TG Telegram Group Link
Channel: የጠቢባን እልፍኝ
Back to Bottom
#Block......un block


ቀን አትናፍቀኝም
ጭራሽ ትዝ አትለኝ

ስምህም ሲጠራ ድንቄም አልደነግጥ
ፎቶህንም ሳየዉ ልቤ አትልም ድልቅ።

ድንገት ትዝ ካልከኝ
ራሴን 'ረግማለሁ
ምን አጃጅሎኝ ነዉ ብዬ እገረማለሁ።

ያንተ ስም ሲጠራ
ብዙ መሠል ስሞች ይመጣል ከኔ ጋር
ሌላም አስባለሁ ከትዝታ ጋራ

የአፍቃሪዬን ብዛት..............

በቃ ረስቻለሁ ብዬ ስደሳሰት
Block🤜

ልክ ሲመሻሽ ደርሶ
ስምህ ይጨንቀኛል
ሳቅህ ይሰማኛል

እንደ ቀኑ አይደለ ፎቶህ ግርማ አለዉ
መፀፀት አይደለ ልቤ አምጪዉ ነዉ ሚለዉ

ምን አተሽ ነዉ ከሱ
እድል ነበር እሱ

እያለኝ እንደቀልድ
ቀን ያመንኩት ልቤ ካንተ ጋራ ሲነጉድ
እንዲሁ አነጋለሁ
ስላንተ አነባለሁ።


ከዛ..............
un block ሳደርግህ ራሴን አገኛለሁ።

ድሮስ ከጨለማ ምን ነበር ጉዳዬ
አንተ መቼም አታዉቅ ሆነ እድል ፈንታዬ

አንተና ጨለማዉ ግብራችሁ አንድ ነዉ
ብቸኝነት ፍርሀት መልሳችሁ ዝም ነዉ።

ደሞ ዛሬም ነጋ.................

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
ተፃፈ በትዝታ ወልዴ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@yetebibanelifign
@yetebibanelifign
Forwarded from የትዝታ ወልዴ ግጥሞች (TIZITA21)
dating #1

ፀጥ ያለ ቦታ ነዉ
እኔ ዝም ብያለሁ🤨 እሱ ግን ያወራል
ከፀጉሬ አንስቶ ጥፍሬን ይታዘባል
ፀጉርሽ በጣም ያምራል ፀጉርሽ ነዉ አይደለ ብሎ ይጠይቃል

ደሞ ይተወዉና
ሽፋሽፋትሽ እስቲ ብሎ ይነካካዋል
ሲገርም እያለ ደሞ ይተወዋል

ያወራ ያወራና
ጉንጮቼን ከንፈሬን ጥርሴን ያሞካሻል
ሲደንቅ እያለ ደሞም ይተወዋል

ዝም ብዬ አየዋለሁ🧐
እሱ ግን ያወራል
ያወራል ያወራል
ያወራ ይለፍፋል

ወረደ....ወረደ.... ከጥፍሬ ደረሰ
እዉነተኛ ነዋ ጥፍሮችሽ ያምራሉ
ሰዉ ያማልላሉ
ያወራል ያወራል
ዝም ብሎ ይለፍፋል

ሊገዛኝ ነዉ መሰል ልቤ አሁን ፈርቷል።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
Forwarded from የትዝታ ወልዴ ግጥሞች (TIZITA21)
ስንት ገባሽ?

አልዋሽክም ከአምናዉ ዋጋዬ ጨምሯል
ከምታዉቀኝ መፈለጌ እጅግ ንሯል

ያንተ እያለሁ ግዢ ተመን
አሁን ብታይ ከቶ አታምን

ስንት ገባሽ አደል ያልከኝ
ስንት ይዘሀል
ምን ሀብት አለህ

ለኔ ሚሆን ጥሬት ካለህ
ላወዳድርህ
ከኔ አለም ጋር ላፎካክርህ......

ግን አለሜ

ያሁኗ እኔ
ማንነቴ
ሂሳብ ተመኔ ስሌቴ
የገዢዉን አቅም ሳይሆን
አመጣጡን ያማከለ

እንደ በፊት
በእኔ አቅልሽ ልሙትልሽ ያልታለለ
ከዉጫዊዉ ዉሳጣዊ ማንነትን ያካለለ።

ስንት ገባሽ አደል ያልከኝ
አልዋሽክም ከአምናዉ ዋጋዬ ጨምሯል
ከምታዉቀኝ መፈለጌ እጅግ ንሯል።

ደሞ አለሜ
ገደምዳሜ ዘለምላሜ

እኔን ካጣሽ ይቆጭሻል
ስታስቢኝ መሽቶ ይነጋል
አለም የለሽ ከኔ ዉጪ
የትም ብትሄጅ ብትፈነጪ

ብለህ አለሜን እንደድሮ
ማጥበብ አትችልም ዘንድሮ

እኔም ግዛት አስፍቻለሁ
ድምበር አጥር አብጅቻለሁ

የኔን አለም ፈጥሬያለሁ
በርም ድልድይ ዘርግቻለሁ

ማንም ደርሶ ማያፈርሰዉ
በአሽዋ ያልታነፀዉ
ከአለት መሀል የፀና
በፈጣሪዉ በእርሱ ፍቃድም የቀና
አለም አለኝ
በድሮ ዋጋ 'ንዳተምነኝ🤏

ገበያዬ ከጥንቱ ማንነቱ እጅግ ረቋል
አሞሌዉን በአሞሌ ጨዉ ማቀያየሩንም ትቷል

መኪና ቤት ዝና ጥቅም የማይገዛዉ
ከአገዛዙ አመጣጡን ያማከለ ገበያ ነዉ

ስንት ገባሽ አደል ያልከኝ...........

...............
...............
...............
ስንት ይዘሀል?


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
Forwarded from የትዝታ ወልዴ ግጥሞች (TIZITA21)
ከሌላ እንዳትቆጥር

ይሀዉልህ ዉዴ
ትላንትና ማታ

እንባዬን አፍስሼ
አፈር ትቢያ ልሼ
ከእግርህ ወድቄ ማረኝ ተዉ ማለቴ
ታቦት እየጠራዉ መማል መገዘቴ

ከሌላ እንዳትቆጥር

ደግሞም ታቦታቱን ጠርቼ ጠርቼ
አንተም ዝም ብትል
የሞተች እናትህን መቃብር አዉጥቼ
በሷ ሞት እያልኩኝ ያኔ መለመኔን
አንተንም እያስማልኩ.......
ቅዱሱን መፅሐፍ በእጆችህ አስይዤ
አልተውሽም ስትል በደስታ ፈንጥዤ

ያኔ መጨፈሬን

ከሌላ እንዳትቆጥር

ከወትሮዉ በሌላ
ካልለመድከዉ ገላ
እራሴን ሰጥቼ ደባብሰኝ ማለቴን
ሳመኝ እቅፍ አርገኝ ብዬ መማፀኔን
ላለፈ ስህተቴ
ከእቅፍህ ገብቼ ንስሀ መግባቴን

ከሌላ እንዳትቆጥር

አንተን ከረሳሁኝ
ባንተ ከማገጥኩኝ
ሳት ብላኝ ነብሴ
ሌላዉን ከሻተች ሞት ይሁነኝ ዋሴ።

ስቅበዘበዝ ልሙት ልክ እንደ ይሁዳ
የሄድኩበት እግሬ ይቅር ምድረ በዳ።

ነፍሴንም አይማረዉ
እግዜሩም ይጣላኝ
እኔ አንተን ከረሳዉ
ያቀፍኩበት እጄን ለምጥ እከክ ይዉረሰዉ
ብዬ መገዘቴን
በራሴ ጨክኜ ርግማን ማዝነቤን

አደራ እንዳትቆጥረዉ
እባክህ በሌላ
ሰክሬ ነዉ እንጂ
ባሌ ትዝ ብሎኝ
ለደቂቃም እንኳን እንዲያዉ ለቅፅበቱ
አንተ የኔ እንድትሆን አልሻም በእዉነቱ።
..........................
..........................
..........................
..........................
አንተን እንደ ንፁህ ወንድሜ ነዉ የማይህ አላለችም😳

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
Forwarded from የትዝታ ወልዴ ግጥሞች (TIZITA21)
አሜን በይ አደራ

ያየሽ አይኑ ይጥፋ
እግርና እግሩን ያርግበት ወልካፋ።

ቡዳ እንደበላዉ ልጅ አይኑ ፈጦ ይቅር አንቺኑ ያየበት
አናቱ ቅል ይሁን አንቺን ያሰበበት
ልቡ ስራ ታቁም ካንቺ የከጀለበት።

ፍቅርሽ እስክመጣ
ፍቅር የተባለ ከወንድ መኖ ይዉጣ
ጠንጋራ ያድርገዉ አንቺን ሊያይ የመጣ።

በፈገግታ ማርኮ ቀልብሽን ለሻተ
ጥርሶቹን አግጥጦ ለተንከራተተ
መጋኛ አግኝቶልኝ ከንፈሩን ያጣመዉ
ጥርሶቹን አርግፎ በድዱ ያስቀረዉ።

እኔ ያንቺዉ መዉደድ ስቃይ እንዳይገባኝ
ቅናት እንዳይገባኝ
ፍርሀት እንዳይገባኝ
ችግር እንዳይገባኝ

የሀገሬዉ ተባዕት በርሀብ ይቀጣ
ሆዱን እያሰበ ወዳንቺ እንዳይመጣ።

የሚበላዉ ይጣ
የሚጠጣዉ ይጣ።
በቃላት ሊያጠምድሽ አንደበቱ ናፍቆ ስምሽን የጠራ
ያሰበዉም ቢሆን ከኔ ፍቅር ጋራ።

ሀረግ ሊደረድር ተፈጥሮ የሰራዉ
ጉሮሮ፣ትናጋ፣ምላስ ከከንፈሩ
ላንቃዉም ሳይቀሩ
የጨዉ ሀዉልት ሆነዉ እዛዉ ደርቀዉ ይቅሩ።

ብቻ ግን አደራ ይሄ ሁሉ ሲሆን
አንዱን አያሳይሽ እንዳይገባሽ ሀዘን
ሲከፋሽ አልወድም።
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
Forwarded from የትዝታ ወልዴ ግጥሞች (TIZITA21)
ጉድ
::::::::::::::::::::::::::::
ሠይጣን መነኮሰ
ገዳም ገባ አሉ ከእግዜር ተታረቀ
ነፍሱን አፀደቀ
ሱባኤ ለሀጥያቱ
ቀኖናዉን ያዘ ለአባ ፍትሀቱ
ሁዳዴን 40ቀን
ሳይታክት ቀን በቀን
እያደገደገ.........
ዳዊት ደጋገመ ሊፀድቅ ወስኖ
ሸይጣን ሰይጣኑ ወጥቶ_ከሰይጣን ተቃርኖ
::::::::::
::::::::::
ሠዉ ሆይ አደራህን እንዳታሳስተዉ
እሱም ብዙ ነበር ካንተ የተማረዉ።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
ለለተ ጥምቀቱ

አንተ ምታስበዉ
ከጉሊት ላይ ሎሚ ገዝቶ ለመወርወር
እኔ የማስበዉ በሰላም ወጥቼ በአሉን ለማክበር።

አንተን ያስጨነቀህ ሎሚ መወደዱ
እኔ እንቅልፍ የነሳኝ ፍቅር መሰደዱ

ያንተ እራስ ምታት እንደምን አግኝቼ የትኛዉ ጋር ልምታት
የኔ ትኩሳት ግን የሞቱት ህፃናት።

የወሬህ ዳርዳሩ መቋጫህ ነገሩ
እኔን ከእጅህ አግብተህ ማዉራት ለሀገሩ

የኔ ምኞት ሀሳብ ቃሌ ንግግሩ
በቃ ሰላም ሆኗል ሲባል ዳር ድንበሩ።

የእዉነት ገረምከኝ...........

እንዲያዉ አደራህን
።።።።።።።።።።።።
።።።።።።።።።።።።
እጅ እንዳታነሳ ሎሚ ለመወርወር
በቋት ለተያዘ ብሶታሙ ምዕመን
ሎሚ መጣል ማለት ቦምብ እንደመወርወር
አስለቃሽ ጭስ ጥሎ ህዝብ እንደ ማባረር።

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ
❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
@Tizita_wolde
ሳልፈቅድ እንዳትወስደኝ

ሞት ሞት ይሸተኛል መኖር ምንአባቱ
ደርሰሀል መሠለኝ ጠነባኝ ክርፋቱ
ከደጃፌ ቆሞ በር ይቆረቁራል
አገዳደል እንጂ አኗኗር የት ያዉቃል

ግባ እንዳልለዉ ወና ነዉ ሌማቴ
አትድረስ እንዳልል እንግዳ ለቤቴ

በባዶ ቤት መጥቶ ሊያበዛዉ ሀጥያቴን
በር ይቆረቁራል.........

እርቃን ነዉ ገላዬ
አልሸፈንኩት ነገር ሸለፈት ስጋዬን
አላበራዉ ነገር መቅረዝ ለጓዳዬ
ጨላልሟል ደማምኗል የቤት ገመናዬ።

ዘንድሮን እለፈኝ ግድ የለም አትምጣ
ከወና ቤቴ ዉስጥ ነፍሴን ይዘህ አትዉጣ።

ለከርሞ..............
ሸለፈት ስጋዬን በቅጠል ሸፍኜ
ለእንጀራ የሚሆን ሊጥ አቀጣጥኜ
የቆሸሸ ልብሴን በእንዶድ አፅድቼ
ለጨለመዉ ጓዳ ፋኖሴን አብርቼ
እጠብቅሀለሁ................

ግን

ልክ ስትመጣ ቤቴ ካልወገገ
መቅረዜ ካልበራ
ጠረኔ አዉዶ ዉጪ ካልተጣራ
እለፈኝ ግድ የለም
አምናም ያለፈችዉ በቸርነትህ እንጂ በብልጠት አይደለም

።።ብለህ ንገርልኝ
ስባሪ ልብ ከያዝክ እግረ መንገድህን ከበራፍ ጣልልኝ።

በትዝታ ወልዴ

JOIN👉 @Tizita_wolde
ንገሪኝ ካልከኝስ💔

ደረቅ፣ግትር፣ጨካኝ ልብ የለሽም አልከኝ
ድንጋይ መሆኔንም በሰዉ አስነገርከኝ
አዎ ነኝ ይግረምህ
እረግጠሀኝ ብትሄድ ምትህ እንዳይገባኝ
አንስተህ ብትጥለኝ ዉስጤን እንዳትጎዳኝ
በሚያማምር ቃላት ልቤን አረስርሰህ
ደርሰህ እንዳታደማኝ
በጥርስህ እየሳክ ልቤን እንዳትወጋኝ
አይዞሽ አይዞሽ ብለህ ሂጅ ጥፊ እንዳትለኝ
ወደድኩሽ እያልከኝ ፍቅሬን እንዳትቀማኝ
ድረሺልኝ ብለህ አልይሽ እንዳትል
በሳቅህ እኔም ስቄ
በደስታህ ቦርቄ
ሲከፋህ አልቅሼ
ስታዝን ሳይ ደሞ ማቅ አመድ ለብሼ
ስኖር እኖርና.................
ድንገት ብትቀየር
ሳቄ ጣዕሙን ያጣል
ሀዘኔ ያስቃል
ደስታዬ ያስለቅሳል
ለቅሶዬ የደስታ መገለጫ ይሆናል
እና በአጠቃላይ ትርጉሜ ይጠፋል
እናምልህ ስማኝ
እህ ብለህ አድምጠኝ
ይህ ዝርክርክ ልቤን በደምብ ስለማቀዉ
ለዛ ነዉ ደንድኜ በሩን የማልከፍተዉ
አንዳንድ ልጆች አሉ
አንኳክተዉ መሮጥን ጀግንነት ያስባሉ።

በትዝታ ወልዴ

JOIN👉 @Tizita_wolde
HTML Embed Code:
2024/04/27 22:56:33
Back to Top