚዋደቅ ቆሞ
አልያም የሀክሙ...
መድህን ለሚሆን ፥ ለሚማቅቅ ታሞ
የተተወላቸው ...አርገን ስንሟገት
ግዜ ጨከነና ... #ገደደን_መጓተት ።
ታዲያ ..ዛሬ...ዛሬ
እኔም ..አንቺም...ሌላው...
መሰንበቻው ጠፍቶን
ጭራቅ መአልት ወርዶ ...አለሙን ሲበላው
ሳልነካሽ መዋሉ ፥ እንዲሆንሽ ገዴ
ጦስ እንዳቶኝብኝ...ሰበብ ለዘመዴ
ግዳጅ ላይ ....ነን #እኛ ...
ወግ ደርሶን ለዜጋ
ቤት መሽቀን ሆኗል..
ስውር ጠላታችን...ከርሞው #የሚናጋ ።
እናም...ጓዴ....ውዴ ❤️❤️❤️
#ዘግተሽ ተቀመጪ ...
አልያ #ተሸፍነሽ... #ተጣጥበሽ ባግባቡ
እጆችሽ ለመንካት ... #ፊትሽ አካባቢ ሳይርገበገቡ
#ሳትተፋፈጊ...!!
#ሳትጨናነቂ...!!
ከሰው ሳትጠጊ ...ካምላክሽ ሳትርቂ
ምን ቢሳሳ ጎኔ......እንዴት ብትናፍቂ
ለኔም ላንቺ ሆነ
ለተቀረቅ ዜጋ ... #ግዳጁን_ጠብቂ!!!
#ያንቺው.... #ጓድ ❤️❤️❤️
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
✍ @Abr_sh
@getem
@getem
@getem
በፊት ድሮ....ድሮ..
ከወንዶች ለይቶ ...ሀሞቱ ኮስትሮ...
ድግን መትረየሱን ..
በዝናር ሸልሞ...ከፈፉ ወድሮ
ባላንጣውን ለቅሞ ...በጥይት የቆላ
የዱር የገደሉ...የሀገሬው ጥላ
ሞት አልያ ጡረታ ...እስኪገላግለው
ግዳጁ... ግንባር ነው
ግንባሩን ...አይነሳም...ግንባር ለለመነው
ክብሩ ለሌላንጂ...
በሱ ደም ጠብታ...ለሚንዘባነነው
ብለን #እያመመን ...ስለሱ ሲነሳ
የተገላቢጦሽ
በኔና ባንች አገር...
ቅቤ ጠባሹ ነው ...የሚያገኘው ምሳ
የሞተልሽ እማ....
ሲሞት ኖሮ ኖሮ...
እንደቀደሙቱ ፥ አያገኝም ካሳ
ብንል ስናወጋ.... ከቀናቶች ቀድሞ
#ግዳጅ...
የወቶ አደር...የሚዋደቅ ቆሞ
አልያም የሀክሙ...
መድህን ለሚሆን ፥ ለሚማቅቅ ታሞ
የተተወላቸው ...አርገን ስንሟገት
ግዜ ጨከነና ... #ገደደን_መጓተት ።
ታዲያ ..ዛሬ...ዛሬ
እኔም ..አንቺም...ሌላው...
መሰንበቻው ጠፍቶን
ጭራቅ መአልት ወርዶ ...አለሙን ሲበላው
ሳልነካሽ መዋሉ ፥ እንዲሆንሽ ገዴ
ጦስ እንዳቶኝብኝ...ሰበብ ለዘመዴ
ግዳጅ ላይ ....ነን #እኛ ...
ወግ ደርሶን ለዜጋ
ቤት መሽቀን ሆኗል..
ስውር ጠላታችን...ከርሞው #የሚናጋ ።
እናም...ጓዴ....ውዴ ❤️❤️❤️
#ዘግተሽ ተቀመጪ ...
አልያ #ተሸፍነሽ... #ተጣጥበሽ ባግባቡ
እጆችሽ ለመንካት ... #ፊትሽ አካባቢ ሳይርገበገቡ
#ሳትተፋፈጊ...!!
#ሳትጨናነቂ...!!
ከሰው ሳትጠጊ ...ካምላክሽ ሳትርቂ
ምን ቢሳሳ ጎኔ......እንዴት ብትናፍቂ
ለኔም ላንቺ ሆነ
ለተቀረቅ ዜጋ ... #ግዳጁን_ጠብቂ!!!
#ያንቺው.... #ጓድ ❤️❤️❤️
#አብርሀም_ተክሉ ( #መርዕድ)
✍ @Abr_sh
@getem
@getem
@getem
#በእውቀቱ_ስዩም
.
እንደ ጊዜው መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት
እንደሰው ጭካኔ፤ እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ ፤ ታምር ነው መኖሬ::
የበጎ ሰው ሀሳብ ፤ ሲካድ እለት በለት
ጉድጏድ ተምሶለት
ሰብእና ሲቀበር፤
በዚህ ምድር መኖር ፤ አያስመኝም ነበር::
ምድሩ ሳር ቅጠሉ፤ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፤ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ
ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር ፤አያስመኝም ነበር::
አዎ
ለጊዜውም ቢሆን፤ ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፤ ወደ ፊት ይጏዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ፤ ሚስቱን ያስረግዛል::
ይቅርታና ምህረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው ፤ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ ፤ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ ፤ ተገርስሶ አይወድቅም::
@getem
@getem
@getem
.
እንደ ጊዜው መክፋት
እንደ ግፉ መስፋት
እንዳገሩ ክስመት
እንዳገሬው ጥመት
እንደሰው ጭካኔ፤ እንደ ልቡ ፍሬ
ታምር ነው መትረፍሽ ፤ ታምር ነው መኖሬ::
የበጎ ሰው ሀሳብ ፤ ሲካድ እለት በለት
ጉድጏድ ተምሶለት
ሰብእና ሲቀበር፤
በዚህ ምድር መኖር ፤ አያስመኝም ነበር::
ምድሩ ሳር ቅጠሉ፤ በስጋት ተሞልቶ
የማለዳው ሰማይ፤ እንዳንቀልባ ቀልቶ
ታረደ
ነደደ
ከዘብጥያ ወጥቶ
ዘብጥያ ወረደ
የሚል ዜና ብቻ አየሩን ሲሞላው
ሰው በገዛ ጥላው
በርግጎ ሲሸበር
በዚህ ምድር መኖር ፤አያስመኝም ነበር::
አዎ
ለጊዜውም ቢሆን፤ ግፍ ያደነዝዛል
በደል ያስተክዛል
ጊዜም ጠብን ሽሮ፤ ወደ ፊት ይጏዛል
በልብ ሰሌዳ ላይ ፤ቂም ይደበዝዛል
በነገ ያመነ
ልጁን ቀብሮ መጥቶ፤ ሚስቱን ያስረግዛል::
ይቅርታና ምህረት
ፍቅርና ህብረት
ከግፍ ጋር ፍልሚያቸው ፤ ቢሆን የሞት ሽረት
ዳገት ይወጣሉ ፤ በንጥፍጣፊ አቅም
የመኖር ፍላጎት
ዘመም ይላል እንጂ ፤ ተገርስሶ አይወድቅም::
@getem
@getem
@getem
#ለምን_ነው_የተውኸኝ ?
[በርናባስ ከበደ]
-
በሰደድ እሳት ውስጥ : እንደ መራመዴ
እንዴት አይሞቀኝም? ይቅርና መንደዴ።
ግግር በረዶ ላይ : በባዶ እግሬ ቆሜ
ለምን ያተኩሳል? ሥጋዬ እና ደሜ ።
ሁሉም በወረፋው : ወር ተራ ሲደርሰው
እንደ ጉሊት ሸቀጥ ፡ ክበህ ስታፈርሰው
በምን ሃጥያቴ ነው : የነጠልኸኝ ከሰው??
ምነው እኔ ብቻ? ያለሁ በእርጋታ
ልድን እወዳለሁ : ማረኝ የኔ ጌታ።
____________________________
@getem
@getem
@getem
[በርናባስ ከበደ]
-
በሰደድ እሳት ውስጥ : እንደ መራመዴ
እንዴት አይሞቀኝም? ይቅርና መንደዴ።
ግግር በረዶ ላይ : በባዶ እግሬ ቆሜ
ለምን ያተኩሳል? ሥጋዬ እና ደሜ ።
ሁሉም በወረፋው : ወር ተራ ሲደርሰው
እንደ ጉሊት ሸቀጥ ፡ ክበህ ስታፈርሰው
በምን ሃጥያቴ ነው : የነጠልኸኝ ከሰው??
ምነው እኔ ብቻ? ያለሁ በእርጋታ
ልድን እወዳለሁ : ማረኝ የኔ ጌታ።
____________________________
@getem
@getem
@getem
ይማርህ ዘንድሮ!
እንዲህ እንደዛሬ ሳይጠፋን ይማርህ
ድንገት ጉሮሮህን ትንጋት ቢጎበኝህ
አንተ አስነጥስ እንጂ ደሞ ምንአባቱ
ያስልህ አስሬ ሳል ይሙታባቱ
ከጎንህ ያለ ሰው ይሽቀዳደም ነበር
ያዥጎደጎድልህ የ"ይማርህ እግዜር"
ይማርህ ነው በቀኝ ይማርህ ነው በግራ
"እኔን" ነበር 'ሚልህ ሁሉም በየተራ::
ዘንድሮ.........ዘንድሮ ጉድ ፈልቷል
ይማርህ ምንድነው? ቃሉ ጠፍቶበታል
ፊቴ ታስላለህ ጎበዝ ምን ነክቶሀል?
"አስነጠሰህ እኮ?" ብርቅ ያረግብሀል!
እግሬ አውጭን ከጎንህ ያንባርቅብሀል
እማይ ድረሽ ብሎ ይጠየፍህ ይዟል
አፉ በእፍኝ ጨርቅ ዙሪያው ተለጉሞ
እጅ አምባር ዙሪያውን ላስቲክ ተሰይሞ!
መዳፍ አይበሉባው በተጠንቀቅ ቆሞ!::
እግዚኦ መሀርነ የዘንድሮ ነገር
ሲያስልህ ብትውል ሲያነጥስህ ብታድር
እግዜርን ና ውረድ ማረው ይል የነበር
አፍንጫ አፉን ይዞ ይሮጥልህ ጀመር::
ኧረግ የጉድ አገር::
ወዴት አለ ማስኩ
ወዴት አለ ጏንቱ
ኮረና የታባቱ
የሰማዩ ጌታ እሱ ባለቤቱ
እግዜር በብልሀቱ
ያድነነ ከመዓቱ
ይሰውረን በምህረቱ
በንተማርያም ወላዲቱ::
©️አቤንኤዘር ጥላሁን/papi
Mar 30, 2020
@getem
@getem
@getem
እንዲህ እንደዛሬ ሳይጠፋን ይማርህ
ድንገት ጉሮሮህን ትንጋት ቢጎበኝህ
አንተ አስነጥስ እንጂ ደሞ ምንአባቱ
ያስልህ አስሬ ሳል ይሙታባቱ
ከጎንህ ያለ ሰው ይሽቀዳደም ነበር
ያዥጎደጎድልህ የ"ይማርህ እግዜር"
ይማርህ ነው በቀኝ ይማርህ ነው በግራ
"እኔን" ነበር 'ሚልህ ሁሉም በየተራ::
ዘንድሮ.........ዘንድሮ ጉድ ፈልቷል
ይማርህ ምንድነው? ቃሉ ጠፍቶበታል
ፊቴ ታስላለህ ጎበዝ ምን ነክቶሀል?
"አስነጠሰህ እኮ?" ብርቅ ያረግብሀል!
እግሬ አውጭን ከጎንህ ያንባርቅብሀል
እማይ ድረሽ ብሎ ይጠየፍህ ይዟል
አፉ በእፍኝ ጨርቅ ዙሪያው ተለጉሞ
እጅ አምባር ዙሪያውን ላስቲክ ተሰይሞ!
መዳፍ አይበሉባው በተጠንቀቅ ቆሞ!::
እግዚኦ መሀርነ የዘንድሮ ነገር
ሲያስልህ ብትውል ሲያነጥስህ ብታድር
እግዜርን ና ውረድ ማረው ይል የነበር
አፍንጫ አፉን ይዞ ይሮጥልህ ጀመር::
ኧረግ የጉድ አገር::
ወዴት አለ ማስኩ
ወዴት አለ ጏንቱ
ኮረና የታባቱ
የሰማዩ ጌታ እሱ ባለቤቱ
እግዜር በብልሀቱ
ያድነነ ከመዓቱ
ይሰውረን በምህረቱ
በንተማርያም ወላዲቱ::
©️አቤንኤዘር ጥላሁን/papi
Mar 30, 2020
@getem
@getem
@getem
# ሊነበብ_ይገባል
፡፡።።።።።።።።
# ከማንበባችሁ_በፊት_እጃችሁን_ታጠቡ !!!!
# ሣሙኤል_ሰሎሞን
ቁስል ደዌ መቶት
ዘመዶቹ የሸሹት
""
ኢዮብ ሰው ነበረ
""
አካሉ የሸተተ
እጅ እግሮቹን ያጣ
""
ኢዮብ ሰው ነበረ
""
ሚስቱ የከዳችው
አለም የተወችው
""
ኢዮብ ሰው ነበረ
""
በማጣቱ አልከፋው
ቢያመው ያላመመው
ህመሙን የረታው
""
በግዜሩ የሚያምን
እዮብ ሰው ነበረ
ከህመሙም በፊት
ከህመሙም ሲድን
አመስጋኝ ነበረ
# ሁሌም '''አመስጋኝ ሁን።
እየውልህ•••••••
እዮብ በጤናው አመስጋኝ ነበር።
እዮብ በበሽታውም አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ሃብትና ንብረት ሞልቶት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ሃብትና ንብረቱ ወድሞ አመስጋኝ ነበር።
እዮብ እጅና እግሩ ተቆራርጦ አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ልጆቹ አልቀውበት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ሚስቱ ከድታው አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ዘመዶቹ ፊት አዙረውበት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ሜዳው ገደል ሁኖበት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ቀንና ለሊት ተፈራርቀውበት ሲነጋ መች ነው ሚመሸው ሲመሽ መቸ ነው።
ሚነጋው እያለ ሰውነቱን ትል እያፈላ አመስጋኝ ነበር።
እዮብ እንዴት አደርክ ስትለው መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ነው።
ታጋሽ እንደ እዮብ እንሆን ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን
@getem
@getem
@getem
፡፡።።።።።።።።
# ከማንበባችሁ_በፊት_እጃችሁን_ታጠቡ !!!!
# ሣሙኤል_ሰሎሞን
ቁስል ደዌ መቶት
ዘመዶቹ የሸሹት
""
ኢዮብ ሰው ነበረ
""
አካሉ የሸተተ
እጅ እግሮቹን ያጣ
""
ኢዮብ ሰው ነበረ
""
ሚስቱ የከዳችው
አለም የተወችው
""
ኢዮብ ሰው ነበረ
""
በማጣቱ አልከፋው
ቢያመው ያላመመው
ህመሙን የረታው
""
በግዜሩ የሚያምን
እዮብ ሰው ነበረ
ከህመሙም በፊት
ከህመሙም ሲድን
አመስጋኝ ነበረ
# ሁሌም '''አመስጋኝ ሁን።
እየውልህ•••••••
እዮብ በጤናው አመስጋኝ ነበር።
እዮብ በበሽታውም አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ሃብትና ንብረት ሞልቶት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ሃብትና ንብረቱ ወድሞ አመስጋኝ ነበር።
እዮብ እጅና እግሩ ተቆራርጦ አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ልጆቹ አልቀውበት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ሚስቱ ከድታው አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ዘመዶቹ ፊት አዙረውበት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ሜዳው ገደል ሁኖበት አመስጋኝ ነበር።
እዮብ ቀንና ለሊት ተፈራርቀውበት ሲነጋ መች ነው ሚመሸው ሲመሽ መቸ ነው።
ሚነጋው እያለ ሰውነቱን ትል እያፈላ አመስጋኝ ነበር።
እዮብ እንዴት አደርክ ስትለው መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ነው።
ታጋሽ እንደ እዮብ እንሆን ዘንድ ፈጣሪ ይርዳን
@getem
@getem
@getem
እንደ እኔ 'ላለ ሰው
እንደ እኔ 'ላለ ሰው
ሃጢያት ለወረሰው
በህንፃ እግዚአብሔር፤በልቡ መንበር ላይ ክፋት ላነገሰው
በአለም ለጠፋ መንገድ ላልመለሰው
ባልጠበቀው ሰዓት መቅሰፍትህ ቢመጣ
ቅጣት ቢያሸብረው መድረሻ ቢያጣ
አምላኩን ቢያስታውስ ፤ከልቡ ቢመለስ
ብሎ ቢጠይቀው "አምላክ ተለመነን መከራውን አስታግስ"
በደሉን ቢረሳ ቢል "እርሱ ይጠብቀኛል"
አሳቡን ቢጥል፤ፍርሃቱን ቢያስወግድ ሸክሙን ቢያቃልል
እንደ እኔ ያለ ሰው
ቀና ብሎ ቢማፀን እርሱን ቢጠይቀው
መልስ ይኖረው ይሆን አምላክ የሚሰጠው?
.
.
.
ለምንወዳቸው ስንል እንጠንቀቅ🙏
21/7/2012 ሶፈ
.
.
.
@getem
@getem
@getem
እንደ እኔ 'ላለ ሰው
ሃጢያት ለወረሰው
በህንፃ እግዚአብሔር፤በልቡ መንበር ላይ ክፋት ላነገሰው
በአለም ለጠፋ መንገድ ላልመለሰው
ባልጠበቀው ሰዓት መቅሰፍትህ ቢመጣ
ቅጣት ቢያሸብረው መድረሻ ቢያጣ
አምላኩን ቢያስታውስ ፤ከልቡ ቢመለስ
ብሎ ቢጠይቀው "አምላክ ተለመነን መከራውን አስታግስ"
በደሉን ቢረሳ ቢል "እርሱ ይጠብቀኛል"
አሳቡን ቢጥል፤ፍርሃቱን ቢያስወግድ ሸክሙን ቢያቃልል
እንደ እኔ ያለ ሰው
ቀና ብሎ ቢማፀን እርሱን ቢጠይቀው
መልስ ይኖረው ይሆን አምላክ የሚሰጠው?
.
.
.
ለምንወዳቸው ስንል እንጠንቀቅ🙏
21/7/2012 ሶፈ
.
.
.
@getem
@getem
@getem
እናቱ ሩቂያ ልጅየው መሃመድ፤
ተሳፈሩ እያለ፤
ባውንዱን ሾፈረው እንደ ራያ መንገድ።
ጥጃም የሰጠ ሰው፤
በሬም የሰጠ ሰው፤ ሰጠሁ ይላል አሉ፤
በሰፊው ዳውላህ፤
መገን ለመሃመድ፤
ዘርፈህ የምትሰጠው እንዴት ነህ ጀሊሉ።
አገሩ ወሎ ነው ቀየው መሃል የጁ፤
በዳና በጫሌ ተመርቋል ልጁ፣
አገር የከፋው ቀን፤
ነይቶ የሚሰጥ በረካ ነው እጁ።
################
ልመርቃችሁ!!!!
የጁ የገጠር ዘመድ ሰርግ ሂጄ ከወጣቶች ዘፈን ስር የሰማሁዋት ስንኝ ደግሞ ይች ነበረች።
የሱፉን ማጌጫ ይሉታል ገበርዲን፤
ከሰርጌ ይመጣል ፤
የባውንዱ ጌታ፤ ሸጋው አላሙዲን።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@Nagayta
ተሳፈሩ እያለ፤
ባውንዱን ሾፈረው እንደ ራያ መንገድ።
ጥጃም የሰጠ ሰው፤
በሬም የሰጠ ሰው፤ ሰጠሁ ይላል አሉ፤
በሰፊው ዳውላህ፤
መገን ለመሃመድ፤
ዘርፈህ የምትሰጠው እንዴት ነህ ጀሊሉ።
አገሩ ወሎ ነው ቀየው መሃል የጁ፤
በዳና በጫሌ ተመርቋል ልጁ፣
አገር የከፋው ቀን፤
ነይቶ የሚሰጥ በረካ ነው እጁ።
################
ልመርቃችሁ!!!!
የጁ የገጠር ዘመድ ሰርግ ሂጄ ከወጣቶች ዘፈን ስር የሰማሁዋት ስንኝ ደግሞ ይች ነበረች።
የሱፉን ማጌጫ ይሉታል ገበርዲን፤
ከሰርጌ ይመጣል ፤
የባውንዱ ጌታ፤ ሸጋው አላሙዲን።
(( ጃ ኖ ))💚💛❤
@getem
@getem
@Nagayta
ቅ ና ት !
(( በአበባው መላኩ))
======©======
.
.
ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ።
~
ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የዕንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የምድር የቀላይ ጥፋት
በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው
ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፍርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ ።
…
ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅ
በዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ።
~
ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ
ያሳበደችኝ ቅ ና ቴ ።
.
.
@getem
@getem
(( በአበባው መላኩ))
======©======
.
.
ፍቅሬን ሜዳ ላይ ጥላ
ስትከዳኝ አይቻታለሁ
እንደገፋችኝ ትገፋ
እያልኩ እረግማታለሁ።
~
ዘወትር ሙሾ ታላዝን
የዕንባ ማዕበል ይጠባት
ደስታዬን እንዳጨለመች
ደስታዋ ይጨልምባት
ሺህ እጥፍ ትጨድ አበሳ
ለዘራችብኝ ጥፋት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የኮራችበትን ገላ
መብረቅ ያንድደው በቁጣ
በላይዋ ዲን ይውረድባት
ጥጋት መሸሻ ትጣ።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የምድር የቀላይ ጥፋት
በላይዋ ይውረድ ኩነኔ
ኑሮዋን ሲዖል ያድርገው
ስቃይዋን ያሳየኝ በዓይኔ።
እንደከዳችኝ ትከዳ
የኔ ያለችው ይሽሻት
ቀላዋጭ ዓይኗን ያፍርጠው
ከውካዋ እግሯን ያልምሻት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ ።
…
ክንዷ በመጅ ይሰበር
ሌላ ያቀፈችበት
አባጨጓሬ ይሙላው
ፍራሹ የተኛችበት።
~
እያልኩ እረግማታለሁ።
…
የሌላ ሆና ብትከዳኝ
አይጠሉ ጠልቻታለሁ
ስለማተቤ ብጠየቅ
በዓለም ላይ ካለ የምሻው
የረገምኳትን እላለሁ
ሌላም እርካታ የለኝ
እሷን አምጡልኝ እላለሁ።
~
ጥላቻዬና ፍቅሬ ናት
እርግማኔና በረከቴ
ያለሷ ሕይወት የሌለኝ
ያሳበደችኝ ቅ ና ቴ ።
.
.
@getem
@getem
HTML Embed Code: