TG Telegram Group Link
Channel: ትምህርተ ወንጌል
Back to Bottom
“ከማናቸውም ዓይነት ክፉ ነገር #ራቁ።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥22

ይሕንን ሃይለ-ቃል የተናገረን የወንጌል ገበሬ የተባለው ብርሃን ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ ነው።
የተሰሎንቄ ሰዎች ሁለት መልዕክት ነው የተላከላቸው ይህም 1ኛ እና 2ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች የሚል ነው።
እነዚህ የተጻፈላቸው ክርስቲያኖች ናቸው። የስነ-ምግባር ችግር እንዳለባቸው ተመልክቶ ሲጽፍ እናነባለን ይህ መልዕክት ለተሰሎንቄ ሰዎች ይጻፍ እንጂ ለመላው ዓለም ህዝበ ክርስቲያን ታላቅ መልዕክት ያዘለ ሃይለ ቃል ነው። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቃል በመረዳት ሐዋርያው እንዳዘዘን ለኛ ከማይጠቅም እና ከእግዚአብሔር የሚለየንን ከማንኛውም ክፉ ነገር መራቅ መሸሽ ከእኛ የሚጠበቅ ሃላፊነት ነው ነገር ግን
ዛሬ በእኛ ዘመን ከክፉ ነገር ከመራቅ ይልቅ አጥብቀን በመከተል መጥፊያችንን እየፈለግን ነው። የተሰሎንቄ ሰዎች ግን በቅዱስ ጳውሎስ መልዕክት እና ስብከት ተመልሰዋል። እኛ ግን እግዚአብሔር ያልፈቀደልንን በመከተል ብዙ ነገር ተበላሽቶብናል ብዙ ነገር ከስረናል ካህናት ሲናገሩን አንሰማም ብለናል።
በዚህም ምክንያት ትዳራችን ተበትኗል ያላገባነው በዝሙት ወድቀናል ነጋዴዎች ከስረናል ከትምህርት ወደኃላ ቀርተናል በምቀኝነት በዝሙት በስካር በጣዖት ማምለክ እንደዚህ በመሳሰሉት ነገሮች በጣም ከእግዚአብሔር እርቀናል። ቅዱስ ጳውሎስ የነገረን ግን ከክፉ እራቁ እንጂ ከእግዚአብሔር እራቁ አላለንም ነበር። ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ከመስማት ይልቅ ጆሯችንን በማዞር ስለ ዓለም ነገር መስማቱን ብቻ ነው የምናውቀው። ሰው የሚቆሽሸው ከማናቸውም ክፉ ነገር ሲጠጋ ነው።
ለምሳሌ:- ከ ''ዝሙተኛ'' ጋ ቢውል ዝሙተኛ የማይሆንበት ነገር የለም!
''ሌባ'' ጋ ቢውል የማይሰርቅበት ምክንያት የለም!
ከተሳዳቢጋ ቢውል ተሳዳቢ ለመሆን ምንም አያግደውም።
ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስን ብንሰማው መልካም ነው። ስለዚህ ከእግዚአብሔር እርቀን ማናቸውንም ክፉ ነገር ብንከተል ሰላማችን ይጠፋል!
ክብራችን ይወርዳል!
የሰውነት ክብራችን ወደ እንሰሳዊ ጸባይ ይለወጣል!
ለሚያልፍ ነገር የማያልፈው እግዚአብሔር ይቀየመናል ስለዚህ ከክፉ ግብራችን በመቆጠብ ወደ እግዚአብሔር መጠጋት ለኛ መልካም ነው።
ደግሞ መጽሐፍ ቅዱስ አንብቡ የምታነቡ በፆለት በልመና አንብቡ የማታነቡ አንብቡ የሌላችሁ ግዙ ሌላ መጽሐፍኮ ትገዛላችሁ አይደል? ስለዚህ ከ500 ብር በታች ነው ግዙ ሰው ስንት ነገር ያጠፋ የለ? ስለዚህ ግዙና አንብቡ መጽሀፍ ቅዱስን በማንበባችሁ ብቻ ትባረካላችሁ ራዕ(1:3).
ስለዚህ ከክፉ ነገር እንራቅ ሰው ክፉ የሆነውን ለራሱ በመተው ክፉ የሆኑትን ወደ ጥሩ በእግዚአብሔር ቃል መክሮ ይመልስ የለ?
ስለዚህ እኛ ከክፉ ነገር ማምለጥ እንዴት ይሳነናል?
“ኢየሱስም፦ #ለሚያምን ሁሉ ይቻላል አለው።”
— ማርቆስ 9፥23
ስለዚህ ከክፉ ነገር ለመላቀቅ አምላካችን እንዳለው #ማመን ብቻ ነው። ቅዱስ ዳዊትም እንደዚህ ሲገጥመው አጭር ምላሽ የሰጠው ይሕን ነበር ያለው

“እናንተ ኃጢአተኞች፥ ከእኔ #ራቁ፥ የአምላኬንም ትእዛዝ #ልፈልግ።”
— መዝሙር 119፥115

መልካሙን ልብ ይስጠን አሜን
አንብቡና #ሼር አድርጉት።

https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
“እግዚአብሔርም የፍርድ አምላክ ነውና ስለዚህ እግዚአብሔር ይራራላችሁ ዘንድ ይታገሣል፥ ይምራችሁም ዘንድ ከፍ ከፍ ይላል፤ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ ሁሉ ብፁዓን ናቸው።”

— ኢሳይያስ 30፥18
“እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ፤ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ፤ ይሮጣሉ፥ አይታክቱም፤ ይሄዳሉ፥ አይደክሙም።”

— ኢሳይያስ 40፥31
“በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፤ አቤቱ፥ አንተ ብቻህን በእምነት አሳድረኸኛልና።”
— መዝሙር 4፥8

https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
‹‹መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በሌሊት የተቀደደ ቀሚስ ለብሶ ታየኝ ፤ እኔም ‹ጌታዬ ሆይ ልብስህን ማን ቀደደው?› ብዬ ጠየቅሁት፡፡ ‹አርዮስ ልብሴን ቀደደው ፤ ከባሕርይ አባቴ (ከአብ) ለይቶኛልና ፤ እንዳትቀበለው ተጠንቀቅ› አለኝ›› አላቸው፡፡ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ በእኔ ደም መፍሰስ የክርስቲያኖች ደም እንደጎርፍ መፍሰሱ ይቁም ብሎ ተስሎ በሰማዕትነት አርፏል፡፡ ጌታችን ‹ልብሴን ቀደደው› ብሎ ለዚህ ፓትርያርክ እንደነገረው የጌታችን የባሕርይ አምላክነት ላይ የክህደት ቃልን የሚናገሩ ሰዎች ሁሉ ሮማውያን ወታደሮች ያልቀደዱትን የክርስቶስን ቀሚስ እንደቀደዱ ይቆጠራል፡፡

ሊቁ ቅዱስ አውግስጢኖስ ደግሞ የጌታችንን ልብስ አለመቀደድ ቤተ ክርስቲያንን ለሚከፋፍሉ ሰዎች ማስተማሪያ አድርጎ ተጠቅሞበታል፡፡ እንደ ሊቁ ትምህርት ያልተቀደደችውና ከላይ ጀምሮ ወጥ የሆነችው ቀሚስ ከዚህ ዓለም ያልሆነችው የቅድስት ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ናት፡፡ ለአራት የተከፈለው ደግሞ የምታስተምረው ወንጌል ነው፡፡ ወንጌል ሊከፋፈልና ለዓለም ሁሉ ሊዳረስ ይችላል፡፡ ወንጌል በዘር በቋንቋ በሀገር አይገደብምና የክርስቶስ ወታደሮች የሆኑ ካህናትና መምህራነ ቤተ ክርስቲያን ወንጌልን ተከፋፍለው ለዓለም ማከፋፈል አለባቸው፡፡

አብያተ ክርስቲያናት በየሀገራቱ ቢቋቋሙ ፣ አህጉረ ስብከቶች ቢስፋፉ ፣ ሊቃነ ጳጳሳት ፣ ካህናት ፣ ዲያቆናት ፣ ሊቃውንት ፣ ሰባክያን በቁጥር በዝተው ፣ በቦታም ተከፋፍለው ቢያገለግሉ እጅግ መልካም ነው፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ‹‹በሁሉ ጎዳና … ክርስቶስ ይሰበካል ስለዚህም ደስ ብሎኛል›› እንዳለ የመምህራን መብዛት የወንጌል መስፋፋት እጅግ ደስ የሚያሰኝ ነው፡፡ (ፊል. ፩፥፲፰)

ቀሚሱ የተባለችን ቤተ ክርስቲያንን ከተቃደዷት ግን አደጋ አለው ፤ ‹የሐዋርያት በሆነች በአንዲት ቤተ ክርስቲያን እናምናለን› ብለን የምንናገርላት ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ ቀሚሱ ናት፡፡ በሰው እጅ ያልተሰፋች ፣ ማንምም ሊሠፋት የማይችል ቀሚስ ናት ፤ ከላይ ጀምሮ ወጥ ሆና በመሠራቷም አትከፋፈልም፡፡ ቤተ ክርስቲያንን ሊከፋፍሏት የሚፈልጉ ሰዎችን ሊቁ አውግስጢኖስ እንዲህ ሲል ይጠይቃቸዋል ፡- ‹‹ሮማውያን እንኳን ያልቀደዱትን የክርስቶስን ልብስ እናንተ ስለምን ትቀድዱታላችሁ?››

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
[email protected]
"ሕማማት"
~ፆመ_ነብያት~

# ፆመ_ነብያት_መቼ_ይገባል ?
ለምንስ_እንፆማለን?
ፆመ ነብያት ወይም የገና ፆም

#ሐሙስ ህዳር 15 ይጀምራል ታህሳስ 29 በዕለተ ይፈታል። ይህ ማለት የዘንድሮ የገና ፆም ቅበላ እስከ ማክሰኞነው ከረቡዕ ጀምሮ የፍስክ ምግቦች አይበሉም።

ይህ ፆም ከቤተ ክርስቲያናችን የአዋጅ ፆሞች ውስጥ አንዱ ሲሆን አበው ነብያት የጌታችን የመድሃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን መውረድ መወለድ በትንቢት መነፅር እየተመለከቱ የፆሙት ታላቅ ፆም ነው።

ዛሬም እኛ ክርስቲያኖች የአባቶቻችንን ፈለግ ተከትለን በፆምና በፀሎት ወቅቱን በማሳለፍ ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱን ዝቅ አድርጎ ወደ አለም መምጣቱንና የዓለም ቤዛ መሆኑን የምናስብበት ነው።

=> ይህ ፆም፣ ፆመ ድህነት፣ ፆመ ማርያም ፣ ፆመ አዳም ፆመ ፊሊጶስ ፆመ ስብከት በመባል ይጠራል።

# ፆመ_ድህነት የተባለበት ምክንያት መርገመ ስጋ መርገመ ነብስ የአዳም እዳ በደል ጠፍቶ ድህነት ስለተገኘበት ነው።

# ፆመ_ማርያም የተባለበት ምክንያት ንፅይተ ንፁሃን ቅድስተ ቅዱሳን እመቤታችን ቅድስ ድንግል ማርያም ጌታን በማህፀኔ ተሸክሞ ልፆም ልፀልይ ይገባል ብላ ለ40 ቀን እስከ ጌታችን መድሃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ልደት ድረስ የፆመችው ፆም ስለሆነ ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል።

# ፆመ_አዳም የተባለበት ምክንያት ለአዳም የተነገረው ትንቢት፣ የሚጠበቀው ሱባኤ እንደደረሰ የሚያበስር በመሆኑ ጾመ አዳም ይባላል፡፡ አዳም ቢበድልም ንስሐ ገብቶ በማልቀሱ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሀለሁ ብሎ የተነገረው ተስፋ መድረሱን፣ ምሥጢረ ሥጋዌ እውን ሊሆን መቃረቡን የሚያስረዳ ጾም ነው፡፡

# ፆመ_ፊሊጶስ የተባለበትም ምክንያት ሐዋርያው ፊልጶስ በአረማውያን ዘንድ ገብቶ ሲያስተምር በሰማዕትነት ሲሞት አስከሬኑ ከደቀመዛሙርቱ ስለተሰወረ እግዚአብሔር የተሰወረውን የመምህራቸውን አስከሬን እንዲገልጽላቸው ከኅዳር አስራ ስድስት ጀምረው ሲጾሙ በሦስተኛው ቀን የመምህራቸው አስከሬን ቢመልስላቸውም ጾሙን ግን እስከ ልደት ቀጥለዋል ለዚህም ይህ ስያሜ ተሰጥቶታል፡፡

# ፆመ_ስብከት የተባለበትም ምክንያት የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት የሰውልጆች ተስፋ የተመሰከረበት የምሥራቹ የተነገረበት

ስለሆነም «ጾመ ስብከት» ይባላል፡፡
ፆሙን የሀጥያታችን መደምሰሻ መንግስተ ሰማያተን መውረሻ ያድርግልን። የቅዱሳን ነብያት አባቶቻችንንም በረከት በሁላችንም ላይ ያሳድርብን።
ወስበሐት_ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ_ድንግል
ወለመስቀሉ_ክቡር
አሜን ።


https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
የእረኞችም አለቃ በሚገለጥበት ጊዜ የማያልፈውን የክብርን አክሊል ትቀበላላችሁ።
መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ
13 1 ከዚህም በኋላ እንዲህ ሆነ ለዳዊት ልጅ ለአቤሴሎም አንዲት #የተዋበች እኅት ነበረችው፥ ስምዋም #ትዕማር ነበረ የዳዊትም ልጅ #አምኖን ወደዳት።
13 2 አምኖንም ከእኅቱ ከትዕማር የተነሣ እጅግ ስለ ተከዘ #ታመመ ድንግልም ነበረችና አንዳች ያደርጋት ዘንድ በዓይኑ ፊት ጭንቅ ሆኖበት ነበር።
13 3 ለአምኖንም የዳዊት ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ የሚባል ወዳጅ ነበረው ኢዮናዳብም እጅግ #ብልህ ሰው ነበረ።
13 4 እርሱም፦ የንጉሥ ልጅ ሆይ፥ ስለ ምን ቀን በቀን እንዲህ #ከሳህ? አትነግረኝምን? አለው። አምኖንም። የወንድሜን የአቤሴሎምን እኅት ትዕማርን እወድዳታለሁ አለው።
13 5 ኢዮናዳብም። ታምሜአለሁ ብለህ በአልጋህ ላይ ተኛ አባትህም ሊያይህ በመጣ ጊዜ። እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ የምበላውን እንጀራ እንድትሰጠኝ፥ መብሉንም እኔ እያየሁ እንድታዘጋጅልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላው እለምንሃለሁ በል አለው።
13 6 እንዲሁም አምኖን፦ ታምሜአለሁ ብሎ ተኛ ንጉሡም ሊያየው በመጣ ጊዜ አምኖን ንጉሡን፦ እኅቴ ትዕማር እንድትመጣና እኔ እያየሁ ሁለት እንጎቻ እንድታደርግልኝ፥ ከእጅዋም እንድበላ እለምንሃለሁ አለው።
13 7 ዳዊትም፦ መብልን ታዘጋጂለት ዘንድ ወደ ወንድምሽ ወደ አምኖን ቤት #ሂጂ ብሎ መልእክተኞችን ወደ ትዕማር ቤት ላከ።
13 8 ትዕማርም ወደ ወንድምዋ ወደ አምኖን ቤት ሄደች፥ ተኝቶም ነበር ዱቄትም ወስዳ ለወሰች፥ እያየም እንጎቻ አደረገች፥ ጋገረችም።
13 9 ምጣዱንም ወስዳ በፊቱ ገለበጠች እርሱ ግን ይበላ ዘንድ እንቢ አለ። አምኖንም። ሰውን ሁሉ ከእኔ ዘንድ አስወጡ አለ ሰውም ሁሉ ከእርሱ ዘንድ ወጣ።
13 10 አምኖንም ትዕማርን፦ ከእጅሽ እበላ ዘንድ መብሉን ወደ እልፍኙ አግቢው አላት ትዕማርም የሠራችውን እንጎቻ ወስዳ ወንድምዋ አምኖን ወዳለበት እልፍኝ አገባችው።
13 11 መብሉንም ባቀረበች ጊዜ ያዛትና። እኅቴ ሆይ፥ ነዪ ከእኔም ጋር #ተኚ አላት።
13 12 እርስዋ መልሳ። ወንድሜ ሆይ፥ አይሆንም እንዲህ ያለ ነገር በእስራኤል ዘንድ #አይገባምና #አታሳፍረኝ ይህንም ነውረኛ ሥራ #አታድርግ
13 13 እኔም ነውሬን ወዴት ልሸከም? አንተም በእስራኤል ዘንድ #ከምናምንቴዎች እንደ አንዱ ትሆናለህ እንግዲህስ ለንጉሡ ንገረው፥ እኔንም #አይነሣህም አለችው።
13 14 ቃልዋን ግን #አልሰማም ከእርስዋም ይልቅ ብርቱ ነበረና በግድ #አስነወራት፥ ከእርስዋም ጋር ተኛ።
13 15 ከዚያም በኋላ አምኖን ፈጽሞ #ጠላት አስቀድሞም ከወደዳት ውድ ይልቅ በኋላ #የጠላት ጥል በለጠ። አምኖንም። ተነሥተሽ #ሂጂ አላት።
13 16 እርስዋም፦ አይሆንም ቀድሞ ከሠራኸው ክፋት ይልቅ አኔን በማውጣትህ የበለጠ ክፋት ትሠራለህ አለችው እርሱ ግን #አልሰማትም
13 17 የሚያገለግለውንም ብላቴና ጠርቶ። ይህችን ሴት ከፊቴ አስወጥተህ በሩን #ዝጋባት አለው።
13 18 ብዙ ኅብር ያለውንም ልብስ ለብሳ ነበር፥ እንዲህ ያለውን ልብስ የንጉሡ ልጆች ደናግሉ ይለብሱ ነበርና አገልጋዩም አስወጥቶ በሩን #ዘጋባት
13 19 ትዕማርም በራስዋ ላይ አመድ ነስንሳ፥ ብዙ ኅብርም ያለውን ልብስዋን ተርትራ፥ እጅዋንም በራስዋ ላይ ጭና እየጮኸች #ሄደች
13 20 ወንድምዋም አቤሴሎም። ወንድምሽ አምኖን ከአንቺ ጋር ነበረን? እኅቴ ሆይ፥ አሁን ግን ዝም በዪ ወንድምሽ ነው ይህን ነገር በልብሽ አትያዢው አላት። ትዕማርም በወንድምዋ በአቤሴሎም ቤት ብቻዋን ተቀመጠች።
13 21 ንጉሡም ዳዊት ይህን ነገር ሁሉ በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ ነገር ግን የበኵር ልጁ ነበረና ስለ ወደደው የልጁን የአምኖን ነፍስ #አላሳዘነም
13 22 አቤሴሎምም እኅቱን ትዕማርን ስላሳፈራት አምኖንን ጠልቶታልና አቤሴሎም አምኖንን ክፉም ሆነ መልካምም #አልተናገረውም
13 23 ከሁለት ዓመትም በኋላ አቤሴሎም በኤፍሬም አቅራቢያ ባለችው በቤላሶር በጎቹን አሸለተ አቤሴሎምም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ጠራ።
13 24 አቤሴሎምም ወደ ንጉሡ መጥቶ። እነሆ፥ ባሪያህ በጎቹን ያሸልታል ንጉሡና ሎሌዎቹ ከባሪያህ ጋር ይሂዱ አለው።
13 25 ንጉሡም አቤሴሎምን፦ ልጄ ሆይ፥ እንከብድብሃለንና ሁላችን እንመጣ ዘንድ አይሆንም አለው። የግድም አለው፥ እርሱ ግን መረቀው እንጂ ለመሄድ እንቢ አለ።
13 26 አቤሴሎምም። አንተ እንቢ ካልህ ወንድሜ አምኖን ከእኛ ጋር እንዲሄድ እለምንሃለሁ አለ። ንጉሡም። ከአንተ ጋር ለምን ይሄዳል? አለው።
13 27 አቤሴሎምም የግድ አለው፥ አምኖንንና የንጉሡንም ልጆች ሁሉ ከእርሱ ጋር ሰደደ።
13 28 አቤሴሎምም እንደ ንጉሥ ግብዣ ያለ ግብዣ አደረገ አቤሴሎምም አገልጋዮቹን፦ አምኖን የወይን ጠጅ ጠጥቶ ልቡን ደስ ባለው ጊዜ እዩ። አምኖንን ግደሉ ባልኋችሁም ጊዜ ግደሉት፥ አትፍሩም ያዘዝኋችሁም እኔ ነኝና በርቱ ጽኑም ብሎ አዘዛቸው።
13 29 የአቤሴሎም አገልጋዮች አቤሴሎም እንዳዘዛቸው በአምኖን ላይ አደረጉበት። የንጉሡም ልጆች ሁሉ ተነሥተው በየበቅሎቻቸው ተቀምጠው ሸሹ።
13 30 ገናም በመንገድ ሲሄዱ ለዳዊት፦ አቤሴሎም የንጉሡን ልጆች ሁሉ ገድሎአል፥ ከእነርሱም አንድ አልቀረም የሚል ወሬ መጣለት።
13 31 ንጉሡም ተነሥቶ ልብሱን ቀደደ፥ በምድር ላይም ወደቀ ባሪያዎቹም ሁሉ ልብሳቸውን ቀድደው በአጠገቡ ቆሙ።
13 32 የዳዊትም ወንድም የሳምዓ ልጅ ኢዮናዳብ። ጌታዬ ጕልማሶቹ የንጉሡ ልጆች ሁሉ እንደ ሞቱ አያስብ እኅቱን ትዕማርን በግድ ካስነወራት ጀምሮ በአቤሴሎም ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረና የሞተ #አምኖን ብቻ ነው።
13 33 አሁንም የሞተ አምኖን ብቻ ነው እንጂ የንጉሥ ልጆች ሁሉ ሞቱ ብሎ ጌታዬ ንጉሡ ይህን ነገር በልቡ አያኑር አለው።
13 34 አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጕልማሳ ዓይኑን ከፍ አደረገ፥ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ።
13 35 ኢዮናዳብም ንጉሡን፦ እነሆ፥ የንጉሡ ልጆች መጥተዋል ባሪያህ እንዳለው እንዲሁ ሆኖአል አለው።
13 36 ተናግሮም በጨረሰ ጊዜ፥ እነሆ፥ ወዲያው የንጉሥ ልጆች ገቡ፥ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ ደግሞ ንጉሡና ባሪያዎቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ።
13 37 አቤሴሎም ግን ኰብልሎ ወደ ጌሹር ንጉሥ ወደ ዓሚሁድ ልጅ ወደ ተልማይ ሄደ። ዳዊትም ሁልጊዜ ለልጁ ያለቅስ ነበር።
13 38 አቤሴሎም ኰብልሎ ወደ ጌሹር ሄደ፥ በዚያም ሦስት ዓመት ያህል ተቀመጠ።
13 39 ንጉሡም ዳዊት ስለ አምኖን ሞት ተጽናንቶ ወደ አቤሴሎም ይሄድ ዘንድ እጅግ ናፈቀ።
መዝሙረ ዳዊት 25 1 አቤቱ፥ ወደ አንተ ነፍሴን አነሣለሁ።
25 2 አምላኬ፥ አንተን ታመንሁ አልፈር፥ ጠላቶቼ በእኔ አይሣቁብኝ።
25 3 አንተን ተስፋ የሚያደርጉ አያፍሩም በከንቱ የሚገበዙ ያፍራሉ።
25 4 አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
25 5 አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
25 6 አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና።
25 7 የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
25 8 እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
25 9 ገሮችን በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል።
25 10 የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።
25 11 አቤቱ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።
25 12 እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል።
25 13 ነፍሱ በመልካም ታድራለች፥ ዘሩም ምድርን ይወርሳል።
25 14 እግዚአብሔር ለሚፈሩት ኃይላቸው ነው፥ ቃል ኪዳኑንም ያስታውቃቸዋል።
25 15 እርሱ እግሮቼን ከወጥመድ ያወጣቸዋልና ዓይኖቼ ሁልጊዜ ወደ እግዚአብሔር ናቸው።
25 16 እኔ ብቻዬንና ችግረኛ ነኝና ፊትህን ወደ እኔ አድርግ ማረኝም።
25 17 የልቤ ችግር ብዙ ነው ከጭንቀቴ አውጣኝ።
25 18 ድካሜንና መከራዬን እይ፥ ኃጢአቴንም ሁሉ ይቅር በለኝ።
25 19 ጠላቶቼ እንደ በዙ እይ፥ የግፍም ጥል ጠልተውኛል።
25 20 ነፍሴን ጠብቅና አድነኝ አንተን ታምኛለሁና አልፈር።
25 21 አንተን ተስፋ አድርጌአለሁና የውሃትና ቅንነት ይጠብቁኝ።
25 22 አቤቱ፥ እስራኤልን ከመከራው ሁሉ አድነው።
✞" ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች። ✞" (መጽ-ምሳሌ ፴፩ ፥ ፴) 🔊(መዝ ፳፫ ፥ ፩-፮)
“በመኝታቸው ላይ በደልን ለሚያስቡ ክፋትንም ለሚያደርጉ ወዮላቸው! ኃይል በእጃቸው ነውና ሲነጋ ይፈጽሙታል።”
— ሚክያስ 2፥1
“ አምላኬ ሆይ፥ በመልካም አስበኝ።”
— ነሀምያ 13፥31
HTML Embed Code:
2024/05/14 02:42:16
Back to Top