TG Telegram Group Link
Channel: Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Back to Bottom
የሰማእትነት ዜና…

"…በሶሪያ ደማስቆ በቅዱስ ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሥርዓተ ቅዳሴ ላይ በነበሩ የሶርያ የግሪክ ኦርቶዶክስ አማኞች ላይ የሶሪያ ጽንፈኛ የእስልምና አሸባሪዎች በፈጸሙት የአጥፍቶ መጥፋት የቦንብ ጥቃት ወደ 25 ያህል ምእመናን፣ ካህናት እና ዲያቆናት ሕፃናት ጭምር ሲሞቱ ወደ 80 ያህሉ ደግሞ ቆስለው ወደ ሆስፒታል ገብተው ህክምና በመከታተል ላይ እንደሚገኙ ከሥፍራው የሚወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።

"…ወዲያው ነው የአንጾኪያው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ኤፍሬም ፪ኛ እና በዱሊያ የማር ኤልያስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዮሐንስ ፲ኛ በደማስቆ ዱሊያ አካባቢ ወደሚገኘውና ጥቃቱ ወደደረሰበት የቅዱስ ኤልያስ ቤተክርስትያን በመሄድ ለሞቱት ጸሎተ ፍትሃት፣ ለቆሰሉትና በህክምና ላይ የሚገኙትን ደግሞ በሆስፒታል በመሄድ ሲያጽናኑ፣ ሲያበረቱና ሲጸልዩላቸው እንዳረፈዱ የተነገረው።

"…በኢትዮጵያ ይሄ ይናፍቅህሃል። በዝቋላ ለታረዱ አባቶች የቤተ ክርስቲያኒቱ ቴሌቭዥን ሳይቀር የሀዘን መግለጫ እንኳ የሰጠው አሁን ከደቂቃዎች በፊት ነው። በሸገር ዙሪያ አቡነ ሳውሮስ ሀገረ ስብከት እየታረዱ ስላሉት ካህናት የተነፈሰ የለም። የኔታ ይባቤ ታፍነው አቡነ አብርሃም፣ አባ ገብረ መድህን ታፍነው አቡነ ቀለሜንጦስ ትንፍሽ አላሉም። የቲክቶክ ሐዋርያቱ እነ አኬም እንኳ የዝቋላው እርድና ጨፍጫፊ ሳይታያቸው የሶሪያውን አራጅ እስላም ጠቅሰው ሲወበሩ እያየሁ ያሁኔያ… ለማንኛውም የሰማዕታቱ በረከታቸው ይደረንብን…!

"…የዘማሪት ዮርዳኖስ ደረጀን ጉዳይ በተመለከተ ሓሳቤን በነገው ዕለት አቀርባለሁ። የኔታ ይባቤ እስከአሁን እዚያው መኮድ ናቸው፣ አባም እስከአሁን የትእንዳሉ አልታወቀም። ደረጄ ዘወይንዬም ፍርድቤት አልቀረበም እንጂ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ እንደሚገኝ ታውቋል።

• ምኑን አረፍኩት ግን…?
• ስለ የኔታ ይባቤ
     አጭር መረጃ

"…በእነ ዳንኤል ክብረት እልህ፣ በእነ ፓስተር ምስጋናው አንዱዓለም ጉትጎታ ዘመነ ካሤን ትነግሣለህ ብለው የቀቡት እርሳቸው ናቸውና እርሳቸውን ይዘን አስረን ስናበቃ የኔታ ለእነ አርበኛ ዘመነ ካሤ ደውለው ትግሉን እንዲያቆሙ እናደርጋለን በሚል የፌደራሉ አገዛዝ የኦሮሙማው ብልጽግና መከላከያ ሠራዊቱን ልኮ ከገዳማቸውና ከጉባኤ ቤታቸው ወስዶ ባህርዳር መኮድ ግቢ እንዳሰራቸው መግለጼ ይታወሳል።

"…የኔታ ይባቤን እነ ዳንኤል ክብረት ወደ አዲስ አበባ መጥተው በዚህ ምርመራ እንዲፈጽማባቸው አዘው ነበር ቢባልም ከመካከለኛው እስከ ከፍተኛው አመራር ድረስ ያሉት የብአዴን አመራሮች ሂደቱን በመቃወማቸው ምክንያት ሊቁ ወደ አዲስ አበባ ሳይላኩ ቀርተዋል። በመሃልም የሀገሬው ሕዝብ በግልጽ ሳይፈራ፣ ሳይሳቀቅ በሰላማዊ ሰልፍ ብልፅግናን "አባታችንን በአስቸኳይ ልቀቁልን በማለት እስከመጠየቅ ደርሷል።

"…በመጨረሻም የአገው ተወላጆች የሆኑ የአገው ሸንጎ አባላት ሊቁን እንዲከሱ ከላይ ከፌደራል ጫና የተደረገ ቢሆንም የአገው ሸንጎ አባላቱም በዚህ ጉዳይ ፈቃደኛ ሳይሆኑ መቅረታቸው ነው የተነገረው። በመጨረሻም ከቤተ ክህነቷ በቀር ሕዝቡ ውስጥም ከውጭም የኔታ ይፈቱ የሚለው ጥያቄ እየበረታ በመምጣቱ የክልሉ ብልጽግና ብአዴን ከፌደራል እጅ ተቀብሎ ሊቁን ዛሬ ከሰዓት በኋላ ለምርመራ በሚል በፓሊ እና ጋምቢ መሃል በቀበሌ 12 በሚገኘው 2ኛ ጣቢያ አስገብተዋቸዋል።

• ይልቅ አይበጃችሁም እና ሊቁን ያለምንም ቅድመ ሆኔታ ልቀቋቸው።

• እኔማ ምኑን አረፍኩት…?
😂😂😂

• ደኅና እደሩልኝ
"…ውሻ ወደ ትፋቱ ይመለሳል፥ ደግሞ፡— የታጠበች እርያ በጭቃ ለመንከባለል ትመለሳለች እንደሚባል እውነተኞች ምሳሌዎች ሆኖባቸዋል። 2ኛ ጴጥ 2፥22

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"…መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
"…እየጠራ መጣ ኩል እየመሰለ…

"…የሚሰማኝ አድማጭ ባይኖርም እየሆነ ስላለው ነገር እንዲህና እንዲህ ይሆናል ብዬ አስቀድሜ የነገርኳችሁ ነገር እኮ ነው እየሆነ ያለው። መቼም ሐበሻ የሞተና ከዓይን የራቀ ሰው አመስጋኝ ሆኖ ነው እንጂ…ሃኣ…?

"…ምንም አትላኩልኝ። አዲስነቱ እያያችሁ ለማታዩ፣ እየሰማችሁ ለማትሰሙ ለእናንተ ነው እንጂ አይደለም። ከዚህም የባሰ የከፋው ቀን ደግሞ ከፊት የሚመጣው ቀን ነው። እኔማ በዚህ ጉዳይ እኮ ከስንቱ ተጣለሁ። ከምወደው ከመረጃ ቴቪና ከኤልያስ ክፍሌ፣ ከማከብራቸው እንደ ቤተሰብም ከማያቸው ከእነ ጋሽ ሰሌና ከመሲም የተለያየሁበት ጉዳይ እኮ ነው። ተፋቱኝ። ምንም አትላኩልኝ።

"…በእርግጠኝነት እነግራችኋለሁ እኔ ከኢዩ ጩፋ፣ ከእስራኤል ዳንሳና ከዮናታን በተሻለ መልኩ ትንቢት መናገር የምችል ይመስለኛል። ከምር እኔ እኮ የሚሰድበኝ፣ የሚረግመኝ፣ የሚያዋርደኝ እንጂ የሚሰማኝ፣ ከልቡ የሚያደምጠኝ የለም እንጂ ከዘመኑ የጴንጤ ማፍያ ነቢያት በብዙ ሳልሻል አልቀርም ብላችሁ ነው? 😂 ቀልድ ነው ደግሞ የምር አርጋችሁ እንዳትይዙት።

"…በአሁን ሰዓት አስረግጬ የምነግርህ ነገር ቢኖር እንደ እኔ የኢትዮጵያም፣ የዐማራም፣ የትግሬና የኦሮሞም ቦለጢቃ የገባው ሰው ያለ አይመስለኝም። ከምር እውነቴን ነው። ይሄ ጅማሮ ነው። ከባዱ ቀጥሎ የሚመጣው ነው። ዐማራ ግን ይሄንንም ተሻግሮ ያሸንፋል።

"…ይልቅ ልንገራችሁማ እስከ አሁን ባይፈቱም የኔታ ይባቤ ከፎሊስ ጣቢያ ወደ መንበረ ጵጵስና ተወስደው በዚያ ነው ያደሩት። ደረጄም ፍርድ ቤት ቀርቦ ወንጀሉ ተነብቦለታል። ሃኪሞች ሳይራቡ ተርበዋል ብለሃል ነው አንደኛው ክሱ። ዐቃቤ ሕግ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ቢጠይቅም ፍርድ ቤቱ ግን ከሀገር እንዳይወጣ አግዶ በ50ሺ ብር ዋስ ይፈታ ዘንድ ወስኗል። ዐርብ ርዕሰ አንቀጽ ይኖረናል።

•ዘመዴ ነኝ ከጮቄ…
የፍርድ ቤት ውሎ…

"…ከቤሮው ለምሳ እየወጣ በመንግሥት የጸጥታ ሰዎች አማካኝነት በቁጥጥር ስር ውሎ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ የከረመው የማኅበረ ወይንዬ ተክለሃይማኖት መንፈሳዊ የጉዞ ማኅበር እና የስለ ኢትዮጵያ ዝም አንልም የፀረ ግብረ ሰዶማውያን ማኅበር መሥራችና ሊቀመንበሩ መምህር ደረጄ ነጋሽ በዛሬው ዕለት ፍርድ ቤት መቅረቡ ተሰምቷል።

"…ሦስት ጠበቆች የቆሙለት መምህር ደረጄ ነጋሽም በፌደራል ፎሊስ መርማሪ አማካኝነት የተከሰሰበትና ለእስር ያበቃውን ወንጀል በችሎቱ ላይ አንብቦ ለፍርድ ቤቱ አሰምቷል። ክሱ የሽብር ክስ ነው።

• መንግሥታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ
• ሃኪሞቹ ሳይራቡ ተራቡ ብሎ በሚዲያ አውርቷል
• መንግሥት በኅብረተሰቡ ዘንድ አመኔታ እንዲያጣ እያደረገ ነው ወዘተ በሚል ነው የከሰሰው። በዚህም ምክንያት የተጨማሪ 14 ቀን የምርመራ ጊዜ ይፈቀደለት ዘንድ ፍርድቤቱን ጠይቆም ነበር ተብሏል።

"…መምህር ደረጄም ይሄ ክስ ፍጹም ሐሰት ነው በማለት የመለሰ ሲሆን ተከላካይ ጠበቆቹም "ይሄ የሽብር ተግባር አያስብልም፣ ደንበኛችን ሓሳባቸውን በሚዲያ በነፃነት ነው የገለፁት በማለት በነፃ ይለቀቅ ዘንድ ወይም በዋስ ይፈታ ዘንድ ያቀረቡ ሲሆን መርማሪውም የዋስትና መብት እንዳይሰጠው ተቃውሟል።

"…በመጨረሻም ግራ ቀኙን ያየው ፍርድ ቤቱ መምህር ደረጄ ነጋሽ በተከሰሱበት ወንጀል በ50 ሺ ብር ዋስትና ከእስር ተፈተው መከራከር እንደሚችሉ ፈቅዶ ነገር ግን የፍርድ ሂደቱ እስኪጠናቀቅ ድረስ ከሃገር እንዳይወጣ በሚል ወስኖ ፋይሉን ዘግቶ ወደ መዝገብ ቤት መላኩ ተነግሯል። ነገ ጠዋት የዋስትናው ሂደት ከተሟላ ደረጄ ወደ ቤቱ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል ብለዋል የፍርድ ቤት አከባቢ ወፎቼ።

• በዘማሪት ዮርዳኖስ ጉዳይ ላይ ነገ ከምስጋና በኋላ በርእሰ አንቀጽ መልክ የመጨረሻ ቃሌን እሰጣለሁ።

"…
"…በበሬና በአህያ በአንድነት አትረስ። ዘዳ 22፥10

"…እንደምን አደራችሁ?
"…እንደምን አረፈዳችሁ?
"…እንደምን ዋላችሁ?
"…እንደምን አመሻችሁ?

"… መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
አጫጭር መረጃዎች

፩ኛ፦ በዝቋላ ደብረ ከዋክብት አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ገዳም ለዓመታዊው የብልፅግና ወንጌል ግብር የታረዱት አበው መነኮሳት የአስከሬን ለቀማ ተካሂዶ የኦሮሞ ብልጽግና እንደተለመደው የሬሳ ማስረከብ ሥርዓት ፈጽሟል።

፪ኛ፦ ለ7 ተከታታይ ቀናት በወኅኒ ቤት የከረሙት ሊቁ የኔታ ይባቤ ከወኅኒ ቤት መፈታታቸውና በዚህ ሰዓት ባሕርዳር ቅዱስ ጊዮርጊስ በመንበረ ጵጵስናው እንዳሉ ተነግሯል። ጉዞ ወደ ጉባኤ ቤታቸው።

፫ኛ፦ ከመሥሪያ ቤቱ ወደ መኖሪያ ቤቱ ለማምራት ወደ መኪናው እያመራ ሳለ በብልፅግና ፎሊሶች ተይዞ ሜክሲኮ ፌደራል ፖሊስ የከረመው መምህር ደረጄ ነጋሽ ፍርድቤቱ ትናንት በዋለው ችሎት የውጭ ጉዞ እገዳ ጥሎበት በ50 ሺ ብር ዋስትና ይፈታ ብሎ የነበረ ቢሆንም፣ ቤተሰብ ዛሬ የዋስትናውን ብር ይዞ ለማስፈታት ቢሄድም ከሳሽ ፖሊስ ይግባኝ ስለጠየቅኩበት አይፈታም ብሎ እዚያው ዘብጥያ እንዳስቀረው ተነግሯል።

፬ኛ፦ የአቡነ ቀለሜንጤስ ዘመድ ሁላ እንደሆኑ የሚነገርላቸውና ለገጣፎ ላይ ታፍነው እስከ አሁን የት እንዳሉ የማይታወቁት የአርበሃራ መድኃኔዓለሙ አባት አባ ገብረመድኅንም በእጅ ስልካቸው ወደ ቤተሰብ እየተደወለ እንድንለቃቸው ከተፈለገ አንድ ነጥብ አምስት ሚልዮን ብር በባንክ እንዲያስገቡ አፋኞቹ እየጠየቁ ስለመሆኑ ተሰምቷል።

• ሲኖዶሱ ግን 🙏🙏🙏

• ዘመዴ ነኝ ከጮቄ ተራራ…!
“…እናንተ ግን ተጠንቀቁ፤ እነሆ፥ አስቀድሜ ሁሉን ነገርኋችሁ።” ማር 13፥23። “…ለእናንተም የምነግራችሁ ለሁሉ እላለሁ፤ ትጉ።” ማር 13፥37። “…የምነግራችሁ ገና ብዙ አለኝ፥።” ዮሐ 16፥12። “…የማይገለጥ የተሰወረ የለምና፥ የማይታወቅም ወደ ግልጥም የማይመጣ የተሸሸገ የለም።” "…በልቡም የተሰወረ ይገለጣል… 1ኛ ቆሮ 14፥28

• እንደምን አደራችሁ?
• እንደምን አረፈዳችሁ?
• እንደምን ዋላችሁ?
• እንደምን አመሻችሁ?

• መልሱ እግዚአብሔር ይመስገን ብቻ
ሰላም ለእናንተ ይሁን…

"…ምንም እንኳ ለእኔና የእኔ ቤተሰብ ለሆናችሁ ለእናንተ ለእኔ ወዳጆች አዲስ ጉዳይ ባይሆንም በእኔ በኩል ለዓመታት ስጮህበት የነበረ ጉዳይ ቢሆንም አሁን ግን ከሁሉ ነገር ገለል ብዬ አየር እየሰበሰብኩ ካለሁበት የእረፍት ስፍራ ድረስ ስቅታ እስኪገድለኝ መተንፈስ እስኪያቅተኝ ድረስ ሰሞኑን ዘማሪት ዮርዳኖስ ደረጄን እና ቀሲስ ደበበ እስጢፋኖስን እንዲሁም ዘማሪት ፋንቱ ወልዴን በተመለከተ በተደጋጋሚ ስሜ የተነሣበት አጀንዳ ለመመከትና ለአስራ ምናምነኛ ጊዜም ልዘበዝባችሁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ እንደተለመደው በቲክቶክ መንደር መድረኬ ላይ ነጭ ነጯን ልቀውጠው ለአጭር ሰዓት ልመጣ ነኝ። አላችሁ አይደል…?

http://tiktok.com/@zemedkun.b
HTML Embed Code:
2025/06/28 01:08:30
Back to Top