TG Telegram Group Link
Channel: ትምህርተ ወንጌል
Back to Bottom
መዝሙር 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤
²⁶ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።
ትምሕርተ ወንጌል:
መዝሙር 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²⁵ ከቸር ሰው ጋር ቸር ሆነህ ትገኛለህ፤ ከቅን ሰው ጋር ቅን ሆነህ ትገኛለህ፤
²⁶ ከንጹሕ ጋር ንጹሕ ሆነህ ትገኛለህ፤ ከጠማማም ጋር ጠማማ ሆነህ ትገኛለህ።

“ አምላኬ ሆይ፥ በመልካም አስበኝ።”
  — ነሀምያ 13፥31

“አንደበትህን ከክፉ ከልክል፥ ”
  — መዝሙር 34፥13
የሰርግ ጥሪ

    🙏  🙏የማክበር ሰላምታችንን እያቀረብን ኢየሱስ ክርስቶስ ቢፈቅድ ና ብንኖር በፊታችን ባለው አንድ ቀን ሙሽራው🔥🔥 ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሙሽሪትን ( ቤተ ክርስቲያንን) 🏥 ከምድር ሊወስዳት ይመጣል ልብ ❤️ ይበሉ የሚመጣበት ሰአት ቀን ባለመገለፁ 😔 /ማቴ24፥36/ ከዛሬዋ ቀን ጀምረው በእውነተኛ ንስሐ ተዘጋጅተው ሙሽራውን ሊጠብቁ ይገባል🥰። ሙሽራው በሚመጣበት ያን ጊዜ የአለም መጨረሻ ይሆናል።

     🔖🔖  በዚህ ሰርግ ላይ ለመታደም     የሚያስፈልጎት  መስፈርቶች፡-

1, ነጭ ልብስ መልበስ አለብዎት
/ ማቴ 22፥11-14 / ይህ ንስሐ ገብተው በክርስቶስ ማመንዎትን የሚገልጥ ነው

2, መብራት እና በቂ የሆነ ዘይት መያዝዎትን አይዘንጉ
/ ማቴ 25፥1-13 /

3, ታማኝነት እና ልባምነት
/ ማቴ 24፥45-51 / ዋና ዋናዎቹ ናቸው።
     
             ታዲያ እርሶ በክርስቶስ ሞት እና
             ትንሳኤ አምነዋልን?? እውነተኛስ
             ንስሐ ገብተዋልን??

   በቃ  ዛሬውኑ  ይወስኑ!!!!!!!!!!!!!!!!!!!!
             
                                  ዝግጁ እንሁን!
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ኦርቶዶክስ መዝሙር 🔔
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 4፥16

“መልካም ቢሆን ወይም ክፉ እንዳደረገ፥ እያንዳንዱ በሥጋው የተሠራውን በብድራት ይቀበል ዘንድ ሁላችን በክርስቶስ በፍርድ ወንበር ፊት ልንገለጥ ይገባናልና።”
— 2ኛ ቆሮ 5፥10

“የሰው ልጅ ከመላእክቱ ጋር በአባቱ ክብር ይመጣ ዘንድ አለውና፤ ያን ጊዜም ለሁሉ እንደ ሥራው ያስረክበዋል።”
— ማቴዎስ 16፥27
ያዕቆብ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ወንድሞቼ ሆይ፥ ከእናንተ ብዙዎቹ አስተማሪዎች አይሁኑ፥ የባሰውን ፍርድ እንድንቀበል ታውቃላችሁና።
² ሁላችን በብዙ ነገር እንሰናከላለንና፤ በቃል የማይሰናከል ማንም ቢኖር እርሱ ሥጋውን ሁሉ ደግሞ ሊገታ የሚችል ፍጹም ሰው ነው።
³ እነሆ፥ ፈረሶች ይታዘዙልን ዘንድ ልጓም በአፋቸው ውስጥ እናገባለን፥ ሥጋቸውንም ሁሉ እንመራለን።
⁴ እነሆ፥ መርከቦች ደግሞ ይህን ያህል ታላቅ ቢሆኑ በዐውሎ ነፋስም ቢነዱ፥ የመሪ ፈቃድ ወደሚወደው ስፍራ እጅግ ታናሽ በሆነ መቅዘፊያ ይመራሉ።
⁵ እንዲሁም አንደበት ደግሞ ትንሽ ብልት ሆኖ በታላላቅ ነገር ይመካል። እነሆ፥ ትንሽ እሳት እንዴት ያለ ትልቅ ጫካ ያቃጥላል።
⁶ አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል።
⁷ የአራዊትና የወፎች የተንቀሳቃሾችና በባሕር ያለ የፍጥረት ወገን ሁሉ በሰው ይገራል፥ ደግሞ ተገርቶአል፤
⁸ ነገር ግን አንደበትን ሊገራ ማንም ሰው አይችልም፤ የሚገድል መርዝ የሞላበት ወላዋይ ክፋት ነው።
⁹ በእርሱ ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በእርሱም እንደ እግዚአብሔር ምሳሌ የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን፤
¹⁰ ከአንድ አፍ በረከትና መርገም ይወጣሉ። ወንድሞቼ ሆይ፥ ይህ እንዲህ ሊሆን አይገባም።
¹¹ ምንጭስ ከአንድ አፍ የሚጣፍጥንና የሚመርን ውኃ ያመነጫልን?
¹² ወንድሞቼ ሆይ፥ በለስ ወይራን ወይስ ወይን በለስን ልታፈራ ትችላለችን? ከጨው ውኃም ጣፋጭ ውኃ አይወጣም።
¹³ ከእናንተ ጥበበኛና አስተዋይ ማን ነው? በመልካም አንዋዋሩ ስራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።
¹⁴ ነገር ግን መራራ ቅንዓትና አድመኛነት በልባችሁ ቢኖርባችሁ፥ አትመኩ በእውነትም ላይ አትዋሹ።
¹⁵ ይህ ጥበብ ከላይ የሚወርድ አይደለም፤ ነገር ግን የምድር ነው፥ የሥጋም ነው፥ የአጋንንትም ነው፤
¹⁶ ቅንዓትና አድመኛነት ባሉበት ስፍራ በዚያ ሁከትና ክፉ ስራ ሁሉ አሉና።
¹⁷ ላይኛይቱ ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፥ በኋላም ታራቂ፥ ገር፥ እሺ ባይ ምሕረትና በጎ ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።
¹⁸ የጽድቅም ፍሬ ሰላምን ለሚያደርጉት ሰዎች በሰላም ይዘራል።
ማርቆስ 8
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁵ ስለ እኔና ስለ ወንጌል ነፍሱን የሚያጠፋ ሁሉ ግን ያድናታል።
³⁶ ሰው ዓለምን ሁሉ ቢያተርፍ ነፍሱንም ቢያጐድል ምን ይጠቅመዋል?
³⁷ ሰውስ ስለ ነፍሱ ቤዛ ምን ይሰጣል?
³⁸ በዚህም በዘማዊና በኃጢአተኛ ትውልድ መካከል በእኔና በቃሌ የሚያፍር ሁሉ፥ የሰው ልጅ ደግሞ በአባቱ ክብር ከቅዱሳን መላእክት ጋር በመጣ ጊዜ በእርሱ ያፍርበታል።

ሰላም ጤና ይስጥልኝ ትምህርተ ወንጌል ቻናል አባላት።
በአምላካችን በመድሃኒታችን በኢየሱስ ክርስትስ ሰላም ሰላም እንላችሁአለን።

ከላይ መድሃኒታችን እንደተናገረው
ስለ እኔ እና ስለ ወንጌል መገደል መቸገር መመስከር ትልቅ የሆነ ዋጋ አለው ይለናል መድሃኒታችን።
ወገኖቻችን ተሰውተዋል ወገኖቻችን የታረዱለት ወገኖቻችን ህይወታቸውን የገበሩለት ወንጌል ምነው በእኛ ዘንድ ለመስማትኳ ጊዜ አጣን?
ይህን የምንለው አባታች ቅዱስ ጊዮርጊስ የተፈጨው የደቀቀው አጥንቱንም ስጋውንም አቃጥለው ወደ አመድነት የቀየሩት ከዛም ነፋስ ላይ የበተኑት ስለ ኢየሱስ እና ስለወንጌል ስለመሰከረ ነው።
እኛስ?
ያባቶቻችን ልጆች ስለሆን የነሱን ያክል ባንሰራም እንደ እነሱ ለመሆን እማንሞክረው ለምንድነው?
ኢየሱስ በቀጥታ ቅዳሴው ላይ ይገኛል
እኛ ግን ቅዳሴውን አቁመነው እንሄዳለን ካልሆነ አርፍደን እንገባለን?
ኢየሱስ የተናገረው ግን ወንጌልን አንብበን ተምረን የገባንን ለአህዛብ እንድንመሰክር  ይህን ነው ያዘዘን
ወንጌል እና ኢየሱስ የሚያድኑ ህይወት ናቸው ያለወንጌል ህይወት የለም በማለት ስለወንጌል የሚመሰክር ይህ ነው ነፍሱን የሚያድናት በማለት ክርስቶስ የነገረን
“አቤቱ አምላክ ሆይ፥ #ተነሥ እጅህም ከፍ ከፍ ትበል፤ ድሆችን አትርሳ።”
— መዝሙር 10፥12
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ከቅዳሴ መልስ መሞቱ ለአገልጋይ ካህኑ
መልካም ነው ለኛ ግን ከአህዛብ መንግስት ምንም ሌላ አይጠበቅም።
ሙሴ እያሱ ዳዊት ኢሳይያስ………ሐዋርያት ኢየሱስም እንዲሁ ነበሩ
“ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤”
— ዕብራውያን 3፥1
The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 30 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
“ስለዚህ፥ ከሰማያዊው ጥሪ ተካፋዮች የሆናችሁ ቅዱሳን ወንድሞች ሆይ፥ የሃይማኖታችንን ሐዋርያና ሊቀ ካህናት ኢየሱስ ክርስቶስን ተመልከቱ፤”
— ዕብራውያን 3፥1
“ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን።”
— መዝሙር 66፥20
The owner of this channel has been inactive for the last 11 months. If they remain inactive for the next 18 days, they may lose their account and admin rights in this channel. The contents of the channel will remain accessible for all users.
“ጸሎቴን ያልከለከለኝ ምሕረቱንም ከእኔ ያላራቀ እግዚአብሔር ይመስገን።”
  — መዝሙር 66፥20
HTML Embed Code:
2024/04/28 17:22:34
Back to Top