TG Telegram Group Link
Channel: MuhammedSirage M/Nur TextPosts
Back to Bottom
የወር አበባ ላይ ያለች ሴት መስጂድ ውስጥ መግባት ትችላለች?
~~~~~~~~~
የወር አበባ ይ ያለች ሴት መስጂድ መግባን በተመለከተ በዑለማእ መካከል ልዩነት መኖሩ የሚታወቅ ነው። አብዛኞቹ የሚከለክሉ ቢሆኑም የሚፈቅዱት ዓሊሞች አቋም ከመረጃ አንፃር የበለጠ ጥንካሬ እንዳለው ስላመንኩኝ እሱን አቀርባለሁ። እዚህ ላይ ተርጉሜ ያቀረብኩት የሸይኽ ሙሐመድ ናሲሩዲን አልባኒን ረሒመሁላህ ፈትዋ ሲሆን ለተጨማሪ ማብራሪያ የሸይኽ ፈርኩስን ፈትዋ ሊንክ አያይዣለሁ። ወደ ፈትዋው:–

ጥያቄ:— የወር አበባ ላይ ያለች ሴት መስጂድ ውስጥ መግባት ትችላለች?

መልስ:– አዎ ይፈቀዳል። ምክንያቱም የወር አበባ ሴትን የእውቀት ማእዶችን— በመስጂዶች ውስጥ ቢሆኑ እንኳ— እንዳትካፈል አይከለክልምና። በወር አበባ ጊዜ የሴት መስጂድ ውስጥ መግባትን የሚከለክል ማስረጃ የለምና። ይልቁንም ከዚህ በተቃራኒ መፈቀዱን የሚያመለክት ነው ያለው።
ከነዚህም ማስረጃዎች ውስጥ ሁለት የእመት ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ሐዲሦች ናቸው።

አንደኛ:— ከነብዩ ﷺ ጋር ሐጅ ስታደርግ ለመካ በቀረበ ‘ሰሪፍ’ የሚባል ቦታ ስትደርስ የወር አበባ ገጠማት። ነብዩ ﷺ ሲገቡ እያለቀሰች አገኟት። "ምን አገኘሽ? የወር አበባ አየሽ?" አሏት። "አዎ የአላህ መልእክተኛ ሆይ!" አለች። "ይሄኮ አላህ ዐዘ ወጀል በሴት ልጆች ላይ የደነገገው ነው። ጦዋፍ እንዳታደርጊ እንዲሁም እንዳትሰግጂ እንጂ ሐጅ የሚያደርግ ሰው የሚያደርገውን ሁሉ ፈፅሚ" አሏት።

በዚህ ሐዲሥ ውስጥ ማስረጃችን ነብዩ ﷺ ከመስጂዶች ሁሉ በላጭ በሆነው መስጂድ እንዳትገባ አልከለከሏትም። እርሱም አልመስጂደል ሐራም ነው። ይልቁንም የከለከሏት ሶላትንና በቤቱ መዞርን (ጦዋፍን) ነው። ይህም ነብዩ ﷺ መስጂደል ሐራም ውስጥ እንድትገባ እንደፈቀዱላት ማስረጃ ነው። ነገር ግን ሶላትንና በቤቱ መዞርን (ጦዋፍን) ከልክለዋታል። … ይ እንግዲህ የወር አበባ ላይ ላለች ሴት መስጂድ ውስጥ — የትኛውም መስጂድ ቢሆን— መግባቷን የሚፈቅድ ሐዲሥ የመጀመሪያ ሐዲሥ ነው።
ከመስጂደል ሐራም ውጭ ያለ ሲሆን ደግሞ ብይኑ ይበልጥ የተፈቀደ ነው ማለት ነው። ምክንያቱም ነብዩ ﷺ እመት ዓኢሻን የወር አበባ ላይ እያለች መስጂደል ሐራም እንድትገባ ፈቅደውላታልና። ከሶላትና በቤቱ ከመዞር (ከጦዋፍ) በስተቀር አልከለከሏትም። ስለሆነም ከመስጂደል ሐራም ውጭ ያሉ መስጂዶች ብይን በበለጠ የተፈቀደ ነው።

ሁለተኛው ሐዲሥ ደግሞ አሁን እንደጠቆምኩት እርሱም የእመት ዓኢሻህ ረዲየላሁ ዐንሃ ዘገባ ነው። የመጀመሪያው ሐዲሥ ሶሒሕ አልቡኻሪ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ሁለተኛው ሐዲሣችን ደግሞ ሶሒሕ ሙስሊም ውስጥ የሚገኝ ነው።
"ነብዩ ﷺ ‘መስገጃዋን አቀብይኝ’ ሲሉኝ ‘የወር አበባ ላይ ነኝ’ አልኳቸው። ‘የወር አበባሽኮ እጅሽ ላይ አይደለም’ አሉ።"
እዚህ ላይ የወር አበባ ሲባል የተፈለገው የወር አበባውን ደም ነው። የወር አበባ ደም ያለ ጥርጥር ነጃሳ ነው። የወር አበባ ላይ ያለችዋ ሴት ግን ነጃሳ (የከሰች) አይደለችም። ከየትኛውም ሰው ነጃሳ መውጣቱ ሰውየውን እራሱን ነጃሳ አያደርገውም። ደግሞም የወር አበባ ላይ ያለች ሴት የዒልም (እውቀት) ጉባኤዎች ላይ መሳተፍ ትችላለች።
ሌላ ጠያቂ:– አሰላሙ ዐለይኩም
ሸይኽ:— ወዐለይኩም አሰላም። እነዚህ ጉባኤዎች በአላህ ተባረከ ወተዓላ ቤቶች (መስጂዶች) ውስጥ ቢሆኑ እንኳ ማለት ነው። በነዚህ ሁለት ትክክለኛ ሐዲሦች መሰረት ብይኑ የተፈቀደ ይሆናል። በዚህ ላይ የሚጨመረው "በነገሮች ላይ መሰረቱ ፍቁድነት ነው" የሚለው እና "መሰረቱ ከተጠያቂነት ነፃ መሆን ነው" የሚሉት ዑለማዎች ዘንድ ታዋቂ የሆኑት መርሆዎች ናቸው። ይህም እነዚህን ሁለት መርሆዎች የሚፃረር ማስረጃ እስከሚኖር ድረስ ነው። ከነዚህ ሁለት መሰረቶች ጋር የሚገጥም ማስረጃ ሲኖር ግን እንዴት ሊሆን ነው? በዚህም የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች ሃይማኖታዊ ትምህርቶችን ለመከታተል፣ ቁርኣን ለማዳመጥ እና ለመሳሰሉት መስጂድ መግባታቸውን አስመልክቶ ለቀረበው ጥያቄ "ይችላሉ" የሚል እንደሆነ ምላሹ በዚህ ይጠናቀቃል።
ጠያቂ:— ሶሒሕ ሙስሊም ውስጥ በሚገኝ ሐዲሥ ላይ ነብዩ ﷺ "(የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች) ከመስገጃው ገለል ይበሉ" እንዳሉ ኡሙ ዐጢያህ ጠቅሳለች። (እንዴት ነው?)
ሸይኽ:— አዎ። "እንዳይሰግዱ" ማለት ነው። ይሄ "ሐጅ ላይ ያለ ሰው የሚያደርገውን ሁሉ አድርጊ። ባይሆን ጦዋፍ እንዳታደርጊ ። እንዳትሰግጂም" የሚለው የመጀመሪያው የዓኢሻ ሐዲሥ አይነት ነው። የወር አበባ ላይ ያሉ ሴቶች የሙስሊሞች መስገጃ ዘንድ እንዲገኙ፣ ትምህርታቸውንና ህብረታቸውን እንዲታደሙ ታዘዋል። ነገር ግን በሶላታቸው ላይ አይጋሯቸውም።
ጠያቂ:– አላህ መልካምን ይመንዳችሁ።
ሸይኽ:— እናንተንም።

ምንጭ:— [ሲልሲለቱል ሁዳ ወኑ፞ር: ካሴት ቁጥር 623]

ለተጨማሪ ማብራሪያ በዚህ ሊንክ ገብተው የሸይኽ ሙሐመድ ዐሊይ ፈርኩስን በሳል ትንታኔ ይመልከቱ።
في حكم دخول الحائض المسجدَ | الموقع الرسمي لفضيلة الشيخ أبي عبد المعز محمد علي فركوس حفظه الله
https://ferkous.com/home/?q=fatwa-35
~~~~~
Ibnu Munewor (ኢብኑ ሙነወር)
የቴሌግራም ቻናል። ይቀላቀሉ። ሌሎችንም ይጋዙ።
https://hottg.com/IbnuMunewor
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ወንጀል ፣ መሃይምነት እና ኢልሓድ በበዛበት በዚህ ዘመን ሙስሊሙን ማህበረሰብ የምንይዝበት መንገድ ጥንቃቄ እና እዝነት የተሞላበት ሊሆን ይገባዋል - የቢድዓ እና የጥመት መሪዎችን አጥብቀን ከመታገላችን ጋር ! እነዚህ የጥመት ምሠሦዎች የጥፋትን በር ሁሉ በሙስሊሞች ላይ ይከፍታሉና የሚገባቸውን ሊያገኙ ተገቢ ነው !
ተራውን አላዋቂ ማህበረሰብ ከነኚህ ጋር ደባልቆ መውቃት ግን ፍትህ አይሆንም !

https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from ⚘ሱና የኑሕ መርከብ ናት قناة السنة سفينة نوح (كوني زوجة صالحة تقية)
እውቀትን ማሰራጨት

ታላቁ ዓሊም ሸኽ ሷሊህ አሊ አሸይኽ እንድህ አሉ;

ታላቁ የአሏህን ጠላቶችና ሸይጧንን የምትዋጋበት/የምትታገልበት እውቀትን ማሰራጨት ነው በየትኛውም ቦታ በምትችለው/ባቅምህ ልክ አሰራጨው(እውቀትን)
አልወሷያ አልጀሊያ (ገፅ 46)
hottg.com/Menhaj_Salafiya
ኢስቲቓሣ እና ዱዓእ
Muhammedsirage M.Nur
በእኛ እና በአሕባሾች መካከል ክፍል 3

ታላቅ ርእሰ !

"ኢስተቓሣ እና ዱዓእ"

የአህሉሱና አቋም ምን ይመስላል?

የአሕባሾችና የመሰሎቻቸውሥ?

በርእሱ ላይ የሚያቀርቧቸው ሹብሃዎች (ማደናገሪያዎች) ከበቂ መልሦቻቸው ጋር!!!
https://hottg.com/Muhammedsirage/1967
አኽላቃችንን እናስተካክል
አቡ ዒምራን
አኽላቃችንን እንናስተካክል

ሱናን የምንከተል ሁሉ :-

ስራችን ንግግራችን ሊፀዳ ይገባል !

ውሽት ማጭበርበር እኛ ላይ ሊታይ አይገባውም !


https://hottg.com/Muhammedsirage
በድሩ ሑሴን ሆይ! ምን እያልክ ነው?
~ ~ ~ ~ ~ ~ ~
በቅርቡ አንዱ “የአይነላህ ተቆርቋሪዎች” እያለ በነብዩ ﷺ ሐዲሥ እና በትልቅ የሙስሊሞች ዐቂዳ ላይ ሲሳለቅ አይተናል። ለዚህ አደገኛ ንግግር እርምት እንደመስጠት አንዳንዶች “ጣሊያን ነው የተማረው”፣ “የታሪክ መፅሐፍ ፅፏል”፣ “አንባቢ ነው”፣ “የሸይኽ ልጅ ነው” የሚሉ አስቂኝ መከላከያዎችን ሲያቀርቡለት ነበር። በጎን ትክክለኛውን ዐቂዳ የሚያስተምሩ ሰዎች ላይ በዚህ መልኩ የማሸማቀቅ ስራ ይሰራሉ። በዚህም ከቡድናዊ ሽኩቻ ውጭ የሆኑ በመምሰል የዋሃንን ይሸውዳሉ። በሌላ በኩል ደግሞ ከስር ተያይዞ እንደምታዩት አሕባሾች የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ለማስተባበል በሚሰብኩበት መልኩ ይሰብካሉ። ይሄ ሰውዬ ከዚህ በፊት “መውሊድ አይለያየንም” ሲል እንደነበር ይታወሳል። ያኔም ከ0ቂዳቸው ይልቅ ለግለሰቦች ይበልጥ የሚሟገቱ ሰዎች ሲከራከሩለት ነበር። ዛሬም ተመሳሳይ ጫጫታ እንደሚኖር እገምታለሁ። ቢሆንስ? መቼም “ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም።” ልክ እንዲሁ የነሱን ጫጫታ ፈርተን ከ0ቂዳችን ለመከላከል የምናፍርበት ምክንያት ሊኖር አይችልም። ይህንን ቪዲዮ ዉስጥ ላይ እንደምታዩት አሕባሾች እያራገቡት ነው። በድሩ ሑሴን የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ከአሕባሾች በተለየ የሚያፀድቅ ከሆነ አሻሚነት የሌለው፣ የሌሎች መጠቀሚያ ያልሆነ ግልፅ ምላሽ ሊሰጥ ይገባዋል። ያለበለዚያ "በቦታም፣ በጊዜም የተገደበ አይደለም ማለት ነው የፈለገው" የሚለው በቂ ማመሀኛ አይደለም። ምክንያቱም አሕባሾችም እንዲህ እያሉ ነውና ከዐርሹ በላይ መሆኑን የሚያስተባብሉት። እየተጠቀመበትም በገሃድ እያየን ነው።
በነገራችን ላይ “አላህ ከቦታም፣ ከጊዜም ወሰን ውጭ ነው” በሚል ሸዋጅ ቃል ጀርባ እያደፈጡ ከዐርሹ በላይ መሆኑን ማስተባበል የጥንቶቹ ጀህሚያዎች አካሄድ ነው። ጀሪር ብኑ ዐብዲል ሐሚድ (188 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
كَلَامُ الْجَهْمِيَّةِ أَوَّلُهُ عَسَلٌ وَآخِرُهُ سُمٌّ وَإِنَّمَا يُحَاوِلُونَ أَنْ يَقُولُوا لَيْسَ فِي السَّمَاءِ إِلَهٌ
“የጀህሚያ ንግግር መጀመሪያው ማር ነው። መጨረሻው ግን መርዝ ነው። የሚጥሩት በሰማይ አምላክ የለም ለማለት ነው።” [ደርእ፡ 6/265] [አልዑሉው፡ ቁ. 111] [አልጁዩሽ፡ 2/220]
“መጀመሪያው ማር ነው” ያሉበት ምክንያት ልክ ዛሬ አሕባሾች እንደሚያደርጉት በተውሒድና አላህን በማጥራት ስም ያቀርቡት ስለነበሩ ነው።
ለማንኛውም “አላህ ከዐርሹ በላይ ነው” የሚለው ዐቂዳ የቀደምት ታላላቅ ዑለማዎች ኢጅማዕ ያለበት እምነት ነው። ለናሙና ያክል የጥቂቶቹን ንግግር እንደሚከተለው አቀርባለሁ፦
1. ኢብኑል ሙባረክ (181 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
فَإِنَّ أَهْلَ الْإِثْبَاتِ مِنْ أَهْلِ السُّنَّةِ يُجْمِعُونَ ... وَأَنَّ اللَّهَ عَلَى عَرْشِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ
“የአላህን መገለጫዎች የሚያፀድቁት የሱና ሰዎች … አላህ ከፍጡሩ ተለይቶ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ኢጅማዕ አድርገዋል።” [አልኢባና፣ ኢብኑ በጧህ፡ ቁ. 694]
2. ሰዒድ ብኑ ዓሚር አዱበዒ (208 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
الْجَهْمِيَّةُ أَشَرُّ قَوْلًا مِنَ الْيَهُودِ وَالنَّصَارَى، قَدِ اجْتَمَعَتِ الْيَهُودُ وَالنَّصَارَى، وَأَهْلُ الْأَدْيَانِ أَنَّ اللَّهَ تَبَارَكَ وَتَعَالَى عَلَى الْعَرْشِ، وَقَالُوا هُمْ: لَيْسَ عَلَى الْعَرْشِ شَيْءٌ
“ጀህሚያዎች ከአይሁድና ከክርስቲያን ንግግራቸው የከፋ ነው። አይሁድ፣ ክርስቲያንና የሌሎችም ሃይማኖት ተከታዮች አላህ - ተባረከ ወተዓላ - ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ከሙስሊሞች ጋር ተስማምተዋል። ጀህሚያዎች ግን ‘ከዐርሽ ላይ ምንም የለም’ አሉ።” [ኸልቁ አፍዓሊል ዒባድ፡ 31]
3. ሐማድ ብኑ ሀናድ አልቡሸንጂይ (230 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
“ይሄ የተለያዩ ሃገራት ነዋሪዎችን ያገኘንበት፣ መዝሀቦቻቸውም በሱ ላይ ያመላከቱት፣ የዑለማዎች ጎዳና ግልፅ የሆነበት፣ የሱናና የባለቤቶቿ መታወቂያ የሆነው አላህ ከፍጡሩ ተለይቶ ከሰባቱ ሰማይ በላይ ከዐርሹ ላይ እንደሆነ ነው። እውቀቱ፣ ስልጣኑና ችሎታው ግን ከሁሉም ቦታ ነው።” [አልዑሉው፡ 527] [ጁዩሽ፡ 2/242]
4. ዐሊይ ብኑል መዲኒይ (234 ሂ.) የአህሉ ሱና ወልጀማዐ አቋም ምን እንደሆነ ሲጠየቁ እንዲህ ሲሉ መልሰዋል፡-
أَهْلُ الْجَمَاعَةِ يُؤْمِنُونَ ... وَأَنَّ اللَّهَ فَوْقَ السَّمَاوَاتِ عَلَى الْعَرْشِ اسْتَوَى
“የጀማዐ ሰዎች ... አላህ ከሰማያቱ በላይ በዐርሹ ላይ እንደሆነ ያምናሉ።” [መጅሙዑል ፈታዋ፡ 5/49] [አልዑሉው፡ ቁ. 473]
5. ኢስሓቅ ብኑ ራሀወይህ (238 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
إِجْمَاعُ أَهْلِ الْعِلْمِ أَنَّهُ فَوْقَ الْعَرْشِ اسْتَوَى وَيَعْلَمُ كُلَّ شَيْءٍ فِي أَسْفَلِ الْأَرْضِ السَّابِعَةِ
“እርሱ ከዐርሹ በላይ ከፍ እንዳለና ከሰባተኛው ምድር ጀምሮ... ሁሉን ነገር እንደሚያውቅ የዑለማዎች ስምምነት አለ።” [ደርእ፡ 2/35] [አልዑሉው፡ ቁ. 487]
6. ቁተይባ ብኑ ሰዒድ (240 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
هَذَا قَوْلُ الْأَئِمَّةِ فِي الْإِسْلَامِ وَالسُّنَّةِ وَالْجَمَاعَةِ نَعْرِفُ رَبَّنَا سُبْحَانَهُ بِأَنَّهُ فِي السَّمَاءِ السَّابِعَةِ عَلَى عَرْشِهِ كَمَا قَالَ تَعَالَى: {ٱلرَّحۡمَٰنُ عَلَى ٱلۡعَرۡشِ ٱسۡتَوَىٰ}
“ይሄ በኢስላም የሱናና የጀማዐ ኢማሞች አቋም ነው። ጌታችንን ጥራት ይገባውና {አረሕማን በዐርሹ ላይ ከፍ አለ} እንዳለው ከሰባተኛው ሰማይ በላይ ዐርሹ ላይ እንደሆነ እናውቃለን።” [ሺዓሩ አስሓቢል ሐዲሥ፣ አቢ አሕመድ አልሓኪም፡ 34]
7. ኢማሙል ሙዘኒ (264 ሂ) የአህለ ሱናን አቋም ሲዘረዝሩ ቁጥር አንድ ያስቀመጡት የአላህን ከዐርሹ በላይ መሆን ነው። ከዚያም ሌሎችም መሰረታዊ ነጥቦችን ከዘረዘሩ በኋላ እንዲህ ብለዋል፦
هَذِه مقالات وأفعال اجْتمع عَلَيْهَا الماضون الْأَولونَ من أَئِمَّة الْهدى
“እነዚህ የመጀመሪያዎቹ ቀደምት የቅኑ ጎዳና ኢማሞች የተስማሙባቸው ንግግሮችና ተግባራት ናቸው።” [ሸርሑ ሱና፣ ሙዘኒ፡ 75፣ 89]
8. አቡ ዙርዐ አራዚይ (264 ሂ.) እና ሓቲም አራዚ (277 ሂ.) የአህሉ ሱናን ዐቂዳ ሲተነትኑ እንዲህ ብለዋል፡-
أَدْرَكْنَا الْعُلَمَاءَ فِي جَمِيعِ الْأَمْصَارِ حِجَازًا وَعِرَاقًا وَشَامًا وَيَمَنًا فَكَانَ مِنْ مَذْهَبِهِمُ: … وَأَنَّ اللَّهَ عَزَّ وَجَلَّ عَلَى عَرْشِهِ بَائِنٌ مِنْ خَلْقِهِ كَمَا وَصَفَ نَفْسَهُ فِي كِتَابِهِ , وَعَلَى لِسَانِ رَسُولِهِ ﷺ بِلَا كَيْفٍ
“በሁሉም ሃገራት - በሒጃዝ፣ በዒራቅ፣ በሻም፣ በየመን፣… ያሉ ዑለማዎችን አግኝተናል። ከመዝሀባቸው ውስጥ … አላህ - ዐዘ ወጀል - እራሱን በቁርኣኑ፣ እንዲሁም በመልእክተኛው ﷺ አንደበት እንደተገለፀው - ያለ እንዴት - ከፍጡሩ ተለይቶ ከዐርሹ በላይ እንደሆነ ማመን ነው። [ላለካኢ፡ ቁ. 321]
9. ኢብኑ ቁተይባህ (276 ሂ.) እንዲህ ብለዋል፡-
وَالْأُمَمُ كُلُّهَا -عَرَبِيُّهَا وَعَجَمِيُّهَا- تَقُولُ: إِنَّ اللَّهَ تَعَالَى فِي السَّمَاءِ مَا تُرِكَتْ عَلَى فِطَرِهَا وَلَمْ تُنْقَلْ عَنْ ذَلِكَ بِالتَّعْلِيمِ
“ህዝቦች በሙሉ ዐረቡም ሌላውም አላህ በሰማይ ነው ይላሉ። በተፈጥሯቸው ላይ እስከተተውና ከዚህ ላይ በስብከት እስካልተወሰዱ ድረስ።” [ተእዊሉ ሙኽተለፊል ሐዲሥ፡ 395]
10. አልኢማሙ ዳሪሚይ (280 ሂ.) ረሒመሁላህ እንዲህ ብለዋል፡-
قد اتَّفقتِ الكلمةُ مِنَ المسلمينَ أنَّ اللهَ فَوْقَ عَرْشِهِ فَوْقَ سَمَاوَاتِهِ
“አላህ ከዐርሹ በላይ ከሰማያቱ በላይ እንደሆነ የሙስሊሞች አቋም ተስማምቷል።” [ረድ ዐለል ጀህሚያ፡ 1/340] [ነቅዱ ዳሪሚ፡ 120]
=
(ኤዲት ተደርጓል።)
(ኢብኑ ሙነወር፡ የካቲት 24/ 2014)
https://hottg.com/IbnuMunewor
የመጨረሻ የውይይት ጥሪ
~ ~~~~
بسم الله الرحمن الرحيم
ከሆነ ጊዜ ወዲህ ያለው ንትርክ ውል ለማስያዝ ብለን የውይይት ጥሪ ያደረግንላቸው አካላት እስካሁን ድረስ ሰበብ እየደረደሩ ማሰናከሉን ተያይዘውታል። አሁን ደግሞ "ህዝብ ምን ያውቃልና ነው ዳኛ የሚሆነው?" በማለት ለህዝብ ክፍት መሆኑን እየነቀፉ ነው። በጉዳዩ ላይ ግር ያለው ሁሉ ከአሉባልታ ባለፈ በቀጥታ በመከታተል የጠራ አቋም ይይዝ ዘንድ ለህዝብ ክፍት ይሁን አልን እንጂ ህዝብ ዳኛ ሆኖ ነጥብ ይስጠን አላልንም። በዚያ ላይ ካልተግባባን የደረስንባቸውን ነጥቦች በጋራ ፅፈን በጋራ ለምናምንባቸው ዓሊሞች እናቅርባለን ብለናል። አንድ ጫፍ ላይ ሳንደርስ "ዓሊም እናስመጣለን" ወይም "ወደ ውጭ እንሄዳለን" ማለት መሸሻ ሰበብ እንጂ መፍትሄ መሻት አይደለም። ይህን ያክል ጉዳዩ ለታላላቅ ዓሊሞች እንዲቀርብ ብትፈልጉ ኖሮማ ተብዲዕ ውስጥ ከመዋኘታችሁ በፊት ተረጋግታችሁ ትጠብቁ ነበር።
ደግሞስ ከዚህ በፊት ለተለያዩ ወገኖች በግልፅ የውይይት ጥሪ ስናደርግ እንደነበር ይታወቃል። ለምን ያኔ አትነቅፉም ነበር? ጉዳዩ ወደናንተ ሲመጣ ነው ሰበብ የምትደረድሩት?
ለማንኛውም "ውይይቱ በአካል ቢሆን" ስትሉ ለነበራችሁ አካላት ሁሉ! ይሄው ጥያቄያችሁን በበጎ በማየት አንድ እርምጃ ለመቅረብ ወስነናል። ስለዚህ ሁለት ወይም ሶስት ሆነን ወደ ባህርዳር እንሄዳለን፣ ኢንሻአላህ። ይሁን እንጂ በር ዘግተን ከጥቂት ሰዎች ጋር ብቻ የምናወራበት ሁኔታ አይኖርም። በእንዲህ አይነት አካሄድ በተደጋጋሚ ተነድፈናል። ስለዚህ ባህዳር ውስጥ ካሉ መስጂዶች ውስጥ በአንዱ ይመቻች። የፈለገ ይታደምበት ዘንድ በሩ ክፍት ይሁን። ውይይቱን መቅዳትም፣ ቀጥታ ማስተላለፍም ለፈለገ አካል እንዲሁ ክፍት እንዲሆን እንፈልጋለን። ውይይቱን ለመምራትም የውጭ ሰው እንዲሆን አንጠይቅም። እዚያው ባህርዳር ያሉ መሻይኾች (ሸይኽ ዐብደላህ፣ ሸይኽ አሕመድ፣ ሸይኽ ሙሐመድ አወል፣ ኡስታዝ ዩሱፍን ጨምሮ) ይምሩት።
ለመረጃ ያክል ከውስጣችሁ ከኢኽዋን ጋር በግልፅ ውይይት ያደረገ ሰው አውቃለሁ። ይህንን የማነሳው ጥሪያችንን በሆነ ማመሀኛ እንዳትገፉት ነው።

NB፦
~~
በነገራችን ላይ ሰሞኑን በሕሩ የለቀቀውን ድምፅ አልሰማሁትም። የሰሙ ሰዎች ሲነግሩኝ ግን በዚህ መጠን መድረሱ ገርሞኛል። እንዲህ አይነቱን የዙልም አካሄድ ለህዝብ መበተኑ "ለአኺራዬ ያዋጣኛል" ካለ ምርጫው የራሱ ነው። ለጊዜው ግን ለራሴ እየተከላከልኩ ምላሽ በመስጠት ዋናውን የውይይት አጀንዳ ማደብዘዝ አልፈልግም። እቅጩን ስናገር ከውይይቱ ጥሪ ሰበብ እየደረደሩ የሚሸሹት የያዙት አቋም ሆድ የሚያስነፋ እንዳልሆነ ጠንቅቀው ስለሚያውቁ ነው። ስለዚህ የሚፈልጉት ወይ በተዘጋ ክፍል ውስጥ ወይ ደግሞ ጭፍን ደጋፊ ብቻ ባለበት ቦታ ያለ ጠያቂ፣ ያለ ሞጋች እንደፈለጉ መወንጀል ነው። በዚሁ መልኩ ብቻ ነው የምንቀጥለው ካሉ፣ ለህሊናቸው ካልጎረበጣቸው መንገዱን ጨርቅ ያድርግላቸው። "እናንተ ዘንድ የሌላ እውነት አለን" ካሉ ይሄው ለመታረም ዝግጁ ነን እያልን ነው። እኛ እጅ ለመስጠት ፈቃደኞች ካልሆንም "እውነታቸውን" ገልጠው እንደሚያስቡት በኛ የተሸወዱትን አካላት የሚያተርፉበትን እድል ይጠቀሙበት። የቀደመ አቋሙን የቀየረው ማን እንደሆነ ይለይ። እዚያም እዚህም የምንሰማው የተምይዕ ውንጀላም ተፍረጥርጦ ይውጣ። ይሄ ወደ ሱና በመጣራትና ቢድዐን በመዋጋት ጭንብል የተንሰራፋው ውሸትም ይጋለጥ። ባጭሩ እንገናኝና ወይ አጥፊው ይታረም፤ ወይ ውሸታሙ ይፈር።
~ ሰላም ~
Channel photo updated
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
Audio
📚رياض الصالحين ٠١

📚ሪያዱ አስ ሷሊሂን -ክፍል 01

# محمد سراج محمد نور

🎙# ሙሐመድ ሲራጅ ሙሐመድ ኑር

(የዕለተ እሁድ ደርስ)
#مدرسة الإمام أحمد
#ከኢማሙ አሕመድ መድረሳ

ትምህርቱን ለመከታተል ቻናሉን ይቀላቀሉ👇
https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from የሙሀመድ ሲራጅ የድምፅ ፋይል የሚሰራጭበት ቻናል (كوني زوجة صالحة تقية)
ክፍል 1____5
( كتاب الصيام" ኪታቡ ሲያም )

عمدة الأحكام ዑምደቱል አህካም
hottg.com/Muhammedsiragecom
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የተከበራችሁ ወንድሞችና እህቶች ፣

ሃገራችን በቀብር አምልኮና በቢድዓ የተሞላ ነው ። ላኢላሃ ኢለሏህን ያልተገነዘበው ከተገነዘበው በሰፊ ልዩነት ይበልጣል ።

አንዳንድ ሰዎች በኛ ላይ የሚያደርጉት ንግግርና ወሰን ማለፍ ሊያሳስበንና ተመሳሳይ መልስ ውስጥ ሊያስገባን አይገባም ።
የኛ በአንዳንድ ርእሶች መጠመድ የተመቻቸው አሕባሾችና መሰሎቻቸው ስራዎቻቸውን ከመቼውም በደመቀ ሁኔታ በመስራት ላይ ናቸው ።

ታገሱ ፣ ፅኑ ። ተዘምቶብናልና እንዝመት ። ተብሎብናልና እንበል የሚል ሙግት ውስጥ አንግባ ።

ስድብ ን ፣ ፀያፍ ንግግርን እና በእልህ መንቀሳቀስን እንራቅ ።
ከራሳችንም ሆነ ከወንድሞች በመከላከል ብዙ ግዜን ከማባከን ከመጨቃጨቅ እንቆጠብ ።

ህዝባችንን እያስታወስን ብዙሃንን በሚጠቅመው ተውሒድ ላይ እንትጋ ።

“ቅድሚያ የተዉሒድ “ ተግባራዊ የሚደረግ የእውነት መፈክራችን ይሁን ።

አላህ ይምራን

https://hottg.com/Muhammedsirage
"ከዐርሹ በላይ" መፅሀፍ ገበያ ላይ ወጥቷል። አልሐምዱ ሊላህ ቢኒዕመቲሂ ተቲሙ ሷሊሓት።

መገኛ፦ አተውባ መክተባ (አንዋር መስጂድ አጠገብ)
=
https://hottg.com/IbnuMunewor
Forwarded from ⚘ሱና የኑሕ መርከብ ናት قناة السنة سفينة نوح (كوني زوجة صالحة تقية)
አሕባሾች እና መሰሎቻቸው አላህ ከዐርሽ በላይ ነው የሚለው እምነት በኢብኑ ተይሚያ ዳብሮ በሙሀመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብ የተሰራጨ የ ወሃቢያ እምነት አድርገው እንደሚያስቡት ህፃን አዋቂው ዘንድ ይታወቃል።በዚህ ስራዬ ውስጥ ለነዚህ ሀሰተኞች ስበብ ላለመስጠት የሙሀመድ ብኑ ዐብዲል ወሃብን ቀርቶ የኢብኑ ተይሚያ እና የተማሪዎቻቸውን ንግግሮችም አላካተትኩም ።
ከቁርኣን እና ከሐዲስ ባለፈ ቀዳሚ ትኩረቴ ያደረኩት የአሽዐሪያ አንጃ ከመፈጠሩ በፊት ባለፊት እስከ 300 ሂ . ድረስ በነበሩ ዑለማዎች ላይ ነው ።
ከዚህ ዘመን በኋላ በመጡ ስመ ገናና ዑለማዎች ሊሞግቱን ለሚሹ ማርከሻ ይሆን ዘንድ ያክል ብቻ ከ300 ሂ . ጀምሬ እስከ 7ኛው ክ/ዘመን 2ኛ አጋማሽ ድረስ ከለፉ ዑለማዎች እያለፍኩ አጣቅሻለሁ።

"ከዐርሹ በላይ" ከሚለው መፅሀፍ መግቢያ የተወሰደ
https://hottg.com/fejir_tube

hottg.com/Menhaj_Salafiya
የሁለቱ ዓሊሞች ንግግር በኢኽዋን አንጃ ላይ
~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~•°~
ለኢኽዋን መንገድና ስልት የሚሟገቱ ግለሰቦች የዚህን አንጃ ክፋትና መጤነት የሚገልፁ የዑለሞችን ትችቶች በምንጠቅስ ግዜ የተለያዩ መከላከያዎችን ያቀርባሉ። አንዳንዶች በኢኽዋን ላይ የሚሰጡ ትችቶችን ከሃይማኖታዊ ይዞታ አውጥተው ፖለቲካዊ ቅርፅን ማልበስ ይሻሉ ። ለዚህም ነው "በኢኽዋኖች ላይ የተከፈተው ዘመቻ የተጠነሰሰው በባህረ ሰላጤው ጦርነት ማግስት ነው" ብለው አንዳንዶች የሚቀጥፉት።
የባህረ ሰላጤው ጦርነት የተከሰተው ከ20 አመታት በፊት ነው። ነገር ግን ዑለሞች ከተጠቀሰው ጦርነት በፊት የአንጃውን ጥመት ሲያጋልጡ ኖረዋል!!

ታላቁ ግብፃዊ የሐዲስ ሊቅ አሕመድ ሻኪር ኢኽዋኖችን በተመለከተ ከ60 አመታት በፊት እንዲህ ይላሉ ። ልብ ይበሉ ከ60 አመታት በፊት ነው!!! ልብ ይበሉ! በርካታ ዑለሞች በመልካም የመሰከሩለት ታላቅ ዓሊም የሰጠው ምስክርነት ነው! !! የታማኝ ንግግር ነው

"حركة الشيخ حسن البنا وإخوانه المسلمين الذين قلبوا الدعوة الإسلامية إلى دعوة إجرامية هدامة، ينفق عليها الشيوعيون واليهود كما نعلم ذلك علم اليقين "ا

"ኢስላማዊ ጥሪን /ዳዕዋን/ ወደ እኩይ እና አጥፊ ሰበካ የቀየረው የሸይኽ ሐሰን አልበና እና የሙስሊም ወንድሞቹ እንቅስቃሴ ሶሻሊስቶችና አይሁዶች በገንዘብ ይደግፉታል— ይህንን በእርግጠኝነት እንደምናውቀው!!"

የመዲናው ታላቅ ሸይኽ ሱለይማን አርሩሓይሊ የተጠቀሰውን የሸይኽ አህመድ ሻኪርን ንግግር ከጠቀሱ በኋላ እንዲህ ይላሉ:–

وإلى اليوم ينفق عليهم لأن هذه الجماعات تحقق أهداف أعداء الدين في الأمة

"ዛሬም ድረስ በነሱ ላይ ወጪ ይድደረጋል (በገንዘብ ይረዷቸዋል)። እንዚህ አንጃዎች የዚህ ሃይማኖት /የኢስላም/ ጠላቶችን አላማ በህዝቡ ላይ የሚያረጋግጡ /የሚያስፈፅሙ/ ናቸውና!!"
hottg.com/Muhammedsirage
የኔዋ መኪና !!!

መዝነቡን ጀመረ ደርሶ ማካፋቱ
ይከባብድ ይዟል ወጥቶ መግባቱ
እንግዲህ ከገባ የዝናብ ወራቱ
ደሞ እነደ ካቻምና እንዳምና ትናንቱ
ዣንጥላየን ልግዛ የኔዋን መኪና
እሷኑ ላሽከርክር በሰፊው ጎዳና!!


https://hottg.com/Muhammedsirage
HTML Embed Code:
2024/05/16 06:50:29
Back to Top