TG Telegram Group Link
Channel: BF SPORT
Back to Bottom
ክሮሽያ የግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል !

120 ደቂቃዎችን በወሰደው የብራዚል እና ክሮሽያ ፍልሚያ የአሰልጣኝ ዝላትኮ ዳሊች ስብስብ ከመመራት ተነስተው አቻ በመውጣት በመለያ ምት ብራዚልን ረተው ወደ አራት ውስጥ ተቀላቅለዋል።

√ ክሮሽያ ለተከታታይ የዓለም ዋንጫዎች የደቡብ አሜሪካዎቹን ሀያላን ብራዚል እና አርጀንቲናን ከውድድሩ አሰናብተዋል።

√ ሮድሪጎ እና ማርኪኖስ የብራዚልን የመለያ ምት ከመረብ ማሳረፍ #ሳይችሉ ቀርተዋል።

√ ኔይማር ለብራዚል ብሔራዊ ቡድን ያስቆጠራቸውን የግብ መጠን ወደ ሰባ ሰባት ከፍ አድርጓል።

√ ኔይማር የብሔራዊ ቡድኑ ከፍተኛ ግብ አግቢነት ሪከርድን ከፔሌ ጋር ተጋርቷል።

√ ብሩኖ ፔትኮቪች ለክሮሽያ ሰባተኛ ጎሉን ሲያስቆጥር የዓለም ዋንጫው የመጀመሪያ ግቡ ሆኗል።

ክሮሽያ በግማሽ ፍፃሜው በቀጣዩ ማክሰኞ ከ #ኔዘርላንድ እና #አርጀንቲና አሸነፊ ጋር የምትጫወት ይሆናል።
ዛሬ በተደረጉት የጥሎ ማለፍ ጨዋታዎች ክሮሺያ እና አርጀንቲና ቀጣዩን ዙር መቀላቀላቸውን አረጋግጠዋል🔥

🔥 ነገ
12:00| 🇲🇦 ሞሮኮ ከ ፖርቹጋል  🇵🇹
04:00|🇫🇷 ፈረንሳይ ከ እንግሊዝ  🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿
🏆 የኳታር አለም ዋንጫ የሩብ ፍፃሜ ጨዋታ!

ጨዋታው ተጀመረ

🇵🇹 ፖርቱጋል 0-0 ሞሮኮ 🇲🇦
በድጋፍ ደሞ ሞሮካዊያን ደጋፊዎች ድጋፉን ተቆጣጥረውታል
ቀዝቀዝ ያለ ጨዋታ ነው
ሞሮኮ ደማቅ አዲስ ታሪክ ፅፋለች !

በአሰልጣኝ ዋሊድ ሬግራጉዊ የሚመራው የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በየሱፍ ኤል ነስሪ ብቸኛ ግብ ፖርቹጋልን በመርታት ግማሽ ፍፃሜውን ተቀላቅለዋል።

√ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በዓለም ዋንጫው ታሪክ ግማሽ ፍፃሜውን መቀላቀል የቻለች #የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

√ የሞሮኮ ብሔራዊ ቡድን በኳታሩ የዓለም ዋንጫ #በተጋጣሚ_ቡድን #ተጫዋች አንድም ግብ ከመረብ አላረፈባቸውም።

√ ክርስቲያኖ ሮናልዶ ለፖርቹጋል ብሔራዊ ቡድን 196 ጨዋታዎችን ማድረግ ችሏል።

√ የሱፍ ኤል ነስሪ በዓለም ዋንጫው ሶስት ጎሎችን ማስቆጠር የቻለ በታሪክ የመጀመሪያው #ሞሮካዊ ተጫዋች ሆኗል።
🏆 የአለም ዋንጫ ሩብ ፍፃሜ ጨዋታ

            Full-Time

🏴󠁧󠁢󠁥󠁮󠁧󠁿 ኢንግላንድ 1-2 ፈረንሳይ 🇫🇷
  #ሃሪ_ኬን 54'       #ቹአሜኒ 17'
                            #ጂሩድ 78'
ዓለም ዋንጫው የቱን ታሪክ ያሳየናል ?

የ 2022 የኳታሩ የዓለም ዋንጫ ሊጠናቀቅ የሳምንታት እድሜ ሲቀሩት ለዋንጫ ለማለፍ አራት ሀገራት ተፋጠው ይገኛሉ።

የዓለም ዋንጫው ፍፃሜ ከወዲሁ ታሪካዊ መሆኑ አይቀሬ ሲሆን ከአራት አዳዲስ ታሪኮች አንዱ እውን የሚሆን ይሆናል።

🇦🇷 አርጀንቲና :- የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ለሊዮኔል ሜሲ

🇭🇷 ክሮሽያ : - የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ ለሀገሪቱ

🇲🇦 ሞሮኮ :- #ለአፍሪካ በታሪክ የመጀመሪያ የዓለም ዋንጫ

🇫🇷 ፈረንሳይ :- የዓለም ሻምፒዮናነታቸውን ከስልሳ ዓመታት በኋላ ማስጠበቅ የቻሉ ሀገር መሆን ይችላሉ።

የትኛው ደማቅ ታሪክ እውን እንዲሆን ይመኛሉ ?
ክርቲያኖ ሮናልዶ በ ኢንስታግራም ገፁ🗣

ለፖርቹጋል የአለም ዋንጫን ማሸነፍ የህይወቴ ትልቁ እና ታላቅ ህልሜ ነበር። እንደ እድል ሆኖ ከፖርቹጋል ጋር ጨምሮ ብዙ የአለም አቀፍ ክብሮችን አሸንፌያለሁ ነገር ግን የሀገራችንን ስም በአለም ከፍተኛ ደረጃ ላይ ማስቀመጡ ትልቁ ህልሜ ነበር።

የታገልኩት ለእሱ ነው። ለዚህ ህልም በጣም ታግያለሁ።

እንደ አለመታደል ሆኖ ትናንት ሕልሙ አብቅቷል ። ትኩስ ምላሽ መስጠት ዋጋ የለውም ብዙ እንደተነገረ፣ ብዙ እንደተፃፈ፣ ብዙ እንደተገመተ ሁሉም እንዲያውቅልኝ እፈልጋለሁ ነገር ግን ለፖርቱጋል ያደረግኩት ቁርጠኝነት ለቅጽበት አልተለወጠም። እኔ ሁል ጊዜ ለሁሉንም ሰው ግብ ለመታገል አንድ ተጨማሪ ሰው ነበርኩ እና ለቡድን አጋሮቼ እና ለሀገሬ ጀርባዬን ፈጽሞ አልሰጥም።

ለአሁን ከዚህ በላይ ብዙ የሚባል ነገር የለም።
ዛሬ የሚደረጉ የኳታር አለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ የሚደረግ ጨዋታ

04:00 | ክሮሺያ ከ አርጀንቲና
ትላንት የተደረገ የኳታር አለም ዋንጫ ግማሽ ፍፃሜ ጨዋታ

🇫🇷 ፈረንሳይ 2-0 ሞሮኮ 🇲🇦
#ሄርናንደዝ 5'
#ኮሎ 79'
HTML Embed Code:
2024/06/03 11:38:58
Back to Top