TG Telegram Group Link
Channel: ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
Back to Bottom
Mahbere Kidusan Album No. 6
MK6
"ለዐቢይ ጾሙ የሚኾኑና በ MP3 የአዘጋጀሁትን የንስሓ የመዝሙራት ስብስብ አጣነው" እያላችሁ በተደጋጋሚ ለጠየቃችሁ እኅት ወንድሞች ኹሉ!
(መዝሙሩን በድጋሚ "share" አድርጌላችኋለሁ። መዝሙራቱ ፍጹም የንስሓ ሲኾኑ ከምድራዊው ዓለም አውጥተው በመንፈስ ቀራኒዮ ወስደው የመድኀኔ ዓለም ክርስቶስን መከራ መስቀል የሚያሳዩን የሚያሳስቡን ስለሆኑ ተጠቀሙባቸው።)

https://hottg.com/kegedilatandebet27217
Audio
"" ተናገርሁ፥ ነገር ግን አልሰማችሁኝም! "" (ኤር. ፴፭:፲፬)

"በዓለ ጻድቃን፤ ዞሲማስ ወእስትንፋሰ ክርስቶስ"

(ሚያዝያ 9 - 2016)

ዝክረቅዱሳን (ማኅበረ ቅዱስ ዳዊት)

" ፍቅር ያጌብረኒ ከመ እንግር ዜናሆሙ ለቅዱሳን"::/የቅዱሳንን ዜና(ታሪክ) እንድመሰክር ፍቅር ያስገድደኛል::
       አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ /መጽሐፈ ምሥጢር/
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Facebook 432050612748813
" ተዝካረ ሰማዕታት ንጹሐን "

በሊብያ ምድር የተሰዉ ሰማዕታት ወንድሞቻችን ፱ኛ ዓመት መታሰቢያ!

https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Audio
"" ቅዱስ ሚካኤል ""

"ጥቂት ሐተታ"

(ሚያዝያ 12 - 2016)

🔍https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Audio
"" ሥርዓተ ጸሎት "" (ክፍል ፬/4)

"የሦስት ሰዓት ጸሎት"

"ጸሎት ዘሰብዓቱ ጊዜያት" (ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

(ሚያዝያ 4 - 2016)

🔎https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Audio
"" ይህ ማን ነው? "" (ማቴ. ፳፩:፲ ፤ መዝ. ፳፫:፰)

"" በዓለ ሆሳዕና ""

(ሚያዝያ 20 - 2016)
🛑በዩቲብለመከታተል👉https://www.youtube.com/@ZikereKedusan
Audio
"" ሥርዓተ ጸሎት "" (ክፍል ፭/5)

"የስድስት ሰዓት ጸሎት"

"ጸሎት ዘሰብዓቱ ጊዜያት" (ዘአባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

(ሚያዝያ 11 - 2016)
Forwarded from 🎤ድምፀ ተዋህዶ🎤 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
#የሰሙነ_ሕማማት_ሰኞ

#መርገመ_በለስ የተፈጸመበት ዕለት ነው

ጌታችንና አምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሆሣዕና ዕለት ቢታንያ አድሮ በማግሥቱም ከቢታኒያ ሲመጡ ተራበ፡፡ (ማር.11፤11-12) ቅጠል ያላት በለስ ከሩቅ አይቶ ወደ በለሲቱ ቀረበ፤ ነገር ግን ከቅጠል በቀር አንዳች ፍሬ አላገኘባትም፡፡ ከአሁን ጀምሮ ማንም ከአንቺ ፍሬ አይብላ ብሎ ረገማት። በለስ የተባለች ቤተ እስራኤል ናት፤ ፍሬ የተባለች ሃይማኖትና ምግባር ናት፤ ከእስራኤል ፍቅርን፤ ሃይማኖትን፤ ምግባርን ፈለገ አላገኘም፤ እስራኤል (ሕዝበ እግዚአብሔር) መባልን እንጂ፤ ደግ ሰው አይገኝብሽ ብሎ ረገማት፤ በመርገሙ ምክንያት እርሱ ከለያቸው በስተቀር ደግ ሰው ጠፋባት፡፡

በለስ ኦሪት ናት፤ ኦሪትን በዚህ ዓለም ሰፍና ቢያገኛት ኦሪትና ነቢያትን ልሽር አልመጣሁም ልፈጽም እንጂ በማለት ፈጸማት፤ ሕገ ኦሪትን ከመፈጸም በቀር በእርሷ ድኅነት አላደረገባትምና፤ ፍሬ በአንቺ አይሁን አላት፤ ደኅነት በአንቺ አይደረግብሽ ብሏታልና እንደመድረቅ ፈጥና አለፈች፡፡

በለስ ኃጢአት ናት፤ የበለስ ቅጠል ሰፊ እንደሆነች ሁሉ ኃጢአት በዚህ ዓለም ሰፍታ ሰፍና አገኛት፡፡ በለስ ሲበሉት ይጣፍጣል፤ ቆይቶ ግን ይመራል፤ ኃጢአትም ሲሰሩት ደስ ደስ ያሰኛል፤ ኋላ ግን ያሳዝናል፤ ወደ እርሷም ሄዶ ማለትም ከኃጥአን ጋር ዋለ፤ ኃጥእ ከመባል በቀር በአንደበቱ ሐሰት፤ በሰውነቱ ክፋት እንዳልተገኘበት ለማመልከት ፍሬ አላገኘባትም አለ፤ በአንቺ ፍሬ አይገኝ የሚለውም፤ በኃጢአት ፍዳ ተይዞ የሚቀር አይኑር ለማለት ነው፤ ስትረገም ፈጥና መድረቋም፣ በአዳም ምክንያት ያገኘችን ዕዳ በደል በእርሱ ካሣነት እንደጠፋችልን ለመግለጽ ነው፡፡

#አንጽሆተ_ቤተ_መቅደስ የተፈጸመበት ዕለት ነው፦

ጌታችን በለስን ከረገማት በኋላ ወደ ቤተ መቅደስ ሄደ፤ ቤተ መቅደስ፣ ቤተ ጸሎት፣ ቤተ መሥዋዕት መሆኑ ቀርቶ ቤተ ምስያጥ (የንግድ ቤት) ሆኖ ቢያገኘው ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች፤ እናንተ ግን የወንበዶች ዋሻ አደረጋችኋት ብሎ የሚሸጡበትን ሁሉ ገለበጠባቸው፤ ገርፎም አስወጣቸው፤ ይህም የሚያሳየው ማደሪያው ቤቱ የነበርን የአዳም ልጆች ኃጢአት ሰፍኖብን ስንኖር ቢያገኘን ኃጢአታችንን ሁሉ እንዳራቀልን የሚገልጽ ነው፡፡

በዚህ በሰሙነ ሕማማት ካህናትና ምእመናን በቤተክርስቲያን ተገኝተው ወዛቸው ጠብ እስኪል ድረስ በነግህ፤ በሠለስተ፣ በስድስቱ ሰዓት፤ በተሰዓቱ ሰዓትና በሠርክ መላልሰው ሲሰግዱና ሲጸልዩ ይሰነብታሉ፤ በተለይም ካህናት በማንኛውም አገልግሎት ጥቁር ልብስ ይለብሳሉ፤ ምክንያቱም የደረሰብን መከራ ኀዘኑን እና 5ሺ ከ5መቶ ዘመን የሰው ልጅ በጨለማ ይኖር እንደነበረ ለማዘከር ነው፡፡

https://hottg.com/dmtse_tewaedo
ኑ ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ
<unknown> – _ ሕማማት _ ክፍል 2 ይሁዳ የመረጠው ጌታ ጸሐፊ ዲ.ሄኖክ ኃይሌ ተራኪ
ሰላም ለናተ ይሁን የዚህ ቻናል ተከታታዮች
    በዲ/ን ሄኖክ ሀይሌ የተዘጋጀ  #ህማማት የተሰኘውን መፀሀፍ በተከታታይ በድምፅ የቀረበውን ወደላይ እየገባችሁ አዳምጡ 🕊🌿👏
HTML Embed Code:
2024/04/29 13:31:36
Back to Top