TG Telegram Group Link
Channel: ✿✟ የ҈ ዳ҈ ዊ҈ ት҈ ዜ҈ ማ҈ ✟✿
Back to Bottom
እግዚአብሔር ❤️

ሲገድሉትም የዋህ ነው፣
ሳይገለጥ ይታወቃል፡፡
ሳይታወቅም ግልጥ ነው፡፡
ሲርቁት ይቀርባል፣
ሲጠሉት ይወድዳል፡፡
አጥሩ ነበልባል ነው ቤቱ ውኃ ነው


በነፋስ ክንፍ ይሄዳል፡፡

መላእክቱንም ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን አደረጋቸው፤

የሚያገልግሉትንም የእሳት ነበልባል አደረጋቸው፡፡
መሬትን የሚመለከታት፣ እንድትንቀጠቀጥ የሚያደርጋትም እርሱ ነው፡፡

ሲነካቸውም ተራሮች ይጤሳሉ።

ዓለም ሁሉ በፊቱ የተመዘነ ነው፡፡

ስለዚህም እርሱ ራሱን ሲገልጥ የእስራኤልን ቅዱስ እኔን በማን ትመስሉኛላችሁ?

ሰማይም እንደ ብረት ትጸናለች፤
መሬትም እንደ ልብስ ታረጃለች።

በውስጧ የሚኖሩትም ሁሉ እንደ አንበጣ ናቸው እንደ ዝናም ነጠብጣብም ናቸው። እንደምትሰበስብ የዓይን ሚዛንም ናቸው፡፡ የአንዱን ሚዛን ጉድለቱን የሚጨምር ትንሽ ሚዛንም ይህ ነው፡፡ በእርሱ ዘንድ የዚህ ዓለም ምሳሌ ሆነው ከተባለው ጋር እኩል ይሆን ዘንድ፡፡ ነቢዩም ይህን ተገንዝቦ «ሰውነቴ በአንተ ዘንድ እንደ ኢምንት ነው አለ፡፡

ስለገናናነቱ መልካምን ያደረገ የእርሱን ነገር ጠንቅቆ መናገር ፈጽሞ አይቻለንምና ዝም እንበል፣ ክብር፣ ቡራኬ፣ ምስጋና በፍጥረታቱ፣ በዓለማቱ ሁሉ ለአብ ለወልድ፣ ለመንፈስ ቅዱስ ይሁን፡፡ አሜን፡፡
👑 መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ  👑   ሰኔ 30

➡️ የዓለም ብርሃን ለሆነው ባሕታዊ ፤ በክብረ ፈጣሪው ለተከበበ ንዑድ ክቡር አባታችን ገባሬ ተአምራት ወመንክራት፤ ሴቶች ከወለዷቸው ቅዱሳን ወገን እሱን የሚበልጥ ማንም እንደሌለና እንደማይኖር አምላካችን በሕያው ቃሉ ለመሰከረለት እንቁ አገልጋይና ጽኑ የእውነት ሰማዕት ለሆነው፤ ክብሩ ማንነቱ ከኹሉ ለላቀው የክርስቶስ መንገድ ጠራጊ የአዲሱ የምህረት ዘመን መሸጋገሪያ ድልድይ፡ የአሮጌው ብሉይ ዘመን ፍጻሜ ማኅተም ለሆነው መምህር መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ዓመታዊ የልደት በዓል እንኳን አደረሳችሁ ! እንኳን አደረሳችሁ! እንኳን አደረሳችሁ ።

➡️ አባታችን መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ በሰማዕትነት ፍጻሜው ወቅት "አቤቱ ጌታዬ ሆይ በቃል ኪዳኔ አምነው ስሜን የሚጠሩ መታሰቢያየን የሚያደርጉ ኃጥአንን ሁሉ ማርልኝ!" ብሎ በትህትና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስን በለመነው መሠረት...

➡️ ጌታችንም በማይታበለው የከበረ ቃሉ፦ በስሙ የተማጸነ፤ ዝክሩን ያዘከረ፤ መታሰቢያውን ያደረገ፤ ስሙን የጠራ በቃልኪዳኑ የታመነ፤ ወዘተ... ወዳጆቹንም በወር በወር የበዓሉ መታሰቢያ ዕለት በውሃ ላይ ገድሉን አንብበው ቢጠመቁ ወር እስከ ወር የሰሩትን ኃጥአት ይቅር እንደሚላቸው...

➡️ ያም ባይሆን መስከረም 2፤ ሰኔ 30 በአመታዊ ክብረ በዓሉ ገድሉ በተነበበበት ማየ ጸሎት (ውሃ) አምኖ፣ ታምኖ፣ ተማጽኖ፣ በሠራው ኃጢአት አዝኖ ተጸጽቶ የተጠመቀ ማንም ይሁን ማን እንደ እግዚአብሔር ቸርነት ከዓመት እስከ ዓመት የፈጸመው ኃጢአቱ ቀልጦ ጠፍቶለት ያለወቀሳ ያለ ከሰሳ ሰተት ብሎ መንግሥተ ሰማያት እንዲገባ ይህንንና የመሳሰለውን ቃልኪዳን ከአምላኩ ተቀብሏል።

➡️ነገር ግን ይህ ሁሉ የሚሆነው በእምነትና በእውነት ሲጠቀሙበት ነውና እንደቃልኪዳኑ ኖረን በቃልኪዳኑ ለመጠቀም ያብቃን! አሜን። 🙏
.ሊንኩን በመጫን ይቀላቀሉን 👇
╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ 👆 ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
ቅዱስ ፓትርያርኩ ወደ አዲስ አበባ ተመለሱ።
---------------------------------------------------


ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት፣ ከብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳትና  ከሀገር ሽማግሌዎች  ጋር  በክልል ትግራይ መቐለ የነበራቸውን ቆይታ አጠናቀው ወደ አዲስ አበባ ተመልሷል ።

ምንጭ: ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽ/ቤት
" ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው " - ቅዱስ ፓትርያርኩ

ቅዱስ ፓትርያርኩ ፤ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን " ራስን በራስ የመሾም " አባዜ መገታት አለባቸው ሲሉ አሳሰቡ።

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ  ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለ ሃይማኖት ዛሬ በተካሄደው ሢመተ ኤጲስ ቆጶሳት ስርዓት ላይ ንግግር አሰምተው ነበር።

በንግግራቸው ላይም ፤ " በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ባልተጠበቀና ባልተለመደ ሁኔታ ብቅ ብቅ ሲሉ የሚታዩት ራስን በራስ የመሾም አባዜ መገታት አለባቸው " ብለዋል።

" ማንኛውም ችግር በውይይትና በምክክር የተበደለውንም በትክክል በመካስ መፈታት ይገባዋል! " ያሉት ቅዱስነታቸው " ከዚህ ውጭ በጥፋት ላይ ጥፋት እየተከሠተ የቤተ ክርስቲያንን ህልውና የሚፈታተን ድርጊት ማቆም አለብን " ሲሉ አሳስበዋል።

ቅዱስ ሲኖዶስ የቤተ ክርስቲያንን አንድነትና ቀኖና ለመጠበቅና ለማስጠበቅ ባደረገው ጥረት፣ እንደዚሁም ኦርቶዶክሳዊው ሕዝበ ክርስቲያን ባቀረበው አቤቱታ ከዚህ ቀደም የተፈጸመው የቀኖና ጥሰት ታርሞ በዛሬው ዕለት ትክክለኛውን ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንና ቀኖናዊ ሕግን የጠበቀ ሥርዓተ ሢመት መከናወኑን የገለፁት ቅዱስ ፓትርያርኩ ይህ በመሆኑ " ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን " ብለዋል።

" ለወደፊትም ለሀገርና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት በሚጠቅም ጉዳይ ሁሉ ፤ በዚህ ዓይነት በውይይትና በምክክር ብቻ እየፈታን ሕዝባችን በመንፈስና በልማት የሚያድግበትን ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር በጋራ እንድንሰራ ጥሪያችንን እያቀረብን መልእክታችንን በእግዚአብሔር ስም እናስተላልፋለን፡፡ " ሲሉ ገልጸዋል።

(የቅዱስ ፓትርያርኩ ሙሉ ንግግር ከላይ ተያይዟል)
💕#ሐምሌ_19_እንኳን_አደረሳችሁ💕

ሊቀ መላእክት ቅዱስ ገብርኤል ቅድስት ኢየሉጣንና ልጇን ቅዱስ ቂርቆስን ከሞት አደጋ እንደታደገበት... የሊቀ መላእክት የቅዱስ ገብርኤል
፣ ቅዱስ ቂርቆስና የእናቱ የቅድስት ኢየሉጣ ተራዳኢነት ጸሎት አይለየን።

╔═★══════════📄══╗
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
         @Zemaryan         
╚══📃══════════★═╝
         ʟɪɴᴋ 👆 ᴛᴀʙ . sʜᴀʀᴇ
HTML Embed Code:
2024/05/16 19:27:52
Back to Top