TG Telegram Group Link
Channel: የቤዝ ደብዳቤዎች✍💕💌
Back to Bottom
ባዶ ተስፋ😥😔

ተመልሻለው😊 ከዛሬ ቡኋላ አልፅፍልህም የሚለውን ቃሌን ሽሬ ዛሬም ልከትብልህ ብዕሬን ይዤ ከአንተ ደጃፍ ጎራ ብያለው:: ለማንም ላወራ ያልቻልኩትን አምቄ የያዝኩትን ስሜቴን በብዕር ላሰፍረው....
@yebezdebdabewoch
🗣 @Enate_Y
😔ከህመሜ አልዳንኩም😔
አሞኛል ህመሜ ደግሞ አንተ ነህ
አዎን በድለኸኛል በሰጠውህ ክብር እጥፉን ንቀኸኛል ለአንተ መድሀኒት ለመሆን ስለፋ ህመምን አሳይተሀኛል

🗣 @Enate_Y
@yebezdebdabewoch
ትዝታህ ደስ ይላል......

.....አብረን ከነበርንባቸው ጊዜያቶች ይልቅ ብቸኝነት ያገዘፍንባቸው ሰዓታት ደስታን ይሰጣሉ.... ነገን ካሰብናቸው ተስፋዎቻችን በበለጠ ዛሬ ላይ ያጣናቸው የትላንት ትዝታዎች ጣፋጭ ናቸው.....

በመሄዴ ውስጥ የመጣው ሳቅህ አሁንም ይታየኛል...በመሄድህ ውስጥ የልቤ ደስታ ዛሬም ከመሀል ልቤ ይደልቃል.... በመሄድህ ውስጥ በምንም ልተካው የማልችለው እንቁ ትዝታህ አብሮኝ ቀርቷል...ደስ የሚል ትዝታ.....የሚያስከፋ ትዝታ... የዘላለም ትዝታ...ከወር ለመዝለል የማልፈቅድለት ያንተ ትዝታ በውስጤ ቀርቷል.... እስካለሁ ይቀጥል ይሆናል ...እኔም አላውቀውም ግን የእውነት ትዝታህ ግን ደስ ሲል...

@yebezdebdabewoch
👉 @DayeBT
የሆነ ጊዜ አለ የሆነ ሰአት ... ማድረግ የፈለግነውን ማድረግ ሲያቅተን ፣ ሀሳባችን ከኑሯችን የተገላቢጦሽ ሲሆን ፣ ብዙ ተስፋ ስናደርግና ተስፋ መቁረጥ በኛ ላይ ተስፋ ሲቆርጥ ፣ ሀዘን በኛዉ ነግሶ በኛዉ ይደሰታል፣ ደስታ በኛ ይከፋል፣ ህልማችን ልባችን ዉስጥ እንጂ እዉኑ አለም ዉስጥ እንደሌለ ስናዉቅ ጉልበት ይከዳናል ፣አቅም ያንሰናል ፣ለምንወዳቸዉ የሚወዱትን ማድረግ አለመቻላችን ከራሳችንም ከምንወዳቸዉም ከፈጣሪም ያጣላናል ፡፡ መጥፎ ጊዜ ነዉ ራስንም ሰዉንም ማጣት ከደስታም ከእርዝቅም ያጣ መሆን፡፡ ይገባኛል ስሜትህ !!! ግን ያልፋል እመነኝ የኔ አለም ልብህ ዉስጥ ያለዉን ሀሳብ በእውንህ ታየዋለህ ፡፡ ነገር ግን ያ ጊዜ እስኪመጣ በዚህ መልኩ አትቀጥል ፍቅሬ ለተሻለ ነገ ስትል ከተሻለ ስራ ይልቅ የተሻለ ማንነት የተሻለ ስብዕና ፍጠር ፡፡ ነገሮች ከማግኘት ና ከማጣት ጋር የተገናኙበት ዘመን ላይ ብንደርስም በቁጥር የማይተመኑ ስሜቶችን ገንዘብ ሊያጠፋቸዉ እንደማይችል እመን! ባጣህበትም በምታገኝበትም ግዜ ደስተኛ ሁን 😘አንተን የሚተካ አንድም ፍጥረት የለምና 🥰

@yebezdebdabewoch
comment👉 @DayeBT
ሳልውቅህ ወደድኩህ ሳላውቅህ ወደፊቴን አሻግሬ ከአንተ ጋር አየሁኝ ሳላውቅህ በደስታ ምመኛትን አለም ኖርኩኝ በአንተ ፍቅር ድጋሚ ህይወቴን ዘራሁኝ ግን አብዝቼ ፈራለው እምነት መስጠትን እኔና አንተ ትልቅ ሚያመሳስለን ነገር በሀዘንተኞች አለም መሆናችን ነው እኔም አንተም ጉዳቶች አስተናግደናል ህይወት እንዴት እንደምታገናኝ አናውቅም ግን እኔና አንተን አገናኝታናለች የቱ ልክ እንደሆነ ባላውቅም በመውደዴ ግን አልፀፀትም ጨረቃ በወጣች ቁጥር አይኔን እየወረወርኩ ምን አለ አጠገቤ በሆነ ብዬ እመኛለው ምን አለ አይን አይንህን እያየውህ ባወራህ ምን አለበት እንደምትናፍቀኝ ብነግርህ እያየውህ በአንተ እንደማልጨክን ብነግርህ ማታ ላይ ያስለመድከኝን ሰአት ያሰለመድከኝ ለስለስ ባለ ድምፅህ ምታንጎራጉርልኝ ሙዚቃ መቼም ከጭንቅላቴ አረሳውም ግን ሁለታችንም ልባችን ውስጥ የጠቀመጠ አንድ ሚስጥር አለ እኔና አንተ ብቻ ምናውቀው ሁኔታ እና ሰአት ለናፍቆት ጊዜ አይመርጥም ትናፍቀኛለህ የህልሜ ጉዋደኛ
ለ..ባለ ህልሜ
👇👇👇👇👇
@yebezdebdabewoch
comment👉 @DayeBT
#ባለንበት_መቆም_ወይስ_ወደ_ነገ_መሄድ

''...እንደኔ ግን መሄድ ከመቆም ይሻላል። መቆም ቢያንስ ለጠላቶችህ የታወቀ አድራሻ ይሰጣል። መሄድ ግን ቢያገኙህ እንኳን ለፍተው እንዲያገኙህ ያደርጋል።

መቆም በቆምክበት ቦታ ብቻ ያለውን እድል እንድትጠቀም ያደርጋል ፤ መሄድ ግን የማታቀውን እድል እንድትሞክረው ያደርጋል። ስትቆም መጀመሪያ ታረጃለህ ፤ ቆይቶም ትበሰብሳለህ። ስትሄድ ግን መጀመርያ ትደክማለህ ፤ ቀጥሎ ግን ትጠነክራለህ።

ባለቀ ትናንት አትታሰር ፤ በተበላ ዛሬ አትወሰን ፤ ይልቅ ወደ ማይታወቀው ነገ ሂድ። ነገ ወዳንተ ሳይመጣብህ አንተ ወደ ነገ ሂድ።

አንድ ቦታ ላይ የግድ እንድንቆም ቢፈለግ ኖሮ እግር ሳይሆን እንደ ዛፍ ስር ይሰጠን ነበር። የመሄዳችን ዋነኛው ምክንያቱ የምንቆምበት ምክንያት አለመኖሩ ነው

@yebezdebdabewoch


     ሙሉ ጨረቃን ማድነቁ ቀላል ሲሆን ሌላኛውን ጎን ማየቱ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡ ቀላል የሆነው ለአንድ ሰው የሆነ ቃል ኪዳን መግባቱ ሲሆን የሚከብደው ደግሞ ያንን ቃል መፈጸሙ ላይ ነው፡፡ እወዳችኋለሁ ማለት ቀላል ሲሆን ከባዱ ደግሞ ያንን በሕይወት ማሳየቱ ነው፡፡ ሌሎችን መተቸት ቀላል ሲሆን ራስን ማሻሻል ደግሞ ከባድ ነው፡፡ ስህተትን መሥራት ቀላል ሲሆን ከዚያ መማሩ ደግሞ ብርታትን ይጠይቃል፡፡ ስላጣነው ፍቅር ማንባቱ ቀላል ሲሆን ላለማጣት መንከባከቡ ግን ይከብደናል፡፡ መቀበል እጅግ ቀላል ሲሆን መስጠት ደግሞ ልባዊ ርኅራኄን ይጠይቃል፡፡ ስለ መሻሻል ማሰብ ቀላል ሲሆን ከባዱ ግን ወደ ተግባር መቀየሩ ላይ ነው፡፡ ወዳጅነትን በቃላት መጠበቁ ቀላል ሲሆን ትርጉማቸውን መጠበቁ ግን ከባድ ነገር ነው፡፡
ልጅ እያለን ከሰማናቸው ነገሮች መካከል አንዱ በአካባቢያችን ውሻ ሲያላዝን (የተለየ ድምጽ ሲያሰማ) "ሰው ሊሞት ነው' የሚለው አባባል ነው፡፡ እጅግ በሚገርም ሁኔታ ግን "እኔ ልሞት ነው' የሚል ያለመኖሩ ጉዳይ ነው፡፡ በተለይ አልጋ የያዙ ካሉ የሰዉ ሁሉ ትኩረት መጠቋቆሚያ የመሆናቸው ጉዳይ አጠያያቂ አይሆንም፡፡ ግን የቱ ይሻላል? ሰውን ማስተካከል ወይስ ራስን ማስተካከል፣ እነርሱ ልክ አይደሉም ማለት ወይስ እኔ ልክ አይደለሁም ማለት፣ የሌሎችን ስህተት መዳኘት ወይስ የራስን ድካም መታገል የቱ ይሻላል?

ምርጦቼ  ለሚከብደውና ለሚበልጠው እንትጋ!
👇👇👇👇👇👇
@yebezdebdabewoch
🍋የዋርካ ስር ጤዛ 🍋

በእለተ ከተራ ፥ በበዓል ዋዜማ፣
አደባባይ ሳይሽ ፥ ደምቀሽ በሃገር ሸማ ፣
ወርውር ወርውር አለኝ ፥ ሎሚውን ግዛና፣
ሎሚ ሻጭ ፈለግኩኝ......
ጎዳናውን ሙሉ ፥ ስዞር አመሸሁኝ።
በጥምቀተ ባህር ፥ ህዝብ ሁሉ በሆታ ፣
እያጨበጨበ ፥ ታቦቱን አጅቦ ሲገባ በእልልታ፣
ማጨብጨብ ተስኖኝ ...
እልልታ ጠፍቶብኝ...
ሎሚ ፈልጋለሁ ፥ ከአይኔ ሳትጠፊብኝ።
ይኸውልሽ ውዴ ....
አትታደል ሲለኝ ፥ ቢጠፋ ነው እንጂ ..
እድሌ ባይቀና ፥ ብኩን ብሆን እንጂ..
ከአስራ አምስት ቀን በፊት ፥ ለጨዋታ ብዬ ፣
ለገና ጨዋታ ፥ ለአሲና ገናዬ ፣
ዱላ እየፈለግኩኝ ፥ ከጫካ ገብቼ ፥
ሎሚ ጨፍጭፌያለሁ ፥ ዛፉን ተመኝቼ ።
እድል እንደዚህ ናት ፥ የዋርካ ስር ጤዛ ፣
ይኸው እኔ ዛሬ ፥ በዋዛ ፈዛዛ፣
እልፍ የሎሚ ዛፍ ፥ ጨፍጭፌ ሳበቃ፣
አንድ ሎሚ አጣው ፥ ለአንቺ የሚበቃ ።
አዬ እድል እያልኩኝ ፥ ከወደ አመሻሽ ፥ ከቤቴ ገብቼ ፣
ሎሚ ዛፍ ተከልኩኝ ፥ ለዓመቱ አስልቼ ።
እስከዛ ግን አንቺ .....
ሎሚ ወርዋሪዎች ፥ በሌሉበት መንገድ
ሂጂልኝ ግድ የለም፣
ዘንድሮን ያለፍኩት ፥ ሎሚ ቢጠፋ እንጂ...
ፈርቼስ አይደለም።
ወርውር ያለኝ ልቤ .....
ተግቶ ተሰናድቶ ፥ ዓመቱን ጠብቆ፥ በእለተ ከተራ ፣
እመጣለሁ ብሏል ፥ ከአስር ሎሚ ጋራ።

---------ሲራክ

@yebezdebdabewoch
🍁
ለመኖር ስትል ብዉ የህይወት መስመሮችን በራስህ ላይ ታሰምራለህ....ነገን ለማየት ስትል ጨካኝ መሆን ካለብህ ሰይጣን ምነው አንተን ባደረገኝ እስኪልህ ድረስ ትከፋለህ.... ዛሬን ለመኖር ስትል ቅን መሆን ካለብህ መልዓክ እስክትሆን ድረስ መልካም ትሆናለህ....የማትፈልገውም ወይም ተመኝተህ ያመጣኸው ባህሪ ሊሆን ይችላል...አላማህ ግን አንድ እና አንድ ነው መኖር።

በዚህ ሁሉ ነገር ውስጥ ግን የማይቀየረው የውስጥህ ማንነት መውደድ ነው። ማንንም አልወድም ብትለኝ እንኳ እመነኝ እራስህን አትጠላም....መውደድ ነውና እያንገሸገሸህም ቢሆን ትወደዋለህ....

👉👉 @yebezdebdabewoch
የበሰለ ወንድ ምረጪ እህቴ "
ስትሳሳቺ የሚያርምሽ ......ስትቆጪ የሚያበርድሽ ........ስታዝኒ የሚያፅናናሽ .......ስትጎድሊ የሚሞላሽ.......ዋጋሽን የሚያዉቅ ወንድ ምረጪ
ያልበሰለዉማ ........ስትሳሳቺ ስህተትሽን ይቆጥርልሻል........ስትቆጪ ስም ይሰጥሻል........ስታዝኚ ይሸሽሻል.......ስትጎድሊ ይተዉሻል.......ቦታሽን አያዉቅምና ያረክስሻል.......ምክንያቱም
ሳይሳሳቱ ልክ መሆን...ሳይቆጡ መረጋጋት ....ሳያዝኑ መደሰት....ሳይጎድሉ መሙላት...እንደሌለ አያዉቅም ጠባብ ጭንቅላቱ ችግርን እንጂ መፍትሄን አያስብም!
እና ሴቶችዬ የበሰለ ፈልጊ ጥሬዉን አበስላለሁ ስትይ ተቃጥለሽ ትጣያለሽ !
አንተም እንደዛዉ ብሮ!

@yebezdebdabewoch
መስሎ መገኘት ሆኖ ከመገኘት የሚበልጥበት አለም ......እውነት እያለ ውሸት የነገሰበት አለም......ዝብርቅርቅ ያለ ሂወት...... አዎ ሊከፋህ ይችላል ግን አትዘን በርግጥ እውነትን ማወቅ ትልቅ ጥረት ይጠይቃል እውነትን መናገር ደግሞ ትልቅ ድፍረት ይጠይቃል.
እናም በሰዎች አትፍረድ አንተ ግን በቻልከው መጠን በራስህ መንገድ ለመሄድ ሞክር ቢያንስ ማነህ ስትባል መልካም ነኝ ለማለት የሰውን ደስታ መውደድ አለብህ አንችም ማነሽ ስትባይ ክብር ነኝ ለማለት ሰውን ከመናቅ መቆጠብ አለብሽ ያኔ ታዲያ ሂወት ትርጉም ይኖረዋል Hab❤️
@yebezdebdabewoch
ተወደድክ ተጠላህ ፤ ተሳካልህ አልተሳካልህ ፤ ተከበርክ አልተከበርክ ፤ ሀብት መጣ አልመጣ ...ቀጭን ሆንክ ወፍራም ፤ ደቃቃ ሆንክ ግዙፍ ፤ አዋቂ ሆንክ መሀይም ....ደንታ የማይሰጣትን.."ዛሬ ምን ይሆን..? ነገስ ምን ይከሰት ይሆን..?" ብላ የማትጨናነቀዋን...ምንም ሊገላት ፤ ማንም ሊያቆስለው ፤ ምንም ሊያሸብራት ፤ በምንም ልትጎዳ የማትችለውን...ከማንም ምንም የማትጠብቀዉን ፤ የማትፈልገውን..ያቺን ያንተን አንተነትህን ያገኘህ ግዜ ...እሷን ያወቅክ ጊዜ...የዛን ግዜማ በመኖርህ እንደ ዛፎቹ እና ወፎቹ ሀሴት ታደርጋለህ።❤️

@yebezdebdabewoch
ስቄ ሸኝሀለሁ😁😁
አትሂድ የኔ አለም ያላንተ አልችልም መኖር ይከብደኛል እሞትብሀለሁ ተመለስ ግዴለም አልልህም። አንተ እኛነትን ትተህ እኔነትን መርጠሀልና ጩኽቴ ምን ሊለውጥ አትሂድ ልበልህ። እንደው ተለምነኸኝ ብትቀር እንኳን ልብህ የኔ አደለምና አለመሄድህ ምን ይረባኛል። አዎ አባት በመቅረትህ ከምትሄድ በመሄድህ የሚቀረው ትዝታህ ይጠቅመኛል። ለምን አልልህም ምኔ አነሰብህ፣ ምን አጎደልኩብህ🤔🤔 ልልህም አልሻም ግን መውደዴ ዛሬ እኮ መልካሙን ልመኝልህ ነው አዎ ዛሬ እኮ እንድለቀው የጠየከኝን እጅህን ልለቀው ነው ይገርማል አደል አለሜ እኔ እኮ ያላንተ ኑሮን ለመጀመር እየተዘጋጀሁ ነው ፍቅርህን ላዳፍነው እንጂ ልቀብረው እንደማልችል እያወኩ ልሰናበትህ ነው። ግን እኮ አላዘንኩም ለምን እንደሆነ ታቃለህ አንተ ነበርክ ፍቅር ለሚወዱት ደስታ መስጠት ነው ያልከኝ አዎ አባት ያለከልካይ ይዤ የነበረው እጅህን ላንተዋ ላስረክባት ነው። በል በቃ ደህና ሁን አዎ የኔ እምነት አልቅሼ ሳይሆን ስቄ ሸኝሀለሁ!!!
@yebezdebdabewoch
መሄድ የፈለገን ሰው ታዘገየዋለህ እንጂ አታስቆመውም::
@yebezdebdabewoch
ባዶ በርሜል

ባዶ በርሜል ስታንከባልለው ይጮሀል፡፡በዛው ልክ በውሀ የተሞላን በርሜል ስታንከባልለው ድምፅ የለውም፡፡ሲንከባለልም በእርጋታ ነው፡፡የሰው ልጅም እንደዛ ነው፡፡ ጭንቅላቱ ባዶ የሆነ ሰው ከመጮህ እና ከመቸኮል የዘለለ ማድረግ ሚችለው ነገር የለም፡፡ በእውቀት የተሞላ ሰው ግን ዝምተኛ እና የተረጋጋ ነው፡፡ በጮህን እና በቸኮልን ልክ ጭንቅላታችን ይገመታል፡፡


ከዶ/ር ምህረት ደበበ
@yebezdebdabewoch
አንዳንዶች ያጨሳሉ........አንዳንዶች ይጠጣሉ..........አንዳንዶች ያፈቅራሉ..........ሁሉም በየሚሞትበት መንገድ ላይ ሱሰኛ ይሆናል....


@yebezdebdabewoch
🍁መውደድ😘

በመውደድ ሁሉም አለ። ጅማሬ እንዳለው ሁሉ ፍፃሜውም ከጁ ነው....መውደድ ማፍቀር አይደለም መውደድ ጥላቻ አይደለም....መውደድ መኖር አይደለም መሞትም አይሆንም...መውደድ መውደድ ብቻ ነው.... በልብ ውስጥ ሀይል ያለው ልንፈታው የማንችለው ቅኔ ነው መውደድ....

@yebezdebdabewoch
እሱን ያለ ልቤ ሲውል ሲከተለው
አይኑ ላይዞር ከኔ ብቻዬን ሳፈቅረው
ፍቅር ሆኖ ጥሩ አይቼ በሌላ
ምነው ለኔ ግዜ ዘዴ ታጣ መላ
@yebezdebdabewoch
ጨረቃዋ ደምቃ ላይን ብትታይም
የናፈቀህ ልቤ አላስተዋላትም
ሰማይ እና ምድሩ ቢደምቁ ተውበዉ
አልደምቅልሽ አለኝ ካንተ ዉጪ ያለው
@yebezdebdabewoch
ሰላም እንዴት አመሻችሁ ዉድ ተከታታዮቻች ን ከዚህ ቀደም ብዙ ስራዎች ስንሰራ እንደቆየን ይታወቃል ግን በአንዳንድ ምክንያቶች ጠፍተናል በአዲስ መልኩ የተለያዩ ስራዎች ይዘን እንቀርባለን ነገ ጠዋት ይጠብቁን🙏

አስተያየት ካላችሁ 👉 @Enate_Y

@yebezdebdabewoch
HTML Embed Code:
2024/04/27 00:23:50
Back to Top