TG Telegram Group Link
Channel: ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል
Back to Bottom
Audio
🍂 የበደል አስከፊነትና አይነቶቹ

🎙 በወንድም ሙሀመድ ሀሰን (ጁድ)

🕌 ደሴ ጨርጫሪት ሁዘይፋ መስጂድ

📆 ቅዳሜ ረመዷን 13/09/1442

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
▪️https://hottg.com/yeilmkazna
Audio
🍂 የነብዩ ውዴታና መገለጫዎቹ

ክፍል : 01

🎙 በወንድም ሙሀመድ ሀሰን (ጁድ)

🕌 ደሴ ጨርጫሪት ሁዘይፋ መስጂድ

📆 ማክሰኞ ረመዷን 16/09/1442

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
▪️https://hottg.com/yeilmkazna
Audio
🎙 የጁሙዓ ኹጥባ

🍂 የመጨረሻዎቹ 10ሩ ቀናት

👤 በወንድም ሙሀመድ ሀሰን (ጁድ)

🕌 ደሴ ጨርጫሪት ሁዘይፋ መስጂድ

📆 ጁሙዓ ረመዷን 18/09/1442

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
▪️https://hottg.com/yeilmkazna
🟣 አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ
⛔️ እባካችሁ ይችን እህታችንን እንተባበራት ⛔️ እንዲህ ትላለች
_____________________
_____________________
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ የአኸራ ወንድም እህቶቼ ወንድሜ ሱቅ እየሰራ ከስሮበት የሰው ዕዳ ገባበት በዕቁብ እየሰራ ነበር እቁብተኞቹ በቼክ መልክ ነበር የሰጡት ነገር ግን እቁቡን ሳይጠናቀቅ ሱቁ ከሰረ በ200,000 ብር ቼክ ነበር ያስመቱበት ብሩ ሳይከፈል የቼኩ ቀን ደርሶ አምና ኮሮና እንደገባ ጀምሮ 5ወር አሰሩት ከዛ በኃላ በ10,000 ብር ዋስ ተፈታ በቀጠሮ እየተመላለሰ ቢከታተለውም ፈይሉ ስላልተዘጋ አሁን በረመዳን ረቡዕ(13/08/2013) ዳግም አሰሩት የዋስ ብር እንኳን ስለሌለው ነው 5 ወር ታስሮ በ10,000 ብር የወጣው መቼም የዱንያ ፈተናው ብዙ ነው የሰው ልጅ አተርፋለሁ ብሎ እንጂ እከስራለሁ ብሎ ስራ ዓለም አይቀላቀልም በፈተና ከወደቅን በኃላ በአላህ ውሳኔ ማመንና ተስፋ ያለመቁረጥ ነው ፍ/ቤቱ እርቅ አውርድ ብሎት ነበር እቁብተኞቹ በገንዘብ እንጂ አይሆንም አሉ ቤተሰብ ይህ መሸፈን አይችልም ክፍለሀገር ናቸው እኔ ታናሽ እህቱ ነኝ ተማሪ ነኝ ብዙም ሰው አላቅም ጉዳዩ ማወያየው ብቻዬ ከምጨናነቅ ችግሬን ላካፍላችሁ ብዬ ነው ምንም አማራጭ ስለሌለኝ ነው የእርዳታ እጃችሁ ልዘረጉልኝ በአላህ ስም ምጠይቃችሁ በናንተም በኩል የምችሉትን አነሰ በዛ ሳትሉ ዘካተል ማልን መስጠት ሚችልም ሰው ካለ እንድጠይቁልኝ በንዲህ ዓይነት ጉዳይ ሚሰሩ ተቛማት እንድታስተባብሩልኝ በአላህ ስም እጠይቃለሁ አንድ ሰው ወንድሙ በመርዳት ላይ እስካለ ድረስ አላህ እሱም በመርዳት ላይ ነኝ ብሎዋልና አላህ ዱንያ አኸራችሁ ያሳካላችሁ መጨረሻችሁ ያማረ ያርገው ከንደዚህ ዓይነት ፈተና አላህ ይጠብቃችሁ ዘር ማዘራችሁ ፍ/ቤት አይርገጥ አስፈላጊውን መረጃ ለመላክም ለማቅረብም ዝግጁ ነኝ ብዙ ሚያሳስት ሰው ስለማይጠፋ!!!
___________________
📮 ነገ በኛ ላይ ላለመድረሱ ዋስትና የለንም ፣ ወንድምና እህቶች እንተባበራት ፣ በጣም ጭንቀት ውስዘት ገብታለች ፣ የጉዳዪን እውነትነት ለመረዳት እንድትችሉ ማስረጃዎችን አያይዣለሁ
🔴 ወሏሂ በጣም ነው የምታሳዝነው ፣ ወንድሟ እንዲህ ግራ ገብቶት እሷም የሰው ፊት እያየች እየተንከራተተች ነው🔴

📮 በወንድሟ ሳቢያ በጭንቀት ውስጥ ያለችውን እህታችንን #ለመርዳት ከፈለግን ይሄው በዚህ አካውንት የቻልነውን እንተባበራቸው 👇

📮 የኢትዪጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር

🟣 1000 31 96 10 123 🟣
ፉርቃን ኦንላይን ቁርኣን ማዕከል pinned «🟣 አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ⛔️ እባካችሁ ይችን እህታችንን እንተባበራት ⛔️ እንዲህ ትላለች _____________________ _____________________ አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ የአኸራ ወንድም እህቶቼ ወንድሜ ሱቅ እየሰራ ከስሮበት የሰው ዕዳ ገባበት በዕቁብ እየሰራ ነበር እቁብተኞቹ በቼክ መልክ ነበር የሰጡት ነገር ግን እቁቡን ሳይጠናቀቅ ሱቁ ከሰረ በ200,000…»
አሰላሙዓለይኩም ወራህመቱላሂ ወበረካቱ ውድ የአኸራ ወንድም እህቶች ወንድሜ ሱቅ እየሰራ ከስሮበት የሰው እዳ ገባበት እቁብ እየጣለ እቃለማስገባት እቁብተኞች አስቀድመው ሰጥተውት ነበር በቼክ መልክ ነበር አስመትተው አስቀመጡት እቁቡ ሳያጠናቅቅ ነበር የከሰረው በ200,000 ብር ቼክ ነበር የተከሰሰው አምና በኮሮና 5ወር አስረውት ከዛ 10 ,000ብር ዋስ ወጥቶ ፈይሉ ስላልተዘጋ በቀጠሮ እየተመላለሰም መክፈል ባለመቻሉ ዳግም በዚህ ረመዳን 13/08/2013 አሰሩት የወስ ገንዘብ ስለሌለው ነው 5ወር ታስሮ በ10,000 ብር የወጣው መቼም ዱንያ ፈተናዋ ብዙ ነው የሰው ልጅ አተርፋለሁ ብሎ እንጂ እከስራለሁ ብሎ ስራ አለም አይቀላቀልም በፈተን ከወደቅን በኃላ በአላህ ውሳኔ ማመንና ተስፋ ያለመቁረጥ ነው መንድሜ እንኳን እዳ ሊከፍል ለራሱ እንኳን ስራ የለውም ፍ/ቤቱ እርቅ ወረቀት አስገባና ጉዳይ ውጪ ሆነህ ተከታተል አለው ነገርግን ያሳሰረው ሰውዮ የርቅ ወረቀቱ በደረቅ አልስማማም አለ ቤተሰብ ይህ መሸፈን አይችልም አቅም የለንም ክፍለሀገር ናቸው እኔ ታናሽ እህቱ ነኝ ተማሪ ነኝ ጉዳዩ ምከታተለው አንዴ ክላስ አንዴ ፍ/ቤት እየተመላለስኩ ነው ሰው የለኝም ተስፋ ባለመቁረጥ ምችለውን መስዋዓት ልክፈል ብዬ ነው ብቻዬ ከምጨነቅ ሀሳቤን ማጋራችሁ ወላሂ አላህ ምስክሬ ነው ምንም አማራጭ ስለሌለኝ ነው የእርዳታ እጃችሁ ልዘረጉልኝ በአላህ ስም ምጠይቃችሁ በናንተም በኩል የምችሉትን አነሰ በዛ ሳትሉ ዘካተል ማል ሚሰጥም ሰው ካለ እንድጠይቁልኝ በንዲህ ዓይነት ጉዳይ ሚሰሩ ተቛማት እንድታስተባብሩልኝ በአላህ ስም እጠይቃለሁ አንድ ሰው ወንድሙ በመርዳት ላይ እስካለ ድረስ አላህ እሱ በመርዳት ላይ ነኝ ብሎናል አላህ ዱንያ አኸራቹ ያሳካላችሁ መጨረሻቹ ያማረ ያርገው ከንዲህ አይነት ፈተና አላህ ይጠብቃችሁ ዘር ማዘራችሁ ፍ/ቤት አይርገጥ አሁን መሸፈን የተፈለገው የቼኩ ሳይሆን በአስቸኳይ የእርቁ ነው ቢያንስ 30,000 ብር ነገር ይፈልጋል ያሳሰረው ሰውዬ ፍ/ቤቱ እስከ 28/08/2013 የእርቅ ወረቀት ካላስገባሽ የመጨረሻ የውሳኔ ቀን 29/08/2013 ነው ከፈረደበት ቂሊንጦ ነው ሚያወርደው አንድ አቃቢ ህግ አናግሬው 2 ዓመት ከ 6ወር በላይ ያሳስረዋል ይህ የቼኩ ቅጣት ነው እንጂ ከወጣ በኃላ ሰርቶ ይከፍላል ለሱ ሚሻለው እርቁ ነው ውጪ ቢከታተለው የተሻለነው አለኝ እኔ የጨነቀኝ በእጄ ምንም ነገር ሳይኖር ቀጠሮ እንዳይደርስ ፈራሁ የቀናቶቹ ጥበት አሳሰበኝ ለማንበብ እንዳሰለቹ ያለውን ተጨባጭ ግልፅ ከማረግ አንፃር ነው ያብራራሁላችሁ ለበለጠ መረጃ ለማግኘት ይህን ንኩት @YufA8550
Audio
🍂 የነብዩ ውዴታና መገለጫዎቹ

ክፍል : 02

🎙 በወንድም ሙሀመድ ሀሰን (ጁድ)

🕌 ደሴ ጨርጫሪት ሁዘይፋ መስጂድ

📆 ማክሰኞ ረመዷን 22/09/1442

◈•┈┈┈┈•✿❁✿•┈┈┈┈•◈
▪️https://hottg.com/yeilmkazna
አንድነት በሁለት ጫፎች መሃል
Ibnu Munewor
“አንድነት በሁለት ጫፎች መሃል”

በቡታጅራ ከተማ ከቀረበ ትምህርት የተወሰደ
🔷 ዘካተል ፊጥር ምንድን ነው🔹

🕰 ፈትዋ ቁጥር : 268

📮 #ጥያቄ

⭕️ ዘካተል ፊጥር ምንድን ነው? ለምንድን ነው የተደነገገው? ቢብራራልን

#መልስ

☑️ ዘካተል ፊጥር በሙስሊሞች ላይ ግዴታ ከሆኑ ዘካዎች መካከል አንዱ ሲሆን ከዒደልፊጥር ሶላት #በፊት ወይም ረመዷን ከመጠናቀቁ በፊት የሚሰጥ ነው። ይህ ዘካ አቅም ባለው ሁሉ ላይ #ግዴታ ነው። ዘካተል ፊጥርም ሶደቀተል ፊጥርም ተብሎ ይጠራል። ስያሜው ወደ ፊጥራ የተጠጋበትም ምክንያት ግዴታ የተደረገበት ምክንያት ስለሆነ ነው። ማለትም ዘካተል ፊጥር #ከረመዳን ወር ፆም መጠናቀቅ ጋር በተያያዘ ግዴታ የሚሆን የዘካ አይነት ነው፡፡

☑️ ከሌሎች ዘካዎች የሚለየውም በገንዘብ ላይ ሳይሆን #በግለሰብ ላይ ግዴታ የሚሆን መሆኑ ነው። ማለትም ይህ ዘካ ግዴታ የተደረገው የፆመኞችን ነፍስ #ለማጥራት እንጅ ልክ እንደ ትልቁ ዘካ ገንዘብን ለማጥራት አይደለም።

📚 ኢብኑ ዑመር ረዲየሏሁ አንሁ እንዲህ ይላል: " ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በሳቸው ላይ ይሁን) ከተምር ወይም ከገብስ አንድ ‹‹ሷዕ›› (ሷዕ የመስፈሪያ አይነት ሲሆን በዘመናዊ መለኪያ አንድ‹‹ሷዕ›› 2.04-2.5 ኪ.ግ ይመዝናል፡፡) በእያንዳንዱ ሙስሊም፤ ባሪያ፣ ጨዋ (ባሪያ ያልሆነ)፣ሴት፣ ህፃን፣ አዋቂ ላይ ግዴታ አድርገዋል፡፡ እንዲሁም ሰዎች ወደ (ዒድ) ሰላት ከመውጣታቸው በፊት ለሚገባቸው ሰዎች እንዲደርስ #አዘዋል፡፡›› (ቡኻሪና [1503] ሙስሊም [984] ዘግበውታል)

☑️ የተደነገገበት #ጥበብ ድሆች በባዕሉ (ዒድ) እለት ሰዎችን ከመለመን #እንዲድኑና የእለቱ ደስታ ተካፋይ እንዲሆኑ ማድረግ እንዲሁም በፆም ወቅት ተከስተው ላለፉ አንዳንድ ጉድለቶች (ግድፈቶች) #ማሟያ እንዲሆን ነው፡፡ ይህን አስመልክቶ ዐብደላህ ኢብን አባስ እንዲህ ይላሉ፡፡

📚 ‹‹የአላህ መልዕክተኛ (የአላህ ሰላትና ሰላም በእርሳቸው ላይ ይሁን) ዘካተል ፊጥርን ለፆመኛ ለ ‘ለግዉ’ (ጥቅም ለሌላቸው ውድቅ ንግግሮችና ተግባሮች) እና ለ ‘ራፈስ’ (ፆታዊ ስሜትን ቀስቃሽ ለሆኑ ንግግሮች) #ማፅጃ፤ ለምስኪኖች (ድሆች) #መብል ሲሆን በግዴታ መልኩ ደንግገውታል፡፡ ስለዚህም ከኢድ ሰላት #በፊት (ዘካውን በመስጠት ግዴታውን የተወጣ) ተቀባይነት ያለው ዘካን ሰጥቷል፤ ከኢድ ሰላት #በኋላ ዘካውን የሰጠ ከሌላ ግዴታ ያልሆነ ሰደቃ አንዱ እንደሆነ ይታሰብለታል፡፡›› (አቡዳውድ [1609] እና ኢብኑ ማጃህ [1827] ዘግበውታል)

•┈┈•◈◉❒❒◉◈•┈┈•

🗂 #ምንጭ

📘 መጅሙዑል ፈታዊ ለኢብኑ ባዝ ፣ 14/32 ፣ 14/197 ፣ 📕መጅሙዑል ፈታዊ ለኢብኑ ዑሰይሚን ፣ 18/258

◈•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•┈┈·•◈
https://hottg.com/yeilmkazna
Forwarded from አቡ ሙዓዝ (ሐሰን ኢድሪስ) (አቡ ሙዓዝ ሀሰን)
#በሁለቶቹ በዓሎች መካከል ያላቸው ልዩነት የሚከተሉት ናቸው።


1/
#በዒደል_ፊጥር ቀን ማረድ ግዴታም ሱናም ተወዳጅም አይደለም‼️

#በዒደል_አድሐ ቀን ግን ለቻለ ሰው ማረድ ግዴታ ነው

2/
#በዒደል_ፊጥር ቀን ተክቢራ ሚጀመረው የፆሙ ጨረቃ ሲያበቃ ማታ ወይም የዒዱ ቀን ጧት ነው።

#የዒደል_አድሐ ቀን ግን ጨረቃው ከታዬ ጀምሮ እስከ_14 ቀን አካባቢ ተክቢራ ይደረጋል።

3/
#የዒደል_ፊጥር ቀን በእያንዳንዱ ሰው ላይ አራት እፍኝ ጥሬ እህል ለድሃዎች ከሶላት በፊት መስጠት ግዴታ ነው።

#የዒድል_አድሐ ቀን ግን ይህ ተግባር ግዴታም ተወዳጅም አይደለም።

4/
#የዒደል_ፊጥር ቀን ፈርድ(ግዴታ)ሶላት ከተሰገደ ቡሃላ ተክቢራ አይደረግም

#የዒደል_አድሐ ቀን ግን ከግዴታ ሶላት ከተሰገደ ቡሃላ ተክቢራ ይደረጋል ያውም ለቀናቶች ያክል

5/
#የዒደልል_ፊጥር ቀን ጧት ላይ ወደ መስገጃው ሜዳ ሲወጣ ቴምር በልቶ መውጣት ሱና ነው

#የዒደል_ አድሐ ቀን ግን እርድ ሚያርድ ሰው ከሆነ ሳይበላ እንድወጣ ነው የታዘዘው።

6/
#የዒደል_አድሐ ላይ ገና ጨረቃው ሲታይ ጀምሮ እርድ አርዳለሁ ብሎ የወሰነ ሰው ከፀጉሩ ከጥፍሩ ምንም ሊነካካ(ሊቆርጥ)አይፈቀድም

#የዒደል_ፊጥርን አስመልክቶ ግን ምንም ነገር የለበትም ማለት እንደፈለገ ጥፍሩንም ብብቻውን ማፅዳት ይችላል።

@abumuazhusenedris
@abumuazhusenedris
በሁሉም የሳውዲ አካባቢዎች ጨረቃ አልታየችም። በመሆኑም ነገ እሮብ የረመዳን ማሟያ 30ኛ ቀን ሲሆን ኢድ አልፈጥር ሀሙስ እንደሆነ ተገልፇል።

@ዛዱል መዓድ
السلام عليكم ورحمة الله وبركاته

ውድ እና የተከበራችሁ ወንድሞቼ እና እህቶቼ
🌹🌹🌹
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
🌹🌹🌹
عيدكم مبارك! تقبلﷲ منا ومنكم صالح الأعمال
🌹🌹🌹
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁
🌹🌹🌹
እንኳን ለ 1442 የ ዒድ አል-ፈጥር በኣል በሰላም አደረሳችሁ! ዒዳችሁ የተባረከ ይሁን!
አላህ ከኛም ከናንተም መልካም ስራችንን ይቀበለን!
🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🎁🌹🌹🌹🥀

ወንድማችሁ፡ ሙሀመድ ሀሰን (ጁድ)
الله أكبر الله أكبر الله أكبر،
لا إله الا الله والله أكبر الله ولله الحمد.
ኢድ ሙባረክ
ተቀበለላሁ ሚና ወሚንኩም ሷሊሀል አእማል።
تقبل الله منا ومنكم صالح الأعمال
ወንደሞቼ እና እህቶቼ ፣ አላህ መልካም ስራዎቻቸንን ይቀበለን !
ወንድማችሁ ሙሀመድ ጁድ
የሸዋልን ፆም አደራ ‼️‼️⁉️

የአሏህ መልእክተኛ ﷺ እንዲህ ብለዋል
«ረመዷንን ፆሞ ከሸዋል ስድስት ቀናትን አስከትሎ የፆመ አመቱን እንደፆመ ይቆጠርለታል።»


📜 ሰሒህ አትርሚዚ
ፍልስጤም - የደም ነጋዴዎች ካርድ!
~~~~~~~~~~
የፍልስጤም ወገኖቻችን ሰቆቃ ከወትሮው በጨመረ ቁጥር ይህንን አስታኮ ዑለማዎች ላይ መዝመት የተለመደ ክስተት ሆኗል። ሙስሊሞች ስሜታቸው የተነካበተን ጊዜ ጠብቀው ዑለማዎችን እንዲንቁ በፍርሃትና በሸፍጠኘነት እየወነጀሉ የጥላቻ መርዝ የሚግቱ opportunisቶች አሉ! የኢኽዋን ቫይረስ ተሸካሚዎች አብይ መታወቂያ ይሄ ነው። የሰለፊያ ዑለማዎች ናቸው በፍርሃትና ጂሃድን በመቃወም የሚወነጀሉት? እነ አልባኒ፣ ኢብኑ ባዝ፣ ዑሠይሚን፣... አይደሉ እንዴ ለአፍጋኒስታን ጦርነት ሲቀሰቅሱ የነበሩት? እነ ረቢዕ የአፍጋኒስታን ጂሃድ ላይ አልተሳተፉም ወይ?! ህይወታቸው በነዚህ የጥመት አንጃዎች አደጋ እየተደቀነበት እንኳ ሐቅን በማድረስ ላይ አልተዋደቁምን? እነ ኢሕሳን ኢለሂ ዞሂር በተጠመደ ቦምብ አልተገደሉም? እነ ጀሚሉ ረሕማን ኩነር አፍጋኒስታን ውስጥ አልተገደሉም? እነ ሙቅቢል መስጂድ ውስጥ ከተጠመደ ቦምብ ለትንሽ አልተረፉም? ለህይወታቸው ቢሳሱ ነው’ንዴ ሌሎች የተሸበቡበትን ርእስ ከፍ በማድረግ ደም የጠማቸው የጥፋት አንጃዎችን የሚጋፈጡት? የኢኽዋን ቆሻሾች እንደሚወነጅሏቸው ፈሪዎች ስለሆኑ ነው በዚህ ደረጃ ህይወታቸው አደጋ እየተደቀነበት እንኳ ወደኋላ የማይሉት? እነዚህ ሳይሞቅ ፈላዎች ጀግና ከሆኑ ለምን ወደ ፍልስጤም አይዘምቱም? ፍልስጤም ብትርቃቸው እዚሁ አፍሪካ ውስጥ ሙስሊሞች የሚበደሉባቸው በርካታ ሃገራት አሉ’ኮ። ፌስቡክ ላይ ከሚፎክሩ ለምን ነፍጥ አንግበው ጫካ አይገቡም? ሁሌ ከዑለማእ ውስጥ ሰለፊዮቹ ላይ፣ ከሃገራት ውስጥ ሳዑዲ ላይ ነው የሚዘምቱት።
ለእስራኤል የደህንነትና የስለላ መረጃዎችን የሚያቀብለው የኩርጂክ የራዳር ማእከል ቱርክ ውስጥ ነው የሚገኘው። ከእስራኤል ከፍተኛ የንግድ አጋሮች ውስጥ አንዷ ቱርክ ነች። ከሙስሊሙ አለም በቱርክ ደረጃ ለሷ ወዳጅ የሆነ የለም። በቅርቡ ቃጠሎ ሲገጥማት የእሳት ማጥፊያ አውሮፕላኖችን የላከች ቱርክ ነች። “የእስራኤል አባት” ተብሎ የሚጠራው ቴዎዶር ሄርዝል ቀብር ላይ የአበባ ጉንጉን ያስቀመጠው ኤርዶጋን ነው። በተለያዩ ጊዜያት የጋራ የጦር ልምምድ ሲያደርጉ እንደነበር የሚታወቅ ነበር። በዚህ ቀውጢ ጊዜ ሳይቀር በጎን ባዶ የቃላት ኳኳታ እያሰሙ ሲያደነዝዙ፣ በሌላ በኩል የንግድ ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ ነው። ይህ ሁሉ ከመሆኑ ጋር ኢኽዋኖችና የነሱን ተውሳክ የተሸከሙ አካላት ነጋ ጠባ “ሳዑዲ፣ ሳዑዲ” እያሉ ማላዘን ነው የሚቀናቸው። ኢላማቸው መሪዎቹ አይደሉም። ወደ ዑለማዎቹ ለመሻገር ነው የነሱን ጉዳይ የሚያነሱት።
እስኪ አሁን “ጂሃድ በደመ–ነፍስ የሚካሄድ ሳይሆን ዝግጅት ይፈልጋል” የሚል ምክር ምን እንከን ይወጣለታል? ሃሳቡን አይቀበሉ! ምናል በቅንነት ተመልክተው ለሌሎች የሚሰጡትን ‘ዑዝር’ ቢሰጧቸው? እንዴትስ እዝነት መቆርቆራቸው በክፋትና በፍርሃት ይተረጎማል? የቢድዐ ልክፍት ያሳበዳቸው ወፈፌዎች ካልሆኑ በስተቀር ይሄ ጤነኛ አእምሮ ላለው የሚሰወር አይደለም። ቤት ውስጥ በሚዘጋጅ የጠርሙስ ቦምብ ነው ኒኩሌር ከታጠቀ ኃይል ጋር የምትዋጋው? በወፍ ማደኛ ወስፈንጠር ነው ከታንክ ጋር የምትፋለመው? በህልም ነው በውን ክላስተር ቦምብ የሚያዘንቡ ጄቶች በወንጭፍ የሚወርዱት? ለመሆኑ ለምንድን ነበር ሙስሊሞች መካ ላይ እያሉ በጂሃድ ያልታዘዙት? ደካማ ስለነበሩ አይደለምን? መዲና ውስጥ አቅማቸው ሲጠነክር’ኮ ነቢዩን ﷺ የተሳደበ አካል እርምጃ ተወስዶበታል። መካ ሳሉስ? ከስድብ በላይ ብዙ አልደረሰባቸውም? የገማ እንግዴ ልጅ አልተጣለባቸውም? ለምን እርምጃ አልወሰዱም? ምክንያት የለውም’ንዴ? ሶሐቦች ያ ሁሉ ሲደርስባቸው፣ እነ ሱመያ እነ ያሲር ሲገደሉ፣ ሌሎች አገር ጥለው እንዲሰደዱ ያደረጋቸው ግፍ ሲያስተናግዱ የፈለገ ይሁን ብለው አሳቻ ቦታ እየጠበቁ ጥቃት ማድረስ አቅቷቸው አልነበረም’ኮ! ቢላል ክፉኛ ሲያንገላታው የነበረውን ኡመያን ለመግደል ከአመታት በኋላ የተካሄደውን የበድር ዘመቻ ሳይጠብቅ ገና ቁስሉ ሳይደርቅ መካ ውስጥ መግደል አቅቶት’ኮ አልነበረም። ሸሪዐው የጂሃድን ትእዛዝ ያዘገየው ያለ ምክንያት ነው’ንዴ? አቅም እንዲያጎለብቱ፣ ዝግጅት እንዲያደርጉ እንጂ! የላቀው አላህ ምንድነው ያለው?
وَأَعِدُّواْ لَهُم مَّا ٱسۡتَطَعۡتُم مِّن قُوَّةٖ وَمِن رِّبَاطِ ٱلۡخَيۡلِ تُرۡهِبُونَ بِهِۦ عَدُوَّ ٱللَّهِ وَعَدُوَّكُمۡ
“ለእነሱም ከማንኛውም ኃይል (መሳሪያ) እና ከታጀቡ ፈረሶችም የቻላችሁትን ሁሉ በእርሱ የአላህን ጠላትና ጠላታችሁን የምታሸብሩበትን አዘጋጁላቸው።" [አልአንፋል፡ 60]
ሶሐቦቹ ይህንን መለኮታዊ ትእዛዝ ተከትለው ጠላትን የሚገዳደር ዝግጅት አድርገዋል። ዛሬ ወደ ጦር ሜዳ የምትጓዘው በፈረስ፣ የምትወረውረውም ቀስት አይደለም። ጠላት አእላፍ ኪሎ ሜትሮችን ርቆ አንተን ማደባየት ይችላል። ሙስሊሙ የትኛው ዝግጅት ነው ያለው? ምናልባት “የሰለጠኑ ፈረሶችን አዘጋጅተናል” ይሉ ይሆን? አይሉም አይባልም እነዚህ ማስተዋል የተሳናቸው ጉዶች? በዓለም ላይ እጅግ አውዳሚ የሆኑ ሃይድሮጂን ቦምቦች፣ አህጉር አቋራጭ ባሊስቲክ ሚሳኤሎች፣ ግዙፍ ባህር ሰርጓጅ መርከቦች፣ ጅምላ ጭራሽ ባዮሎጂካል መሳሪያዎች፣ ከራዳር ቁጥጥር ውጭ የሆኑ የተራቀቁ የጦር አውሮፕላኖች፣ ወዘተ የታጠቁት ሙስሊም ሃገራት አይደሉም። ወደ 16 ሺህ ከሚገመተው የዓለም ኒኩሌር 90 ከመቶ በላይ በአሜሪካና በራሺያ እጅ ነው ያለው። በሁለተኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በጃፓን ሂሮሽማና ናጋሳኪ ከተሞች ላይ 2 መቶ ሺህ አካባቢ ህዝብ ያለቀው በሁለት ኒኩሌር ብቻ ነው። ይህን ያክል ርቀዋል። የዛሬ ሙስሊም ሃገራት የ1945ቷን ጃፓን አያክሉም። ከመሆኑም ጋር ሰቅጣጭ በሆነ መልኩ ተንኮታኩታ ነበር እጅ የሰጠችው። ጋዳፊን በቀናት ውስጥ ያሽመደመደው የፈረንሳይ አየር ኃይል እንጂ ተቃዋሚዎቹማ እዚህ ግባ የሚባል አቅም አልነበራቸውም። በርካቶች ዘንድ ተጋኖ ተስሎ የነበረው የሳዳም ጦር እንደ ቅቤ የቀለጠው ያለ ምክንያት አይደለም!! “የዐረብ ሃገራት ናቸው ጉድ የሰሩት” እያሉ ዋናውን ምስል መዘንጋት እራስን ማታለል ነው? ወደድንም ጠላንም በመሃላችን ያለው ርቀት ከምንገምተው በላይ እጅግ የሰፋ ነው። 
እጅግ በርካታ “ሙፈኪሮች” ያለንበትን ተጨባጭ በውል አልተረዱም። ምነው ችግሩ በዚህ በቅቶ መከራችን በቀለለ?! በዚህ ሰመመናቸው ውስጥ ሆነው “ፊቅሁል ዋቂዕ አልገባቸውም” እያሉ ዑለማዎች ላይ መዝመታቸው ባሰ እንጂ። የነሱ የጥመት አውራዎች ሲነኩ ግን “ዑለማእ ተሰደበ” እያሉ አገር ያቃጥላሉ። ዑለማዎቻችንን ተውልን። ክፍተት ቢኖራቸው እንኳ እንደ ቀርዷዊ ካሉ የጥፋት ቁንጮዎች ጋር የሚነፃፀሩ አይደሉም። በምን ስሌት ነው እነዚያ እየታለፉ በነዚህ ላይ ሌት ከቀን የሚዘመተው?!
እንዲህ አይነቱ ኸዋሪጅ ጋር እየዋለ፣ የኸዋሪጅ ፊክራ እየጠጣ፣ ኸዋሪጅኛ የሚያስነጥስ የጥጃ ቀንዳም ነገሮችን በውል መመዘን፣ ግራ ቀኝ መመልከት የሚባል አያውቅም። ሙስሊሙ ዓለም ከአሜሪካም፣ ከራሺያም፣ ከፈረንሳይም፣ ከእንግሊዝም፣ ከቻይናም፣ ከህንድም፣ ከእስራኤልም ጋር እንዲዋጋ ነው የሚሹት። ተጨባጩ ግን እንኳን ከነዚህ ሁሉ ቀርቶ አንዱንም በሚቋቋምበት ቁመና ላይ አለመሆኑ ነው። ቱርክ ጦሯን ድንበር ተሻግራ ሶሪያ ውስጥ ብታስገባም "ለሃገሬ ስጋት ናቸው" የምትላቸውን የኩርድ ታጣቂዎች ከማጥቃት ባለፈ በሻረል አሰድን ለመንካት የማትደፍረው ወዳው አይደለም፤ ራሺያን ፈርታ እንጂ። ቻይና “የግዛቴ አካል ናት” የምትላትን
ታይዋንን ለመጠቅለል ከሰባ አምታት በላይ አድፍጣ የምታደባው ለታይዋን የሚሆን አቅም አጥታ አይደለም። ከታይዋን ጎን ከቆምችዋ አሜሪካ በኩል የሚመጣባትን ጣጣ ሽሽት እንጂ። ሙስሊሙ ዓለም አቅሙ ከቻይና በጣም ያነሰ ነው። ቻይና ለዚህ አላማ በሁሉም ዘርፍ አቅሟን ለማጎልበት ሌት ከቀን እየተጋች ነው። እኛጋ ደግሞ መካሪ ዑለማዎቹን እያብጠለጠለ፣ ከንቱ ቀረርቶ እያሰማ ደካማ ሃገራቱን ከጠላት ቀድሞ ያፈርሳል፤ እጁን በእጁ ይቆርጣል። ይህንን የተሳከረ አካሄዱንም ጀብድ አደርጎ ይኮፈስበታል።
እንደሚታወቀው የሙስሊም ዓለም መሳሪያ ሸማች እንጂ አምራች አይደለም። በገንዘቡ ለሚገዛውም ብዙ ቅድመ ሁኔታ ይቀመጥበታል። እንዲያውም ብዙዎቹ መሳሪያ መተኮስ፣ ሰራዊት ማዝመት ሳያስፈልግ ጠላት እነዚህን እንጭጮች በመጠቀም ሰላማቸውን ያናጋቸው ናቸው። እነዚህ ወፈፌዎች ግን ጉዳዩን ከሴትና ህፃናት መሃል አድፍጦ የአጭር ርቀት ሮኬቶችን በማስወንጨፍ የሚሞከር አድርገው ያስባሉ። በአጥፍቶ መጥፋትና በትንንሽ ሮኬቶች/ድሮኖች ጥቃት ጊዜያዊ ቡረቃ እንጂ ዘላቂ ድል አይመጣም። ይሄ ቅዠት ነው። ጠላትማ ምን ያድርግ? እነዚህ አሉ እንጂ ጠላት ወደ ሙስሊም ሃገራት እንዲገባ ተልእኮ ፈፃሚ የሆኑ ወልጋዶች!!
“ምሳርማ ምን ያርግ * የብረቶች ልጅ
ያ የኛ ወልጋዳ * አስጨረሰን እንጂ!!”
ዑለማዎች “ጂሃድ የኢማንም፣ የትጥቅም፣ የሰው ሃይልም ዝግጅት ይፈልጋል” ማለታቸውን በመቃረን “እነ ሶላሑዲን,… አሽዐሪዮች ነበሩ” ይላሉ። የኢማን ዝግጅት አያስፈልግም ለማለት ነው እንግዲህ ይሄ የሚቀርበው? “ተመጣጣኝ ወይም ተቀራራቢ አቅም መኖር ሸርጥ አይደለም። ሶሐቦቹም በቁጥር ትንሽ ሆነው ነው የተዋጉት” ይላሉ፣ እነዚህ የሚዲያ ላይ ነብሮች። በመጀመሪያ የዑለማዎቹን ንግግር ለትችት በሚመቻቸው መልኩ ነው አዛንፈው የሚያቀርቡት። ደግሞ’ኮ አብዛኞቹ ከሶሻል ሚዲያ ቀረርቶ ያለፈ ሙከራም የላቸውም። በተለይ ደግሞ የኛዎቹ። እስኪ ከነዚህ በያመቱ የፍልስጤምን ጉዳይ ለቡድናዊ ፕሮፓጋንዳ ከሚጠቀሙ አካላት ውስጥ ወደ እስራኤል የሚዘምት ጥቀሱ? እዚያው ፍልስጤም ውስጥ ከሚንደፋደፉ ደካማ ቡድኖች ውጭ እራሳቸውን ወደ ሰለፊያ የሚያስጠጉ ተውሳኮችን ጨምሮ፣ አይሲስ፣ አልቃዒዳ፣ ኢኽዋን፣ ቦኮ ሀራም፣ ... በፍልስጤም ጉዳይ ይነግዳሉ እንጂ እስራኤልን አይዋጉም። 
ደግሞስ የኢማን፣ እንዲሁም ከትጥቅና ከሰው ኃይል ደግሞ ምክንያታዊ የሆነ ዝግጅት ያስፈልጋል ማለት እንዴት ያስወቅሳል?! እና ጠላት ባካፋና በዶማ ነው የሚሸነፈው? ጠላት ባመረተው መሳሪያ እየተታኮስክ መሃል ላይ “አንዴ አቁሙ! ጥይት ጨርሻለሁ” ልትል ነው? ጂሃድን የህፃናት ጨዋታ አስመስሉት’ኮ! ፍልስጤሞችን ውሰዱ! ለፍልስጤማዊያን ተፈናቃዮች ከፍተኛውን እርዳታ የሚያቀርቡት እነማን ናቸው? አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት! ኤሌትሪክና የነዳጅ አቅርቦት እንኳ ከእስራኤል’ኮ ነው የሚገዙት። ከዚህ በላይ አቅመ ቢስነት አለ?! በዚህ አቅም ተሁኖ ነው ስለ ጂሃድ የሚወራው? እሱ በታንክ አንተ በድንጋይ ሆነህ ነው ድል የምትጠብቀው? እስካፍንጫው የታጠቀን ወታደር ቀይ ካርድ ስላሳየኸው የሚሟሟ ይመስለሃል? ጂሃድን በዚህ መልኩ ነው የምትረዳው? ሱብሓነ’ላ፞ህ!! መቼም የምፅፈው ለፍልስጤማውያን እንዳልሆነ ግልፅ ነው። የምፅፈው ይህን ክስተት እያስታከኩ ዑለማዎችን ስለሚያንቋሽሹ አካላት ነው። የሚገርመው ከነዚህ ዋልጌዎች ቅርሻት ስር የሚልከሰከሱ “ሰለፊ ነን” ባዮች መኖራቸው ነው። አንድ ሰው የሆነን ዓሊም አቋም ቢነቅፍ ወግ ነው፣ አቅሙ ካለው። በዚህ መልኩ ከዑለማዎች መርጦ ሰለፊዮቹን በጅምላ የሚዘረጥጥ፣ እልህን መንሃጁ ያደረገ፣ ከሰለፊዮች ጋር መፋጠጥን እንደ ጀብድ የሚቆጥር፣ ከዑለማእ ንግግር ውስጥ አቃቂር ማውጣትን፣ ‘ሰቀጧት’ መልቀምን ንቃት ያደረገ ከንቱ ፍጡር ማየት ነው የሚደንቀው።
ደግሞም የሰው ኃይል ቁጥርም ቢሆን እነዚህ ስሜት ያሰከራቸው አካላት እንደሚስሉት ሳይሆን በተጭባጭ ከግምት ይገባል። ይሄው ቁርኣናዊው ማስረጃው፦
يَـٰٓأَيُّهَا ٱلنَّبِيُّ حَرِّضِ ٱلۡمُؤۡمِنِينَ عَلَى ٱلۡقِتَالِۚ إِن يَكُن مِّنكُمۡ عِشۡرُونَ صَٰبِرُونَ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفٗا مِّنَ ٱلَّذِينَ كَفَرُواْ بِأَنَّهُمۡ قَوۡمٞ لَّا يَفۡقَهُونَ
“አንተ ነቢዩ ሆይ! ምእምናንን በመዋጋት ላይ አነሳሳቸው፡፡ ከናንተ ውስጥ 20 ታጋሾች ቢኖሩ 200ን ያሸንፋሉ፡፡ ከናንተም 100 ቢኖሩ ከነዚያ ከካዱት እነሱ የማያውቁ ህዝቦች ስለሆኑ 1,000ን ያሸንፋሉ።” [አል አንፋል፡ 65]
አስተውሉ! ንፅፅሩ አንድ ለአስር ነው። ሊያውም ተዋጊን ከተዋጊ ጋር። አሰስ ገሰሱን ሁሉ ሂሳብ እንዳታስገባ!! ቀጠለ፦
ٱلۡـَٰٔنَ خَفَّفَ ٱللَّهُ عَنكُمۡ وَعَلِمَ أَنَّ فِيكُمۡ ضَعۡفٗاۚ فَإِن يَكُن مِّنكُم مِّاْئَةٞ صَابِرَةٞ يَغۡلِبُواْ مِاْئَتَيۡنِۚ وَإِن يَكُن مِّنكُمۡ أَلۡفٞ يَغۡلِبُوٓاْ أَلۡفَيۡنِ بِإِذۡنِ ٱللَّهِۗ وَٱللَّهُ مَعَ ٱلصَّـٰبِرِينَ 
“አሁን አላህ ከእናንተ ላይ አቀለለላችሁ፡፡ በናንተ ውስጥም #ድክመት መኖሩን አወቀ፡፡ ስለዚህ ከናንተ 100 ታጋሾች ቢኖሩ 200ን ያሸንፋሉ፡፡ ከናንተም 1,000 ቢኖሩ በአላህ ፈቃድ 2,000ን ያሸንፋሉ፡፡ አላህም ከታጋሾቹ ጋር ነው፡፡” [አል አንፋል፡ 66]
ልብ በሉ! እዚህ ላይ ደግሞ አንድ ለሁለት ሆነ። ለማቃለሉ የቀረበው ምክንያት ሙስሊሞች ዘንድ ድክመት መኖሩ ነው። ዛሬስ ያለው ድክመት እዚህ ላይ ከተጠቀሰው የባሰ ነው ወይስ የተሻለ? እጅግ በርካታ ዓሊሞች ናቸው “የዛሬ ሙስሊሞች ከድክመታቸው አንፃር ሲታዩ የመካ ዘመን ምሳሌ ላይ ነው ያሉት” የሚሉት። የሙስሊሙ ቁጥር ከቢሊዮን በላይ መሆን ከጦርነት አንፃር ቁም ነገር ሆኖ የሚነሳ አይደለም። የጠላትን ዝግጅት በሚገዳደር መጠን ዘመኑን የዋጀ ለሌሎች የሚተርፍ የሰለጠነ ኃይል ሊሆን ቀርቶ ለራሱም መሆን አቅቶታል። በ1948ቱ የዐረብ እስራኤል ጦርነት ጊዜ ዮርዳኖስ ባይዘልቅም በጥቂት ሰራዊት ከሌሎቹ ዐረብ ሃገራት የተሻለ ድል አስመዝግባ ነበር። ለዚህም በቀዳሚነት የሚነሳው ምክንያት በእንግሊዝ የሰለጠኑ ጠንካራ ወታደሮች ስለነበሯት ነው። ከሰመመንህ ንቃ ወንድሜ! የፈለገ ብትደፈን ቴኳንዶ እንኳ ቁም ነገር ሆኖ ክትትል በሚደረግበት ሃገር እየኖርክ “በቂ የሰው ኃይል አለን” “ዋናው በቁጥር መብዛት አይደለም” እስከማለት አትጨፈን! አዎ! የቁጥር ብዛት ሸርጥ አይደለም። በአላህ ፈቃድ ስንት ትልቅ ጭፍራ ጠንካራ ኢማን ባለው ትንሽ ጭፍራ ተሸንፏል?! ከመሆኑም ጋር “የኢማንም፣ የቁስም ዝግጅት እስከምናደርግ እንታገስ። አሁን ባለንበት ሁኔታ ሙስሊሞችን መማገድ ከጥቅሙ ጉዳቱ ያደላል” ማለታቸው በምን አግባብ ነው እንደ ፍርሃት የሚቀጠረው?
ደግሞም መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ እየነገርኩህ እንጂ በፍርሃት ቆፈን እንድትንቀጠቀጥ እያስፈራራሁህ አይደለም!! አቅምን ማወቅ ብስለት እንጂ ፍርሃት አይደለም። አቅምህን ስታውቅ ነው ለተሻለ የምትዘጋጀው። ሰላም!!
HTML Embed Code:
2024/03/29 05:46:37
Back to Top