TG Telegram Group Link
Channel: አንደበት
Back to Bottom
የቤተ መቅደስ ንዋየ ቅዱሳት

2⃣4⃣ቱ ዓበይት የቤተ ክርስቲያን ንዋያት

1⃣ ታቦት
2⃣ መንበር
3⃣ መስቀል
4⃣ እርፈ መስቀል
5⃣ የእጅ መስቀል
6⃣ የመጾር መስቀል
7⃣ መሶበ ወርቅ
8⃣ ሙዳይ
9⃣ ጻህል
1⃣0⃣ ጽዋ
1⃣1⃣ አውድ
1⃣2⃣ ጽንሃ
1⃣3⃣ መጎናጸፊያ
1⃣4⃣ መንጦላዕት
1⃣5⃣ መዕፈድ
1⃣6⃣ አጎበር (ጨርቅ)
1⃣7⃣ መብራት
1⃣8⃣ አልባሳት
1⃣9⃣ ቃጭል
2⃣0⃣ ጥላ
2⃣1⃣ ድባብ
2⃣2⃣ ከበሮ
2⃣3⃣ ጽናጽል
2⃣4⃣ መቋሚያ









@yewket
አስገራሚ አሟሟቶች

1)በ1063 አንድ ቀዳማዊ ቤላ የተባለው የሃንጋሪ ንጉስ ዙፋኑ ላይ ዘፍ ብሎ
ሊቀመጥ ሲል ድንገት የዙፋኑ እግር ስለተሰበረ ወደ ኋላ ተንጋሎ
ጭንቅላቱ ከመሬቱ ጋር በመላተሙ ምክንያት ህይወቱ አለፈች::

2)በ1387 ዳግማዊ ቻርለስ የተባለው የናቫሬ ንጉስ ሌሊት ላይ "ብርድ በሽታዬ
ተነሳብኝ" በማለት ወፍራም ብርድልብስ በመከናነብ ኩሽና ውስጥ እሳት
እየሞቀ ማዕድ አጠገብ ተኝቶ እንቅልፉን ሲለጥጥ በአጋጣሚ ሌሊት
በጨለማ ለስራ የተነሳችው የማዕድ ቤቱ ሰራተኛ አይኗ ተጨናብሶ በደምብ
አልታያትም ነበርና "እንዴት ያለ ደፋር ሌባ በቤተ መንግስት ውስጥ ገባ"
በማለት በግዙፍ መጥረቢያ አናቱን ለሁለት ገመሰችው:: ንጉሱም በዚሁ
ባልታሰበ አደጋ እስከ ወዲያኛው አሸለበ::

3)ጀምስ ኦቲስ የተባለ አሜሪካዊ የነፃነት ታጋይ "ምን ጊዜም ምኞቴ በሰው
እጅ ሳይሆን በመብረቅ ተመትቼ መሞት ነው" እያለ ለጓደኞቹ ይናገር ነበር
ታዲያ አንድ ቀን ምሽት ከዝናብ ሊጠለለ ወደ ጓደኛው ቤት ሊገባ ሲል
ድንገት ከሰማይ በወረደ መብረቅ ተመቶ ህይወቱ አለፈች:: ምኞቱ ተሳካ

4)በ1660 ቶማስ ኡርክ ኡሀርት የተባለ የስኮትላንድ ንጉሳውያን ቤተሰብ
አባል እና ምሁር አንድ በጣም የገረመውን ዜና ይሰማል ዜናው "ዳግማዊ
ቻርለስ የታላቋ ብሪታንያ ንጉስ ሆነ" የሚል ነበር መስፍኑ ቶማስ ግን
በሁኔታው እጅጉን በመገረሙ ለረጅም ሰአት እየተንተከተከ ሲስቅ ድንገት
አየር አጥሮት ሞተ::

5)ከከርስቶስ ልደት 620 አመት በፊት ድራኮ የተባለው እጅግ በጣም ታዋቂ
የአቴና ህግ አርቃቂ በኤጂንያ ትያትር ቤት ውስጥ መድረክ ላይ ድንቅ
ንግግር ካደረገ በኋላ በሺህ የሚቆጠሩ አድናቂዎቹ ከሀር የተሰራ የካባ
ስጦታ አጎረፉለት:: ታዲያ አድቂዎቹ እየተረባረቡ ካባውን እላዩ ላይ ጣል
ጣል እያደረጉ ሲያከማቹበት ድራኮ ሳይታሰብ በጨርቁ ክምር ታፍኖ ሞተ::

6)ቅድመ ከክርስቶስ ልደት በፊት 210 አመት ላይ አንድ ክሪሲፐስ የተባለ
ግሪካዊ ፈላስፋ የገዛ አህያውን ብዙ የወይን ጠጅ ከጋተው በኋላ አህያው
ሰክሮ የበለስ ዛፍ ላይ ለመውጣት ሲታገል በማየቱ በተፈጠረው አስቂኝ
ትዕይንት ለረጅም ደቂቃዎች ያለማቋረጥ ሲስቅ ትን ብሎት ሞተ::

7)በ1940 ማርኩስ ጋርቬይ የተባለ ሰው የራሱን የሀዘን መግለጫ በአንድ
ጋዜጣ ላይ ታትሞ ያነባል:: የሀዘን መግለጫውን ጋዜጣው ላይ ያወጡት
ጠላቶቹ ነበሩ የሚገርመው ማርኩስ በዚህ ንዴት ምክንያት የደም ግፊቱ
ጨምሮ ጋዜጣውን ባነበበበት እለት ሞተ::

8)የፎርድ ካምፓኒ ሰራተኛ የሆነው ሮበርት ዊልያም በሮቦት የተገደለ
የመጀመሪያው ሰው ነው:: ሮቦቱ በፕሮግራም ስህተት የዊልያምን
ጭንቅላት በቡጢ በመምታት ነበር ለሞት የዳረገው::

9)በ1981 ኬንጂ ኡራንዳ የተባለ ጃፓናዊ የክዋሳኪ ፋብሪካ ሰራተኛም
ፕሮግራሙ በተበላሸበት አንድ ሮቦት ሊገደል ችሏል:: ሮቦቱ ሌላ እቃ
አንስቶ ወፍጮ ውስጥ መክተት ሲገባው በተፈጠረ የሶፍትዌር ስህተት
የተነሳ ኡራንዳ የተባለውን ይህን ግለሰብ አንስቶ የወፍጮው ማብሰልሰያ
ድንጋይ ውስጥ በመወርወር ለሞት ዳርጎታል::

10) ከሀገር ውስጥ
ድርጊቱ የተፈፀመው በቦሌ ኢንተርናሽናል አየር ማረፊያ ነው:: አንድ
ባለስልጣን ወደ ሀገር ውስጥ ሊገባ ሲል ፖሊሶች ለጥበቃ ቦታ ቦታዎችን
ያዙ:: አንድ የፖሊስ አዛዥ ፖሊሶቹ እየተኙ ነው? ወይስ እየጠበቁ ነው?
የሚለውን ለማጣራት በሌላ በር ገብቶ ቀስ እያለ ወደ ፖሊሶቹ ሲመጣ
በአንድ ፖሊስ ተኩስ ተመቶ ሞቶዋል:: ገዳዩ ፖሊስ ሲጠየቅ "ባላሰብኩት
ቦታ ተደብቆ ሲመጣ ሌባ መስሎኝ መትቼዋለው" ብሎዋል::

@myfny
ዕፀ አንግስ
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ ጸሎት በእንተ ዕፀ አንግስ ወመአንግሠ መፅሐፍ ወዕፅዋት አንቲ ውእቱ ዕፅ ቡሩክ ዕፀ ህይወት ዕፀ መድሐኒት ህየንተ ዕፀ ህይወት ዘውስተ ገነት ዘኮንኪ ዕፀ ህይወት በዲበ ምድር ከመ ጳጳስነ እገሌ ተጰጰሲ ወከመ ንጉስነ ዕገሌ ንገሢ ወከመ ሰሎሞን ልበ ጠቢባን ሐድሲ ወልበ መሠርያን ደምስሲ ሕሙማነ ፈውሲ ወሙታነ አንስኢ
አግሎን ፯
እድሬክ ፯
ምድሬክ
ያሬክ ፯
ፍሌክ ፯
ሰንተው ፯
ቀንተው ፯
ቀርነው ፯
ቀርነለው ፯
ጉሐኤል ኢያኤል አማኑኤል በእሉ አስማቲከ ወበእሉ ቃላቲከ በከመ አንገሥኮ ለአዳም ወለ ሔዋን በውስተ ገነት ከማሁ አንግሦ ለቃልየ ወመፀሐፍትዬ ሊተ ለገብርከ
ወአንግሣ ለዛቲ ዕፅ ላዕለ እደ ገብርከ ዕገሌ።

ገቢር

ኅቡዕ ስሞቹን በእያንዳንዳቸው ዕፅዋቶች ላይ ፯ ፯ ጊዜ ደግመህ የሚቆረጠውን ቁረጥ የሚነቀለውን ንቀል።
እንዲሁም አስማት ስትፅፍ በዕፀ ደለሹት ደግመህ አስማቱን ፯ ጊዜ ደግመህ ከቀለሙ ጨምረህ ብትፅፍ ሁሉ።






@yewket
ለማንኛውም አጋንንት መጠበቂያ

🌿የዘረጭ አንቧይ
🌿አንዳሁላ
🌿ጭቁኝ
🌿ቀስተንቻ
🌿ጥፍራንዶ
🌿ዋጊኖስ
🌿አጋም
🌿ግመሮ
🌿የግሜ ሐረግ
🌿ጂባራ
🌿ልምጭ : ሥራቸውን የጂባራ ደም የጽድ የዝግባ ሙጫ
አልቴት: ከርቤ: እንቆቆ: ነጭ ሽንኩርት: ጤና አዳም:

እነዚህን በአንድ ላይ ከጂብ ጉበት ጋር ቀላቅሎ ለሚያስጨንቀው ለሚጥለው ጋኔን ለያዘው ለሚያስደነግጠው ለሚያቃዠው ሁሉ በአፍንጫው ብታሸተው ደቂቃ አይቀመጥም።

መጠብቅም ነው !





@yewket
"ማርያም እኮ ሞተች"
ኤልያስ ሽታኹን

*           *         *         *        *            *       *

"የአብ ወዳጁ
የወልድ ደጁ
የቅዱስ መንፈስ እጁ፡፡"
                                ማርያም እኮ ሞተች፡፡


የአባጊዮረጊስ ዘጋስጫ
የማትወዳደር ምረጫ
የአባ ሕርያቆስ ቅዳሴው
የቅዱስ ኤፍሬም ውዳሴው
ዮሴፍ ሲገፍፍ የለበሳት
ያዕቆብ በልቡ ያነገሣት

                              ማርያም እኮ ሞተች፡፡
ገብርኤል ለብስራት
ወዴት ልላክ? ብሎ ጌታን ያልጠየቀው
የቱ ጋር ነች? ብሎ ጌታን ያልጠየቀው
እናትህ የቷ ናት? ብሎ ያልጠየቀው
በሚካኤል አክናፍ መልኳን ስለሚያውቀው፡፡
ሰማይን ያለባላ ያቆመ
ወንዳቺ ሆድ ያዘመመ
ጥንተ ናፍቆት
የመለኮት
ዓይንሽ የሰባቱ ሰማያት መስኮት፡፡
ያ ትሁት ገፅሽን
በክንፍ ላይ ስሎሽ መላእክት ያያሉ
ለምነውት ነበር ፍጠራት እያሉ፡፡
(ቶሎ በል እያሉ)

                                   ማርያም እኮ ሞተች፡፡

በመኑ በአምሳለ መኑ ናስተማስለኪ
ነፍሴ ወዴት ደረስሽ? ማርያምን ሳትነኪ
አንቲ ውዕቱ
እኔ ምዑቱ
አንቲ መሶበ ወርቅ
እኔ የበደል ጨርቅ
አንቺ እመአምላክ
የቱ መግነዝ ቻለሽ
ትንሳኤን ወልደሽው ሞትን ትቀምሻለሽ?
አንቺም? እመብርሃን

                                      ማርያምእኮ ሞተች፡፡

ሰማይና ምድር
ወይቦ መልካቸው ሀዘን እያማጡ
እስከዛሬ አሉ
መላእክት ሁሉ እንደደነገጡ፡ 
ለክልዔቱ ጊዜ እስራኤል ጨነቀው
ከስደት ጀምሮ ኮቴዋን የሚያውቀው፡፡
የዳዊት በገና
ብቻውን ያለቅሳል ራሱን በመግረፍ
ዳዊት አላወቀም የልጅ ልጁን ማረፍ፡፡
ክልዔቱ ጊዜ ጨነቀው እስራኤል
እንኳንና አርፋ
ሲከፋት አይችልም በእርሷ እኮ ሚካኤል::
ክልዔቱ ጊዜ
ሰማይ አለቀሰ የመረረ ከሀሞት
መላእክት አያውቁም ማርያም እንደምትሞት፡፡

                               

                                           ማርያም እኮ ሞተች፡፡

ስትሰማ ኖሯ በሆዷ ቅዳሴ
አረፈች ይሉኛል  ወዮ ነው ለራሴ፡፡
አንቺን እመብርሃን ሞት በምኑ ያዘሽ
አላየሽም እንዴ አምላኩን እንዳዘዝሽ፡፡
የቱ መልአክ ሞት ተላከ ወዳንቺ
ችሎ አይገባም ቤትሽ እሺ ብለሽ እንጂ፡፡
ፍትሃት የለም ለማርያም
የተፈታ የሚገባባት እርሷ ራሷ አርያም፡፡
ለማርያም አይቀደስላት
እርሷ ራሷ ቅዳሴ ናት፡፡

                                        ማርያም እኮ ሞተች፡፡



*       *        *         *        *         *

#ማስታወሻ
   * በነገረ - ማርያም
   * ስንክሳርም እንደተነገረን
እመቤታችን በ፷፬ አመቷ  በገዛ ፍቃዷ አርፋ፡፡
ሞትን ቀምሳለች፡፡ነሐሴ ፲፮  ከሞት ተነስታ ማረጓን ልብ ይሏል፡፡
"ሞትሰ ለመዋቲ ለመዋቲ ይደሉ
ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ"



@yourpoim
@yourpoim
ጤና ይስጥልኝ እንዴት ቆያችሁ ውድ የቻናላችን ቤተሰቦች
ዛሬ ስለአንዲት አስገራሚና ስራዋ ብዙ እፅዋት እናያለን

እች እፅ
ጠለንጅ
ደመከትር
የአውድማ መጥረጊያ

በመባል ትታወቃለች ለብዙ መድሐኒት ቅመማ ከተለያዩ እፅዋት ጋር ታገለግላለች
እራሷ ብቻዋንም ለተለያየ በሽታ ፈዋሽ መድሐኒትም ናት

፩ . ለሴቶች የወር አበባ መዛባት ችግር የጠለንጅ ስር በቀንድ ካራ ቆፍሮ የእገሊትን ደም እንደዚህ ቁርጥ ብሎ ስም የገክርስትና ስም ጠርቶ በካራው ቆርጦ እንደ ቀለበት ሰርቶ በአንገት በኪስ መያዝ ።

፪, እሴት ልጅ ወልዳ ደሟ አልቆምም ካለ እንደላይኛው ገቢር መጠቀም ( ፩ ) ።

፫ ሰው እሳት በተበላ ጊዜ ቅጠሉን ቀጥፎ ጨቅጭቆ ከተበላው ላይ ማሰር ያለምግለት ድርቅ ያደርገዋል ።

፬ አንድ ሰው በስለት በጥይት በድንጋይ በዱላ ተመትቶ በተጎዳ ጊዜ በስሙ ቅጠሏን ቀጥፎ ጨቅጭቆ ከተጎዳው አካል ላይ ማሰር ነው በጣም ከተጎዳ አዳዲስ ቅጠል ደጋግመው ይሰሩበት ፈጥኖ ይድናል

፭ ቶንሲል በታመሙ ጊዜ ቅጠሏን ቀጥፎ እያኘኩ መትፋት ነው።

፮ ለክፉ መናፍስት መጠበቂያ ስሯን ከትቦ መያዝ ።

የተፈተነ ትክክለኛ ጥበብ ነው የተቸገረ መጠቀም ይችላል



@yewket
መክስተ ቃል
በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
ጸሎት በእንተ መክስተ ቃል አዝዮስ አዝዮስ አዝዮስ ቃለ አዝዮስ ስድርቃኤል አብድርቃኤል አቅናፌድር ዮሴዴቅ አተርጋዎን አትሪኮን በትሪኮን በርፎሪኮን ስጥጥ ግልባበ ልብየ ቀምጃም ክስት ቃላተ ንባብ ወማህሌት ወቅኔ ሊተ ለገብርከ
ገቢር በእፀ ሥላሴ ቅጠል በሴት ቀስት ብዕር ፅፈህ ሶስት ቀን አስቀድሰህ በማርለውሰህ ብላ
አሌፋት ነቢያት መልክአ ኢየሱስ ዉዳሴ ማርያምን ፯ቀን ድገም ተጠበቅ


@yewket
*አስደናቂ ምስጢር....

*ጣና ባህላዊ ታሪካዊ፣ጂኦሎጂካዊና ሥነ ውበታዊ እሴት ባለፈ ከባድ ምስጢር አለ።እጅግ በጣም ከባድ ምስጢር።በጣና ሐይቅ ዙሪያ ከሚገኙት አብያ ክርስቲያናት ደኖች እና የአበባ ዝሪያዎች ያለምንም ጥርጥር የእውቀት ማነስ እንጅ መድሀኒት ናቸው።

*እነዚህ አብያተ ክርስቲያኖች ከባድ ምስጢር አለ በእጅ የያዙት ወርቅ እንደ መዳብ ይቆጠራል ሆኖብን እንጅ ገዳማቱን ለማወቅ በመጨረሻም ለማጥፋት የምስጢር ማህበረሰቡ በPedro Paez፣Jeronimo Lobo፣Alfonsi Mendes፣ ፖርቱጋላዊው ሚሲዮናዊ ማኖኤሊ ደ አልሜዳ፣ጀምስ ብሩስ አማካኝነት ሲመረመር ቆይቷል። 'The hidden of treasure Ethiopia' በሚለው መጽሐፍ ውስጥ ጣናን ከነቅርሶቹ እንደሰለሉ ገልጾ ዋና ዓላማቸው "አዲሱ የኢሉሚናቲና 666 የአገዛዝ እቅድ ሊከሽፍ የሚችለው ጣና ደሴቶች በሚገኝ ጥበብ ነው" ብለው እንደሚያምኑ መጽሐፉ አስቀምጦታል።

*በጣና ደሴቶች ዙሪያ ያለው የተደበቀው ምስጢር ምንድነው? አባቶቻችን ያካተተ ሰፊ ጥናት ይጠይቃል።

1.ከኤዶም እየወጣ ገነትን ከሚያጠጡ ወንዞች መካከል ሁለተኛው ግዮን ነው።ግዮን ወይንም አባይ የኢትዮጵያን ምድር (7) ጊዜ ይከብባል።የሚያበራ እና የሚያብረቀርቅ ዕንቁም ይገኝበታል። (ዘፍ 2፥13)

2.አዳም የተፈጠረው የግዮን ወንዝ ከሚወጣበት ኤዶም ነው።

3.ኖህ ከማየ አይኅ የጥፋት ውኃ ልጆቹ፣ሚስቱና የልጆቹ ሚስቶች የዳኑት በመርከብ ነው። በዐፄ ይኩኖ አምላክ ዘመነ መንግሥት በአቡነ ሒሩት አምላክ የተመሰረተው የዳጋ እስጢፋኖስ ቤተ ክርስቲያን የተሠራው በኖኅ መርከብ ቅርፅ ነው።

4.የኖኅ መርከብ ማየ አይኅ መጉደል ሲጀምር በ7ኛ ወር ከወሩም በ27ኛው ቀን በአራራት ተራሮች ላይ ተቀመጠች።አራራት ተራራ ደግሞ የሚገኘው ከዚሁ ጣና ነው።

5.ከክርስቶስ ልደት በፊት በጣና ቂርቆስ የኦሪት መስዋዕት ይቀርብ ነበረ፥ዛሬም አራት ማዕዘን ቅርጽ ያለው ከአናቱ ላይ እንደ ሙቀጫ የተቦረቦረው ድንጋይና የኦሪት የብረት መስዋዕት ማቃጠያ በሥፍራው ይገኛሉ።

6.ጣና ቂርቆስ ገዳም ለሙሴ የተሰጠው የቃል ኪዳን ታቦቱ ለ800 ዓመት የተቀመጠችበት ቦታ ነው።

7.አስገራሚ ነገር የኦሪት መስዋዕት እና ታቦተ ጽዮን ምስጢር ለሚገባው ሰው ከእነዚህ ቀጥሎ ድግሞ
ድንግል ማርያም ልጇን ይዛ ወደ ምድረ ግብጽ በተሰደደችበት ወቅት ለ3 ወራት ከ10 ቀን በዚሁ ገዳም ከልጇ ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ቆይተዋል። ድንግል ማርያም በገዳሙ የነበራትን ቆይታ አጠናቃ ስትመለስ “ፀአና በደመና” በደመና ጫናት የተባለው በጊዜ ብዛት ለአሁኑ የሐይቁ መጠሪያ ስም “ጣና” መሠረት ሆኖታል።

8.ቅዱስ ያሬድ የመጀመሪያውን የዜማ መጽሐፉን የፃፈውና ብዙ ተግባራትን ለመከወን የመረጠው ጣና ቂርቆስን ነው፡፡መጽሐፍ ሲጽፍ ለጥቁርና ቀይ ቀለማት መበጥበጫነት ይጠቀምባቸው የነበሩ ከድንጋይ ተቦርቡረው የተሠሩ ጉድጓዶች፣የቅዱስ ያሬድ ድጓና ካባ
በገዳሙ ይገኛሉ።በተጨማሪም በጣና ቂርቆስ፦

*የአቡኑ ሰላማ መቋሚያና የብረት መስቀል፣

* ከብርጭቆ የተሠራ የብርሌ ቅርጽ ያለው የንጉሥ ሰለሞን የእጅ ማስታጠቢያ፣

*ከአንድ ሜትር በላይ ቁመት ያላቸው ሁለት የእንጨት መቅረዞች፣

*ቁመቱ 75 ሳ.ሜ ርዝመቱ ደግሞ 5 ሜትር የሆነ በሐዋርያትና በነቢያት ሥዕል ያሸበረቀ ከብራና የተሠራ ተጣጣፊ የብራና ሥዕል (ልፋፈ ፅድቅ)፣ የመሳሰሉት ይገኙበታል።

*ዋናው ነጥብና ሊመረመሩ የሚገባቸው አስደናቂ ምስጢሮች ግን ዛሬም እንደተሰወሩ ናቸው።
+ ኤዶም እና ግዮን (አባይ)
+ ኤዶም፥አዳም፥ግዮንና ጣና
+ ኖኅ፥መርከቧና ጣና
+ ኖኅ፥መርከቧ፥አራራት ተራራ፥ጣና እና ግዮን
+ ኖኅ፣መርከቧ፣ታቦተ ጽዮን፣ቅድስት ድንግል ማርያም፣ክርስቶስ፣ጣና ቂርቆስ፣አራራት ተራራ እና ግዮን

ይኼ ሁሉ ከጣና እና ከግዮን ጋር የተቆራኘ አስደናቂ ምስጢር ሊመረመር ይገበዋል።በርግጥም የሚገለጥበት ዘመን ሩቅ አይሆንም!!





@yewket
planet x
​ሙሉ ለሙሉ መኖሩ ያልታወቀው ፕላኔት ወይም በእንግዘኛው "planet x"

ይሄ ፕላኔት አለ ተብሎ የሚታሰበው በኛው ስርሀት ፀሐይ ስር ወይም በኛ ሶላር ሲስተም ውስጥ ሲሆን ዘጠኛው ወይም ከፕላኔት ኔፕቱን ከጠሎ ያለ ፕላኔት ነው ።

ይሄ "planet x" የተባለ ፕላኔት ሊኖር ይችላል የተባለው አጠቃላይ ሰለስምንቱ ፕላኔቶች በተሰራ ሒሳባዊ ትንታኔ ነው እንደሚታወቅው ኔፕቱን የተባለው ፕላኔት መጀመሪያ መኖሩ የታወቀው በሒሳባዊ ትንታኔ ወይም በሀሳብ ደረጃ ነበረ ነገረ ግን በተገመተበት ቦታ እና አቅጣጫ ሊገኝ ችሏል ይሁን እንጂ ይሄ "planet x" የተባለው ፕላኔት በሒሳብ እና በአሳብ ደረጃ አለ ይባል እንጂ ፕላኔቱ እስካውን ሊገኝ አልቻለም ልክ እንደ ኔፕቱን ወይም እሰሰካውን የተ እንዳለ, እንዴት እንደሚሽከረከረ አይታወቅም ይሄ ብቻ ሳይሆን አንዴም እንኳን በቴሌስኮፕች አይን አለመግባቱ ነው።

ሰለ ፕላኔቱ ሳይንቲስቶች የሰሩት ጥናት አደሚያሳየው ከሆን ፕላኔቱ የኛን መሬት በክብደተ አስር እጥፍ እንደሚያክል ወይም ሳተርን ከተባለው ፕላኔት ጋር በክብደት አቻ ነው ይሄ ፕላኔት አንድ ዙር ፀሐይን ዙሮ ለመጨረስ ከ10,000 አመት እስከ 20,000 አመት ያስፈልገዋል ይሄም የሆነው ፕላኔቱ እጅግ ከፀሐይ እርቆ ሰለሚገኘ ነው በጠፈር ሳይንስ ሕግ ከኮከባቸው እርቀው የሚገኙ ፕላኔቶች ኮከባቸውን በእረጅም አመተ ውስጥ ዙረው ሲጨርሱ በጣም ቅርብ ለምሳሌ እንደ ሜርኩሪ ያሉ ፕላኔቶች ደግሞ ባጭር ጊዜ ውስጥ ዙረው ይጨርሳሉ።

ይሄ ፕላኔት አለ ተብሎ የሚታስብበተ ቦታ ከፃሐይ እስከ መሬት ያለውን እርቀተ ከ200 እስከ 1200 ሊያጥፍ ይችላል ወይም ምን አልባት ከፀሐይ 200ቢልዬን ኪሎ ሜትሮች ይርቃል ይሄም ከፀሐይ እጅግ እሩቅ የሚገኝ ፕላኔት ያስብለዋል ሰለዚህ ፕላኔት ጠፍርተኞቹ ብዙ ነገረ ይበሉ እንጂ ይሄ ፕላኔት የመገኘት እድሉ ወይም ቻንሱ 1/150,000 ነው ባጠቃላይ ትንሽዬ ቻንስ ያለው ይመስላል

ይሄ ፕላኔት ለምን አልተገኘም?

እንደ አንዳዶች መላምት ከሆነ ይሄ ፕላኔት እንደሌሎች ፕላኔቶች አደለም ፀሐይን የሚዞረው ማለትም ሁሉም ፕላኔቶች ፀሐይን የሚዞሯት ትይዩ ሁነው ነው ወይም በእንግልዘኛው አቀማመጣጨውን "plane orbital " ልንለው እንችላለነ ግልፅ ለማረግ ያክል ፀሐይ መሀል ላይ ስትሆን ፕላኔቶቹ ግን በትይዩ ይዞሯታል ለዚህ ሁሉም ፕላኔቶች ላይ ሁናቹ የተቀሩትን ፕላኔቶች ማየት ትችላላቹ ምክንያቱም ትይዩ ሁነው ሰለሚንቀሳቀሱ በዚህም ምክንያት ነው መሬት ላይ ሁነን ሁሉንም ፕላኔቶች ማየት የምንችለው ነገረ ግን ይሄ "planet x" የተባለ ፕላኔት ፀሐይን የሚዞራት እደተለመደው አይነተ አደለም ወይም በተፃራሪ አቃጣጫ ወይም በእንግልዘኛው "perpendicular" ሁኖ ነው የሚዞረው ከሌሎቹ ፕላኔቶች አንፃር ሰለዚህ ይሄ ፕላኔት በተለመደው አይነተ ቴክንሎጂ ላይገኝ ይችላል የሚል መላምት አለ።




@yewket
ጤና ይስጥልኝ እንደት ቆያችሁ ውድ የጥበብ ቤተሰቦች
ሰላም
ጤና
እድገት
ብልፅግና በያላችሁበት ተመኘሁ

#የወባ_በሽታ ችግርና #መፍትሔውን ላካፍላችሁ ወደድኩ

👉 የወባ በሽታ / malaria ምንድን ነዉ??

👉 በኢትዮጲያ ሀገራችን በዋናነት ሁለት አይንተ የወባ በሽታ አሉ ፡፡
የወባ በሽታ ወቅትን ጠብቆ በተድጋጋሚ በስፋት የሚከሰት በሽታ ሲሆን በሴት ወባ ትንኝ ንክሻ ወቅት ከምራቅዋ ጋር ወደ ደም ዝውውራችን የሚገባ በአይን በማይታይ ጥቃቅን ፕሮቶዞአል ዝርያ ነው ፡፡
የወባ በሽታ በኢትዮጲያ ብዙ
ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እና ሞት በማስከተል ቀዳሚ በሽታ ነው ።

👉 በኢትዮጲያ በዋናነት ሁለት አይነት የወባ በሽታ አሉ፦
1.#የጭንቅላት ወባ ፡- በአብዛኛው በኢትዮጲያ ቆላ ቦታዎች የሚከሰት ሲሆን ከፍትኛ ጉዳት እና ብዙ ሞት ያስከትላል
2.#ትንሽዋ ወባ ፡-በአብዛኛው በኢትዮጲያ ጋምቤላ አካባቢና በአነስተኛ መጠን በቆላ ቦታዎች የሚከሰት ሲሆን በተደጋጋሚ በመነሳት ታማሚውን በማሰቃየት ትታወቃለች ፡፡

👉 የወባ በሽታ ምልክቶች፡-
ፕሮቶዞአል ደም ዝውውራችን ውስጥ ከገባ በኋላ ለመራባት እና ለማድግ የቀይ ደም ህዋስን አካል በመብላት እና የቀይ ደም ህዋስን ቅርጽ በመቀየር ቶሎ እንዲሞቱ ያደርጋል፡፡
ከዚህም በተጨማሪ የሰውንታችን ተፈጥሮአዊ መከላከል ሂደት ጋር በተያያዘ ብዙ ምልክቶችን
ይፈጠራል፦
እራስ ምታት
ድካም
የሆድ ህመም
የጡንቻ ህመም
ትኩሳት
ብርድ ብርድ ማለት አና ማንቀጥቀጥ
ማቅለሽለሽ አና ማስመልስ
ፈጣን የልብ ምት
ደም ማነስ ምልክት
ጣፊያ ማደግ
ደም ውሰጥ ስኳር ማንስ / የረሀብ ምልክት
ቶሎ ህክምና ካላገኘ በጣም መዝለፍለፍ
የሰውነት ሙቀት አተነፋፈስ ልብ ምት እና ደም ግፊት መዛባት
እራስን መሳት
ሽንት በደንብ አለመአጣራት እና ትንሽ ሽንት መውጣት
የደም መርጋት መፍሰስና ደም ማነስ
አሲድ በሰውነታችን ውሰጥ መከማቸት

👉የወባ በሽታ መፍትሄ

የመቅመቆ ስር ነቅሎ አድርቆ አልሞ ሦሥት የሾርባ ማንኪያ መቅመቆ ትንሽ ማር ጨምሮ በአንድ ሌትር ውሀ አንተክትኮ አፍልቶ ግማሹ ሲቀር አንድ የውሀ ብርጭቆ ሞልቶ ጥዋት በባዶ ሆድ መጠጣት ነው መርዛማነት ሳይድ ኢፌክት የለውም የተወሰነ ያስቀምጣል ከሆድ ላይ ያለውን የወባ ስራይ ጠራርጎ ያወጣዋል ሙሉ በሙሉ ከወባ ይፈውሳል በረሀማ ቦታ በወባ ለሚሰቃዩ ወገኖቻችን ይደርስ ዘንድ ሽር በማድረግ አጋሯቸው።




@yewket
ማርያም
ስምኪ ጥዑም!
****
“ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ እንዲህ አለ:-

በቅድስና ውበት ስለተሞላችው ንጽሕት ትሕት እናገር ዘንድ አንደበቴ ብቁ አይደለም፡፡ ... የተራ ቀለማት
መዋሐድ ለማይመጥኗት ለዚህች እጅግ ክብርት እንዴት ያለ ሥዕልን ልሣል? ውበትዋ ከእኔ መጠበብ በላይ ነው ፤ አእምሮዬም እንዲሥላት አልፈቅድለትም፡፡

የድንግል ማርያምን ክብርዋን ከመግለጥ ፀሐይን ከነብርሃንዋና ከነሙቀትዋ መሣል ይቀልላል፡፡ ምናልባት የፀሐይ ጨረር በሥዕል ሊቀመጥ ይችል ይሆናል፡፡ ስለ እርስዋ የሚነገረውን ነገር ግን አሟልቶ ለመስበክ አይቻልም፡፡

እርስዋን ከነማን ጋር መመደብ ይቻላል? ከደናግል ጋር? ከቅዱሳን ጋር? ከንጹሐን ጋር? ካገቡ ሴቶች ጋር? ከእናቶች ጋር? ከአገልጋዮች ጋር? እነሆ የድንግልናን ማኅተም ከወተት ጋር የያዘ ሰውነትዋን እዩ! መውለድዋንም ከታተመ ማኅፀንዋ ጋር እዩ! ከደናግል መካከል ናት ስል ሕፃን ይዛ ስታጠባ አያታለሁ! ከዮሴፍ ጋር ትኖራለች ስል በጋብቻ ቃልኪዳን እንዳልታሠረች አያለሁ!

ስለ እርስዋ እንድናገር ፍቅር ያስገድደኛል ፤
የክብርዋ ከፍታ ግን ያስቸግረኛል፡፡ ከቶ ምን ባደርግ
ይሻለኛል? ስለ እርስዋ ለመናገር ብቁ እንዳልሆንሁ
በግልፅ እናገራለሁ፡፡ ከፍቅር የተነሣ ግን ተመልሼ
መናገር ያምረኛል፡፡...

ሱራፌል ከእሳቱ የሚሸሸጉለትን የእርሱን ከንፈሮች በቡሩካን ከነፈሮችዋ የሳመች እርስዋ የተባረከች ናት! ዓለማት ሕይወትን የጠጡበትን ምንጭ እርሱን ያጠባች እርስዋ የተባረከች ነች’

(የብርሃን እናት ገፅ 352)
እንኳን አደረሳችሁ
መልካም በዓል ይሁንላችሁ
ለዓመቱ በሠላም ያድርሰን!
🙏🙏🙏

(Click here )

@yewket
ምናልባት አጠገባችን የተሰወረ ነገር ቢኖርስ?
ስለ እጸ መሰውር ምን ያህል ያውቃሉ?
.
.
( 👉 Click here )

(The Cloaking Device)
.
.
Marvel የተሰኘው የፊልም አምራች ድርጅት በሰራቸው በርካታ ፊልሞች ላይ
የማይጠፋ አንድ ቴክኖሎጂ አለ! ይህ ቴክኖሎጂ ትንሽ ቆየት ብሎ የወጣውን
black panther እና እንደ marvel agents of shield የተሰኙት
ፊልሞች ላይ ያስተዋልነው Cloaking device የተሰኘው መሳሪያ ነው!

❤️ይህ መሳሪያ በተግባር ላይ እንደዋለ የሚያሳዩ መረጃዎች ያሉ ሲሆን በተለይ
የአሜሪካና የእንግሊዝ የጦር ሀይል ተጠቅሞበታል!
በተለይ የእንግሊዝ የጦር ሀይል በዚህ መሰወሪያ መሳሪያ በመጠቀም ታንክ
ሰውሮ ለውጊያ እንደተጠቀመ የሚያሳዩ መረጃዎች አሉ።

በተጨማሪ Mercedes የተባለው የመኪና አምራች ድርጅት በዚህ መሰወሪያ መሳሪያ የተቀመረች መኪና አምርቶ ለሙከራ አብቅቶም ነበር

👉ነጮቹ ይህን የቴክኖሎጂ ምርታቸውን
እና ጥናታቸውን እንደ Harry potter እና Hollow man በተሰኙ የሆሊውድ
ፊልሞች ላይ አሳይተውናል።
Black Panther ፊልም ላይ የተሰወረችው ከተማ ዋካንዳ እና ከሰው እይታ የሚሰወሩት ጀቶች ምስጢር ይህ ግዝፈት ያላቸውን ነገሮች ለመፈብረክ የተዘጋጀው የክሎኪንግ ዲቫይስ ቴክኖሎጂ ነው!
ሊሆን የሚችል ቴክኖሎጂ ነው...ለሙከራ ያህል እንጂ ሙሉ ለሙሉ ጥቅም ላይ አልዋለም፣ ዋነኛው ችግሩ ለስራው አስፈላጊ የሆነ ማቴሪያል ማምረቱ ላይ
ነው...ጽንሰ ሃሳቡ የተነደፈው በከፍተኛ ሙቀት ሠዐት ለምሣሌ አስፓልት ላይ
ከምናየው የብርሃን መጨበርበር ነው

👉ተመራማሪዎችም የካርበን ቲዩቦች ውስጥ ከፍተኛ ሙቀት በማሣለፍ clocking effect መፍጠር
ችለዋል...ቢሆንም በማቴሪያሉ አቅም የተነሣ ያንያህል experment ተግባራዊ
ሊሆን እንደሚችል ከማሣየት የዘለለ ነገር አልተሠራም።

👉ይህ ጥበብ በኛ ዘንድ የበርካታ ሺህ ዘመናት ታሪክ አለው!
በዚህ ጥበብ ልክ ብላክ ፓንተርስ ላይ እንደተመለከትነው አያቶቻችን በርካታ
ከተሞችን ከሰው እይታ ሰውረዋል! እነኚህ ከተሞች ልክ እንደ ዋካንዳ በርካታ
ሀብት ጥበብና ምስጢር ያዘሉ ናቸው! እነኚህን ከተሞች አያቶቻችን የሰወሩበት
መንገድ እና ቴክኖሎጂ ደግሞ መሰውር ይሰኛል!

👉ይህን ጥበብ በመጠቀም አበው በርካታ ቅርሶችን ከዘራፊዎች ታድገዋል።
አሁንም እንደተሰወሩ የቀሩ ዋሻዎች ፣ ቅርሶች ፣ ፒራሚዶችና መንደሮች አሉ።

መሰወር የተሰኘው የመሰወሪያ መሳሪያ ሙሉ ለሙሉ ከእፅዋት ተቀምሞ
እንደሚዘጋጅ የዘርፉ ሊቃውንት ይናገራሉ! በተለምዶም እፀ- መሰውር እየተባሉ ይጠራሉ እፅዋቱ።

የኛ ሰው ይህን ጥበብ ጥንቆላ ብሎ ቢያንቋሽሸውም ምዕራቡ አለም የአዲሱ ዘመን አስደናቂ technology አድርጎታል።

ምን አልባት ይህ ጥበብ አገራችንን ከጠላት የምንከላከልበት ጥሩ አማራጭ ሊሆንም ይችላል።
የሚገርመው ገዳማውያን
አባቶች አሉ ፡ አብረዋቸው ከሚጓዙት ሰወች ተሰውረው ቀድመው ባሰቡት ቦታ የመድረስ ጥበብ ያላቸው አሉ።

👉ከተማሪዎቻቸው (ከትውልዱ) በምግባር
የበቃ ተከታይ ስላልተገኘ ጥበባቸውን
አያወርሱም። ከዚህም በላይ ተማሪዎች
(የቆሎ) ፈሪሀ እግዚአብሔርን ከመማር
ይልቅ ጥበቡን በአቋራጭ ለመማር
የሚያደርገው መፍጨርጨር ስላላስደሰታቸው ትውልዱ ያለምግባር እግዚአብሔር በሰጠው ጥበብ የሰይጣን አጋዥ እንዳይሆን ጥበቡን ራሳቸው ጥንቆላ መተት መርገምት የሚል ካባ በመሸፈን ይጠብቃሉ።
ነገር ግን ይህ ጥበብ ከምድረገጽ ፈፅሞ ሳይጠፋ እንፈልገው ከወደቀበት እናንሳው።

አለም ላይ ተወልደን/ተፈጥረን ሳለን ሚስጢሯን ሳናውቅ ባሰመሩልን ኖረንላቸው መሞት ሞት ነው!!



@yewket
❖#ዓይነ_ጥላ_በወንዶች_ላይ

➥ሴት_ዛር_ወይም ዓይነ ጥላ

#የሴት_ዛር የዓይነ ጥላ

መንፈስ ያለችበት ወንድ ልክ እንደ ሴት ተመስላ ሌሊት እየመጣች ወንዱን ትገናኘዋለች
ዘሩን ታፈስበታለች
ብልቱ እንዲልፈሰፈስ ታደርጋለች
ብልቱን ወደ ውስጥ ትሰበስበዋለች
ብልትን በመጠን ታሳንሰዋለች
ብቻውን ሲተኛ ስሜቱ ይነሳል ከሴት ጋር ሲሆን አይነሳም ቢነሳም ዘሩ ተሎ ይፈሳል
ፆታዊ ግንኙነት በሚያደርግበት ጊዜ የዘር ተሎ መፍሰስ ታመጣለች
የመራቢያ ዘሩን በማቅጠን በማሳሳት ልጅ እንዳይወልድ ታደርገዋለች (መካንነት)

# ሰውነቱን ታደቀዋለች
ሰውነቱን ታቀጭጨዋለች
የሆድ መንፋት ታመጣለች
የፍቅር አጋሩን እንዲጠላ ታደርገዋለች
ትዳር እንዳይዝና ትዳር የያዘውም አስጠልቶት እንዲለያይ ታደርገዋለች
ብቸኝነት
ድብርርት
ጭንቀት
እራስን ዝቅ አድርጎ መገመት
ግለ ወሲብ እንዲፈጽም ታደርገዋለች
የፀባይ መቀያየር ታመጣበታለች

??#ሴት ዛር (የዓነ ጥላ መንፈስ ) በብዙ ትመሰላለች
በቤተሰብ
በፍቅር አጋር
ቀን ባዩት ነገር በሚያውቁትና በማያውቁት
ባስ ሲልም በእንስሳት በመመሰል ወንድ ልጅን በህልመ ሌሊት እየመታች ስታሰቃይ ትኖራለች

👉ልብ ይበሉ
➥ሴቶችን ደግሞ ሌሊት እየመጣች በመደበት ከባላቸው ጋር ሩካቤ እንዳይፈጽሙ
➥በባላቸው ዘንድ እንዲጠሉ ወይም እንዳይወደዱ
➥ለሩካቤ ስጋ ፍላጎት እንዳይኖራቸው ታደርጋለች
➥ከትዳር አጋር ጋር ሰላም እንዳይኖር ታደርጋለች

#ሴት ዛር ያለችበት ወንድ መንፈሷ የሕልመ ሌሊት ሰለባ ከማድረጓም ባሻገር
ስሜታዊ(ስነ ልቦናዊ) ጉዳት ታደርስበታለች
ሞራሉን ትጉዳዋለች
ብቻውን እዲኖር አድርጋ እራሷ ባል (ጓደኛ ታደርገውና) የስውር ሚስእስኪያልትኖራለች

👉መፍትሔ
➱#አስተናግር ሥርና ፍሬ
➱#የጊዜዋ ሥር
➱#የአብላሊት ሥር
➱#የእጸ መናሔ ሥር
➱#እጽ ደብተራ ሥር
➱#የሴት ቀስት ሥር

👉ጊዜዋ፣እጸ መናሔ፣አብላሊት እነዚህን እጽዋት ማክሰኞ ቀን በንፅህና ነቅሎ ቀጥቅጦ አድርቆ ወግጦ በወንፊት ነፍቶ እኩል እኩል አድርጎ ማገናኘት ከተገናኘ በኃላ ከእሩብ ኪሎ ማር ጋር አዋህዶ ለ9 ቀን በስኳር ማንኪያዋ ጧት በባዶ ሆድ መውሰድ።

👉ለዓይነ ጥላ/ለሴት ዛር መንፈስ፦
#የሴት ቀስት ሥር በንጽህና ማክሰኞ ቀን ቆርጠው አድርቀው ሸርከት አድርጎ በመደቆስ ማታ ማታ ከከርቤ ዕጣን ጋር ለ9 ቀን ማታ ማታ እየታጠኑ መተኛት።

👉ለዓይነ ጥላ/ለሴት ዛር መንፈስ
#የአስተናግሩንና የእጸ ደብተራ ሥራቸውዋ ሰብስቦ ቀጥቅጦ አድርቆ የአስተናግሩን ፍሬ በመጨመር ከ7-14 ቀን አንዳንድ የስኳር ማንኪያ ማታ ማታ እየታጠኑ መተኛት።

የሚከለክሎ ነገሮች #አልኮል #ተልባ #ፆታዊ ግንኙነት መድሐኒቱ እስኪያልቅ




@yewket
እንቆቅልሽ ምንድነው?
═════ ❁ ═════
እንቆቅልህ በግዕዝ "አንቆቅሆ" ማለት ነው። ወደ አማርኛ ሲመለስ አንቆቅሆ እንቁላል ማለት ይሆናል፤ ስለዚህ እንቆቅልህ ማለት በስረ መሰረቱ እንደ እንቁላል ድፍን የሆነ ፍቺው ያልታወቀ መመርመርን የሚጠይቅ ፈተና ማለት ነው።

እንቆቅልህ የአዕምሮ ንቃትን ይጠይቃል፤ ተጠያቂው ወይም ተፈታኙ ሰው በተወሰነ ሰዓት የምሳሌውን ፍቺ ማግኘት አለበት፤ አለዚያ አገር መስጠት እና መሰደብ ይኖርበታል። ነገር ግን በተወሰነ ደቂቃ ውስጥ ትክክለኛ የሆነውን ፍቺ ያገኘ እንደሆነ አገር ከመስጠት እና ከመሰደብ ይድናል። የአዕምሮ ዝቅተኛነትም አይሰማውም።

እንቆቅልሽ ስዕላዊ ምርመራን ይፈልጋል። ጠያቂው የረቀቀ እና የበሰለ ምስጢር ያዘለ ምሳሌን ሲያቀርብ ተጠያቂው ከምሳሌው ጋር የሚነፃፀሩትን ነገሮች ሁሉ እያሰበ ትክክለኛ ከሆነ መልስ እስኪደርስ ማውጣት፣ ማውረድ እና መመርመር የሚያሻው ነው። ትርጉም የሚሆኑትን ነገሮች ሁሉ በዓይነ አእምሮ እየተመለከተ ከምሳሌው ጎን ለጎን እየኮለኮለ ማስተያየትና ማነፃፀር ይኖርበታል።

ተፈታኙ እንደ ኢላማ አነጣጥሮ ከእውነተኛው ትርጉም ሲደርስ የእንቆቅልሹ ትርጉም ይህ ነው ብሎ ይመልሳል። በትግል አቅምን በመገመት ጉልበትን መፈተን እንደሚቻል ሁሉ በእንቆቅልሽም የአእምሮን ንቃትና የአሳቡን ኃይል ማወቅ ይቻላል። ሰው ሁሉ አንድ ዓይነት አስተያየት የለውም፤ አንዱ ከሌላው በችሎታ ይበልጣል፤ አንዱ ደግሞ የተለየ ተሰጥኦ ኖሮት በአንደኛው ነገር ንቁ ሲሆን በሌላው ይደክማል።

ስለዚህ አንዳንድ ልጆች ብቻ እንቆቅልሽን ቶሎ ለማግኘትና ትክክለኛ ፍቺ ለመስጠት ይችላሉ። እንቆቅልሽ ጊዜን የሚጠይቅ የምርመራ ፈተና ነው። ይሁን እንጂ ጥያቄው በተወሰነ ደቂቃ ውስጥ መመለስ አለበት፤ የእንቆቅልሹ አቅራቢ "መሸብህ እንቆቅልሼ ተነዛብኽ፣ ዋለብህ አደረብህ አገር ስጠኝ?" እያለ ተጠያቂውን ይወተውተዋል፣ ያዋክበዋል። ተጠያቂው እንቆቅልሹን መፍታት፣ ከትርጉሙ መድረስ ያቃተው እንደሆነ አገር ይሰጠዋል፤ በዚህም ድል መሆኑን እና መሸነፉን ስለሚገልፅ የአእምሮ ዝቅተኛነት ይሰማዋል፤ የእንቆቅልሹ ባለቤት በበኩሉ ይደሰታል።

የአገሩን ስም እየጠየቀ "አነሰኝ፣ ጨምርልኝ" እያለ ያስገድደዋል፤ የሚመኘውን እና የሚፈልገውን ካገኘ በኋላ፣ "እዚህ ተቀምጬ ምን አጥቼ፤ ሁሉ በእጄ፣ ሁሉ በደጄ፤ እንዳልሰድብህ ወንድሜ፣ እንዳተውህ ጠላቴ" እያለ ይወቅሰዋል። በዚህ ጊዜ በጠያቂውና በተጠያቂው ፊት ላይ የበላይነትና የበታችነት ስሜት ማንበብ አዳጋች አይሆንም። የእንቆቅልሹ ባለቤት በጌታ ሁናቴ፤ "በሰንጋ በቅሎ ሆኜ አንተን አሽከሬን በገጣባ አህያ አስቀምጬ" እያለ የተሸናፊውን ዝቅተኛነት ያስረዳዋል።

ከዚህም አነጋገር ታላቅ ምስጢር እናገኛለን፤ ይኸውም በአእምሮ ያልጎለመሰ የማሰብ ኃይሉ ከተፈጥሮ ጓደኛው ያነሰ ሁሉ፣ ለወንድሙ አሽከር ሆኖ መኖሩን የሚያስገነዝብ ነው። ምንም እንኳን በቀድሞ ጊዜ ለጉልበት ሥራ ብቻ ከፍተኛ ግምት ቢሰጠው፤ አባቶቻችን የማስተዋል ንቃት፤ የመንፈስ ብርታትና የናላ ኃይል አስፈላጊ መሆኑን አልዘነጉትም።

ለምሳሌ፦
ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
ላዩ ሰርዶ ውስጡ ብርንዶ።
መልስ፦ ቀይ ሽንኩርት።

ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
ሲወለድ ይጠቁር፣ ሲያረጅ ይቀላ።
መልስ፦ በርበሬ።

ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
ወተቱ ጥቁር፣ ማለቢያው ነጭ።
መልስ፦ ቡና።

ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
እልም ካለ ዱር ገብቼ፣ የምቆርጠው አጥቼ።
መልስ፦ ጉም።

ጥያቄ፦ እንቆቅልህ? - ምን አውቅልህ?
ልብስም ጉርስም ትሆን።
መልስ፦ በግ።

━━━━━━━━━━━━
📓 የብላቴን ጌታ ማህተመ ስላሴ
ወልደ መስቀል ስብስብ ሥራዎች
ምንጭ 👉 ሰዋስው
📖 📖 📖 📖 📖





@yewket
ረቡኒ
__

የሆነ ቀ ሌሊት
ገላየ እንቅልፍ አጥቶ
ከሆነ ሕልሙ ጋር የትዝታ ጠረን
በልቡ ያሸታል ፣
ከወዲያ ጫፍ ደግሞ ፣ «ጥላሁን» ተከፍቷል ፣
.
ፍቅር ለብቻየ
የሚል እንጉርጉሮ
.
ከዚህ ዘፈን በታች
Pablo Neruda
''Every Day You play the light of the Universe '' !

እያለ ይወርዳል ፣
ከማን ጋር ልስማማ
ትዝታ አቅም ኑሮት ፣ ማንን ይጋርዳል ?
.

ዮሐንስ አድማሱን
በድሉ ዋቅጅራን
ቸርነት ወ/ገብሬልን
ወይ ደግሞ ኤፍሬምን
«ፍቅር እዚህ ቦታ ፈገግ ብሎ ነበር» ያለሽን ልቀፈው ፣
ከሁሉም ለመሸሽ
እንደምን ? እንደምን ? ፣ ይኼን ቀን ልለፈው ?
.
አሁን ለምሳሌ

የአምስት ግጥም ዕድሜ
ከሚለው መጽሐፍ ላይ
.

ከወዝ መጋራት ጋር
የሚመሽ አንድ ቀን
ይነጋል እያለ
የጻፈላት ግጥም ፣ መንጋቱን ሸረፈው ፣
ወቅትን እንደ ኩታ ፣ ዘቅዝቆ አነጠፈው ።

.
ታዲያ በዚህ መሃል
ናፍቆት ግፉን ትቶ ፣ ሲሄድ እያየሽው ፣
ፍቅር ለብቻየን ፣ ለምን ነበር ያልሽው ?

እንጃ ።

ብቻ ግን አንዳንዴ !
.
ሰትዮዋ እንዴት ናት ?
የሚል ግጥም ጽፎ
አቦል የፍቅር ወዝ ፣ መድፋት ስለሚቻል ፣
የኖሩት እያለ ፣ የሚመጣው ነገ እንዴት ይሰለቻል ?

ቢሆንስ

ቢሆንስ
.
አሁን በዚህ ሰዓት
ሴትዮዋ እንዴት ናት ?
.

በነገራችን ላይ

ከዚህ ሁሉ ኋላ
የጥላሁን ዘፈን
ሥራውን እርስቶ ፣
መዳፌ ላይ ያለ ፣ መጽሐፍ አንቺን ትቶ ፣
.
ፍቅር እዚህ ቦታ
ብለው የሰቀሉት ፣ ግጥም የለም ጠፍቷል ፣
ገጣሚው እንደ እግዜር ፣ ብቸኝነት ፈርቷል ።
.
በእርግጥ !
.
የሆነውን ሁሉ
አሁን የለም ብለው ፣ ሲገፉት እንዳሻው ፣
ከሁሉም መሸሽ ነው ፣ የሰው መጨረሻው ፣

_____
ሶሎሞን ሽፈራው

JOIN
@yourpoim
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሆነብንን አስብ💔

[ እዮብ ]
Join
@yourpoim
@yourpoim
Forwarded from Ethio entertainment
Delighting your life is our job
HTML Embed Code:
2024/05/21 00:51:10
Back to Top