TG Telegram Group Link
Channel: MuhammedSirage M/Nur TextPosts
Back to Bottom
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
በሞታቸው ከሚያርፉት እንጂ ከሚታረፍባቸው , ላለመሆን እንታገል !!

ነብዩ፡ በሐዲሳቸው መልካም የሆኑ የአላህ ባሮች ከዱንያ ድካምና ችግር በሞት እንደሚገላገሉ ሲገልፁ ፣ በአመፀኞችና ክፉዎች ሞት ደግሞ የአላህ ባሮች ፣ አገሮች ፣ ዛፎችና ፣ እንስሶች እንደሚያርፉ አስተምረዋል ! _ በክፉዎች ሞት ይሄ ሁሉ ፍጡር ይርፋል ! እነሡ ግን በሞታቸው የሚያርፉ አይሆኑም!

ለአላህ መልካም ባሮች በመሆን ከሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ልናሣምር እንቁረጥ ! በአላህ ባሮች ላይ ክፉን በመዶለትና እነሱን አዛ በማድረግ በራሣችን ላይ መጥፎን በር አንክፈት ! ዘርንና ቀየን መሠረት ሳናደርግ ለወንድሞችና ለእህቶች ሁሉ መልካምን የምናስብ መልካሞች ለመሆን እንጣር ....

አላህ በሞታቸው የዱንያን ድካምና አስቸጋሪ ነገሮች ከሚገላገሉት ደጎች ያድርገን !!!https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ወንድሞች እና እህቶች

የሃገራችን የተለያዩ ክፍሎች ላይ የተፈጠረው ነገር እጅጉን ከባድ ነው ። የሞተው ሞቶ የተራበው እየተራበ ከቤት ከንብረቱ የተፈናቀለው ተፈናቅሏል ። ወዳጅ ከወዳጅ ተለያይቷል ።

የአላህን ውሳኔ አለም ቢሰበሰብ ሊቀይረው አይችልምና እሱ የወሰነው ሁሉ እየሆነ ነው ።
ሁሉም በአላህ የተወሰነ መሆኑን በማመን ታላቅ አጅርን ለሚያጎናፅፈው ትእግስት እንዘጋጅ - አላህን ከመለመንና ወደሱም ከመመለስ ጋር


مَا أَصَابَ مِن مُّصِيبَةٍ فِي الْأَرْضِ وَلَا فِي أَنفُسِكُمْ إِلَّا فِي كِتَابٍ مِّن قَبْلِ أَن نَّبْرَأَهَا إِنَّ ذَلِكَ عَلَى اللَّهِ يَسِيرٌ (٢٢) [ሱረቱ አል ሐዲድ: 22]

* በምድርም በነፍሶቻችሁም መከራ (ማንንም) አትነካም ሳንፈጥራት በፊት በመጽሐፍ የተመዘገበች ብትኾን እንጅ፡፡ ይህ በአላህ ላይ ገር ነው፡፡


لِّكَيْلَا تَأْسَوْا عَلَى مَا فَاتَكُمْ وَلَا تَفْرَحُوا بِمَا آتَاكُمْ وَاللَّهُ لَا يُحِبُّ كُلَّ مُخْتَالٍ فَخُورٍ (٢٣) [ሱረቱ አል ሐዲድ: 23]

* (ይህ ማሳወቃችን) ባመለጣችሁ ጸጋ ላይ እንዳታዝኑ አላህም በሰጣችሁ ነገር (በትዕቢት) እንዳትደሰቱ ነው፡፡ አላህም ኩራተኛን ጉረኛን ሁሉ አይወድም፡፡

ትእግስት ማጣትና ተገቢ ያልሆነን ንግግር መናገራችን አንዳች ነገር ሊቀይርም ሆነ የተፈለገውን ሊያስገኝልን አይችልም - በወንጀላችን ላይ ሌላን ወንጀል ይጨምራል እንጂ ።

ወደ አላህ መንገድ እንመለስ በየአቅጣጫው ለሚገኙ ወገኖቻችን ሁሉ ዱዓ እናድርግ ።

የመንደራችን ብጥብጥ ብቻ ሣይሆን የወንድምና የእህት ሁሉ ሁኔታና ሠላም ማጣት ያሣሥበን !

የዱንያው ፈተና እምነታችንን እንዳይሸረሽረውና እንዳያጠፋው ጥንቃቄን እናድርግ !! ጉዳዩ ከባድ ነውና በጉዳዩ ላይ እንዳሻን እየተናገርን የፈትዋ ባለቤቶች ከመሆን እንቆጠብ ።

ሰላም ማጣት የመን ውስጥ አፍጋኒስታን ውስጥ ሌሎች ቦታዎችም ውስጥ አለ የነሱንም ሆነ የኛን ሰላም አላህ ይመልስልን

አገራችንን አላህ ሰላም ያድርግልን
hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የቢድዓ ሰዎችን መታገል ከትልልቅ ስራዎች መሆኑን እናምናለን። ይህንን ታላቅ ስራ በመሸርሸር ላይ ያለን ሁሉ መንገዱ የጥፋት እንደሆነ አንጠራጠም ... የአህሉሱና የተለያዩ መገለጫዎች ላይ ቸልተኝነት ላይ ያሉ ግለሠቦችንና ቡድኖችን በዝምታ ማለፍም አደጋ መሆኑን እንመለከታለን ።

የተጠቀሱት አካል ላይ የሚደረገው ትግል ግን የእገሌን ዛቻ ወይም በእገሌ በጥመት መፍፈረጅን መፍራት የተከተለ አይደለም ።

የአላህን ምንዳ ፈልገንበት እንጂ " አልተናገሩም ፣ አይናገሩም " የሚለው የሰዎች ንግግር ተፈርቶ አይደለም ።

ለማንኛውም ፦

ዛሬም በትናንቱ ላይ ነን ! ትናንት ትክክል አይደሉም " ያልናቸውን '' ዛሬም ትክክል አይደሉም " እንላለን ... ትናንት በዓቂዳ፣ በመንሃጅ ጉዳይ የራቅናቸውን ዛሬ አለቀረብንም ... በየግዜው አዳዲስን ንግግርን ማስሰማት ግን ግድ አይደለም

ይሄው ነው ባጭሩ!

https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ጥቂት ነጥቦች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ
~ ~ ~ ~~~ ~~~~ ~~~~
1- ቁርኣናችን ማንም የማንንም ወንጀል እንደማይሸከም በግልፅ ያስቀምጣል። የትኛውም ሰው ቢበድለን በዘር ሰንሰለት እያገናኘን በጅምላ ሌሎች ላይ አንፍረድ። በሌሎች ጉዳትም አንደሰት።
2- አቅማችንን እንወቅ። ከአቅማችን በላይ በሆነ ጉዳይ ውስጥ እየገባን አናቡካ። አደብ ይኑረን። እውነት ለመናገር ብዙዎቻችን ሚሊዮኖችን ስለሚያነካካ ጦርነት ቀርቶ በአንፃራዊነት ቀላል ስለሚባሉ የፊቅህ ርእሶች እንኳ ለማውራት አቅም የለንም። ሁሉ ነገር ላይ ሃሳብ ካልሰነዘርን አንበል።
3- ከየብሄሩ የግጭት ተዋንያን ያልሆኑ፣ ግና በግጭቱ ሳቢያ ዘመድ፣ ቤተሰብ የተጎዳባቸው ብዙ ምስኪን ወገኖች እዚሁ ማህበራዊ ሚዲያ ውስጥ አሉ። የምንፅፈውን ያያሉ፣ የምንናገረውን ይሰማሉ። ኢንሻአላህ ይሄ ቀን ያልፋል። ለሚያልፍ ቀን የማያልፍ ቃል አንናገር። ያመጣልንን እያወራን በቁስላቸው ላይ እንጨት እየሰደድን እንዳንጎዳቸው፣ ቅስማቸውን እንዳንሰብር እንጠንቀቅ።
4- በያካባቢው ለፖለቲካ ባይተዋር የሆኑ ወገኖች መርጠው ባልተፈጠሩበት ብሄር የተነሳ ሲሳደዱ ማየት የተለመደ ሆኗል። ከፊሎች ወቅታዊ ፍተሻዎችንና ክትትሎችን ተከትሎ ያለ ወንጀላቸው ለቂም በቀል ጥቃትና ለስግብግብ ጅቦች ሲሳይ ሆነዋል። እነዚህን ወገኖች ብንችል ልናግዛቸው፣ አጥፊዎችን ልናወግዝ ይገባል። እሱ ቢቀር በሞራል እንኳ ከጎናቸው ልንቆም ይገባል። እንጂ ፈፅሞ ለበደል አጋዥ እንዳንሆን መጠንቀቅ አለብን።
5- ከሞቱ፣ ከንብረት ውድመቱ ባሻገር በተለያዩ የሃገራችን ክፍል እልፍ አእላፍ ከቀያቸው ተፈናቅለዋል። ሌሎች ደግሞ መሸሸም ቅንጦት ሆኖ አጣብቂኝ ውስጥ ገብተው ከዛሬ ነገ እልቂትን እየጠበቁ የሰቀቀን ህይወት እየገፉ ነው። 30ሺ እና 40ሺ የሚያወጡ ንብረቶቻቸውን 2ሺ እና 3ሺ እንኳ እንዳይሸጡ ታድሞባቸው እየተንከራተቱ ነው። እነዚህን ወገኖች የምናግዝበት አቅሙ ካለን እናግዛቸው። እሱ ቢቀር ቢያንስ በዱዐ አንርሳቸው።
6- አሰሰ ገሰሱን ሁሉ እየተከታተልን ለጅላጅል የዩቲዩብ ቃራሚዎች መጠቀሚያ አንሁን። ጥላቻን የሚዘሩ ስራዎችን ከማሰራጨት እንቆጠብ። የሴራ ፖለቲካ ከሚተነትኑ ከንቱዎች እንራቅ። ይልቁንም ትኩረታችን ለዱያንም ሆነ ለአኺራ በሚጠቅመን ላይ ይሁን። በዱዓ ላይ እንበርታ።

https://hottg.com/IbnuMunewor
https://hottg.com/IbnuMunewor
https://hottg.com/IbnuMunewor
የደበዘዘ ትዝታ
~~~~ ~~~
ጊዜው 1999 (?) ነው። ሙስሊም ተማሪዎች በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ በሶላትና በአለባበስ የተነሳ ሰፊ ወከባ እየደረሰባቸው ነበር። በዚህ ወሳኝ ጊዜ ላይ በተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን (ECA) የስብሰባ አዳራሽ በሃይማኖቶች መቻቻል ዙሪያ ዝግጅት ይደረጋል። የመድረኩ መሪ የአ.አ.ዩ. ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ ነበር። የተለያዩ ምሁራን፣ ታዋቂ ሰዎች፣ የህዝብ ተወካዮች፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እንደተገኙ አስታውሳለሁ። ፕሮግራው በአንዲት ነጭ ተዘጋጅቶ በቀረበ አጭር ዶክሜንተሪ ቪዲዮ ነው የተከፈተው። በጊዜው በየአደባባዩ ፎቷቸው ተስቅሎ የነበረው የሁለት ሴቶች (በላይነሽና ማን ?) ምልልስ ላይ ያተኮረ ነበር። የኮምቦልቻ ነዋሪዎች ናቸው። በላይነሽ ሙስሊም መሆኗ ነው። ሌላኛዋ ክርስቲያን። ህይወታቸው ኑራቸው ሁሉ አንድ እንደሆነና የሚለያዩት ሙስሊሞች ሲሞቱ መስጂድ፣ ክርስቲያኖቹ ደግሞ ቤተ ክርስቲያን መሄዳቸው ብቻ እንደሆነ ይገልፃሉ። ዶክሜንታሪው እንዳለቀ ካልተሳሳትኩ "ሰላም በመፅሐፍ ቅዱስ" የሚል ይዘት ያለው ፅሑፍ በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ ቀረበ። አለማቀፍ የኢትዮጵያ አይሁዶች ሊቀመንበር ተብሎ መሰለኝ የተዋወቀው። የራሱ ርእስ ላይ ሳይገደብ ኢስላምን በነገር እየወጋጋ ነበር ስራውን ያቀረበው። ይታያችሁ እንግዲህ! ስለ መቻቻል በተጠራ ድግስ ላይ፣ ሙስሊሞች በተጋበዙበት ፕሮግራም ላይ ኢስላምን በነገር እየሸነቆጠ ጥናት ሲያቀርብ። ወትሮም ፍቅር ባይኖረኝ ይበልጥ ነበር ቋቅ ያለኝ።
ከሙስሊሙ በኩል አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ አልፎ አልሮ የማየው ብዙም የማላውቀው ፕሮፌሰር አህመድ ሐሰን (ስሙን እርግጠኛ አይደለሁም) አቀረበ። ይዘቱ ያን ያህል ሳቢ ሆኖ አልተሰማኝም። በኢትዮዽያ ያልነበረውንና የሌለውን መቻቻል እንደነበር ለማሳየት አጉል መጋጋጡ ስራውን እጅ እጅ አስብሎበታል። የሌለን ነገር ያለ አስመስሎ ማቅረብ ምን ያህል ደባሪ እንደሆነ አቀራረቡ ይናገራል። ቢያንስ ግን እንደ ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅ የእለቱን የመቻቻል ስብከት የሚያደፈርስ እብሪት አላሳየም። ትሁት ነበር። ደካማነት የተጫጫነው ትህትና።
በመቀጠል የፕሮግራሙ መሪ ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ ወደ መድረክ ወጥቶ ፕሮፌሰር ሑሴን አሕመድን በቀረቡት መጣጥፎች ላይ ሃሳብ እንዲሰጥ ጋበዘው። ፕሮፌሰር ሑሴን አሕመድ (አላህ ይዘንለት) ወደ መድረክ ወጣ። ሰዓት እንደሌለው በመግለፅ ለ6 ደቂቃዎች ያክል ብቻ ትንሽ ልበል አለ። ቆሽታችንን ያሳረረውን ፕሮፌሰር ኤፍሬም ይስሃቅን እንዳይበላ እንዳይዘራ አድርጎ አበራየው። ሰውየው እያየሁት ነበር ኩምሽሽ ያለው። የኤፍሬም ይስሓቅን ፀረ ኢስላም ክስ "የቅርብ ጊዜ ጥናቶችን ከግንዛቤ ያላስገባ ጊዜው ያለፈበት ኋላ ቀር ውንጀላ" በማለት አጣጣለው። "ኢስላም አስገድዶ እምነት በማስለወጥ በጎራዴ ጫፍ የተስፋፋ ሃይማኖት ነው" የሚለውን የኤፍሬምን ንግግር የኢስላም ጠላቶች እንኴ እውነት እንዳልሆነ አውቀው የተውትን ክስ እንዳዲስ ታራግባለህ። እኔ ራሱ በዚህና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በረከት ያሉ ፅሁፎችን ፅፌያለሁ። አንዱንም ግን አላጣቀስክም ..." አለ። ሙስሊሙን ሰውየም አጥጋቢ ባይሆንም በሰሱ ሸንቆጥ አድርጎት ወረደ።
በመንግስታዊ ተቋማት ውስጥ ሰፊ ወከባና እንግልት እያስተናገድን ባለበት ጊዜ መቻቻል የሚል ድግስ መደገሳቸው ለኛ በጣም ስላቅ ነበር። ጉዳዩ በጣም ስላበሳጨን በስሜት ለመናገር ነበር ባልተጠራንበት ድግስ የተገኘነው። ነገር ግን እውነት ለመናገር ለመድረኩ የሚመጥን ቁመና አልነበረንም።
ፕሮግራሙ ለታዳሚ ክፍት ሲሆን በኢትዮዽያ ያለውን የሃይማኖቶች መቻቻል የሚያወድሱ ጥቂት ሃሳቦች ከተንሸራሸሩ በኋላ እድሉ ለአቶ ዐብዱል ዋሲዕ ዩሱፍ ደረሰ። ሰውየው ሲበዛ ደፋር ነው። አንድ ኮርስ (Isamic Law) ሲያስተምረን ይህንን አይቻለሁ። በሌሎች መምህራን ላረረው ቆሽታችን እፎይታ ቢሰጠንም አለፍ እንደሚል ማስተዋል ግን ይቻል ነበር። ማይኩን እንደተረከበ እንዲህ ነበር ያለው፦ "እዚህ አዳራሽ ውስጥ ያለው በሙሉ በአንድ ድምፅ ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት መቻቻል አለ ቢል እኔ ዐብዱል ዋሲዕ ብቻየን የለም ብየ እቆማለሁ። ሌላው ሁሉ ይቅር አሁን በዚህ ሰዓት ሙስሊም ተማሪዎች ላይ እየደረሰ ያለው ምንድነው? ሶላት ሰገዳችሁ፣ ሻሽ አደረጋችሁ ተብሎኮ ነው ስንትና ስንት ወከባ እየደረሰባቸው ያለው። ኢትዮጵያ ውስጥ በግለስብና በቤተሰብ ደረጃ መቻቻል አለ። እንደ ተቋም ግን ፈፅሞ መቻቻል የሚባል የለም!" አለ፣ ፍርጥም ብሎ።
ከዚህ በመቀጠል ከሌሎችም ታዳሚዎች ሙስሊም ካልሆኑት ጭምር ተቀርራቢ ሃሳቦች ተሰነዘሩ። ሙስሊሞች ላይ በታሪክ የደረሱ መድሎዎችና መገለሎች ተነሱ። የአፄ ዮሐንስ የቦሩ ሜዳ አዋጅና ሙስሊሞች ላይ የፈፀመው ጭፍጨፋ፣ ልጅ እያሱ በሙስሊምነት ተጠርጥሮ የደረሰበት መፈንቅለ መንግስት ተጠቀሰ። አፄ ሱስንዮስ እምነቱን ከኦርቶዶክስ ወደ ካቶሊክ በመቀየሩ የተነሳ የተከተለው ጦርነትና እልቂት ወዘተ ተመዘዘ። ይሄ ሁሉ የሚያሳየው ኢትዮጵያ ውስጥ የሃይማኖት መቻቻል እንዳልነበረ ነው የሚለው ሃሳብ ሙስሊም ባልሆኑት ጭምር በግልፅ ተነገረ። ስብሰባው የታለመለትን ግብ ሳይመታ ቀረ። ፕሮፌሰር እንድሪያስ እሸቴ እጅግ በቀዘቀዘ ድምፅ "ያው እንግዲህ ሙስሊሞች ተበድለናል እያሉ ነው ፣ ..." በማለት ሃሞቱ ፍስስ ብሎ ነበርየተናገረው። ቀረፃው እራሱ መሃል ላይ የቆመ ይመስለኛል።
ፕሮፌሰር ኤፍሬም ኢስሓቅ ስለሚባለው እባብ በብስጭት የሚናገሩ ሰዎችን ሳይ ትዝ ቢለኝ የሞነጫጨርኩት ነው።
===
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://hottg.com/IbnuMunewor
ሰለፊ እና ፓለቲከኛ
<unknown>
እኛ እና ፖለቲከኛ

https://hottg.com/Muhammedsirage
Audio
የአላህ ባህሪዎችን በተመለከተ የኢማም አትቲርሚዚ እና የሌሎች አኢማዎች አቌም ...

https://hottg.com/Muhammedsirage
Audio
ኢኽዋኖችን ተጠንቀቋቸው!!
hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
በሞት ሣትቀደም!

ያንን ፀያፍ ቦታ የገማውን መንደር
ተዉ አትስፈሩበት ስትል እንዳልነበር
ከትበህ እንዳልነበር ላይሠፈር በዘር

ገብተህበት አየን አንተም እንደነሡ

በዘር ከሚዘልፉት በሱ እያወደሱ ...

ስትል እንዳልነበር ቅድሚያ ለኢማኑ
ሠብከህ እንዳልነበር " ተቅዋ ነው ሚዛኑ ''


በኢማን በተውሒድ መተሳሰር ቀርቶ
መገማመድ ጀመርክ በዘርህ ድሪቶ

ተዉ ተመለስ ወንድም ዛሬም አልረፈደም
ያብቃለት ከ'ንግዲህ መመዘንም በደም
ነቃ በል ወገኔ በሞት ሣትቀደም !


https://hottg.com/Muhammedsirage
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
ሰዎችን በዘር፣ በቆዳ ቀለም ፣ በቋንቋና በትውልድ መንደር የሚመዝን ሁሉ መሃይምነትን በውስጡ የተሸከመ ነው ! !
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
የሰዎች ኢስላምና ተውሒድ አላጠግብህ ብሎት የዘር ሃረጋቸውን መመዘኛ ያደረገ ሁሉ በጉዳዩ ላይ የታላቁን ነብይ ሳይሆን የታላቁን ከሃዲ የአቡ ጀህልን ና የመሠሎቹን ኮቴ በመከተል ላይ ነው!
Forwarded from MuhammedSirage M.NOOR (MuhammedSirage MuhammedNoor)
አዛኝ፣ ደግ ፣ እጅጉን ቸር ፣ የሰዉ ዘር ሁሉ አለቃ የሆኑት ታላቁ ነብይ صلى الله عليه وسلم ዘረኝነትን በዚህ መልኩ ገልፀውታል

" ተዋት እሧ ጥምብ ናትና "

በዘር ማላቅና ማዝቀጥ የኢስላምን አስተምህሮ የሚፃረር የባዶዎች እምነት ነው!

እውነተኛው መለኪያ እምነት ነው!

ሚዛኑ ሱና ፣ ስነ ምግባር ነው !
hottg.com/Muhammedsirage
Audio
የላአኢላሃ ኢለሏህ መልእክት

https://hottg.com/Muhammedsirage
Audio
ሁለቱ የሃይማኖታችን (የሸሪዓችን) መሰረቶች

https://hottg.com/Muhammedsirage
ነጃሺና ሸህ ሁሴን ጅብሪል፣ የፖለቲከኞች መጫዎቻ ካርዶች
-----------------------------------------------------------------------------
ፖለቲከኞች የህዝብን ስስ ብልት በመንካት አጫፋሪ ለማብዛት መሞከራቸው የተለመደ አካሄድ ነው። በዚህ ረገድ በቀዳሚነት ከሚጠቀሙባቸው ነገሮች ውስጥ ደግሞ አንዱ ሃይማኖት ነው። በተለይም ውጥረት ውስጥ በሚገቡ ጊዜ በሰላም ጊዜ ቦታ ያልሰጡትን ሃይማኖት ሊመሽጉበት ተፍ ተፍ ሲሉ ይታያሉ። ኢስላምን እንደ ምሳሌ ብንወስድ እራሳቸው የሙስሊሞችን መብት ባለ ከበሩበትና በሚያከብሩበት ሁኔታ፣ የራሳቸው የኢስላም ጥላቻ ባፈጠጠ ባገጠጠበት ሁኔታ በሌሎች ጥቃት ሆድ ሊያስብሱን፣ በሸንጋይ ቃላት ሊሸነግሉን ይፈልጋሉ። ችግራቸው የራሳቸው ጊዜያዊ ቁማር ላይ ቢቆም በቂ ጥፋት ነበር። ችግሩ ከዚያም አልፎ እምነታዊ ግንዛቤን የሚያፋልስ መሆኑ ነው። በወቅታዊው ሁኔታ ከሚንፀባረቁ ነገሮች ውስጥ ሁለት ምሳሌዎችን ልጥቀስ፦

አንድ፦ የነጃሺ ጥቃት ጉዳይ፦
እንደ መግቢያ ከስር የተያያዘው ምስል የነጃሺ መስጂድ ሳይሆን የዶሪሑ (መቃብሩ) ምስል ነው። መስጂዱ ላይ የደረሰ ጥቃት ይኑር አይኑር አላውቅም። ጥቃቱን የፈፀመውን አካል በተመለከተ የጦርነቱ ተዋንያኖች አንዱ ሌላውን እንደሚከስ የሚታወቅ ነው። ዶሪሑን በተመለከተ ብዙ ሺርክያት እንደሚፈፀምበት በቦታው ተገኝቼ በአይኔ በብረቱ አረጋግጫለሁና በደረሰው ነገር ምንም የማዝንበት ምክንያት የለም። የኔ ትኩረት ይህንን ዶሪሕ መነሻ በማድረግ ቦታውን በአለም ላይ ካሉ መስጂዶች በተለየ ቅዱስ አድርጎ ለማቅረብ በሚደረገው ሙከራ ላይ ነው።
በኢስላም ልዩ ቦታ እንዳላቸው የተጠቀሱት መስጂዶች ሶስት ናቸው። እነሱም ከላይ ወደታች በቅደም ተከተል የመካው መስጂደል ሐራም፣ የመዲናው መስጂደ ነበዊ እና የፈለስጢኑ መስጂደል አቅሷ ናቸው።

1. መስጂደል ሐራም:-
በመስጀደል ሐራም የሚሰገድ ሶላት በሌላ ቦታ ከሚሰገድ ሶላት የመቶ ሺ ብልጫ አለው።

2. መስጂደ ነበዊ
በመስጂደ ነበዊ የሚሰገድ ሶላት በሌላ ቦታ ከሚሰገድ ሶላት የአንድ ሺ ብልጫ አለው፣ መስጂደል ሐራም ሲቀር።

3. መስጂደል አቅሷ
በመስጂደል አቅሷ የሚሰገድ ሶላት በመስጂደ ነበዊ የሚሰገደውን እሩብ ያክል ዋጋ አለው። 250 ማለት ነው። [አሶሒሐህ፡ 2902]
ማሳሰቢያ፦ በመስጂደል አቅሷ የሚሰገድ ሶላት በሌላ ቦታ ከሚሰገድ ሶላት የ 500 ብልጫ አለው የሚል ሐዲሥ አለ። ነገር ግን ደካማ ስለሆነ ማስረጃ መሆን አይችልም። [ተማሙል ሚና፡ 292]

ከነዚህ በተጨማሪ መዲና ውስጥ የሚገኘው የቁባእ መስጂድም ከፍ ያለ ቦታ አለው። ይሁን እንጂ በኢስላም ከሶስቱ መስጂዶች ውጭ ስንቅ ቋጥሮ፣ አገር አቋርጦ ለጉብኝት መጓዝ የሚፈቀድባቸው ቦታዎች የሉም።
መካ (መስጂደል ሐረምን ማእከል በማድረግ) እንዲሁም መዲና (መስጂደ ነበዊን ማዕከል በማድረግ) ጥብቅ ክልሎች (ሐረሞች) ናቸው። ስለሆነም በውስጣቸው ጦርነት መዋጋት፣ አደን ማደን እና በሰው ያልተተከሉ ዛፎችን መቁረጥ የተከለከለ ነው። መስጂደል አቅሷ ግን ሐረም እንደሆነ የሚጠቁም ማስረጃ ስለሌለ እነዚህ ህግጋት አይመለከቱትም። በኢስላም ትልቅ ቦታ እንዳለው በቁርጥ የሚታወቀው መስጂደል አቅሷ ሐረም ካልሆነ ቅንጣት ታክል የቁርኣንም ይሁን የሐዲሥ ማስረጃ ያልመጣባቸው ሃረር ወይም ነጃሺ የተለየ ቦታ አይኖራቸውም። ይህንን የምለው በዚህ መልኩ የሚያምኑ የተለያዩ ሰዎችን ስላየሁ ነው። ስለዚህ ሃረር ከተማ ከጂጂጋ፣ ከድሬዳዋ፣ ከአሰብ፣ ከምፅዋ፣ ከጧኢፍ፣ ከጂዳ፣ ወዘተ ምንም የተለየ ደረጃ የላትም። በትግራይ ውቅሮ ከተማ አጠገብ የሚገኘው የነጃሺ መስጂድም "ከመካ ቀጥሎ ቅዱስ ስፍራ'' ሊባል ቀርቶ ከሌሎች መስጂዶች #የተለየ ብልጫ የለውም። የማወራው ታሪክ አይደለም። ከቁርኣንና ከሐዲሥ አንፃር ሊጠቀስ የሚገባን ደረጃ እንጂ። ከስር ያያያዝኩትን የፃፈው ሙስሊም አይደለም። ነገር ግን ሙስሊሞችም ከቁም ነገር ሲቆጥሩት ስላየሁ ነው ማስታወሴ።

ሁለት፦ የሸህ ሁሴን ጂብሪል ትንቢት ጉዳይ፦

የፖለቲካው ትኩሳት ብዙ ሙስሊሞችን ልክ እንዲያልፉ እያደረጋቸው ነው። "ወያኔ የሚጠፋው ወሎ ምድር ላይ እንደሆነ ሸህ ሁሴን ጅብሪል ተንብየዋል" እያሉ የተግተለተለ ግጥም የሚቀባበሉ ሙሐመዶችና ፋጢማዎች ብዙ ናቸው። "ሸህ ሁሴን" በሚል የሙስሊም ስም ስለሚቀርብ ነው ብዙዎች የሚሸወዱት። እንጂ በቄስ ወይም በደብተራ ስም ቢቀርብ ትኩረት አይሰጡትም ነበር። የሚገርመው ይሄ ቆሻሻ ግጥም ከዚያ በካ*ሩ ቦጋለ ተፈሪ በዙ ከተሰበሰበው '' ትንቢተ ሸህ ሁሴን ጅብሪል" የኮተት መፅሀፍ ውስጥ የሚገኝ አይደለም። በሃገሪቱ አነጋጋሪ ክስተቶች በገጠሙ ቁጥር በሶላት የለሹ ሸህ ሁሴን ስም አዳዲስ ስንኞችን እየፈበረኩ የሚመዙ ሰዎች አሉ። የተፈሪ ቦጋለ ስራ አይን ያወጣ ዅራፋት ነው። መሰረት የለሽ አጉል እምነት። በኢስላም በቦጋለ ይቅርና በሸይኽና በኡስታዝ የተላለፈም ታሪክ ጥብቅ ፍተሻ ይደረግበታል። ፍተሻውን ያላለፈ ዘገባ ታቢዒይ ቢያስተላልፈው እንኳ ያለምንም ማመንታት ይጣላል። በታዋቂውና በታላቁ ሐሰኑል በስሪይ የተላለፉ ከመሆናቸው ጋር የሐዲሥ ምሁራን ያልተቀበሏቸው ስንት ዘገባዎች አሉ?! አስተላላፊዎቹ እነ ቦጋለ ሲሆኑስ? በዚያ ላይ አቶ ቦጋለ የመጽሐፉ መግቢያ ላይ እንደገለፀው ሸህ ሁሴን አገኘሁ የሚል ሰው ከነ ጭራሹ አላገኘም። የሸህ ሁሴን ጅብሪል ልጅም ይሁን የልጅ ልጅ አላገኝም። ይህንን የሚጠቁም ሰነድም አላገኘም። ከምን አይነት ሰዎች የተወሰደ ነው? “የሸሁን መናቄብ ያቃሉ የተባሉት ዓይናቸው የፈዘዘ፣ ጆሯቸው የደነዘ፣ ጉልበታቸው የዛለ፣ አንደበታቸው የተሳሰረ” በማለት ይገልፃቸዋል ፀሐፊው፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ “ያውቃሉ የተባሉት ከግጥሙ ይልቅ ታሪኩን ብቻ ማወቃቸው” አንዱ በመሰነድ ሂደቱ ላይ የገጠመው ችግር እንደሆነ ገልጿል፡፡ [ቦጋለ፡ 2-3] ያውቃሉ የተባሉት ካላወቁት እና ግጥሞቹ የማን ናቸው? አንባቢ ሆይ! እራስህን ጠይቅ!
ፀሐፊው ሸህ ሑሴንን የሚያውቅ ሰው አግኝቷል ወይ? እንዳላገኘ በቁርጥ አስቀምጧል፡፡ ይህም ብቻ አይደለም፡፡ የሸህ ሑሴንን ልጅም ሆነ የልጅ ልጅ አላገኘም፡፡ በኪታብ መልክ የፃፈም የተፃፈም አላገኘም፡፡ [ቦጋለ፡ 6] “ሸህ ሁሴን ጅብሪልን አነጋግሬያቸዋለሁ የሚል አልተገኘም” በማለትም ቀጥተኛ የቅብብሎሽ መስመር እንደሌለው ጠቆሟል፡፡ [ቦጋለ፡ 23]
ፀሐፊው እንደሚለው የሰውየውን የግጥም ስንኞች ለማግኘት በጣም ደክሟል፡፡ “ተሳካለት ወይ ታዲያ?” አትሉም? የዚህን “ሸህ ግጥሞች ለማግኘት ያልፈነቀልኩት ድንጋይ፣ ያልገረሰስኩት ጉቶ፣ ያልበጠስኩት ቅጠል አልነበረም፡፡ ግን ቄሱም ዝም መጣፉም ዝም እንደተባለው ሆነ” በማለት እንዳልተሳካለት እቅጩን ይናገራል፡፡ [ቦጋለ፡ 7] እና ከየት ያገኘውን ነው የሰበሰበው? ከህዝብ ነው የሚለው፡፡ እሱ እራሱ ጫፍ እየያዘ እያባዛና እየለጠጠ አቅርቦትስ ቢሆን ምን ያክል ይታመናል? ከተባለ ምን ይዘን፣ የት አውቀነው በምን መነሻ እናምነዋለን ነው መልሱ፡፡
ሸይኽ ሑሴን ጂብሪል ማነው?
የሸህ ሑሴንን ታሪክ የሚገልፀው አንድ ለናቱ ስራ ይሄው ቦጋለ ተፈሪ በመጽሐፉ መግቢያ ላይ የጠቆመው ብቻ ነው፡፡ ከዚህ ውጭ ሰውየው ምናባዊ ይሁን እውነተኛ ሰው ምንም ማረጋገጫ የለም፡፡ ፀሐፊው እንዲህ ይላል፡- “ሼህ ሁሴን የነቢዩ መሐመድ ተከታይ ነበሩ፡፡ ቢሆኑም እንደ እስላሞች ጫት አይቅሙም፣ ሶላት አያደርሱም፣ መስገጃ ቁርበት፣ ውኃ መያዛ ጦሌ አያንጠለጥሉም፡፡ እንደ ዓባይ ጠንቋይም መጽሐፍ አይገልጡም፣ ጠጠር አይጥሉም። ግን ሱረት (ሐቀኑር) ያሸታሉ፣ ብርዝ ይጠጣሉ፣ ፍርድም ሲፈርዱ ማለት የሚታያቸውን ሲናገሩ ብርዝ በፎሌ (በሽክና) ይዘው ነበር ይባላል። [ቦጋለ፡ 23]
አያችሁ አይደል? ውዱእ እንኳ ያልነበረው ሰው ነው።

በነገራችሁ ላይ መጽሐፉ አንዳንድ የሃገራችን ህዝቦችንና ቋንቋዎችን የሚያነውሩ ቆሻሻ ስንኞች አሉት። ይህም የሚያሳየን አቶ ቦጋለ አንዳንድ በብሄር ጥላቻ የታወሩ ሰዎች የገጠሙትን አሰስ ገሰስ እንደሰበሰበ ነው። እኔ እንዲያውም እራሱን ቦጋለን ነው የምጠረጥረው። በሸህ ሁሴን ትንቢት ስም የራሱን ቅርሻት ለቅልቆ ሊሆን ይችላል። በነገራችን ላይ ቦጋለ ተፈሪ ጥሩ ነጋዴ ነው። ይህንን ብሽቅ መፅሀፍ ከ15 ጊዜ በላይ በማሳተም በደምብ አድርጎ ቸብችቧል። ታዲያ ገበያው እንዳይቀዘቅዝበት የኋላ ኋላ አሪፍ ዘዴ ዘይዷል። የመጽሐፉ የኋላኛው እትሞች ላይ እነዚያ ትግሬውን፣ አሮሞውን፣ ጉራጌውን የሚያንቋሽሹ ፀያፍ ፀረ ህዝብ ስንኞችን አውጥቷቸዋል። ችግሩ ግን የሱን ፈለግ የተከተሉ አያሌ ቦጋለዎች መፈልፈላቸው ነው። ከቀደሙ ህትመቶች ላይ ያሉትን ጨምሮ የራሳቸውን ጅምላ ፈራጅ የሆኑ ፀያፍና መደዴ ስንኞችን በማከል በኢንተርኔት ይለቃሉ። ወገኔ ሆይ! የቦጋለዎች መጫወቻ አትሁን። እንዴት ከቦጋለ ያነሰ ግንዛቤ ይኖርሃል? ቦጋለኮ ቢያንስ 15 ጊዜ ይህንን ኮተት እያተመ ቸብችቦታል። ሞኝነት ብዙ ደረጃ አለው። እንደ ቦጋለ ባሉ ቂሎች በዚህ መጠን መታለል ግን የእውነት በጣም የሚያሸማቅቅ ነው።

Ibnu Munewor
የቴሌግራም ቻናል፦
https://hottg.com/IbnuMunewor
Audio
በኢማን ላይ መጠራጠር
እና ወስዋስ (ጉትጎታ ) የተለያዩ ነገሮች ናቸው
hottg.com/Muhammedsirage
"መስጊድህን አፍርሼ ቤተ ክርስቲያን ባልሰራ እምዬ ማርያም አትለመነኝ"
=
የኃይለ ስላሴ አባት ራስ መኮነን ወልደ ሚካኤል ሃረርን ሊወር ሲዘጋጅ በአሚር ኑር ላይ የፎከረው ነው። ፎክሮም አልቀረ እድሜ ጠገቡን የፈረስ መጋላ መስጅድ አፍርሶ መድሃኔያለም የተሰኘ ቤተ-ክርስትያን በቦታው ገነባ። ይህም ሳይበቃ የቁርአን መማሪያ ማእከላትን ፈርሰው በምትካቸው ስላሴ ቤተ ክርስቲያን፣ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን እና ቁልቢ ገብረኤል ቤተክርስቲያን ተገንብተዋል።
.
እና ታሪክ እየፈጠራችሁ ያም የኛ ይሄም የኛ የምትሉ ሁሉ! የደረቀ ቁስል ባትነካኩ መልካም ነው። ይሄ በሙስሊሙ ብቻ አይደለም የሚነሳው። በአሁኑ ሰዓት በሰፊው ከሚታወቁት አብያተ- ክርስትያናት ውስጥ ከሌሎች ቀደም ብሎ ከነበሩ ልማዳዊ እምነት ቦታዎች ተነጥቀው የተሰሩት ብዙ ናቸው። የታደሰ ታምራትን Church & State መፅሀፍ መመልከት ይቻላል።
ስለዚህ ታሪክ እያጣቀሱ ያም የኔ ነው፣ ይሄም የኔ ነው ማለት መዘዙ ብዙ ነው። ሌሎችም ተመሳሳይ ጥያቄ ያነሳሉና። በርግጥ አብዮት አደባባይ ከስም ባለፈ የቤተ-ክርስትያን ንብረት አይደለም። ካርታ ብለው የሚያቀርቡትም ከእምነት ተቋም የማይጠበቅ አይን ያወጣ ማጭበርበር ነው። ባለቤትነትን የሚያሳይ ካለመሆኑም ጋር መሀተም የለውም። ህጋዊ የባለቤትነት ሰነድ የላቸውም እንጂ ቢኖራቸው እንኳ መነጠቅ ነው ያለበት። ምን ሲባል ነው አደባባይ የአንድ ሃይማኖት ንብረት የሚሆነው? ጭራሽ አደባባይ እናስፈቅድ እንዴ? ሆ!
እንዲያውም የምታነሱት የአፄው ዘመን ታሪክ ቤተ ክርስትያን ምን ያክል ምዝበራና ብዝበዛ ላይ እንደነበረች የሚያሳይ፣ የዚያ የጭቆና ዘመን ጠባሳ ማሳያ ነው። ሊታፈርበት ሲገባ ጭራሽ ጅብድ?! "ያልፈሳንበት ዳገት የለም" አለች አሉ አህያ። ቤተ ክርስትያን ምዝበራና ብዝበዛ ላይ ስለነበረች እኮ ነው አፄ ቴዎድሮስ ጋር ተፋጣ ጳጳሱን እስከሚያስር፣ ካህናትን እስከሚያባርር፣ መሬት እስከሚነጥቅ የደረሰው። ይህ ሁሉ ከመሆኑም ጋር ተበደልኩ ባዩዋም እሷው ሆናለች። "እናትና አባቱን የገደለ ሰው ትዝ ይለኛል። የፍርድ ውሳኔ ሊሰጥበት ሲል 'እናትና አባት የሌለኝ ሰው ነኝና ምህረት ይደረግልኝ' አለ" የሚል አባባል ነበር። ይህንን ነውረኛ ተግባር ግን በደንብ አልገልፅልኝ አለ።

ብቻ መስቀል አደባባይ ተብሎ ስለተሰየመ የኛ ነው ካሉ ነገ ከነገ ወዲያ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ፣ ልደታ ክፍለ ከተማ፣ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍል ከተማ፣ ጨርቆስ፣ አቦ፣ ሀናማርያም፣ ቀጨኔ፣ አማኑኤል፣ ... ጎዳናና አደባባዩን ሁሉ ካላስረከባችሁን አይሉም አይባልም። ስለዚህ ሳይቃጠል በቅጠል!
በነገራችን ላይ ቅዳሴና አዛኑ የሚለው ዘፈን ባዶ ኳኳታ እንጂ መሬት ላይ ብዙ መገፋፋት ነው ያለው። ለቤተ ክርስቲያን በ100 ሜትር ርቀት ላይ እንዴት የመስጂድ ቦታ ይሰጣል ብለው እነ ምህረታብ ሲፈጥሩት የነበረው አካኪ ዘራፍ እሩቅ አይደለም።
ባጭሩ መንግስት በለሰለሰ የዲፕሎማሲ ቋንቋ ቢነግራቸውም እየገባቸው አይደለም። ጭራሽ ወደ ግርግርና ሙስሊሙን ወደ መተንኮስ እየሄዱ ነው። በየዘርፉ ያሉ አካላትም ያጋደለ ፅሁፍ እየፃፉ ጫና በመፍጠር ላይ እየተረባረቡ ነው። መንግስት ሆይ! በዚህ የአደባባይ ጉዳይ በነሱ ጩኸት ተሸንፈህ ታሪካዊ ስህተት እንዳትፈፅም። ሰዎቹ ለወቅታዊ ብሶታቸው ማባበያ አድርገህ እንድታቀርብላቸው ነው የሚፈራገጡት። እንዲያውም ህዝባዊ ተቋማት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል፣ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል፣ አማኑኤል ሆስፒታል፣ ከሚሉ ስያሜዎች መውጣት ነበረባቸው።
=
ኢብኑ ሙነወር
የቴሌግራም ቻናል፦
https://hottg.com/IbnuMunewor
በህይወታችን በተደጋጋሚ ከምንፈፅማቸው ፀያፍ ስህተቶች ውስጥ አንዱ የሌሎችን ሚስጥር መዝራት ነው። የሚገርመው የራሳችን ሚስጥር ያመንነው ሰው ለሌላ ቢያወጣብን የማንወድ ሆነን ሳለ ለሌሎች አለመታመናችን ነው። አስገዳጅ ሁኔታ ካልገጠመ በስተቀር የሌላን ሰው ሚስጥር ለባልም ይሁን ለሚስት፣ ለቅርብም ይሁን ለሩቅ ማውጣት አይገባም። የጓደኛውን ሚስጥር እንደ ዋዛ ለሚስቱ ይነግራል። ሚስቱ ለቅርብ ጓደኛዋ፣ ያቺ ደግሞ ለሌላ ቅርብ ጓደኛዋ ወይም ለባሏ፣ ... እያለ ያደባባይ ሚስጥር ይሆናል። የቤቷን መከፋት ለጓደኛዋ ትነግራለች። ወ/ሮ ጓደኛ ለባሏ፣ እሱ ለጓደኛው፣ ... እያለ መጨረሻ መቆራረጥ፣ መቀያየም ያስከትላል። ከዚህ አይነት ጥፋት የሚተርፈው ከስንት አንድ ነው። ከመሰል ጥፋቶች ላይ ላለመውደቅ ይህንን የነብዩን (ﷺ) ሐዲሥ ማስታወስና መተግበር ተገቢ ነው፦
لا يُؤْمِنُ أحَدُكُمْ، حتّى يُحِبَّ لأخِيهِ ما يُحِبُّ لِنَفْسِهِ
{አንዳችሁ ለራሱ የሚወደውን ለወንድሙ እስከሚወድ ድረስ አያምንም።} [ቡኻሪ]

ሚስጥርህ እንዲጠበቅ ትውዳለህ ኣ? እንግዲያውስ የሌሎችን ሚስጥር ጠብቅ። ለራስህ የምትጠላውንም በወንድምህ ላይ አትፈፅም። ሚስጥርህ ወጥቶ ማግኘት እንደማትፈልግ ነጋሪ አያሻም። ልክ እንዲሁ ወንድምህም ሚስጥሩን ስትዘራበት ድንገት ቢደርስ ምን እንደሚሰማው አሰብ። ያመንከው እንዲከዳህ እንደማትፈልገው አንተም ላመነህ ታመን። የስነ ምግባር፣ የሞራል ቁንጮ የሆኑት ውዱ ነብይ (ﷺ) እንዲህ ይላሉ፦
أدِّ الأمانةَ إلى منِ ائتمنَكَ، ولا تخُنْ من خانَكَ
"አምኖ ለሰጠህ አማናውን አድርስ። የካደህን አትካድ።] [አሶሒሐህ፡ 423]
=
ኢብኑ ሙነወር
https://hottg.com/IbnuMunewor
HTML Embed Code:
2024/06/01 00:37:01
Back to Top