TG Telegram Group Link
Channel: ዘተዋሕዶ - zetewahedo
Back to Bottom
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
††† እንኳን ከዘመነ ክረምት ወደ ዘመነ መጸው አሸጋግሮ ለቅዱስ ዮናስ ነቢይ ዓመታዊ የዕረፍት በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ስንዱ #እመቤት #ቤተ_ክርስቲያን (ሃገራችን) ሁሉ ነገሯ በሥርዓት ነውና ዓመቱን በዘመናት ከፍላ ትጠቀማለች:: እሊሕም ዘመናት #መጸው (ጽጌ): #ሐጋይ (በጋ): #ጸደይ (በልግ) ና ክረምት ናቸው:: ዘመናቱ ወቅቶችን ከመለየትና ማሳወቅ ባሻገር የእኛ ሕይወትም ምሳሌዎች ናቸውና ልብ ልንላቸው ይገባል::

#ዘመነ_መጸው / #ወርኀ_ጽጌ/ #ጥቢ እየተባለም ይጠራል:: በዚህ ወቅት ምድር በአበባ የምታጌጥበት: ክረምት የተለፋበት አዝመራ የሚደርስበት በመሆኑ ደስ ያሰኛል:: በጊዜውም:-
1.የእመቤታችን የቅድስት #ድንግል_ማርያም ስደቷ ይታሠባል:: እርሷ ስለ እኛ:-
*የሕይወት እንጀራን ተሸክማ መራቧን::
*የሕይወት መጠጥን ይዛ መጠማቷን::
*የሕይወት ልብስን አዝላ መራቆቷን::
*ሙቀተ መንፈስ ቅዱስን የሚያድለውን ተሸክማ ብርድ መመታቷን እናስባለን::
*ዘመኑ የበረከት ነው::

2.በሌላ በኩል ጊዜው ወርኀ ትፍሥሕት (የደስታ ወቅት) ነው:: በክረምት የደከመ ዋጋውን አግኝቶ: በልቶ: ጠጥቶ ደስ ይለዋልና:: ያልሠራው ግን ከማዘን በቀር ሌላ እድል የለውም:: ይኼውም ምሳሌ ነው::

ዘመነ ክረምት የዚህ ዓለም ምሳሌ: ዘመነ መጸው ደግሞ የመንግስተ ሰማያት:: በዚህ ዓለም ምግባር ትሩፋትን የሠራ በወዲያኛው ዓለም ተድላን ሲያደርግ ሰነፎች ኃጥአን ግን እድል ፈንታቸው: ጽዋ ተርታቸው ከግብዞች ጋር የመሆኑ ምሳሌ ነው::

በወርኀ ትፍስሕት እንደ ሊቃውንቱ እንዲህ ብለን ልንጸልይ ይገባል::
"ድኅረ ኀለፈ ክረምት ወገብአ ዝናም: ዘአስተርአይከ እግዚኦ ጽጌያተ ገዳም:
አፈወ ሃይማኖት ነአልድ ወፍሬ ምግባር ጥዑም:
አትግሃነ ለስብሐቲከ ከመ ትጋሆሙ አዳም:
ለጽብስት ንሕብ ወነአስ ቃሕም::"

††† የዘመናት ባለቤት ዘመነ መጸውን #ወርኀ_ትፍስሕት ያድርግልን::

††† ቅዱስ ዮናስ ነቢይ †††

††† ዮናስ ማለት 'ርግብ: የዋህ' ማለት ሲሆን ከ12ቱ #ደቂቀ_ነቢያት አንዱ ነው:: በሰራፕታ ተወልዶ ያደገው ነቢዩ በልጅነቱ ታሞ ሙቶ ነበር:: ታላቁ ነቢይ #ኤልያስ ግን 7 ጊዜ ጸሎት አድርጐ ከሞት አስነስቶታል:: (1ነገ. 17:17) እናቱ የሰራፕታዋ መበለትም ደግ ሴት ነበረች::

ቅዱስ ዮናስ በእድሜው ከፍ ሲል የቅዱስ ኤልያስ ደቀ መዝሙር ሆነ:: የነ ኤልሳዕና አብድዩም ባልንጀራ ነበረ:: ነቢየ እግዚአብሔር ኤልያስ ካረገ በሁዋላ: ቅ.ል.ክርስቶስ በ800 ዓመት አካባቢ የነነዌ ሰዎች ኃጢአት ከመሥፈርቱ በማለፉ የእግዚአብሔር ቃል ወደ አማቴ ልጅ ወደ ዮናስ መጣ::

"ሒድና ለነነዌ ሰዎች ንስሃን ስበክላቸው" አለው:: ከነቢያት ወገን ከሙሴና ከዳዊት ቀጥሎ የዮናስን ያህል የዋህ (ገራገር) የለምና እንቢ አለ (ሰምቶ ዝም አለ):: #እግዚአብሔር እየደጋገመ ሲናገረው ግን "እንዲህ የሚዘበዝበኝ ከፊቱ ብቀመጥ አይደል!" ብሎ ወደ #ተርሴስ ኮበለለ::

ወገኖቼ አንድ ነገርን ልብ እንበል:: እንኩዋን ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ዮናስ እኛ ክፉዎችም ከጌታ ፊት መሸሸት እንደማይቻል ጠንቅቀን እናውቃለን:: ታዲያ ለምን ሸሸ ቢሉ:- ጥበበ እግዚአብሔር በውስጡ ስለ ነበረበት ነው::

ምክንያቱም ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ 3 ቀን እና ሌሊት ኖሮ: ሙስና (ጥፋት) ሳያገኘው መውጣቱ ለጌታ ትንሳኤ ጥላ (ምሳሌ) ነው:: ለዚህም ምስክሩ ራሱ ጌታችን ነው::
"ወበከመ ነበረ #ዮናስ ውስተ ከርሠ አንበሪ ሠሉሰ ዕለተ ወሠሉሰ ለያልየ: ከማሁ ይነብር ወልደ እጉዋለ እመ ሕያው ውስተ ልበ ምድር ሠሉሰ ዕለተ: ወሠሉሰ ለያልየ" እንዲል:: (ማቴ. 12:39)

ቅዱስ ዮናስ በገንዘቡ ዋጅቶ ወደ መርከብ በገባ ጊዜ ታላቅ ማዕበል ሆነ:: የእምነት ሰው ነውና እንዲያ እየተናወጡ እርሱ በእርጋታ ተኝቷል:: እነርሱ ግን ቀስቅሰው ቢጠይቁት (እጣ ወድቆበታልና) "የእኔ ጥፋት ስለ ሆነ ወደ ማዕበሉ ጣሉኝ" አላቸው::

እያዘኑ ቢጥሉት ታላቅ ጸጥታ ሆነ:: እነዚያ አሕዛብም እግዚአብሔርን በመስዋዕትና በስዕለት አከበሩ:: ዮናስ ግን በማዕበልና በአሣ አንበሪ ሆድ ውስጥ ለ3 ቀናት ጸለየ:: አሣ አንበሪው በ3ኛው ቀን ወደ ነነዌ ተፋው::

ቅዱሱም "እስከ ሠሉስ ዕለት ትትገፈታእ #ነነዌ ዐባይ ሃገር" እያለ ንስሃን ሰበከ:: የነነዌ ሰዎች ኃጢአታቸውን አምነው ቢጸጸቱ ከሰማይ ወርዶ ከደመና ደርሶ የነበረው የእሳት ማዕበል ተመልሶላቸዋል::

የነቢዩ ትንቢት ግን አልቀረምና ታላቋ ነነዌ ከ300 ዓመታት በሁዋላ ጠፍታለች:: ቅዱስ ዮናስ ግን በቀሪ ዘመኑ ፈጣሪውን እያገለገለ ኑሯል:: ጠቅላላ እድሜውም 170 ዓመት ነው::

††† አምላከ ቅዱስ ዮናስ እድሜ ለንስሃ: ዘመን ለፍስሃ አይንሳን:: ከበረከቱም ይክፈለን::

††† መስከረም 25 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ጸአተ ክረምት (የክረምት መውጫ)
2.ቅዱስ ዮናስ ነቢይ
3.ቅዱስ እንጦንዮስ
4.ቅድስት በርባራ
5.ሐዋርያት ዼጥሮስ ወዻውሎስ
6.ቅዱስ ዕፀ መስቀል

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ መርቆሬዎስ ሰማዕት
2.ቅድስት ቴክላ ሐዋርያዊት
3.ቅዱስ አበከረዙን ሰማዕት
4.ቅዱስ ዱማድዮስ ሶርያዊ
5.አቡነ አቢብ (አባ ቡላ)
6.ቅዱስ አባ አቡፋና ጻድቅ
7.ታላቁ አባ ቢጻርዮን ገዳማዊ

††† "ክፉና አመንዝራ ትውልድ ምልክት ይሻል:: ከነቢዩም ከዮናስ ምልክት በቀር ምልክት አይሰጠውም:: ዮናስ በአሣ አንበሪ ሆድ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት እንደ ነበረ: እንዲሁ የሰው ልጅ በምድር ልብ ሦስት ቀንና ሦስት ሌሊት ይኖራል:: የነነዌ ሰዎች በፍርድ ቀን ከዚህ ትውልድ ጋር ተነስተው ይፈርዱበታል:: በዮናስ ስብከት ንስሃ ገብተዋልና:: እነሆም ከዮናስ የሚበልጥ ከዚህ አለ::" †††
(ማቴ. 12:39)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
††† እንኳን ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እና ለቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††

††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† ተአምረ ማርያም †††

††† ተአምር ማለት "ድንቅ: ምልክት: ከተፈጥሮ ሥርዓት ውጪ የሆነ ክዋኔ: በሰብአዊ አቅም ሊሠራ የማይችል ተግባር (ድርጊት)" ነው:: ተአምራት ከባለቤቱ ከጌታችን ሲሆኑ የባሕርዩ ናቸው:: ከቅዱሳኑ ሲሆኑ ደግሞ የጸጋ እንላቸዋለን:: ቅዱስ መጽሐፍ ላይ በእግዚአብሔር ወዳጆች የተሠሩ ተአምራት እጅግ ብዙ ናቸው:: ነገር ግን:-
*ተአምራት ከአጋንንትም ሊሆኑ እንደሚችሉ መረዳት::
*ሁሌ ምልክትን (ተአምርን) አለመፈለግ::
*መመርመርና ማስተዋል ከአንድ ክርስቲያን ይጠበቃል::
*ቅዱስ ዮሐንስ አፈ ወርቅ በድርሳኑ እንደ ነገረን ተአምር መሥራት ከሲዖል እሳት አያድንም:: ጌታም በዚህ ነገር ተባብሮበታል:: (ማቴ. 7:22, 12:39)

ከጌታችን እግዚአብሔር ቀጥሎ የድንግል ማርያምን ያህል ተአምራትን የሠራ አይገኝም:: እንዲያው ሌላውን ትተን በእያንዳንዳችን ሕይወት ላይ እንኳ ብዙ ድንቅ ነገሮችን አድርጋለችና ምስክሮቹ እኛው ራሳችን ነን:: የእመቤታችን ተአምር የተጀመረው ገና ከፍጥረተ ዓለም ነው::

በእርግጥ ይህንን ለመረዳት ሠፊ አዕምሮና አስተዋይ ልቡናን ይጠይቃል:: ድንግል ማርያም ማለት የእግዚአብሔር የቸርነቱ ግምጃ ቤት: የጸጋው ደጅ ናት:: እርሱ ይህንን መርጦ ወዷልና:: እመ ብርሃን ተጸንሳ ከተወለደች በኋላ ደግሞ እጅግ ብዙ ኃይልን ታደርግ ነበር:: በዚህ ዕለት ከ2007 ዓመታት በፊት ያደረገችው ተአምር ደግሞ ድንቅ ነው::

አጐቷ /ጠባቂዋ/ አገልጋዩዋ አረጋዊ ቅዱስ ዮሴፍ ከቤተ መቅደስ ተቀብሎ ካመጣት በኋላ እርሱ እንጨትን ይጠርብ ነበር:: ዘመኑ ዘመነ ዐጸባ (የችግር ዘመን) በመሆኑ ለሥራ ጉዳይ ወደ ሩቅ ሃገር ሒዶ የተመለሰው ከወራት በኋላ ነው::

ዮሐንስ የሚሉት ፈላስፋ ባልንጀራ ነበረውና ሽማግሌው ዮሴፍ ልብ ያላለውን ነገር ነገረው:: "ይህች ብላቴና ጸንሳለችና መርምራት" ብሎ ሔደ:: ቅዱስ ዮሴፍ ግን ደነገጠ:: "እኔ እንዲህ ያለ ነገር እንኳን በገቢር (በሥራ) በሃሳብም አላውቅባት" ብሎት ወደ ቤት ገባ::

ቀጥሎም እመቤታችንን "ልጄ ሆይ! ከማን ጸነስሽ" አላት:: "እመንፈስ ቅዱስ" አለችው:: ግራ ገባው: ምሥጢርም ተሠወረበት:: "እንዴት አንዲት ሴት ያለ ወንድ ዘር ልትጸንስ ትችላለች?" ብሎ ያወጣ: ያወርድ: ይጨነቅም ገባ:: የእኛ እመቤት ግን እንደ ጨነቀው ባወቀች ጊዜ ጠርታ ወደ ውጪ ይዛው ወጣች::

ከረዥም ጊዜ በፊት ጠርቦ የጣለውን እንጨት አንስታ ተከለችውና ጸለየችበት:: በደቂቃም የአረጋዊው ዐይን እያየ ያ ደረቅ እንጨት ለምልሞ: አብቦ አፈራ:: ቅዱስ ዮሴፍ በጣም ደነገጠ::

"አባቴ ተመልከት እስኪ! ይህንን ማን አደረገ?" አለችው:: "ልጄና እመቤቴ! እግዚአብሔር ነው" አላት:: እርሷም "በማሕጸኔ ያለውም ኢሳይያስ ትንቢትን የተናገረለት አምላክ ነውና ሁሉን ይችላል" አለችው:: አረጋዊውም ቅዱስ ኤራቅሊስ በሃይማኖተ አበው እንደ ነገረን "ሰገደ ላቲ" ወደ ምድር ወድቆ በፊቷ ሰገደ::

††† ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ †††

††† ቅዱስ ወንጌል ላይ ከእመቤታችን ቀጥሎ የዘካርያስን ቤተሰብ ያህል ክብሩ የተገለጠለት ፍጡር ይኖራል ብሎ መናገሩ ይከብዳል:: ቅዱስ ሉቃስ የጀመረው በዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነውና መንፈስ ቅዱስ እንዲህ ሲል አጽፎታል:: "ዘካርያስ ካህኑና ቅድስት ኤልሳቤጥ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ የሚኖሩ ጻድቃን ነበሩ" ይላቸዋል:: (ሉቃ. 1:6)

የሰውን እንተወውና በእግዚአብሔር ፊት ያለ ነቀፋ መኖር ምን ይረቅ? ለዚህ አንክሮ (አድናቆት) ይገባል! እሊህ ቅዱሳን ባልና ሚስት ግን መካኖች በመሆናቸው ልጅ ሳይወልዱ ዘመናቸው አልፎ ነበር::

እንደ ቤተ ክርስቲያን ትውፊት ዕድሜአቸው የኤልሳቤጥ 90 የዘካርያስ ደግሞ 100 ደርሶ ነበር:: ፍጹም መታገሳቸውን የተመለከተ ጌታ ግን በስተ እርጅናቸው ከሰው ሁሉ በላይ የሆነ: ትንቢት ለብቻው የተነገረለት (ኢሳ. 40:3, ሚል. 3:1) ታላቅ ነቢይን ይሰጣቸው ዘንድ መልአከ ብሥራት ቅዱስ ገብርኤልን ላከላቸው::

ቅዱስ ዘካርያስ ሰው ነውና ከደስታ ብዛት በመከራከሩ ድዳ ሆነ:: ቅድስቲቷ ግን መስከረም 26 ቀን ታላቁን ሰው ጸንሳ ለ6 ወራት ራሷን ሠወረች:: በ6ኛው ወር የፍጥረት ሁሉ ጌታ በተጸነሰ ጊዜ የአርያም ንግሥት ድንግል እመቤታችን ደጋ ደጋውን ወደ ኤልሳቤጥ መጣች:: ሁለቱ ቅዱሳት የእህትማማች ልጆች ናቸው::

የአምላክ እናቱ ስትደርስና "ሰላም" ስትላቸው መንፈስ ቅዱስ በእናትና ልጅ ወርዶ ኤልሳቤጥ በምስጋና: ዮሐንስ ደግሞ ገና በማሕጸን ሳለ በደስታ ዘለለ (ሰገደ):: ከዚህ በኋላ ሰኔ 30 ተወልዶ: አባቱ ዘካርያስ "ዮሐንስ" ሲለው አንደበቱ ተፈትቶለታል::

††† የእመቤታችን ልመናዋ: ክብሯ: የልጇ የወዳጇም ቸርነት በእውነት ከሁላችን ጋር ይሁን:: የመጥምቁንም በረከት ያብዛልን::

††† መስከረም 26 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ድንግል ማርያም
2.ቅዱስ ዮሴፍ አረጋዊ
3.ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ (ጽንሰቱ)
4.ቅዱሳን ዘካርያስና ኤልሳቤጥ
5.ቅዱስ አቦሊ ሰማዕት (ፍልሠቱ)

††† ወርሐዊ በዓላት
1.ቅዱስ ቶማስ ሐዋርያ
2.አቡነ ሐብተ ማርያም ጻድቅ
3.አቡነ ኢየሱስ ሞዐ ዘሐይቅ
4.ቅዱሳን ሰማዕታተ ናግራን
5.ቅዱስ አቡነ ሰላማ ከሣቴ ብርሃን

††† "ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ጽንሱ በማሕጸኗ ውስጥ ዘለለ:: በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት:: በታላቅ ድምጽም ጮኻ እንዲህ አለች:-
'አንቺ ከሴቶች መካከል የተባረክሽ ነሽ: የማሕጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው:: የጌታየ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል? . . . ከጌታ የተነገረላት ቃል ይፈጸማልና ያመነች ብጽዕት ናት::" †††
(ሉቃ. ፩፥፵፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††

††† መስከረም 28 †††

††† ቅዱሳን አባዲርና እህቱ ኢራኢ †††

††† በ3ኛው መቶ ክ/ዘመን የሮም መንግስት ዓለምን የሚያስተዳድረው በሁለት ከተሞች: ማለትም በራሷ በሮምና በአንጾኪያ ነበር:: የወቅቱ ንጉሥ ኑማርያኖስ ሲሆን የቤተ መንግስቱ ልዑላንና የጦር አለቆች ቅዱሳኑ:- ፋሲለደስ: ገላውዴዎስ: ፊቅጦር: መቃርስ: አባዲር: ቴዎድሮስ (ሦስቱም): አውሳብዮስ: ዮስጦስ: አቦሊ: ሌሎቹም ነበሩ::

ሴቶቹ ደግሞ ቅዱሳቱ:- ማርታ: ሶፍያ: ኢራኢ: ታኡክልያ: ሌሎቹም ነበሩ:: ለእነዚህ ሁሉ የበላይ ደግሞ ቅዱስ ፋሲለደስ ነበር:: ወቅቱ ከፋርስ: ከቁዝና ከበርበር ጦርነት የሚበዛበት ነበርና ባጋጣሚ ንጉሡ ኑማርያኖስ በሰልፍ መካከል ተመትቶ ወደቀ / ሞተ::

የሮም መንግስትም ባዶ ሆነች:: ዙፋኑን መያዝ ለቅዱስ ፋሲለደስም ሆነ ለሌሎቹ ቅዱሳን ቀላል ነበር:: ግን እነሱ ዝም ብለው ጠላትን ለመዋጋት ወጡ::

በዘመኑ ደግሞ በግብጽ የፍየል እረኛ የነበረና ከልጅነቱ ሰይጣን የሚያናግረው አንድ አግሪዻዳ የሚሉት ጉልበተኛ ሰው ነበር:: ንጉሡ ከወለዳቸው ልጆች ሁለቱ ሴቶች ክፉዎች ነበሩና ትንሿ አግሪዻዳን ማንም በሌለበት አንግሣ ጠበቀቻቸው:: ስሙንም ዲዮቅልጢያኖስ አለችው::

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ከሰይጣን ቀጥሎ እንደዚህ የከፋ ስም የለም:: የዓለም ክርስቲያኖችን የጨፈጨፈ ሰው ነው:: ትልቋ ደግሞ የትንሿን አይታ መክስምያኖስ የሚባል አውሬ አግብታ አነገሠችው:: ዓለምም በእነዚህ ጨካኝ ሰዎች እጅ ወደቀች::

ሠራዊቱ ሁሉ በሚሊየን ይቆጠራሉ:: የተደረገውን ሲያዩ ተበሳጩ:: ይህንን የተመለከተው ቅዱሱ ፋሲለደስ ግን ልዑላኑንና አለቆችን ሰብስቦ:- "ይህ ዓለም ከነ ክብሩ ጠፊ ነው:: ስለዚህ የተሻለውን የክርስቶስን መንግስት እንምረጥ" አላቸው:: ሁሉም እንደ አንድ ልብ መካሪ ደስ ተሰኝተው ምድራዊ ክብራቸውን ሊተው ወሰኑ::

ቀጥለውም በአንድ ቤት ተሰብስበው ይጾሙ: ይጸልዩ ገቡ:: ወደ ውጪ የሚወጡት ለምጽዋት ብቻ ነበር:: ቅዱሳኑ አባዲርና ኢራኢም ከእነዚህ መካከል በመሆናቸው ተጋድሏቸውን ቀጠሉ:: በተለይ ቅዱስ አባዲር በሌሊት በመካነ ጸሎቱ ሲጸልይ ያድርና በቀን ነዳያንን ይጐበኛል::

አመሻሽ ላይ ደግሞ ልብሱን ለውጦ ወደ እሥር ቤት ይሔዳል:: እሱ የአንጾኪያ ሠራዊት አለቃ: ኃያል የጦር መሪ ነውና ሁሉ ይወደውና ያከብረው ነበር:: በዚህም ምክንያት የእሥር ቤት ዘበኞች ምንም ከዲዮቅልጢያኖስ ከባድ ትዕዛዝ ቢኖርባቸውም ለቅዱሱ ግን ይከፍቱለት ነበር::

እርሱም ወደ እሥር ቤት ገብቶ ቁስላቸውን ጠርጐ: እግራቸውን አጥቦ: ለረሃባቸው መደገፊያ የሚሆን ማዕድም አጉርሷቸው ይወጣ ነበር:: በእንዲህ ያለ ግብር ሳለ ስለ ክርስቶስ የሚሰዋበት ጊዜ ደረሰ::

አንድ ቀን በመካነ ጸሎቱ ለምስጋና ሲተጋ ክብር ይግባውና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ተገለጠለት:: "ስምህን ለዘለዓለም አከብረዋለሁ:: በሰማያዊት ርስቴም አነግሥሃለሁና ከእህትህ ኢራኢ ጋር ወደ ምድረ ግብጽ ወርዳችሁ መስክሩ" ብሎት: ለእሷም በተመሳሳይ "ወንድምሽ የሚያዝሽን ሥሪ" ብሏት መድኃኒታችን ዐረገ::

ከዚያች ቀን ጀምሮ ቅዱስ አባዲርና እህቱ ኢራኢ ወደ ግብጽ የሚወርዱበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር:: እናታቸው ግን (የቅዱስ ፋሲለደስ እህት ናት) ነገሩን ስትሰማ አለቀሰችባቸው:: "ልጆቼ አትሙቱብኝ: ዲዮቅልጢያኖስንም አትናገሩት" ስትል አማለቻቸው::

ከጥቂት ቀናት በኋላም ቅዱሱ ከእህቱ ጋር ከሶርያ ጠፍቶ ግብጽ ገቡ:: በዚያ ግን ፈተና ገጠመው:: በየመንገዱ የሚያየው ሕዝቡና ሠራዊት ሁሉ "ጌታችን አባዲር" እያለ ይሰግድለት ገባ:: ቀደም ሲል እንዳልነው እርሱ ኃያል የጦር መሪ: የሠራዊቱም አለቃ ነውና::

ቅዱሱ ግን ወደ ክርስቶስ ሊሔድ ናፍቋልና ሠራዊቱን እና ሕዝቡን:- "የሚገርማችሁ ሁሉም ሰው እንዲህ ይለኛል:: ግን'ኮ እኔ አንድ ተራ ምስኪን ክርስቲያን እንጂ የምትሉት ሰው አይደለሁም" ብሎ አታለላቸው::

ቀጥሎ በክርስትናው ተከሶ ከእህቱ ጋር ለፍርድ ቀረበና ስቃይ ታዘዘባቸው:: ለሰው ዐይን የሚከብዱ ብዙ ስቃዮችን ካሳለፉ በኋላም ሞት ተፈረደባቸው:: ነገር ግን አንገታቸው ከመሰየፉ በፊት መኮንኑ አርያኖስ ትክ ብሎ ሲያየው ተጠራጥሮ "ማንነትህን እንድትነግረኝ በአምላክህ አምየሃለሁ" አለው::

ቅዱስ አባዲርም መልሶ "አንተም ማንነቴን ካወቅክ በኋላ እኔን መግደል እንዳትተው ማልልኝ" አለው:: ማለለትም "እኔ አባዲር ነኝ" አለው:: በዚያች ቅጽበት አርያኖስ ከመደንገጡ የተነሳ መሬት ጠበበችው:: በፊቱ ተደፍቶ "ወዮልኝ! ጌታየን አባዲርን ያሰቃየሁ" እያለ አለቀሰ:: ነገር ግን ምሏልና በ300 ዓ/ም አካባቢ እያዘነ በዚህች ቀን ቅዱስ አባዲርንና እህቱን ኢራኢን አሰይፏቸዋል::

††† ቅድስት ሶስና †††

††† ይህች እናት የነበረችው ቅ.ል.ክርስቶስ በ500 ዓመት አካባቢ ነው:: እሥራኤላውያን በናቡከደነጾር ተማርከው ፋርስ ባቢሎን ወርደው ሳሉ: የኬልቅዩስ ልጅ: የደጉ ኢዮአቄም ሚስት የሆነች እናት ናት::

ቅድስት ሶስና በስደት ሃገር እግዚአብሔርን የምታመልክ: ለባሏ የምትታመን: ለቤተሰቦቿም ኩራት የሆነች ወጣት: በዚያውም ላይ እጅግ የምታምር ነበረች:: በዘመኑ ሕግን እናውቃለን የሚሉ 2 ረበናት ግን ከቅድስናዋ ሊያጐድሏት ይሹ ነበርና: አልሳካላችሁ ቢላቸው በሃሰት ከሰው በወገኖቿ ፊት ሞትን አስፈረዱባት::

በፍርድ ፊት ቁማ ሳለ እርሷ በፍጹም እንባ ወደ ፈጣሪዋ ትጸልይ ነበርና እግዚአብሔር ፍርዱን ላከ:: ሊገድሏት ሲወስዷት የኋላው ነቢዩ ቅዱስ ዳንኤል ያን ጊዜ ብላቴና ነበርና "እኔ ከዚህች የተባረከች ሴት ደም ንጹሕ ነኝ" ሲል ጮኸ::

ይህንን የሰሙ ዳኞችም የፍርድ ዙፋኑን ለቀቁለት:: ሁለቱን ረበናት ለየብቻቸው አድርጐ ዝሙትን ስትሠራ በየት ቦታ ላይ እንዳዩዋት ጠየቃቸው:: ጌታ ሲፈርድባቸው አንዱ በኮክ: ሌላኛው በሮማን ዛፍ ሥር አለ:: በዚህ ጊዜ ሕዝቡ እነዚህን ሃሰተኛ ረበናት (መምሕራን) ስለ እርሷ ፈንታ ወግረው ገደሏቸው:: ቅድስት ሶስና ግን ባለ ዘመኗ ሁሉ ፈጣሪዋን አገልግላ በዚህች ቀን ዐርፋለች::

††† አምላከ ቅዱሳን ከክፉ ሰዎች ምክር: ከአጋንንትም ሴራ በቸርነቱ ይጠብቀን:: የወዳጆቹንም ጸጋ ክብራቸውን ያድለን::

††† መስከረም 28 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅዱስ አባዲር ሰማዕት
2.ቅድስት ኢራኢ እህቱ
3.ቅድስት ሶስና እናታችን
4.ቅዱስ ሉቃስ መነኮስ
5.ቅዱስ ዻውፍርና

††† "ሶስናም ቃሏን አሰምታ ጮኸች:- 'ዘላለም ጸንተህ የምትኖር: የተሠወረውን የምታውቅ: የሚደረገውን ሁሉ ሳይደረግ የምታውቅ ፈጣሪ ሆይ! በሐሰት እንደ ጣሉኝ አንተታውቃለህ:: እነዚህ መመሕራንም ክፉ ነገርን ባደረጉብኝ ገንዘብ: የሠራሁት ኃጢአት ሳይኖር እነሆ እሞታለሁ' አለች:: እግዚአብሔርም ቃሏን ሰማት::" †††
(ሶስና. ፩፥፵፩)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
✞✞✞ እንኳን ለድንግልና ሰማዕት አርሴማ ቅድስት ወዮሐንስ ወንጌላዊ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ✞✞✞

✞✞✞ በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! ✞✞✞

✞✞✞ ቅድስት አርሴማ ድንግል ✞✞✞

✞✞✞ እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው:: መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል::
¤ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት::
¤ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት::
¤ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት::
¤ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት::
¤ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት::
ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ:-
አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ከሆነ ቅዱሱ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው:: በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት:-
1.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት::
2.ትምሕርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት::
3.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት::

ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ:: ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት:: መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ: ይጾሙ: ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር::

ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው:: በኋላ ግን ማሕደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ 127 ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ::

በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ: ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው:: የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ::

በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ:: በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር:: መከራው ግን አለቀቃቸውም:: ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከው::

ድርጣድስ ግን ቅድስት አርሴማን ባያት ጊዜ ከውበቷ የተነሳ መታገስ ባለመቻሉ "ካላገባሁሽ" አላት:: ድንግሊቱ ግን "እኔ የክርስቶስ ሙሽራ ነኝ: አይሆንም" አለችው:: ሊያስፈራራት ሞከረ:: ዐይኗ እያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው::

አልሳካልህ ቢለው በአደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞክር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው:: እጅግ ስላፈረ አስገረፋት: አሰቃያት: ዐይኗንም አወጣ:: በመጨረሻም አንገቷን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት::

ከነገር ሁሉ በኋላ ድርጣድስና ባለሟሎቹ ለአደን በሔዱበት ርኩስ መንፈስ ወደ አውሬነት (እሪያነት) ቀየራቸው::

የንጉሡ እንስሳ (አውሬ) መሆን በአርማንያ ታላቅ ድንጋጤን ፈጠረ:: የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ "ለእመ ኢያዕረግምዎ ለጐርጐርዮስ አልብክሙ ድኂን - ጐርጐርዮስን ከተቀበረበት ካላወጣችሁት አትድኑም" አላቸው:: ወዲያውም ቆፍረው አወጡት::

ቅዱሱ እንደ ወጣ ዕረፍትን አልፈለገም:: ለ15 ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማንና የሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው:: ድርጣድስና ባለሟሎቹንም ወደ በርሃ ሒዶ ፈወሳቸው::

የሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ አጽም በ14ኛው መቶ ክ/ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ወደ ሃገራችን እንደ መጣ አባቶቻችን በትውፊት ነግረውናል:: ለዚህም ይመስላል ቡርክቷ እናታችን ከሌሎች ሃገራት ለይታ ለኢትዮዽያውያን ልዩ ፍቅር ያላት:: በዋናው ገዳሟ (ወሎ / ኩላማሶ / ስባ / ውስጥ የሚገኝ ነው) ጨምሮ ስሟ በተጠራበት ሁሉ ኃይልን ታደርጋለችና::

ነገር ግን ወንድሞቼና እሕቶቼ በቅድስቷ እናታችን ስም የሚነግዱ ሥጋውያን ሰዎች በዝተዋልና እንጠንቀቅ:: የሰማዕቷ ክብር ብዙ ነውና በሕልም ላይ ብቻ አንታመን:: አባ እንጦንስ እንዳሉት "በሕልሙ የሚታመን ሰው ከንቱ ነውና::"

በዚህ ዕለት ከሰማዕቷ ጋር የመንፈስ እናቷን ቅድስት አጋታን ልናስባት ይገባናል:: ይህች እናት እመ-ምኔት ስትሆን ቅድስት አርሴማን ታስተምራት: ታጸናት: ከጐኗም ትቆምላት ነበር:: ረሃቧን: ጥሟን: ስደቷን: መከራዋንም ሁሉ አብራት ተሳትፋለች:: በፍጻሜውም አብራት ተሰይፋለች::

✞✞✞ ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ ✞✞✞

*የቤተ ክርስቲያን ምሰሶ
*ምድራዊው መልአክ
*የጌታ ወዳጅ
*የድንግል ማርያም የአደራ ልጅ
*የንጽሕና አባት
*ቁጹረ ገጽ
*የፍቅር ሐዋርያ
*የምሥጢር አዳራሽ
*የሐዋርያት ሞገሳቸው
*ነባቤ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ ዛሬ ይከብራል::

ምክንያቱም "ቀዳሚሁ ቃል" (ዮሐ. 1:1) ብሎ እንደ ንስር መጥቆ ወንጌሉን በዚህች ቀን ጽፏልና::

✞✞✞ አምላከ ቅዱሳን ለኛ ለባሮቹ የቅድስቷን ጽናት: የወንጌላዊውንም ፍቅር ያድለን:: በረከታቸውን ከማይጐድል እጁ አብዝቶ ይስጠን::

✞✞✞ መስከረም 29 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት አርሴማ ድንግል (ሰማዕት)
2.ቅድስት አጋታ (እመ ምኔት)
3."119" ሰማዕታት (የቅድስት አርሴማ ማሕበር)
4.ቅዱስ ዮሐንስ ወንጌላዊ (ነባቤ መለኮት)
5.ቅድስት ክርስቶስ ክብራ ኢትዮዽያዊት (በዚህ ቀን ነፍሳትን ከሲዖል ታወጣለች)

✞✞✞ ወርኀዊ በዓላት
1.የፈጣሪያችንና ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ልደት
2.ቅዱስ ዼጥሮስ ተፍጻሜተ ሰማዕት
3.ቅዱስ ማርቆስ ዘቶርማቅ
4.ቅድስት ፍቅርተ ክርስቶስ ኢትዮዽያዊት
5.ቅዱስ ዘርዐ ክርስቶስ (ጻድቅና ሰማዕት)

✞✞✞ "በመጀመሪያ ቃል ነበረ:: ቃልም በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ቃልም እግዚአብሔር ነበረ :: ይህ በመጀመሪያው በእግዚአብሔር ዘንድ ነበረ:: ሁሉ በእርሱ ሆነ:: ከሆነውም አንዳች ስንኳ ያለ እርሱ አልሆነም:: በእርሱ ሕይወት ነበረች:: ሕይወትም የሰው ብርሃን ነበረች:: ብርሃንም በጨለማ ይበራል:: ጨለማም አላሸነፈውም::" ✞✞✞
(ዮሐ. ፩፥፩)
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
"የኛ መጽሀፍ እናንተ ናችሁ ፦በመጋቤ ሐዲስ ወቡሉይ ቆሞስ አባ ገብረ ኪዳን ፦የሰማእትነት ዋጋ የቅድሰት አርሴማ" on YouTube
https://youtu.be/dEMeoNrS-Ng
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን። †††

††† ጥቅምት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት †††

+" ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ "+

††† ሰማዕቱ የተወለደው በምድረ ግብጽ አሕዛብ (ተንባላት) በሰለጠኑበት የመጀመሪያው ዘመን ነበር:: በተለይ ተንባላቱ ግብፅና ሶርያን ከያዙ በኋላ ባልተጠበቀ ፍጥነት በኃይልም በሰውም ተደራጅተው ነበር:: ቅዱስ ጊዮርጊስ (ልብ በሉልኝ ሊቀ ሰማዕታት አይደለም) የተወለደው በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ነበር::

+እናቱ የተመሠከረላት ክርስቲያን ብትሆንም እንዳለመታደል አባቱ ተንባላታዊ (አሕዛብ) ነበር:: ስሙንም መዛሕዝም ይሉታል:: ሕጻኑ እንደተወለደ ያወጡለት ስም አሕዛባዊ ከመሆኑ ባለፈ በሰዓቱ መጠመቅ አልቻለም:: የወቅቱ ሕግ ከወላጆቹ አንዱ አሕዛባዊ ከሆነና አጠምቃለሁ ቢባል የሚከተለው ሰይፍ ነበር:: በዚሕ ምክንያት ሳይጠመቅ 7 ዓመት ሞላው::

+እናቱ ግን ሕጻን ቢሆንም ፍቅረ ክርስትናን ታስተምረው ነበር:: ባይጠመቅም ጸበሉን: እመነቱን ትቀባው ነበር:: ደብቃ ቅዳሴ ታሰማውም ነበር:: አንድ ቀን ግን ሕጻናት ሲቆርቡ አይቶ ካልቆረብኩ ብሎ አለቀሰ:: ምን ታድርገው? ወደ ውጪ አውጥታ ከአውሎግያ (የሰንበት በረከት) አበላችው:: "ጌታየ! ልጄን እርዳው" አለች::

+ልክ በአፉ ሲቀምሳት መዓዛ መንፈስ ቅዱስ አደረበትና ፍጹም ተደሰተ:: ትንሽ ከፍ ሲል ለምን እንደማይጠመቅና እንደማይቆርብ እናቱን ጠየቃት:: "ልጄ ሆይ! ይገድሉሃል" አለችው::
ከዚህች ቀን ጀምሮ የሚጠመቅበትን ዘዴ ይፈልግ ጀመር::

+አስቀድሞ ትምሕርተ ክርስትናን ተማረ:: ለአካለ መጠን ሲደርስ አፈላልጐ ጠንካራ ክርስቲያን የሆነች ሴት አገባ:: ጥቂት ጊዜ ከቆየ በኋላ ሚስቱን ስለ መጠመቅ አማከራት:: "ሌላ ሃገር ሒደህ ተጠመቅ" አለችው:: ከግብፅ ተነስቶ ሶርያ ገባ::
አባቶችን አፈላልጎ ተጠመቀ:: ቀጥሎም መንገዱን ወደ ልዳ አደረገ::

+ወደ ደብሩ ተጠግቶ አባቶችን "ስም አውጡልኝ" ቢላቸው መንፈስ ቅዱስ አናግሯቸው "ጊዮርጊስ" አሉት:: እሱም ደስ እያለው: ባጭር ታጥቆ የልዳውን ቅዱስ ጊዮርጊስ ያገለግለው ገባ:: ትንሽ ቆይቶ ሁከት መንፈሳዊ ተሰማው:: ማለትም ስለ ሃይማኖቱ ደሙን ማፍሰስ ፈለገና ወደ ግብፅ ተመለሰ::

+በዚያ ያሉ አሕዛብ በክርስትና ስም: ልብስና ሞገስ ሲመለከቱት ተበሳጩ:: ዕለቱኑ አሠሩት:: ሌሊት እናቱና ሚስቱ መጥተው አሉት:- "አደራ! ፍቅረ ዓለም እንዳያታልልህ:: ሰማዕት ብትሆን ላንተም ክብር: ለእኛም ሞገስ ነው" ብለውም አጽናኑት:: እንዲህ ያሉ እናትና ሚስት ማግኘትም ታላቅ እድል ነው::

+ሐዲስ ጊዮርጊስም ጸና:: ከዚያች ቀን ጀምሮ ለተከታታይ ቀናት ደበደቡት: አካሉን ቆራረጡት: ደሙንም መሬት ላይ አንጠፈጠፉት:: በየመንገዱ እየጎተቱ ተሳለቁበት:: እርሱ ግን ክርስቶስን ወዷልና ሁሉን ታገሰ:: ሌሊት በሆነ ጊዜም ጌታችን ተገልጦ "ከሰማዕታት ተቆጠርህ" አለው::

+በማግስቱ በአደባባይ አንገቱን በሰይፍ ቆረጡት:: ክፋታቸው የጸና ነውና ሥጋውን በእሳት አቃጠሉት:: ወደ ባሕርም ጣሉት:: እናቱ ከባሕር ስታወጣው ግን ምንም አላገኘውም ነበር:: በዚሕች ቀን እናቱና ሚስቱ በክብር ቀብረውታል::

+" አባ ስምዖን ሊቀ ዻዻሳት "+

+በምድረ ግብጽ ተነስተው: በማርቆስ ወንጌላዊ መንበር ላይ ይቀመጡ ዘንድ ከተገባቸው ሊቃነ ዻዻሳት አንዱ እኒህ አባት ናቸው:: ከልጅነታቸው መንነው ብዙ ዘመናትን በተጋድሎ በማሳለፋቸው ሥጋዊ አካላቸው ደካማ ሆኖ ነበር::

+ከገዳማዊ አገልግሎታቸው ቀጥሎም ከእርሳቸው በፊት ለነበሩ ሁለት ፓትሪያርኮች ረዳት ሆነው አገልግለዋል:: በዚህ ጊዜም ለመንጋው የሚሆኑ ተግባራትን ከመፈጸማቸው ባሻገር በጾምና በጸሎት መጋደልን አልተዉም ነበር::

+ጊዜው ደርሶ በእግዚአብሔር ፈቃድ: በሕዝቡና ዻዻሳቱ ምርጫ: የእስክንድርያ 51ኛ ፓትርያርክ ሲሆኑ እርሳቸው እንደ ሌሎቹ አበው 'አልፈልግም' ብለው ነበር::

+ቀደም ሲል እንዳልነው አካላቸው በተጋድሎ የተቀጠቀጠ ነበርና በመንበራቸው ላይ ለብዙ ጊዜ መቆየት አልቻሉም::እግራቸውን በጠና በመታመማቸው ፈጣሪ ነፍሳቸውን እንዲቀበል ለመኑት: እርሱም ሰማቸው:: ሊቀ ዻዻሳት ሆነው በተሾሙ በ165ኛው ቀን (ማለትም በ5 ወር ከ15 ቀናቸው) በክብር ዐርፈው ተቀብረዋል::

††† ቸሩ አምላክ ከሰማዕቱ ጽናትን: ትእግስትን: ጸጋ በረከትን ይክፈለን::

††† ጥቅምት 3 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሐዲስ (ሰማዕት)
2.አባ ስምዖን ሊቀ ዻዻሳት
3.ቅዱስ ጐርጐርዮስ ዘአርማንያ
4.ቅድስት ታኦድራ ልዕልት
5.ቅድስት ታኦፊላ

††† " ስለዚሕ ወንድሞቼ ሆይ ጣዖትን ከማምለክ ሽሹ:: ልባሞች እንደመሆናችሁ እላለሁ:: በምለው ነገር እናንተ ፍረዱ:: የምንባርከው የበረከት ጽዋ ከክርስቶስ ደም ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን? የምንቆርሰውስ እንጀራ ከክርስቶስ ሥጋ ጋር ኅብረት ያለው አይደለምን?... እኛ ብዙዎች ስንሆን አንድ ሥጋ ነን:: ሁላችን ያን አንዱን እንጀራ እንካፈላለንና:: "††† (1ቆሮ. 10:14-18)

††† ወስብሐት ለእግዚአብሔር †††
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
Forwarded from ዝክረ ቅዱሳን zikre kidusan (ɴᴀᴛɴᴀᴇʟ)
አዲስ መንፈሳዊ መጽሐፍ ከዚያውም "ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያን" "ኅብረ ሥርዐት ዘቤተ ክርስቲያን ኦርቶዶክሳዊት" በሚል ርእስ በኅትመት ላይ መሆኑን ስናበሥረዎ በደስታ ነው። በቅርቡ ገበያ ላይ ይውላል። አዲስ አበባ፣ጎንደር፣ ባሕር ዳር..... ይሰራጫል። በመጽሐፉ ውስጥ ሥርዐተ ቤተ ክርስቲያንን በማብራሪያ ይማራሉ። አመክንዮአዊ ሐሳቦችን በአበው መንፈሳዊ አተያይ ይረዳሉ።በዘመናዊው ወጣት ዘንድ የሚነሡ ልዩ ልዩ ጥያቄዎችን በመ/ቅዱስ፣በፍትሐ ነገሥት እና በሌሎች የአበውን ትምህርት በያዙ የግእዝ መጻሕፍት ምስክርነት ለራስዎም ለሌላውም ይህን መጽሐፍ አንብበው ይመልሳሉ። ያንብቡ ይማሩ ይወቁ ይህን ይጠብቁ ይጽደቁ። "ካልተማሩ አያውቁ ካላወቁ አይጸድቁ" እንዲሉ።
HTML Embed Code:
2024/05/03 06:49:01
Back to Top