TG Telegram Group Link
Channel: BF SPORT
Back to Bottom
ፈረንሳይ ለተከታታይ ዓመት ለፍፃሜ አልፈዋል!

የ 2018 የዓለም ሻምፒዮኖቹ ፈረንሳይ በግማሽ ፍፃሜው ሞሮኮን 2ለ0 በመርታት ለተከታታይ ዓመታት ለዓለም ዋንጫው ለፍፃሜው ማለፋቸውን አረገግጠዋል።

√ ራንዳል ኮሎ ሙአኒ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ጎሉን ለሀገሩ አስቆጥሯል።

√ አንቱዋን ግሪዝማን በዘንድሮው የዓለም ዋንጫ ብዙ የግብ እድሎችን መፍጠር የቻለ ቀዳሚው ተጫዋች ሆኗል።

√ ፈረንሳይ በዓለም ዋንጫ ታሪክ ለተከታታይ ዓመት ለፍፃሜ ማለፍ ያቸሉ ስድስተኛ ሀገር ሆነዋል።

√ ፈረንሳይ እሁድ አመሻሽ 12:00 ሰዓት በሚደረገው የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ፍፃሜ #አርጀንቲናን የምትገጥም ይሆናል።

√ ለሶስተኛ ደረጃ በሚደረግ ጨዋታ #ሞሮኮ እና #ክሮሽያ ቅዳሜ 12:00 ሰዓት መርሐ ግብራቸውን ያካሂዳሉ።
#QatarWorldCup 🇶🇦

ያለፉትን አስር ዓመታት በፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝነት እያገለገሉ የሚገኙት ዲድዬ ዴሻምፕ ስኬታማ የሚባል ጊዜን ከብሔራዊ ቡድኑ ጋር እያሳለፉ ይገኛሉ።

ለአብነት ያክል :-

2014 👉 የብራዚል ዓለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ

2016 👉 የአውሮፓ ዋንጫ ፍፃሜ

2018 👉 የሩሲያ ዓለም ዋንጫ ሻምፒዮን

2021 👉 የአውሮፓ ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ

2022 👉 የኳታር ዓለም ዋንጫ የፍፃሜ ተፋላሚ
" ሶስተኛ ደረጃ ለመጨረስ እንሞክራለን "

ለፍፃሜ ለማለፍ የነበራቸው እድል በዓለም ሻምፒዮኖቹ ፈረንሳይ የተገታው ሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን ዋና አሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ ያገኟቸውን እድሎች አለመጠቀማቸውን ተናግረዋል።

" የተቻለንን ሁሉ በዛሬው ዕለት አድርገናል ፣ አንዳንድ ተጫዋቾቻችን በሚያሟሙቁበት ወቅት ጉዳት አጋጥሟቸዋል የተወሰኑ እድሎችን ብናገኝም ወደ ግብነት መቀየር አልቻልንም ፣ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ ለማጠናቀቅ የተቻለንን እናደርጋለን " ሲሉ ተደምጠዋል።
Watch "ሄኖክ አበበ ይቅርታ" on YouTube
https://youtu.be/Ru0u0Eg0Aew
የሄኖክ አበበ አዲስ አልበም
ዘፈኑ ስለሚጠፋ ቶሎ ዳውሎድ አርጉት
ዛሬ የሚደረግ የፊፋ አለም ዋንጫ የደረጃ ጨዋታ

12:00 | ክሮሺያ ከ ሞሮኮ
ሞሮኮ አራተኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል !

በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ለሶስተኛ ደረጃ በተደረገ መርሐ ግብር ክሮሽያ 2ለ1 በሆነ ውጤት የሰሜን አፍሪካዊቷን ሀገር ሞሮኮ በመርታት #ሶስተኛ ደረጃን ይዘው አጠናቀዋል።

√ ግቫርዲዮላ እና ኦርሲች የክሮሽያን የማሸነፊያ ጎሎች ከመረብ ሲያሳርፉ ዳሪ የሞሮኮን ብቸኛ ግብ ያስቆጠረው ተጫዋች ሆኗል።

√ በዘንድሮ የዓለም ዋንጫ ደማቅ ታሪክን መፃፍ የቻሉት አፍሪካዊቷ ሞሮኮ #አራተኛ ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን አገባደዋል።

√ የክሮሽያ ብሔራዊ ቡድን በተከታታይ ዓለም ዋንጫዎች በምርጥ ሶስት ውስጥ ማጠናቀቅ ችለዋል።
ዛሬ የሚደረግ የፊፋ አለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ

12:00 | አርጀንቲና ከ ፈረንሳይ
ማን የአለም ዋንጫውን ያነሳል??
Anonymous Poll
67%
አርጀንቲና 🇦🇷
33%
ፈረንሳይ🇫🇷
🏆 የፊፋ አለም ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ


         Full-Time

🇦🇷 አርጀንቲና 3-3 ፈረንሳይ 🇫🇷
#ሜሲ 22'[p]   #ምባፔ 80' (p)
#ዲማሪያ 37'   #ምባፔ 82'
#ሜሲ 109' #ምባፔ 119'
[ፔናሊቲ 4-2]
#CHAMPION 🏆🏆🏆

የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን በታሪካቸው ለሶስተኛ ጊዜ የዓለም ዋንጫ አሸንፈዋል።
የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን አቀባበል ይደረግለታል !

በኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ያጠናቀቀው የፈረንሳይ ብሔራዊ ቡድን ወደ ሀገራቸው ሲገቡ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ተገልጿል።

በኳታር ተገኝተው የፍፃሜ ጨዋታውን የተከታተሉት ፕሬዝዳንቱ ኢማኑኤል ማክሮን ቡድኑ ፈረንሳይ ሲደርስ ደማቅ አቀባበል እንደሚደረግላቸው ገልፀዋል።
ሊዮኔል ሜሲ ጫማውን አይሰቅልም!

የዓለም ዋንጫ አሸናፊው የአርጀንቲና ብሔራዊ ቡድን አምበል ሊዮኔል ሜሲ ራሱን ከብሔራዊ ቡድን እንደማያገል ከምሽቱ ጨዋታ በኋላ ተናግሯል።

ሊዮኔል ሜሲ ምን አለ?

" ራሴን ከ ብሔራዊ ቡድን አላገልም ፣ ሻምፒዮን ሆኜ መጫወቴን መቀጠል እፈልጋለሁ ፣ ፈጣሪ ይህን ዋንጫ እንደሚሰጠኝ አውቅ ነበር ፣ በእግር ኳስ ህይወቴ ይህ ዋንጫ ያስፈልገኝ ነበር።

ይህ ስኬት ህይወቴን በሙሉ ስፈልገው የነበረ ዋንጫ ነው ፣ ከልጅነቴ ጀምሮ ህልሜ የዓለም ዋንጫን ማሸነፍ ነበር " ሲል ተናግሯል።
የእንግሊዝ ፕሪሚየር በ17ተኛ ሳምንት ጨዋታ በቦክሲንግ ደይ ጨዋታ ይጀምራል!

📆|ሰኞ

09:30 | ብሬንትፎርድ ከ ቶተንሃም
12:00 | ክርስቲያል ፓላስ ከ ፉልሃም
12:00 | ኤቨርተን ከ ወልቭስ
12:00 | ሌስተር ሲቲ ከ ኒውካስትል
12:00 | ሳውዝሃምፕተን ከ ብራይተን
02:30 | አስቶንቪላ ከ ሊቨርፑል
05:00 | አርሰናል ከ ዌስትሃም

📆|ማክሰኞ

02:30 | ቼልሲ ከ ቦርንማውዝ
05:00 | ማን,ዬናይትድ ከ ኖቲንግሃም

📆|ዕሮብ

05:00 | ሊድስ ከ ማን,ሲቲ
HTML Embed Code:
2024/05/21 06:48:40
Back to Top