TG Telegram Group Link
Channel: MuhammedSirage M/Nur TextPosts
Back to Bottom
ማረኝ ጌታዬ ሆይ !

ያምና የካቻምና ክምሩን ወንጀሌ
የዛሬን የትላንት የከፋው አመሌ
ሳስታውስ በዛብኝ በረታ ለቀልቤ
አልዘለቅ አለኝ ቆጥሬና አስቤ
የጄን ወንጀል ሳስብ ምላሴ እየመጣ
ያይኔ ሲያቃጥለኝ ደግሞ የግሬ ጣጣ
እጅግ ያስፈራኛል ህልፈቴ እንዳይመጣ
በድፍርስ ተግባሬ በጨቀየ ስራ
ቀብሬን ብጎበኘው ደርሶ የኔ ተራ
ምን ይሆን እጣዬ
የቀብሩ ድርሻዬ
ብዬ ሳሰላስል እጅጉን ጨነቀኝ
ክምሩ ወንጀሌ አሳሞ አማቀቀኝ
አዛኙ ጌታዬ በዝነትህ ጠብቀኝ
አምናለሁ ጌታዬ ባርያህ ነኝ ርካሹ
ስራው ያላማረ ደም ስጋው ብልሹ
…… ባመጽ የቆሸሹ!!
ባበዛሁት ወንጀል ቀልቤ የቆሸሸ
አልጸዳም እያለኝ እየጠቀረሸ
ነኝና ጌታዬ ………
በሰፊው እዝነትህ አውጣኝ ከወንጀሌ
ቀብሩን ሳልገናኝ ሳይነዳኝ አጀሌ
አንተንም ስገናኝ ማረኝ የኔ ጌታ
ተስፋ አይቆረጥም በራሕማን ችሮታ
አቋድሰኝ በዝነትህ ከጀነት ገበታ

በሙሓመድሲራጅ አቡ ዒምራን

https://hottg.com/Muhammedsirage
Audio
ረመዳንን አስመልክቶ አጭር ምክር

ኢኽስላስ ፣ ነብዩን መከተል

hottg.com/Muhammedsirage

የድምፅ ፋይሎችን ለማግኘት👇
hottg.com/Muhammedsiragecom
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
አሏህ ለዚህ ለተከበረ ወር በሰላም አድርሶናል ። ምግብንና መጠጥን በመራቅ ብቻ ሳይሆን ምላሳችንን ከከንቱ ንግግር ፣ አይኖቻችንን ከሐራም በመጠበቅ ረመዷንን እንፁም ።

ዒባዳ ላይ በተቻለ አቅም ለመበርታት እንሞከር ።

ምንኛ ያማረ ወር ነው !!!

ያ ሰላም !!!

https://hottg.com/Muhammedsirage
ከአደብ ተራቁቶ ፣ መኮፈስና ንቀት ከተቆራኘው ዒልም አለማወቅ በብዙ ጣእሙ የተሻለ ነው ።
አማኞችን ቁልቁል መመልከትና መዝለፍ የትኛውንም ወገን አይጠቅምም ። መተናነስና በአደብ ማስተማር መንደርን አሳምሮ ይቀይራል ። ይህንን ነው ከዑለማእ የተማርንው ። በዒልምና በአደብ አካባቢያቸውን ተሻግረው አለምን ለመቀየር ሰበብ ሆነዋል - በአሏህ ፈቃድ ።

አሏህ ዒልምን ከአደብ ጋር ይለግሰን ።

https://hottg.com/Muhammedsirage
ኢንተርኔት !
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ዱንያ እና አኺራ

ይህንን ጎዶሎና ሞት የሚከተለውን የዱንያ ህይወት ለመግፋት የሚደከመው ድካም ፣ የሚከፈለው መስዋእትነት የከበደና የበዛ ነው ።
ድካም ፣ በሽታ ፣ እንግልት የሌለበትን ዘላለማዊ ደስታ ያለበትን የጀነት ህይወት ለማግኘት ግን እንቅልፋችን ረዝሟል ፣ ጉልበታችን ዝሏል ።

ጀነት ውስጥ አይን ተመልክቶት ፣ ጆሮ ሰምቶት የማያውቅና በልቦናችን ውል ብሎ የማያውቅ ፀጋና አስደሳች ነገር አለ ።

ጀነት ውስጥ የማይቋረጥ ፀጋና ደስታ አለ አቃጣይ ሙቀትም ሆነ አንጥቃጭ ብርድ የለም ። የጀነት ሰዎች ጭንቀትም ሆነ ረብሻን አያውቁም ።

ከምንም በላይ ፈጣሪያቸውን አሏህን ያያሉ !!!

መልካም ስራዎችን በመስራትና ሐራም ነገችን በመራቅ ለጀነት እንሽቀዳደም


ወንድሞቼና እህቶቼ ፣

የዱንያ ህይወት የሽንትና የሰገራ ህይወት ነውና አያታለን ። ጠፊ ነውና አይሸንግለን !

https://hottg.com/Muhammedsirage
ጎንደር
-
የአህለ ሱና መስጂድ ላይ ድብደባ የተፈፀመ ሲሆን ውስጥ የነበሩትን ሙስሊሞች ወስደው አስረዋቸዋል።
=
https://hottg.com/IbnuMunewor
Forwarded from كوني زوجة صالحة تقية (S . A .D)
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
مؤثر فقد العلماء - العلامة صالح اللحيدان رحمه الله رحمة واسعة وغفر له
hottg.com/Kunizewjeten1
Audio
አጭር ምክር ለተማሪዎች

🎙በኡስታዝ ሙሐመድ ሲራጅ
https://hottg.com/MedrestuImamuAhmed
https://hottg.com/MedrestuImamuAhmed
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ሶላታችን ከወንጀል ፣ ከክፉ ስራዎች ትጠብቀን ዘንድ በጥንቃቄ እንፈፅማት ።

የዒባዳውንም ጣእም ለማግኘት መስፈርቶችን በመሟላት ተረጋግተን እንስገድ ።

የምንቆመው ለአሏህ ነውና አሯሩጦና አጣድፎ መሰገድ ይብቃ ።

በእርጋታና አሏህን በመፍራት ለመስገድ የቻልንውን ያህል እንታገል - በዚህ ግዜ ( ይህንን ስናደርግ ውጤቱ ጎልቶ ይታየናል ።
hottg.com/Muhammedsirage
ብሄርተኝነት ጣኦት ነው!
~~
* የሃይማኖት አጥር የማይከበረበት፣
* ሙስሊም ወገን የሚታረድበት፣ ንብረቱ የሚነጠቅበት፣ የሚቃጠልበት፣
* "ሃይማኖት አይከፋፍለንም" እያሉ የሚሰበክበት፣
* ጣኦታዊ በአላት የሚታደሙበት፣

አማራነት፣ ኦሮሞነት፣ ትግሬነት፣ አፋርነት፣ ... ወሎየነት፣ ጎንደሬነት፣ ሀረሪነት፣ ወለጋነት፣ ... ጣዖት ነው።

* {እሷ የሸህ ልጅ ናት እኔ የመምሬ
ምን ያስጨንቀኛል ወሎ ተፈጥሬ}
የምትዘፍንበት ወሎየነት ቆሻሻ ነው።
* የእምነት የለሾች ውጤት በሆነችው ሉሲ ላይ ተመርኩዞ "አፋር የሰው ዘር መገኛ" እያሉ በክህደት እንዲጀነኑ የሚያደርግ ብሄርተኝነት ገዳይ ነው።
* ታቦት እስከሚሸኙ፣ መስቀል እስከሚጣዱ፣ ገና እስከሚያደምቁ፣ ... የደረሰ የአማራ ብሄርተኝነት ነቀርሳ ነው።
* ኢሬቻ እስከሚካፈሉ፣ ሙስሊም ወገኖች ዘራቸው እየታየ እስከሚጠቁ፣ ... የደረሰ የኦሮሞ ብሄርተኝነት አጥፊ ነው።
ጥፋት በማንም ቢፈፀም ጥፋት ነው። በዘርና በቋንቋ በሚመስሉህ ሰዎች ስለተፈፀመ ወግነህ አትከራከር።
ወገኔ ሆይ! ከምንም በላይ ኢስላምህን አስቀድም። ያንተ ዘር ከዐረብ አይበልጥም። ዐረብ እንኳ አላህን መፍራት ከሌለው በስተቀር በሌላው ላይ ብልጫ የለውም። ዘርህ ከመተዋወቂያነት ባለፈ ስሙኒ ታክል ዋጋ የለውም። ስለዚህ አትኮፈስ፣ አትሸማቀቅ። ዘርን መሰረት አድርገህ በጅምላ አትውድድ፣ በጅምላ አትጥላ።
ሁሌም አኺራህን አስቀድም። በቃልም በፅሁፍም የዘር ጥላቻ እንዳትቀስቅስ ተጠንቀቅ። ጊዜው የሰው ህይወት የረከሰበት ጊዜ ነው። በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ እጅህ ላይ የሰው ደም እንዳይኖር ፍራ።
=
የቴሌግራም ቻናል
https://hottg.com/IbnuMunewor
ከዐረብ ጥላቻ ጀርባ
~~~~
ድሮ ድሮ ህዝባችን ለዐረቦች ውዴታም አክብሮትም ነበረው። ህዝባችን ሙሐመድ ዐረብ፣ ዐረቡ፣… እያለ ልጆቹን መሰየሙ ለዐረቦች የነበረውን ከፍ ያለ ቦታ አመላካች ነው። እንዲያውም ይህን አክብሮቱን ለክፉ አላማ የሚጠቀሙበት አካላት ነበሩ። "ዐረብ ነን" እያሉ የነገሱበት፣ ያሻቸውን የፈፀሙበት በታሪክ ብዙ ናቸው። ይህ ሁሉ ለዐረቦች ካለው ከፍ ያለ አክብሮትና ግምት የተነሳ ነበር።
ዛሬ ትላንት አይደለም። በዐረብ ጥላቻ የሰከሩ ከሃዲያን ፕሮፓጋንዳ ብዙ ሙስሊሞችን ሸርሽሯል። ዛሬ በዐረብ ጥላቻ ያበዱ ብዙ ሙስሊሞችን እናገኛለን። ሌባው፣ ቀማኛው፣ ዝሙተኛው፣ ፈሪው፣ ጨካኙ ፣ … በቃ ክፋት ሁሉ የተሰባሰቡበት ፍጡር ዐረብ ነው አንዳንዱ ዘንድ። የሃገራችን የኢኽዋን አስተሳሰብም ለዚህ የጥላቻ ተውሳክ የራሱ ድርሻ አለው።
ብቻ ዐረብ እንደማንኛውም ፍጡር ነው። ክፉም ደግም አለው። ክፉዎች በውስጡ ስለኖሩ በጅምላ ልንጠላውም፣ ልናወግዘውም ፍትህ አይደለም። ያውም እኛ! በየትኛው መመዘኛ ነው ከነሱ የምንሻለው? ሌቦቻችን ከሌቦቻቸው፣ ዘረኞቻችን ከዘረኞቻቸው፣ ጨካኞቻችን ከጨካኞቻቸው፣ ፈሪዎቻችን ከፈሪዎቻቸው፣ ባለጌዎቻችን ከባለጌዎቻቸው፣ መሀይሞቻችን ከመሀይሞቻቸው፣… ይበዛሉ ይከፋሉ እንጂ አያንሱም አይሻሉም።
ደጎቻቸው፣ ጀግኖቻቸው፣ አዛኞቻቸው፣ ምሁሮቻቸው፣… ከኛዎቹ የበዙም የበለጡም ናቸው። ይሄ የትላንት ታሪካቸውን ቀርቶ የዛሬ ኑባሬያቸውን በጥልቀት ያስተዋለም በቀላሉ የሚያገኘው ሐቅ ነው። ዐረብ ሃገር ስንቱ ነው በነፃ የሚታከመው? ስንቱ ነው በነፃ የሚማረው? ስንቶች ናቸው በሐጅ ፣ በዑምራ፣ በረመዳን ዘርፈ ብዙ እርዳታዎችን የሚያከፋፍሉት?
በሃገራችንስ በዐረብ ለጋሶች ስንቱ አቅመ ደካማ ፣ የቲም፣ ስንቱ ዱዓትና መሻይኽ ነው የሚደጎመው? ስንት መስጂድና መድረሳ ነው የተገነባው? ስንት መንገድ፣ የውሃ ጉድጓድ፣ የህክምና ተቋም፣ … ተሰርቷል። ከዐረብ ሐገር በመጡ የህክምና ቡድኖችና በዐረብ እስፖንሰሮች እልፍ አእላፍ ህዝብ ታክሟል። በመቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ (ምናልባት በሚሊዮንም ሊሆን ይችላል) በዐረብ ሃገር እየሰራ እራሱን፣ ወገኑን አልፎም ሃገሩን ይህን ያክል ነው ተብሎ በማይገመት መጠን ደጉሟል። ዐረብ ሃገር ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሸሻም ነው። በአረመኔዎች የተሳደደው፣ ለደህንነቱ የሰጋው ሁሉ የሚኮበልለው በአብዛኛው ወደ ዐረብ ሃገር ነው።
እውነቱ ይህ ከሆነ ቅናት ካልሆነ በስተቀር ዐረብን በጅምላ እንድንጠላ የሚያደርገን ምን ምክንያት አለ?! መጥፎ ትርክቶችን እየነቀሱ የሚያራግቡ ምቀኞች ሴራ ሰለባ አንሁን። አዎ ዐረብ ውስጥ የደካማ ሐቅ የሚበላ፣ ለሌሎች ንቀት ያረገዘ፣ ጨካኝ፣ ቦቅቧቃ፣ ክፉ፣ ወዘተ አለ።
የኛስ ሰው ከነዚህ እንከኖች ነፃ ነው? ግብረ ገብነታችን፣ ባህላችን ተንኮታኩቶ የት እንደደረስን እያየንኮ ነው። ኧረ ያገር ቤቱ ይቅር። የኛ ሰው በዐረብ ሃገር ስንት መጥፎ ነገር እየፈፀመ አይደለምንዴ? እርስ በርስ አይገዳደልም? ቪዛ ቆርጦ ለስርቆት የሚኳትን የለም?! አረቄ፣ ሀሺሽ የሚያከፋፍል የለም? የሴት ድለላ ላይ የተሰማራ የለም?! የአገርን ገፅታ የሚያቆሽሹ ሰላም ወዳዱ ሐበሻ የሚሳቀቅባቸው ስንት ጥፋቶች አይፈፀሙም? ልጆቻቸው በሰራተኞች አልተገደሉም? እኛ ስለነሱ እንደምናወራው እነሱም ስለኛ የሚያወሩት ብዙ አላቸው።

ግን ለምንድን ነው የነሱ ጥፋት ገኖ የሚታየን?አዎ ምክንያቱ ወዲህ ነው። ምክንያቱ እነሱን ከፍ አድርገን መጠበቃችን ነው። በዚህ የተነሳ ከኛ ጃሂል የነሱ ጃሂል፣ ከኛ በዳይ የነሱ በዳይ፣ ከኛ ባለጌ የነሱ ባለጌ፣ ከኛ ጨካኝ የነሱ ጨካኝ ይጎላብናል፤ ይገንብናል። የተሻለ ቦታ ስለምንጠብቃቸው እነሱ ዘንድ የሚታየው ጋጠ ወጥነት እኛ ዘንድ ካለው የበለጠ ይረብሸናል። ይሄ እንጂ እውነት እነሱ ከኛ ብሰውም ከፍተውም አይደለም።
ሌሎቻችን ደግሞ የኢስላም ጠላቶች ፕሮፓጋንዳ ሰለባ ሆነናል። በተለያዩ ስልቶች ህዝባችን ውስጥ የዐረብ ጥላቻ እንዲጨምር ሳይታክቱ ይሰራሉ። ከዐረብ የምናገኘውን ጥለው የሚደርስብንን፣ የምንፈፅምባቸውን አልፈው የሚፈፅሙብንን ያራግባሉ። ወደ ዐረብ ሃገራት የሚሰደዱ ዜጎች የሃገርን ገፅታ ከሚያጠለሹ ተግባራት እንዲቆጠቡ ከማሳሰብና ከማስተማር ይልቅ በጥቂት ዐረቦች የሚፈፀሙ ጥቃቶችን ማስጮህ ላይ ይረባረባሉ።
እነሱ ዐረብን ቢያብጠለጥሉ አላማ አንግበው ነው። ብዙ የእምነታችንን እሴቶች የዐረብ ባህል አድርጎ በማቅረብ እየሸራረፉ ከሃይማኖታችን ሊያለያዩን ያምራቸዋል። በፈረንጅ ልብስ እያጌጡ ኢስላማዊ አለባበሳችንን በዐረብ ባህልነት በመፈረጅ ሊያጣጥሉ ይሞክራሉ። በአይሁድ ስም እያሸበረቁ የዐረብኛ ስሞቻችንን ጥለን "እርገጤ"፣ "ጎንጤ" እንድንሆን ያባብሉናል።
ወንድሜ ከያንዳንዱ ጩኸት ጀርባ ያደፈጡ ሴራዎች አሉ። ለወገን በመቆርቆር ስም መቅረባቸው ሽፋን ብቻ ነው። ያኔ ትዝ ይልሀል ወገኖቻችን ተፈናቀሉ ተብሎ ሳር ቅጠሉ ሲቆጭ? በደርግ ጊዜ ስንትና ስንት ዐረብ ንብረቱን ጥሎ ከሃበሻ መባረሩኮ ሩቅ አይደለም። ሁሉንም ልክ ነው ወይም ስህተት ነው ብየ ልመዝን አይደለም። ግን የኛን ቅዱስ የነሱን እርኩስ የማድረጉ አባዜ ሰበቡ ከተራ ጥላቻ ያለፈ ነው።
እንጂማ በሰው ሃገር ሰልፍ የወጣው፣ መኪና የሰባበረው ወገናችን ታፍሶ ሲገባ ምን እንደደረሰበት እናውቃለን። የጠበቀው የአበባ ጉንጉን አልነበረም። በመጣ በወሩ እግሩ በመራው አገር እያቆራረጠ መሰደዱ የሚያስተላልፈው መልእክት ከግልፅም በላይ ነው።
አንዳንድ እራሱን እንኳን የማያውቅ ጥራዝ ነጠቅ አለ። ፀረ ዐረብ እሳቤው ሲሞገት "ዐረቦች ድሮ ነበር እንጂ ዛሬ ዘቅጠዋል" ይላል። "አመድ በዱቄት ይስቃል" አሉ። ማን ያልዘቀጠ አለ?! "ድሮ ድሆች እንጂ ባለጌዎች አልነበራችሁም። አሁን ግን ድሃም ባለጌም ሆናችሁ" ተብሎ በፈረንጅ የተተረተብንኮ እኛ ነን።

ብቻ እርግጠኛ ሁን! ይሄ በሶሪያና በግብፅ ዐረቦች የተጠመቀ አካል አምስት አመት ከቀጠቀጠው ጣሊያን በላይ የትላንት ባለውለታውን ዐረብን የሚጠላበት ምክንያት ኢስላምና ዐረብን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታ አድርጎ በመሳሉ ነው። እትብቱ በተቀበረባት ሃገር ነፃነት የተነፈገው ሙስሊም በዐረብ ድጋፍ እምነቱን እንዳይማር፣ ንቃተ ህሊናውን ከፍ እንዳያደርግ፣ አቅሙን እንዳያጎለብት የሚሰጉ ኃይላት ብዙ ናቸው። እኛን ከወንድሞቻችን ጋር ሆድና ጀርባ ሊያደርጉ የማይፈነቅሉት ድንጋይ የማይምሱት ጉድጓድ የለም። ስለዚህ ንቃ!! ቆም ብለህ ተመልከት። (በመጨረሻም የምነግርህ ቢኖር ከዚህ ፅሁፍ የተረዳሀው "ዐረብ ፍፁም ነው፣ አይሳሳትም፣ …" እንዳልኩ ከሆነ በአረዳድህ ቁንፅልነት ከማዘን ውጭ ምንም ልረዳህ አልችልም።)
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ ግንቦት 29/2011)
የቴሌግራም ቻናል
https://hottg.com/IbnuMunewor
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (كوني زوجة صالحة تقية)
اسلام عليك ورحمة الله وبركاته

ለእውቀት ፈላጊዎች በሙሉ ደስ የሚያሰኝ ዜና
ኢርሻድ ፣ መንሀጅ ሳሊሂን ፣ ሪያዱ ሳሊሂን ሌሎችም በሙሀመድ ሲራጅ ( ሐፊዘሁላህ ) እየተቀሩ ስለሆነ ኑ እውቀትን እንቅሰም ወደ ቻናሎቹ join በሉ ሌሎች ዘንድ ይደርስ ዘንድ ሸር አርጉት ባረከላሁ ፊኩም
hottg.com/Muhammedsirage
hottg.com/Muhammedsirage
👇ሸር 👇
hottg.com/MedrestuImamuAhmed
hottg.com/MedrestuImamuAhmed
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
record.ogg
8.5 MB
ነብዩን መከተልና መታዘዝ

ደሴ የሰለፊዮች መስጅድ ግንባታ ግሩፕ ላይ በቀጥታ የተደረገ ሙሐደራ


https://hottg.com/Muhammedsirage
በድጋሚ የተለጠፈ

የነብዩ ባልደረቦች በብዙ ችግርና ፈተና ውስጥ አለፉ ። በተውሒድና አሏህን በመፍራት የታነፀ ልቦና ነበራቸውና ለከበዱ ነገሮች እንኳን የሚንበረከኩ አልነበሩም ።

ሙስዐብ ኢብኑ ዑመይር ያደገው የተቀማጠለ ኑሮን ከተላመደች ሃብታም እናቱ ዘንድ ነበር ።
የነብዩን ጥሪ በተቀበለ ማግስት እናቱ ጦር ሰበቀችበት ። ወደኔው እምነት ካልተመለስክ “አይንህን ላፈር “ አለቸው! ! የተውሒዱ ጥሪ ልቡ ውስጥ ጠልቋልና አልሰማትም !! ለዛቻዋ ቁብ አልነበረውም ። ከእናቱ ጋር ተቆራረጠ!!
እናም መከራና ችግር ተፈራረቀበት!! በምቾት ያደገ ገላው ተጎሳቆለ! ቆዳው ተሸልቅቆ እስኪረግፍ ድረስ በብርቱ ተንገላታ! ሙስዐብ ዱንያን በአኺራው ለውጧልና የሆዱ ነገር አላሳሰበውም ነበር ! ! አቀማጥላ ካሳደገቸው እናቱ ይልቅ ወደ ኢስላም የጠሩትን ታላቅ ነብይ አስበለጠ! !

መጨረሻም ከሃዲያንን ሲታገል በህይወት እያለ ችላ በማለት የተሰናበታትን ዱንያ በሞት ተሰናበተ ። ቀብር ከመግባቱ በፊት ገላው በበቂ ልብስ ሊከፈን ይገባው ነበር ። ነገር ግን ከራስ እስከ እግሩ ድረስ የሚሸፍን ጨርቅ አልተወም ነበርና ገላውን በከፈን ማዳረስ አልተቻለም ። በነብዩ ትእዛዝ እግሩ ላይ ሳር ብጤ ተደርጎና ሌላው አካሉ በጨርቅ ተከፍኖ ተቀበረ — ያ ጀግና! !
ኢማን ይሏችሇል ይሄ ነው

ምን ሆነናል እኛ ?! ኧረ እናስተውል ጎበዝ! !! ለዱንያ ስንል ሐራምን መዳፈር ፣ ለሆድ አቋምን መለዋወጥና መደበቅ! .......

ግዚያዊና እንስሳዊ ለሆነ ደስታ ወደ ሓራም መመልከት .... ኧረ ስንቱ ከንቱ ነገር ውስጥ ተነክረናል ጎበዝ !! ወደ አላህ እንመለስ! ! አላህ ይመልሰን! !!
ይድረስ ለወይዘሪት አ - ሕ - ባ - ሽ
ይዘገያል እንጂ አህያ የጅብ ነው!!
~~ ~~~~
በናንተ ምክኒያት ስንት ኢስላማዊ ተቋም ተዘጋ? ስንቱ ተደበደበ? ስንቱ ታሰረ? ስንቱ ሀገሩን ጥሎ ተሰደደ? ስንት የደዕዋ እንቅስቃሴ ተገታ? ስንትስ ቤተሰብ ተናጋ? ከምንም በላይ ደግሞ በኢስላም ስም ስንት የተበላሸ ዐቂዳ ደካሞች ላይ አሰረፃችሁ? ኢስላምን ስንት አመት ወደ ኋላ ለመጎተት እየተውተረተራችሁ እንደሆነ ለማንም አይሰወርም - ለካ * ፊ & ር እንኳን፣ ለናንተ ሲቀር፡፡ እናንተማ ከሰል ጠቆረ ውሃ ቀጠነ ብላችሁ የምትከራከሩ ናችሁ፡፡ እናንተ'ኮ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው፤ የነካውም ሰው አወቀም አላወቀም ሶላቱ ውድቅ ነው” የምትሉ ናችሁ፡፡ ሀሰት ካላችሁ ኪታባችሁ ይናገራል፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 87(ሁለተኛ እትም፡ 119)) እንዴት ያለች “ፅድት” ያለች እምነት ነችi የዝንብ ጡሃራ አይነት እንዳትሆን ብቻ። “የዝንብ ጡሃራ ከነጃሳ እኩል ነው” ትል ነበር እህቴ፡፡ አባባሉን ከየት እንዳመጣችው አላውቅም፡፡ ብቻ ሳስታውስ አጓጉል የሆነ ንፅህና ስታይ ነበር እንዲህ የምትለው፡፡ ግን አ - ሕ - ባ - ሽ “ጡሃሪት” በነጃሳ ያውም በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል ትላለች፡፡ (ቡግየቱ ጧሊብ፡ 99 - 100 (አዲሱ እትም፡ 131-132))፡፡
እኔን የገረመኝ “የትኋንና የቅማል ደም ነጃሳ ነው” ማለታቸው አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ “በውሻ ኩስ፣ ሽንትና ልጋግ ተጨማልቆ መስገድ ይቻላል” ማለታቸውም አይደለም፡፡ ምንም እንኳን የሚገርም ቢሆንም፡፡ እኔን የገረመኝ የሚገርመኝም ሁለቱ የተራራቁ ሀሳቦች ከአንድ አካል መውጣታቸው ነው፡፡ እስኪ አስቡት “የውሻ ኩስ አይነጅስም” ያለ ሰው “የትኋን ደም ይነጅሳል” ይላል? ኧረ ተመስጌን በሉ። “ምራቋም ይነጅሳል” ብለው የካ * ፊ & ር መሳለቀያ ቢያደርጉን ምን ይባል ነበር? ሞኝ ባያፍር የሞኝ ዘመድ ያፍር፡፡
ለነገሩ እንዲያው ቢገርመኝ አነሳሁት እንጂ ከዚህ የከፋ ስንት የዐቂዳ ክፍተት አለባቸው አይደለም ወይ? ለምሳሌ “አላህ አለም ውስጥም የለም፣ ከአለም ውጭም የለም፣ ከአለም ጋር ተያይዞም የለም፣ ተነጣጥሎም የለም” የሚሉት፡፡ ሱብሐነላህ! ሰዎቹ ምን እየሆኑ ነው? ይሄ ምን ማለት ነው? ይሄ ብቻ አይደለም “አላህ በሁሉም ነገር ላይ ቻይ አይደለም” ይላል ሸይኻቸው አብደላህ አልሀረሪ፡፡ ምነው ስትሉ “ለምሳሌ አላህ መበደል አይችልም” ሲል ይፈላሰፍባችኋል፡፡ እናስ አላህ ስላቃተው ነው እንዴ የማይበድለው? ፍትሃዊ ስለሆነ እንጂ፡፡ ይሄውና በሐዲሠል ቁድሲ ላይ፡- “ባሮቼ ሆይ! እኔ በራሴ ላይ በደልን ክልክል አድርጊያለሁ፤ በናንተም መካከል እንዲሁ ክልክል አድርጌዋለሁና አትበዳደሉ” ይላል ጌታችን፡፡ ስለዚህ ስለሚችል አይደለም እንዴ በራሱ ላይ ክልክል ያደረገው? ባይችል እንዲህ ይል ነበር? ኧረ እነኚህ ሰዎች በምንኛ ነው የሚያስቡት?
ይሄን ሁሉ እያደረጉ ከማንም በላይ ለኢስላም እየሰሩ እንደሆነ ይነግሩናል፡፡ ድንቄምi “ጊዜ የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል” ነውና ነገሩ ይሄው ለጊዜው የሚችሉትን ብቻ ሳይሆን ከጉልበተኛ ተጠግተው የማይችሉትንም ጭምር እያደረሱ ነው፡፡ “ውጭ ካለ መቶ ጠላት ቤት ውስጥ ያለ አንድ ጠላት የከፋ ነው” ይላሉ ዐረቦች፡፡ ጥፋታችሁ ምንኛ ከፋ?! ይሄ አቋማችሁ ድንገት አንድ ቀን ተሳስታችሁ ካሰባችሁ ያሳፍራችኋል፡፡ ምናልባት ካሰባችሁ።
ኧረ አላህን ፍሩ! ሞት አለ፣ የቀብር ጥያቄ አለ፣ ነገ አላህ ፊት መቆም አለ፣ ሲራጥ አለ፣….፡፡ ከውስጣችሁ አላህን የሚፈራ የለምንዴ? ለነገሩ ይሄ ቋንቋ መቼ ይገባችኋል? ጨው ቀምሳችኋላ! ምነው “አልገባንም” ብላችሁ ዝም ባላችሁ!!! ገልብጣችሁ መረዳታችሁ ከፋ እንጂ፡፡
ግን ቢገባችሁም ባይገባችሁም ወላሂ ወቢላሂ ወተላሂ ትሸነፋላችሁ! እርግጠኛ ሆኜ ነው የምናገረው! እየጠነቆልኩ አይደለም፡፡ በጥንቆላም በኹራፋትም አላምንም፡፡ ይቺ የናንተ ናት፡፡ እናም እላለሁ፡፡ አይወድቁ አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ሰማያዊ፣ መለኮታዊ መመሪያ አንብቤ ነው ይህን የምለው፡፡ ኢስላምን ሊያጠቃ የመጣ የውስጥም ይሁን የውጭ ጠላት መቼም ቢሆን ቋሚ ድል ሊቀናው አይችልም፡፡ ይሄው አብረን እናንብብ፡-
{ یُرِیدُونَ أَن یُطۡفِـُٔوا۟ نُورَ ٱللَّهِ بِأَفۡوَ ٰ⁠هِهِمۡ وَیَأۡبَى ٱللَّهُ إِلَّاۤ أَن یُتِمَّ نُورَهُۥ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡكَـٰفِرُونَ (32) هُوَ ٱلَّذِیۤ أَرۡسَلَ رَسُولَهُۥ بِٱلۡهُدَىٰ وَدِینِ ٱلۡحَقِّ لِیُظۡهِرَهُۥ عَلَى ٱلدِّینِ كُلِّهِۦ وَلَوۡ كَرِهَ ٱلۡمُشۡرِكُونَ (33) }
((የአላህን ብርሃን በአፎቻቸው ለማጥፋት ይፈልጋሉ፡፡ አላህም ከሓዲዎች ቢጠሉም እንኳ ብርሃኑን መሙላትን እንጅ ሌላን አይሻም፡፡ እርሱ ያ አጋሪዎቹ ቢጠሉም መልክተኛውን (ሙሐመድን) በቅን መንገድና በእውነተኛ ሃይማኖት ላይ ከሃይማኖት ሁሉ በላይ ይፋ ያደርገው ዘንድ የላከው ነው፡፡
[አሶፍ፡ 32-33]

ታማኙና እውነተኛው ነብይም ዐለይሂ ሶላቱ ወሰላም እንዲህ “ውርደትና የበታችነት ትእዛዜን በጣሰ ላይ ይሁን” ብለዋል።
በርግጥ ብዙ መስዋእትነት ታስከፍሉ ይሆናል፡፡ ቢሆንም ዲኑ ብዙ ሊከፈልለት የሚገባ ዲን ነውና ወደ ኋላ አንልም፡፡ በአላህ ፈቃድ ትወድቃላችሁ፡፡ እንዲያውም የሮማን አወዳደቅ ነው የምትወድቁት፡፡ ታዲያ አትሰሙም እንጂ ወድቃችሁ መውደቃችሁ ላይቀር መፈራገጥ ባታበዙ መልካም ነበር፡፡ “የማይበስል ጭንቅላት መብሰሉ ላይቀር የሰው ማገዶ ያስጨርሳል።”
-
ማሳሰቢያ፦
ከላይ ምንጭ እያያዝኩ የጠቀስኳቸውና ሌሎችም የአ - ሕ - ባ - ሽ ጥፋቶች የኋላ እትሞች ላይ ከፊሎቹን ገፅ በመቀየር ከፊሎቹን ደግሞ ከነ ጭራሹ በማውጣት አስወግደዋል። ታዲያ ካጠፉ ለምን ይነሳል? እንዳይባል "ስህተት ነበር ታርሟል" በማለት ፋንታ ሽምጥጥ አድርገው "ተዋሽቶብን ነው" እያሉ ነው።
=
(ኢብኑ ሙነወር፣ መስከረም 10 / 2005)
የቴሌግራም ቻናል፦
https://hottg.com/IbnuMunewor
Forwarded from የሙሀመድ ሲራጅ የድምፅ ፋይል የሚሰራጭበት ቻናል (كوني زوجة صالحة تقية)
1 . አል ቀዋዒዱል ሙስላ
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/7

2 . መሳኢል ጃሂሊያ 1 እስከ 20
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/17

3 . ዓቂደቱ ተውሂድ 1 እስከ 70
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/38

4 . አቂደቱል ዋሲጢያ 1 እስከ 26
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/109

5 . ኡምደቱል አህካም 1__ 31
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/136

6 . ኩን ሰለፍየን አለል ጃዳ
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/168

7 . ሶስቱ መሰረቶች ( الأصول الثلاثة )
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/201

8 . ሚን ኡሱሊ አቂደቲል አህሉል ሱና ወልጀማዓ
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/215

9 . እስልምናን የሚያፈርሱ (نواقض الإسلام )
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/222

10 . ከሽፉ ሹበሃት كشف الشبهات
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/228

11 . ነዋቂዱ አልኢስላም
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/241

12 . ሙቀዲመቱል አጅሩምያ
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/249

13 . ኪታቡ ሲያም ) ( كتاب الصيام)
ዑምደቱል አህካም عمدة الأحكام
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/273

14 መሳኢሉል ጃሂሊያ ከክፍል 1____17
https://hottg.com/Muhammedsiragecom/295

የድምፅ ፋይሎችን ለማግኘት ቻናሉን ይቀላቀሉ ለሌሎች ይደርስ ዘንድ ሸር ያርጉት
👇 ባረከላሁ ፊኩም 👇
hottg.com/Muhammedsiragecom
hottg.com/Muhammedsiragecom
hottg.com/Muhammedsiragecom
HTML Embed Code:
2024/04/29 13:41:29
Back to Top