TG Telegram Group Link
Channel: የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል
Back to Bottom
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል via @like
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 . 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር የፉሲካው በግ  እግዚአብሔር ለእስራኤል የሰጣቸው ሕግ የመጨረሻው ዕለት የፋሳኪው በግ ቀንዱ ያልከረከረ ጠጉሩም ያላረረ ተባዕት የሆነ ጥፍሩ ያልዘረዘረ የተባለው በግ የዓለማት ፈጣሪ ክርስቶስ ነው ንጹሐ ባህሪ 10 ቀን ይዘው 14 ቀን ያቆዩት ሕማማቱን ነው አራቱን ቀናት በጉን በማኅበር ሆነውም አረዱት አይሁድ ክርስቶስን በመስቀል ሰቀሉት…
ዮሴፍ ታሪኩ👆
በጣም ጥሩ ነው ርዕሱ ከመዋቅሩ ጋር አልተጋጨም እንደመነሻ ...
ስህተት
1) ውበት የለውም በሳድስ መግጠምህ ቅልም አውርዶታል
2 ) ቃላት "መላእክ ሞት "
3) ሀሳብ ድግግሞሽ
.….......….……………………
የዳኛ ውጤት።                 44/50
  የlike።                           ?/50
   ቦነስ።                             5/10
ጠቅላላ ድምር                      ???
የዘማሪ ትንሣኤ ፍቃዱ ግጥሞች ቻናል via @like
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆 . 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ                  አህዱ አምላክ  አሜን። “እነሆ፥ እንደ ሌባ ሆኜ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ እፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”  — ራእይ 16፥15              ብኩርናን እንጠብቅ ብኩርናን እንጠብቅ    የተቸረችንን ሳለን  በልጅነት፣ በ40 በ80 ወደ       ቤቱ መጥተን…
በረከት ከበደ 👆
መነሻ ሀሳቡ ጥሩ ነው
ሰፊ እንደመሆኑ ርዕሱ ከመዋቅሩ ጋር ቁርኝቱ በማጥበቅ ሀሳቡ ማሳጠር ትችላለህ ነገር ግን ያ ስላልሆነ ንባብ ሆነ ግጥም ደግሞ በባህሪው አንባቢው በቀላሉ መረዳት የለበትም ቀለም እንዲኖረው ይዘቱ ላይ ማትኮር በጥቂት ቃላት ብዙ ማለት ልምምድ ማድረግ።
.....…………………………………………

የዳኛ ውጤት።                 45/50
  የlike።                           ?/50
   ቦነስ።                             6/10
ጠቅላላ ድምር                      ???
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር

ይህችን አመት ተወኝ
አልጉደል ከቁጥር ባይጥምም ስራዬ
ይህችን አመት ብቻ አኑረኝ ጌታዬ
ሁሉን እያሟላህ አንዳች ሳይጎድልብኝ
ቅጠል ነው ዙሪያዬ ፍሬ ስትሻብኝ
ምን ጎደለ ከእጅህ ለወይንህ ዘለላ
ነጠፈች ከፍሬ ቢመቻትም እንኳን ብትኖርም በተድላ
ልክ እንደመሻትህ በሀሳብህ ባልገኝ
በመላዕኩ ምልጃ
በእመብርሀን ምልጃ ይህችን አመት ማረኝ
ደግሞ ለቀጣዩ ቆሜ እንድለማመን የምህርትህን ካባ
አልብሰኝ ነጭ ልብስ ደጅህ እንድገባ
እንጅማ እንጅማ
ገሸሽ ካለብኝ የለበስኩት ኩታ ነጩ ነጠላዬ
ለሰው የሸሸኩት ወጥቶ የሚያሳጣኝ ጉድ አለ ጀርባዬ
የእግሬን ኮቴ ብቻ እየተከሉ የሚያሞጋግሱኝ
ከልቤ ጥቂቷን ብትገልጥላቸው ...
እንዴት ባለ ቃል ነው ስሜን የሚያነሱኝ
ታዘበኝ እንግድህ
ሁሉን እያሟላህ ከአትሮኖስህ ከመንበር ብታቋቁመኝም
ፍሬ አልባ ነኝ አንድ አልጠቀመኝም
ታዘበኝ እንግድህ ዘውትር ሲፈተት ስጋህ ቤተመቅደስ
አለሁ ስጎሳቆል በርሀብ ጠኔ ሳለቅስ
ታዘበኝ እንግድህ ቅዱስ የሆነ ደምህ ሰርክ እየነጠፈ
ተጠማሁ ነው ቃሌ ምንጭ ይለማመናል ዥረት እያለፈ
ታዘበኝ እንገድህ መሰቃያ ያልኳት ገመዷ ብትመክረኝ
ለንስሀ የሚሆን ጥቂት ጊዜ አጠረኝ
ታዘበኝ እንግድህ ቅዱስ ቤተመቅደስ ብታደርገው መልኬን
ከሚዛን አይቀርብም ክቡድ ነው ሸክሙ የመከፋት ልኬን
የዘወትር ልመና ሰርክ ጥያቄዬ
የምመፃፀነህ ይሄ ነው ጌታዬ
ምን ይዤ ነው የምጠብቅህ በምን ልኬ ልሰናዳ
ታውቀው የለ የእኔን ጉድለት ግልፅ አይደለ የኔ ጓዳ
ሳልዘጋጅ በንስሀ ስጋ ደምህ ሳይገነባኝ
የመምጫህ ቀን የሚገለጥ ምን ገፅ አለኝ
እያወከው ጉልድፍ እግሬን አካሄዴ የተምታታ
እስከመቼ አንገድ ልድፋ እንደወጣሁ ከሰው ተርታ
ጥዑም ጠረን እያማረኝ የሚስማማ ለመቅደስህ
ጎልዳፋ ነው የእኔ ምላስ በምን ከንፈር ላወድስህ
እድሜ ገፋሁ ሸበት ሞላው መላ አካሌ
ከእድሜ እኩል 'ማስመስለው በምላሴ መሸንገሌ
ተጎተትኩኝ ወደሀጥያት ተዘነጋኝ የዋልክልኝ
አፍካው ልቤን በመንፈስህ ታሪክ መልኬን ቀይርልኝ
ተጨነቀች ድኩም ነፍሴ በርትቶባት ሀጥያት ሸክሟ
አቅርቅራ ጉዞ ሆነች እያስማጣት ክፉ ህመሟ
ይብቃሽ በላት ይህችን ነፍሴ አለምልመኝ በመንፈሰህ
ተቀይሮ የሀጥያት ልቤ ምሉዕ ሆኜ ላወድስህ
እስከመቼ በሀጥያት ጎጆ በደል ኩራዝ እንዳበራሁ
የሀጥያት ጣሪያ እያቆምኩኝ የሀጥያት ቤት እየሰራሁ
ይሄን መልኬን ታውቀዋለህ ሸፍኖት ነው ነጭ ነጠላ
ጥቁርነት ያጠለሽው ውበት የለው ከአንተ ሌላ
የግድ የግድ ደጅህ ቆሜ ስላነባሁ
የግድ የግድ ከማህሌት ስለገባሁ
የግድ የግድ የግድ የግድ ብሸፋፈን በነጠላ
በምን ያህል እንዳደፈ ታውቀዋለህ የእኔን ገላ

ምን ይዤ ነው 'ምጠብቅህ...
በምን መልኩ ልስተካከል ከየት በኩል ነው 'ምቃና
እየሸሸሁ ስትከል ስትፈልገኝ የእግሬን ዳና
የማስመሰልን ነጠላ ገፈፍ ሲል ከትከሻ
እግር እንኳን አላጣሁም ልብን እንጅ መመለሻ
እንደት ሆኜ ልጠብቅህ...
እፈራለሁ መጣ ሲሉኝ ሸርተት አለ አፈር ገላ
እንደት ብዬ ጠበቅ ልበል ፅድቅ አልሰራሁ ከሀጥያት ሌላ
ሙሽራ ነህ ከእጄ አይጠፋ የሚለኮስ የፅድቅ መብራት
ከደጅ አልቅር እንድታደል አብሮ መግባት
ከረፈደ ከምሯሯጥ መብራት ጠፍቶ ከምምታታ
እንደት ብዬ ነው የምዘጋጅ ምን ልተካ በምን ቦታ
ቅጠልነት እንዳይከበኝ...
ፍሬ አልባነት እንዳይከበኝ የዛሬ አመት ስትመጣ
ልቦናዬን መልስልኝ ከሀጥያት ህይወት እንድወጣ

ዓቢይ አለሙ(ሚተራሊዮን)

ግጥሙን ከወደዳችሁለት ላይክ እና ሼር ተባበሩት

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. @Tins7
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር

አንተ ማን ብትሆን ነው?

               የቅላፄህ ውበት
    እጄን እንድሰጥህ ቃላትህ ማረከኝ
              የአንደበትህ ለዛ
     የመልክህ ፍሰት ስሜቴን የገዛ
    ፍቅርህ ተሰንቅሮ ፀርሶ ልቤ ላይ
   ጥልቅ ፍቅር የያዘኝ ካንተ የማይለየኝ
         አንተ ማን ብትሆን ነው?
             ሚስጥሩን ንገረኝ

           በየትኛው አቅም እንዴት
       ባለ ጥበብ ስስ ነፍሴን ቃኘኸው

          እንዴት ብትበረታስ አለቱን
        መንፈሴን በድል አገኘኸው
     
            እስቲ በል አስረዳኝ
            ሚስጥሩን ንገረኝ
         አንተ ማን ብትሆን ነው
             ልቤን የረታኸው
           የጨረቃን  ውበት
           የፀሀይን ድምቀት
             የአበባን ፍካት
         የመውደድን ጥጋት
  የፍቅርን ሸማ በላይህ ደርበህ
            ልቤንም የሰረክ
        አንተ ማን ብትሆን ነው?
            ሚስጥሩን ንገረኝ

✍️ብሌን ስንታየሁ

ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. @Tins7
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር
ይናፍቃል ለካ!


ማለዳ ተነስቶ ነጠላ አጣፍቶ በቤቱ መገኘት
የቤተክርስትያን ደጅ ዝቅ ብሎ መሳም በእምነት ማሻሸት
ስዓታት ኪዳኑን በጥኡም ዜማ በካህናት መስማት
ይናፍቃል ለካ ተቀብሎ ማዜም
በአንድነት በህብረት


አሀዱ አብ ተብሎ ቅዳሴን ማስቀደስ
በፍቅር በህብረት ተሰጥኦን መመለስ
በእጣኑ መዓዛ በመስቀሉ መቅደስ
ደጀ ሰላም ገብቶ ፀበል ፃዲቅ መቅመስ
ይናፍቃል ለካ በካህኑ መስቀል በእጆቹ መዳሰስ


እያወክ በስህተት ሳታውቅም በስህተት
እግዚአብሔር ይፍታህ የሰራኽሁ ኃጢያት
መባል በካህኑ ከእስራት መፈታት
ይናፍቃል ለካ የአባቶች ድምጽ መስማት



የህፃናት ድምፅ መስማት ለቁርባን መሰለፍ
ሁሉ ነጭ ለብሶ ከቤቱ መሳተፍ
ቅዱስ ወንጌል  መሳም ታዓምሯ መስማት
ይናፍቃል ለካ የዲያቆን ድምፅ የካህን በረከት


የሰንበት መዝሙር በህብረት መዘመር
ትምህርተ ወንጌል መማር በመምህር
ተሰልፎ መውሱድ የቅዳሴ ፀበል
ይናፍቃል ለካ ሰላም ግባ መባል


አቅለን ያየነው በሳምንት አንድ ዕሁድና ወር በቤትህ መገኘት
ተኝተን አረፈድን ባላሰብነሁ ሰዓት
መጣብን ይህ መዓት
አዎ አምላካችን ናፍቆናል ይህ ሁሉ በዚች አጭር ቀናት
መኃሪው ጌታችን ይቅር በለንና
መልስን ወደ ቤትህ


ወለተ እየሱስ

ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. Tins7
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር

Date: May 28, 2024
Subject: ✍️የመኖር ትርጉሙ ✍️

በጠዋት ተነስቶ ፊትን ታጥቦ
ልብስ ለብሶ ቁርስን ተመግቦ
መውጣት ደግሞ ሲመሽ መግባት
መች ይበቃል ስቆ መጫወት
ብዙ ጓደኛ ብዙ አጫዋች
ለምንሰራው ስራ ብዙ ኮማች
ቢከበንም ዙሪያ ገባችን
ካላረፈ ቀዥቃዣው ልባችን
የቱ ጋ ነው የህይወት ትርጉም
የቱ ጋ ነው የመኖር አቅም
ሳንጠራው ከጎን ያለ
በባህሪው እኛን የመሰለ
በርቀት ውስጥ የታገለ
የሰው ከንቱ ያልተባለ
ይሄ ሰው የታለ
ከላይ ከአምላክ ለኛ ተብሎ የታደለ
ኧረ ይሄ ሰው የት አለ
የልቤን እውነት አይቶ
የማወራውን ከልብ ሆኖ ሰምቶ
ማንም የማይደፍረኝ እሱ እያለ ከቶ
እሱ ነው የመኖር ትርጉሜ
የሚረዳኝ እንድኖር በአቅሜ
ስታመምም የሚገባው የኔ ህመሜ
እሱ እኮ ነው ለኔ አለሜ
የማስብው በእውኔ አይደል ሁሌ በህልሜ
ርቀቱ ብቸኝነት የማይፈጥር
ባጠፋ እንኳን ቂም በቀልን የማይቋጥር
እሱ ነው የኔ ትርጉም
እስካገኘው የሆነብኝ ህልም
አምላክ ፈቅዶ ያንን ሰው (ትርጉሜን) ቢያሳየኝ
ይህን ብቻ ቆሜ ምመኝ። ✍️✍️✍️

ፋሲካ

---

ግጥሟን ከወደዳችሁላት ላይክ እና ሼር ተባበሯት

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. Tins7
🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆🏆
. 12 ኛ ዙር ግጥም ውድድር

ተፅናንቻለሁ ተረጋግቻለሁ
እንባዬ ቁሞ መሳቅ ጀምሬአለሁ
እማ ታምኛለሽ አንቺን ቀብሬ መኖር ቀጥያለሁ
እማ እስቲ ቀና በይ ታዘቢ ሁሉንም
ታመሽ ያላየሽ ለቀብር ሲሽቀዳደም
እናታቸው ሞተች ኑ ለቅሶ እንድረስ
ለቀብር ለሳልስት ሠዉ ሲመላለስ
እዝን ሲመጣ እኛ ስንጠረቅቅ
ይታወቀኛል ያይን እንባዬ ሲደርቅ
ሁሉም እግዜር ያፅናሽ እያለ ያቅፈኛል
ለኔ ግን ያኔ እግዜር ይማርሽ ቢሉሽ ይሻለኛል
አንድ ልቤ
እንዲ በህመም ከምትሰቃዪብኝ
እንኳንም ሞተሽ አረፍሽልኝ
ሞት ላይቀርላት በበሽታ ማቃ
እንኳንም እግዜር ወሰዳት በቃ
እልና
ቀንም እድሜ ነው ጠረኗ መድሀኒት
እንዲም ብትኖርልኝ እናቴ ባትሞት
ገና እኮ ናት ብዙ አልኖረችም
የልጅ ልጆቿን ወግ አላየችም
ምነው ጨከንክብኝ እግዜር
ማን አለኝ እኔስ ከሷ በቀር
በምህረትህ አመታትን ምታቀዳጅ ጌታ
ምነው የእኔንስ  ሀጥያት ማትፈታ
የበደሌ ብዛት ከዚ ባያስጠለኝ
እንዴት ለኔ ምህረት ማትሰጠኝ
ይላል ልቤ ሀዘኔ በርትቶ ማጣቴ ሲያገረሽ
አለቅሳለው ብታይ በከንቱ አንቺም ላትመለሽ

Nardi

ግጥሟን ከወደዳችሁላት ሼር እና ላይክ ተባበሯት

🏆🏆🏆
ለመቀላቀል
👇👇👇
hottg.com/zemaritnsae

🏆🏆🏆🏆🏆
ግጥም ለመላክ
. 👇👇👇
. @Tins7
ሰላም እንዴት ናችሁ ተወዳዳሪዎች ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ነጥብ ይነገራል
በወስጥ መሥመር እየጠየቃችሁኝ ያላችሁ ተወዳዳሪዎች የእዚህ ዙር ዳኛ ገጣሚ ሔለን ስላልተመቻት ነገ ወይም ከነገ ወዲያ ታስቀምጥላችኋለች
❗️❗️❗️አስደሳች ዜና


የክረምት ልዩ የቤት ለቤት ስልጠና
።።።።።። ክራር
።።።።።።። በገና
።።።።።።። መሰንቆ
።።።።።።። ከበሮ
በሚፈልጉት ቀን እና ሰአት ከሰኞ እስከ እሁድ

❗️❗️እንዲሁም ለአንድ ወር የሚቆይ ዩቲዩብ ለመስራት ያሰባችሁ❗️❗️❗️❗️ ከመጀመርያ እስከ ገንዘብ ክፍያ ያለውን ሂደት አሰራር  በአጭር ጊዜ ውጤታማ የሚሆኑበትን መንገድ እናሳያለን
☎️ +251900819497 ይደውሉ
Forwarded from 🟢ናታኒም ፖሮሞሽን🟢
🙋‍♂አንድጥያቄ

✞በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ሰውን መግደል የጀመረው በማን ነበር ?✟

          👇👇👇
https://hottg.com/addlist/2TkBck2rFoxMjNk
https://hottg.com/addlist/2Tk_Bck2rFoxMjNk
HTML Embed Code:
2024/06/16 00:23:04
Back to Top