Channel: Addis Ababa Education Bureau
በአዲስ አበባ ከተማ የ2017በዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል 88.8 % ያህሉ 50% እና ከዛ በላይ በማምጣት ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስታወቁ።
(ሰኔ 17/2017 ዓ.ም) ኃላፊው በዛሬው እለት የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በማስመልከት ለተለያዩ የመንግስትና የግል የመገናኛ ብዙኃን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰተዋል።
በከተማ አስተዳደሩ የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤት በየአመቱ መሻሻል በማሳየት ላይ መሆኑን ኃላፊው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫው ጠቁመው በ2017 ዓ.ም ፈተናውን ከወሰዱ 70,525 ተማሪዎች መካከል 88.8 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች 50% እና በላይ አስመዝግበው ወደ ቀጣዩ የክፍል ደረጃ መሸጋገራቸውን አስታውቀዋል።
ዶክተር ዘላለም አያይዘውም የ2017 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤታማ እንዲሆን ከተማ አስተዳደሩ ለትምህርት ሴክተሩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ቤት ምገባን

ጨምሮ የደንብ ልብስ እና ሌሎች ተጨማሪ የትምህርት ግብአቶች ማቅረቡ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን ገልጸው በየትምህርት ቤቱ የማጠናከሪያ ትምህርትን ጨምሮ ተማሪዎች በቴሌቪዥን የሚማሩበት አማራጭ መመቻቸቱ እና ባለድርሻ አካላት በቅንጅት መስራታቸው ለውጤቱ መገኘት ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን አመላክተዋል።
ዘንድሮው በከተማ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡ 20 ተማሪዎች መካከል 13 የሚሆኑት በእቴጌ መነን የልጃገረዶች እና በገላን የወንዶች አዳሪ ትምህርት ቤቶች የተማሩ መሆናቸው አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ የተቋቋሙበት አላማ ስኬታማ መሆኑን እንደሚያሳይ ኃላፊው በመግለጫቸው ጠቁመው የዘንድሮው ውጤት በ2016ዓ.ም ከነበረው የ78.9% ወደ 88.8% ማደጉን በመግለጽ መምህራንን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ተማሪዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ ላበረከቱት አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።
ተፈታኝ ተማሪዎች ከታች የተቀመጠውን ሊንክ በመጠቀም ከዛሬ ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት እንደሚችሉ በጋዜጣዊ መግለጫው ተጠቁሟል።
https://aa.ministry.et/#/result
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc

ቀደም ሲል በስትራቴጂክ እና ጠቅላላ ካውንስል ደረጃ የተገመገመውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የመደበኛ እና የሪፎርም ስራዎች እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 የትምህርት ዘመን መሪ እቅድ እንዲሁም የ90 ቀናት እቅድ ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ተገመገመ ::
(ሰኔ 17/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ቀደም ሲል በስትራቴጂክ እና ጠቅላላ ካውንስል ደረጃ የተገመገመውን የ2017 የመደበኛ እና የሪፎርም ስራዎች እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 የትምህርት ዘመን መሪ እቅድን ከቢሮ ሰራተኞች ጋር ገመገመ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ አስተባባሪ ወ /ሮ አበበች ነጋሽ በውይይቱ ላይ ባስተላለፉት መልእክት በትምህርት ዘመኑ ቁልፍና አበይት ተግባራት የታቀዱ ሥራዎች የላቀ ውጤት የታየባቸው መሆኑን አስታውሰዋል:: በተጨማሪም ቀደም ሲል በስትራቴጂክ እና ጠቅላላ ካውንስል ደረጃ የተገመገመውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 የመደበኛ እና የሪፎርም ስራዎች እቅድ አፈጻጸም እና የ2018 የትምህርት ዘመን መሪ እቅድን ከቢሮ ሰራተኞች ጋር መገምገም በማስፈለጉ መድረኩ መጠራቱን ገልጸዋል :: አያይዘውም የዉይይቱ ተሳታፊዎች የ2017 ትምህርት ዘመን አጠቃላይ ስራችንን በመገምገም ክፍተት የታየባቸውን በሙሉ አቅምና በበለጠ የስራ ተነሳሽነት ለመስራት የሚያስችሉ ገንቢና ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች እንዲሰጡ ይጠበቃል ብለዋል::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፅ /ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ በበኩላቸው ያለፈው በጀት ዓመት አፈፃፀምና የቀጣይ እቅድ ላይ ውይይት መደረጉ ቢሮው ያለውን የአፈፃፀም አቅም የምናይበትና በቀጣይ ለሚኖረን ሥራ ራሳችንን የምናዘጋጅበት ይሆናል ብለዋል:: አክለውም የውይይቱ ተሳታፊዎች የሚሰጡትን እቅድ ማዳበሪያ ሀሳብ በማከል የተማሪ ውጤትን ለማሻሻል በበለጠ ትጋት ለመስራት ራሳችንን እናዘጋጅ ብለዋል ::
በውይይቱ የእቅድ በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የ2017 ትምህርት ዘመን ስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸምና የ2018 ትምህርት ዘመን ረቂቅ እቅድ አቅርበዋል:: በተያያዘም የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የ2017 በጀት አመት የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት የቅንጅታዊ ስራዎች እቅድ አቅርበው በቀረቡትን ሪፖርቶች የሚያዳብሩ ፍሬ ሀሳቦች በተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል ::
በእቅድ ግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጠቅላላ ሰራተኞች እና ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
በውይይቱ የእቅድ በጀት ዝግጅት ክትትል ግምገማ ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ የ2017 ትምህርት ዘመን ስትራቴጂክ እቅድ አፈጻጸምና የ2018 ትምህርት ዘመን ረቂቅ እቅድ አቅርበዋል:: በተያያዘም የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ድጋፍ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፈንታሁን እያዩ የ2017 በጀት አመት የአገልግሎት አሰጣጥና መልካም አስተዳደር ስራዎች አፈጻጸም ሪፖርትና የ2018 በጀት አመት የቅንጅታዊ ስራዎች እቅድ አቅርበው በቀረቡትን ሪፖርቶች የሚያዳብሩ ፍሬ ሀሳቦች በተሳታፊዎች ተነስተው ውይይት ተደርጎበታል ::
በእቅድ ግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጠቅላላ ሰራተኞች እና ስትራቴጂክ ካውንስል አባላት በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ::
መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያውን ይጫኑ!
https://linktr.ee/aacaebc
በከተማ አስተዳደሩ በበይነ መረብ (online) ለሚሰጠው የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ የቅድመ ዝግጅት አካል የሆነ የሙከራ ፈተና በዛሬው እለትም በሁሉም የመፈተኛ ጣቢያዎች ተሰጥቷል።
(ሰኔ 17/2017 ዓ.ም) በዛሬው እለት በተሰጠው የሙከራ ፈተና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ አመራሮችን ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የሁለቱ ሴክተር ባለሙያዎች በየፈተና ጣቢያው በመገኘት ሂደቱን የተከታተሉ ሲሆን በዛሬው እለት የተሰጠው የሙከራ ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ከየፈተና ጣቢያው የተገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።
የዛሬው የሙከራ ፈተና ከሰኔ 23/2017 ዓ.ም ጀምሮ ለሚሰጠው መደበኛ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በአግባቡ መዘጋጀት እንዲችሉ ምቹ ሁኔታ እንደፈጠረላቸው የሙከራ ፈተናውን የወሰዱ ተማሪዎች አረጋግጠዋል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ሙሉ ለሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት የተለያዩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች እየተከናወኑ የሚገኝ ሲሆን የዛሬው የሙከራ ፈተና ፈተናውን በበይነ መረብ ለመስጠት የተዘጋጁ የመሰረተ ልማቶች ብቁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚያስችል መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ገልጸዋል።

በ2018 የትምህርት ዘመን ማስተማር የማይችሉ የትምህርት ተቋማትን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን ይፋ አድርጓል።
(ሰኔ 18/2017 ዓ.ም) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን በ2018 የትምህርት ዘመን ማስተማር የማይችሉና እውቅናቸው የተሰረዘ ትምህርት ቤቶችን አሳውቋል።
በ2016 ዓ.ም ማጠቃለያ ላይ በተደረገው የእድሳት ፍቃድ ምዘና ለ2017 የትምህርት ዘመን ካሳዩት ዝቅተኛ ውጤት መሻሻል እንዲያሳዩ እስከ 2017 ዓ.ም ታህሳስ ድረስ ዝግጅት እንዲያደርጉ ፤ በ2017 የትምህርት ዘመን ላይ በማስጠንቀቂያ እንዲያስተምሩ ጊዜ ቢሰጣቸውም በታህሳስ 2017 በተደረገ የእድሳት ፍቃድ ምዘና ውጤታቸው መሻሻል ባለማሳየቱና ዝቅተኛና ከደረጃ በታች በመሆኑ ምክንያት በ2018 የት/ት ዘመን ማስተማር የማይችሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር ባለስልጣን አሳውቋል።
በመሆኑም የትምህርት ማህበረሰቡ እና ወላጆች ይህን በማወቅ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እንድታከናውኑ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ስልጠና ጥራት ቁጥጥር አሳውቋል።

HTML Embed Code: