TG Telegram Group Link
Channel: Ahadu picture
Back to Bottom
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 13

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
"ማማዬ ማማዬ ሸጋ ልጅ ማማዬ"አለ ዞላ
"ነይ ማማዬ"ሁለቱ ዮኒዎች ተቀበሉ ።ዮርዳኖስ ፅፎ ለመጨር ጥቂት ምዕራፍ የቀረውን ልቦለዱን እያገላበጠ ነው።ዜኖ ላይብረሪ መሽጓል።
"ማማዬ ማማዬ ሸጋ ልጅ ማማዬ "ዞላ ቀጠለ
"ነይ ማማዬ "ዮናስ ጎጄ እና ዮኒ ተቀበሉት
"ማማዬ ገንዘብ አላት ብሎ መልከ ጥፉ ማግባት"
" ነይ ማማዬ '
"ማማዬ ገንዘቡንም ያልቅ እና ሁለተኛ ጥፋት"ዞላ ዘፍኖ ጨረሰ እና ልቡ እስኪፈርስ ሳቀ ሁለቱ ዮናሶች ተክትለው ዶርሙን በሳቅ አናጉት።ናቲ እየተናናደደ ነበር ።ምክንያቱም እሱን ለመንካት ብሎ ነው ዞላ የዘፈነው።
"አይገርምህም እንዳንተ በእየሳምንቱ አዲስ ትዳር ከመመስረት እኔ አልሻልም?"አለ ናቲ
"እንደዛማ እንዳትል ይቺን ድብልብል ሰው አትላት ጉማሬ የሆነች ፍቅረኛህ ጋር ፍቅር ፍቅር እያለ እሱ እንዳንተ አይጃጃልም"አለ ዮኒ ጎጄ ዞላን ወግኖ
"ፍቅር የት ታውቅና ነው ደግሞ አንተ።ፍቅር በአንተ አፍ ሲጠራ ደስ አይልም"አለ ናቲ ዮኒ ጎጄን
ናቲ ሰሞኑን ቺክ ጠብሶ ዞላ አላስበላ አላስተኛ ብሎታል።ለነገሩ እውነቱን ነዉ በዞላም አይፈረድም።ይሔን የመሰለ ሸበላ ልጅ ከዚያች ጉርድ በርሜል ከምታክል ሰው ጋር ሆኖ ሲታይ አይደለም ጓደኞቹ ሌላም መንገደኛ ቢያይ መናደዱ አይቀርም።ምኗም እኮ አያምርም።ምኗን አይቶ ነው የወደዳት ብለው ጓደኞቹ ገርሟቸዋል።ዞላ የባለሀብት ልጅ ነች ገንዘቧን አይቶ ነው እያለ ገንዘብ አላት ብሎ መልከ ጥፋ ማግባት እያለ ይዘፍንበታል።ናቲ ግን የምን ገንዘብ ነው የምታወሩት በቃ ተመችታኛለች ከማለት ውጭ ሌላ መልስ አይመልስም ።
ዞላም ፀባዩ ብሶበታል ካልቃመ የማያወራ ሱሰኛ ሆነ።ዶርም የሚያድርባቸው ቀናቶች በጣት ይቆጠራሉ።ዛሬ ከሊሊ ነገ ከቲቲ ከነገ ወዲያ ከጀሪ አዳሩ እንደዚህ ሆኖ አርፏል።ታዲያ ዮኒ እና ዮርዲ ቁጭ አድርገው ቢመክሩት አልሰማ ብሏቸዋል።ሱሱም ይቅርብህ ሴት ጋር መዝለሉም ተዉ ዘመኑን ለአንተ መንገር አያስፈልግም ትልቅ ሰው ነህ ብለው ሲነግሩት እሱ ግን አሻፈረኝ ብሏል ።ጋጥ ውስጥ ታጉራ የዋለች እምቦሳ ስትለቀቅ እንዴት እንደምትሆን ታውቃላችሁ አይደል?በቃ እኔንም እንደዛ ተመልከቱኝ ተውኝ እንደልቤ ልሁን።ለሌላው ነገር አታስቡ እኔ ጅል አይደለሁም በመላጣው አልጠቀምም ብሎ ከኪሱ ሴንሴሽን አውጥቶ አሳይቷቸዋል።ዮኒ እና ዮርዲም የሚያደርጉት ጠፍቶባቸው ዝም ብለዋል።
ዮኒ ቆንጆ የልጅነት ፍቅረኛ አለችው።አንድ ላይ አገር ሞልተው ከአንድ ሰፈር የመጡ ጥንዶች ናቸወ።ሔለን ትባላለች አውርቶ አይጠግባትም።በእየ ሰከንዱ ነው የምትርበው።ዮርዲ እነሱን ሲመለከት ሔዋን አሜሪካ ባትሔድ እኔም እኮ እንደ ዮኒ ነበርኩ።ይላል።ዮርዳኖስን የሚረዳው ዮኒ ነው።ሁሌም ከዛሬ ነገ ይሻላል ሔዋን ፍቅርህ እምነትህ ሁሉ ነገርህ ነች እምነቷን ጠብቀህ ጠብቃት ፍቅር ዋጋውን ይከፍልሃል።ብሎ ዮኒ ሲናገር፤ዮኒ ጎጄ ጣልቃ ይገባና፦አረ ወዲያ ምን ፍቅር ፍቅር እያላችሁ ትጃጃላላችሁ።እዚህ ምድር ላይ ፍቅር የሚባል ነገር ያለው በፊልም እና ልቦለድ ላይ ነው።ዝም ብላችሁ በምናባችሁ የምትፈጥሩትን ህይወት አትኑሩ።አንዳንዴ ዮርዳኖስን እና ዮኒን ስመለከት ቆንጆ የህንድ ፊልም እያየሁ ወይም በጥሩ ደራሲ የተደረሰ የፍቅር ልቦለድ እያነበብኩ ነው የሚመስለኝ።ሔይ ፍቅር ምንድን ነው?ፍሬንዶች አይናችሁን ግለጡ ፍቅርን ይሁዳ ገድሎ ቀብሮታል ለፍቅር ብሎ የወረደውን ጌታ በሰላሳ ዲናር ሲሸጠው ያኔ ፍቅር ሞተ።ለፍቅር የወረደውን ጌታን ሲሰቅሉ ያኔ በአይሁዳውያን እጅ ተጨፍልቃ ፍቅር ጠፍታለች ።ታዲያ የት የምታውቁትን ነው ፍቅር የምትሉ።አስመሳዮች አንሁን።ዮርዳኖስ የራስህን ኑሮ ኑር ሔዋንን እርሳት እሷም አሜሪካ ኑሮዋን እየኖረች አይደል።በቃ እርሳው ምንም እንዳልፈጠረ።ኑር ይላል ዮኒ ጎጄ ።
"ዮኒ ጎጄ አትሳሳት ፍቅር ለዘለዓለም ትኖራለች።አላዋቂዎች አጎደፏት እንጂ ፍቅር ትላንትም ዛሬም ነገም ሁሌም ትኖራለች።እስኪ ልጠይቅህ ዮኒ ጎጄ፦እናትህ ላይ ሽጉጥ ተነጣጥሮባት ብታይ ይግደላት ብለህ ዝም ትላለህ?
"አረ በናትህ ዝም በል"ዮኒ ጎጄ መለሰ
"አየህ ይግደላት ብለህ ዝም አትልም።አሷን ትቶ አንተን እንዲገድልህ ትማፀናለህ እንጂ።ከዚህ በላይ ፍቅር አለ እንዴ?ይላል ዮኒ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዜኖ በጣም ተረብሾ ዶርም ገባ።ከወዲያ ወዲህ ይንጎራደድ ተያይዞታል ።
"ምነው ቴንሽን ነገ ፋይናል ይጀምራል አሉህ እንዴ"አለ ናቲ
"ዝም በል ባክህ ለፋይናል ሁለት ሳምንት ነው እኮ የቀረን ነገ ማለት አይደለም? ይልቁንስ እሱን ተወው እና የዚህ ዶርም ነዋሪ በሙሉ ጉድሽ ፈልቷል"አለ ዜኖ በጣም ከመፍራቱ የተነሳ እያላበው ነው።
"የምንጉድ አመጣህ"አለ ዮኒ ደንግጦ ከአልጋው ላይ እየወረደ።
"ዞላ ገና ከዚህም በላይ ነው የሚያደርገን ይሔ ጦሰኛ ልጅ"አለ ዜኖ
"ደግሞ እኔ ምን አደረግሁ "አለ ዞላ
"ምነው የትኛዋ ልጅ አረገዘች፤በናትህ ዞላ የልጅ አባት ሊሆን ነው በለኝና ልሳቅ"አለ ዮኒ ጎጄ
"እሱማ በምን እድላችን።አንዷ ብታረግዝማ እሷን የሙጥኝ ብሎ እግሩን ሰብስቦ ይቀመጥ ነበር"አለ ዜኖ እየተንቆራጠጠ
"አረ ዜኖ ዝም በል አድጌ ሳልጨርስ ልጅ አሳዳጊ ልታደርግኝ ነው።የሰይጣን ጆሮ ይደፈን።"አለ ዞላ
ዮርዳኖስ ከአልጋው ላይ ተነሳ እና ዜኖን አስቀመጠው።"ዜኖ እስኪ ተረጋጋ እና የሆነውን ንገረን"አለ ዮርዲ
"እንዴት ነው የምረጋጋው።አሁን ሻንጣችንን እንሸክፍ እና ጊቢውን ለቀን እንውጣ"አለ ዜኖ
"ቆይ ይሔ ልጅ ምንድነው የሚያቃዠው"አለና ዮኒ ጎጄ የሀይላንድ ውሀ እረጨው
"የምን ቅዠት ነዉ የምታወራው።ልጁን ብታዩት እኮ ጎሊያድን ያስንቃል።"አለ ዜኖ የበለጠ እየተንቀጠቀጠ...

ሴትዮዋ ልጇ ከመሔዱ በፊት አስቀምጦላት የሔደውን ደብዳቤ ከአነበበች በኋላ ምንም መረጋጋት አልቻለችም።ትንሿ ግሮሰሪ ውስጥ ጨዋታዋን ለምደው እስከ እኩለ ሌሊት ያመሹ የነበሩ ደንበኞች ዛሬ ሴትዮዋ ፍዝዝ ስትል ገና በሁለቱ ሰዐት ቤቱ ጭር ብሏል።መንጋው ቀበሮ እንዳየ የበግ መንጋ ተበትኗል።ከአቅሟ በላይ ይጨፈርባት ይጠጣባት ይሰከርባት የነበረች ግሮሰሪ ዛሬ ግን አስከሬን የወጣባት ለቅሶ ቤት መስላለች።ግሮሰሪዋ ለሰፈሩ ብቸኛ ግሮሰሪ ስለሆነች የሰፈሩ ጠጪ በሙሉ ይችን ቤት የሙጥኝ ብሎ ነው የሚያመሸው።መቀመጫ ጠፍቶ ባንኮኒ እና ግድግዳ ተደግፎ የሚጠጣውን ሰው ቤት ይቁጠረው።
ሰው ሁሉ ማርዘነብ አንች ዝም ስትይ አታምሪም ባይሆን ድብርትሽ ሲለቅሽ ነገ መጥተን እንጠጣለን አያለ ውጥቶ አልቋል።በእድሜያቸው ገፋ ያሉ አዛውንት በግምት ወደ ሰማኒያ አመት ገደማ የሚጠጉ አቶ አድማሱ እሳቸው ብቻ ቀርተዋል።ፀጉራቸው ለምልክት እንኳ ጥቁር ፀጉር የሚባል ነገር የላቸውም።አናታቸው ላይ ሀጫ በረዶ የመሰለ ያደገ ፀጉር ተደፍቶባቸዋል።እድሚያቸው የገፋ ቢሆንም ጉልበታቸው እና ሃይላቸው ግን ወጣትን ያስንቃል።ታዲያ ጨዋታ አዋቂ ስለሆኑ የሚጣጣው ሰው ሁሉ ነው የሚጋብዛቸው።እሳቸውም የማርዘነብን ግሮሰሪ ሳይሳለሙ ማደር አይሆንላቸውም።
ጠርሙሳቸውን ይዘው ወደ ማርዘነብ ሔደው ተቀመጡ።
"ማርየ እንደው አፈር ስሆን ምን አገኘሽ ልጄ"አሉ አባ ባይወልዷትም እንደ ልጃቸው ነው የሚመለከቷት።እድሜዋ ሰላሳዎችን ጨርሳ አርባወችን መጣሁላሁላችሁ እያለች ነው።
"ጋሽ አድማሱ ግሮሰሪው እንደሚያዩት ዛሬ ጭር ብሏል እንዝጋው እና ቡና አፍልተን ያጫውቱን?"አለች ማርዘነብ
"አረ ምን ገዶኝ"ይለፍ ሀሳብ ነው አሉ ከቢራቸው እየተጎነጩ
"ማነሽ ፀሐይ አንቺ ቡናውን ግቢና አደራርሽ ፣እርግቤ አ
ንቺ ደግሞ እራት ስሪ "ብላ ትዕዛዝ አስተላፈች ማርዘነብ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ግሮሰሪው ካለወትሮው ገና በሁለት ሰዐት ተኩል ተዘጋ ።አቶ አድማሱ አቦል ቡናቸውን ፉት እያሉ "እሺ ማርዘነብ ምንድን ነው ያስጨነቀሽ የኔ ልጅ ?"አሉ
"ልጄን የንስሐ አባቴ ያስፈልገኛል ብለው እንደወሰዱት አጫውቸወት ነበር"አለች ማርዘነብ
"እንዴታ እሱንማ ነግረሽኛል"አሉ አቶ አድማሱ
"ሲሔድ ይሔንን ወረቀት ፅፎልኝ ነበር"ብላ የተጠቀለለ ወረቀት ሰጠቻቸው ።
በለሆሳስ ማንበብ ጀመሩ"እማዬ ለስሙ አባት አለኝ እጠራበታለሁ ልብስ ሁሉን ነገር ይገዛልኛል።ግን አላውቀውም ለምን?እማዬ አንቺን ይከፋሻል ብዬ አባት እየራበኝ እህት ወንድም እየራበኝ ዝም ብዬ ኖርኩ።አባቴን ሳላውቅ አስራ ስምንት አመት አለፈኝ።ከአንቺ ጋር ተለያይቶ ከሆነ በእርግጠኝነት ሌላ ቤተሰብ ሌላ ልጆች ይኖሩታል።ስለዚህ እኔም ወጉ ይድረሰኝ ወንድም እህት ይኑረኝ።ከሔድኩበት ስመለስ አስበሽበት አባቴን ማግኘት እፈልጋለሁ ።ቻው እወድሻለሁ እማ"
ደብዳቤውን አንብበው ጨረሱ "ማርዘነብ ልጁም እኮ አይፈረድበትም ተገቢ የሆነ ጥያቄ ነው የጠየቀው"አሉ
"ልጄን ምን ያህል እንደበደልኩት ዛሬ ነው የገባኝ።ገና ለገና የአባቱን ቤተሰብ እንዳልበትን ብዬ ልጄን እህት እና ወንድሞቹን ሳያውቅ ባይተዋር ሆኖ አደገ።አስራ ስምንት አመት ሙሉ በብቸኝነት ቀጣሁት"አለች ማርዘነብ ምርር ብላ።
"እና ምን አሰብሽ"አሉ ፂማቸውን እያፍተለተሉ
"ሱቅ ድረስ ሄጄ ልክ ልኩን ነው የምነግረው አባት ተብየውን"አለች
"እንደዛማ አይሆንም ልጄ ነገር ታበላሺያለሽ ባይሆን እኔ ዝግ ብየ አናግረዋለሁ"አሉ
"እውነትወትን ነው ጋሽ አድማሱ?"አለች
"እንዴታ ወትሮም ከአንቺ ይምጣ ብዬ እንጂ ይሔ ቁምነገረኛ መልከ መልካም ልጅ ብቻውን ነሁለል ሲል ያሳዝነኝ ነበር"አሉ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አቶ አድማሱ ቡናውን አብርከው ለመጪው እሁድ ሔደው የልጁን አባት እንደሚያነጋግሩ ለማርዘነብ ቃል ገብተውላት ሔዱ ።ማርዘነብም ጭንቀቷ ቀለል ብሎላት ለአመታት ያህል የልጇ ጥያቄ ተመልሶለት አባቱን ሲያገኝ እየሳለች በተስፋ ወደ ምኝታ ቤቷ ሔደች።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 14

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
አባ ቶማስ ሴራሚክስ አምራቹን ቡድን ጨምሮ ሔኖክ፣ ኢያሱ፣ ሔዋን እና ቃለአብን ይዘው ውይይት ላይ ናቸው ።አባ ቶማስ መናገር ጀምረዋል።"ተወልጄ ያደኩት ቢቸና ነው።ቤተሰቦቼን ካጣሁ በኋላ እኔ እና ሁለት ታናናሽ ወንድሞቼ እዚህ ግቡ የማይባሉ ዘመዶቻችንን ትተን እግራችን ወደመራን ተሰደድን።እኔ ከልጅነቴ ጀምሮ አብነት መማር ህልሜ ነበር እና በእየገዳማቱ በእየደብሩ እዞር ጀመር።ከብዙ አመታት በኋላ አንደኛው ታናሽ ወንድሜ በነበርኩበት ዲማ ጊወርጊስ አፈላልጎኝ መጣ።ተለውጦ ነበር ምን ተዐምር ተፈጠረ ብየ ስጠይቀው እንዲህ ሲል ነገረኝ።
አንተ አብነት ለመማር ስትነሳ እኛ አዲስአበባ በጭነት መኪና ተጭነን ገባን።ብዙ ቀናት በርሀብ በብርድ ጎዳና ላይ ስንሰቃይ ቆየን እና አንድ ቀን ግን እግዜር የባረካቸው አዛውንት አገኙን።ከወደቅንበት ጎዳና አንስተው ቤታቸው አስገቡን።ታሪካችንን ሰምተው ልባቸው በሀዘን ተኮማተረ።መውለድ እንደማይችሉ ነግረውን ከባለቤታቸው ጋር እንደ ልጅ ሊያሳድጉን እና በአዲስ አመት ትምህርት ቤት እንደሚያሰገቡን ቃል ገብተው ከቤታቸው አስጠጉን።ትምህርት ገባን።ኤሊያስ ጥሩ ውጤት ሰርቶ የውጭ የትምህርት እድል አገኘ።እኔም አዲስአበባ ዮኒቨርስቲ በማኔጅመንት ተመርቄ የአሳደገኝን አባቴን ድርጅት መምራት ጀመርኩ።አሳዳጊዎቻችን አሁን ከዚህ አለም ተለይተዋል።እኔም የድርጅቱ ባለቤት ሆኘ ትዳር መስርቼ አንድ ልጅ ወልጃለሁ።ኤልያስም አሜሪካ ትምህርቱን ጨርሶ ጥሩ ቦታ ተቀጥሯል ብሎ ነገረኝ"ወንድሞቼ በገጠማቸው መልካም እድል ተደሰትኩ።አዲስአበባ ያለው ወንድሜ ኢሳያስም ሊውስደኝ እንደመጣ ነገረኝ።እኔ ግን ያለሁበት እንደተመቸኝ ነግሬው ሔደ።በአመቱ የአሜሪካው ወንድሜ ኤሊያስ እና ኢሳያስ ከእነባለቤቱ እና አንድ ልጁን ኢያሱን ይዞ መጥቶ ጠየቀኝ።
እናም ስልክ ገዝተውልኝ ሔዱ።በእየጊዜው መደዋወል ጀመርን።እዛው ዲማ ደብር በህግ ያገባኋት ሚስቴ ሁለተኛ ልጅ ልትወልድ በምጥ ልጁንም እሷንም አጣሁ።እኔም ሀዘኑ ሲከብደኝ ብቸኛ ልጄን ማስረሻየን ሔኖክን ይዤ ከዚህ ጥንታዊ ቂርቆስ ምንኩስናን ተቀብዬ መኖር ጀመርኩ።ከብዙ አመት በኋላ የሚወራውን ሰማሁ።የዘንዶ ዋሻ በተባለው ዋሻ በድፍረት ገባሁ።ግን እንደሚወራው ዘንዶ ሳይሆን በምትኩ ያንን ሁሉ ንብረት ጣልያን አከማችተው አገኘሁ።በሰዓቱ ብዙ ነገር አሰብኩ።ግን ይሔ ህዝብ እንብላው ስለሆነ መናገሩ አስፈላጊ ሆኖ አልታየኝም።ይልቁንስ ይሔንን ድንጋይ ወፍጮ ሌላ ሰው ይዞት ሚስጥሩ ከመውጣቱ በፊት ለወንድሜ ለኢሳያስ ተ/አረጋይ ደወልኩለት እና ነግሬው ድንጋይ ወፍጮዉን እንዲገዛ አደረኩ።ለብዙ ጊዜ ሳስብ ቆይቼ በመጀመሪያ ደረጃ ይቺን አነሳ ቤተክርሰቲያን ላሳንፅ ወሰንኩ።ግን ህዝቡ ሁሉን ልወቅ ባይ ነውና ከየት አምጥተህ ብሎ ማሰቡ አይቀርም።ስለዚህ የንስሐ ልጄን የአቶ አንድነትን ልጅ ምናሴን በወንድሜ በኤሊያስ በኩል ወደ አሜሪካ ላኩት።አላማየ ምንድን ነበር ቤተክርስቲያኗን ፎቶ አንስቶ ወስዶ ልህንፃ ቤተክርስቲያን ማሰሪያ እርዳታ ለማሰባሰብ በሚል ሰበብ ነበር።ግን ነገሩ ተገለበጠ።እኛ ያሰብነው ምናሴ ላከ እያልን ዋሻው ላይ የተደበቀውን ሀብት ወደ ገንዘብነት ቀይሮ ቤተክርስቲያኑን መስራት ነበር።ግን ምናሴ እድል ቀናው ብዙ ብር ማጉረፍ ጀመረ ።ፈረንጆቹ እጃቸውን ዘረጉለት።ከዋሻው ሀብት አምስት ሳንቲም ሳንነካ ምናሴ በሚልከው ብር ይሔው ህንፃው ተጠናቆ ሊመረቅ ነው።
ከዚህ በኋላ ግን ሀሳባችን ሌላ ነው።"አሉ አና የሐይላንድ ውሀ ተጎነጩ።

"የምን ቅዠት ነው የምታወራው?ልጁን እኮ ብታዩት ጎሊያድን ያስንቃል "አለ ዜኖ የበለጠ እየተንቀጠቀጠ
"አረ በናትህ ምን ሁነህ ነው ለምን በግልጽ አትናገርም"አለ ዮኒ
"ይሔ ጦሰኛ ልጅ በባለፈው ክለብ ውስጥ አስክሮ ያወጣት ማነች ማህደር ነች ማሒ ምናምን የምትባለዋ ልጅ ፍቅረኛ አላት"አለ ዜኖ ወደ ዞላ እየጠቆመ ።
"እና ለዞላ ፍቅረኛ ያላት ችክ ማውጣት ብርቁ ነው እንዴ?አለ ዮኒ ጎጄ
"ችግሩ እሱ አይደለም።ችግሩ ፍቅረኛዋ ከዞላ ጋር ምን እንደተፈጠረ ሰምቶ ጓ ብሏል እኮ ነው የምላችሁ ።"አለ ዜኖ
"ምን?" አለ ዞላ በድንጋጤ። ሁሉም በድንጋጤ አፋቸውን ከፍተው ቀሩ።
"አንተ እንዴት ልታውቅ ቻልክ?"አለ ዮርዲ
"እኔማ አገር ሰላም ብየ ከሶሻል ላይብረሪ በበግ ተራ ስመጣ ብሎክ 19 ላይ አንድ ግብድየ ልጅ ብዙ ተማሪዎች ከበውት ይገለገላል።ታዲያ ጆሮ ልጥባ ብየ ጠጋ ብየ ስመለከት ስልኩ ላይ የዞላን ፎቶ ለከበቡት ተማሪዎች እያሳየ "እመኑኝ እወገዋለሁ እንዴት እዚህ ግቢ ሶስት አመት ተከብሬ ኖሬ በዚህ ቀጫጫ ፍሬሽ ልደፈር እገለዋለሁ" እያለ ሲዝት ሰምቼ ነው በደመነፍስ እየሮጥኩ የመጣሁ ።እዚህም የደረስኩት በፈጣሪ እርዳታ ነው"አለ ዜኖ ቁና ቁና እየተነፈሰ።
"ልጁ ማን ነው?"አለ ዮርዲ
"ደርቤ ተው መቸኮል አያስፈልግም"እያሉ ስሙን ጠርተው ሲመክሩት ሰምቻለሁ አለ ዜኖ
"ደርቤ"አለ ዮኒ ጎጄ ደንብሮ እየተነሳ
"አዎ ደርቤ። ምነው ታውቀዋለህ እንዴ?"አለ ዜኖ
"እንዴ ደርቤን የማያውቅ አለ?ደርቤ ማለት እኮ ከጨርቁ የተጣላ ገለባ ነው።በቀደምለት ላውንች ትዝ አይላችሁም እንዴ?"አለ ዮኒ ጎጄ
"ላውንች ምን አሉ" ዜኖ ግን ዝም አለ ምክንያቱም የትኛውም እንቅስቃሴአቸው ላይ ተሳታፊ አይደለም ።
"ላውንች ሻይ አስቀድቼ ወደ እናንተ ስመጣ ወለሉ አንሻቶኝ ሻይ ደፍቼበት ካልገደልኩህ ብሎ የተገለገለው ልጅ እኮ ነው "አለ ዮኒ ጎጄ ።
"ወይኔ እዛ ልጅ ላይ ደግመን ተገናኘን"አለ ናቲ ምርር ብሎ።
"በቃ ሔጄ አናግረዋለሁ እናንተ ተረጋጉ"አለ ዞላ
"አንተ ያምሀል እንዴ ፍቅረኛውን ያወጣኸው እኮ አንተ ነህ እሱ የደረሰብህ መሰለህ እንዴ?በዛ ላይ ደግሞ እወገዋለሁ እያለ ሲዝት ሰማሁ እያለ ነው ዜኖ።ባይሆን ሌላ መፍትሔ እንፈልግ።"አለ ዮርዲ "እንዴ መፍትሔ ምናምን ትላላችሁ።እየው እሱ ዞላን ብቻ አይፈልግም ግብረ አበሮቹ ናችሁ ብሎ ሁላችንንም ነው እሚፈጀን።ስለዚህ ነገሩ እስኪረጋጋ ከግቢ ውጭ እንቆይ "አለ ዜኖ
"እንተ ወንድ ልጅ አይደለህ ምንድን ነው እንደዚህ እሚያንቦቀቡቅህ "አለ ዞላ
"አንተ ዝም በል ይሔ ሁሉ በእንተ መንዘላዘል ነው።አፍ የለህም ስለዚህ ዝምምምምምም በል "አለ ዜኖ አፉን በመጠቆሚያ ጣቱ እየሸፈነ ።
"ዝም በሉ እስኪ የእናንተን ጭቅጭቅ እንስማ ወይስ መፍትሔ እንፈልግ?"አለ ዮኒ ተቆጥቶ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮኒ እና ዮርዲ ደርቤን ሊያናግሩት እንደሚፈልጉ ነግረውት ከበደ ግሮሰሪ ይዘውት ሔዱ።
"እሺ ለምን ነበር የፈለጋችሁኝ "አለ ደርቤ የተቀዳለትን ድራፍት እየተጎነጨ።
"ይሔንን ልጅ ታውቀዋለህ?"አለ ዮኒ የዞላን ፎቶ ከስልኩ ላይ ለደርቤ እያሳየው ።
"ችግር የለውም የእናንተን እርዳታ እልፈልግም ብልቱን ነው እምቆርጥለት"አለ ደርቤ ጠረጴዛውን በቡጢ ነርቶ
"አይ እንደሱ አይደለም።አኛ ጓደኞቹ ነን"አለ ዮርዲ በሁኔታው ተዳናግጦ
"አሀ አሀ አሀ
ብር አምባር ሰበረልን ብር አምባር ሰበረልን
ኦሆሆ ጓደኛችን
ብላችሁ ልትዘፍኑልኝ ነው የመጣችሁ"አለ ደርቤ የንዴት ሳቅ ስቆ
"ምን መሰለህ ደርቤ እንዳጋጣሚ ሆነና ማህደርን የኛ ጓደኛ አወጣት እንጂ በሰዓቱ ሰክራ ስለነበር ሌላ ሰው ጋርም ቢሆን ማደሯ አይቀርም ነበር አይደል?"አለ ዮኒ
"እና ምን ይጠበስ?"አለ ድራፍቱን ደጋግሞ እየተጎነጨ
"ምን አልባትም ችግሩ የእኛ ጓደኛ ብቻ ላይሆን ይችላል።ማህደር አንተን የመሰለ ፍቅረኛ እያላት ብቻዋን ክለብ መውጣት አልነበረባትም ።ሲቀጥል ሰክረዋ
ል ወጣቶች ናቸው ይሳሳታሉ።ስካር አይደለም እነዚህ አፍላ እድሜ ላይ ያሉ ልጆችን የስንቱን አባወራ እና እማወራ ትዳር መሰለህ የሚበትን"አለ ዮርዲ ጥፋቱን ወደ ማህደር አብሮ በማላከክ ።
"እሺ እኔን ምን አድርግ ነው እምትሉኝ"አለ ደርቤ ድጋሜ የመጣለትን ድራፍት በአንድ ትንፍሽ ግማሽ ድረስ ጨልጦ ።
"በቃ ይሔንን ስህተት እንዳልተፈጠረ እርሳው እና ይቅርታ አድርግለት "አለ ዮኒ እየተለማመጠ
"ይቺ የውሻ ልጅ እሷን ግን አሳያታለሁ።ጓደኛችሁን ግን እናንተ ጥሩ ሰዎች ስለሆናችሁ ምሬዋላሁ።ንገሩት ስለ እናንተ ብዬ እንደተውኩት" አለ ደርቤ
ደርቤን እስኪበቃው ድረስ አጠጥተው በደንብ ተግባብተው ወደ ግቢ ተመለሱ።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

💞ክፍል 15

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ሔዋን ለምን እዚህ ቦታ እንደመጡ በምክንያት አስደግፈው አባ ቶማስ ከተናገሩ በኋላ እራሷን እንደ እድለኛ ሰው እየቆጠረች ነው።አሁን ከዚህ ግቢ ለመውጣት ሳይሆን እየቸኮለች ያለችው ምናሴ መጥቶ ፕሮጀክቱ በይፋ የሚጀመርበትን ቀን ነው።በዛው ልክ ደግሞ የቃለአብ ጉዳይ በጣም አጣብቂኝ ውስጥ ከቷታል ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"ሔዋን ግጥም መፃፍ ትወጃለሽ መሰለኝ"አለ ሔኖክ
"አይ ማንበብ ነው እመወደው "አለች ሔዋን
"ብዙ ጊዜ አንድ ደብተር ላይ አተኩረሽ እመለከትሻለሁ "አለ ሔኖክ
"አዎ የጓደኛዬ ግጥሞች ናቸው"አለች እጮኛዬ ለማለት እየፈረች
"ታዲያ ለምን አትሰጭኝም አላነብለትም።እንደዚህ ፍዝዝ አድርጎ የሚያውልሽን የሚመስጥሽን" አለ ሔኖክ
"አረ ግጥም ትወዳለህ?"አለች ሔዋን
"አልፅፍም እንጂ"አለ ሔኖክ ፍርጥም ብሎ
"እሺ ይዤልህ እመጣለሁ"አለች እና ሔዋን ወደ ክፍሏ አመራች።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አቶ አድማሱ ከማርዘነብ ጋር በተነጋገሩበት መሰረት የልጁን አባት ለማናገር የሽማግሌ አለባበስ ወጉን አሟልተው ተነስተዋል።ጋቢያቸውን ለብሰው ጭራቸውን ነስንሰው ከዘራቸውን ይዘው ወደ ልጁ አባት ሱቅ ገሰገሱ ።
ከሱቅ እንደደረሱ ከሱቁ ባለቤት ጋር ሰላምታ ተለዋውጠው በረንዳው ላይ ተቀመጡ ።
"ማነሽ አሰለፍ እስኪ ሁለት ሲኒ ወፈር ያለ ቡና ስሪልን"አለ ባለሱቁ።ሱቁ በረንዳ ላይ የጀበና ቡና የምትሸጠዋን ልጅ
ባለሱቁ እና አቶ አድማሱ ስለ ኑሮ ስለ ገበያ ሲያወሩ ከዋሉ በኋላ
"ጋሽ አድማሱ ምን ጎርፍ ጣልዎ?"አለ ባለሱቁ
"እንደው ምን መሰለህ ወዳጄ .........እ.....እኔማ አመጣጤ ከማርዘነብ መልዕክት ለማድረስ ነበር"አሉ አቶ አድማሱ
የማርዘነብ ስም ሲጠራ ባለ ሱቁ ሰውየ በአንዴ ፊቱ ተለዋወጠ
"ማ....ማርዘነብ ምን አለች?"አለ ባለ ሱቁ እየተንተባተበ።
"ምን መሰለህ ወዳጄ ልጁ በጣም እየተጎዳ ነው አባቴን እና የአባቴን ልጆች አስተዋውቂኝ እያለ አስጨንቋታል።ልጅህ ሰው እርቦታል።"አሉ አቶ አድማሱ
ባለ ሱቁ ሰውየ ሲያስብ ከቆየ በኋላ "ጋሽ አድማሱ ትንሽ ጊዜ ብቻ እንድትሰጠኝ አግባቡልኝ?"አለ አየተለማመጠ።
"ኤዲያ አንተ ደግሞ አስራ ስምንት አመት ሙሉ ገመናህን ሸፈነች።ይልቁንስ ነገር ሳይበላሽ ፈጥነህ ለባለቤትህ እውነቱን ብትነግራት ነው የሚሻል።ልጆችም ይገናኙ።ያ አንድ ፍሬ ልጅ አያሳዝንህም?"አሉ ተቆጥተው
"ጋሽ አድማሱ አሁን ግን ወስኛለሁ ትንሽ ጊዜ ብቻ።እኔስ ልጄን እንደ አባት ሆኘ አቅፎ መሳም እማይናፍቀኝ ይመስሎታል?እንደ አባት እቅፌው መተኛት እንደ አባት ማጉረስ እማይናፍቀኝ ይመስሎታል ?ግን በቃ ትንሽ ጊዜ ባለቤቴን እውነቱን እስክነግራት ድረስ"አለ ባለሱቁ
አቶ አድማሱ ከባለሱቁ ጋር በአጭር ጊዜ ውስጥ ነገሮችን አመቻችተው በመልካም ዜና እንደሚገናኙ ተነጋግረው ተሰነባበቱ ።
፨ ፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሔኖክ ሔዋን የሰጠቺውን የግጥም ደብተር ሲመረመር ከዋላ በኋላ ሔዋንን አስጠራት።
"እኔ እምልሽ ሔዋን አሁን የዚህ ደብተር ባለቤት ማለቴ ዮርዳኖስ የት ነው የሚኖረው?"አለ ሔኖክ
"እኔ ወደዚህ መጣሁ እሱ ደግሞ የት ዮኒቨርስቲ እንደደረሰው አላውቅም?ምክንቱም ምንም አይነት ስልክም ሆነ ማህበራዊ የሶሻል ሚዲያ መጠቀም አልችልም ከልክላችሁናል ።ስለዚህ አላውቅም ግን አንደኛ ደብረ ብርሃንን ነበር የመረጠው እዛ የገባ ይመስለኛል"አለች
"እሱን ተይው እና በዚህ ወር በዞን ደረጃ የሚዘጋጅ የወጣቶች የስነፅሁፍ ወድድር አለ ለምን ግጥሙን አናስገባለትም?የዞን ያሸነፈ እንደክልል ይወዳደራል እሱን ያሸነፈ እንደ ኢትዮጵያ ክልል ወክሎ ይወዳደር እና በመጨረሻ አሸናፊው በባህል እና ቱሪዝም ሚኒሰቴር ስፖንሰርነት ይታተምለታል።ማስታወቂያው እንደዛ ነው የሚለው"አለ ሔኖክ
"እውነትህን ነው ?"አለች ሔዋን በደስታ እየቦረቀች
"አዎ"አለ ሔኖክ የተቀመጠበት ወንበር ላይ እየተንጠራራ
"የጀመረው ልቦለድም ነበረ በእርግጠኝነት እስከ አሑን ያጠናቅቀዋል ለምን አሱን አስልከህ አብረን አናስገባም"አለች ሔዋን
"እሱን እንደ ዞን ካሸነፈ የዚያን ጊዜ አብሮ ለክልል ይሔዳል ።አሁን ግን ስራ ልሰጥሽ ነው ።ግጥሞቹን ኮምፒውተር ላይ ተፅፈው ፕሪንት አድርጌ እስከ ሳምንት ማስገባት አለብኝ።ዮርዳኖስን ወክዬ ግጥሙን አስገባለሁ አንቺ እሱን ገልብጠሽ ጨርሺ" አለ ሔኖክ

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😋ሰሜናዊት ሙሽራ😋

🔥ክፍል 16

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ሔዋን ለአመታት ያህል ተለይቷት የኖረው ወንድሟ ምናሴ አንድነት ከአሜሪካ ከተመለሰ ሁለት ሳምንት አልፎታል።የዮርዳኖስ ግጥም ደግሞ ወረዳውን ወክሎ ለዞን እንዲወዳደር ተመርጦ በሔኖክ ተወካይነት ለምስራቅ ጎጃም ዞን ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ቢሮ ተልኳል ።ሔዋን አጥፍ ድርብ ደስታ ላይ ነች።
ሔዋን ኮሪደሩን አቋርጣ ስትሔድ ቃለአብ ይከተላት ነበር።
"ሔዋን ሔዋን" ቃለአብ ተጣራ
መንገዷን ገታ አደረገችና "ወየ ቃል"አለች
ስሙን አቆላምጣ ስትጠራው ልቡ እንደ ሻማ ስትቀልጥ ታወቀው
"እንድናወራ ፈልጌ ነበር ከድንኳኑ ጀርባ እጠብቅሻለሁ"ብሎ መልሷን እንኳን ሳይጠብቅ ደንብሮ ሔደ።ወንዳ ወንዱ ቆፍጣናው ፍርሀትን የማያውቀው ቃለአብ ዛሬ ምን እንደነካው ለሱም ግልፅ አልሆነለትም ።ልቡ ፈርቷል ።
ሔዋንም መደነግጧ አልቀረም።በጣም እየፈራችው ነው ።ሰሞኑን ደግሞ ባህሪው ሁሉ ተለዋውጦባታል።በፊት ለምን ትደናበሪያለሽ ለምን አፈቅርሀለሁ ብለሽ እርፍ አትይም እያለ የሚያስደነብራትን እረስቶ እሱ መደናበሩን ተያይዞታል ።
ከድንኳኑ ጀርባ ከዋንዛው ዛፍ ስር ከተቀመጠበት ጎን ሔዳ ቁጭ አለች።
"ምነው ቃል በሰላም ነው የፈለግከኝ?"አለች ሔዋን
ቃል አልመለሰላትም እንዲሁ አይኗን ጠልቆ እየመረመራት ነው።
"ቃል ሰላም አይደለህም እንዴ?"አለች
"ሔዋን አዎ ሰላም አይደለሁም ሰላምም ልሆን አልችልም ።"አለ
"ምነው ያልተመቸህ ነገር አለ እንዴ? አባ ቶማስን አናግራቸው እሳቸው ችግርህን ይረዳሉ "አለች
"ሔዋን ነገሩን ዙሪያ ጥምጥም አትውሰጅው ችግሬን እውነት ሳታውቂው ቀርተሽ ነው?ከእውነታው ለመራቅ አትሞክሪ"አለ
"ለምን በግልፅ አታወራም እኔንም አስጨነቅከኝ እኮ"አለች
"ሔዋን ልቤን አማክሬው ውስጤን አድምጨዋለሁ እና ደመነፍሳዊ ሳይሆን ደግሜ ደጋግሜ ያሰብኩት ነገር ነው አ.ፍ..ቅ..ሬሻለሁ"የግዱን ተነፈሰ።
ሔዋን ከተቀመጠችበት ደንብራ ተነሳች።ደግሞ እንደገና ተቀመጠች
"ቃለአብ ይቅርታ ልብህን እንደገና አድምጠው ተሳስተህ እንዳይሆን "አለች
"ልቤማ የነገረኝ ለእኔ የመጀመሪያ ፍቅሬ እንደሆንሽ ነው"አለ
"ቃለአብ አይሆንም ስላፈቀርከኝ ግን አመሰግናለሁ ለልብህ ግን እህትህ እንደሆንኩ ንገረው"ብላ ተነስታ ልትሔድ ስትል እጇን ጎትቶ አስቀመጣት ።
"ለምን አይሆንም?"አለ
የጣቷን ቀለበት ከፍ አድርጋ አሳየችው እና"አየህ አሁንስ ይሆናል?"አለች
ቃለአብ እስኪበቃው ሳቀና "ሔዋን አንቺ እኮ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነሽ እንዴት ነው በዚህ እድሜሽ ቀለበት የምታስሪው?"አለ
"ሆነ" አለች
"ሔዋን ህፃን ነሽ ስልሽ ለጋብቻ እንጂ 18 አመት ሞልቶሻል ልክ እንደትልቅ ሰው እናውራ"አለ
"በላ ተናገር "አለች
"እንደምታፈቅሪኝ አቃለሁ ይሔ የሴት ወግ መግደርደር እንዳይሆንብሽ"አለ
ሔዋን ሳቀች እና "ጥሩ ትቀልዳለህ ሌላስ እምትቀልደው የለህም?"አለች
"ስታይኝ ትደናበሪያለሽ ብዙ ጊዜ ተደብቀሽም ስታይኝ ይዤሻለሁ ታዲያ ይሔ የፍቅር መገለጫ አይደለም እንዴ?"አለ
"እውነቱን ልንገርህ ፍቅረኛየ አንተን ስለሚመስል እንጂ በሌላ አይደለም። ቃለአብ በተሳሳተ መንገድ ነው የተረጎምከው።"አለች
"አይደለም ፍቅረኛየ ይሆናል ብለሽ ታልሚው የነበረን ልጅ ስላገኘሽ ነው"አለ
"ቃለአብ እንደዛ ነው ብየ አጉል ተስፋ ልሰጥህ አልፈልግም ልብህን ምከረው እና አደብ ሲገዛ እናወራለን"ብላው ሔደች ።
ቃለአብ ያለችውን ነገር መቀበል አልቻለም አልፈለገምም።ታፈቅረኛለች ዛሬ ባይሆንም ነገ የእኔ ነች በሚል አቋም ፀና።

"በመጀመሪያ ደረጃ የፕሮጀክታችንን ምንነት ምንም ሳታውቁ አባ ቶማስን ብቻ በማመን እዚህ አዳራሽ ውስጥ የቆያችሁ ወንድሞቼ እህቶቼ እንዲሁም ይሔ ማህበር እንዲቋቋም በእርጅና ዘመናቸው የእድሜያቸው ሁኔታ መሰናክል ሳይፈጥርባቸው ለዚህ ያበቁን አባ ቶማስን በአዲሱ ማህበራችን ስም ላመሰግኖት እወዳለሁ።እንግዲህ በሁለቱ የአባ ቶማስ ወንድሞች በአቶ ኢሳይያስ ተ/አረጋይ እና በአቶ ኤሊያስ ተ/አረጋይ ስም ይህንን መንግስታዊ ያልሆነ የእርዳታ ማህበር እንድናቋቁም መንግስት ፈቃዱን ሰጥቶናል።ስለዚህ ይህ ሴራሚክስ አምራቹ ግቢ እንደ ዋና ቢሮአችን እንጠቀምበታለን።የማህበራችን ስም በይፋ ባነር ተሰርቶለት ከግቢው በር ላይ ይሰቀላል።"ማህበረ ትጉሃን '"
እንደነገርኳችሁ ወረዳው የሰጠን የድሮ ሃኪም ቤት አለ አሱ ላይ ሶስት ብሎኮችን እያሰራን ነው።ብሎኮቹ ተጠናቀው ሲያልቁ የጉዳና ተዳዳሪዎችን አረጋውያንን እንሰበስባለን።ማህበረ ትጉሀን የአረጋውያን እና የወላጅ አልባ ህፃናት መርጃ ማዕከል ይሆናል።
ዋና አላማችን ግን ይህ ብቻ አይደለም።ይህን ምስጢራዊ ቦታ ለማንም ትንፍሽ ማለት ክልክል ነው ለራሳችሁም ቢሆን ደግማችሁ እንዳትነግሩት።ዋሻው ላይ የተደበቀውን ሀብታችንን በቀን ውስጥ አንድ ጊዜ መብላት የማይችሉትን እየመገብን ትምህርት ቤቶችን ሆስፒታሎችን እየገነባን የኢትዮጵያን ሀብት ለኢትዮጵያ ህዝብ እናውላለን።ከዛሬ ጀምራችሁ ሚስጥሩን በልባችሁ ይዛችሁ ለማህበረ ትጉሀን እውቀታችሁን ጉልበታችሁን ሳትሳሱ እንደምትለግሱ ቃል ገብታችሁ እንደ ማንኛውም ማህበረሰብ ኑሮአችሁን ከዚህ አዳራሽ ውጭ አድርጋችሁ ለማህበረ ትጉሃን እንደንሮጥ ስል አሳስባለሁ"አለ ምናሴ
በመቀጠል አባ ቶማስ ተናገሩ
"እንግዲህ ልጆቼ ምናሴ ሁሉን ነገር ተናግሮታል።አሁን የዚህን ዋሻ ምስጢር ጠብቃችሁ እንደምትኖሩ በዚህ መስቀል ላይ ማህላችሁን አስቀምጣችሁ ወደ እየመጣችሁበት ትሔዳላችሁ።ከዚህ በኋላ እዚህ አዳራሽ የምንገናኘው በስራ ሰዐት ብቻ ይሆናል"አሉ አባ ቶማስ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሁሉም የአዳራሹ ነዋሪዎች ቦርሳቸውን ይዘው ሲወጡ ሔኖክ፣ኢያሱ፣ምናሴ እና አባ ቶማስ ብቻ ቀሩ።
ሔዋን የግቢውን በር ከወጣች በኋላ ቀና ብላ የተሰቀለውን አዲስ ባነር ተመለከተች "ማህበረ ትጉሃን የእርዳታ ማህበር" ይላል።ፈገግ አለችና ወደ ቆመው መኪና ለመሔድ ስትንቀሳቀስ ከኋላዋ እጇን ቃል ጎተት አደረጋት።
"እንዴ ቃል ቀድመህ የሔድክ መስሎኝ ነበር?"አለች
"አይ አልሔድኩም።እኔ እምልሽ በዚሁ ለምን እኛ ቤት አንሔድም እናቴን አላስተወውቅሽም?"አለ ቃል
"አይ ይቅርብኝ በሌላ ጊዜ"አለች
"አይሆንም ካልሽ ምን አደርጋለሁ።እና ዛሬም አምቢታሽ ላይ ነሽ ?"አለ ቃል
"ቃል ምንም እሚቀየር ነገር አይኖርም ፍቅረኛየን በቅርቡ አስተዋውቅሀለሁ" ብላ በቆመበት ትታው ሔደች።
ሔዋን እቤቷ ደርሳ ለዮርዲ ለመደወል በጣም ጓጉታለች።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

ክፍል 17

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ዮርዳኖስ ኪሱ ውስጥ የሚንፈራፈረውን ስልኩን አውጥቶ ሲመለከት አይኑ ፈጥጦ ቀረ።ቃለአብ ነበር። ለብዙ ጊዜ ጠፍቶበት የቆየው ቃል ነበር የደወለለት።ዮርዳኖስ ተስገብግቦ ስልኩን አነሳው።
"ሔሎ ቃልየ አንተነህ"አለ ዮርዲ
"አዎ ወንድሜ እኔ ነኝ ዮርዲዬ ደህና ነህልኝ?"አለ ቃለአብ
ከቃለአብ ጋር ለብዙ ሰዓታት አወሩ።ራቅ ወዳለ ቦታ ሔዶ እንደሆነ እና ከዚህ በኋላ እንደማይጠፋበት ነግሮት ተሰነባበቱ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከደቂቃዎች በኋላ የዮርዲ ስልክ ደግሞ ተንፈራፈረ።አውጥቶ ሲመለከተው አዲስ ቁጥር ነው የቤት ስልክ።
"ሔሎ ማን ልበል?" አለ ዮርዲ
"ሰላምታ አይቀድምም የሚል ድምፅ ከወዲያኛው ጫፍ አስተጋባ"
ዮርዳኖስ ድምፁ አዲስ አልሆነበትም ግን ደግሞ ይሔን ድምፅ በዚህ ሁኔታ ላይ እሰማዋለሁ ብሎ ስላልጠበቀ ጆሮዬ ይሆናል ብሎ ተጠራጠረ እና "ይቅርታ የእኔ እመቤት ልክ ነሽ ሰላምታ ይቀድማል ሰላም ነሽ?"አለ
"የእኔ እመቤት? ዮርዲ ሔዋን እኮ ነኝ"አለች
ዮርዳኖስ በድንጋጤ ሁሉ ነገሩ ተንዘፈዘፈበት መቆም አቃተው እና አልጋው ላይ ዘፍ ብሎ ተቀመጠ።ልሳኑ ተሳሰረበት።ልቡ መምታት እስክታቆም ድረስ ፀጥ ያለች መሰለው።
"እንዴት ሊሆን ቻለ?አለ የግዱን አደቡን ገዝቶ
"ዮርዲ እሱ ብዙ ታሪክ ነው አሜሪካ አልሔድኩም ነበር"አለች
"ምን እና የት ሁነሽ ነው እየቀለድሽ አይደለም ሳልሳዊት ?"አለ
"ዮርዲዬ አምበር ነኝ ስትመጣ ሁሉን አጫውትሀለሁ'"አለች
ብዙ አወሩ አወጉ።ስልኩ ተዘጋ።
ዮርዳኖስ በደስታ ዶርሙን በጩኸት አናጋው።ተኝተው የነበሩት ሁለቱ ዮናሶች እና ናቲ ደንብረው ተነሱ።
"አንተ ያምሀል እንዴ ምንድን ነው እንደዚህ እማያስጮህህ"አለ ናቲ
"ዮኒዬ ሔዋን ደወለች እኮ ሳልሳዊት ደወለችልኝ" ብሎ ተንደርድሮ ሔዶ አቀፈው።
"እንኳን ደስ አለህ ጓደኛዬ ደስ የሚል ዜና ነው" አለ ዮኒ
"እና አሜሪካ ኑሮ እንዴት ነው አለችህ?አግብቻለሁ ምናምን አላለችም?አለ ዮኒ ጎጄ
"ገደል ግባ እሺ!ለማንኛውም አሜሪካ አልሔደችም አምበር ነች"አለ ዮርዲ ደስታ እየተናነቀው
"አትቀልዳ!እንዴት እንዲህ ይሆናል?እየቀለደችብህ እንዳይሆን? ደግሞ አፕሪል ዘፉል አልፏል"አለ ዮኒ
"እንዴት ሊሆን ቻለ ለሚለው ለእኔም እንቆቅልሽ ነው ነገር ግን እኔ እስኪገባኝ ድረስ ሔዋን እንደዚህ አይነት ቀልድ መቀለድ እንደማይመቻት ነው እማውቀው።"አለ ዮርዲ
"ስለዚህ የሆነ ነገር ይኖራል ጠርጥር ፣ጠርጥር" አለ ናቲ
"ባክህ ዝም በል።ይልቁንስ ይቺን የደስታ ቀናችንን ማክበር አለብን ምን ይመስላችኋል?"አለ ዮርዲ
"ደስ ይለናል ስለዚህ ለዞላ ይደወልለት ከቅምቀማ ቤት ይመለስ ዛሬ ኦቨር ነው"አለ ዮኒ ጎጄ
"ኦቨሩ ይብራብን እና በጊዜ አንድ ሁለት ብለን እንመለሳለን" አለ ዮኒ
"ስማ ይሔ ቀን ለእኔ ከልደቴ ቀን አይተናነስም ሁለት በህይወቴ ውስጥ ትልቅ ቦታ ያላቸው ሰዎች ናቸው ጠፍተው ከርመው የተገኙት ።ስለዚህ እንኦቭራለን"አለ ዮርዳኖስ
"ምነው ቃለአብም ተገኘ እንዴ" አለ ዮኒ
"እዎ ቃለአብ ከደወለ በኋላ ደግሞ ሔዋን ደወለች"አለ ዮርዲ
"ግን በአንተ ልብ ውስጥ ሁለት ትልቅ ቦታ ያላቸው ሰዎች የሆነ ሰዐት ላይ ጠፍተው ዛሬ ደግሞ በተመሳሳይ ሰዐት መደወላቸው ግጥምጥሞሽ ነው ብለህ አመንክ?"አለ ዮኒ ጎጄ
"ለምን አላምንም ምክንያቱም ቃለአብ እና ሔዋን አይተዋወቁም፣አረ እንዲያውም ከተፈጠሩ እንኳን ተያይተው ሁሉ እሚያውቁ አይመስለኝም"አለ ዮርዲ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ምሽት ላይ ጓደኛሞች ተሰብስበው ክለብ ገብተዋል።ከዜኖ ውጭ ።ምክንያቱም እንደዚህ አይነት ነገር ውስጡ አይደለም ።xo ክለብ በሙዚቃ እና በሚዉረገረጉ ወጣቶች ድብልቅልቅ እያለ ነው።ምሽቱም በዛው ልክ እየገፋ ነው።መጠጡ እዬተጠጣ ነው።ዮኒ እና ዮርዲ ብዙም እየጠጡ አይደለም የቡድኑ መሪዎች ናቸውና እነዞላን ተንከባክበው አልጋ ቤት ማድረስ አለባቸው።ናቲ እና ዮኒ ጎጄ መሰማማት አቅቷቸው በዛው ላይ መጠጡ ተደምሮ እየተጯጯሁ ነው።ዞላ ከጨፋሪዎች መሀል ገብቶ አንዴ ከአንዷ አንዴ ከአንዷ ጋር አብሮ ይውረገረጋል።በጣም እንደጠጣ አይኑ ያሳብቅበታል አይኑ ፈጧል።
ምሽቱ በጣም እየገፋ ጭፋራውም በዛው ልክ እየተጋጋለ በሔደበት ሰዐት ላይ ድንገት አንድ ሰው ተዝለፍልፎ ሲወድቅ ዮርዳኖስ ተመለከተ።

የማርዘነብ ግሮሰሪ እንደተለመደው ሲቀወጥባት አምሽታ አሁን እንቅልፍ እንቅልፍ ይላት ጀምሯል።ማርዘነብም ከወራት በኋላ የመጣላትን ልጇን ቃለአብን በእናት ወጉ ለማጫወት ስትሽለመለም የነበረችውን ግሮሰሪ አንደኛዋን እንድታሸልብ አስተኝታት ወደ ቃለአብ መጥታለች።ፀሐይም ያን ወፍራም ቡናዋን ቱግ ቱግ እያደረገች ሳሎን ከመንበሯ ላይ ጉብ ብላለች።እርግቤ ጓዳ ጉድ ጉድ እያለች ነው።
"እንደው ለመሆኑ አባ ቶማስ ለምን ጉዳይ ነበር እንደዚህ ደብቀውህ የከረሙት?"አለች ማርዘነብ
"እማ ስራ ሊቀጥሩኝ ነበር።እናም አዲስ የተከፈተ የእርዳታ ድርጅት ውስጥ ስራ አስጀመሩኝ"አለ ቃል።
"እንዴት ያለ ስራ ልጄ ?ገና ትምህርትህን እንኳን በወጉ ተምረህ ሳታበቃ?አለች ማርዘነብ በግርምት
"እሱን ተይው እና እማዬ አንድ ልጅ ወድጄ ግራ ገብቶኛል"አለ ቃል
"እሰይ እሰይ እሰይ አንድ ልጄ ለእኔም ወግ ደርሶኝ ምራት ሊያመጣልኝ ነው "አለች ማርዘነብ እጇን ወደፈጣሪ እየዘረገች
"ቃልየ ቆንጆ ናት?"አለች ፀሐይ ቡናውን እያቀበለቻቸው
"አንቺ ደግሞ ምን ማለትሽ ነው ይሔን የመሰለ ሸበላ እንዴት የማታምር ልጅ ያመጣል ብለሽ ነው?"አለች ማርዘነብ ።
"እሱስ ቆንጆ ወንዳ ወንድም ነው ሸጋዋን ነው መርጦ የሚያመጣት"አለች ፀሐይ
"አባቱም ወንዳ ወንድ ነው በአባቱ ነው የወጣው"አለች ማርዘነብ አምልጧት።
ታዲያ እዚህ ጋር ቃለአብ ፍሬን ያዘ።ምክንያቱም የዘመናት የአይምሮም ሆነ ከልሳኑ የሚወጣው ጥያቄ ነው።
"እማዬ ዛሬ ግን እንደ እስከዛሬው ተናደሽብኝ እኔም አኩርፌ ዝም ብየ አላልፍም አባቴ ማነው ፣ምንድን ነው ፣የት ነው የሚኖረው?"አለ ቃል ፍጥጥ ብሎ
የዛሬው ድርቀቱ የተለየ ነው እውነቱን ሳይሰማ ወደኃላ የሚል አይመስልም።
" በአፍ ይጠፉ በለፈለፉ አለ የአገሬ ሰው"አለች ማርዘነብ በሆዷ።"ቃልየ እሱን ጊዜ የሚፈታው ጥያቄ ነው እኔ አልነግርህም"አለች ማርዘነብ ለማስተባበል እየሞከረች
"እማዬ እናቴ ትሙት እውነቱን ካልነገርሽኝ ቤትሽን ትቼልሽ እጠፋለሁ"አለ በእናቱ ስም እየማለ።
ቃለአብ እንደዚህ ሲሆን አይታው የማታውቀው ማርዘነብ በዛሬው ሁኔታው ተደናገጠች።እርግቤና ፀሐይም ምን እንደሚፈጠር አድፍጠው እየተመለከቱ ነው።
ማርዘነብ ግራ ቢገባት "የት እምታውቀው አባትህ ነው የናፈቀህ?"አለች
"እማዬ ከአባቴ በላይ የአባቴ ልጆች ይናፍቁኛል "አለ ቃል
"አባትህ ልጅም እንዳለው እርግጠኛ ሆነህልኛል"አለች ማርዘነብ
"እማ በቃ እውነቱን ንገሪኝ በኋላ ይፀፅትሻል ደግመሽ አይኔን አታይኝም" አለ ቃለአብ
ማርዘነብ ዛሬ እንደማይለቃት አመነች።አማረጭ የላትምና ለመናገር ወሰነች ።
"እሺ የምነግርህን እስከተወሰነ ጊዜ ደብቀህ እንደምትቆይ ቃል ግባልኝ"አለች ማርዘነብ በረጅሙ ተንፍሳ።
ቃለአብ በእናቱ በማርዘነብ ስም ምሎ ቃል ገባላት።
"ልጄ የዛሬ አስራ ዘጠኝ አመት ገደማ መሆኑ ነው።ከበሽተኛዋ እናቴ ጋር ሻይና አረቄ እየሸጥን ነበር የምንተዳደረው።እና ታዲያ ከዚህ በፊት ይሔን ቤት እረግጦት የማያውቀው አባትህ ድንገት ተከሰተ።እዝን ብሎ አይኖቹ በእንባ ሞጭሙጨው እንዴት ያሳዝን ነበር መሰለህ።ማንንም አያናግርም የሚቀዳለትን አረቄ
ዝም ብሎ ይኮመኩማል።እንዴት አንጀቴን እንደበላው አትጠይቀኝ።እንዳጋጣሚ ሆኖ በበጋው ወር ታይቶ የማይታወቅ ዶፍ ዝናም አጥለቀለቀው።የሚያስፈራ ደግሞ የማያባራ ዝናብ።ምሽቱ ገፋ አባትህም አረቄውን እየኮመኮመ ሞቅ ብሎታል።በዝናቡና በሞቅታው ምክንያት አደረ።ተሳሳትን።"አለች ማርዘነብ
"እሺ ከዚያስ" አለ ቃል የሚፈጠረውን ለመስማት እየጓጓ
"ከዚያማ ጠዋት ሲነቃ አብረን ተኝተን ራሱን አገኘ።ደነገጠ።ከአልጋው ላይ ሳይወርድ ማንባት ጀመረ።
"ምነው ምን ሆነህ ነው"ስለው
አንድ ሴት ልጅ እንዳለችው እና የሚስቱ ቤተሰቦች በድህነቱ ምክንያት ልጁን እና ባለቤቱን እንደወሰዱበት ነገረኝ። እኔም አዘንኩ።ተለያየን።ከወራት በኋላ ማርገዜን አወቅኩ።አባትህን አፈላልጌ ማርገዜን ነገርኩት።በዚያ ሰዐት መሬት እንኳን ተከፍታ ብትውጠው ደስተኛ ነበር።ባለቤቱ መጥታ አብራው መኖር እንደጀመረች እና እርጉዝ እንደሆነች ነገሮኝ ሚስጥሩን ደብቄለት እንድቆይ እና የቻለውን ሁሉ እንደሚረዳኝ ቃል ገባልኝ።"አለች ማርዘነብ
"ለምን?"አለ ቃል
"አየህ በእኔ ምክንያት ትዳሩ እንዲበተንበት አልፈለገም።አንተም ተወለድክ።አባትህም ቀን ከሌት ህይወቱን ለመለወጥ ይተጋ ነበር።ከአመታት በኋላም ተሳካለት።ሀብታም ባይባልም መካከለኛ ገቢ ያለው ነጋዴ ሆነ።ለእኔም ይቺን ግሮሰሪ ከፈተልኝ።ነገር ግን ለባለቤቴ ከዛሬ ነገ እውነቱን ነግሬ ልጄን ከልጆቼ እቀላቅለዋለሁ እያለ ሳይሳካ ለዚች ቀን ደረስን።አሁን ግን አብቅቷል ትንሽ ቀን ብቻ ታገስ ጋሽ አድማሱ አማክረውት በቅርብ ቀን ብሏቸዋል።"አለች ማርዘነብ ።
ቃለአብም እህትና ወንድም እንዳለው ሲያረጋግጥ ያቺን ቀን ናፈቃት።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
‍ 😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 18

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ምሽቱ እየገፋ ጭፈራውም እየተጋጋለ በመጣበት ሰዐት ድንገት አንድ ሰው ተዝለፍልፎ ሲውድቅ ዮርዳኖስ ተመለከተ።ወለሉ በአንዴ በሚጠጣው ህዝብ ተከበበ።ቦግ እልም ሲል የነበረው መብራት ቀረና ኖርማል አምፖል በራ።ዮርዳኖስ ወደ መሀል እየበረቃቀሰው ገባና የወደቀውን ልጅ ሲመለከት የሱው ጉድ ነው።ሁዱን በእጁ ይዞ ያቃስታል።ደም ሆዱን የሸፈነበትን እጁን አምልጦ ዠረር ይላል።
ዮርዳኖስ በደመነፍስ ዞላየ ብሎ ከአንገቱ ቀና አደረገው ። ዞላ መናገር አልቻለም አፉ እየተንቀጠቀጠ ነው።አዎ ዞላ ማን እንደወጋዉ ሳይታወቅ በጩቤ ተዋግቷል ።
ሌሎችም ሁለቱ ዮናሶች እና ናቲ አምቡላንስ ጥሩ እያሉ ይጮሀሉ።ናቲ እና ዮናስ ጎጄ በድንጋጤ ስካራቸው በኖ ሄዷል።
xo ክለብ በአንዴ ድብልቅልቁ ወጣ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዞላ ደብረ ብርሀን ሪፈራል ሆስፒታል ሲገባ ራሱን ስቶ ነበር።በጣም ብዙ ደም ፈሶታል ።
ዞላ በገባበት ክፍል ውስጥ ብዙ ነርሶች እና ዶክተሮች ሲሯሯጡ ቆዩ።
ከደቂቃዎች በኋላ ዶክተሩ እነ ዮርዳኖስ ወደተቀመጡበት አመራ።ሁሉም ዶክተሩ የሚለውን ለመስማት ከተቀመጡበት በብርሀን ፍጥነት ተነሱ።
"ዶክተር እንዴት ነው?"አለ ዮኒ
"መጥፎ ሆኔታ እንደማይፈጠር ተስፋ አደርጋለሁ።ጩቤው ያን ያክል ዘልቆ ስላልገባ ፈጣሪን ልታመሰግኑ ይገባል"ብዙ ደም ስለፈሰሰው ደም ያስፈልገዋል ከእናንተ መሀል ወንድም አለው እንዴ ?"አለ ዶክተሩ ።
"አይ ወንድሞቹ እንኳን አይደለንም ግን እኛ ልንሰጠው እንችላለን"አለ ናቲ
"መልካም እንግዲያውስ ኑ ተከተሉኝ የደም ግሩፖችሁን እንወቅ እና ከእሱ ጋር የሚመሳሰል ካለ ደግ።ከሌለ ደግሞ ሌላ መፍትሔ እንፈልጋለን"አለ ዶክተር።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ደማቸው ሲመረመር የዮርዳኖስ ደም o ሆኖ ተገኘ።አስፈላጊውን ምርመራ አካሒዶ ደም ለመለገስ ዞላ ወደተኛበት ክፍል አመራ።ዞላ በሰመመን ውስጥ ነው።አልነቃም።
ዮርዳኖስ ዞላን ሲመለከት እንባው ጉንጩን እየዘለለ ዱብ ዱብ አለ።እራሱን እንደጥፋተኛ እየቆጠረ ነው።ዛሬ ጓደኛዬ ጉዳት የደረሰበት በእኔ ምክንያት ነው።እኔ እንኦቭራለን ብየ ባልገግም ኖሮ ይሄ ጉድ አይመጣብንም ነበር እያለ ያለማቋረጥ ፀጉሩን እየነጨ ነው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በነጋታው ዞላ ከቀኑ አምስት ሰዐት አካባቢ ነቃ።እነ ዮርዳኖስንም ተመስገን ብለው ምግብ ቀመሱ።
"ዞላየ እስኪ የሆንከውን ንገረኝ"አለ ዮኒ
ዞላም በተዳከመ ድምፅ ማውራት ጀመረ።
" ቅምቀማ ቤት ወስጥ ሞገስ እሚባል ልጅ ጋር ተጋጭተን ተፍቼበት ነበር።ሰዎች አገላግለውን ዝቶብኝ ነበር የሔደው።እናም ዳንሱ መሀል ተገናኘን።
አጅሬ ስፈልግህ አገኘውህ አለኝ
ምነው ምራቄ ናፈቀህ።በአንተ ምራቅ ሻወር ካልወሰድኩ አልጠራም አልክሳ ።አልኩት
አይ ዛሬ እኔ በደም እንድትታጠብ ላደርግህ ነው አመጣጤ አለኝ
አረ አታስቀኝ አሁን ልደንስበት ዞር በልልኝ አልኩት።ከዘያ በኋላ ሆዴን የሆነ ነገር ሲወጋኝ ብቻ ነው ትዝ እሚለኝ"አለ
ዮርዳኖስ"እኔ እነኝ እንደዚህ እንድትሆን መንስኤው እኔ እንውጣ ባልል ኖሮ እኮ አንተ እንደዚህ አትሆንም ነበር"አለ እያለቀሰ።
"ተው እንደዚህማ አትበል ከልጁ ጋር እኮ ተጋጭተናል ትላንት ባይሆንም ነገ ያሰበውን መፈፀሙ አይቀርም ነበር"አለ ዞላ

ማህበረ ትጉሃን ሶስቱ ብሎኮች ሙሉ በሙሉ እስኪጠናቀቁ ድረስ ከዚህ ቀደም የድሮ ሐኪም ቤት የነበሩት ብሎኮች ላይ ሰላሳ አካባቢ የሚደርሱ ከወረዳው ውስጥ እና ከወረዳው ውጭ የሰበሰቡአቸውን አረጋውያን ይዘው ስራ ጀምረዋል።ቃለአብም የሔዋንን ስልክ ከተቀበለ በኋላ ጠዋትም ማታም እየደወለ እንዲሁ ሲያወሩ ነው የሚውሉት።ሔዋንም ግራ እሚያጋባ ስሜት ውስጥ ገብታለች አትደውል ልበለው ትልና እንደገና ደግሞ ልቧ መቁረጥ አቅቶታል ።ልቧን ተጠራጥረዋለች።እኔ ዮርዳኖስ ብቻ ነኝ ቃለአብ ዮርዲን ስለሚመስል እደነግጣለሁ እንጂ ምንም የተለየ ነገር የለም ብላ ራሷን ለመሸወድ ብዙ ጊዜ ትሞክራለች።ነገር ግን እየሆነላት አይደለም በቃለአብ መነሁለል ጀምራለች ።አንድ ቀን እንዲያውም ቢሮ ውስጥ ሊሳሳሙ ሲሉ ድንገት ስልክ ጮሆ ረበሻቸው።
ቃለአብ ቢሮ ሆኖ እንደተለመደው ደወለላት።
"ሔሎ እመቤት ሔዋንን ፈልጌ ነበር"አለ
"ይቅርታ ለቦዘኔወች ጊዜ የላትም"አለች
"ማንን ነው ቦዘኔ ባክሽ "አለ
"እና ስራማ ቢኖርህ አትደውልም ነበር" አለች እየሳቀች።
"እሺ መቼም ሁልጊዜ ተሸናፊሽ ነኝ።አሁን ስራዬን ጨርሻለሁ አንቺስ ?"አለ ቃል
"ጨርሻለሁ"አለች ሔዋን
"እሺ በሩ ጋ ውጪ ሀሳብ አለኝ"አለና ስልኩን ዘጋው።
ሔዋን መጣች።መቼም ውበቷ እያደር እየጨመረ ነው የሚሔደው።"አንቺማ መቼም ቢሆን የእኔ ነሽ አልፋታሽም"አለ ቃል በልቡ
መጣች እና ጉንጩን ስማው "ሀሳብህ ምንድንነው?"አለችው
"ወክ እናድርግ ብየ ነው"አላት
"ደስ ይለኛል"ብላው ተያይዘው የጥንታዊ ቂርቆስን ኮረብታ መውጣት ጀመሩ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ኮረብታውን ወጥተው ጥንታዊ ቂርቆስን ከተሳለሙ በኋላ ወደታች ወረዱ።ወሩ ሚያዚያ አልቆ ግንቦት የገባ ቢሆንም ልክ ሰኔ እስኪመስል ድረስ የጣለው ዝናብ አካባቢውን በአረንጓዴ አሽቆጥቁጦታል።የዚባ ወንዝም ተርቦ የነበረውን ውሀ አግኝቶ መደንፋት ጀምሯል።
ከወንዙ ዳር ሔደው ተቀምጡ።ለብዙ ደቂቃ ያህል ራሳቸውን ሲያዳምጡ ከቆዩ በኋላ ቃለአብ ወደ ሔዋን ዘወር አለ።ቀለበቷን እያሽከረከረች እሩቅ ቦታ ሔዳለች።
ቃለአብ ቀለበቱን ሲያይ ተናደደ።
"ሔዋን እስኪ ልብሽን ከቀለበቱ አውጥተሽ አድምጭው"ብሎ ጮሆ ከሀሳቧ መለሳት።
"ቃለአብ ፍቅረኛየ እኮ"ብላ ሳትጨርስ አቋረጣት።ስለ ፍቅረኛዋ እንድታወራ እድሉን እንኳን ሰጧት አያውቀውም።ያንገሸግሸዋል።ስሙንም እንኳን አያውቀውም።
"እውነቱን ልንገርሽ ፍቅረኛሽ በቀለበት ስላሰረሽ እንጂ እኔን ግጥም አድርገሽ ታፈቅሪኛለሽ።ራስሽን ከቀለበቱ አውጭው።ልብሽን ተከተይ"አለ ቃለአብ
"እንደዛ አይሆንም አፈቅረዋለሁ"አለች ፍዝዝ ብላ
"እሺ እኔን አላፈቅርህም በይኝ።አይኔን እያየሽ አላፈቅርህም በይኝ" አለ ጮሆ።
ሔዋን ያንን ማለት አልደፈረችም አላፈቅርህም የሚለውን ቃል አንደበቷ ደፍሮ ሊያወጣው አልቻለም።በዝምታ ውስጥ ትኩር ብላ አይን አይኑን ብቻ ታየዋለች።
"አየሽ ታፈቅሪኛለሽ"ብሎ እነዛ ውብ ከንፈሮቿን ጎረሳቸው።ልትከለክለው አልደፈረችም።ሌላ አለም ውስጥ ገቡ።የማያውቁት መግነጢሳዊ ሀይል አስተሳስሯቸው።
።ከወንዙ ዳር ላይ ያለው የሸንበቆ ደን ውስጥ እንኳን ሲገቡ አላውቁትም።ተሳሳሙ።ተሻሹ።በቃ አበቃ።ድንግልና እንስሳዊ በሆነ መልኩ ደን ውስጥ ተወሰደ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ከሰዓታት በኋላ ሔዋን ቃለአብን በሙሉ አይኗ ማያት ከበዳት።ራሷን ጠላች ቃሌን በላሁ።ቃልኪዳኔን አጠፍኩ እያለች እንደ እብድ እየጮኸች ማልቀስ ጀመረች ።
"አየሽ ስለ ፍቅረኛሽ ሳይሆን ስለ ቃልኪዳንሽ ብቻ ነው አሁንም የምታለቅሽው።ሔዋን ጥፋተኛ ነኝ ብለሽ እንዳታስቢ በቃ ልብሽ ያለሽን ነው የተከተልሽው" አለ ቃለአብ።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 19

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ሁለተኛው ሴሚስተር ተጠናቆ እነ ዮርዳኖስ ወደ እየቤተሰቦቻቸው ለመሔድ ዛሬ የመጨረሻ ቀን ነች።እነ ዮርዳኖስ ዶርም አዲስ ተዓምር ተፈጥሯል።ዞላ በጩቤ ከተወጋ በኋላ አዲስ ሰው ሆኖአል ሱስ ለምኔ ብሎ አብረውት የነበሩትን ደባል ሱሶች አራግፎ አዲስ ህይወት አዲስ ምዕራፍ አዲስ እርምጃ በሚል መርህ ሙሉ ጊዜውን ለትምህርቱ እና ለጓደኞቹ ሰጥቷል።ሙሉ የዶርሙ ተማሪ ደስታ ተሞቷል ።የዮኒ ጎጄንም ምስጢር ተዘርግፏል።ቀን ያደረገውን ሁሉ ሌሊት ሲቃዥ የሚያድረው ዜኖ በእንቅልፍ ልቡ ሲቃዥ ናቲ ሰምቶ እርፍ።
እንዲህ ሆነ።
የእነ ዜኖ ክላስ ልጅ ገሊላ እምትባል ውብ የሆነች ልጅ አለች።ዮኒ ጎጄ ፍቅር የለም ሲል የነበረው ልጅ ወደዳት እና እርፍ።ከዚያም ዜኖ እና ገሊላ አንድ ክላስ ስለሆኑ ዜኖ የገሊላ ስልክ አለው።ዮኒ ጎጂ ቀለል አድርጎ ዜኖ የገሊላን ስልክ ስጠኝ ይለዋል።ዜኖም አንተ ምን አባህ ሊያደርግልህ።አለ ዜኖ። ዮኒ ጎጄም አንድ ጉዳይ ነበረኝ ስጠኝ ሲል።ዜኖ ምክንያት ካልነገርከኝ ብሎ ድርቅ ማለቱን ተከትሎ ዮኒ ጎጄም ምስጢር ነው እሺ እንዳትናገር የእነ ዮርዲን ፉገራ አልችለውም።ሳልወዳት አልቀርም ።አለ ዮኒ ጎጄ ።ዜኖም ስልክ ቁጥሯን ሰጠው ።
በማግስቱ ሁሉም የዶርሙ ተማሪዎች ቀን ላይ ተኝተው ናቲ አሳይመንት እየሰራ ነበር።ከዛም ዜኖ መቃዠት ጀመረ።
"እ.እ እእእእ ዮኒ ጎጄ ገሊላን ...እእእእ....ከልብህ....አፍቅረሀት .....አአአአአአ....ነው "እያለ የቃዠውን ናቲ ሰማ።
ማታ ሁሉም በተሰባሰቡበት ናቲ "አንተ ዮርዲ ገሊላን ታውቃታለህ እንዴ?" አለ።ሆን ብሎ ነበር እንደዛ ያለው።
ዮኒ ጎጄ ዜኖ ጋር አፈጠጠበት።ዜኖም "ማርያም ዮኒ ጎጄ አልተናገርኩም" አለ።
"ምንድንነው የምታወሩት" አለ ዮርዲ ግራ ተጋብቶ።
ናቲ ሁሉንም ነገር ዝርግፍ አድርጎ ተናገረ።በዮኒ ጎጄ የተወሰነ ቀን ከሳቁበት በኋላ ሁለቱን አንድ የማድረግ እቅድ ነድፈው መንቀሳቀስ ጀመሩ።ገሊላ ቀድማ በዮኒ ጎጄ ታማሚ ሆና አገኟት። እቅዳቸው ሰመረ።ፍቅር የለም እያለ ቱሪናፋውን ሲነፋ የነበረ ልጅ በፍቅር አለም ሰጠመ።በፍቅር አክናፍ በረረ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"ዮርዲዬ በቃ ነገ እኮ አገር ቤት ልትገባ ነው።ናፍቆትህንም ልታገኛት ነው"አለ ዮኒ
"ምን ባክህ ሔዋን ምን እንደነካት አላውቅም ስልክ አትደውልም ስደውልላትም ደስተኛ አይደለችም ደስ ሲላትም ስልክ አታነሳም"አለ ዮርዲ እዝን ብሎ
"ምነው አለች?"አለ ዮኒ
"እኔ እንጃ ልቤ ፈርቷል።ውስጤ ተረብሿል የሆነ ነገር እንደሚፈጠር እየነገረኝ ነው።ለመልካም ይሁን እንጂ "አለ ዮርዲ
"ፈጣሪ የፈቀደው ነው እሚሆነው።ለማንኛውም ልቦለድህን እንዴት እንደወደድኩት አትጠይቀኝ"አለ ዮኒ
"አረ እውነትህን ነው"አለ ዮርዲ
"እውነት ለማንኛውም ኮሜንት ፅፌ ውስጥ አስቀምጬልሀለው "አለ ዮኒ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እነ ዮርዳኖስ ዮኒቨርስቲ ላይ አንድ አመት በፍቅር በመተሳሰብ አስቆጥረው ወደ እየቤተሰቦቻቸው ተበታተኑ።ዮኒቨርሲቲ ህይወትን ተምረውበታል።ልዩነትን ውበት አድርገው በአንድነት ከሌሎች ብሔሮች ጋር ዘምረው።ባህል ወግ ቋንቋን አካፍለው ከሌሎች ደግሞ ቀስመው።ማህበራዊነትን መቻቻልን ከትምህርታቸው በበለጠ ተምረው ሔዱ።


ዮርዳኖስ ሲጓዝ ውሎ አመሻሽ አስራ ሁለት ሰዐት አካባቢ ነበር የገባው።በጉዞው በመድከሙ የተነሳ ቤተሰቦቹን እንኳን በቅጡ አላጫወታቸውም።ሻወር ወስዶ እራት እንደነገሩ ከቀማመሰ በኋላ ክፍሉ ገብቶ ተኛ።ሰላም ያለው እንቅልፍ ወሰደው።የንጋት ጎህ ተቀዶ የወፎች ዝማሬ እና የጊወርጊስ ቤተክርስቲያን ጥዑም የቅዳሴ ዜማ በአንድነት ተደምሮ ዮርዳኖስን ቀሰቀሰው።አልተናደደም ።ምክነያቱም እልፍ አዕላፍ ህዝብ በሁካታ በግርግር በኑሮ የትግል ሽኩቻ ውስጥ ሲዋከብ ውሎ የደከመ ጎኑን ለማሳረፍ ወደቤቱ ሲገባ የክለብ ዳንኪራ ጩኸት፣የግሮሰሪዎች ክፍት አፍነት፣የመሸታ ቤቶቹ ከአቅም በላይ ጫጫታ፣የባህል ምሽቶች አፈኛ አዝማሪ አላስተኛ ብለውት ሲገላበጥ አምሽቶ ሲነጋጋ ደግሞ በቁርስ ቤቶች ሙዚቃ የሚቀሰቀሰውን ምስኪን ህዝብ ማሰብ በቂ ነው። ዮርዲ ግን ለብዙ ወራት ሲናፍቀው የከረመው የጊወርጊስ ጥዑመ ዜማ ነው ያባነነው።እድለኛ ነው።
ፊቱን ታጠበና ቅዱስ ጊወርጊስን ተሳልሞ ሊመለስ ወደ ጊወርጊስ ሔደ።ከቤተሰቦቹ ጋር በሰላም ያገናኘውን ቅዱስ ጊወርጊስን አመስግኖ ከተመለሰ በኋላ ቁርስ ከቤተሰቦቹ ጋር ተመግቦ ወደ እነ ሔዋን ቤት አመራ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፧፧፧፧፧፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዲ ለሔዋን እና አባት ሰላምታውን አቅርቦ አብርሀምን ከልብ በመነጨ ፍፁም ወንድማዊነት በተሞላበት አስተቃቀፍ አቀፈውና ሰላምታ ሰጥቶት ተቀመጠ።
ሔዋን ፍለጋ አይኑን ቢያማትርም ሔዋንን ሊያያት አልቻለም።
"ምነው መምጣትህን እኮ ሔዋን አልነገረችንም"አለ አቶ አንድነት
"አዎ ስደውልላት ስልክ አታነሳም ነበር"አለ ዮርዲ
"ስራው አጨናንቋት ይሆናል"ብሎ አቶ አንድነት ወንድሟ ምናሴ ከአሜሪካ ተመልሶ አዲሱ የእርዳታ ድርጅት ውስጥ ተቀጥረው መስራት እንደጀመሩ ነገረው።
፨፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ ከእነ ሔዋን ቤት ከተመለሰ በኋላ ለሔዋን ደወለላት እና መምጣቱን ነገራት።ምሳ ሰዐት ላይ ስትመለስ እንደምትደውልለት ነግራው ስልኩን ዘጋችው።ሔዋን መምጣቴን ስትሰማ በደስታ እየጨፈረች ትመጣልኛለች ብሎ የጠበቀው ዮርዲ በተቃራኒው ሲሆን የሆነ ዝብርቅርቅ ያለ ስሜት ውስጡን ወረረው።
ቃለአብ ላይ ደወለለት እና መምጣቱን ሲነግረው።የት ልምጣ ዮርዲዬ አለ ለማግኘት እየቸኮለ። ቴሌው ጋር እጠብቅሀለሁ አለ ዮርዲ።ይሔው ተነሳሁ አለና ቃል ስልኩን ዘጋው።
ዮርዲ ሔዶ ቴሌው ፊት ለፊት ካለው የቲቪ ፓርክ መቀመጫ ላይ ተቀመጠና ቃልን በጉጉት መጠበቅ ጀመረ።ባለብስክሌቱ ቃለአብ ብስክሌቱን እያበረረ መጥቶ ዮርዲ አቀርቅሮ በተቀመጠበት ቦታ ላይ ዱብ አለ።ዮርዲ ቃል ከሰማይ የተከሰተ መሰለው።ሲያየው በፊት ይረበሽ እንደነበረው አሁንም ያ ስሜቱ አልተወውም ልቡ መታች።ቃል እቅፍ አደረገው ዮርዲም አቀፈው።ለደቂቃዎች ያህል ተቃቅፈው ከቆዩ በኋላ ቃል ዮርዲን ቀና አደረገውና ግንባሩ ላይ ሳም አደረገው። ተቀምጠው አወሩ አወጉ።ናፍቆታቸውን አይን አይን እየታያዩ ተወጡ።ቃለአብ ትምሀርት አቁሞ የእርዳታ ድርጅት ውስጥ ተቀጥሮ እየሰራ እንደሆነ ነገረው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
"ዮርዲዬ ዛሬ ማዘሪቱን አስተዋውቅሀለሁ ተነስ እንሒድ"አለ
"አንተ ያምሀል እንዴ እኔ ትልቅ ሰው በጣም ነዉ እምፈራው።ደግሞ ምንድነው ብለህ ነው እምታስተዋውቀኝ"አለ ዮርዲ
"ዮርዲ ወንድሜ እኮ ነህ ።ምን ብየ እንዳስተዋውቅህ ነበር የፈለግከው?አሁን በል ተነስ"ብሎ ቃለ አብ ድርቅ አለ።
ዮርዲ እና ቃለአብ ግራና ቀኝ ሁነው ብስክሌቷን እየገፉ ወደ እነ ቃል ቤት አመሩ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ማርዘነብ ግሮሰሪ እንደደረሱ "ይቺ ናት ግሮሰሪያችን መተዳዳሪያችን።"አለ ቃል።
ከግሮሰሪው ጎን ባለው የግቢያቸው በር ወደ ዋናው ቤታቸው ዮርዲን ይዞት ገባ እና ቤት አስቀምጦት ወደ ግሮሰሪው ማርዘነብን ለመጥራት ገባ።
"እማዬ ዛሬ ወንድሜ ነው እያልኩሽ የነበረውን ጓደኛዬን አስተዋውቅሻለሁ።"ብሎ ወደቤት ማርዘነብን እየጎተተ ይዟት ገባ።
ማርዘነብ ዮርዲን እንዳየችው በድንጋጤ ክው ብላ ቀረች።መደንገጧ እንዳይታወቅባት "እእ......እ..አንተ ነህ የቃል ጓደኛ?"አለች የግዷን ፈገግ ብላ።
"አዎ እኔ ነኝ ዮርዳኖስ እባላለሁ" ብሎ ሰላም አላት
ማርዘነብ እሚበላ ነገር አቅርባላቸው።የሚፈልጉትን ከፍሪጁ እንዲጠቀሙ ነግራቸው።በሉ ተጫወቱ ደንበኛ አለብኝ ብላ በተረበሸ ስሜት ውስጥ ሆና ወደ ግሮሰሪው ገባች።
"እርግቤ ስልኬን ስጭኝ" አለችና ማርዘነብ ቃለአብ አባት ላይ ደውላ
"እየውልህ ትዳርህን የሚበትን ዜና ልንገርህ ልጆቹ ተዋውቀዋል እንዴት እንደሆነ አላውቅም የኔው ቃለአብ ጓደኛዬ ነው ብሎ ቤት ድረስ ልጅህን ይዞት መጥቷል"አለች ማርዘነብ ድንጋጤዋ አሁንም አለቀቃትም።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 20

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ቃልና ዮርዳኖስ እስከ ስድስት ሰዐት ድረስ ሲጫወቱ ከቆዩ በኋላ ስድስት ሰዐት ላይ ሔዋን ደወለች።ሚስቴ ነች የደለወለችው ቃል አንዴ ላናግር አለ ዮርዲ በሹፈት ቃለአብን እያስፈቀደው።
"ሔሎ ሳልሳዊት"አለ ዮርዲ
"ዮርዳኖስ ከስራ ወጥቻለሁ ላግኝህ"አለች
ዮርዲ በሙሉ ስሙ ጠርታው የማታውቀው ልጅ ዮርዳኖስ ብላ ስትጠራው መገረሙ አልቀረም "አሁን ራቅ ብያለሁ ግን በ 40 ደቂቃ ውስጥ እደርሳለሁ እደውልልሻለሁ ፍቅር"ብሎ ስልኩን ዘጋው።
"በል ና ሸኘኝ"አለ ዮርዲ
ዮርዲ ማርዘነብን አመስግኖ በድንጋጤ ላይ ሌላ ድንጋጤ ጨምሮባት ወጣ።
ቃለአብ እየሸኘው "ስማ ሚስትህን መች ነው እምታስተዋውቀኝ"አለ ቃል
"እንዴ አታስብ፣ይልቁንስ በስልክ አንድ ልጅ እንደወደድክ ነግረኸኝ ነበር አለ"ዮርዲ ለወሬ መጀመሪያ
"አረ ተወው ዮርዲዬ ባክህ ፍቅረኛ አላት"አለ ቃል
"እና ፍቅረኛ ካላትማ......"ሲል ዮርዲ ቃለአብ ከአፋ ነጠቀው
"አዎ ፍቅረኛ አላት ግን ደግሞ ታፈቅረኛለች"አለ ቃል
"ማለት እስኪ ግልፅ አድርገው ?"አለ ዮርዲ
"ስማ እኔ እንጃ ከስንቱ እንደምመሳሰል።ይኸው ከአንተ ጋር እመሳሰላሁ።ከልጅቷ ፍቅረኛም ጋር እንደዚሁ"አለና ፈገግ ብሎ ቀጠለ "እየውልህ ልጁን ትወደዋለች እንደምታፈቅረው ግን እንኳን እኔ እሷም እርግጠኛ አይደለችም።እኔን ደግሞ በእርግጠኝነት ታፈቅረኛለች።እሱ በቀለበት አስሯት እንጂ ልቧን በፍቅር አላሰረውም"አለ ቃል
"እና ልጁ ይህን ያውቃል"
"አይመስለኝም"አለ ግን አንተ ምን ትመክረኛለህ?"አለ ቃል
"ምን መሰለህ እውነት ነው እማታፈቅረው ከሆነ ቃልኪዳን አለብኝ ብላ አብራው መሆን የለባትም።እንዲያውም ትልቅ ሀጢያት የሚሆንባት ሌላ ማፍቀሯ ሳይሆን ሳታፈቅረው ለቃልኪዳን ብቻ ብላ አብራው ብትሆን ነው።ግን እውነቱን ለልጁ መነገር አለበት" አለ ዮርዲ
"ልክ ነህ"አለ ቃል ንግግሩን እንዲቀጥል በሚገፋ መልኩ
"አየህ አንዳንድ ሰዎች በአመታት አብሮ መኖር ውስጥ መላመድን ይፈጥሩና የምር የተፋቀሩ መስሏቸው ፍቅር ይመሰርታሉ አልፎም ትዳር ይመሰርታሉ።ነገር ግን ትዳራቸው አይሰምርም።ምክንያቱም ልባቸው ውስጥ ያለው ፆታዊ ፍቅር ሳይሆን የእህትና የወንድምነት አይነት ሆኖ አልጋም ላይ ሆነ ኑሯቸው ላይ ስሜት አልባኝነት ይፈጠራል።ምን አልባትም አንተ የምትለኝ ልጅ ላይ ያለው ነገር ይሔ ሊሆን ይችላል።ነገር ግን ልቧን አድምጣ ልቧ የሚላትን ለመከተል እንዲበጃት ጊዜ ስጣት" አለ ዮርዲ
"ልክ ብለሀል እሷም ይሔንን ነው ያለችኝ ጊዜ ስጠኝ አትቅረበኝ ብቻየን ሆኘ ማሰብ እፈልጋለሁ ነው የለችኝ"አለ ቃል
"ጥሩ ነው ይሳካልህ ወንድሜ ደስታህ ደስታዬ ነው።ለማንኛውም ደሳለኝ ነገ ይመጣል።ነግሮሀል?"አለ ዮርዲ
"ደውየለት ነበር እኔም መምጣቱን በጉጉት እየጠበኩ ነው"አለ ቃል።
ቃለአብ ዮርዲን ግማሽ መንገድ ከሸኘው በኋላ በል ሚስትህን አግኝ ወንድሜ ነገ አብረን ደሴን እንቀበለዋለን ብሎ ተሰናብቶት ተመለሰ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሔዋን እና ዮርዲ ፍቅራቸው ፈገግ ብሎበት በነበረው ዋርካ ላይ ሔደው አረፍ አሉ።ዮርዲ ሔዋን ላይ ብዙ የተቀየሩ ነገሮች እንዳሉ ታዝቧል።ቀለበቱ ከእጇ ላይ የለም ሀብሉ ከአንገቷ ላይ የለም።ደንግጦ ሲጠይቃት ጠፋብኝ አለች።እውነታው ግን ከዛ የራቀ ነው።ግራ ተጋብታ መወሰን አቅቷት ነው።የዮርዳኖስን ቃልኪዳን ቃለአብ ሰብሮታል።በቃለአብ ፍቅር የዮርዳኖስ ቀለቀት ከሔዋን እጅ ላይ አፈትልኮ ወደቀ።ይህ ነው እውነታው።
ሔዋን ግራ ተጋብታ ግራ እያጋባችው ነው።የጠየቃትን እረስታ ሌላ ትመልሳለች በራሷ አለም ውሰጥ ንጉድ ብላለች።"ዮርዲ ብዙ የሆነልኝ ንፁህ አፍቃሪየን ቃሉን በላሁ።ከፊቱ መቆም የማይገባኝ ርካሽ ሰው ነኝ ትልና ደግሞ እንደገና ልቤ የፈቀደውን ነው የመረጥኩት ምን አጠፋሁ" እያለች አራሷን እየሞገተች ከዮርዳኖስ ጋር አካሏ አለ እንጂ መንፈሷ ጭልጥ ብሎ ሔዷል።
"ሔዋን ምን ሆነሽ ነው?"ብሎ ዮርዲ ከሀሳብ መለሳት ።
"ልክ ነኝ አይደል አዎ ትክክለኛ ውሳኔ ነዉ"አለች ያልተጠየቀችውን
"እንዴ ሒዊ ምንድነው የሆንሽው?አሞሻል እንዴ?"አለ ዮርዲ
"አየሰ ስለ ስራ እያሰብኩ ነው"ደና ነኝ አለች
"እንደዚህ እስክትሆኝ? እምትሰሪ እኮ ለስጋሽ ነው።ስራው ከአንቺ ይበልጣል?መተው አለብሽ"አለ ዮርዲ እየተጨነቀ
"ዮርዳኖስ ደና ነኝ አታስብ"አለች
ይሔ ሙሉ ስሙን መጥራቷ ቢከፋውም ዋጥ አድርጎ "ሒዊ ያኔ ስትሔጅ የሰጠሽኝን ስጦታ ሀብል አንቺ አንገቴ ላይ እስክታጠልቂኝ ድረስ እጄ ጋር ነበር።አሁን አንቺ ታደርጊልኛለሽ"አለ በፍቅር አይን አይኗን እያየ
"አይ እጅህ ጋር ያምራል እንዲሁ ይቀመጥ"አለች
"እሺ ታዛዥ ነኝ እመቤቴ" ብሎ ሊስማት ሲጠጋ ጉንጯን ሰጠችው
እሷም ደስ እንዲለው ብላ ጉንጩን ሳመችው እና በል ወደ ስራ መሔድ አለብኝ ሰላሳ ደቂቃ አሳልፊያለሁ አለች ለመሄድ እየተነሳች....

አቶ ተሾመ ከደብረ ማርቆስ ከተመለሰ በኋላ ምንም ጥሩ ስሜት እየታየበት አይደለም።ከራሱ ጋር ያወራል።ወይዘሮ አለም ምን ሆነህ ነው ስትለው መልስ አይመልስም።አረ እንዲውም ዘግቷቸዋል።የማታ ማታ የግዱን "አንተ ዮርዲ ከደሴ ውጭ ሌላ ጓደኛ አለህ አይደል?አለ አቶ ተሾመ
"አባየ ከጓደኛም በላይ ወንድሜ ነው።ቃለአብ ተሾመ ይባላል የሚገርመው ያባታችን ስም ብቻ አይደለም የሚመሳስለው መልካችን እና የተወለድንበት ቀን ወር እድሚአችንም ሁሉ ተመሳሳይ ነው"አለ ዮርዲ ከስልኩ ላይ የቃልን ፎቶ እየፈለገ።
አቶ ተሾመ የበለጠ ተረበሸ።
"አባዬ ምነው ልጁን ታውቀዋለህ እንዴ?መጥፎ ልጅ ነው?ለምን ተረበሽክ?"አለች ቤዛ
አቶ ተሾመ ግን ምንም መልስ አልሰጠም።ዮርዲም ከስልኩ ላይ የቃልን ፎቶ እያሳየው "እየው እስኪ አንመሳሰልም?"አለ ዮርዲ
"እሚገርም ነው ወንድማማቾች ነው እምትመስሉት።የት ነው የተዋወቃችሁ?" አለ አቶ ተሾመ
"በህልሜ ነው አባ ቤዛ ይሔ መንታ ወንድምህ ነው ብላ አስተዋወቀችኝ።ከዚህ በፊት አላውቀውም ነበር ከዛም ተዋወቅን እሱም ወንድሙ እንደምመስለው ነገረኝ"አለ ዮርዲ
"ፃድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ ማለት ይሔ ነው"አለ አቶ ተሾመ
"አንተ ሰውየ ምን ሆነሀል ድካም ነው በቃ ግባና አረፍ በል"አለች ወይዘሮ አለም።
"አይ ግዴለም ይልቁንስ አሁን የፊታችን እሁድ እንግዶች ይመጡብናል ተዘጋጁ አለምየ"አለ አቶ ተሾመ
"የምን እንግዳ?"አለች ወይዘሮ አለም
"እሱ ይሰደርሳል እናተ ተዘጋጁ"አለ
"እኔ እምለው ቆይ የኔና የሔዋንን ፎቶ ከሳሎን የት አደረሳችሁት"አለ ዮርዲ
"ምን ቤዛ ስታፀዳ ተሰበረ ምኝታ ቤት ቁም ሳጥኑ ጋር አለ"አለች ወይዘሮ አለም
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ማህበረ ትጉሃን ቢሮ ውስጥ ብዙ አዳዲስ ሰዎች እየገቡ ነው።ስራቸውን እያጧጧፉ ነው።በወረዳው ወስጥ ሶስት ሀይስኩሎች በማህበረ ትጉሀን እየተገነቡ ነው።በተሰጣቸው ቦታ ላይ ብሎኮችን ጨምረው ገንብተው ወደ ሶስት መቶ የሚደርሱ አረጋውያንን እየጦሩ ነው።ወላጅ አልባ ዘጠና ህፃናትን ይዘዋል።በመጭው መስክረም ትምህርት ሊያስገቧቸው እቅድ ይዘዋል።በትግራይ ክልል በድርቅ ለተጎዱ አካባቢዎች አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ብር እርዳታ ሰጥተው በፌዴራል ደረጃ የምስጋና ምስክር ወረቀት ተበርክቶላቸዋል።ሁሉም አባል ፍፁም በሆነ ታዐማኒነት እና በፍቅር ነው እሚሰራው።
ምናሴ እርዳታ እሚሰጥባቸውን አካባቢዎች ለማጥናት ከሔኖክ ጋር መላ ኢትዮጵያን እያካለለ ነው።
"እንዴት አደርሽ ሒዊ"አለና ቃል ጉንጯን ሳም አደረጋት
"ቃል እንዴት ነህ?"አለች ኮምፒውተሩ ላይ
እንዳፈጠጠች
"እኔ እምልሽ ምን አዲስ ነገር አለ እረሳሽኝ እኮ"አለ ቃል
"እንዴት ብዬ ልርሳህ ብረሳህማ በምን እድሌ"አለች
"ሔዋን አትቀልጂ"አለ ቃል
"እውነቱን ልነግረው እያሰብኩ ነው"አለች
"ቃል ደስ አለው የኔ ፍቅር እንኳንም የኔ ነሽ።"አለ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ምሳ ሰዐት ላይ ዮርዲ ሔዋንን ምሳ ሊጋብዛት ደመቀ ሬስቶራንት ቀጥሯት ቀድሞ እየጠበቃት ነው።
ሔዋን መጣችና ሰላም ብላው ተቀመጠች።ምሳ እየበሉ "እኔ እምልህ ዮርዳኖስ ከአንተ ሌላ ፍቅር ቢይዘኝ ምን ትሆናለህ?"አለች እየሳቀች
"ምንም አልሆንም ምክንያቱም ያ አይሆንማ"አለ ዮርዲ
"ቢሆንስ?"አለች
"ከሆነማ መርቄ እልል ብዬ ነው የምሸኝሽ ከእኔ የተሻለ አግኝተሽ ወይም መጀመሪያውኑ አታፈቅሪኝም ነበር ማለት ነው።"አለ
"አትቀልዳ" አለች ኮስተር ብላ
"እውነቴን ነው ልብሽ እኔ ጋር ሳይኖር በድንሽ አብሮኝ እንዲኖር አልፈልግም?"አለ ዮርዲ
አንጀቷ እንጥልጥል አለባት አሳዘናት እውነቱን እንዴት እንደምታሸክመው ጨንቋት ርዕስ ቀየረች።"ሀምሌ አስራ ሁለት ውድድር አለብህ አለች"ሔዋን
"እህ የምን ውድድር?"አለ ዮርዲ
"የወሰድኩትን የግጥም ደብተርህን ለውድድር አስገብተነው ወረዳ ወክሎ ለዞን እንዲወዳደር ተመርጧል"አለች
"አረ ደስ ይላል"አለ ዮርዲ የእውነት ደስ ብሎት
"ሁሉንም ዙሮች ያሸነፈ በኢፌዴሪ ባህልና ቱሪዝም ስፖንሰርነት ለህትመት ይበቃል ማለት ነው"ብላ ትልቅ የምስራች ነገረችው...


ይቀጥላል....

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
ሽ የሚነሳ ነገር አይደለም"አለምየ ይቅርታ አድርጊልኝ" አለ ከጉልበቷ ሳይነሳ።ከአባ ውጭ ሌላው ሰው በሙሉ ግራ ተጋብቷል
አባም በግንባራቸው ለወይዘሮ አለም ተግሳፅ ሰጡ።
"እንዴ ምን በደልከኝ እና ይቅርታ ትጠይቀኛለህ"አለች
"ይቅርታ አድርጌልሃለሁ ካላልሽ በፍፁም አልነሳም"አለ
"አሺ ይቅርታ አድርጌልሃለሁ"አለች ግራ ተጋብታ
አባም አቶ ተሾመን ወክለው በምክር እያዋዙ በተግሳፅ እያለዘቡ መጨረሻ ላይ እውነታውን ዘረገፉት።ለአመታት ተደብቆ የኖረ ጎረምሳ ወንድ ልጅ እንዳለው ተናገሩ።ወይዘሮ አለም መብረቅ የወረደባት ያክል በድንጋጤ ድርቅ ብላ ቀረች።ቤዛም ደንግጣለች።ዮርዳኖስ ደንግጧል ግን ደግሞ ወንድም እንዳለው ሲሰማ ደስ ብሎታልም።እልፍነሽ በመገረም ጭንቅላቷን ትነቀንቀዋለች።
ወይዘሮ አለም የስሜት ህዋሳቶቿ እየተነቃቁ ሲመጡ ትቀውጠው ጀመር።"ተሾመ አንተ በእኔ ላይ ሔድክ በእኔ ላይ ሌላ ሴት ተኛህ።"እያለች ሳሎኑን ትንጎራደድበት ይዛለች ።
አባም ተቆጥተው አስቀመጧት እና"ተይ ልጄ አስቦበት አይደለም አባትሽ ድህነትነቱን ነግረው ከእነ ልጁ ነጥቀው ሲወስዱበት ብቸኝነቱን አልችለው ብሎ በመጠጥ ሀይል ወደቀ።ልጄ ተይ እንደዚህ አትሁኝ"አሉ ተቆጥተው ።
ወይዘሮ አለም ተለያይተው በነበረበት ሰዐት መሆኑን እና እሷ እያለች ሔዶ አለመሆኑን ስትሰማ ትንሽ ሆዷ ውስጥ ሲነድ የነበረው እሳት መጥፋት ጀመረ።
"አባም ይቅር ሰንል ነው ይቅር የምንባለው እያሉ" ሲመክሯት አምሽተው አረጋግተዋት አቶ ተሾመን ከልቧ ይቅርታውን እንድትቀበል አድርገው ነገ ልጅ እና እናት መጥተው እንደሚተዋወቁ ተናግረው ሔዶ።
ወይዘሮ አለም ከሁሉም ሰው ቀድማ ገብታ ተኛች።ዮርዲ ደግሞ ወንድሙን ለማወቅ ጓጉቶ ሲያስብ አመሼ።ቤዛም ምን አለበት ሴት በሆነች ማለቷ አልቀረም ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እሁድ ከሰዐት በኋላ ......................................
ቃለአብ ዝንጥ ብሏል የሚለው ቃል አይገልፀውም።አረ እማዬ ምንድን ነው ምስራቹን ንገሪኝ አለ።
"ወይ አንተ ደግሞ፤በቃ እሺ አባትና እህት ወንድምህን ልትተዋወቅ ነው"ብላ አበሰረችው
"ቃለአብ በደስታ ዘሎ እናቱ ላይ ተጠመጠመባት።ጉንጯን እያገላበጠ በደስታ ሳማት።
ከሁሉም በላይ ወንድሙን ለማወቅ ቋመጠ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
እነ ወይዘሮ አለም ቤቱን ሞቅ ደመቅ አድርገው ምግቡን በእየፈርጁ ሰርተው እንግዶቹን እየጠበቁ ነው።ዮርዲም እንደ ቤተሰብ አባል የሚቆጠረውን ደሴን እውነቱን ነግሮት ከዮርዲ ጋር እሚሆነውን እየጠበቁ ነው።
በር ተንኳኳ ሁሉም ከመቀመጫቸው ተነሱ።እልፍነሽ በሩን ከፈተች።እናት እና ልጅ ገቡ ።ሳሎን በር ላይ እንደደረሱ ቃለአብ ከዮርዳኖስ እና ከደሴ ጋር አይን ለአይን ተጋጨ።ዮርዲ ድንገት ልቡ ቀጥ ስትል ተሰማው።በህይወት ዘመኑ እንኳን ይሔንን ያክል የደነገጠበትን ቀን አያስታውስም።ቃለአብም ልቡ ከዳችው ደነገጠ ልቡን በእጁ ያዘ።ደሴ የዮርዳኖስን ህልም እና ወንድማማችነት እያያያዘ አግራሞት ተሞልቷል።
ዮርዳኖስ ሮጦ ቃለአብ ወንድሜ አለ ቃለአብም ዮርዲዬ አለ ተቃቀፋ።ህልም አይደለም አይደል ቃል አለ ዮርዲ ።አንተን ልጠይቅህ ወንድሜ እየቃዠሁ አይደለም አለ ጥያቄውን በጥያቄ እየደገመ።
ሙሉ ቤተሰቡ ተዋወቀ።ቃለአብ ተሾመ እና ዮርዳኖስ ተሾመ ከሁለት ማህፀን ግን በአንድ ቀን የተወለዱ የሁለት ማህፀን መንትዮች።

ይቀጥላል

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 21

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
ቃለአብ የማህበረ ትጉሃን አረጋውያን መርጃ ማዕከልን ለማስጎብኘት ደሴን እና ዮርዲን ይዞ እየሔደ ነው።ከግቢው እንደደረሱ ቃለአብ ቁርስ ተመግበው ፀሐይ እየሞቁ ያሉት አዛውንቶችን እና ህፃናትን እጁን አውለብልቦ ሰላምታ ከሰጣቸው በኋላ።
"እንግዲህ ስራችን እነዚህን ምስኪን ሰዎች መንከባከብ ነው "አለ ቃለአብ
"በዚህ ትንሽ ጊዜ ውስጥ እንዴት ይህ ሁሉ ስራ ልትሰሩ ቻላችሁ"አለ ደሴ
"የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ"አለና ቃል ፈገግ አለ።
ግቢውን እየዞሩ ሲጎበኙ ከቆዩ በኋላ ህፃናቱ ወደ እሚቦርቁበት ሰፋ ያለ ሜዳ ሔደው ተቀመጡ ። ግማሾቹ ህፃናት ይራወጣሉ ሌሎቹ ደግሞ አባ ቶማስን ከበው ተቀምጠው በአፅንኦት ያዳምጣሉ።
አባ ቶማስ ቃልን ሲያዩት ከተቀመጡበት ድንጋይ ተነስተው ልጆቹን እንዲጠብቋቸው ነግረው ወደ እነ ቃል እያዘገሙ መጡ።አሁን አሁን እርጅናቸው እየተጫናቸው መምጣቱን አካሔዳቸው ማሳበቅ ጀምሯል ።
ቃል ዝቅ ብሎ ጉልበታቸውን ስሞ በመስቀል ተባረከ።ደሴ እና ዮርዲም እንደዛው።
"አባ ጓደኞቼ ናቸው ይተዋወቋቸው ይሔ ደሳለኝ ይሔ ደግሞ ዮርዳኖስ ይባላል"ብሎ ፀጉራቸውን አሸት አሸት እያደረገ እነ ደሴን አስተዋወቃቸው
"መልካም ቶማስ ተ/አረጋይ እባላለሁ።የጥንታዊ ቂርቆስ ደብር አስተዳዳሪ ነኝ።ታዲያ የእነ ልጅ ቃለአብን ማህበር ማህበረ ትጉሃንን እንዴት አገኛችሁት ልጆቼ?"አሉ አባ ቶማስ
"መልካም ስራ እና ልንኮራበት የሚገባ ተግባር ነው እየፈፀማችሁ ያላችሁት።በእውነቱ በዚች አናሳ ከተማ ውስጥ ይሔንን ሁሉ አረጋውያን እንዲሁም ህፃናትን የሚያስተዳድር ማህበር ወይም ድርጅት መመስረት ለሌሎች አርዐያ መሆን ማለት ነው።ግን የገቢ ምንጫችሁ ምንድን ነው?"ዮርዲ ጠየቀ
"እስኪ ልጅ ቃል ንገራቸው"አሉ አባ ቶማስ ፈገግ ብለው
"የገቢ ምንጮቻችን ሁለቱ የአባ ቶማስ ወንድሞች ናቸው።ኢሳያስ ተ/አረጋይ የድንጋይ ወፍጮውን እና ሴራሚክስ ማምረቻውን ሰጥቶናል ሌላኛው ደግሞ ኤሊያስ ነው አሜሪካ ነው የሚኖረው በእነርሱ እርዳታ ነው የምንቀሳቀሰው"አለ ቃል
"መልካምነት ለራስ ነው በርቱልን"አለ ደሴ
"ለምን ራሳችሁን ከሓላፊነት ገሸሽ ታደርጋላችሁ በርቱልን ሳይሆን እንበርታ ነው እሚባለው።እነዚህ እምታዪቸው ምስኪኖች የማህበሩ ብቻ ሀላፊነት አይደሉም።የመለው የኢትዮጵያ ህዝብ ሃላፊነቶች እንጂ።የጎረቤት ቤት ሲዘረፍ እኔ ምናገባኝ ብለህ ከተኛህ ነገ የአንተ ቤት ሲዘረፍ ደራሽ አታገኝም።ዛሬ ጎዳና ላይ ወድቀው ብርዱ ፀሐዩ ውርጬ ዝናቡ ሲፈራረቅባቸው ምን አገባኝ ብለህ የምትሔድ ከሆነ ነገ የአንተ ቤተሰቦች በእርጅና ወቅታቸው አንተ የሆነ ነገር ብትሆንባቸው ማን ይከባከብልሀል።ኢትዮጵያዊነት እየሞተች ነው።ወጣቱ የምዕራባውያን ስልጣኔ የአይን ቆብ ሆኖበት ኢትዮጵያ የምትባል ሀገርን ከስሟ ውጭ ሌላው ባህሏን እርግፍ አድርጎ ትቶ አብሮ መጠጣት አብሮ መብላት የታመመን መጠየቅ የተራበን ማብላት የታሰረን መጠየቅ እንደ ሀጢአት እየተቆጠረ ነው።"አባ ቶማስ ሲናገሩ ቁጭት እየተናነቃቸው ነበር።
"እስኪ ኑ ተከተሉኝ"ብለው ከህንፃው ጀርባ የተሰራ ሰፊ ድንኳን ላይ ወሰዷቸው። አብዛኞቹ አዛውንቶች ገላቸውን የማህበሩ አባላት እያጠቧቸው ተመለከቱ።
"ተመልከቱ እነዚህን አባላት።ከአዛውንቶች መሀል በህመም ምክንያት እይነምድራቸውን እና ሽንታቸውን መቆጣጠር አልችል ብለው ዳይፐር የሚጠቀሙ አሉ።አባሎቹ ግን ሳይፀየፉ በእየ ሰአቱ ዳይፐር ቀይረው ገላቸውን እያጠቡ ተመልከቷቸው።ኢትዮጵያዊነት እንደዚህ ነው።ስለ ሌሎች መኖር ስለ ታመሙት መታመም ስለተራቡት መራብ።ግን ምን ዋጋ አለው ስንቱ የአልጋ ቁራኛ ሆኖ የሚጠይቀው አጥቶ በተዘጋ ቤት ውስጥ ህይወቱ አልፏል?ቤት ይቁጠረው።"አባ ቶማስ ሲናገሩ እንባ እየተናነቃቸው ነበር።
"ኑ ተከተሉኝ"አሉ እና ከትልቅ ቋጥኝ ላይ ተቀመጥው ፀሐይ ወደሚሞቁ አዛውንት ወሰዷቸው።
"እሳቸውን አጫውቷቸው እና እናወራለን"ብለው አባ ቶማስ ወደ ህፃናቱ ተመለሱ።
"አባት የኔነህ እንዴት ነዎት?"አለ ቃለአብ
"ክብሩ ይስፋ ለድንግል ልጅ እናንተ እያላችሁልኝ እኔማ አለሜን እያየሁ ነው የኔ ልጅ"አሉ ወደ ፈጣሪ አንጋጠው።
"እስኪ ለእነዚህ ጎረምሳዎች እዚህ እንዴት እንደመጡ ይንገሯቸው?"አለ ቃለአብ
"ምን ገዶኝ የእኔ ልጅ"አሉ አዛውንቱ ለመናገር ጉሮሯቸውን እዬጠራረጉ
"ልጆቼ እኔ መሃን ነኝ መውለድ አልችልም።ታዲያ ሳገባ መውለድ አይችልም እያሉ ሲፈቱኝ እድሜየ ገፋ።ታዲያ ልጅ የማሳደግ ፍላጎቴ እየናረ ሲመጣ አግብታ የፈታች ሁለት ህፃናት የያዘች ወይዘሮ አገባሁ።ታዲያ ብዙ አመታትን አብረን ኖረን ሳለ ድንገት ጠባዪ መለዋወጥ ጀመረ።ሀብቴን በስሟ እንዳዞርላት ጠየቀችኝ።አደረግኩላት።ከዛም ሁለት ጉረምሶችን ቤቴ አስገባች።ለካ ከህፃናቱ በፊት የወለደቻቸው ልጆቿ ነበሩ።ንብረቴን ተደላድለው ከያዙ በኋላ እኔን ፊት መንሳት ጀመሩ።ታዲያ አንድ ቀን በጠላ መርዝ ጨምረው ሰጡኝ።ነገር ግን ጠጥቸው በእግዚአብሔር ቸርነት ተረፍኩ።ነገር ግን የጨንጓራ በሽተኛ ሆኜ ቀረሁ።እሱ አልሳካ ሲላቸው እዩት ተመልከቱኝ"ብለው ሆዳቸው ላይ በጩቤ የተወጋ ለምፅ አሳዪቸው።"እንዲህም ሆኜ ተረፍኩ።ከዛማ ጓዳ ዘጉብኝ።ምግብ የለ ውሀ የለ።ሽንቴን ሁሉ ጠጥቻለሁ ብለው ማልቀስ ጀመሩ። ምን አደርጋለሁ ዘመድ አዝማድ የማላውቀው እኔ ምስኪኑ የት እደርሳለሁ ከበረንዳ በረንዳ እየዞርኩ።እድል ሲቀናኝ ሳንቲም ለማምኜ እህል እቀምሳለሁ።አልሆን ሲል ሆዴን አስሬ ጎዳና አድራለሁ አሉ።
ታዲያ እነዚህ ብሩክ የሆኑ ሰዎች ከጎዳና አንስተው ለዚህ አበቁኝ።አሉ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አባ ቶማስ"እንግዲህ እዚህ ማህበር ውስጥ የሚደረገውን ነገር ተመልክታችሁ መልካም ነገር ለማድረግ ወደኋላ እንደማትሉ ተስፋ አደርጋለሁ እግዚአብሔር መልካም ለሰራ ሁሉ ድንቅን ያደርጋልና"አሉ አባ ቶማስ
ዮርዳኖስ ከፊታቸው በርከክ አለና "አባቴ የዚህ ሰናይ ማህበር ክብርን አግኝቼ በህይወቴ እንኳን አንድ ይበል የሚባል ስራ እሰራ ዘንድ ምረጡኝ"አለ ዮርዲ።ከልቡ ነበር መማፀኑ
ደሴም ተከተለና "አባቴ የሁላችንም ሀላፊነት ነው ካላችሁ አይቀር ከእነዚህ ምርጦች ጋር ተመርጠን እኛም ሰብዐዊ የሆነ ስራን እንስራ አለ"
አባ ቶማስም የወጣቶችን ተማፅኖ ከአዳመጡ በኋላ"እንግዲህ ስሜታዊ ሆናችሁ መወሰን አይጠበቅባችሁም።ግዜ ወስዳችሁ ተማከሩና በልጅ ቃለአብ በኩል ውሳኔአችሁን አሳውቁኝ።"አሉ

እሁድ ጠዋት.....................................
ጠዋት ከአልጋው ላይ ቃለአብ ከሔዋን ጋር ስልክ እያወራ ሳለ ማርዘነብ አንተ ቃለአብ እያለች መጣራት ስትጀምር፤በቃ ሒዊ በኋላ እደውላለሁ ብሎ ስልኩን ዘጋውና።
"አቤት እማየ"አለ ቃለአብ
"ውይ ነቅተህ ነው እንዴ እንደዚህ የምታስለፈልፈኝ"አለች ማርዘነብ
"ስልክ ይዤ ነበር ለዛ ነው።"አለ ቃለአብ
"ዛሬ የምስራች አለኝ ሻወር ውሰድና ዝንጥ ብለህ ሳሎን ና""ብላ ማርዘነብ ሔደች
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ትላንት ቅዳሜ ማታ...................................
አዝወትረው እቤት የማይመጡት የእነ አቶ ተሾመ የንስሐ አባት ማታ አካባቢ ድንገት ተከሰቱ።እልፍነሽ ቡናዋን እያፈላች ነው።ሌሎቹ የቤተሰቡ አባላትና አባ ወ/ቂርቆስ ተቀምጠዋል።
"እንግዲህ ምሽቱ ሳይገፋ ልጄ ጀምር "አሉ አባ አቶ ተሾመን እያዩ።
አቶ ተሾመ ሲፈራ ሲቸር ከቆየ በኋላ ወይዘሮ አለም ፊት ላይ ሔዶ ተደፋ
እሷም ግራ ተጋብታ"ምንሆነህ ነው"ብላ ለማንሳት ስትሞክር ጭራ
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 22

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
.
የተሰበሩ ሶስት ልቦች
ዮርዳኖስ እና ደሴ ማህበረ ትጉሃን ስራቸውን እንዲጀምሩ ደብዳቤ ልኮላቸው በዝግጅት ላይ ሳሉ አስደንጋጭ ክሰተት ተፈጠረ።ዮርዳኖስ እና ቃለአብ ወንድማማችነት ላይ ነፋስ ገባ።
ቃለአብ ዮርዲን አብረን እንደር ብሎት ደሳለኝን ጨምሮ እነ ዮርዲ ቤት ተሰባስበዋል።ዮርዲ ክፍሌን ላስጎብኝህ ምክንያቱም ከዚህ በኋላ ክፍል ተጋሪየ ደባሌ ነህ እንግዳ እንዳይሆንብህ ብሎ እየቀለደ ከደሴ ጋር ይዞት ገባ።ዮርዲ ክፍሌ ይቺን ትመስላለች።አለና እሚጠጣ ነገር ለማምጣት ወደ ሳሎን ተመለሰ።
ቃለአብ ጠባቧን ክፍል ዞር ዞር እያለ ሲመለከት ከቆየ በኋላ ቀና ሲል ከአንድ ፎቶ ጋር ተጋጨ።አይኑ ፈጠጠ።ከግድግዳው ላይ አወረደው እና ተመለከተው።የሔዋን እና የዮርዳኖስ ፎቶ።ተቃቅፈው የተነሱት ፎቶ።ቃል በቁሙ ለቀቀው።ደሴ ደነገጠና "ምነው ምን ሆነህ ነው "አለ የወደቀውን የፎቶ ፍሬም እያነሳ
ቃለአብ ግን ጭራሽ እየሰማ አልነበረም ሰማይ እና ምድሩ ተገለባበጠበት።ክፍሉን ትቶ ከግቢ ወጥቶ ሮጠ።ደሴ ተከተለው ጭራሽ ሊቆም አልቻለም። ጊወርጊስ በር ላይ ሲደርስ ከቁሙ በሩ ጋር ወደቀና መጮህ ጀመረ።ደሴ ግራ ገብቶት ደንግጦ ቆመ።
"ፈጣሪዬ ማፍቀሬ ሀጢያት ነው እንዴ ንገረኝ ምን ብበድልህ ነው የወንድሜን ፍቅረኛ ፣ካልጠፋ ሴት ምን አደረኩልህ ለዘመናት የተራብኩትን የወንድምነት ፍቅሩን ሳልጠግብ።ሔዋን ምን አደረኩሽ በምንስ የተረገመ ቀን ነው ያገኘሁሽ"እየጮኸ እሪታውን አቀለጠዉ
ደሴ የሰማውን ማመን አልቻለም ጆሮው መሰለው ነገር ግን ደግሞ ቃል አሁንም እየጮኸ ነው።
"ፈጣሪ ሆይ የዮርዲን ሀዘን የማይበት አቅም የለኝም ግደለኝ እባክህን አሁኑን ግደለኝ" እያለ ጮኸ
ደሴ ከወደቀበት ሊያነሳው ምከረ የሚሆን ነገር አይደለም።ዮርዲ ደወለ።ደሴ አነሳው።"አንተ የት ሔዳችሁ ነው"አለ ዮርዲ
"ዮርዲዬ ተኛ ትንሽ ጉዳይ ኖሮብኝ ቃልን ይዤው ሔጃለሁ"ብሎ ደሴ ስልኩን ዘጋው
ቃለአብ እዛው ተደፍቶ እየጮኸ ከሌሊቱ ስድስት ሰዐት ሆነ።ደሴ በመከራ በልመና ተማፅኖ አነሳው።ሳግ እየተናነቀው የሆነውን ሁሉ ለደሴ ነገረው።ደሳለኝ የተፈጠረውን ሲሰማ እንባው ውስጡን ፈንቅሎ ፈሰሰ።በእውነቱ ለሁለቱም ነበር ያለቀሰላቸው።ቃል የጮኸበት ጉሮሮው ደርቆ መናገር ተስኖት የግዱን ነው ቃል የሚያወጣው ።"ዮርዲዬ ጉድ ሰራሁ ወንድሜ በቁምህ ቀበርኩህ።ፈጣሪዬ ለምን በብቸኝነት አኑረኸኝ ደግመህ ለምን ትጨክንብኛለህ "እያለ ሌሊቱን ሙሉ ሲያለቅስ አደረ።ደሴም የሚለው ግራ ገብቶት ቁጭ ብሎ አብሮት ሲያለቅስ አደረ።
ጠዋት ቃል ሙት አካሉን የግዱን ሰብስቦ በደመነፍስ መንቀሳቀስ ጀመረ።ደሴ ተከትሎት ቤቱ አደረሰውና ምንም ሳይል ተመለሰ።ደሴ የታየው አንድ እና አንድ ነገር ነበር።ለሔዋን ደወለ እና ሊያገኛት እንደሚፈልግ ነግሯት ወደቀጠረችው ቦታ ሔደ።ልክ እንደደረሰ ለአይን እንኳ ተፀየፋት።እንደዛ የህቱን ያክል ይወዳት የነበረች ልጅ ቅፍፍ አለችው።"ሔዋን አሳፋሪ ሰው ነሽ አንቺ ዮርዳኖስን እንደዚህ ታደርጊውላሽ?ዮርዲ እኮ ነው።በዮርዲ ላይ ሌላ ወንድ"አለ ደሴ ገንፍሎ።ንዴቱ ከልክ በላይ ሆኖ ቀንድ አብቅሏል።
"ደሴ ላስረዳህ"አለች ያልጠበቀችው መዐት ሲወርድባት በሀፍረት ሽምቅቅ ብላ
"ሔዋን አፈ የለሽም እውነት ብትሞቺ ነበር የሚሻልሽ።እኔ አንቺን ብሆን እዚህ ከምቆም ሞቴን ነበር የማፋጥነው"አለ
ሔዋን ተናደደች"እስኪ ማነው እኔንስ እሚያዳምጠኝ?"አለች
"ቃለአብ ማን እንደሆነ ግን አውቀሻል?"አለ ደሴ
"እንዴት ልታውቀው ቻልክ?"አለች ሔዋን
"እሱ ነው እንዴ የገረመሽ?ቃለአብ ተሾመ ማለት የምስኪኑ አፍቃሪሽ ዮርዳኖስ ተሾመ ወንድም መሆኑንስ ታውቂያለሽ?"አለ ደሴ።
ሔዋን የሰማቺውን ማመን አቃታት መሬት ተሽከረከረችባት ወዲያውኑ ዝልፍልፍ ብላ ወደቀች።ደሳለኝ ደንግጦ ከወደቀችበት ተንበርክኮ ከራሷ ቀና ሲያደርጋት እጁ በደም ተላወሰ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ቃለአብ ሱቅ ሒዶ በወረቀት የተጠቀለለ ነገር ገዝቶ ተመለሰ።ማንም ሳያየው በጓዳ በር ገባና ወረቀት ላይ እንደነገሩ ጫር ጫር አደረገ እና ከሱቅ ይዞት የመጣውን ወረቀት ፈታታው።ትንሽዬ ብልቃጥ ነች።ዮርዲዬ ይቅርታ አለና ቢልቃጧን ሻት አደረጋት።


የማርዘነብ ቤት ድብልቅልቁ ወጣ።አምቡላንስ መጣ ቃለአብ በአፍ በአፍንጫው አረፋ ይደፍቃል።እጁጋ የጨመደዳትን ወረቀት ነርሶች ነጥቀው ለማርዘነብ ወረወሩላት።አምቡላንሷ ወደ ሆስፒታል ከነፈች።ማርዘነብም እየጮኸች መንገዶን ተከትላ ሮጨች።
፨፧፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሔዋን ቀድማ ሆስፒታል ገብታለች።የሔዋን ቤተሰቦች እና የዮርዳኖስ ቤተሰቦች ሆስፒታሉን ድብልቅልቁን እያወጡት ነው።ምስኪኑ ዮርዲ ምን እንደተፈጠረ አያውቅም ከደሴ ጋር ቁጭ ብሎ ለፍቅሩ ያለቅሳል።ከቆይታ በኋላ ሌላ አምቡላንስ መንገዱን በጩኸት እያናጋች መጣች።ዶክተሮች ተረባርበው ይዘውት ገቡ።ከደቂቃዎች በኋላ ማርዘነብ "ልጄ ልጄ የአይኔ ማረፊያ ቃልአቤ ቃልአቤ"እያለች ስትገባ የዮርዳኖስ ቤተሰቦች ተመለከቱ።በመርዶ ላይ ሌላ መርዶ።የሐዘን ጉም በንኖ በንኖ እነ ዮርዳኖስ ቤተሰቦች ላይ ተሰበሰበ።ዮርዳኖስ ፈገግ ማለት ጀምሯል ትርዒት እየተመለከተ መሰለው።
ሔዋን ክፍል የነበሩት ዶክተሮች ወጥተው ስለሔዋን መልካም ዜና አበሰሩ።የሔዋን ቤተሰቦች በእፎይታ ሌላኛውን ውጥረት ተቀላቀሉ።
ማርዘነብ እሪታዋን እያቀለጠችው ነው።ዮርዳኖስ ፈገግ ብሎ መጣና"ማዘር ቃለአብ እኮ እያሾፈብን ነው የሚሆነው"ልሒድ ልጠይቀው ብሎ ሊሔድ ሲል ጎተተችው እና ወረቀት ሰጠቺው።
አነበበው "ዮርዲዬ የኔ ፍቅር ወንድም ለአንተ ይሔ አይገባህም ነበር ።ለካ የአንተውን ሔዋን አፍቅሬ ነው ስጃጃል የከረምኩት።ዮርዲዬ የአንተንም የእሷንም ህይወት አበላሸሁ።ዮርዲዬ ይቅር በለኝ አንተ ፊት መቆም የምችልበት ሞራል የለኝም።የአንተን እንባ ቆሜ ከማይ ሞትን መርጫለሁ።ይቅርታ ወንድሜ።ሳልጠግብህ እንዲህ ሆነ።ፈጣሪ ፍቅራችንን አልወደደም።ቂም እንዳትይዝብኝ መልካም ነህና መልካም ይግጠምህ።እ.....ወ......ድሀለሁ።"
"ደሴ ቃልየ ምንድን ነው እሚለው?እየቀለደ ነው በለኝ ደሴ"አለ እየተንተባተበ
ደሳለኝ ዮርዲን ደግፎ አስቀመጠው እና የተፈጠረውን እውነት እረዳው ።ዮርዲ መጮህ ጀመረ።"ቃል አይሆንም ትተኸኝ አትሔድም፥የእኔ እና የአንተ መጨረሻ እንደዚህ አይሆንም "እያለ መጮህ ጀመረ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የማታ ማታ ከቃለአብ ክፍል ዶክተሮች ወጡ እና።ፈጣሪ ጩኸታችሁን ሰምቷል።ልጃችሁን ማትረፍ ችለናል።ብለው ሌላኛውን ውጥረት ገሸሽ አደረጉት።
የሔዋን እና የቃለአብ እንደዚህ መሆን ምስጢሩ ተገለጠ።ድብቁ ፍቅራቸው ይፋ ወጣ።እነሱ ባሸለቡበት ሀቁ ተሰማ።ዮርዳኖስ ግን ምን ማለት እንዳለበት ግራ ገብቶት ደንዝዟል።ምንም እያሰበ አይደለም።ግን ደግሞ ብቻውን እያወራ ነው።
ማርዘነብ አቶ ተሾመ የተቀመጠበት መጣችና በአይበሉብሽ ጥፊ ፊቱን ላጥ አደረገችው።ሁሉም አይኖች ወደ ማርዘነብ ተወረወሩ።"አየህ ይህ ሁሉ የሆነው በአንተ ምክንያት ነው።እውነቱን ተናገር እያልኩ ስለምንህ ዳሩ አንተ ልትሰማኝ አልቻልክም።ተመልከት የልጆቹን ህይወት ምስቅልቅሉን አወጣኸው እንኳን ደስ አለህ"አለች።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ ደንዝዞ በተቀመጠበት ስልኩ አምባረቀ።እየቀፈፈው በዛለ ስሜት ውስጥ ሆኖ ስልኩን አውጣው።ዮኒ ስለሆነበት እንጂ ማንሳት አልፈለገም ነበር።አነሳው።ዮኒ እያለቀሰ ነበር።
ዮኒ ጎጄ መኪና አደጋ ደርሶበት
እንዳረፈ መርዶ ነገረው።ዮርዲ እንባ በአይኖቹ ፍስስ አለ።ዮኒ አሁንም እየተናገረ ነበር።ቀብር ነገ ነው።እና አሁን በአባዱላ እያመጣሁ ነው እንደምንም ብለህ መኪና ፈልገህ ደጀን እሚባለው አገር ትጠብቀኛለህ አሁኑኑ ተነስ ገብተን ማደር አለብን"አለ።
ዮርዳኖስ ዙሪያው ገደል ሆነበት የጨለማ ዳስ ወርዶ ወርዶ ከፊቱ ተዘረገፈ።ዮርዲ እንባው እንደጅረት እየወረደ ለደሴ ነገረውና። በደመነፍስ ቤቱ ሔደ ደሴ ተከተለው። ኤቲኤም እና ጋቢ ይዞ ወጣ።ደሴም ድርቅ ብሎ አብሬህ ነው እምሔደው አለና ተከተለው።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨

ይቀጥላል


@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
😘ሰሜናዊት ሙሽራ😘

🔥ክፍል 23

✍ደራሲ ዮሴፍ ተሾመ
.
.
#የመጨረሻ ክፍል..
.
.
የዮኒ ጎጄ ግብዐተ መሬት ከተፈፀመ ሶስት ቀን ሞላው።ዮኒ ጎጄ እንደዋዛ አረፈ።እነ ዮርዲ እሚወዱትን ጓደኛቸውን እንደዋዛ አጡ።ቀብር ላይ የተገኙት ከዶርም አባላት ዮናስ እና ዮርዳኖስ ናቸው።ሌሎቹ ስልካቸው ሊሰራ አልቻለም።በሶስተኛው ቀን ዮርዲ ዮኒና ደሴ መቃብሩ ጋር አበባ ይዘው ሊሰናበቱት ሔዱ።መቃብሩ ጋር ደርሰው እርማቸውን ካወጡ በኋላ መቃብሩን ከበው ተቀመጡ።ዮርዲዬ እንግዲህ መፅናናትን ይስጠን።አለ ዮኒ
"እመፀናበት ልብ አጣሁ
እሸሸግብት ጥግ አጣሁ አለ ሎሬቱ።ዮኒዬ አልቻልኩም ህይወቴ ምስቅልቅሉ ወጣ።አለ እያለቀሰ።
"ምነው ዮርዲዬ የተለየ ነገር ተፈጥሯል እንዴ?"አለ ዮኒ
ደሴ የተፈጠረውን በሙሉ ለዮኒ ነገረው። ዮኒ ከልቡ አዘነ ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ ደሴ እና ዮናስ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝተው ተሰናበቱ እና ጉዙ ጀመሩ ።ደጀን ደረሱና ወረዱ።ዮርዲ ዮኒን ሊሰናበተው ሲል።ዮኒ አምበር አብሬህ ነው መሔድ አለብኝ በዚህ ሰአት አብሬህ ሆኜ ካላበረታሁህ ጓደኝነታችን ለመቼ ነው።አለ።ወደ አምበር አብረው ዘመቱ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ሔዋን እና ቃለአብ ከሰመመናቸው ነቅተዋል።ነገር ግን ከሆስፒታል አልወጡም።ዶክተሮች ለቤተሰቧ የሶስት ወር ነፍሰ ጡር መሆኗ ተነገራቸው ።
ዮርዲ ደሴ እና ዮኒ አምበር ደርሰው ከእነ ዮርዲ ቤት አረፉ።ዮርዲ ለዮናስ መቀየሪያ ልብስ ሰጠው እና ደሴም ከዮርዲ ልብስ አንስቶ ሻወር ወሰዱ።የዮርዳኖስ ቤተሰቦች ቅስማቸው ምንም እንኳን ቢሰበር ዮናስን በጥሩ ሁኔታ ተቀብለው ነው የተዋወቁት።ምሳ ከበሉ በኋላ ተሰባስበው ተቀመጡ።በዮርዳኖስ ጓደኛ ሞት የዮርዲ ቤተሰቦች ከልባቸው አዝነዋል።
"ልጄ የእኔ ጀግና እንግዲህ አንተ ትልቅ ሰው መሆንህን የምታስመሰክርበት ሰዐት አሁን ነው።መሸነፍ የለም።ችግሮች እንደው አንዴ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ሆነው መጥተውብሀል።መጠንከር አለብህ"አለ አቶ ተሾመ
"አባዬ በዚህ ሰዐት እኔን ሳይሆን ቃለአብን ነው ልትመክረው የሚገባ።ምን ያህል ደካማ እንደሆነና ምን እንደወሰነ አይታችኋል አይደል።እኔ ምንም አልሆንም" አለ እንባው ቀድሞት እየወረደ።
"ዮርዲዬ እሱን ቀለበት አውልቅ አንተ ጋር ከዚህ በኋላ ቦታ የለውም።ሔዋን ከቃለአብ አርግዛለች"ብላው ሌላኛ ዱብዳ ጨመሩለት።
ዮርዲ ቀለበቱን እና እጁ ጋር ያለውን ሀብል ፈቶ ጠረጴዛው ላይ አስቀመጠው እና በጉልበቱ ድፍት ብሎ ስቅስቅ አለ።ማንም ተው አላለውም በዚህ ሰዐት ተው ማለት ማባባስ መስሎ ታያቸው።የዮርዳኖስ ስልክ ተንጫረረ።
ደሳለኝ ከዮርዲ ኪስ አውጥቶ አነሳው።ሔሎ ሔኖክ ነኝ ከማህበረ ትጉሃን ዮርዳኖስ?"አለ።
"ነኝ ቀጥል"አለ ደሴ
"ለተፈጠረው ነገር በጣም አዝናለሁ"አለ
"አመሰግናለሁ"አለ ደሴ
"ወንድም ዮርዳኖስ ነገ ግጥሞችህ ወረዳችንን ወክለው ለዞን ይወዳደራሉ ።ስለሆነም ደብረማርቆስ ነገ ፕሮግራሙ ላይ መገኘት አለብህ"አለ ሔኖክ
"እሺ አመሰግናለሁ"አለ ደሴ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ መሔድ ሳይፈልግ በደሴ እና ዮኒ ጉትጎታ ብቻ እሺ አለ።ማርቆስ ከመሔዳቸው በፊት ታማሚዎችን መጠየቅ አለባቸውና ሶስቱም ሆስፒታል ሔዱ።መጀመሪያ ወደ ሔዋን ክፍል አቀኑ ።ደሴ ቀድሞ ገባና ጠይቋት ወጣ።ዮርዲ ገባ።ስታየው ደነገጠች።እሱ ሲያያት እንባው ተናንቀው እና ጉንጩን ሳይነካ ዱብ ዱብ አለ።ሲቃ እየተናናቀው ግን ዋጥ አደረገውና።እንኳን እግዚአብሔር አተረፈሽ አለ።
"አመሰግናለሁ "አለችና ማልቀስ ጀመረች
"ወይዘሮ ሔዋን ተይ አታልቅሺ ልትደሰቺ ነው የሚገባው እኮ።በዛ ላይ እኔንም አጎት አድርገሽኛል።ደስ ብሎኛል"አለና ክፍሉን በሳቅ አናጋው።ዮኒና ደሴ ክፍሉን በርግደው ገቡ እና ይዘውት ወጡ።
ዮርዲ ትንሽ ከተረጋጋ በኋላ ሶስቱም ወደ ቃለአብ ክፍል ገቡ።ቃለአብ ዮርዲን ሲያየው በሽታው አገረሸበት"ዮርዲዬ ውጣልኝ ዮርዲ ተወኝ ሒድልኝ"አለ።ዮርዳኖስ ግን ጠንክሮ ሊታየው ስለወሰነ የግዱን ፈገግ አለና።ሔዶ ግንባሩን ሳም አደረገዋና ተቀመጠ።ደሴም እንደዛው።ዮኒ እጁን ጨበጠው።
"ዮርዲ ልለምንህ ሒድልኝ እባክህ ልለምንህ ሒድ" እያለ አለቀሰ
ዮርዳኖስ በደመነፍስ ከተቀመጠበት ሔደና ቃለአብን በተኛበት በጥፊ አቀመሰው።"እውነቱን ልንገርህ ወንድምህ አልመስልህ እያልከኝ ነው እኔ በጭራሽ ተሸናፊ ደካማ ሞትን እንዳማራጭ የሚወስድ ልፍስፍስ ወንድም ሊኖረኝ አይችልም"አለ።
ቃለአብ ህመሙን እረስቶ ከአልጋው ላይ በደመነፍስ ተነሳ።"ዮርዲ ንገረኝ፣እኔ ማለት እኮ ህይወትህን በቁንጮው ያቆምኩት ሰው ነኝ።እንዴት ነው የአንተን ደስታ ነጥቄ የምኖረው"አለ እየጮኸ
"ቃለአብ ንገረኝ ፈልገህ ነው ያደረከው?ዮርዲን ልጉዳው ብለህ አስበህ ነው ያደረከው?"አለ
"ዮርዲ እባክህ ተወኝ" አለ ቃል በተሰላቸ ስሜት
ዮርዲ ቃለአብን እየጎተተ ሔዋን ክፍል ይዞት ገባ።ደሳለኝ እና ዮናስ ግራ ገብቷቸው ቆመው ያዩታል።
"ሔዋን ንገሪው ምንም እንዳላጠፋ ንገሪው።እባክሽ አስረጂው።ሁለታችሁም ምንም እንዳላጠፋችሁ በያ ንገሪው።"ብሎ ሔዋን የተኛችበት አልጋ ላይ ቁጭ አደረገው።በል ቃለአብ እውነቱን ንገረኝ።እኔ እንድበረታ ነው አይደል የምትፈልገው።እሱን ከሆነ የምትፈልገው ሔዋን ፍቅረኛህ ብቻ አይደለችም ከዚህ በኋላ የልጅ እናትህም ጭምር አለ ዮርዲ።
"አይሆንም አይሆንም"አለ ቃለአብ
"የምትደክምብኝ ከሆነ እኔ መበርታት እንዴት ይቻለኛል።የአንተን ውሳኔ ልክ ነው ማለት ነው።እኔ እደግመዋለሁ"ብሉ ሊወጣ ወደ በሩ ሲራመድ ቃለአብ ቀድሞት ከዮርዲ እግር ስር ወደቀ።
"ዮርዲ ገድለኸኝ ሒድ።ጭራሽ አታደርገውም"አለ
"ውሳኔዬን ካላከበርክ አደርገዋለሁ"አለ ዮርዲ እልህ ተያይዞት
"እሺ ዮርዲዬ እባክህ ተው ውሳኔህን አከብራለሁ"አለ ቃል።


ፍቅር ምንድን ነው?
ወጣቶች ሆይ የፍቅር ትርጉም እየገባን አይደለም።ፍቅር ማለት የሆነ ሰዐት ላይ አገርሽቶ የሆነ ሰዐት ላይ ደግሞ ሰከን የሚል ስሜት አይደለም።መላመድ ፍቅርን አያመጣም።መጀመሪያ ልብ ላይ የሌለን የፍቅር ስሜት ለማምጣት መሞከር ቂልነት ነው።ስንቶቻችን ነን ከነገ ለማይዘል ስሜት የፍቅርን ስም የምናጎድፍ።ፍቅር ግጥምጥሞሽ እንጂ ስሜቱን እናምጣ ብለን ስበን የምናመጣው አይነት የፍትወት ስሜት የለውም።ሔዋን እንደዚህ ትላለች።ዮርዲ ላይ የነበረኝ ፍቅር ወንድማዊ እንጂ ፍፁም ፆታዊ አልነበረም።መቀራረባችን ብቻ ፍቅር መስሎኝ ከዮርዲ ጋር ነበርኩ።ከዛም በዘለለ ጓደኞቼ በሙሉ ፍቅረኛ ስለነበራቸው እኔም ፍቅረኛ አለኝ ለማለት የማይሆን ጉድ ውስጥ ገብቼ ነበር።የዘመኑ ሙድ በቃ ጥንድ ነች ለመባል ወይም ጥንድ ነው ለመባል አፈቀርኩህ አፈቀርኩሽ እየተባባሉ የፍቅርን ትርጉም መላቅጡን አሳጥተው ከአልጋ ላይ ያልዘለለ ሆኖ ይቀራል።ግን በዮርዳኖስ ፍቅሬ ቃለአብን አገኘሁ።ዮርዳኖስን ለፍቅር ራሱን ሰጥቷልና አምላክ ይከፍለዋል ትላለች።ቃለአብ በበኩሉ እንደዚህ ይላል።ፍቅር አጋጣሚ ነው።ፍቅር ዮርዳኖስ ነው።ለወደደን ለእኛ ራሱን አሳልፎ ሰጠ።ዮርዲ እንደዚህ ይላል ።ፍቅር እግዚአብሔር ነው።እግዚአብሔር የሰው ልጆች በድለውት እንኳን ስለፍቅር ብሎ ራሱን መሰዋት አድርጎ አቀረበ።እኔም ሁለት ለተፋቀሩ ሰዎች ራሴን ገታሁ።ሔዋን ትክክለኛ አፍቃሪ ነች ለወንድሜ ለቃለአብ ትገባዋለች ይገባታል።እውነት የሔዋንን ውሳኔ ከልቤ ተቀብየዋለሁ።ለአሰበችበት አላማ ፅኑ ሆኖ መቆምን አየሁ።ይሉኝታ ይዟት ከእኔ ጋር አልተቀመጠችም።ልባችንን ማዳመጥ መቻልን እንዳለብን ሔዋን አስተምራኛለች።እኔም ያቺ ፍቅ
ሬ እስክትመጣ እየጠበኩ ነው።ደግሞም አትቀርም ትመጣለች።ይላል።
ዮናስ ከዮርዳኖስ ፍቅርን ተምሯል ፍቅር አፍቅሮ ማግኘት ብቻ አይደለም።የአፈቀሩትን ሰው ህልም ማሳካትም እንጂ።ፍቅር ራስ ወዳድነት አይደለም።ዮርዲ ራስ ወዳድ ሆኖ ሔዋን የእኔ ነች አላለም ።
ፍቅር ይህ ነው የአፈቀሩትን ሰው ደስታ መሻት።የአፈቀሩትን ሰው አግኝቶ መኖር ብቻ አይደለም።ራስን መሰዋት ራስን አሳልፎ መስጠት ።ከፈጣሪ የተበረከተልን ፍቅር ይህ ነው።


የስኬት ጥግ
ከአመታት በኋላ ............................
ማህበረ ትጉሃን ከወረዳው ውጭ በሁሉም የክልል ከተሞች መቀመጫውን አስፋፍቶ ሰናይ ተግባሩን ቀጥሏል። ዮናስም በዛው ኮብልሎ አባል እንደሆነ ቀረ።አባ ቶማስ ይሔንን የስኬት ጥግ ተመልከተው በክብር አረፉ ።የኢትዮጵያን እና የኤርትራን እርቅ ተከትሎ ማህበረ ትጉሃን በሰሜናዊት ሙሽራ አስመራ ከተማ ማህበራቸውን አቋቁመዋል።ዮርዳኖስም ገጣሚ እና ደራሲ ዮርዳኖስ የመባል ክብርን አገኘ።በባህል እና ቱሪዝም ስፖንሰርነት አንድ የግጥም መድበል እና ልቦለዱ ታተመ።ሙሉ ገቢውን ለማህበረ ትጉሃን አደረገ።ከክብር ጠቅላይ ሚኒስቴር እጅ ወጣት የሰላም ገጣሚ ተብሎ ሽልማትም ተበርክቶለታል።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ወና ዋና የማህበሩ አባላት አስመራ ተሰብስበዋል።"አጎቴ ዮርዳኖስ ሁልጊዜ እዚህ ለምን አታመጣኝም"አለ የቃለአብ ጩጬ
"አሸናፊ ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር እዚህ ነው የምንኖረው"አለ ዮርዲ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
በተሰበሰቡበት አዳራሽ ምናሴ ወጥቶ ንግግር ማድረግ ጀመረ።
እኛ ኢትዮወኤርትራዊያን ባህላችን ያለንን ተካፍለን መብላት እንጂ ያለንን ብቻችንን ማውደም አይደለም።በምዕራብዊያን የተመረዘውን እና ይህን ዘመናዊ ባርነትን ሰብረን።ፍፁም የሆነ ትውልድ እንፈጥራለን።ይቺን ሀገረ እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ከተከለሰው ባህላችን አላቀን አንዲት ኢትዮጵያን እንገነባለን።አለ።ጭብጨባ ተከተለ።
የምዕራባውያንን ቴክኖሎጂያቸውን እንጂ ይሔን እዚህ ግባ የማይባል ባህላቸውን መቅሰም ትተን በራሳችን ቋንቋ ባህል እንዲሁም ወግ የምንኮራ የድሮዋ ኢትዮጵያወኤርትራ እንሆናለን።ሌላው በባዕድ ሀገር እሰከ ፒኤችዲ ድረስ የሚሰጠውን እና ኢትዮጵያ ውስጥ እየተመናመነ የመጣውን የግዕዝ ቋንቋን በሀገራችን ጀምረን የሀገራችንን ሰርዶ በሀገራችን በሬ።ጥንቱን ስልጣኔ እንደገና መመርመር።ያልተገለጡ መፅሐፍትን መግለጥ።ችላ የተባሉ የሚስጢር ቋቶችን መበርበር።ታሪክን መገንባት ስምን ማደስ።እርዳታ የምትሰጥ እንጂ የማትቀበል ሀገርን መመስረት።አንድ ሆነን ከቆፈርን የማናገኘው ታሪክ የለም።አባቶች ቀብረው ያለፏትን የሚስጢር ጉሽጉሽ ፈተን ዳግም የስልጣኔ ማማ ላይ መድረስ።ሀገራችንን የሀገራት ቁንጮ ጋር ማስቀመጥ።አለ።ጭብጨባ እና ፋጨት ድብልቅልቅ አለ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
ዮርዳኖስ መድረክ ላይ ወጣና ማይኩን ያዘ።በፊታችሁ አንድ ነገር ቃል ልገባ እወዳለሁ።አለ።ይሔ በአላዋቂወች አድር ባዮች እና ቅጥረኞች እንዲሁም ልወደደ ባዮች እየተፃፈ የሚያፋጀንን ታሪክ እገረስሰዋለሁ።ከዛሬ ጀምሮ በእየገዳማቱ በእየ አድባራቱ እየዞርኩ ታሪካችንን ለቅሜ ትክክለኛውን የኢትዮጵያን ታሪክ ፅፊ አሳትማለሁ።ያልተበከለውን ንፁህ ታሪካችንን።ያልተዛባውን እከትባለሁ። ከኖህ እስከ አሁን ያለውን የማንጣለበት ግን የምንስማማበትን ታሪክ የሚያፋቅረንን እንጂ የማያፋጀንን ታሪክ ፅፌ ጠላቶቻችንን ድል ለመንሳት እንደምነሳ ቃል እገባለሁ።አለ።ጭብጨባ ተከተለ።
ግን ደግሞ ዮናስ እና ደሴ በታሪክ አሰሳየ ውስጥ ከጉኔ ሆናችሁ እንደምታግዙኝ ቃል ግቡልኝ አለ።ደሴና ዮኒ እጃቸውን አጣምረው አወጡለት ።ጭብጨባ ቀጠለ።
አሁን ቃለአብ እና ሔዋን እባካችሁ ወደ መድረክ።አለ ዮርዳኖስ
ቃለአብ እና ሔዋን ልጅ አሸናፊን ከመሀል ይዘው ወደ መድረክ በጭብጨባ ታጅበው ወጡ።
ዮርዳኖስ በሀብል የታሰሩ ሁለት ቀለበቶችን ከፍ አድርጎ አሰየ እና እነኚህ ቀለበቶች ትክክለኛ መድረሻቸውን አግኝተዋል።ብሎ ለቃለአብ ሰጠው።ቃለአብ አጠለቀላት አሷም እንደዚህ።አዳራሹ በእልልታ ተናጋ።ቃለአብ ዮርዲን አቀፈው እና የደስታ እንባ አነባ።የወንድሙ ውለታ ከአቅሙ በላይ ሆነበት።ከሁለት ማህፀን የፈለቁ መንትዮች።
ሔዋን በሰሜናዊት ሙሽራ አስመራ ተሞሸረች።ፍቅር ከቤቱ ገባ።
ሙሽራዬ ሙሽራዬ
የወይን አበባዬ
ሙሽራው ሙሽራው
ቃለአብ አበባው
፡
፡
፡
፡
፡
🔥ተፈፀመ🔥

እንዴት ነበር ሰሜናዊት መሽራ እስኪ ሀሳብ አስተያየታችሁን
በ 📩inbox ➭ @Ethio_leboled_bot ላይ ያድርሱን !!
እስካሁን በጥሞና ስለተከታተላችሁን እናመሰግናለን ።

@Ethio_leboled #Share
❥❥________⚘_______❥❥
Gg
HTML Embed Code:
2024/05/03 21:28:42
Back to Top