TG Telegram Group Link
Channel: ትምህርተ ወንጌል
Back to Bottom
ሮሜ 12
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው።
² የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም በጎና ደስ የሚያሰኝ ፍጹምም የሆነው ነገር ምን እንደ ሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በልባችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይህን ዓለም አትምሰሉ።
³ እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን እንዳካፈለው፥ እንደ ባለ አእምሮ እንዲያስብ እንጂ ማሰብ ከሚገባው አልፎ በትዕቢት እንዳያስብ በመካከላችሁ ላለው ለእያንዳንዱ በተሰጠኝ ጸጋ እናገራለሁ።
⁴ በአንድ አካል ብዙ ብልቶች እንዳሉን፥ የብልቶቹም ሁሉ ሥራ አንድ እንዳይደለ፥
⁵ እንዲሁ ብዙዎች ስንሆን በክርስቶስ አንድ አካል ነን፥ እርስ በርሳችንም እያንዳንዳችን የሌላው ብልቶች ነን።
⁶ እንደ ተሰጠንም ጸጋ ልዩ ልዩ ስጦታ አለን፤ ትንቢት ቢሆን እንደ እምነታችን መጠን ትንቢት እንናገር፤
⁷ አገልግሎት ቢሆን በአገልግሎታችን እንትጋ፤ የሚያስተምርም ቢሆን በማስተማሩ ይትጋ፤
⁸ የሚመክርም ቢሆን በመምከሩ ይትጋ፤ የሚሰጥ በልግስና ይስጥ፤ የሚገዛ በትጋት ይግዛ፤ የሚምር በደስታ ይማር።
⁹ ፍቅራችሁ ያለ ግብዝነት ይሁን። ክፉውን ነገር ተጸየፉት፤ ከበጎ ነገር ጋር ተባበሩ፤
¹⁰ በወንድማማች መዋደድ እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ፤ እርስ በርሳችሁ ተከባበሩ፤
¹¹ ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ፤
¹² በተስፋ ደስ ይበላችሁ፤ በመከራ ታገሡ፤ በጸሎት ጽኑ፤
¹³ ቅዱሳንን በሚያስፈልጋቸው እርዱ፤ እንግዶችን ለመቀበል ትጉ።
¹⁴ የሚያሳድዱአችሁን መርቁ፥ መርቁ እንጂ አትርገሙ።


¹⁶ እርስ በርሳችሁ በአንድ አሳብ ተስማሙ፤ የትዕቢትን ነገር አታስቡ፥ ነገር ግን የትሕትናን ነገር ለመሥራት ትጉ። ልባሞች የሆናችሁ አይምሰላችሁ።
¹⁷ ለማንም ስለ ክፉ ፈንታ ክፉን አትመልሱ፤ በሰው ሁሉ ፊት መልካም የሆነውን አስቡ።
¹⁸ ቢቻላችሁስ በእናንተ በኩል ከሰው ሁሉ ጋር በሰላም ኑሩ።
¹⁹ ተወዳጆች ሆይ፥ ራሳችሁ አትበቀሉ፥ ለቍጣው ፈንታ ስጡ እንጂ፤ በቀል የእኔ ነው፥ እኔ ብድራቱን እመልሳለሁ ይላል ጌታ ተብሎ ተጽፎአልና።
²⁰ ጠላትህ ግን ቢራብ አብላው፤ ቢጠማ አጠጣው፤ ይህን በማድረግህ በራሱ ላይ የእሳት ፍም ትከምራለህና።
²¹ ክፉውን በመልካም አሸንፍ እንጂ በክፉ አትሸነፍ።
ማቴዎስ ፫
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
፲ አሁንስ #ምሳር በዛፎች ሥር ተቀምጦአል፤ እንግዲህ መልካም ፍሬ #የማያደርግ ዛፍ ሁሉ #ይቈረጣል ወደ እሳትም #ይጣላል
፲፩ እኔስ #ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ የማይገባኝ ከእኔ #በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ #ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ በመንፈስ ቅዱስ #በእሳትም ያጠምቃችኋል፤
፲፪ #መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም #በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን #በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።
፲፫ ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።
---------------*-----------------
ምሳር የተባለው እንጨትን የሚቆርጥ መሳሪያ ነው።
በዚህ የወንጌል ክፍል ግን #መልካም ፍሬ የማያፈራ መቁረጫ ተብሏል። ቁ፰ ላይ ለንስሃ የሚያበቃ መልካም ስራ (ፍሬ) አድርጉ በማለት እንደተናገረው አሁንደሞ መልካም ፍሬ የማያፈራው ተቆርጦ ወደ እሳት እንደሚጣል ይነግረናል።
የወንጌሉ አጻጻፍ ከላይ አብርሃም አባታችን እያሉ በአብርሃም በመመካት ነገር ግን አብርሃም ያደረገውን ነገር የማያደርጉ በተቃራኒው ክፉ ስራ እየሰሩ ደግሞም ክፉ ስራ አትስሩ ሲባሉ እኛኮ የአብርሃም ዘር ነን በማለት ሲናገሩ የነበረውን ንግግር አስመልክቶ #አሁንስ ምሳር(Axe) በዛፎች #ሥር ተቀምጧል #መልካም ፍሬ የማያፈራ #ይቆረጣል መቆረጥ ብቻ? አይደለም ወደ እሳት 🔥 ይጣላል.
የሚጠፋ እሳት? አይደለም ወደማይጠፋ እሳት ነውጂ። ማቴ(፳፭÷፵፩).
ቅዱስ ማቴዎስ #አሁንስ በማለት የነገራቸው እንደ እስከዛሬው በአብርሃም በመመካት በጅምላ ደግሞም መልካም ሥራ የሚሰራ እና መልካም ሥራ የማይሰራ እና መልካም ሥራ ሊሰራ ያልወደደ ሁሉ ከአብርሃም እርስተ-መንግስተ ሰማያት እንደማያገኝ ተለይቶ ወደ ዘላለም እሳት እንደሚወረወር የተናገረበት የወንጌል ክፍል ነው።
ምሳሩ የሚቆርጠው መልካም የማያፈሩትን ነው የሚቆርጠው።
የሚቆርጠው አቀማመጡ እንደሚያመለክተን ከስሩ ነው።
#አሁን የደጉ የአብርሃም ልጆች ነን በማለት አይዳንም። ምክንያቱም ከአብርሃም የተለየ ስራ የሚሰሩት ተለይተው ወደ እሳት ይጣላሉና።
መድኃኒታችንም ሲያስተምራቸው እንደ ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ይላቸው ነበረ።
#መልካም_ፍሬ_የማያደርግ_ዛፍ_ሁሉ_ይቆረጣል_ወደ_እሳትም_ይጣላል።”
— ማቴዎስ (፯÷፲፱).
በማለት በቀጥታ አስተምሯል።

በመቀጠልም ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ ይላል

“እኔስ #ለንስሐ በውኃ አጠምቃችኋለሁ፤ ጫማውን እሸከም ዘንድ #የማይገባኝ ከእኔ #በኋላ የሚመጣው ግን ከእኔ #ይልቅ ይበረታል፤ እርሱ #በመንፈስ_ቅዱስ_በእሳትም ያጠምቃችኋል፤”
— ማቴዎስ(፫፥፲፩)
*ቅዱስ ዮሐንስ እኔስ የማጠምቃችሁ #የንስሃ ጥምቀት ነው በማለት የሥላሴን ልጅነት ከምናገኝበት ማለትም ወንድ እና ሴት በ፵እና በ፹ቀን ከሚጠመቁት ጥምቀት ይለያልና። ደግሞም አይሁድን ቅዱስ ዮሐንስ ያጠመቃቸው በፍጹም ኢየሱስን ካጠመቀው የሚለይም ነው።
ስለዚህ #የንስሃ ጥምቀት ነው ማለትም ሃጢአታቸውን ሲናዘዙ ያጠመቃቸው መሆኑን ልብ ብለን እናስተውል።
“ዮሐንስ በምድረ በዳ እያጠመቀ #የንስሐንም_ጥምቀት_ለኃጢአት_ስርየት እየሰበከ መጣ።”
— ማርቆስ (፩፥፬).
“ከመምጣቱ በፊት ዮሐንስ አስቀድሞ ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ #የንስሐን_ጥምቀት ሰብኮ ነበር።”
— ሐዋርያት (፲፫፥፳፬).
#ጫማውን እንኳ ለመሸከም የማይገባኝ በማለት በሚቻለው አቅም ስለ ክርስቶስ ታላቅነት የመሰከረው ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ የአዲሱ ምዕራፍ(የሐዲስ ኪዳን) መሸጋገሪያ ድልድይ በመሆኖ ኢየሱስን አስተዋውቆ ዘወር ነው ያለው። ነገር ግን የብሉይ ኪዳን የመጨረሻው ነብዩ ዮሐንስ ነው የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያው ሐዋርያ ነው። ኢየሱስ የመረጣቸው ሐዋርያት አንዳንዱ ቀድሞም የቅዱስ ዮሐንስ ደቀመዝሙርም ነበሩ። ኢየሱስ በቀጥታ ትምህርት ከመጀመሩ በፊት ስለኢየሱስ ያስተዋወቀ አዋጅ ነጋሪ ነው።
እንደተናገረው ከእኔ በኋላ የሚመጣው ከእኔ በፊት ነው። በማለት የኢየሱስ የባሕሪ አምላክነት ይመሰክራል።
በውነት በጽንሰት እንኳ ብናይ #ስድስት ወር ኢየሱስን ይበልጣል
ነገር ግን ከእኔ በፊት ነበር ነው ያለው። ይህ ማለት ቅድመ ዓለምም የነበረ እራሱን ዮሐንስን የፈጠረ ነው ዮሐ(፩÷፫).
ኢየሱስ ይመጣል ያላቸውም ቀደምት ነቢዩ እንዲህ ነበር ያለው
“አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፤ ከአንቺ ግን #አወጣጡ_ከቀድሞ_ጀምሮ_ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን #ይወጣልኛል።”
— ሚክያስ (፭÷፪).
ስለዚህ ኢየሱስ በመለኮታዊ ባሕሪው ከቀድሞ ጀምሮ የነበረ እግዚአብሔር ነው ዮሐ(፩÷፩).
ከእኔ በፊት ነበረ በማለት አምላክ መሆኑን ሊያስረዳ ነው። እንዲያማ ካልሆነ #ስድስት ወርኮ ይበልጠዋል ኢየሱስን።ሉቃ(፩÷፴፮).
ነገር ግን አይሁድ እንደ ሙስሊም ከድንግል ማርያም ከተወለደ ቡሃላ እንጂ ከዛ በፊት አልነበረም በማለት ያምናሉ ለዚህም ነው ለቀድሞ አይሁድ ለዛሬ ሙስሊም ተከታይ መልስ ሊሰጣቸ መንፈስ ቅዱስ ለሚኪያስ እንዳመለከተው ደግሞም ለቅዱስ ዮሐንስ :- #የሚመጣው_ከእኔ_በፊት ነበረ
በማለት እንደ ወንጌላውይ ቅዱስ ዮሐንስ ዮሐ(፩÷፩).
ኢየሱስ በሁለት አይነት ያጠምቃል አለ ፩ኛ.በመንፈስ ቅዱስ
፪ኛ.በእሳት.
እሽ ብለው አምነው የተጠመቁት አይሁድ በመንፈስ ቅዱስ ሊያጠምቃቸው ሲወድ, እንቢ በማለት አልጠመቅም አላምንም ያሉትን ደሞ በእሳት 🔥 ያጠምቃቸዋል። ይህ ግን ከፍርድጋ የተገናኘ ነው።ራዕ(፳፪÷፲፪).
ቀጥሎም ቅዱስ ዮሐንስ እንዲህ አለ

“መንሹም በእጁ ነው፥ አውድማውንም ፈጽሞ ያጠራል፥ ስንዴውንም በጎተራው ይከታል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”
— ማቴዎስ (፫፥፲፪).
አውድማው ==የትንሳኤ ቀን
ስንዴ ====የጻድቃን
ገለባ ====የኃጣን
እሳቱ ====የገኃነብ
ጎተራው====መንግስተ ሰማያት
ስለዚህ መልካም ስራ የሰሩት(ስንዴዎቹ) በጎተራ ሲከተቱ
መልካም ፍሬ የሌለዌ(ገለባው) ግን ወደ ገሐነም እሳት ይጣላል።
ይሕንም ኢየሱስ እንዲህ ይላል
ራእይ ፳፪
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
፲፪ እነሆ፥ በቶሎ እመጣለሁ፥ ለእያንዳንዱም #እንደ ሥራው መጠን #እከፍል ዘንድ ዋጋዬ ከእኔ ጋር አለ።
፲፫ አልፋና ዖሜጋ፥ ፊተኛውና ኋለኛው፥ መጀመሪያውና መጨረሻው እኔ ነኝ።

#መንሹ_በእጁ ነው:- ስልጣኑ የራሱ ነው ማቴ(፳፭÷፴፩-፵፩).

ማቴዎስ ፫
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
፲፫ ያን ጊዜ ኢየሱስ በዮሐንስ ሊጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ መጣ።
፲፬ ዮሐንስ ግን፦ እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን? ብሎ ይከለክለው ነበር።
፲፭ ኢየሱስም መልሶ፦ አሁንስ ፍቀድልኝ፤ እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና አለው። ያን ጊዜ ፈቀደለት።
፲፮ ኢየሱስም ከተጠመቀ በኋላ ወዲያው ከውኃ ወጣ፤ እነሆም፥ ሰማያት ተከፈቱ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንደ ርግብ ሲወርድ በእርሱ ላይም ሲመጣ አየ፤
፲፯ እነሆም፥ ድምፅ ከሰማያት መጥቶ፦ በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው አለ።

https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
ትምህርተ ወንጌል
Photo
መዝሙር 25
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ አቤቱ፥ መንገድህን አመልክተኝ፥ ፍለጋህንም አስተምረኝ።
⁵ አንተ የመድኃኒቴ አምላክ ነህና በእውነትህ ምራኝ፥ አስተምረኝም፤ ቀኑን ሁሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
⁶ አቤቱ፥ ምሕረትህንና ቸርነትህን አስብ፥ ከጥንት ጀምሮ ናቸውና።
⁷ የልጅነቴን ኃጢአትና መተላለፍ አታስብብኝ፤ አቤቱ፥ ስለ ቸርነትህ ብዛት እንደ ምሕረትህ አስበኝ።
⁸ እግዚአብሔር ቸር ቅንም ነው፤ ስለዚህ ኃጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
⁹ ገሮችን በፍርድ ይመራል፥ ለገሮችም መንገድን ያስተምራቸዋል።
¹⁰ የእግዚአብሔር መንገድ ሁሉ ቸርነትና እውነት ነው። ቃል ኪዳኑንና ምስክሩን ለሚጠብቁ።
¹¹ አቤቱ፥ ኃጢአቴ እጅግ ነውና ስለ ስምህ ይቅር በለኝ።
¹² እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ማን ነው? በሚመርጠው መንገድ ያስተምረዋል።
#ጓደኛ_ያበዛ#መከራ_አበዛ

ለወጣቶች ታላቅ መልእክት ነው

ሁሉን ሰው መውደድ እንጂ ሁሉን ጓደኛ ማድረግ አይቻልም ፤ ደግሞም ተገቢ አይደለም። #ሁሉን ሰው በእኩል ማየት እንጂ ለሁሉ ሰው ጓዳን መግለጥ ተገቢ አይደለም ፤ ደግሞም ጎጂ ነው።

#በሚጠሉህ መሐል ወዳጅህን እንደምታገኘው ፤ ከሚወዱህ መሐልም የሚጠላህን ታገኘዋለህ። ሁሉ ይወደኛል ብሎ የሚያስብ ጅል ብቻ ነው። ሁሉ ይጠላኛል ብሎ የሚያስብም ትላንትን ያልረሳ ነው።

#አንተ ቀድሞ ትጠላቸው የነበሩትን አሁን በጣም ትወዳቸዋለህ ፣ ቀድሞ በጣም ትወዳቸው የነበሩትን አሁን ባሰብካቸው ቊጥር ትታመማለህ። ሰዎችም እንዳንተ ናቸው።

#ሳያውቁህ ሊጠሉህ ይችላሉ፣ ጥላቻ ስሜት ነውና ስሜቱ ሲሄድ እንደገና ይወዱሃል። ይወዱህ የነበሩም ከዓይናቸው ጆሮአቸውን አምነው ሊርቁህ ይችላሉ። #የሄደው ይመጣል ፣ የመጣውም ይሄዳል። በዚህ ዓለም ላይና በሚመጣው ዓለም ቋሚው #መንግሥተ_ሥላሴ_ብቻ ነው።

#እግዚአብሔርን ከማያምኑና እናምናለን ከሚሉ ግብዞች ተጠንቀቅ። #ክርስቲያን ሁነው ጭካኔን የሚለማመዱ እንደ አርዮስ በልብ ክደው በአፍ የሚያምኑ ናቸው። የእነዚህ ሰዎች ወዳጅነት እንደ ፍግ እሳት ነው ፣ ውስጥ ውስጡን ሂዶ መጨረሻ ላይ ያቃጥላል።

ጻድቅ ለመምሰል ከሚሞክሩ ስጦም ውያለሁ፣ #ስጸልይ አድሬአለሁ ከሚሉ ፣ ለወሬ እየነቁ ለቃለ እግዚአብሔር ከሚተኙ ፣ ሌሎችን ሲኰንኑ ከሚውሉ ፣ ለመናገር እንጂ ለመስማት የተፈጠሩ ከማይመስላቸው ሰዎች ጋር ያለህን ወዳጅነት እንደገና መርምረው። #እነዚህ ሰዎች አንተን በተለያየ ነገር ተገዥአቸው ሊያደርጉህ ይፈልጋሉ። ድራማቸውን ከነቃህበት እንደ ጠላት ያዩሃል።

እንባ ሊያበዙ ፣ ተጎዳሁ የሚል ድርሰት ሊያነቡልህ ይችላሉ። የሚናገሩት የተጠና የመከራ ታሪክ አላቸው ፤ ተሳስተው ከሚጎዱህ አልመው የሚጎዱህ እነዚህ ናቸውና ተጠንቀቅ። የአየር ትራፊክ ሠራተኛ ብዙ አውሮፕላኖችን አየር ላይ ደርድሮ አንዱ አንዱን ሳያይ ሲያሳርፍና ሲያስነሣ እንደሚውል እነዚህ ሰዎችም የተለያዩ ወገኖችን ለተለያየ ጥቅም የሚጠቀሙ ስልታዊ ናቸው።

የሚደልሉላቸው ብዙ ሠራተኞች ፣ ጽድቃቸውን እያወሩ የሚከፈላቸው ሎሌዎች አሉአቸውና ተጠንቀቅ።

#የታወቁ ሰዎችን ለማወቅ አትጣር። ከሹም ጋር ለመታየት ጥረት አታድርግ። ከባለጠጎች ጋርም ጊዜ ለማጥፋት አትሻ። ዝነኞችንም በቤትህ ለመጋበዝ አትከጅል።

እነዚህ ሁሉ የነፋስ ጎረቤቶች ናቸውና ሲጠረጉ አብረህ ትጠረጋለህ። በእነዚህ መንደር ስላደረጉት ጀብዱ ስለሚፈጽሙት በቀል እንጂ ስለ ሕይወት አይወራምና ወዳጅነታቸውን አትውደደው። ደግሞም በሩቅም በቅርብም ውብ #እግዚአብሔር ብቻ መሆኑን አትዘንጋ ።

በሥራ ሰነፎች የሆኑ ፣ በየቤቱ እየዞሩ በጸሎት ስም አድማ የሚረጩ ሰዎች አብረውህ ቢቆዩ እንኳ ስለ ሆዳቸው እንጂ ስለ ፍቅር አይደለምና ወዳጆችህን የሚያጠፉብህ እነዚህ ስለሆኑ በቶሎ ሸኛቸው።

#አለዝዘው የሚገድሉ ረጅም ሞት ማለት እነዚህ ናቸው። እምነት የሚመስል ግዴለሽነት ፣ ትዕግሥት የሚመስል ስንፍና እንዳላቸው ልብ በል። #ሥራ ስትላቸው ዋናው ጸሎት ነው የሚሉና ጸሎትን የስንፍና መጋረጃ ያደረጉ ናቸውና ከእነዚህ ዘባቾች ጋር ከቻልህ ጎረቤት አትሁን።

ገለባ እንደማይበቅል ሰነፍም ወዳጅ አይሆንም። አፈ ቅቤ የሆኑትን ተጠንቀቅ። #እግዚአብሔር ተናጋሪውን አሮንን ሳይሆን ኮልታፋውን ሙሴን እንደ መረጠ እወቅ። ተናጋሪ ሰው መጨረሻው ጥፋት ነው።

የሚያቆላምጡህን አትውደድ ፣ የስምህም ጥገኛ ሁነህ የሚያሞካሹህን አትጋብዝ። እነዚህ ሰዎች አዝማሪ ናቸውና ለሞቀበት የሚዘፍኑ ናቸው።

እኔ ብቻ ነኝ ያንተ ወዳጅ የሚሉህንም አትመን። እነዚህ ሰዎች አንተን በማምለክና አንተን የፈጠሩህ በሚመስል ስሜት ያበዱ ናቸው።

#በማምለክ ስሜታቸው ያለ አንተ የሚኖሩ አይመስላቸውም ፣ በመፍጠር ስሜታቸው እነርሱ ሳያውቁ ማንንም እንድትወድ አይፈቅዱም። እነዚህ ሰዎች ፍቅር በሚመስል ነገር በቅኝ የሚገዙህ ናቸውና ተጠንቀቅ።

ራስህን ነጻ ያወጣህ ቀን ለእኔ ካልሆነ ለማንም አይሁን በሚል ስሜት ሊያጠፉህ ይነሣሉ። የጅል ጠብ ማብቂያ የለውምና እባክህ ተጠንቀቅ።

#ለሚያደርሱብህ ጉዳትም ጸጸት አይሰማቸውም። ምክንያቱም በፈጠሩት ላይ የፈለጉትን የማድረግ ስሜት ስለሚሰማቸው ነው። ቆንጥር እንደያዘው ልብስ ቀስ ብለህ ተላቀቅ።

ሌሎችን የሚያዋርዱ ሰዎች አንተን እያከበሩህ ቢቀርቡ አትመናቸው። #ኃይለኛ ውሻ እንኳ የሚወድህ ለሌላ ውሻ ደግነት ስታደርግ ሲያይህ ነው። ይህ ሰው የእኛ ወዳጅ ነው ብሎ አላስቀርብ ያለ ውሻ ይቀርብሃል።

ይለዝብልሃል። ውሻ እንኳ በሌላ ውሻ ከለካህ አንተም ሰውን በሰው ለካው። #ባለጌ የሚሰድበውን ሲጨርስ ወዳንተ ይዞራል። ስድብ ሥራው ነውና። #በተሾምህበት ስፍራ አብሮ አደጎችህን ይዘህ አትሂድ።

በር ዘግተህ ካልሆነም ከአብሮ አደጎች ጋር አትጫወት። #ልክና ዕረፍት ያጣ ወዳጅነትን ተጠንቀቅ። እሳትን የሚያነደው እፍ እንደሆነ ሁሉ የሚያጠፋውም እፍ ነው። ያበዱለት ወዳጅነት አድራሻው እስኪጠፋ ብን ይላል ። ሁሉን በልክ አድርገው። የዓመቱን በዕለት አትሥራው ።

አሰቃቂ ነገርን በራሳቸው ላይ የሚናገሩትን ፣ ራሴን አጠፋለሁ የሚሉትን ሰዎች በጥንቃቄ ተመልከት። #አንዳንዶች ኑሮ ከፍቶባቸው እንዲህ ይላሉና እዘንላቸው።

ሌላውን እስረኛ ለማድረግና ሌላው ሲጨነቅ በመስተዋት እያዩ ለመሳቅ ፣ ሌላውን አንቅተው እነርሱ ለመተኛት እንዲህ የሚሉ ሰውን የኅሊና እስረኛ በማድረግ የሚረኩ ሰዎች እንዳሉ አትዘንጋ ።

#ርኅራኄህን ካገኙት በኋላ ያሰቃዩሃል ። እነዚህ ሰዎች በጣም ራስ ወዳድ ናቸውና ሁሉን ነገርህን እንዳያራቁቱብህ ተጠንቀቅ ።

#እነዚህ ሰዎች አንድ ቀን ቀድመው ባስመዘገቡት እብደት ቤትህንና ኑሮህን ሊያወድሙ ይችላሉ ።

#ለወዳጆችህ እኩል ፊት አሳይ ፣ ለአንዱ ትንሽ ለሌላው ብዙ ነገር አታድርግ። ፍቅር አነሰብኝ የሚለው ጠላትህ ይሆናልና ።



#እግዚአብሔር ከሌለበት ወዳጅነት እግዚአብሔር ያለበት በረሃ የተሻለ ነው ። ስሜትህን ሁሉ አትግለጥ ። ሁሉ በልቡ ይንቅሃል ፣ ወይም እንደ እብድ ያይሃል ።

#ከልክ_በላይም_ድብቅ_አትሁን። አንዳንድ ምሥጢር ሲገለጥ የነፋስ እርግዝና ነው። ነፋስ ሲያረግዙት ያስጨንቃል ፣ ሲወለድ ግን አይጨበጥም። #በሆንከው ደስ ይበልህ። ዕድገትህን ኑሮህን ቀባብተህ አታቅርብ።

እንደውም ተደስተህ ተርከው። የራቀህን ወዳጅ ምክንያቱን ባወቅሁት አትበል ። እርሱ የጨረሰበት ምክንያት አንተን ቂም ያስጀምርሃልና ። ደንበኛ እንኳ ሲሄድ አመስግኖ ነው ። ይህ ከደንበኛ ያነሰ ነውና ተወዉ ።

#የበታችነት ከሚሰማቸው ሰዎች ጋር አትዋል። ምልክታቸው የበላይነት ስሜት ይሰማቸዋል። ዓለም እየታመሰ ያለው በእነዚህ ሰዎች ነው። ዘሬ፣ክብሬ፣ስሜ የሚሉ እነዚህ ሰዎች ናቸው ።

#ጓደኛ አታብዛ መከራህ እንዳይበዛ !!



እግዚአብሔር የሚስፈልገንን ጓደኛ ይስጠን🥰
ወንጌል ከመስማትና ከማንበብ ምን አዘገየን ምንስ አደከመን

እግዚአብሔር ደሙን አፍስሶ ነጻ አወጣን
ጌታችን አምላካችን መድሀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛ በቀላሉ ልናየው የማይገባ እጅግ ትልቅ ነገር ነው ታዲያ ክርስቶስ ይህን በዋጋ የማይተመን እና በዋጋ የማይገለጽ እጅጉን ከባድ ውለታ ሰጥቶናል፡፡

እኛስ ምን ያክል

ተገንዝበናል

ጌታችን በምንም አይደለም የገዛን በደሙ ነው!
ከሲኦል ነጻ ወጥተናል ከባርነት ነጻ ወጥተናል እንደ ሀጢያተኛ ስንቆጠር የነበረበት ዘመን አልፏል መጋረጃው የጥል ግድግዳ በእርግጥ ፈርሷል ታዲያ እኛ በዘመነ ሐዋርያት ጊዜ አባቶቻችን ሐዋርያት የጻፉልን ወንጌል ይህንን ነገር በጉልህ ያስረዳናል ነገር ግን እግዚአብሔር ለብሉይ ኪዳን ሰወች ኦሪቱን በነቢያቱ እጅ አጽፍ በዘመነ ሐዲስ ደሞ ትምህርተ ወንጌልን ካስተማረ ቡሃላ ሐዋርያት ትምህርተ ወንጌልን ሰብከው አስተምረው ወንጌልን ጽፈዋል
እኛ ክርስቶስን የምንረዳበት የድህነታችን(የመዳናችን) ዜና የሆነውን ወንጌል ቅዱስ ወንጌል ጌታችን እጃቸው ውስጥ አስገብቷል ጽፈውታልም፡ማር(16:8).
እኛ ይህነን ወንጌል አንብበን የምናገኘው በረከት በራሱ ብጹዓን ያስብለናል ራዕይ(1:3).
ሌላው አይደለም የሚያነበው ብቻ እራሱ ብጹዕ ይባላል በማለት ቅዱስ ዮሐንስ ይነግረናል፡
ወንጌልን በማንበብ እራሳችን በዋጋ የተገዛን መሆናችንን በጥሞና እንረዳ ነገር ግን እኛ ወንጌልን ከመማር ይልቅ ወንጌልን ከማንበብ ይልቅ የልብ ወለድ እና የፈጠራ ተራ ወሬና ተረት አዘል መጽሐፍ በየ ገበያው በየሱቁ በየትራንስፖርቱ እየገዛን ቅንጭላታችንን ስንበርዝ እንውላለን የሚገርመው እነዚህ መጽሐፍቶች ከነ ደራሲው ሳይቀር የከሌ መጽሐፍ ሁለተኛው አልያም ሶስተኛው ህትመት አልወጣምወይ በማለት ይጠይቃል፡፡ በነገራችን ላይ ይህ ሰው የሐዋርያት ስራ የሚባለውን መጽሐፍ ማን ጻፈው ብሎ አያቅም አንዳንዴም የሐዋርያት ስራ የሚባል መጽሐፍ መኖሩንም ከነ አካቴው አያውቅም፡፡
ነገር ግን የአለም ፈላስፋ የጻፉትን ተረት አንዳንዴም ከሐይማኖት የሚያስወጡትን እርኩሳን መጽሐፍ ለማንበብ አይታክትም የህይወት መሪ የሆነውን ቅዱስ ወንጌል ለማንበብ ይታክታል ወይ ከነ ጭራሹ ፍላጎቱ የተዘጋም አይጠፋም፡፡
ይሕ ነገር የሚመነጨው ከስንፍና እና እያወኩ ሐጢያት ከማደርግ ሳላውቅ ይሻለኛል በማለት የራሱን የቅድመ ሁኔታ እና ሐሳብ ያራምዳል፡፡
በነገራችን ላይ ለማወቅ(ለማንበብ) ፍቃደኛ ባለመሆን እራሱ ሐጢአታችን መሆኑ ተቀምጧል ሮሜ( 1:28).
የህይወት መጽሐፍ ቅዱስ ወንጌልን መማር ማንበብ በረከት እንጅ አለማንበብ እና ለማወቅ ባለመውደድ የሚገኝ ጥቅም የለም፡፡
ቅዱስ ወንጌል የህይወት ቃል እንጅ ሌላ አላማ የለውም ባለማወቅም የሚደረግ ስህተት ከስህተት ይቆጠራልጂ ከስህተት ሐጢአት እና ከመከሰስ አያድንም እንደውም ለማወቅ ባልወደዱት ላይ ቅጣት አለው ሮሜ1:28
አላዋቂነትም ከተጠያቂነት አያስመልጥም ምሳ1:22
ስለዚህ የእግዚአብሔር ወንጌል ሕይወት የሚያድን መንፈስ የሚየድስ ከእግዚአብሔር ሕብረት የሚመጣ ሰይጣንን የሚያቃጥል ጠላት የሚያሳፍር ከክህደትም የሚያስመልጥ የተበላሸ ሕይወትን ወደ ንስሃ የሚያደርስ አንደበተ ክርስቶስ ቅዱስ ወንጌል እስትንፋሰ መንፈስ ቅዱስ የሆነ ቅዱስ ወንጌል ነው ስለዚህ ይህንን ወንጌል በማንበብ ሕይወትን ከተያዝንበት ነገር ነጻ እናውጣ ምክንያቱም ሰው ለተሸነፈበት ነገር ባሪያ ነውና (ቅዱስ ጴጥሮስ(2ኛጴጥ(2:19))).
ያሸነፈን ሱስ ከሆነ የሱስ ባሪያ ነን
ያሸነፈን ዝሙት ከሆነ የዝሙት ባሪያ
ያሸነፈን ክህደት ከሆነ የክህደት ባሪያ
.
.
.
ስለዚህ ለሐጢያት ባሪያ ከምንሆን ለክርስቶስ ልጆች ብንሆንስ?
ልጆች ከሆንን ደሞ ልጅ ያባቱን ይወርሳል (ቅዱስ ጳውሎስ(ሮሜ(8:17))).
Audio
በፍጥረት እሑድ ቀን ምን ተደረገልኝ? ሊቀ መምህራን መምህር ዘበነ ለማ🌷🌹🌹 https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
የእግዚአብሔር ወንጌል የህይወታችን ዓምድ(ምሰሶ) ነው፡፡

..............
የእግዚአብሔር ወንጌል ህይወታችንን የሚቆጣጠር (Control of Life) ዋነኛ መሣሪያ መሆኑን ማወቅ መገንዘብ ተገቢ ነው፡፡
ህይወታችንን በእግዚአብሔር ወንጌል መምራት የምንችለው ግን ከወንጌሉ ጆሮአችንን ከመጽሐፍ ቅዱስ ዓይናችንን ያለመሰልቸት በማንበብ እና በመሥማት የሰሙትን ለማስተዋል መንፈስ ቅዱስን በመለመን ያነበቡትን ወደ ህይወት እንዲቀየር ክርስቶስን በመለመን ጊዜያችንን ለእግዚአብሔር በመሥጠት ሕይወታችንን እግዚአብሔርጋ እና የእግዚአብሔር ወንጌልን መሪ አድርገን መኖር እንችላለን፡፡
ወንጌሉን ስናነብ የኛን የውስጥ ስነምግባር ይነግረናል ይመረምረናል እንድናስተካክል ይረዳናል ከዛ የተሰበረውን እንጠግናለን የተበላሸውንም ሕይወት እናድሰዋለን፡፡
ነገር ግን በዙሪያችን ያሉት ሁከት ፈጣሪወች ህይወታችንን አደጋ ላይ የጣሉት ወይ አደጋላይ ሊጥሉ ጫፍ ላይ የደረሱት ይታገሉናል
ለምሳሌ፡- አንድ ሰው በሆነ አጋጣሚ ቁስል ይቆስላል ቁስሉ ደግሞ መግል ይይዛል ያን መግል ሁል ጊዜ እያፈረጠ ያጥበዋል እናም ከዚህ መግል ተቋዳሽ የነበሩ ዝንቦች ሲታጠብ አይወዱም ነበረ ሲታጠብ ይበሳጩና አያርፉም ቁስሉ ላይ፡፡ እናም አንተን እንደ ዝንቦቹ ያሉ በዙሪያህ ያሉት አንተ እንድትታጠብ ላይፈለጉ ይችላሉ አንተ ንስሃ ገባህ አንተ እራስህን ለካህን አሳየህ ስለዚህ እነሱ ባንተ ላይ ወደ ነበርክበት እንድትመለስ የማያደርጉት ነገር የለም አንተ ግን ምናልባት መጀመሪያ ላይ ከሆነ ተጠንቀቅ ብትችል ቀስ በቀስ አምጣቸው ወደ እግዚአብሔር፡፡
ግን እነሱን በፍጹም እንዳትመስል፡፡ አመጣቸዋለሁ ብለህ እንዳትቀር ይህንም እንዳትዘነጋ ጉድጓድ ውስጥ ላለ ሰው ዱላ ስጠው እንጂ እጅህን አትስጠው የሚባለው ለዚህ ነው አንተን ወደጉድጓዱ ለማስገባት ከፈለገ ዱላውን ለቀቅ አድርገህ ትመለሳለህ እጅህን ከሰጠህው ግን እጅህን ስቦ ጉድጓዱጋ ያስገባሃል፡፡ ለዚህም ነው አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜ የነገርከው ካልሰማ ፈቀቅ በለው (ቅዱስ ጳውሎስ)





https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
“ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው በየውሃት መንፈስ #አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን #ራስህን ጠብቅ።”
— ገላትያ 6፥1

ይሕን ሐይለ ቃል የተናገረው ተወዳጁ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ ነው ለገላቲያ ክርስቲያኖች የተናገረው የጻፈላቸው ተስማምተው እንዲኖሩ በተለይ በቅርብ ስለሚገናኙ ወገኖች ነው።
ከመሃል አንዱ ኢ-ስነምግባራዊ ወይም ጡሩ ያልሆነ ስራ ሲሰራ ብናይኳ ቀድሞ ያለመንቀፍ ልምድ እንድናዳብር እና ከመንቀፍ ተቆጥበን ይህንን ተግባሩን በመልካም እንዲቀይረው ማቅናት(መመለስ) ተገቢ መሆኑን ነው የመከረን ያስማረን የጻፈልን ለኛ ለክርስቲያኖች።
ስለዚህ እህታችን ከመሃላችን ጡሩ ያልሆነ ንግግር ጡሩ ያልሆነ ስራ በአጠቃላይ ኢ-ክርስቲያናዊ ጸባይ ስታሳየን ከመንቀፍ ይልቅ መምከር ወንድማችንም ሲያጠፋ አለማሸማቀቅ መሆን አለበት።
ማሳሰቢያ
መፅሐፍ ቅዱስ የሚነግረን አንድ ጊዜ ሁለት ጊዜ ከነገርከው አንተ ደግሞ እሱን እንዳትመስል ተጠንቀቅ እራቅ ነው የሚለን ቲቶ(3:-11)።
ለምሳሌ:- ብዙ ጊዜ ብልሹ(የተበላሸ) ስነምግባር ያላቸው ወገኖች የነሱ መበላሸት ሳያንስ ደህናውንም ጨምረው ሲያበላሹት የተለመደ ነው።
ለዚህም ነው አንተም እንዳትፈተን ተጠንቀቅ ያለን።
ስለዚህ አመንዝራይቱ እህትሽ አታመንዝሪ ብለሽ ስትመክሪ ደግመሽ ነግረሻትም የማትሰማ ከሆነ እራቂ ምክንያቱም ከእሳት አጠገብ ያለ ማገዶ ሳይማገድ አይቀርምና። ስለዚህ እሷን /እሱን ማስተካከል ካልቻልሽ አንችም እንዳትፈተኝ እንዳትፈተን ፈቀቅ ማለቱ ጡሩ መሆኑን ነው የጻፈልን
በተለይ በተለይ የነሱን ጸባይ እናርማለን እናስተካክላለን በላት የነሱን ጸባይ እንዳንላበስ እንጠንቀቅ ፈጣሪም ያግዘን ይርዳን ቅዳሴ ለምን ቀረህ ጾምስ ለምን... እያልን እየመከርን እኛም እሱን እንዳንመስል እንጠንቀቅ የምንቀራረብበት ልክ እና ገደብ ሊኖረን ይገባል ፈጣሪያችን ይርዳን ቃሉን በድጋሜ እናብበው
👇👇👇
“ወንድሞች ሆይ፥ ሰው በማናቸውም በደል ስንኳ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ያለውን ሰው #በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተ ደግሞ እንዳትፈተን #ራስህን ጠብቅ።”
— ገላትያ 6፥1

https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
“ለእኔ #ሕይወት ክርስቶስ፥
#ሞትም ጥቅም ነውና።”
— ፊልጵስዩስ 1፥21
_***____:

በክርስቶስ ተወዳጅ የሆናችሁ ክርስቲያኖች ሰላማችሁ ይብዛ።
ጌታችን አምላካችን መድኃኒታችን ብርሐን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ከምስጋና ሌላ የምንቸረው ሌላ ስለማይኖረን ከዘላለም እስከዘላለም የተመሰገነ ይሁን አሜን!
እርሱ ከሁሉ በላይ ሆኖ ለዘላለም የተባረከ አምላክ ነው አሜን ሮሜ(9:5).

እንደምናውቀው እና እንደ ምናምነው ጌታችን የህይወት ዋጋ ከፍሎልናል ተይዞ ተገርፎ ተሰቃይቶ ተሰቅሎ ሙቶ ተቀብሮ ከዛም ተነስቶ እኛንም አድኖናል።
ሕይወት ያልነበረን እኛ ሕይወት አግኝተናል የረከስን የነበርን ተቀድሰናል ሙታን የነበርን ሕያው ሆነናል ባሪያ የነበርን ልጆች ሆነናል ልጆች ከሆን ደግሞ ወራሽ ሆነናል ስለዚህ እናመሰግነዋለን እንገዛለታለን እንሰግድለታለን እጣን ወርቅ እና ከርቤ ካመጡለትጋ በቅዳሴ በምስጋና በከበሮ በበገና በማሲንቆ ከመላዕክትጋ አብረን እናመሰግናለን ይህም ሙሉ ስልጣን ተሰጠን ዮሐ(1:12).
እኛን ጌታችን ዝቅ ብሎ ከፍ አድረገን ስለዚህ ከጌታችን እቅፍ ዳግም ዝቅ ለማለት ምን አስፈለገን?
እኛ አንዳች የለለን ስንሆን ሁሉ የኛ ነው 2ኛቆሮ(6:10).
-----***----
ነገር ግን ከአምላካችን እቅፍ ስንወጣ ሁሉ የኛ ሁኖ ምንም እንደሌለን ይሰማናል።
ከእግዚአብሔር እቅፍ የሚያስወጣን ምንድነው?
ብቸኛው መልስ ሀጢያት መሆኑ ግልጽ ነው።
ሀጢያት ደግሞ ሞት ነው ወይም ሀጢአት ሞትን ይወልዳል ያዕቆብ(1:15).
ከአምላካችን ተለይቶ ከመርከስ የበለጠ ምን አይነት ሞት አለ?
እስኪ ሀጢአት ሰርቶ የተደሰተ ማን አለ? ሃጢአት ሰርቶ ያላዘነ ማን አለ? ሀጢአት ሰርቶ ህሊናው ያልወቀሰው ማን አለ? ከሀጢአት መልስ ያላለቀሰ ያልከፋው ማንም የለም። ወይም እየሰራው ያለው ሀጢአት አላለቀ ከሆነ ካለቀ በኋላ ልቅሶ ይተካል።
ቅዱስ ጳውሎስ ለክርስቶስ መሞቴ ለኔ ሕይወቴ ነው። በቃ አከተመ።
ስለዚህ እኛ የሞትነው በእውነት ኢየሱስ እንደዚህ ነው እንደዚህ ነው እያሉ ለሚተቹት ሰዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት ነው? ወይስ በራሳችን ሞትን በመጥራት?
ኢየሱስ አማላጅ ነው በማለት ስለኢየሱስ የተሳሳተ መርዝ ለሚረጨው ለበረሃማው እና ለመርዛሙ እባብ አይ ኢየሱስ የሁሉ አምላክ ነው በማለት መጽሐፍ ቅዱስን በመግለጥ ተገቢውን ምላሽ በመስጠት የምትሞተው ሞት ነውን? ምክንያቱም ለእባቡ አማላጅ ሳይሆን አምላክ የዘላለም አባት የሰላም አለቃ ነው ብለህ ስትመልስ መርዙን ይረጫል ነገር ግን በዚህ መርዝ አትሞትም ማር(16:18).
ሞት ሁለት አይነት ነው።
፩ኛ.ዋጋ የሚያሰጥ ሞት
፪ኛ.ዋጋ የሚያሳጣ ሞት
እነዚህን በደንብ ማየት ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ ስለ ክርስቶስ መሞት ሕይወት ነው ያለው ስለ አምላኩ ትክክለኛ ነገር መስክሮ በፈሪሳውያን ሰዱቃውያን የሚመጣውን ቁጣና ድብደባ ነው።
እኛስ?
ለማመስገን ወደ ቅዳሴ ስንሔድ አትሔዱም አታስቀድሱም በሚለው በሃይማኖታዊ ነገር ነው የሞትነው?
ወይስ ወደ ዝሙት የሚራመዱ እግሮቻችን በዚሁ ምክንያት ሲሰበሩ ነው?
ዛሬ ጤና ሳለን ሙቶ በሕይወት ላኖረን ለክርስቶስ ያልሰገድነው ነገር ግን ላንዲት ጋለሞታ ስንቴ ሰግደናል? ላንድ ተራ ጋለሞታ ስንቴ ሰግደሻል? ዋጋ የሚያሳጣ ሞት ይህ ነውና።
ለኢየሱስ ያልተንበረከከ ጉልበት ለዝሙት ስንቴ ተንበርክኳል?
ኢየሱስ ደሙን የፈሰሰበትን መስቀል አንገታችን ላይ አስረን ስንት ጊዜ አመንዝረናል ኢየሱስ የሞተለትንስ ሰው ስንቴ አስከፍተነው ይሆን?
በደም ዋጋ የተገዛችውን ልጁን በመሥቀሉ ላይ አጥንቱ ድቅቅ እስከሚል በስቃይ የተወለደውን ልጁን ስንት ጊዜ አስከፍተናል አሳዝነናል? ይሕ አይነቱ ሞት ዋጋ አልባ ሞት ይባላል። በሌላ በኩል ኢየሱስ እርሱ እግዚአብሔር ነው አምላክ ነው በማለቷ የሚመጣባት የመወገር የመድቀቅ የመቁሰል ሞት ከሆነ እንደ ጳውሎስ ሕይወትሽ ነው እንጂ ሞትሽ አይደለም። ለኢየሱስ በመንበርከክሽ ስጋሽን ቢጎዱ ነፍስሽን ግን የሚያንበረክክሽ አይኖርም ማቴ(10:28).
ከመላዕክት ከሰማያዊ ቅዱሳን ወገን በመሠለፍሽ አትሞችም።
ለዚህም ነው ለክርስቶስ መሞቴ ህይወቴ ነው ብሞትም ጥቅሜ ነውጂ የሚለን ተወዳጁ ሐዋርያ።
ከእነ ቅዱስ ጊዮርጊስ እምነት ያካፍለን እስከመጨረሻው የጸናው እርሱ ነበርና

https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
አንተ ክርስቶስ ሆይ!

እንፍጠር ያልከው በማይሻር ቃልህ
ልታበጀው ነበር ሰውን እንደመልክህ
እንፍጠር ያልከው በማይነጥፈው ቃልህ
ልትፈጥረው ልትሰራው ነበር በምሳሌህ

ተረዳሁትና ስመለከት መልኬን
የአንተን ሚመስል አጣው ሰውነቴን

እና የቱን ሰው ነው አምላክ የፈጠርከው?
ከአርያም ወርደህ በእጅህ የሰራህው?
እስትንፋስን ሰጥተህ ህይወት የዘራኸው?

>>>ያኔ ስለሐጢያቱ÷

ፊትህ ላይ የተፉት ከዙፋንህ ወርደህ
ፍቅርን ያሳየህው ፍቅር አንተ ሆነህ
ወንጌልን አስተማርክ ፍሬ እንዲያፈራ
በልቡ ዙፋን ውስጥ መልካም ዘር ልትዘራ
በግርግም ተወለድክ በከብቶቹ ስፍራ
ትሕትናን አላብሰህ በፍቅር አስጊጠኸው
አምላካዊ ቃልክን ዞረህ አስተማረከው
በእጅህ ደባብሰህ ሸክሙንም ስታቀል
ዓይኑ ስታበራ ምርኩዙን ስታስጥል
እነሱ ግን ከዱህ ከአንተ ፈቀቅ አሉ
ከሳሾች ሆኑና አንተን ወነጀሉ

የሰማዩ አምላክ የምድሩ ጌታ
ተላልፈህ ስትሰጥ በወንበዴ ፈንታ
በየ አደባባዩ እየተሳለቁ ፊትህ ላይ ተፉብህ
እንደ ሚታረድ በግ እየተሳለቁ ሲወስዱ ሊሰቅሉህ
አንተ በዝምታ ተገፋህ ገረፉህ ሲያሻቸው ተፉብህ
ደግሞም ቀራኒዮ በዚያ በጎልጎታ
አምላክ አንተ ሆነህ የሁላችን ጌታ
ከወንበዴ መሃል ሲሰቀሉህ በደስታ

አልፋና ኦሜጋ መሆንህን ስታወቅው፣
ስለ ሀጢያቱ ፈንታ ደምን የከፈልከው
ከፈጠርከው ሁሉ እሱ ሰው የቱ ነው?

ዛሬም በዚህች አለም
ቋንቋ ብሔር ጎሳ ጥላቻ ያደለበው
ግጭት ሴሰኝነት ርኩሰት ያደለው
በወንድሙ ደስታ ዓይኑ የሚቀላው
ከአንተ ፍቅር ይልቅ ነዋይ ያሰገደው
ሞልቶ በአደባባይ እሱም ሰው ነኝ ይላል።

ታዲያ ዛሬም ያኔም የሰቀለህ ሰው ነው
ገነትን ስታወርሰው ሲዎል የተመኘው!
እሱ ሰው ካልሆነ አንተ የፈጠርከው
አምላክ ሆይ ንገረኝ ሰው ያልከው የቱን ነው?
እንፍጠረው ብለህ  በእጅህ ያበጀኸው ????????
በከበረ ደምህ አንተ የገዛህው
አጥንትህ ተቆጥሮ ጎንህ የተወጋው
ከዙፋንህ ወርደህ ቀኝ እጁን የያዝከው
ትናንትናም ዛሬም የሰቀለህ ሰው ነው።







https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
“እነሆም፥ ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ #ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ”
— ዳንኤል 10፥13

ምስጋና ለእግዚአብሔር ይድረሰው እንደምን ናችሁ ውድ ክርስቲያኖች
ጌታችን አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ለፍጥረቱ እንደሚራራ ሁሉ እንዲሁም ጠባቂ መላእክት ለኛ ያዝልናል የሚያዝልን መላእክት ከመከራ ከጭንቀት ከህመም ከደዌ አጠቃላይ እኛን አደጋ ውስጥ የሚከቱ ነገሮች ፈጥነው ይታደገናል ይረዱናል። ስለዚህም እያንዳንዳቸው በነገድ የተከፋፈሉ ናቸው ቁጥራቸውን ግን እግዚአብሔር ብቻ ነው የሚያቀው ነገር ግን ዕልፍ አዕላፍ እየተባሉ ይጠራሉ ቁጥራቸውን ካለማወቅ የተነሳ ስለዚህም ፯ሊቃነ መላዕክት አሉ ከእነዚህ አንዱ ቅዱስ ሚካኤል ነው። ዳን(፲፪:፩)
የሰማይ ሰራዊት እየተባሉም ይጠራሉ።
“ሚክያስም አለ፦ እንግዲህ የእግዚአብሔርን ቃል ስማ፤ እግዚአብሔር በዙፋኑ ተቀምጦ፥ #የሰማይም ሠራዊት ሁሉ በቀኙና በግራው ቆመው አየሁ።”
— 1ኛ ነገሥት 22፥19
የእነዚህ ሰራዊት (መላእክት) አለቃቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው ይሁዳ(፩÷፱).
ይህ ታላቅ መልአክ እስራኤልን በበረሃ በሐሩር በቁር እየመራ ከግብፅ አውጥቶ ወደ ሐገራቸው አግብቷቸዋል። ቅዱስ ሚካኤል አባታችን ኢያሱን ሊረዳው ሊነግረው በመጣ ጊዜ በግምባሩ ድፍት በማለት ሲሰግድለት አይተናል ኢያሱ (፭÷፲፬)።
ቅዱስ ሚካኤል ለተማጸነው ለተማመነው በረከተ አምላክን ምህረተ አምላክን ከኢየሱስ ክርስቶስ ዘንድ ያሰጠናል ያሳስባል ይሕንም የተደረገላቸው የተደረገልን እናውቀዋለን የእግዚአብሔር መልአክ ከአምላካችን ይቅርታ ይጠይቃል ይቅርም ያስበለናል መፅሐፍ ቅዱሳችንም ይነግረናል።

“የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ፦ አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች #የማትምራቸው እስከ መቼ ነው? አለ።”
— ዘካርያስ (፩÷፲፪)::
ስለዚህ ጥበቃው ፍቅሩ አማላጅነቱ ከኛ አይራቅ አሜን። አጽናኛችንም እሱ ነው

“ነገር ግን በእውነት ጽሑፍ የተጻፈውን እነግርሃለሁ፤ በዚህም ነገር ከአለቃችሁ ከሚካኤል በቀር ማንም የሚያጸናኝ የለም።”
— ዳንኤል 10፥21



.
https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
“መልአኩም መልሶ፦ እኔ በእግዚአብሔር #ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ፥ እንድናገርህም ይህችንም የምሥራች እንድሰብክልህ ተልኬ ነበር፤”
— ሉቃስ 1፥19

እንደምን ሰነበታችሁ ውድ ክርስቲያኖች እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል በዓል አደረሳችሁ አደረሰን አሜን የቅዱስ ገብርኤል አምላክ የኛም አምላክ የድንግል ማርያም ልጅ በቀራኒዮ ለታረደው በግ ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የምስጋና ይድረሰው አሜን።
ከ72ቱ አርድእት መካከል ቅዱስ ሉቃስ የኢየሱስን ወንጌል ለመፃፍ የተመረጠ ደቀመዝሙር ነበረ ይሕ ደቀመዝሙር ከቅዱስ ጳውሎስጋ እየወጣ እየወረደ እንደሚያስተምር እና በሕክምና ስራ ላይ የነበረ እጅግ እጅግ ድንቅ የሆነ ሰው እንደነበረ ቅዱስ ጳውሎስ በመልክቶቹ ጽፎለታል። ቆላ(4:14)
ይሕ ተወዳጅ ከሌሎቹ ወንጌላዊያን ለየት የሚያደርገው አንድ ነገር አለ ይህም ምንድነው?
ኢየሱስ ከመጸነሱ በፊት ከድንግል ማርያም ብስራት ጀምሮ ነበረ ስለ ኢየሱስ የፃፈው ነገርግን ስለ ዮሐንስ መወለድ ከዚህ 6ወር ቀደም ብሎ ካህኑ ዘካርያስጋ መጥቶ እንደነበረ ይታወቃል ነገር ግን የኢየሱስን ፅንሰት ውልደት አስተዳደግ በሚገባ መዝግቦ የምናገኘው ወንጌላዊ ነው። ለዚህም መተርጉማነ ወንጌል የቅዱስ ሉቃስን ወንጌል በላም መስለውታል ይህም ኢየሱስ በከብት በረት መወለዱጋ የተያያዘ ምስጢር ነው።
#በእግዚአብሔር_ፊት የምቆመው ገብርኤል ነኝ።
ብሎ በአንደበቱ የተናገረው እራሱ ቅዱስ ገብርኤል ነው።
በዚህ ቅዱስ ወንጌል የምናገኘው የመጀመሪያው እና ስር መሰረቱን ጠብቆ ለመጻፍ የቻለው ሐዋርያው ቅዱስ ዮሐንስ እንደሚወለድ ለዘካርያስ እየነገረው ነበረ ዘካርያስ ተጠራጠረ እንጂ። የዘካርያስን መጠራጠር እንደ ክፉ መውሰድ የለብንም ምክንያቱም መናፍስት ከየት እንደሆኑ መርምሩ የሚል ቃል ስለ ተቀመጠ። በዚሁ መሰረት ከዘካርያስ በፊት ነቢዩ ኢያሱን እንደማስረጃ መውሰድ እንችላለን ቅዱስ ሚካኤል ሲመጣ በቀጥታ አንተ ከየት ወገን ነህ በማለት ሲጠይቀው እኔ የሰራዊት አለቃ ነኝ ሲለው በግባሩ ድፍት ብሎ ሰገደለት ኢያሱ(5:13-14)።
መጠራጠር መመርመር የታዘዝነው ስለሆነ ችግር የለውም። ለኛ በተለይ ሐሰተኛ ሰው በሚነሳበት ወቅት ሐሰተኛ ነቢይ በሚነሳበት ጊዜ አስፈላጊ ነው።
ቅዱስ ገብርኤል ለኛ ሕይወት አስፈላጊ መልዐክ ነው። ስንሔድ መሪያችን ስንተኛ ጠባቂያችን መልካም ዜና አብሳሪያችን ከዳቢሎስ ከቀደመው እባብ የሚጠብቀን ልመናችንን ይዞ ወደ አምላካችን ፊት የሚያደርስ ደግ መልአክ ነው። በአንድም በተለያየ መልኩ መላእክትን የማትቀበሉ ካላችሁ ስህተተኞች ናችሁ ምክንያቱም ዓለም ሲጀመር በመላእክት መፈጠር ሲጠናቀቅም በመላእክት መለከት መንፋት ስለሆነ በእነዚህ ሁለት ጫፎች ያለመላእክት የሆነ የሚሆን ነገር የለም አይደለም በቁማችን ከሞትን ቡሃላ በትንሳኤ ጊዚ ስለኛ እና የኛን እሬሳ የሚሰበስቡ መላእክት ናቸው ዳን12:1, 1ኛ ተሰሎንቄ 4
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁶ ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና፥ በክርስቶስም የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ፤
¹⁷ ከዚያም በኋላ እኛ ሕያዋን ሆነን የምንቀረው፥ ጌታን በአየር ለመቀበል #ከእነርሱ ጋር በደመና እንነጠቃለን፤ እንዲሁም ሁልጊዜ ከጌታ ጋር እንሆናለን።

ዛሬም ከመላእክትጋ ህብረት እንዳለን በትንሳኤውም ከእነርሱጋ በሕብረት እንሆናለን። ስለዚህ
ቅዱስ ገብርኤል ከአምላክ ምህረት ልመና እና በጌታ ፊት የሚቆም ታላቅ መልአክ ነው።
ጥበቃው እና መሪነቱ አይለየን ቅዱስ መልአክ ከራቀን ደግሞ እርኩስ መልአክ የማይቀርበን ምክንያት የለም። ስለዚህ ነው ቅዱስ መላእክት የማናከብረው ለጋለሞታ እየሰገድን ለገብርኤል አንሰግድም እያልን እንታያለን
ለዝሙት የሚንበረከክ ጉልበት ለገብርኤል አይጎነበስም
ለአላስፈላጊ ነገር ስንዘምር ስንዘፍን ለገብርኤል መዝሙር መስማት እና መዘመር ሐጢአት ሆኖብን በየ አዳራሹ ወንጌል በማጣመም ሲጮሁ እየሰማን ነው። እኛስ እንደ ቅዱሳን አባቶቻችን እንደ ኢያሱ በርከክ ብለን እንሰግዳለን እናከብራለን።
አንድ ጥያቄ መጠየቅ የምፈልገው የትኛው ንጹህ ሰውነት ነው ሲጀመር በገብርኤል ፊት የሚሰግድ? እንደምናየው ዘካርያስ ጻዲቅ ተብሎ ያልቻለው አንተ በአዳራሽ ስትዳራ ስትጮህ መላዕክት ስትሳደብ ሰውነትህ የረከሰ እንዴት ነው በገብርኤል ፊት የምትቆመው? ከድንግል ማርያም ውጭ ማን ሊቋቋመው ቻለ?
ታላቅ ስልጣን ያለው በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ይህ ሐያል መልአክ ነው። ራዕ18:1
እኛም ንጽሕናችን ቢታወቀንም ምህረት ቢያሰጠን ይለምንልን ዘንድ እንጂ እኛ ንጹህ ነን ማለት አይደለም።
ዘካርያስ በገብርኤል ፊት የመቆም አቅሙን ሲያጣ አንተ ግን ገብርኤልን ሰድበህ የሰማይ የምድር ንጉስ ፈጣሪጋ የመቆም አቅሙ ኖረህ ያሳዝናል።

“የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል፥ #ያድናቸውማል።”
— መዝሙር 34፥7

https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
“ኃጢአተኞችን #ሊያድን ክርስቶስ ኢየሱስ ወደ ዓለም መጣ የሚለው ቃል የታመነና ሁሉ #እንዲቀበሉት የተገባ ነው፤ ከኃጢአተኞችም #ዋና #እኔ ነኝ፤”
  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥15

በአብ ስም አምነናል አብን #አባት(ወላዲ) ብለን
በወልድ ስም አምነናል ወልድን #ተወላዲ(ልጅ) ብለን
በመንፈስ ቅዱስ አምነናል መንፈስ ቅዱስን #ሰራጺ ብለን በአካል ሶስት በመለኮት አንድ ብለን ልዩ ሶስት አንድ አምላክ እግዚአብሔር የተመሰገነ ይሁን አሜን።
ልዩ ሶስት ስንል ምን ማለታችን ነው?
በአለማዊ የሒሳብ ስሌት ውስጥ 1+1+1=3 የሚል ሲሆን መልሰን ደግሞ 3ቱን 3-2=1 ካልሆነ በቀር 1 ማድረግ የማይቻል ነው።
የቅድስት ሥላሴን ግን እንደዚህ ባለ ሁኔታ መረዳት አይቻልም 
#ልዪ ሶስት የምንለውም አንድ ስንል እኛ አንድ እንደምንለው አንድ ያለ አይደለም ሶስት ስንልም እኛ ከምናውቀው ሶስትጋ አንድ አይደለም ለዚህ ነው ልዪ ሶስት የምንለው ሶስት ሲሆኑ አንድ የሚሆን አምላክ እግዚአብሔር ልንመረምር የማንችለው ለዚህ ነው። ቀድሞም የውስኑ የፍጡር አእምሮ የማይወሰነውን የፈጣሪውን
ሁኔታ መርምሮ እደርሳለሁ ማለቱ እጅግ የማይቻል ነገር ነው።
_*_*__
ቅዱስ ጳውሎስ ለሚወደውና ለእውነተኛ ልጁ ለጢሞቴዎስ በላከው መልእክት ብዙ አያሌ መልእክት ትምህርት የያዘ ልኮለታል ነገርግን ሐዋርያው በላከው የወንጌል መልእክት
ጢሞቴዎስ የሐሰትን ትምህርት እንዲቃወም እና ትክክለኛውን የወንጌል ትምህርት እንዳይዘነጉ እና እንዳይበርዙ ማስጠንቀቂያም ጭምር ነው።  በመቀጠል ቅዱስ ጳውሎስ የአይሁድን ልበድንዳኔ እና እኔም ከሐጢያተኛ ሰው ዋናው ነኝ በማለት ቀደም ሲል የበደለውን በደል ይነግረዋል። ቅዱስ ጳውሎስ ማለት ጸረ-ክርስቶስ የነበረ ነው 1ኛጢሞ(1:13).ገላትያ(1:13).ሐዋርያት(9:2).ሐዋ(9:13).1ኛቆሮ(15:9).ገላ(1:23).
ነገን ግን እግዚአብሔር ሊያድነን ሲፈልግ ከየትም ጎዳና መልሶ የራሱ አገልጋዮች ማድረግ ይችላል ይሕንም በራሱ ወንጌል ሰባኬ በቅዱስ ጳውሎስ ማየት እንችላለን።
ወንጌል ሲሰበክ ወንጌልን የሚቃወም፣ ዮሐንስ ሲሰብክ ዮሐንስን የሚቃወም ጸረ ሐዋርያ የነበረ ከሐዋርያት ሲመደብ ሰረ ክርስቶስ የተባለ ለዓለም ክርስቶስን የሰበከ...እጅግ የሚደንቅ ተዓምር የተደረገለት የቅዱስ ጳውሎስ ሕይወት ዛሬም በእኛ ጓዳ እያንኳኳ ነው። ከእኛ የሚጠበቀው ጥፋትን አውቆ ይቅርታ መጠየቅ ብቻ ነው።

“አስቀድሞ ተሳዳቢና አሳዳጅ አንገላችም ምንም ብሆን፥ ይህን አደረገልኝ፤ ነገር ግን ሳላውቅ ባለማመን ስላደረግሁት #ምህረትን አገኘሁ፥”
  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥13

*
ስ ጳውሎስ ስለራሱ ሕይወት መጻፍ ፈልጎ ሳይሆን የሚያስተላልፈው ዓበይት ዋና ነጥብ አለ ይህም

“ስለዚህ ግን፥ #የዘላለምን ሕይወት ለማግኘት በእርሱ #ያምኑ ዘንድ ላላቸው #ሰዎች_ምሳሌ #እንድሆን፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ዋና በምሆን #በእኔ ላይ ትዕግስቱን ሁሉ #ያሳይ ዘንድ፥ ምህረትን አገኘሁ።”
  — 1ኛ ጢሞቴዎስ 1፥16

በእውነት ለቃሉ ባለቤት ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ አምላክ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው አሜን

https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
ቆላስይስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
⁴ ሕይወታችሁ የሆነ ክርስቶስ በሚገለጥበት ጊዜ፥ በዚያን ጊዜ እናንተ ደግሞ ከእርሱ ጋር በክብር ትገለጣላችሁ።
⁵ እንግዲህ በምድር ያሉቱን ብልቶቻችሁን ግደሉ፥ እነዚህም ዝሙትና ርኵሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣኦትንም ማምለክ የሆነ መጎምጀት ነው፤
⁶ በእነዚህም ጠንቅ የእግዚአብሔር ቍጣ በማይታዘዙ ልጆች ላይ ይመጣል፤
⁷ እናንተም ደግሞ ትኖሩባቸው በነበራችሁ ጊዜ፥ በፊት በእነዚህ ተመላለሳችሁ።
⁸ አሁን ግን እናንተ ደግሞ ቍጣንና ንዴትን ክፋትንም፥ ከአፋችሁም ስድብን የሚያሳፍርንም ንግግር እነዚህን ሁሉ አስወግዱ፤
⁹ እርስ በርሳችሁ ውሸት አትነጋገሩ፥ አሮጌውን ሰው ከሥራው ጋር ገፋችሁታልና፥
¹⁰ የፈጠረውንም ምሳሌ እንዲመስል እውቀትን ለማግኘት የሚታደሰውን አዲሱን ሰው ለብሳችሁታል፤
¹¹ በዚያም የግሪክ ሰው አይሁዳዊም የተገረዘም ያልተገረዘም አረማዊም እስኩቴስም ባሪያም ጨዋ ሰውም መሆን አልተቻለም፥ ነገር ግን ክርስቶስ ሁሉ ነው፥ በሁሉም ነው።
¹² እንግዲህ እንደ እግዚአብሔር ምርጦች ቅዱሳን ሆናችሁ የተወደዳችሁም ሆናችሁ፥ ምሕረትን፥ ርኅራኄን፥ ቸርነትን፥ ትህትናን፥ የዋህነትን፥ ትዕግሥትን ልበሱ፤
¹³ እርስ በርሳችሁ ትዕግሥትን አድርጉ፥ ማንም በባልንጀራው ላይ የሚነቅፈው ነገር ካለው፥ ይቅር ተባባሉ፤ ክርስቶስ ይቅር እንዳላችሁ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉ፤
¹⁴ በእነዚህም ሁሉ ላይ የፍጻሜ ማሰሪያ የሆነውን ፍቅርን ልበሱት።
¹⁵ በአንድ አካልም የተጠራችሁለት ደግሞ የክርስቶስ ሰላም በልባችሁ ይግዛ፤ የምታመሰግኑም ሁኑ።
¹⁶ የእግዚአብሔር ቃል በሙላት ይኑርባችሁ፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ አስተምሩና ገሥጹ፤ በመዝሙርና በዝማሬ በመንፈሳዊም ቅኔ በጸጋው በልባችሁ ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤
“ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ @እስኪገለጥ ድረስ ያለ እድፍና ያለ ነቀፋ ሆነህ ትእዛዙን #ጠብቅ፤”
— 1ኛ ጢሞቴዎስ 6፥14
“ስለዚህ፥ ወዳጆች ሆይ፥ ይህን እየጠበቃችሁ ያለ #ነውርና ያለ #ነቀፋ ሆናችሁ በሰላም በእርሱ እንድትገኙ #ትጉ፥”
— 2ኛ ጴጥሮስ 3፥14

“የሰላምም አምላክ ራሱ ሁለንተናችሁን ይቀድስ፤ መንፈሳችሁም ነፍሳችሁም ሥጋችሁም ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመጣ ጊዜ ያለ #ነቀፋ ፈጽመው ይጠበቁ።”
— 1ኛ ተሰሎንቄ 5፥23
“ ኢየሱስም፦ እኔም አልፈርድብሽም፤ ሂጂ ከአሁንም ጀምሮ #ደግመሽ ኃጢአት አትሥሪ አላት።”
— ዮሐንስ 8፥11

“ኃጢአተኛውም ካደረጋት ኃጢአት ሁሉ #ቢመለስ ትእዛዜንም ሁሉ ቢጠብቅ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ፈጽሞ በሕይወት ይኖራል እንጂ አይሞትም።”
— ሕዝቅኤል 18፥21
“ኃጢአተኛውም ከሠራው ኃጢአት #ቢመለስ ፍርድንና ቅን ነገርንም ቢያደርግ ነፍሱን ይጠብቃል።”
— ሕዝቅኤል 18፥27
“ከዳተኞች ልጆች ሆይ፥ #ተመለሱ፥ ከዳተኛነታችሁንም እፈውሳለሁ። እነሆ፥ አንተ አምላካችን እግዚአብሔር ነህና ወደ አንተ እንመጣለን።”
— ኤርምያስ 3፥22


ኢዮኤል 2
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹² አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ።
¹³ ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቍጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ።

“ስለዚህ እንዲህ በላቸው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወደ እኔ #ተመለሱ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር፥ እኔም ወደ እናንተ #እመለሳለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር።”
— ዘካርያስ 1፥3



ሕዝቅኤል 18
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
³⁰ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለዚህ እንደ መንገዱ በየሰዉ ሁሉ እፈርድባችኋለሁ፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ንስሐ ግቡ ኃጢአትም ዕንቅፋት እንዳይሆንባችሁ ከኃጢአታችሁ ሁሉ ተመለሱ።
³¹ የበደላችሁትን በደል ሁሉ ከእናንተ #ጣሉ አዲስ ልብና አዲስ መንፈስም ለእናንተ አድርጉ፤ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ስለ ምን ትሞታላችሁ?
³² የምዋቹን ሞት አልፈቅድምና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር፤ ስለዚህ ተመለሱና በሕይወት ኑሩ።


https://hottg.com/Tmhrte_Tewahdo
HTML Embed Code:
2024/06/08 05:35:11
Back to Top