TG Telegram Group Link
Channel: ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ
Back to Bottom
‹‹ወልድኪ መድኃኔዓለም ዲበ ዕፅ ተቀነወ ዘፄወወ ሕዝበ በደሙ ቤዘወ››
‹‹ልጅሽ መድኃኔዓለም በመስቀል ላይ ተቸነከረ በባርነት የነበረውን ሕዝብ በደሙ ተቤዠ››

አባታችን አዳም በበሊዓ ዕጸ በለስ (ዕጸ በለስ በመብላት) ከአምላኩ ተጣልቶ ከገነት ወጥቶ ጸጋውን አጥቶ ለድካም ለመከራ ከምድረ ፋይድ ገብቶ ባለበት ጊዜ ራሱን ጎድቶ ያነባውን ያለቀሰውን የዕንባ ለቅሶ በደሙ ያቀረበውን የይቅርታ መስዋዕት ፈጣሪው ተመልክቶለት የመጀመሪያውን ከሰው ልጅ ጋር ያደረገውን ቃል ኪዳን ለእርሱ ሰጠው፡፡ ቃል ኪዳኑም ይህ ነበር ‹ዓለም (አንተና ዘርህ) በአንተ ደም አትድንም ከአምስት ቀን ተኩል በኋላ (ከ5500 ዘመን) ከልጅ ልጅህ ተወልጄ በደሜ አድንሃለሁ›፡፡
በመሆኑም አዳም የተሰጠውን የተስፋ ቃል በማሰብ በተስፋ ይኖር ጀመር፡፡ ይህ የተገባለት ተስፋ ከአምላኩ ይቅርታን አግኝቶ ‹በእንተ ሔዋን ተአጽወ ኆኅተ ገነት› ‹በሔዋን ምክንያት የገነት ደጅ ተዘጋ› እንዲል በበደላቸው ተዘግታ የነበረችው ገነት መከፈትን የምታበስር ታላቅ ተስፋ ነበረች፡፡ከአዳም በኋላ የተነሳው በህገ ልቡና ቀናውን ቢከተል በረከት እየበዛለት እድሜው እየተጨመረለት ጥፋትን ቢከተል እድሜው እያጠረበት ሞቱ እየቀረበበት ያለ ሕግ በልቡና መሪነት ይኖሩ ነበር፡፡ ሆኖም ግን መልካም የሠራው በጽድቅ ሥራው ገነትን ሊከፍት አልቻለም ነበር፡፡ ምግባሩ ሰናይ ካልሆነው ጋር በሲኦል ይደመር ነበር እንጂ! ምንም ቅሉ ይህ ቢሆንም መልካም ሥራ ሠርተው ያረፉትን ቅዱሳን ጻድቃን ነቢያትን በቸርነቱ በረድኤቱ ይጠብቃቸው ነበር፡፡ ጥላ የፀሐይን ሙቀት እንዲከላከል እንዲሁ ረድኤተ እግዚአብሔር መልካም ስራ የሰሩትን በሲኦል ካለው ስቃይ እና መከራ ይጠብቃቸው ነበር፡፡
እግዚአብሔር ለአዳም የገባውን ቃል በየዘመኑ በተነሱ ነቢያት ተፈፃሚ እንደሚሆን አፍ ከፍቶ ቃል አሣክቶ ንግግር አቅንቶ ሕዝቡን ያፅናና ነበር፡፡ ሕዝቅኤል ነቢይ በዘመኑ “ርኢኩ ኆኅተ በምሥራቅ ኀቱም በዓቢይ መንክር ማኀተም አልቦ ዘቦአ ዘእንበለ እግዚአ ኃያላን” “በታላቅ ቁልፍ የተዘጋች ደጅ በመሥራቅ አየሁ ከኃያላን ጌታ በቀር ወደ እርስዋ ገብቶ የወጣ የለም” /ህዝ 4፡4/ ሲል፣ ነቢዩ ኢሳያስም “ህፃን ተወልደ ለነ ወልድ ተውህበ ለነ” “ህፃን ተወልዶልናል ወንድ ልጅም ተሠጥቶናል” /ኢሳ 9፡6/ “ናሁ ድንግል ትፀንስ ወትወልድ ወልደ ወትስምዮ ስሙ አማኑኤል” “እነሆ ድንግል በድንግልና ትፀንሳለች ወንድ ልጅም ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ትለዋለች “ /ኢሳ 7፡14/ ፣ እና ሌሎችም ነቢያት ከደቂቀ ነቢያት እንደሚክያስ ያሉ ከአበይት ነቢያት ከላይ ከተጠቀሱት ውጪ እንደ ነቢዩ ዳንኤል ያሉ ነቢያቶች አባታችን መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊትም “ናሁ ሰማዕናሁ በኤፍራታ ወረከብናሁ ውስተ ዖመ ገዳም” “እነሆ በኤፍራታ ሰማነው በዱር ውስጥም አገኘነው” በማለት ስለ ወልደ እግዚአብሔር ሰው መሆን ትንቢት ተናግረዋል፡፡ አምላካችን ቅዱስ እግዚአብሔር ይታየው ምሣሌ የተነገረው ትንቢት ይፈፅም ዘንድ ጊዜው ሲደርስ ንጽሐ ሥጋ፣ ንስሐ ኀሊና፣ ንጽሐ ነፍስን አስተባብራ በያዘችው አስቀድሞ በሥላሴ ኀሊና በታሰበችው በድንግል ማኀፀን በብሥራተ ገብርኤል አደረ፡፡ ጠባቧ የድንግል ማኀፀን ስፍሕት (ሰፊ) ሆና የሠማይ ስርዓት ተከናወነባት ኋላም እንደ ሠው ስርዓት ፈጣሬ ዓለማት ወልድ ኢየሱስ ክርስቶስ በበረሃ ውስጥ በቤተልሔም ተወለደ /ሉቃ 2/ “ፈቂዶ ይፌውስ ትዝምደ ሰብእ ተገረም በማኀፀነ ድንግል “የሠውን ወገን ያድን ዘንድ ወዶ ፈቅዶ በድንግል ማኀፀን አደረ” እንዲል ትምህርተ ኀብአት በተጨማሪ “ሥጋ ለብሰ ዘይማስን ወዘኢይማስን ለሥጋ መዋቲ ረሰዮ ዘኢይማስን” “የማይፈርሰው የሚፈርሰው ሥጋ ለበስ የሚሞተው ሥጋ እንዳይሞት /እንዳይፈርስ/ አደረገው” ተብሎ እንደተፃፈ (በትምህርት ኀቡአት)፡፡አባታችን ቅዱስ ያሬድም በአንቀጸ ብርሃን “እንዘ አልቦቱ እም በሰማያት ወአብ በዲበ ምድር “በሠማይ እናት በምድር ደግሞ አባት የለውም” በማለት ሁለተኛ ልደቱ ያለ አባት መሆኑን ይገልፃል ጌታችን ከወላዲተ አምላክ ከድንግል ሥጋን ከነሣ በኋላ /ከተወለደ በኋላ/ እንደ ህፃናት እየተጫወተ እየተማረ ከኃጢአት በስተቀር የሠውን ስርአት ሁሉ ፈፅሟል፡፡ ‹ወኮነ ሰብአ ከማነ ዘእንበለ ኃጢአት በህቲታ› “ከኃጢአት በቀር እንደ እኛ ሰው ሆነ› እንዳለ ቅዱስ ኤፍሬም /ውዳሴ ማርያም ዘሐሙስ/ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የዕብራውያንን ህግ ተምሮ በ30 ዘመኑ በዮሐንስ እጅ በዮርዳኖስ ከተጠመቀ በኋላ አርባ ቀንና ሌሊት ፆሞ ብዙ ተአምራትን ፈፅሟል፡፡ ይህንን ሲገልፅ ሊቁ ቅዱስ ሕርያቆስ እንዲህ አለ ‹ፍጹመ ኮነ ሰብአ ወኩሎ ሕገ ሰብአ ፈጸመ ዘእንበለ ኃጢአት› ‹ከኃጢአት በስተቀር የሰውን ሕግ ፈፀመ ‹እምኀበ ዮሐንስ ተጠምቀ ውስተ ገዳም ተመከረ ርኀበ ወጸምአ ወተአምራት ገብረ› ‹ፍፁም ሰው ሆነ ከኃጢአት በስተቀር የሠውን ህግ ፈፀመ የዕብራውያንን ሕግ ተማረ ከዮሐንስ ዘንድ ተጠመቀ በበረሀ ተፈተነ ››/ቅዳሴ ማርያም/
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ አዳምን ነፃ የሚያወጣበት ራሱን አሣልፎ የሚሠጥበት ጊዜ ከመድረሱ አሰቀድሞ በዕለተ ሐሙስ ምሽት መድኃኒት የሚሆን ሥጋውና ደሙን ለዓለም ሠጥቷል፡፡ ስርዓተ ቁርባንን ሠርቷል፡፡ /ማቴ 26፡26/ ይህንን ሥርዓት ከሠራ በኋላም አይሁድ ተሰብስበው ሊይዙት ገመድ ይዘው ወደ ጌቴሴማኒ መጡ፡፡ ‹‹ዘይሰሰይ አክልየ አንስአ ሰኰናሁ በላዕሌየ› ‹እንጀራዬን የበላ በእኔ ላይ ተረከዙን አነሣ /መዝ 40፡9/ እንዳለ ቅዱስ ዳዊት፣ ያስተምረው የነበረው የአስቆሮቱ ይሁዳ በ30 ብር አሳልፎ ሠጠው አይሁደም፣ < አምላክ ነኝ ይላል>፣ ፣ ፣ የሰንበትን ቀን ሽሯል በሚሉ የሐሰት ሀሳቦች ተነሥተው ከተያዘበት ሠዓት ጀምረው ያሰቃዩት ነበር፡፡ ሲነጋም በሐሰት ክስ አስፈርደውበት ሊቀጡት በጲላጦስ ፊት አቆሙት፡፡ ‹ሰላም ለአዕጋሪከ እለ ጠብዓ ለቀዊም ቅድመ ጲላጦስ መስፍነ ይሁዳ ወሮም› ‹በሮም እና በይሁዳ መስፍን በጲላጦስ ፊት ያለ ፍርሃት በድፍረት ለቆሙ እግሮችህ ሠላም እላለሁ> እንዲል /መልክዓ ኢየሱስ/›፡፡ የይሁዳ እና የሮም መስፍን የሆነው ጲላጦስ በደል ባያገኝበት የሕዝቡን ዓመፅ ፈርቶ አንደ ፈቃዳቸው ፈረደላቸው አይሁድም እየገፉ፣ እያዳፉ መስቀል አሸክመው ወደ ቀራንዮ አወጡት፡፡ በዕለተ አርብ 6፡00 ሰዓት በሆነም ጊዜ እጆቹን እግሮቹን ቸነከሩት በመስቀል ላይ ሰቀሉት ከገረፉት ግርፋትም የተነሳ ሥጋው አልቆ አጥንቶቹ ይታዩ ነበር (ድርሳነ ማኅየዊ)፡፡ በመዝ 21 ላይ ‹‹ዐገቱኒ ከለባት ብዙኃን ማኀበረ ለእኩያን ቀነውኒ እደውየ ወእገርየ፣ ወኆለቁ ኩሎ አዕፅምትየ›› ‹‹ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼን እግሮቼን ቸነከሩኝ አጠንቶቼ ሁሉ ተቆጠሩ›› ተብሎ በቅዱስ ዳዊት እንደተነገረ ጌታችን አዳም እፀ በለስን ስለመብላቱ ጌታ በአፍ ሀሞት ተጐነጨ፣ ይህንን ሁሉ መከራ ስለ አዳም ተቀበለ በጠቅላላው 13 ሕማማትን ስለ ሠው ልጆች ተሸከመ፡፡ በቅዳሴ እግዚእ ላይ “ሰፍሐ እደዊሁ ለሕማም ሐመ ከመ ሕሙማን ያድኀን እለ ተወከሉ በላዕሌሁ” ‹‹እጆቹን ለሕማም ዘረጋ በእርሱ የታመኑትን ያድን ዘንድ አንደ ሕሙማን ታመመ›› ተብሎ እንደተፃፈ፡፡
ከብዙ ሕማም በኋላ የሠማያትና የምድር ጌታ በመስቀል ሆኖ “ተፈፀመ” አለ፡፡ በ9፡00 ሰዓት ላይ ሥጋውን ከነፍሱ ለየ ሰይጣንም እንደልማዱ ይህች ነፍስ የእኔ ናት ብሎ ቢጠጋ አምላካችን በነፋስ አውታር አሠረው በዚህ ጊዜ ዲያቢሎስ አንዲህ ሲል ጮኸ ‹መኑ ዝንቱ ዘምድረ ለብሰ ውእቱኬ ሰማያዊ ውእቱ› ‹እንደ ምድራዊ የለበሰ /ምድራዊ የመሠለ/ ነገር ግን ሠማያዊ የሆነ ይህ ማን ነው? በማለት ተናገረ፡፡
በዚህ ቅጽበት ጌታ ሲኦልን በረበረ አዳም እና ልጆቹን ከዲያቢሎስ ባርነት ነፃ አወጣ፡፡ ይህንን ታሪክ ማውሳታችን ስለምን ነው ቢሉ በ መጋቢት 27 ቀን በቤተክርስቲያን ትምህርት ጌታችን የተሠቀለበት ጥንተ ስቅለቱ የሚታሰብበት ስለሆነ ነው፡፡ ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ግን በዲሜጥሮስ ቀመር መሠረት አጽዋማትን በጠበቀ መልኩ ከትንሣኤ በዓል በፊት ያለውን አርብ “ስቅለት” ተብሎ እንዲከበር ሥርአት ሠርተዋል፡፡
የጌታችን የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ የህማሙ ረድኤተ በረከት በሁላችን ላይ ይደርብን የድንግል ማርያም ፍቅሯን በልቡናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ይሣልብን። መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዚህ ከሃላፊው ዓለም ያድነን።
አሜን


Join :-\ @yetenantun_lenege
ይድረስ ለወዳጆቻችን በሙሉ በያላችሁበት ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ በወዳጃች በቀሲስ ያሬድ https://www.youtube.com/watch?v=qbFZ4zRGVXM
ቻናል እንቀርብና እናወጋለን። ጠብቁኝማ።

ነጭነጯንማ እናወራለን።

ሻሎም ! ሰላም !
YouTube - A call to refrain from double killing the victims

#Zemedkun_Vs_YouTube

Here is the fact that the YouTube company is unaware about. A massive massacre and displacement of The Ethiopian Orthodox Tewahdo believers and burning to ash of her Churches is being conducted.

The magnitude of such act is increasingly aggressive in the last three years. Upon a single phone call of an activist named Jawar, the precious lives of 86 Christians were slain away, just a year ago. The aftermath shown several displacements, burning down and demolition of more than 20 Churches.

Not limited to this, following a premeditated attack on 1st of July 2020, brutal genocide effected in the eastern and south eastern regions of Ethiopia. The corpse of the diseased were chopped. A child in its mother womb was brought to death, so that a Christian successor shouldn’t get born in “their land” as the aggressors proclaimed.

The right to life is at stake, especially when one is found to be Orthodox. There was an attempt to kill 5 Bishops as the charge of the attorney general shows. The houses and merchandises of the Orthodox believers were turned to ash devastatingly. All horrific things happen to the Christians.

The violent attacks were led by local and federal officials as the Ethiopian government itself witnessed. The Church condemned the act on her press release. And pronounced the attack as genocide.

Advocating to these people can’t in any way be considered hate speech. Zemedkun Bekele is one of many advocates to this regard. He has been doing his best to rehabilitate the displaced through a tireless effort. He uses YouTube as a social media platform, to facilitate and coordinate the purpose.

Recently we have learnt that YouTube has banned his channel as a result of hate speech report. Those people who reported against him should be the prime suspects who are in alliance with the same people instigating the death and the uncountable suffering the Church received.

Listening to this people is like double killing the victims. Hence we strongly disagree the decision of banning Zemedkun. Let YouTube show it stands with humanity by lifting the embargo.

#YouTube_lift_the_ban_against_Zemedkun_Bekele
ተደራጁ ተብላችኋል።
*~★★~*

• ፎቶዎቹን ለብልጽግና ደጋፊዎችና አባላት፣ ለሄት ስፒች ተሟጋቾች፣ ለጠልፎ ጣይ አፈጻድቆች ሁሉ አድርሱልኝ።

• እኔን እንደ እብድ ብቻዬን የሚያስጮኸኝ እናንተንም እስቲ ያስጩሃችሁ። እኔን እና ጥቂቶችን ብቻ እንቅልፍ የሚያሳጣኝ እስቲ እናንተም ሞክሩት። ዐማራ ዘሩ እንዴት እየጠፋ እንዳለ ከጅምላ እርዱ ተመልከቱ።

• ኢሳያስ አፈውርቂ የመጣው የመተከሉን እርድ ለማስቀየስ፣ የአንበጣውን ውድመት ለማስቀየስና አጀንዳ ለማስቀየር መሆኑ ግን ሁሉ ይወቅ።

#ETHIOPIA | ~ “ Network Against Hate-Speech ቾች” ግን በዚህ ደግሞ እንዳያኮርፉኝ። አደራ !!

•••
“ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን አስተባብራና አደራጅታ ራሷን ለመከላከል የተገደደችበት ዘመን ላይ ደርሰናል። አለበለዚያ ዕጣ ፈንታዋ እጅግ አስጊ እየሆነ መጥቷል። ልጆቿ እየተገደሉባት፣ ነጻነት አጥተውና ተሳቅቀው እየኖሩ ቤተ ክርስቲያንን ጠበቅን ማለት አይቻልም። [ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ] ”

•••
“ የአካባቢው ነዋሪ ራሱን አደራጅቶ አስፈላጊውን ትጥቅ ታጥቆ የተጠናከረ የመከላከል አቅም መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን።

https://m.facebook.com/story.php?story_fbid=2800450193548933&id=1903939863199975

•••
እኔ ዘመዴም አስቀድሜ ያልኩት ይሄንኑ ነበር። ከአዲስ አበባ የሚነሣውና ከአቢይ (አብዱ) አሕመድ የብልፅግና ቤተ መንግሥት ድጋፍ በሚያገኘው በማኅበረ ቅዱሳኑ አባል በእነ ቀሲስ ሙሉቀንና ዮሴፍ አባይ የሚመራው በኢዜማ መሪዎችና ደጋፊዎች በብርሃኑ ነጋ አምላኪዎች በእነ ኢዮብ አለነ በሚታገዘው Network Againest hate-Speech አማካኝነት በተደረገ ውትውታ ከዩቱዩብ ላይ እንዲወርድ የተደረገው ቪድዮዬ ላይ የልኩት የተናገርኩትም ይሄንኑ ነበር። እኔ ቀደም ብዬ ተናገርኩትና አሁን ቅዱስነታቸውና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ትናንትናና ዛሬ የተናገሩት አንድና ተመሳሳይ ነው። አሁን እነሱ ጻድቅ ሆነው እኔን ትክክል አይደለህም ሲሉኝ የነበሩ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና፣ እንደተሳዳቢም ቆጥረው ከፌስቡክም ከዩቲዩብም እንድወርድ ሲወተውቱ የነበሩ የግንቦት ሰባት አባላትና አመራሮች ምን ይሉ ይሆን? አሁንስ ለዩቲዩብ እና ለፌስቡክ ይህን ራስን የመከላከል ዜና ሪፖርት ያደርጉ ይሆን? ወንድሜ ዮሐንስ ሞላም ይሄን ጥቆማዬን ይዘህ አንተ ራስን መከላከል ኃጢአት ነው ባይ ነህና ለፌስቡክም፣ ለዩቲዩብም ሪፖርት ታደርግባቸው ዘንድ ጥቆማዬን አቀርብልሃለሁ።

•••
መጪው ጊዜ ለኢትዮጵያ ከባድ ነው። የውጭ ጠላት ሁሉን ሊያርድ ሁሉን ሊበላ አሰፍስፎ ከደጅ ቆሟል። የሚያሳዝኑት የቤታችን ጉዶች፣ ሰው መሳይ በሸንጎዎች፣ ጎጠኛ መንደርተኛ፣ ለመጣ ሥርዓት ሁሉ አለቅላቂዎች፣ ገንዘብ መሰብሰብ እንጂ ሌላ ህልም የሌላቸው ከንቱዎች፣ ሌላ ሰው መጥቶ ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲያሰማና ሲደመጥ የተሸፈኑ የሚመስላቸው ነውረኞች፣ በጓዳ መርዝ የመርዝ ብልቃጦች፣ በአደባባይ በሸንጎ ሰው መሳዮች። የቤት ውስጥ ቀጋ የውጭ አልጋዎች እነሱ ናቸው የሚያሳዝኑኝ።

•••
ሁለተኛ ዙር “ የበረኞቹ ” መልእክት መጥቷል። ደርሶኛልም። አውርተውኛልም። ሰሞኑን ለህዝቡ ሁሉ በቴሌግራሜ እለቀው ዘንድም አውርተውኛል። ልቀቀው ባሉኝ ቀን እለቀዋለሁ። ንስሐ ገብቶ ተዘጋጅቶ መጠበቁ የግድ ነው። የዘንድሮው የዐብይ ጾም ደግሞ ከአምናው የከበደና የባሰ ሳይሆን አይቀርም። የማይነቅዝ እህል እና ጨው አስቀምጡ ብለው ከዛሬ ዓመት በፊት በእኔ በኩል የነገሯችሁን ምክርም ምን ያህሎቹ ተግባራዊ እንዳደረጋችሁ አይታወቅም። ወደ መትረፊያ ገዳማትም ላኩላቸው የተባለውንም እንዲሁ አድርጉ።

•••
ባለፈው መስከረም 5/2013 ዓም በረኸኞቹ ባስተላለፉት መልእክት ላይ “የኢትዮጵያ ብር የወረቀት ያህል እንኳ ዋጋ አያገኝም” ያሉትንም አሁን እያየነው። በከተማ የምትኖሩ ዜጎች በገጠር ለሚኖሩ ቤተሰቦቻችሁ ከፎርጅድ ብር እንዲጠነቀቁም አድርጉ። ሥርዓተ መንግሥቱ ከሽፏል። የዱርዬ ስብስብም ሆኗል። ምከሩም። ራቡ ግልጽ ነው። በሽታውም ተከታይ ነው። ጦርነቱም የሚታይ ነው።

•••
በአቢይና ሽመልስ የሚታዘዝ ጦር ዐማራን፣ ባለማተቦችን ከመተከል ከርስቱ የማጽዳት ሥራውን ቀጥሎበታል። በደቡብ ጉማይዴም ዐማሮች እየታረዱ ነው። ምንም ሲያዩአቸው ቢያስጨንቁም በነገው ዕለት ቪድዮዎቹን እለቅላችኋለሁ። እነ ዮሐንስ ሞላ፣ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን መብት አስጠባቂዎች ነን ባዮቹ እነ ቀሲስ ሙሉቀን፣ እነ ዮሴፍ አባይን የመሳሰሉ እኩያን፣ ከሃይማኖታቸው ዘራቸውና ፍርፋሪ የበለጠባቸው አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና መሪዎችም ይበሳጫሉ፣ ይናደዳሉ ብዬ፣ የኢዜማ ግንቦት ሰባት መሪዎችና ደጋፊዎች፣ እነ ህወሓት ብልፅግና፣ ኦነግና ብአዴኖች ያኮርፉኛል፣ ይበሳጩብኛል ብዬም እኔ ዘመዴ በአደባባይ ለሚታረደውና ዘሩ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ለተፈረደበት ምስኪኑ ዐማራ መጮሄን አላቋርጥም።

•••
ዛሬ ዐማራው ሲታረድ፣ ሲሰደድ፣ ሲሰቃይ፣ ዘሩ ሲጠፋ ከዳር ቆማችሁ ያያችሁ፣ ዝም ጭጭ ያላችሁ፣ በደስታም ጮቤ የረገጣችሁ፣ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጣችሁ፣ እነዚያን ምስኪኖች ያገኘ፣ ስብራትና ሃዘን እናንተንም ያግኛችሁ። በላያችሁም ላይ ይውደቅ። በቤታችሁና በራሳችሁ የእኔ በምትሉትም ሁሉ ላይ ደርሶ ያሳያችሁ። “ አቢይ እሱ ምን ያድርግ? ብላችሁ ለዐብይ ጥብቅና የቆማችሁ፣ በእናንተ ደርሶ ዐብይ ምንያድርግ? ብዬ እናንተን ለመጠየቅ ያብቃኝ። የህጻናት፣ የእናቶችና የአባቶች ደም ይፋረዳችሁ። እንቅልፍ፣ ሰላም፣ እረፍትም ያሳጣችሁ። ቤታችሁ በሃዘን ይጎብኝ፣ ማቅ ያልብሳችሁ፣ ኃዘን ከቤታችሁ ይግባ፣ ከአቢይ አህመድ መንግሥት ጋር ቆማችሁ ለምስኪኖች ላለመድረስ የተለጎማችሁ ዲዳም ዱዳም ያድርጋችሁ። በራስ በቤተሰባችሁ ስብራት ይድረስ። አሜን !!

•••
በግፍ የታረዱትን ዐማሮች ነፍስ ይማር !!
•••

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥቅምት 3/2013 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
+ + + + + + + + + + + + +

ራስን በራስ የመጠበቅ ጥሪ


"ቤተ ክርስቲያን ራሷን በራሷ ወደ መጠበቅ ካልተሸጋገረች ዕጣ ፈንታዋ አስጊ ኾኗል።"
ቅዱስ ፓትርያርኩ

ቅድመ ሲኖዶስ በሚካሔደው በ፴፱ኛው የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ የተናገሩት የመክፈቻ ቃል ነው። ቅዱስነታቸው ከ፳፻፲፪ ዓ.ም. የደመራ በዓል ጀምሮ ያልተሸራረፈ ቀጥ ያለ አቋማቸውን እያሰሙ ቆይተዋል። በዘንድሮው የደመራ በዓልም "ከመስቀሉ በላይ ለመኾን የሚደረግ ሩጫ አያዋጣም" ማለታቸውበአይዘነጋም።

በዛሬው የመክፈቻ ንግግራቸው ከተጠቀሱት ፡-

◦ በአሁኑ ጊዜ በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እየደረሰ ካለው መከራ አንጻር ከምንም ጊዜ በላይ ታጥቀን ለቤተ ክርስቲያን ህልውና መቀጠልና ለሕዝበ ክርስቲያኑ የሕይወት ዋስትና መረጋገጥ በአንድነት የምንቆምበት ጊዜ ነው፤

◦ ቤተ ክርስቲያናችን ዛሬ ከገጸ ምድር እናጥፋሽ የሚሉ በምሥራቅም በምዕራብም እየተበራከቱ መጥተዋል፡፡ ከዛሬ ነገ ይሻል ይኾናል፤ ፍትሕም ይገኝ ይኾናል እያልን በተስፋ ብንጠባበቅም ሲኾን አናይም፤ ይልቁንም ከጊዜ ወደ ጊዜ ነገሩ እየተባበሰ፣ ክርስቲያን ልጆቻችንም ለተደጋጋሚ ጥቃት እየተዳረጉ በክርስቲያንነታቸው ብቻ የግፍ ግፍ እየተፈጸመባቸው ይገኛሉ፡፡

◦ አበው ሲናገሩ ‹‹ከራስ በላይ ነፋስ›› እንደሚሉት ቤተ ክርስቲያናችን እየገጠማት ያለውን ችግር ለመቋቋም ልጆቿን አስተባብራና አደራጅታ ራሷን በራሷ ወደመጠበቅ አማራጭ ካልተሸጋገረች ዕጣ ፈንታዋ እጅግ አስጊ እየሆነ መጥቶአል፤ ክርስቲያን ልጆቻችን ተሸማቅቀው፣ ነጻነታቸው ተገፎ፣ በሀገራቸውና በወገናቸው መካከል የመኖርና ሃይማኖታቸውን የመከተል መብት አጥተው ባሉበት ሁኔታ ቤተ ክርስቲያንን እየጠበቅን ነው ማለት አይቻልም፡፡
ስለሆነም ሕዝበ ክርስቲያንን የመጠበቅና የማጽናናት ኃላፊነት ከሁሉ በፊት በቅዱስ ሲኖዶስ ጫንቃ ላይ ያረፈ እንደመኾኑ መጠን በኢትዮጵያ ኦርቶዶከስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የሚዘንበውን መከራ ለመግታት ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ጉባኤ ተገቢውን መፍትሔ ማስቀመጥ ይጠበቅበታል፤

◦ ሌላ ተቀጥላና የቤተ ክርስቲያንን ዓቅም በመከፋፈል ለማዳከም በውስጣችን የሚደረጉ ሤራዎችም ለቤተ ክርስቲያን አንድነትና ጥንካሬ ከባድ ዕንቅፋቶች እየኾኑ መምጣታቸው ሌላ የጥፋት ገጽታ ሆኖ እየታየ ነው ፡፡

በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት የተፈጸመው ሕገ ወጥና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጭ የኾነ የኤጲስ ቆጶሳት ሢመት የኹለት ሺሕ ዘመን ሐዋርያዊ ቀኖና እና ሥርዐት ባላት ቤተ ክርስቲያናችን ቀርቶ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ተደርጎ የማያውቅ ድፍረትና ስሕተት ነው፡፡ በመኾኑም ለዚህ ድርጊት መነሻ የኾኑ ምክንያቶችና የምክንያቱ ሰለባ የኾኑ፣ እንደዚሁም ሳይላኩና ሥልጣኑ ሳይኖራቸው ዳግም ጥምቀትን ዳግም ክህነትን በማወጅ ለዚህ አደጋ መከሠት ምክንያት የኾኑ ሁሉ በማያዳግም ሁኔታ ይህ ጉባኤ የማስቆሚያ መፍትሔ እንዲያበጅላቸው በዚህ አጋጣሚ አጥብቀን እናሳስባለን፡፡

◦ በሀገራችን ያለው ያልተረጋጋ ሁኔታ ያልኾነ መልክ እንዳይዝ መንግሥታችንና የሀገራችን ተፎካካሪ ፓርቲዎች ወንድማማቾች እንደመሆናቸው መጠን ምንም ልዩነት ሳይኖር በክብ ጠረጴዛ ኾነው በመመካከር ችግሮችን ሁሉ እንዲፈቱ እንጂ ወደ አላስፈላጊ ሁኔታ እንዳይገቡ ቤተ ክርስቲያናችን በገለልተኝነትና በእናትነት መንፈስ ማገዝ አለባት፤ ማስታረቅም ማስተማርም አለባት፤ ሁሉም ነገር በሰላምና በውይይት ብቻ እንጂ ከዚህ ባፈነገጠ መልኩ የሚደረግ አማራጭ ከጉዳት በቀር ውጤት አናገኝበትም።

የሚሉ መሠረታዊ አሳቦችን አስገንዝበዋል። እንዲህ እረኝነት ልዕልናውን ሲይዝ በጎቹም በሥርዓት ይከተላሉ።

Share @yetenantun_lenege
በምርጫም በቆጠራም በንቃት ተሳተፉ

ብፁዕ አቡነ ያሬድ


የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ያስተላለፉት ብርቱ መልእክት ነው።

ብፁዕነታቸው ፡-

- [ ] መንግሥት በመስቀል ዐደባባይም በጃን ሜዳም ያደረገውን ሁሉ ሲጀምር አላማከረንም።

- [ ] በዓለ መስቀልን በድምቀት ያላከበርነው በግንባታው የተነሣ የተቆፈረ የተከመረ አፈር ሰፊውን ቦታ ስለያዘው ጭምር እንጅ በወረርሽኙ ብቻ አይደለም። የተከመረው አፈር ባይኖር ርቀት ጠብቆ ብዙ ሰው ሊገኝ ይችል ነበር።

- [ ] የይዞታ ችግር ያለው በሆሳዕና እና በጋሞጎፋ ብቻ አይደለም። በብዙ ቦታዎች ችግሮች አሉ።

- [ ] ቤተ ክርስቲያን በየትኛውም ዓለም በሌለ ሥርዓት ከመቃብር ስፍራዋ ቀንሳ ለሠራቻቸው ት/ቤቶች ሳይቀር ታክስ ክፈይ እየተባለች ነው።

- [ ] መንግሥት በ፳፻፲፫ ዓ.ም. ምርጫ ይካሔዳል እያለ ነው። መብታችንን ለማስከበር በምርጫም በሕዝብ ቆጠራም በንቃት መሳተፍ ይገባናል በማለት ጥሪ አስተላልፈዋል።


እንደዚህ ዓይነት መልእክቶችን #Share ማድረግ አትርሱ
እንኳን ደስስ ያለን !!
*~★★~*

• ከተቻለ ዛሬ ወደ ማታ በፌስቡክ Live ለመግባት እሞክራለሁ። ኣ

#ETHIOPIA | ~ እልልልልልልልል ተመስገን አባቴ መድኃኔዓለም። ከምስጋና በቀር ምን ይከፈልሃል?

… ማዕዶታችን … “ ማዕዶት ዘኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የትናንቱ ለነገ ማኅበራችን ” በፈቃደ እግዚአብሔር የመሠረትነው ማዕዶታችን። ቀደም ሲል ከቤተ ክህነቱ ከቅዱስ ሲኖዶሳችን፣ ዛሬ ደግሞ በወርሀ ጥቅምት በዕለተ ማክሰኞ በበዓለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ፣ በዝቋላው አንበሳ፣ በምድረ ከብዱ ኮከብ በአቡኤ ጣዲቁ ዓመታዊ በዓለ ንግሥ በጻድቁ አማላጅነት በዕለተ ቀናቸው ከኢትዮጵያ መንግሥት ከቤተ መንግሥቱ ከማኅበራት ማደራጃ የዕውቅና ሰርተፍኬቱ በይፋ ተቀብሎ ሥራህን በይፋ ጀምር ተብሏል።

• ሰርተፊኬቱን የማዕዶታችን የቦርድ አባል፣ የኢትዮጵያ ዕንቁዋ ሴት በግሌ የእኔ እህት አትሌት ደራርቱ ቱሉና የማዕዶታችን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ዮናስ በግንባር ቀርበው ተቀብለዋል።

•••
እንግዲህ … እግዚአብሔርም፣ ቤተ ክህነትም፣ ቤተ መንግሥቱም ያሰብነውን፣ ያቀድነውን እንሠራ ዘንድ ያለ ምንም ግርግርና ክርክር ጥርጥርም ፈቅደውልናል። እንኳን ደስ ያለን። እንኳን ደስስ ያላችሁ። ሌላ ምን ይባላል። ኡፋ…ኣ።

•••
ድምጽ ያጠፋነው፣ ወሬም ያላበዛነው፣ በትእግስት የሠራነው ሥራ ፍሬ አፍርቷል። ምስጋና ለእግዚአብሔር፣ ምስጋና ለቅዱሳን ፓትርያርኮቻችን፣ ምስጋና ለቅዱስ ሲኖዶሳችን፣ ምስጋና ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የሕግ ክፍል፣ ምስጋና ለማኅበራት ማደራጃ ሠራተኞችና የሥራ ኃላፊዎች በሙሉ።

… ምስጋና ለማዕዶት ዋና ሥራ አስኪያጅ ለዮኒዬ፣ ምስጋና ለማዕዶት ዘኦርቶዶክስ የቦርድ አባላት በሙሉ። የቀረውን በቀጣይ እመለስበታለሁ። አሁን አውቀን ፈተና ለመቀነስ ሲባል የሌለን እስኪመስል ድረስ የጠፋንበትን የቴሌግራም ግሩፕ እንቅስቃሴ እንደ አዲስ እናቀጣጥለው። ሁላችሁም ግሩፓችሁን አንቀሳቅሱት። ዳይ ፍጠኑ ወደ ሥራ።

… አሁን ቢሮዎች ይከፈቱ። የባንክ አካውንቱ ይከፈት። አባላት በይፋ ለመመዝገብ ተዘጋጁ። አምላኬ ሆይ እንደው ምን አባቴ ልሁንልህ። ለአንተ ውለታ ምንስ ባደርግ፣ እንዴትስ ባመሰግንህ እረካ ይሆን? ብቻ ተመስገንልኝ።

• ስለ አሐዱ ባንክ
• ስለ እኔ ዩቲዩብና
• ስለ ሳታላይት ተሌቪዥን ደግሞ ሌላ የምስራቾች አሉኝ። ዛሬ ዕለቱ የደስታ ማብሠሪያ ብቻ ነው።

#ማስታወሻ | ~ ከተቻለኝ ለመጀመሪያ ጊዜ ዛሬ ወደ ማታ በፌስቡክ Live ለመግባት እሞክራለሁ። የቀጠሮ ሰው ይበለን። አከተመ። ከኑመ ጋ ዱቢን።

•••

ሻሎም ! ሰላም !

ዘመድኩን በቀለ ነኝ።
ጥቅምት 5/2012 ዓም
ከራየን ወንዝ ማዶ።
+ አስከሬን ቢቃጠልስ? +

ከቀብር መልስ እጅህን ታጥበህ ተስተናግደህ ታውቃለህ? ንፍሮስ ቀምሰህ ታውቃለህ? ንፍሮውን ስትበላ እኔ እንደማደርገው ሽንብራ ሽንብራውን ለቅመህ በልተህ ስንዴውን ለሌላ ሰው ትመርቃለህ ወይስ ሁለቱንም ትበላለህ? በሆድህ "ለምንድን ነው ግን ጨዉን የሚያሳንሱት" እያልክ ተመራምረህ ይሆን?

እኔ ደግሞ ዛሬ ከቀብር መልስ ካልጠፋ እህል ስንዴ ለምን እንደሚቀርብ ልነግርህ ነው:: ነገሩ ባሕል ብቻ ሳይሆን ሃይማኖትም ነው::

ቀብረን ከተመለስን በኁዋላ ስንዴ ስንበላ የንፍሮውን ጣዕም ማሰላሰል ትተን ይህንን የጌታችን ቃል እናስታውስ :-

"እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ የስንዴ ቅንጣት በምድር ወድቃ ካልሞተች ብቻዋን ትቀራለች፤ ብትሞት ግን ብዙ ፍሬ ታፈራለች" ዮሐ 12:24

ከቀብር መልስ በንፍሮ መልክ የምንበላው ስንዴ ኀዘንተኞችን የሚያጽናና ትልቅ መልእክት ይዞአል::
ክርስቶስ ስንዴ የሚያፈራው ሞቶ በምድር ሲቀበር ነው ብሎ ስንዴን ለእኛ ሞትና ትንሣኤ ምሳሌ አድርጎታል:: ቀብረህ ስትመለስ በእጅህ የዘገንከው ስንዴ ቀብረኸው የመጣኸው ወንድምህ ትንሣኤ እንዳለው እየነገረ ያጽናናሃል:: በምድር የወደቀ ስንዴን ያልረሳ አምላክ የሞተውን አይረሳም::
ቀብረነው መጣን ብለህ አትዘን:: ዘርተኸው እንደመጣህ አስብ:: በመዋረድ ብትዘራውም በክብር ይነሣል:: በድካም ብትዘራውም በኃይል ይነሣል:: ለመበስበስ ብትዘራውም ባለመበስበስ ይነሣል ይልሃል ሐዋርያው (1 ቆሮ 15:42-43)

ነፍሳችን ከሥጋችን በተለየች ጊዜ በምድር አስከሬናችን ይቀራል:: አስከሬን (በግሪክ ስክሪኒዉም) ኮሮጆ መያዣ ማኅደር ማለት ነው:: "ንዒ ማርያም ለእግዚአብሔር አስከሬኑ" "የእግዚአብሔር ማደሪያው ማርያም ሆይ ነይ" እንዲል:: የነፍሳችን ማደሪያ የሆነው ሥጋ ከአዳሪዋ ነፍስ ሲለይ አስከሬን (ማደሪያ) የነፍስ ሳጥን የሚል ስም ይሠጠዋል:: ሬሳ የሚለው ቃል የበሰበሰ ነገር

ምሥራቃውያኑ የቡድሃና ሂንዱ ተከታዮች ሥጋን የነፍስ እስር ቤት አድርገው ስለሚያምኑ ሥጋ ሲቃጠል ነፍስ ነፃ ይወጣል ብለው አስከሬን ያቃጥላሉ:: በዳግም ሥጋዌ (reincarnation) የሚያምኑ በመሆናቸውም አንድ ሰው ድጋሚ ሲፈጠር የተሻለ አካል ይዞ እንዲወለድ አሮጌው ሥጋው መቃጠል አለበት ብለው ያስተምራሉ::

እኛ ግን እንቀብራለን እንጂ በፍጹም አስከሬን አናቃጥልም:: የሚቀበር ነገር ዋጋ ያለውና በኁዋላ የሚፈለግ ነገር ነው:: ገንዘብ የምትቀብረው ሌላ ጊዜ ልታወጣው ካሰብክ ነው:: የምታቃጥለው ግን የማትፈልገውን ነው:: የምንቀበረው እንደምንወጣ ስለምናምን ነው:: የመለከት ድምፅ ሰምተን እንደምንነሣ ተስፋ ስላለን ምንም ብንሞትም በተስፋ እንቀበራለን:: እንደምንበቅል ተስፋ አድርገን እንዘራለን:: ሌላው ቢቀር በእሳት ተቃጥለን ብንሞት እንኳን አመዱንምና የከሰለውን አጥንትም ቢሆን በተስፋ እንቀብረዋለን::

"የሙታንን መነሣት ተስፋ እናደርጋለን የሚመጣውንም ሕይወት ለዘለዓለሙ አሜን!"

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ጥቅምት 5 2013 ዓ ም
አዲሳባ

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን ስለ እኔ ዘንድ ጸልዩ! ሌሎች እንዲያነቡትም የሚከተሉት አድራሻዎች Like እና Share ያድርጉ
FB: https://www.facebook.com/officialHenokhaile/
Telegram: https://hottg.com/deaconhenokhaile
Instagram: https://www.instagram.com/p/CBnMF0nnhcQ/?igshid=549jvl607bv4
Youtube: https://www.youtube.com/channel/UCOaVsWC05aUjeqIEW3fWj7g
HTML Embed Code:
2024/05/15 01:17:07
Back to Top