TG Telegram Group Link
Channel: አርማጌዶን
Back to Bottom
[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia (RSS)

ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

— ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡

— ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ?

— ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው።

— ምኑ ነው ግራ ያጋባህ?

— የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ።

— አልገባኝም?

— አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን ሰምቼ ግራ ግብት ብሎኛል።

— ምንድነው የተናገሩት?

— ዛሬ ይህንን ድልድይ እንዳስመረቅነው ሁሉ የትርክት ድልድይ መገንባትም ያስፈልገናል አሉ።

— የምን ድልድይ?

— ቆይ የተናገሩትን ቃል በቃል ልንገርህ።

— እሺ…

— ‹‹በአማራና በኦሮሞ፣ በአማራና በትግራይና በሌሎችም ሕዝቦች መካከል በአልባሌ ትርክቶች ምክንያት እየላላ ያለውን ትስስር ሊያጠናክር የሚችል የትርክት ድልድይ መገንባትም እንፈልጋለን፤›› ነው ያሉት።

— እና እንደዚያ ማለታቸው ግራ ያጋባል እንዴ?

— ድልድይ መገንባት እንፈልጋለን ማለታቸውማ ጥሩ ነገር ነው።

— ታዲያ ድልድይ እያስመረቁ ድልድይ ማፍረስ ያልከው ምኑን ነው?

— ከቀናት በፊት ወደ ምዕራቡ አካባቢ ሄደው የተናገሩት ትዝ ብሎኝ ነዋ?

— እዚያ ሄደው የተናገሩትን እንኳ አልሰማሁም፣ ምንድነው ያሉት?

— ሕዝባችን በገዛ አገሩ ለመቶና ከዚያ በላይ ዓመታት እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ ቆይቷል፣ ዛሬ ግን ነፃ ወጥቷል።

— ታዲያ ይህን ማለታቸው ምን ችግር አለው?

— ኢትዮጵያ ውስጥ በመሪዎች የተጨቆነው አንድ ማኅበረሰብ ብቻ ነው እንዴ?

— እሱስ ልክ ነህ ሁሉም ተጨቁኗል።

— ዛሬ ደግሞ በአልባሌ ትርክቶች ምክንያት እየላላ ያለውን የሕዝቦች ትስስር ሊያጠናክር የሚችል የትርክት ድልድይ መገንባት አለብን ይላሉ፡፡

— ይህንን ማለታቸው ትክክል አይዳለም እያልክ ነው?

— ትክክል አይደለም!

— ምኑ ነው ትክክል ያልሆነው?

— ማኅበረሰባችን ቀደም ሲል የጨቆኑትን መሪዎች የብሔር ማንነት እየቆጠረ ዛሬ እርሱ በእርሱ ተካሮ ሳለ እንዲህ ያለ ንግግር ተገቢ አይደለም፡፡

— በእርግጥ እንደዚያ ባይናገሩ ጥሩ ነበር።

— ይኼን ብቻ መሰለህ እንዴ የተናገሩት?

— እ… ሌላ ምን ብለዋል?

— በታሪክም ቢሆን ሕዝባችን ለጠላት ጭቆና የተዳረገው የውስጥ አንድነት ስላልነበረው ነው፣ ዛሬ ከጠላት ጋር ውይይት ማድረግ ትልቅ ውርደት ነው፣ ስለዚህ ከዚህ ስህተት ተምረን በአንድነት በመቆም ጠላቶቻችንን እንመክት።

— እንደዚያ ማለት አልነበረባቸውም፣ ግን ያው…

— እ… ያው ምን?

— አልፎ አልፎ የአፍ ወለምታ ሊያጋጥም ይችላል።

— ከጭቆና ተነስተው ዛሬም ጠላቶቻችንን እንመክት እስከማለት የደረሱበትን ንግግር ነው የአፍ ወለምታ ነው የምትለኝ?

— ለእኔ ወለምታ ነው የሚመስለኝ።

— በጭራሽ! ይኼ የአፍ ወለምታ ሳይሆን አቅደው የተናገሩት ነው።

— እንደዚያ አንኳን እርግጠኛ መሆን የሚቻል አይመስለኝም።

— በደንብ ይቻላል፣ ከፈለግክ ንግግራቸውን ሲጀምሩ የተናገሩትን አድምጥ፣ ያኔ ጠላት ያሉት ማን እንደሆነ ጭምር ይገለጽልህ ይሆናል።

— ንግግራቸውን ሲጀምሩ ምንድነው ያሉት?

— ሕዝባችን ያሳለፈውን ጭቆና ለእናንተው መልሶ መናገር አልፈልግም፣ ነገር ግን አጠገቤ ላሉት እንግዶች እንዲገባቸው በደንብ እነግራቸዋለሁ።

— እንግዶቹ እነማን ነበሩ?

— በቦታው ላይ የተገኙ ናቸዋ!

— በሕዝብ ፊት እንደዚያ መናገር አልነበረባቸውም ቢሆንም ግን…

— እ… ቢሆንም ምን?

— እኔ አሁንም የአፍ ወለምታ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ።

— በዝርዝር የተነገረ ሐሳብ እንዴት የአፍ ወለምታ ይሆናል?

— እኔ በበኩሌ እሳቸው እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ አላቸው ብዬ አላምንም።

— ምክንያት?

— ምክንያቱም እኔ ለአገራቸው ያላቸውን ፍቅር በደንብ አውቃዋለሁ።

— ምንድነው የምታወቀው?

— በየትኛውም አጋጣሚ ስለኢትዮጵያ እያወሩ ከሆነ…

— እ…?

— በዓይናቸው ዕንባ ግጥም ይላል።

— የምርህን ነው!?

— የምሬን ነው።

— ወንድሜን!

— ምነው?

— እንዲያው አንድ ወንድሜን!

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ገብተው ከባለቤታቸው ጋር እየተጨዋወቱ ሳለ ባለቤታቸው ስለቴሌቶኑ ጥያቄ አነሱ]

— እንዲያው ምን ስትሉ ነው ቴሌቶን ውስጥ የገባችሁት?

— የምን ቴሌቶን?

— ቴሌቶኑን ነዋ? በአንድ ጀንበር 50 ሚሊዮን ብር ያላችሁትን?

— ኦ… እሱንማ ከዕቅዳችን በላይ አሳክተን አጠናቀቅነው እኮ፣ አልሰማሽም?

— እሱንማ ሰምቻለሁ፣ የእኔ ጥያቄ ገንዘቡን ለምን ፈልጋችሁት ይሆን ብዬ ነው?

— ዘመናዊ የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን ለመገንባት ነዋ።

— የት ነው የምትገነቡት?

— አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ።

— አዲስ አበባ የት አካባቢ?

— የኮሪደር ልማቱ በሚያልፋባቸው አካባቢዎች።

— እኔም እኮ መጠየቅ የፈለግኩት እሱን ነው።

— ምኑን?

— በዚያ አካባቢ የሕዝብ መፀዳጃ ቤት ለምን ይገነባል?

— እንዴት? ምን ማለትሽ ነው?

— ሕዝብ በሌለበት?

— ለምን የለም?

— እንዲነሳ ተደርጓላ።

— ለምንድነው የሚነሳው?

— ለኮሪደር ልማቱ!

The post [ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት] first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by በጋዜጣዉ ሪፓርተር
የተመድ የፍልስጤም አባልነት ውሳኔና ተጠባቂው የፀጥታው ምክር ቤት ምላሽ
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia (RSS)

ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia

የተመድ የፍልስጤም አባልነት ውሳኔና ተጠባቂው የፀጥታው ምክር ቤት ምላሽ

ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ሙሉ አባልነት ተገድባ የኖረችው ፍልስጤም፣ የድርጅቱ አባል እንድትሆን የቀረበው የውሳኔ ሐሳብ በአብላጫ ድምፅ ድጋፍ ያገኘው ዓርብ ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. ነበር፡፡

143 አገሮች የደገፉት፣ ዘጠኝ አገሮች የተቃወሙትና 25 አገሮች በድምፅ ተአቅቦ ያለፉት የፍልስጤም የአባልነት ጥያቄ በአብላጫ ድምፅ ቢያልፍም፣ የአባልነት ጥያቄው ምሉዕ እንዲሆን የፀጥታው ምክር ቤት ውሳኔ ይጠበቃል፡፡

በተመድ የእስራኤል አምባሳደር ጊላድ ኤርዳን የፍልስጤም የሙሉ አባልነት የውሳኔ ሐሳብ በተመድ በአብላጫ ድምጽ መፅደቁን ተከትሎ ተቃውሟቸውን የድርጅቱን

መተዳደሪያ ደንብ ቅጂ በመቅደድ አሳይተዋል (ኤኤፍፒ)ጋር መክረዋል

(ሮይተርስ)
የፀጥታው ምክር ቤት በቀጣይ በፍልስጤም የተመድ አባልነት ላይ የሚሰጠው ምላሽ አዎንታዊ ከሆነ፣ ፍልስጤም እ.ኤ.አ. ከ2012 ጀምሮ ከተሰጣት የታዛቢነት ወንበር ተሸጋግሯ መምረጥና መመረጥን ጨምሮ ምሉዕ የአባልነት መብት ይኖራታል፡፡

ከ193 የተመድ አባል አገሮች ውስጥ በ139 አገሮች የአገርነት ዕውቅና ያላት ፍልስጤም፣ ከእስራኤል ጋር ባለው የግዛት ይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ከሃያላን አገሮች የምታገኘው ድጋፍ እዚህ ግባ የሚባል አይደለም፡፡

በተለይ የፍልስጤም ጋዛን የሚያስተዳድረው ሃማስ ከእስራኤል ጋር በተደጋጋሚ የሚገባበት ግጭትና ጦርነት ለፍስጤምና ፍልስጤማውያን መከራ ሆኗል፡፡

ከሰባት ወራት በፊት በእስራኤልና በጋዛ መካከል በተነሳው ጦርነት ከ34 ሺሕ በላይ ፍልስጤማውያን፣ ከአንድ ሺሕ በላይ እስራኤላውን ሕይወታቸውን ተነጥቀዋል፡፡

በፍልስጤም ግዛቶች ውስጥ እስራኤል መስፋፋቷና ዜጎች ማስፈሯ፣ በየጊዜው በሁለቱ አገሮች መካከል ለሚነሱ ግጭቶች አንዱ ምክንያት ተደርጎ ይነሳል፡፡ የእየሩሳሌም የይገባኛል ጥያቄና ሌሎችም በሁለቱ መካከል የተፈጠሩ ቁርሾዎች፣ ምዕራቡ ዓለምና የመካከለኛው ምሥራቅ አገሮች ልዩነት ውስጥ እንዲገቡም አድርጓል፡፡

እስራኤልና ፍልስጤምን ለማስማማት የተደረጉ ውይይቶችም ዘላቂ መፍትሔ አላመጡም፡፡ ከሁለቱ አገሮች በሚመነጭ ሐሳብ በቀጣናው ሰላም ለማስፈን የፍልስጤም የተመድ ሙሉ አባልነት አስተዋጽኦ ቢኖረውም፣ ዛሬም በአሜሪካ ይበልጡኑ የምትደገፈው እስራኤል፣ የፍልስጤምን አገርነትም ሆነ የተመድ አባልነት አትቀበለውም፡፡

የተመድ አባል አገሮች በአብላጫ ድምፅ ውሳኔ ሲያስተላልፉም፣ ‹‹ለፍልስጤም የአባልነት ዕድል መሰጠቱ ሽብርተኝነትን እንደመደገፍ ነው›› ስትል እስራኤል ተቃውማለች፡፡

ፍልስጤም በበኩሏ፣ አባል አገሮቹ በአብላጫ ድምፅ ያሳለፉት ውሳኔ በፀጥታው ምክር ቤት ለሚሰጠው ውሳኔ ማሳያ መሆኑን ገልጻለች፡፡

የተመድ ጠቅላላ ጉባዔ፣ የፍልስጤምን የሙሉ አባልነት ውሳኔ ሐሳብ የፀጥታው ምክር ቤትም እንዲያፀድቀው ሲጠይቅ፣ በተናጠል አገሮች ምክር ቤቱ ፍልስጤምን እንዲቀበል ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡

ቻይና ፍልስጤም በተመድ ውስጥ ያልተገደበ መብት ሊሰጣት ይገባል ስትል ሐሳቧን ገልጻለች፡፡

ከሰባት ወራት ወዲህ በእስራኤልና ፍልስጤም ጋዛ መካከል የተቀሰቀሰውን ጦርነት ተከትሎ፣ በአሜሪካ በተለያዩ ግዛቶች እንዲሁም በአውሮፓ አገሮች የሚገኙ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እስራኤል በፍልስጤም ላይ የምታደርውን ወታደራዊ ዕርምጃ እንድታቆም በተቃውሞ እየጠየቁ ባለበት ወቅት፣ ከዚህ ቀደም ባልተለመደ መልኩ አብላጫው የተመድ አባል አገሮች ለፍልስጤም አባልነት ድጋፍ ሰጥተዋል፡፡

የኖርዌይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርን ጠቅሶ አናዶሉ እንዳቀረበው፣ የኖርዌይ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፀጥታው ምክር ቤት ለፍስልጤም ሙሉ አባልነት እንዲሰጥ ጠይቋል፡፡  

ኖርዌይ፣ ፍልስጤም እ.ኤ.አ. በ2012 የታዛቢነት ወንበር እንድታገኝ ከደገፉ አገሮች አንዷ ስትሆን፣ አሁን ላይም የፍልስጤም የተመድ ሙሉ አባል መሆን፣ በቀጣናው ያለውን ችግር ለመፍታት ያስችላል ብላ ታምናለች፡፡

ከወር በፊት ፍልስጤምን የተመድ ሙሉ አባል ለማድረግ ለፀጥታው ምክር ቤት በገባው ማመልከቻ፣ 12 የፀጥታው ምክር ቤት አባላት የፍልስጤምን ሙሉ አባልነት ሲደግፉ፣ አሜሪካ ድምፅን በድምፅ የመሻር መብቷን ተጠቅማ ውድቅ እንዳስደረገችው ይታወሳል፡፡

The post የተመድ የፍልስጤም አባልነት ውሳኔና ተጠባቂው የፀጥታው ምክር ቤት ምላሽ first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by ምሕረት ሞገስ
ለፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ትግል መቀዛቀዝ ምክንያቱ የጠራ ርዕዮተ ዓለም አለመኖር ወይስ የምሁራን መዳከም?
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia (RSS)

ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia

ለፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ትግል መቀዛቀዝ ምክንያቱ የጠራ ርዕዮተ ዓለም አለመኖር ወይስ የምሁራን መዳከም?

መሬት ላራሹ ብለው በተነሱ ተማሪዎችና ምሁራን ድምፅ የተቀጣጠለው የመጀመሪያው የኢትዮጵያ አብዮት፣ ከኢምፔሪያሊዝም ወደ ሶሻሊዝም በተደረገ ርዕዮተ ዓለም ለውጥ ከተደመደመ ዘንድሮ ግማሽ ምዕተ ዓመት አስቆጥሯል።

ኢትዮጵያ ከ1966 ዓ.ም. በኋላ ከጥቂት ዓመታት በፊት የተደረገውን ጨምሮ የተለያዩ በትጥቅ ትግልና በተቃውሞ ጫና የተፈጠሩ ለውጦችን አስተናግዳለች።

ነገር ግን አሁን 50 ዓመታትን ያስቆጠረውን አብዮት የቀሰቀሱትም ይሁን ተከትለውት የመጡት የመሬት ባለይዞታነት መብት ጉዳይ፣ የብሔር ትግልና ማንነት ተኮር ፖለቲካ ጥያቄዎች አሁንም እንደቀጠሉ ናቸው።

እነዚህ ጥያቄዎች ላለፉት 50 ዓመታት ሳይመለሱ መቀጠላቸው የአገሪቱንም ሆነ የአገረ መንግሥቱን ግንባታ ሲፈታተኑት ይታያል።

ያለመፍትሔ እየተወሳሰቡ መሄዳቸው እስካሁን ድረስ በሒደት የመጡ የተወሰኑ ለውጦችንም ወደኋላ እንዳይቀለብሱ የሚያሠጋቸው ጥቂቶች አይደሉም።

የጥያቄዎቹ አለመመለስ በአገሪቷ ላይ የደቀኑት ሥጋት ሲነሳ ለአብነትም የሚጠቀሱት በተለያዩ የአገሪቷ ክፍሎች የተቀሰቀሱና የቀጠሉ ግጭቶች፣ በሁለት የተለያዩ ጫፎች ላይ የቆሙ የማኅበራዊና የፖለቲካ ዕሳቤዎችና እንቅስቃሴዎች ናቸው።

በታሪክ ከዚህ ቀደም እንደተስተዋለው የመፍትሔ ሐሳቦችን በማፍለቅና በኅብረተሰቡ ዘንድ በማስረጽ በኩል የምሁራንም ይሁን የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሚና ከመቼውም ጊዜ በላይ ተቀዛቅዞ መገኘቱ፣ በእርግጥም በግማሽ ምዕተ ዓመት ውስጥ እየተጋጋሉ የመጡትን ጥያቄዎች ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ውጤት ማምጣት መቻላቸው ላይ ተስፋ ሰጪ የማይመስል አጠራጣሪ ሁኔታዎችን ፈጥሯል።

የሕግ አማካሪና ጠበቃ አቶ አንዷለም ቡኬቶ ይህን አስመልክቶ ለሪፖርተር በሰጡት ምላሽ፣ አሁን ያሉ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያላቸው ሚናና አስተዋጽኦ በ1966 ዓ.ም. ለውጥ ማምጣት የቻሉትን ያህል ያልሆነበትንና እየቀነሰ የመጣበት ያሏቸውን የተማሪዎችን ብዛት፣ የትምህርት ጥራትና የኢኮኖሚያዊ አቅም ጉዳይ ጋር የተያያዙ ምክንያቶችን አስቀምጠዋል።

መጀመሪያ ላይ ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ወይም ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የደረሰው ተማሪ፣ በ1960ዎቹ በጣም ትንሽ የሚሆነውን ክፍል ወይም ሕዝብ ቁጥር ነበር የሚይዘው ያሉ ሲሆን፣ ከአገር በቀል እውቀት ውጭ ላለው ለምዕራባዊውም ሆነ አጠቃላይ እውቀት በመባል ለሚነሳው ጉዳይ የተሻለ ተጋላጭነት (Exposure) የነበረው ተማሪ ነበር ብለዋል።

አቶ አንዷለም ‹‹ከዚህ አንጻር ተማሪ ቁጥሩ ትንሽ በመሆኑ ብቻ የመሪነት ሚና ነበረው። እንደ መሪም ይታይ ነበር። ከቤቱ ተማሪ የወጣበትም ቤተሰብም በልዩ ሁኔታ ነበር የሚታየው። በወቅቱ ተማሪ የተሳሳተ ሐሳብ እንኳን ቢኖረው በዚያን ወቅት በሕዝቡ ዘንድ የመቀበል ነገር ነበር። ምንም ቢሆን የሚያውቁት ነገር አለ ተብሎ ስለሚታመን። ያደጉት አገሮች የደረሱበትን ነገር ሰምተዋል አውቀዋል ተብሎ ስለሚታሰብ። በአገሪቱ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ጉዳዮች ላይ በሕዝቡ ዘንድ ተፅዕኖ ፈጣሪ የሆነበት ሚና ነበረው፤›› ሲሉ ተናግረዋል።

ይህ ለአሁኑ ትውልድ ተግባራዊ ሊሆን የማይችል ሁኔታ እንደሆነ የገለጹት የሕግ ባለሙያው፣ የተማሪዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ መጨመሩን በማንሳት ይህ ብቻ እንደ መሪ የሚታይበትን አቅም እንደሚቀንሰው ገልጸዋል።

በሁለተኛነት በ1960ዎቹ ጊዜ የነበረው የትምህርት ጥራት ደረጃና አሁን ያለው ልዩነት አስተዋጽኦም ከፍተኛ እንደሆነ ይናገራሉ።

በወቅቱ የነበሩ የከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስን መሆን በፈጠረው ሁኔታም ጭምር ከማኅበረሰቡ ውስጥ እጅግ በጣም ጥቂት የሚባሉ ተማሪዎች ተጣርተው የሚያልፉበት አሠራር እንደነበረ በመግለጽ፣ ዩኒቨርሲቲን ይቀላቀሉ የነበሩት ጥቂት ባለብሩህ አዕምሮ ባለቤቶች ነበሩ፡፡ ይህ በመሆኑ ብቻ በዕውቀታቸው ልህቅና ላይ ተዓማኒነት እንዲኖር አድርጓል ብለዋል።

በተቃራኒው አሁን ያለው የትምህርት ጥራት ወድቋል ያሉት አቶ አንዷለም፣ ይህን ወላጅም፣ ቤተሰብም ሆነ የወጡበት ማኅበረሰብ በጠቅላላ የሚረዳው እውነታ ነው ሲሉ ገልጸውታል።

‹‹አሁን ላይ ተምሮ የመጣውም ካልተማረው ብዙም ልዩነት የለውም። ስለዚህ ተማሪ  የኢኮኖሚም ይሁን የማኅበራዊ ወይም የፖለቲካ ጥያቄዎችን አንስቶ ቢወጣ እንኳን በሕዝቡ ዘንድ ይህን ልጅ አናውቀውም እንዴ? ምን ተምሮ? ምን አውቆ? ነው ተብሎ የሚጠየቅበት ዝቅተኛ ቦታ ተሰጥቶታል። ተማሪ በሕዝቡ ዘንድ የሚሰጠው ቦታ እንደ ድሮ አይደለም፤›› ያሉ ሲሆን፣ በዚህም ምክንያት የተማሪ የመሪነት ሚናው ቀንሷል ብለው እንደሚያምኑም ገልጸዋል።

በሌላ በኩል በ1960ዎቹ የለውጥ ጥያቄዎችን የሚያነሱ ተማሪዎች በሥርዓቱ ከፍተኛ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ጥቅም ከሚያገኝ ሀብታም ቤተሰብም ጭምር የወጡ እንደነበሩም ተጠቅሷል። ይህ ደህና የሚባል የኢኮኖሚ ደረጃ ሁኔታ ተማሪዎቹ የሚያጡት ነገር አልነበረም ሊያስብል የሚችል ማለትም የገዛ ቤተሰባቸውን ጥቅም የሚያስቀሩና የሚቃረኑ ሐሳቦችንም ያነሱ እንደነበር ሲገለጽ፣ አብዛኛዎቹ የቀድሞ ተማሪዎች የነበራቸው ነገር ተምሬ ቤተሰቤን ልርዳ የሚል ጫና የሚፈጥር (survival) ጉዳይ እንዳልነበራቸው ተገልጿል።

ይህ ሁኔታም መሬት ላራሹን ጨምሮ የኅብረተሰቡን ጥያቄዎች የማንሳት ዕድል እንደሰጣቸው ተነግሯል። ከዚህ በተቃርኖ አሁን ይህ አስቻይ ሁኔታ በእጅጉ የተመናመነ ነው ተብሏል።

የሕግ ባለሙያው አቶ አንዷለም ‹‹አሁን ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚገባው አብዛኛው የደሃ ልጅ፣ እንዲሁም ከትምህርት ቤት ቢባረር መጠጊያ መውደቂያ የሌለው ነው። ከዚህ አንጻር የአሁን ተማሪ ያ መታገል የሚያስችለው የኢኮኖሚ አቅም የለውም፤›› ሲሉ ተናግረዋል።

አሁን ታዋቂ የነበሩ በስልሳዎቹ ዓመታት ወቅት የተማሪዎችን ትግል ይመሩ የነበሩ ሰዎችን እናገኝ ነበር፡፡ አስተማሪዎቻችንም ነበሩ፣ ከትምህርት ቤት ተመርቆ ከተማሪዎች ትግል ላለመራቅ ሲባል የወቅቱ ተማሪዎች ሆነ ብለው የተወሰኑ የትምህርት ዓይነቶችን በመውደቅ የቆይታ ዓመታት ይጨምሩ እንደነበር ሲገለጽ፣ በአሁን ወቅት ግን እንደዚህ ዓይነት ማድረግ የሚያስችል ሁኔታ የለም ተብሏል።

የ1966 አብዮትን የፊት ለፊት ገጽ ሆነው የኅብረተሰቡን ጥያቄ ምላሽ እስኪያገኝ ድረስ ያስተጋቡት እና የትኛውንም ጫና ተቋቁመው የተጋፈጡት ተማሪዎችና ምሁራን እንደነበሩ የተለያዩ የታሪክ መጻሕፍት ሲያስረዱ፣ በአሁን ወቅት በከፍተኛ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ግን የሕዝብ ጥያቄ በሆኑ ኢኮኖሚያዊ፤ ፖለቲካዊ፤ ማህበራዊና ሌሎችም ጉዳዩች ላይ ጥያቄ ማንሳት ጋር እንኳን ሳይደርስ የትኩረት ጉዳያቸው የመሆኑ ሁኔታ ከሚጠበቀውም ይሁን ከሚፈለገው አንጻር ሲታይ ይህን ያክል ተብሎ ሊጠቀስ የማይችል መሆኑም በተለያዩ መድረኮች
ሕይወትም እንዲህ ናት!
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia (RSS)

ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia

ሕይወትም እንዲህ ናት!

ከዊንጌት ወደ አየር ጤና ነው የዛሬው የጉዞ መስመራችን፡፡ አንዳንዴ በአድካሚው ውጣ ውረድ በበዛበት ሕይወት ውስጥ፣ ለራስ ፋታ ሰጥቶ ውጣ ውረዱን መገምገም የግድ ይሆናል፡፡ በሥራም ሆነ በትምህርት ምክንያት በቀን ቢያንስ አንድ ጊዜ ታክሲ ውስጥ ገባ ብሎ መውረድ አይቀርም፡፡ ይህ ጉዳይ የሚመለከተው መኪና የሌላቸውን ብቻ ነው፡፡ ታዲያ በታክሲ ሲሄዱ አፌ ቁርጥ ይበልላችሁ የሚባሉ፣ ወይም ደግሞ አፋችሁ ይቆረጥ መባል የሚገባቸው ወያላና ሾፌር ሊያጋጥሙን ይችላሉ፡፡ በአንዳንድ ሥርዓተ አልባ ወያላዎች የተማረሩ ሰዎች፣ ‹እግዜር ይይላችሁ› ብለው ተራግመው ሲወርዱ፣ ሌሎች ደግሞ ለመብቴ መንግሥትንም ሆነ እግዜርን መጥራት አይጠበቅብኝም በሚመስል ስሜት የአፍ ጦርነት ይማዘዛሉ፣ ይጨቃጨቃሉ፣ የሚቧቀሱም አይጠፉም፡፡ እነሱ እንደሚሉት መብታቸውን ያስከብራሉ ማለት ነው፡፡ መብት ለማስከበር የምንሄድበት ርቀት እንደ ቁርጠኝነታችን የሚለያይ መሆኑን መርሳት የለብንም፡፡ መብት ለማስከበር የዓላማ ሰው መሆኑን መገንዘብም እንዲሁ!

ብዙ ጊዜ ወያላዎች፣ ‹‹መብቴ ነው…›› የሚላቸው ሰው ጠላታቸው ነው ሊባል ይችላል፡፡ ‹‹መብታችሁ ታክሲ ውስጥ ትዝ አይበላችሁ…›› በማለት ታክሲያቸው ውስጥ በሰቀሉት ጥቅስ ይከራከራሉ፡፡ ከዚህም አልፈው ተርፈው ካሳፈሩት ሰው ጋር ይጨቃጨቃሉ፣ ይወዛገባሉ፡፡ በአንድ በትንሽዬ አጋጣሚ ሳይሆን በርስት ወይም በሌላ ንብረት የሚከራከሩ ነው የሚመስሉት፡፡ አንድ ሰው፣ ‹‹ወገኖቼ ኧረ በደህና ነገር እንጨቃጨቅ፣ ማን ይሙት አሁን ደህና ውይይት የሚሻ አገራዊ ጉዳይ ጠፍቶ ነው እንደዚህ በረባ ባልረባው የምንነታረከው?›› አለ፡፡ ሌላኛው ሰው ደግሞ፣ ‹‹አየህ ሰው በርካታ ብሶቶች ሳይኖሩበት አይቀርም፡፡ ስለዚህ ትንሽ ነካ ስታደርገው በሆዱ ውስጥ አፍኖ ያቆየውን ሁሉ ይዘረግፈዋል፡፡ ወዶ አይደለም በሰው አትፍረድ፤›› አለው፡፡ ነገሩ ይፈረድብሃልና ነው፡፡ ከህሊና በላይ ፈራጅ ማን ይሆን!

የሁለቱ ሰዎች ክርክር ታክሲዋን በከፊል ተቆጣጠራት፡፡ የመጀመሪያው ወጣት፣ ‹‹ቢሆንም ለአገርም ለሕዝብም በሚጠቅሙ ጉዳዮች ላይ መከራከር ያዋጣል፡፡ በማይረቡ ጉዳዮች ጊዜያችንን እያጠፋን አዕምሮአችንን ከምናደንዘው ጠቃሚ ጉዳዮች ላይ መነጋገሩ ይበጀናል…›› ሲል አንዲት ወጣት ደግሞ፣ ‹‹እውነት ነው፣ ለምን ስለዓባይ ጉዳይ አናወራም? ለምን ሕገ መንግሥቱን በተለመለከት እኛም ሐሳብ አንለዋወጥም? ኧረ እንዲያውም ወሳኝ ስለሆነው ሐሳብን የመግለጽ ነፃነት ላይ ለምን አንነጋገርም? የኑሮ ውድነት ሊያደርስ የሚችለውን ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ጉዳት እንዴት ማስወገድ እንደምንችል አንመክርም?›› በማለት አስተያየቷን ሰነዘረች፡፡ ወሬውም እየጦፈ ሄደ፡፡ ወጣቱና ወጣቷ በእነዚህ ጉዳዮች ላይ የራሳቸውን ወግ ቀጠሉ፡፡ ሌሎች ተሳፋሪዎች አፌን በዳቦ ያሉ ይመስል ጭጭ አሉ፡፡ አንድ ጎልማሳ በታፈነ ድምፅ፣ ‹‹አሁን ፖለቲካ ምን ያደርጋል? ክፉ እያናገሩ ለክፉ ይዳርጉናል…›› አለ፡፡ የማይለቀንን ነገር እየሸሸን የት እንደበቅ ያሰኛል እኮ!

ወያላው በተጀመረው ውይይት ብዙ የተመሰጠ አይመስልም፡፡ ለሾፌሩ የድሮ ታሪኩን ይተርክለት ጀመረ፤ ‹‹ድሮ ልጅ እያለሁ ጫማ የሚባል ነገር ጠላቴ ነበር…›› አለ፡፡ ቀጥሎም፣ ‹‹እግር ኳስ እንኳን ታኬታ ካደረጉ ልጆች ጋር በባዶ እግሬ ነበር የምጫወተው፡፡ የመጫወቻ ሥፍራዬ ተከላካይ ነበር…›› አለ፡፡ ሾፌሩም፣ ‹‹እሺ እባክህ እስቲ በደንብ አጫውተኝ…›› በማለት ለታክሲዋ ነዳጅ እየሰጠ ወያላውም እንዲያወራ ቆሰቆሰው፡፡ ወያላው ቀጠለ፣ ‹‹ቅፅል ስሜ ‹ቀልጥመው› ነበር፡፡ እያቆላመጡ ‹ከቀልጥም ኳስ ቢያልፍ እግር አያልፍም› ሲሉኝ በቃ ማንም ይሁን እንኳን በታኬታ በታንክ ቢመጣ ማንንም አላሳልፍም ነበር፡፡ ኳሱን አታሎኝ ቢያሳልፍ ልጁን ግን ተዓምር ቢፈጠር አላሳልፈውም…›› እያለ ተረከለት፡፡ አያችሁ ጎበዝ እንዲህ ዓይነቶቹ እኮ ናቸው ሊቀለጥሙን ያሰፈሰፉት!

ወያላው በዚያ እንደ ብረት በሚከተክተው እግሩ የስንቱን ቅልጥም እንደሰበረ ሲናገር የጦር ሜዳ ውሎ የሚተርክ ይመስል ነበር፡፡ ሾፌሩ ብስጭት እያለ፣ ‹‹በፈጠረህ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አንተን አሠልፈውህ ቢሆን ኖሮ በሰላሳ አምስተኛ ሰከንድ ፈጣን ጐል እየገባብን ሪከርድ ላያችን ላይ አይሰበርም ነበር…›› አለው፡፡ ይኼኔ ወያላው፣ ‹‹እባክህ እነሱን ተዋቸው እንኳን የአፍሪካ ዋንጫን ይቅርና የበረኪና ዋንጫ አያነሱም፡፡ አታስታውስም እንዴ ከምድብ ማጣሪያ ማለፍ አቅቶን በጊዜ ስንሸኝ?›› አለ፡፡ ወያላው ቀጥሎ፣ ‹‹እኔን ግን ሠፈር ውስጥ በጣም የሚያማርሩኝ ልጆች ነበሩ…›› በማለት የድሮውን እያስታወሰ ይስቅ ጀመር፡፡ ሾፌሩም፣ ‹‹ለምንድን ነው የሚያማርሩህ? አታነክታቸውም እንዴ?›› አለው፡፡ እሱም፣ ‹‹ያላነከትኩት የለም፣ ግን ትችታቸውን አያቆሙም፡፡ አንዴ ምን እንዳሉኝ ታውቃለህ?›› አለው፡፡  ሾፌሩም፣ ምን ብለው እንደ ተቹት ለመስማት እየጓጓ፣ ‹‹ደግሞ ምን አሉህ?›› አለው፡፡ ወያላው ከመናገሩ በፊት ሒሳብ መሰብሰብ ጀመረ፡፡ ይኼኔ ቅድም የተጀመረውን ወሬ ለመስማት ፋታ ተገኘ፡፡ የመጀመሪያው ወጣት አንድ ነገር ሲናገር ጆሮአችንን ውስጥ ጥልቅ አለ፡፡ ጆሮአችን ያልቻለው ጉድ የለም!

የመጨረሻው ወንበር ላይ በጥግ በኩል የተቀመጠው ወጣት፣ ‹‹በአንድ አገር ውስጥ የሕዝብ ንዴት በየትኛው ቅጽበት እንደሚነሳ ማወቅ አይቻልም…›› ብሎ የተወሰኑ ሰዎችን ጆሮዎች ሰበሰበ፡፡ ቀጥሎም፣ ‹‹ትዝ ይላችሁ እንደሆነ ለዓረብ አገሮች የፀደይ አብዮት መነሻ በሆነችው ቱኒዚያ በተነሳው አመፅ፣ ራሱን አቃጥሎ በመግደል ለቱኒዝያውያን መነሳሳት ምክንያት የሆነው ሰው ይህን ያህል ቀውስ እንደሚያስከትል መንግሥት ቢያውቅ ኖሮ፣ እንኳን መንገድ ላይ አትክልት አትሽጥ ሊለው ይቅርና እባክህ ቤተ መንግሥት ውስጥ ገብተህ የፈለግከውን ሽጥ ብለው ሁኔታዎችን ያመቻችለት ነበር…›› ሲል መሀል ወንበር ላይ ለብቻው የተቀመጠ ጎልማሳ፣ ‹‹እኔ እንዲያውም የፕሬዚዳንቱ ገበታ ላይ በየቀኑ እንዲሳተፍ የሚያደርጉት ይመስለኛል፡፡ ፕሬዚዳንቱ እያባበሉና እያጎረሱት ያሞላቅቁት ነበር…›› ሲል፣ የባሰ አታምጣ አልን በሆዳችን፡፡ የመጀመሪያው ወጣት ከሰውዬው አፍ ተቀብሎ፣ ‹‹ስለዚህ አመፅ የቱ ጋ በምን ቅጽበት እንደሚነሳ ማወቅ አይቻልም፡፡ የኑሮ ውድነት በፈጠረው ጭንቀት የአዕምሮ ሁከት የሚያጋጥማቸው ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ስለሚሄድ፣ መንግሥትም ሆነ ፀጥታ አስከባሪዎች የሚወስዱት ዕርምጃ ከፍተኛ ጥንቃቄ ያስፈልገዋል…›› አለ፡፡ ወጣቱን ምን እንዳስጨነቀው በቅጡ ባይታወቅም ከመናገር የሚገታው ጠፋ፡፡ ‹‹ውኃ ቀጠነ ብለን በመንግሥት ላይ መማረር አንፈልግም፡፡ ነገር ግን እንጀራችን ሲቀጥን፣ ዳቦአችን ሲያርና የሚያሰማራቸው ሹሞች የዘፈቀደ ዕርምጃ ሲወስዱ ዝም ብለን መቀመጥ አንችልም፡፡ ስለዚህ ተገቢው ድጋፍና ማበረታቻ ሊደረግልን ይገባል…›› አለ፡፡ ብዙዎች አይናገሩም እንጂ ከተናገሩ ይዘረግፉታል!

የወጣቱ እንደዚያ መማረር ያስገረማቸው አንድ አባት
ላይ በሚቀርቡ ወቀሳዎች እንዲሁም በሚነሱ ሐሳቦች ላይ ይስተዋላል።

አቶ አንዷለም የተማሪዎች ፍላጎትና ተነሳሽነት ማጣትን አስመልክቶ ለሪፖርተር በሰጡት ማብራሪያ የፖለቲካ ጥያቄ የሚባለው በጊዜ ብዛት ወደ ብሄር ተሻግሮ አንድ ጥግ ይዟል ይላሉ።

‹‹ያን ጊዜ ተማሪ ያነሳ የነበረው ጥያቄ፣ ተማሪውን ሊበትን የሚመጣው አድማ በታኝ እንኳን፣ የሚነሳውን ጥያቄና ሐሳብ ውስጥ ለውስጥ ይጋራው ነበር። ለምሳሌ ከ60ዎቹ የተማሪ ጥያቄዎች መካከል የኑሮ ውድነትን ወይም መሬት ላራሹ እንደነበር መጥቀስ ይቻላል። እነዚህን አንስተው ሲታገሉ አድማ በታኙም ፖሊስ ቢሆን፣ ወታደሩም ይሁን ደህንነቱ ወይ አርሶ አደር አባት ያለው አልያም ደግሞ ደሃና ለጥያቄው መነሻ ያለው ነው። ስለዚህ በግላጭም ባይሆን ይደግፈው ነበር፤› ሲሉ ተናግረዋል።

አሁን ያለው ሁኔታ ከዚህ በእጅጉ የራቀ እንደሆነ ተብራርቷል። የፖለቲካ ጥያቄው ቅርጹን ከመቀየር ባሻገር ያልቆመ ቢሆንም አሁን በየኮሌጁና ዩኒቨርሲቲው የሚነሳው የፖለቲካ ጥያቄ የብሔር እንደሆነ ግልጽ ነው።

‹‹በየከፍተኛ ትምህርት ተቋሙ የፖለቲካ ጥያቄን ቅርጽ የያዘ የብሔር ግጭት ነው ያለው። በብሔርና በጎሳ ቡድን ይቧደኑና ይፈነካከታሉ፣ ትምህርት ይቋረጣል፣ በባለፉት አምስት ዓመታት ስናየው የነበረ ነው›› ብለዋል አቶ አንዷለም።

ይህ የተማሪዎቹ ሁኔታ ወደ ኅብረተሰቡ ወርዶ የመሪነት ሚና ሊያሰጥ እንደማይችልና የኅብረተሰቡ ጥያቄም ሊባል እንደማይችልም ተናግረዋል፡፡

ይህን ጉዳይ ትኩረት ሰጥተው የሚከታተሉ ምሁራን እንደሚገልጹት፣ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ የብሔር ጥያቄ የሚነሳው ከሚኖሩበት የተወሰነ ቦታ ወጥተው በሌላ አካባቢ በሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ ለመደባደብ፣ ለመጣላትና ጸብ ለማንሳት ያክል እያደረጉት ያሉት እንጂ፣ ይህ ነው ተብሎ ሊጠቅስ የሚችል የወጡበትን ማኅበረሰብ የሚወክል ወሳኝ ማኅበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ወይም ፖለቲካዊ ጥያቄ ተማሪ አነሳ ሊያስብል የሚችል እንዳልሆነ ይናገራሉ።

የሕግ ባለሙያው አቶ አንዷለም ይህን አስመልክተው ‹‹የብሔር ፖለቲካ ሙሉ ለሙሉ ፖለቲካ አይደለም ባልልም፣ አድማ በታኙ ትግላቸውን እንዲቀላቀል የሚያስችላቸው ግን አይደለም። ምክንያቱም አድማ በታኙ፣ ፖሊሱ ወይም ደኅንነቱ የተቃዋሚው ብሔር አባል አይደለም። በዚህም ምክንያት ተቃውሞው የሕዝብ ጥያቄ አነሳ የሚያስብል አይደለም›› ብለዋል።

የ66 ዓ.ም. አብዮትን ያስቻሉት ተማሪዎች ያነሷቸው ጥያቄዎች የቡድን እንዳልነበሩ፣ ይልቁንም አብዛኛውን የኅብረተሰብ ክፍል የሚያስማሙ ጉዳዩች ላይ ያተኮሩ እንደነበሩና አሁን እንደ እነዚህ ዓይነት ጥያቄዎች ያን ያክልም እንደማይስተዋሉ፣ በአገሪቱ የታሪክና የፖለቲካ ዘርፎች ላይ ተሰማርተው አንቱ የተባሉ ምሁራን በተለያዩ መድረኮች በስምም ሲገልጹት ይታያል።

አቶ አንዷለም ከዚህ ጋር አያይዘው አሁን ዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያለ ተማሪ፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የብሔር ፖለቲካ ውስጥ ከገባች በኋላ የተወለደ እና በስርዓቱ ውስጥ ያደገ እንደሆነ በማንሳት፣ ይህም ካለፉት አርባ ዓመታት በላይ እየጎለበተ ከመጣው የብሔር ፖለቲካ ጋር ሲተያይ በተማሪዎች የሚነሳ ጥያቄ ሰፊ ድጋፍ ያገኛል ብለው እንደማያምኑ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በሰለሞናዊ ሥርወ መንግሥት ሥር ለ700 ዓመታት እየተመራች ስትቆይ፣ የነበረው ፖለቲካ በቤተ መንግሥት ተወስኖ ማን ይንገሥ ማን አይንገሥ በሚል ላይ ተገድቦ መቆየቱን ያነሱ ሲሆን፣ ሰፊው ሕዝብን ያማከለ ፖለቲካ ግን እንዳልነበረ የታሪክ መዛግብት ያስረዳሉ።

ሰፊውን ሕዝብ ያማከለ ፖለቲካ ከተጀመረ በኋላ ባለው ጊዜ ግን ለአብነትም፣ ቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴን ከመንበር ያወረደው ፖለቲካ የሚመስለው የነበረው የምሁራን ተሳትፎ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበረው ቢሆንም፣ በስተመጨረሻ ግን ሥልጣን የተረከበው ወታደራዊ ኃይሉ እንደነበር ይታወቃል።

ከዚህም በኋላ ይህን ወታደራዊ ኃይል ለመታገል የተፈጠሩ አንዳንድ የፖለቲካዊ አደረጃጀቶች ጅምር ቢታይም፣ የደርግን ወታደራዊ ኃይል የጣለው ግን ሌላ ወታደራዊ ኃይል ማለትም የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዩታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) እንደነበር ይታወሳል።

ልክ እንደ ተማሪዎች ሁሉ፣ የምሁራንም የፖለቲካ ሚና ቀንሷል ሲሉ የሚሟገቱት የሕግ ባለሙያው አቶ አንዷለም፣ የኢሕአዴግንም ኃይል ከሥልጣን ያነሳው ቅንጅትን የመሳሰሉ ትልቅ ድጋፍ አግኝተው የነበሩ ወይም ሌሎችም የፖለቲካ ፓርቲዎች ሳይሆኑ፣ ከራሱ ከኢሕአዴግ ውስጥ የወጣ ሌላ ኃይል ነው ይላሉ።

እንደ እርሳቸው አስተያየት፣ እነዚህ ተከታታይ የታሪክ ኩነቶች የኢትዮጵያ ሕዝብ ፖለቲካውን በእውቀት መለወጥ ሳይሆን ጉልበት ነው የሚቀይረው የሚል እየዳበረ የመጣ ዕሳቤ እንደያዙና ተስፋ የመቁረጥ ነገር እንደሚታይ አውስተዋል፡፡

‹‹አሁንም ድረስ ኃይል ያላቸው አካላት እርስ በርስ ሲጣጣሉ ይታያል። ወይም ኃይል ላይ ያለው ቡድን እርስ በርስ ይከፋፈል ይሆናል እንጂ ምሁራን ተሰብስበው የፖለቲካ ፓርቲ አቋቁመው፣ ፕሮግራሞቻቸውን ጽፈው፣ ታግለው ምን አመጡ የሚል አመለካከት አለ›› ሲሉ ተናግረዋል።

በተደጋጋሚ በኃይል በተደረገ እንቅስቃሴ የመንግሥት ሥልጣን ለውጥ ስለተደረገ የዚህ ልምምድ የፖለቲካ ሐሳብን በጠመንጃ የማራመድ ሁኔታ ይሁንታን ያገኘ ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።

በማብራሪያቸው አሁንም የመንግሥትን ሥልጣን የያዙት አካላት ምሁራን በዕውቀታቸው ያመጡት ለውጥ እንደሌለ፣ ይልቁንም በኃይል በተደረገ እንቅስቃሴ እንደሆነ የመታየት ነገር መኖሩንና ይህ ደግሞ ደርግን በጣለው በኢሕእዴግ የአገዛዝ ዘመንም ይስተዋል የነበረ ኩነት መሆኑን ጠቅሰዋል። አክለውም ከእነዚህ ነጥቦች በመነሳት የምሁራን የፖለቲካና ኢኮኖሚያዊ አስተዋጽኦም ይሁን ሐሳባቸው በሕዝብ ዘንድ ያለው የተቀባይነት ደረጃ መቀነሱን ገልጸዋል።

በዚህ ሒደት ውስጥ የአገሪቱ ምሁራን በተለያዩ መድረኮች፣ በንግግሮቻቸው፣ አደረግን የሚሏቸውን ጥናት ጠቅሰው በሚያቀርቧቸው ጽሑፎች በኩል ሲታዩ ሁለት የተለያዩ ጫፎች ላይ ቆመው ሲሟገቱ ይስተዋላሉ፣ በአንድ ጎራ አሁን ያለው የክልሎች በወሰን ተከልሎና በቋንቋ ተከፋፍሎ ተግባራዊ እየተደረገ ያለው የአስተዳደር ሒደት መፍረስና የቀደመው አንድነታዊ አካሄድ መመለስ አለበት የሚሉ ምሁራን ሲኖሩ፣ በሌላኛው ጥግ ደግሞ በትንሹ የክልል አስተዳደር ከፍ ሲልም ቋንቋን መሠረት ያደረገው ፌዴራሊዝም በፍጹም መነካት የለበትም የሚሉ ሙግቶችን የሚያቀርቡ ምሁራን፣ ሕዝቡን የሚጠቅመው የእኔ ሐሳብ ብቻ ነው የሚሉ አካሄዶች ላይ የመጠመዳቸው ትዝብት የአደባባይ ሚስጥር መሆኑን ብዙዎች ያነሳሉ።

ይህን ዓይነት የምሁራን ክፍፍል የሕዝቡን የየዘርፍ ጥያቄዎች የ66 ዓ.ም ዓይነት አብዮት መፍጠር የሚያስችል አስተዋጽኦ እንዳይኖራቸው አግዷቸዋል፡፡ ተፅዕኖ ፈጣሪነታቸውን ነስቷቸዋል የሚሉ አስተያየት ሰጪዎች ጥቂት የሚባሉ አይደሉም።

በሌላ በኩል ምሁራን አሁን ባለው ሁኔታ የሚያነሷቸው ጥያቄዎች ተቀባይነት እንዲመነምን ካደረጓቸው ጉዳዩች መካከል፣ ትኩረታቸው በመደብ ወይም ሰፊውን ሕዝብ በአጠቃላይ በሚመለከት የኢኮኖሚ ጉዳይ ከመሆን ይልቅ፣ እርስ በርሳቸው የየራሳቸውን የግል ማንነት ወይም ብሔር ጋር የተያያዘውን ጉዳይ ብቻ ተንተርሰው ቆመው መገኘታቸው፣ በሕዝቡ ዘንድ ያላቸውን አመኔታ እንደሸረሸረውም የሚገልጹ አሉ።

‹‹ቅድሚያ ለሰብአዊ መብቶች ኢትዮጵያ›› (Human Rights First) የተባለ አገር በቀል የሲቪል ማኅበር ዋና ዳይሬክተርና የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቶ ተስፋለም በርሃ በበኩላቸው፣ በስልሳዎቹ ወቅት የበላይነት
ኤስ ኦ ኤስ እና ወርቅ ኢዮቤልዩ
ሪፖርተር – Ethiopian Reporter – #1 Best and reliable news source in Ethiopia (RSS)

ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia

ኤስ ኦ ኤስ እና ወርቅ ኢዮቤልዩ

ኤስኦኤስ የሕፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ1949 ዓ.ም. ጀምሮ የቤተሰብ እንክብካቤ ላጡ ሕፃናት ቤተሰባዊ አገልግሎት ሲሰጥ የቆየው የዓለም አቀፉ ኤስኦኤስ የሕፃናት መንደሮች ፌደሬሽን አካል ነው፡፡ በኢትዮጵያ የቤተሰባቸውን እንክብካቤ ላጡ ሕፃናትና ወጣቶች ባቋቋማቸው ማዕከላት የቤተሰብ ተኮር ክብካቤ፣ የትምህርትና የጤና አገልግሎቶችን  ይሰጣል። በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ ሕፃናት፣ ወጣቶች፣ ቤተሰቦችና ማኅበረሰቦች የተጋረጡባቸውን ችግሮች አሸንፈው የተሻለ ሕይወት መገንባት እንዲችሉ እየሠራ የሚገኘው የኤስኦኤስ የሕፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት (ኢዮቤልዩ) ማክበር ጀምሯል፡፡ የተመሠረተበትን 50ኛ ዓመት  አስመልክቶ የድርጀቱ ካንትሪ ዳይሬክተር አቶ ሳህለማርያም አበበ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ለሚመለከታቸው የመንግሥት አካላትና ለጋዜጠኞች ገለጻ አድርገዋል፡፡ ምሕረት ሞገስ እንደሚከተለው አጠናቅራዋለች፡፡

ጥያቄ፡-  ኤስኦኤስ ሕፃናት መንደሮች እንዴት ተቋቋመ?

አቶ ሳህለማርያም፡- ኤስኦኤስ ሕፃናት መንደሮች በኢትዮጵያ ላለፉት 50 ዓመታት በተለያዩ ክልሎች ውስጥ ሕፃናት ላይ ትኩረት ያደረጉ መርሐ ግብሮችን ዘርግቶ ሲንቀሳቀስ ቆይቷል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ በርካታ ሕፃናትን፣ ወጣቶችን፣ ቤተሰቦችንና ማኅበረሰብን ከተለያዩ ችግሮች ታድጓል፡፡ ከነበሩባቸው አሰቃቂና አስቸጋሪ የሕይወት ገጠመኞች አውጥቶ ስኬታማ ወደሆኑ የሕይወት መስመሮች ማሻገር ችሏል፡፡ ድርጅቱ የዓለም አቀፉ የኤስኦኤስ ሕፃናት መንደሮች አባል ነው፡፡ ዓለም አቀፉ ድርጅት የተቋቋመው እ.ኤ.አ. በ1949 በኦስትሪያ ከሁለተኛው ዓለም ጦርነት ማግሥት ነው፡፡ በወቅቱ በተለያየ ምክንያት የተጎዱ ሕፃናትንና ወጣቶችን ሰብስቦ ልጆቹ ያጡትን ቤተሰብ፣ ማኅበረሰብ የመገንባት ሥራን ዓላማ አድርጎ የተነሳ ነው፡፡ በዓለም አቀፍ ደረጃ 75ኛ በኢትዮጵያ ደግሞ 50ኛ ዓመቱን እያከበረ የሚገኘው ድርጅት፣ አሁን ላይ 137 አገሮች ውስጥ ይሠራል፡፡

ጥያቄ፡- በዋናነት ትኩረቱ ምን ላይ ነው?

አቶ ሳህለማርያም፡- የቤተሰቦቻቸውን ጥበቃና እንክብካቤ ያጡና ለተመሳሳይ ችግር የተጋለጡ ሕፃናት ላይ መሥራት ዋና ትኩረቱ ነው፡፡ ተጋላጭነት ያላቸውን ወጣቶችና ሕፃናት ስናስብ፣ ያለቤተሰብ ማሰብ ከባድ ነው፡፡ ስለሆነም በሕፃናትና በቤተሰብ ልማት ላይ ይሠራል፡፡ ቤተሰብ የማኅበረሰብ አካል ስለሆነ ጠንካራ ቤተሰብ በመፍጠር ረገድ ማኅበረሰብ ጠንካራ አስተዋጽኦ ስላለው ለማኅበረሰብ ልማትም ትኩረት እንሰጣለን፡፡ ሁሉም ልጆች በቤተሰብ ታቅፈው በፍቅር፣ በሰላምና በሙሉ ዋስትና ሲያድጉ ማየትም ራዕያችን ነው፡፡ ሁሉም ልጆች ዕድገታቸውን በሚደግፍ፣ ፍቅርንና ሰላምን በሚለግስ ስብዕናቸውን፣ ልዩነታቸውንና ማንነታቸውን በሚያከብር ቤተሰብ ውስጥ እንዲታቀፉ እናደርጋለን፡፡ በቤተሰብ ታቅፈው ሲያድጉ የነገ ዕድላቸውን እንዲያስተካክሉ የሚያስችላቸውን ድጋፍ እንዲያገኙ እናደርጋለን፡፡ ማኅበረሰብ ልማት ላይ መሳተፍና የልጆች መብቶች እንዲከበሩም እንሠራለን፡፡

ጥያቄ፡- በኢትዮጵያ በምን ያህል ክልሎች ትሠራላችሁ?

አቶ ሳህለማርያም፡- ድርጅቱ በ1966 ዓ.ም. ተከስቶ የነበረውን ድርቅ ተከትሎ የመንግሥትን ጥሪ ተከትሎ ነው ወደ ኢትዮጵያ የገባው፡፡ ደርቁ በርካታ ሕፃናት፣ ወጣቶችንና ማኅበረሰቡን በእጅጉ ጎድቶ ስለነበር፣ ድርቅ አደጋ በተከሰተበት በትግራይ ክልል መቀሌ ከተማ ሥራውን የጀመረው ድርጅቱ፣ የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ ለመስጠት ቢገባም፣ ይህንን ካጠናቀቀ በኋላ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ መሥራት አስፈላጊ ስለነበር የመጀመርያው የኤስኦኤስ የሕፃናት መንደር በመቀሌ ከተማ ተደራጅቷል፡፡ በርካታ ሕፃናትና ወጣቶች በፕሮግራሙ እንዲታገዙ ተደርጓል፡፡ በጊዜ ሒደት ችግሮችንና አደጋዎችን እየተከተልን በአሁኑ ሰዓት በዘጠኝ ክልሎች ውስጥ የተለያዩ ፕሮግራሞችን እየተገበርን እንገኛለን፡፡

ጥያቄ፡- ከሕፃናት መንደርነት በተጨማሪ ምን ፕሮግራሞች አሏችሁ?

አቶ ሳህለማርያም፡- ከሕፃናት መንደር በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ ፕሮግራሞችን እየጨመርንና እያደግን መጥተናል፡፡ ብዙ ጊዜ የምንታወቀው በሕፃናት መንደር ነው፡፡ ነገር ግን ብዙ ሥራችን ያለው ማኅብረሰብ ውስጥ ነው፡፡ ከፍተኛ ሀብት የሚፈስበት ሥራችን ማኅበረሰብ ውስጥ ነው፡፡ በአንድ የአስችኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮግራም የጀመረው ድርጅታችን፣ በአሁኑ ጊዜ 41 ፕሮጀክቶችን እየተገበረ ይገኛል፡፡ ከእነዚህ ውስጥ ሰባቱ ብቻ ናቸው የሕፃናት መንደሮች፡፡ 34ቱ ማኅበረሰብ ውስጥ የሚሠሩ ፕሮጀክቶች ናቸው፡፡ ከፕሮጀክቱ አንዱ ቤተሰብ ማጠናከሪያ ፕሮግራም ነው፡፡ ለተለያዩ ችግሮች ተጋላጭነት ያላቸውን ቤተሰቦች ከመንግሥትና ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን ለይተን፣ በፕሮግራሞቻችን ታቅፈው የሚጠናከሩባቸውን ሥራዎች እንሠራለን፡፡ ተጠናክረው ለልጆቻቸው ሁለንተናዊ ዕድገት የሚያስፈልገውን ድጋፍ የሚያደርጉበት አቅም ላይ እናደርሳቸዋለን፡፡ ቤተሰብ በተለያዩ ችግሮች ምክንያት እንዳይፈርስና ልጆቻቸው ወደ ውጭ እንዳይወጡ የምናደርግበት ሥራ ነው፡፡ የማኅበረሰብ ልማት ሥራም ጎን ለጎን የምንሠራው ሌላው ፕሮግራማችን ነው፡፡ በምንገባባቸው ማኅበረሰቦች ውስጥ አገር በቀል፣ ማኅብረሰብ በቀል ከሆኑ ድርጅቶች ጋር በጋራ እንሠራለን፡፡ ከዕድር፣ ከወጣት ማኅበራት፣ ከሴቶች ማኅበራትና ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር እንሠራለን፡፡ የእነሱን አቅም እንገነባለን፡፡ ከገነባን በኋላ ለተቸገሩ ልጆች፣ ቤተሰቦች የመድረስ ሥራን እንዲከውኑ እናደርጋለን፡፡ ልጆችን ወደ ቤተሰብ የመቀላቀል ሥራም እንሠራለን፡፡ ከጎዳናና አማራጭ እንክብካቤና ጥበቃ ከሚሰጡ ድርጅቶች ልጆችን ወስደን እንንከባከባለን፡፡ ይህንን የምናደርገው ልጆች ትክክለኛው፣ ሊያድጉበት የሚገባው ቤተሰብ ውስጥ ነው ብለን ስለምናምን ነው፡፡

ጥያቄ፡- በወጣቶች ላይ ምን ትሠራላችሁ?

አቶ ሳህለማርያም፡- የወጣቶች ልማት ሥራ አንዱ ፕሮግራማችን ነው፡፡ የሥራ ፈጠራ ሥራ እንሠራለን፡፡ ወጣት ማጎልበት ላይ የተለያዩ ፕሮግራሞችን አሉን፡፡ ይህ ለወጣቶች ራሳቸውን የሚችሉበትን ዕድል የምንፈጥርበት ነው፡፡ የተለያዩ ትምህርቶችንና ሥልጠናዎችን ይወስዳሉ፡፡ የራሳቸውን ሥራ የሚጀምሩበት ፈጠራ ውስጥ የሚገቡ ከሆነ ተያያዥ ሥልጠናና የገንዘብ ድጋፍ የሚያገኙባቸው አግባብ ይፈጠራል፡፡ የንግድ ትስስር ሥራ እንሠራለን፡፡ በዚህ አግባብ ወጣቶች ራሳቸውን እንዲችሉ እናደርጋለን፡፡

ጥያቄ፡- የአደጋ ጊዜ ፕሮግራማችሁ ምን ይመስላል?

አቶ ሳህለማርያም፡- በተለያዩ
ምክራቸውን ለገሱት፣ ‹‹ተው ልጄ አንተ ገና አንድ ፍሬ ልጅ ነህ፤…› ብለው ወሬያቸውን ሲጀምሩ ልጁ ተቆጣ፡፡ ‹‹ምኔ ነው አንድ ፍሬ? ተማርኩኝ፣ ተመረቅኩኝ፣ አሁን ሰላሳ ዓመት ሊሞላኝ ነው፡፡ ታዲያ ምኑ ነው አንድ ፍሬ ያሰኘኝ?›› ሲላቸው አዛውንቱ አሁንም በሰከነ አንደበት፣ ‹‹ድሮ ወጣቱ በሰላም መኖር አይችልም ነበር፡፡ ልማት ቢባልም ለሕዝቡ ጠብ የሚል ነገር አልነበረም፡፡ ዴሞክራሲም ቢሆን አልነበረም፡፡ ያ ጨቋኝ ሥርዓት በማለፉ ፈጣሪን ማመሥገን ነው የሚገባህ…›› ሲሉት የባሰ ተበሳጨ፡፡ ‹‹ለምንድነው ዕድሜ ልካችንን ያለውን መንግሥት ካለፈው መንግሥት ጋር ብቻ የምናወዳድረው? ለምን ከአሜሪካ ወይም ከአውሮፓ ወይም ደግሞ ከእነ ደቡብ አፍሪካ ጋር አናወዳድረውም? ድሮም የወደቀ ዛፍ ምን ይበዛበታል አሉ…›› በማለት መቶ ሜትር የሮጠ ይመስል ቁና ቁና ተነፈሰ፡፡ የወጣቱ ነገር ያላማራቸው አዛውንት ዝም አሉ፡፡ ሌሎቹ ተሳፋሪዎች በሥጋት እያዩት አሁንም ዝም ብለዋል፡፡ የቅድሙ ጎልማሳ ወጣቱን በጥርጣሬ እያየው፣ ‹‹አንተ አስመሳይ ሳትሆን አትቀርም፡፡ እኛ ዝም ብለን አንተን የማያስለፈልፍህ ምንድነው?›› ሲለው ጥቂት ሰዎች ሳቁ፡፡ ወጣቱ ግን በንዴት እያየው ዝም አለ፡፡ ካልተዋወቅን እኮ የፍላጎታችን ምንጭ አይታወቅም!

የተነሳውን ወግ አይሉት ንትርክ እያሰብኩ፣ ‹‹እንዲህ ዓይነቱን ነገር እንኳን ማውራት መስማትም አንዳንዴ ሊያስጠይቅ ይችላል…›› የሚሉ ጎረቤቴን ምክር ተግባራዊ ማድረግ ከጀመርኩ ጥቂት ዓመታት ተቆጠሩ፡፡ ጎረቤቴ፣ ‹‹አንዳንዱ ባልሆነ መንገድ ወሬ ይጀምርና ወይ ያስከስስሃል ወይ ያስጠይቅሃል…›› ይላሉ፡፡ የጎረቤቴ ጥንቃቄ እኔ ዘንድ ተጋብቶ እኔም እንደ እሳቸው የጥርጣሬ ማርሼን ቀይሬአለሁ፡፡ ሾፌሩ ወያላውን፣ ‹‹በፈጠረህ ታሪክህን ቀጥልልኝ፣ ምን እያሉ ነበር የሚተቹህ?›› አለው፡፡ ወያላውም ሳያቅማማ ማውራት ጀመረ፡፡ ‹‹እንዳልኩህ ጫማ የሚባል ነገር አልወድም፡፡ እናም ሁልጊዜ በባዶ እግሬ ስሄድ ነበር ሰላም የሚሰማኝ፡፡ ታዲያ አንድ ቀን ቤተሰቦቼና እኔ የተጋበዝንበት አንድ የቅርብ ዘመድ ሠርግ ነበር፡፡ እዚያ ሠርግ ላይ ታዲያ ባዶ እግሬን መገኘት ለእኔም ሆነ ለቤተሰቦቼ ውርደት ነበር፡፡ ስለዚህ ቤተሰቦቼም እንደ ምንም ተጣጥረው አሮጌ አዲዳስ ጫማ ገዙልኝ፡፡ ያንን ጫማ አድርጌ ትንሽ ‹ወክ› ለማድረግ ከቤት ወጣ ስል እነዚህ እርጉም የሆኑ የሠፈራችን ልጆች አጋጠሙኝ…›› ብሎ ወሬውን አቋርጦ ‹‹መጨረሻ!›› በማለት አየር ጤና መድረሳችንን አወጀ፡፡ ወያላው የጀመረው ወሬ መጨረሻው ሳይታወቅ ፒያሳ ላይ ተሰነባብተን ተለያየን፡፡ ሕይወትም እንዲህ ናት! መልካም ጉዞ!

The post ሕይወትም እንዲህ ናት! first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by በጋዜጣዉ ሪፓርተር
የነበረው የርዕዮተ ዓለም ትግል እንደነበር አውስተዋል።

በዓለም አቀፍም፣ በአኅጉርም ሆነ በኢትዮጵያ ደረጃ የነበረው የርዕዮተ ዓለም ትግል እንደነበረ ገልጸው፣ ይህ አካሄድ የቀዝቃዛው ጦርነት ማብቃትን ተከትሎ ዓለም አቀፉን ትግል የሊበራሊዝም ወገን ካሻነፈ በኋላ፣ የመደብ ትግል ተቀዛቅዞ አሁን በዓለም አቀፍ ደረጃም ቢሆን እየሆነ ያለው ማንነትን መሠረት ያደረገ (nationalism) ትግል ነው ብለዋል።

አቶ ተስፋለም፣ ‹‹በኢትዮጵያም እየታየ ያለው ከሐሳብ ወይም ከርዕዮተ ዓለም ይልቅ ማንነት መሠረት ያደረገ ትግል ነው ወይም ብሔርተኝነት ነው ጎልቶ እየወጣ ያለው። በአገሪቱ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ማንነትን መሠረት ያደረግ ትግል ጠፍቷል የለም። ወደ ብሔር ወርዷል፤›› ሲሉ ተናግረዋል።

በማብራሪያቸው ድሮ ድሮ የመደብ ትግል ያገናኛቸው ነበር። ለላብ አደር፣ ለአርሶ አደር ወዘተ እየተባለ ሁሉንም ብሔር የሚያገናኝ፣ አብረው እንዲሠሩ የሚያደርግ የመደብ ትግል ነበር። ምሁራንም ይሁኑ ፖለቲካ ፓርቲዎች በእዚህ ማዕቀፍ ውስጥ ይንቀሳቀሱ የነበረ ሲሆን ‹‹አሁን ግን ወደ ብሔርተኝነት ስለወረደ ሁሉም የየራሱን ወገን ይዞ፣ የትግራዩም ስለትግራይ ነው የሚታገለው፣ የኦሮሞውም ስለኦሮሞ ነው፣ ሌላውም እንደዚያው›› ሲሉ ገልጸውታል።

‹‹ከመንግሥት ጀምሮ አሁን ያለው ፖለቲካዊ ሁኔታ በሐሳብ አይደለም፣ ይህ ነው ተብሎ ሊጠቀስ የሚችል ሁንሉንም የሚያስማማ ሐሳብ የለውም። ወጥ የሆነ ትግል እንዳይካሄድ ያደረገው በዓለም አቀፍ ደረጃ ያለው የኩነቶች ለውጥና በሀገሪቷ ያለው የፖለቲካ እሳቤ ያደረገው ሽግግር ነው›› ብለው እንደሚያምኑ ገልጸዋል።

በምሁራን መካከል የውይይት አጀንዳ ከሆኑ ጉዳዮች መካከል፣ ከ1966ዓ.ም አብዮት እስካሁን ድረስ ባሉት ዓመታት የተደረጉ የመንግሥታት ለውጦች ላይ ከተስተዋሉ ኩነቶች መካከል፣ በዋናነት ተጠቃሾቹ ሥልጣን የሚይዘው ኃይል አንድነታዊ ኃይል ሲሆን፣ የብሔርተኞች ተቃዋሚ ኃይል ሆኖ መገኘትና ብሔርተኛው ኃይል መንበር ሲይዝ ደግሞ የአንድነቱ በተቃርኖ የመቆም ጉዳይ ተጠቃሽ ናቸው።

ይህ ሁኔታ እንደዚህ ዓይነት የልዩነት ጫፎችን እንዴት ነው አስታርቆ መቀጠል የሚቻለው ወይስ ሌላ አማራጭ ሊበጅ ያስፈልጋል? የሚለውን ጥያቄ ፈጥሯል።

የሕግ ባለሙያው አቶ አንዷለም አሁን በሥልጣን ላይ ያለው ኃይል በየትኛው ወገን ነው ያለው የሚለው ጉዳይ ግራ አጋቢ እንደሆነ ተናግረዋል።

‹‹እርግጥ ነው በብሔር የተደራጀ ኃይል ነው ሥልጣን የያዘው ምንም ጥያቄ የለውም። ነገር ግን በተመሳሳይ ጊዜ ፖለቲካዊ ርዕዮተ አለሙና ሊደርስበት የሚፈልገው ግብ አንጻር ግን በእርግጥም ብሔርተኛው ኃይል ነው ሥልጣን ላይ ያለው ብዬ ለመወሰን ይከብደኛል›› ብለዋል።

ለሐሳባቸው ማስረጃ ያቀረቡት ምክንያት፣ የሚፈልገው ኃይል ነው የሚለው ጉዳይ ጥያቄ ውስጥ እንዳለ ሆኖ፣ ነገር ግን የአንድነት ኃይል የሚባለውንም ሥልጣን እንዲጋራው ማቅረቡን በመጥቀስ፣ የብሔርተኛ ኃይል ሥልጣን ይዞ የአንድነት ኃይል ተቃዋሚ ሆነ የሚለው ሁኔታ ላይ መገኘቱን ግን የሚያስረግጥ አካሄድ አይደለም ያለው ሲሉ ተናግረዋል።

‹‹በጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) የሚመራው መንግሥት በርዕዮተ ዓለም ደረጃ ሲታሰብ የአንድነት ኃይል ነው የሚመስለው›› ብለው ‹‹ወረድ ሲባልና መሬት ላይ ያለው ሲታይ ደግሞ የጎሳ ፖለቲካ ከመቼውም ጊዜ በላይ የጨመረው አሁን ነው። እንደ ግብ ግን የጠቅላይ ሚኒስትሩ መንግሥት እየሄደ ያለው ወደ ብሔርተኝነት ነው ብዬ አላምንም፤›› ሲሉ ተናግረዋል።

የአንድነት ኃይል መገለጫዎች ምንድናቸው የሚለው ጥያቄ ከሰንደቅ ዓላማም ይሁን ከቋንቋ አንፃር ወይም ሌላ ትክክለኛ መገለጫዎቹ ምንድናቸው የሚለው ጉዳይ ላይ የሚነሱ ጥያቄዎች በምሁራን መካከል ምላሽ የሚፈልግ ጉዳይ መሆኑም ተገልጿል።

በአሁን ወቅት ለሚታየው ለፖለቲካም ይሁን ለኢኮኖሚ ለውጥ የሚደረጉ ሰላማዊ ትግሎች መቀዛቀዝ ምንጭ ወሳኝ የሆነና በግልጽ የተቀመጠ ርዕዮተ ዓለም መታጣት ነው የሚሉ የክርክር መነሻ ሐሳቦች ከተለያዩ ወገኖች ይደመጣሉ።

እነዚህን ሐሳቦች የሚያነሱት አካላት በማስረጃነት የሚያቀርቡትም ለ66 ዓ.ም. አብዮት ሶሻሊዝምን እንደ ፍቱን አማራጭ አድርገው የያዙ ብዙኃን የነበሩት መሆኑን፣ የ83 ዓ.ም. የመንግሥት ለውጥም አብዮታዊ ዴሞክራሲ የሚለውን ይዞ መምጣቱን በመጥቀስ አሁን ላይ የሚደረጉ የፖለቲካ ትግሎች ግን ይህ ነው የሚባል ርዕዮተ ዓለም ሐሳብ ይዘው የሚነሱ አለመሆናቸውን ይጠቅሳሉ።

የሕግ ባለሙያው ይህ በግልጽ የሚታይ ክፍተት ነው ያሉ ሲሆን፣ በምሳሌነትም አሁን ያለው መንግሥት እየተመራበት ያለው ርዕዮተ ዓለም መደመር ነው ከተባለ፣ መደመር ርዕዮተ ዓለም ነው የሚለው ጉዳይ ግራ አጋቢ መሆኑን ተናግረዋል።

ምክንያት አድርገው ያቀረቡትም፣ አንድ ርዕዮተ ዓለም አንድን አገር ለመምራት ደርሷል ተብሎ መታየት የሚችለው መጀመሪያ በእውቀት ደረጃ ተንሸራሽሮ፣ በከፍተኛ ትምህርት ቤቶች፣ በፀሐፊዎችና በሌሎችም ደረጃ በውይይት ዳብሮና ቀስ እያለ አድጎ ርዕዮት ዓለም ለመባል ሲበቃ ነው ብለዋል።

ሶሻሊዝምም ቢሆን በአንድ ጊዜ ርዕዮተ ዓለም ለመባል እንዳልበቃ፣ ይልቁንም የማርክስን የመነሻ ሐሳብ ይዞ በዓመታት ውስጥ ዳብሮ ተቀባይነት ለማግኘትና ለመተግበር ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጸው፣ በኢሕእዴግ ተግባራዊ የተደረገው አብዮታዊ ዴሞክራሲም ርዕዮተ ዓለምም ቢሆን በተለያዩ የዓለም አገሮች ተግባራዊ የተደረገ ርዕዮተ ዓለምን ለኢትዮጵያ ማኅበረሰብ ይመጥናል ተብሎ በታሰበው መንገድ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ለሕዝቡ እንደሚገባው መጠን ከርክመው ወደታች ያወረዱት ርዕዮተ ዓለም ነው በማለት አብራርተዋል።

የ66 ዓ.ም. አብዮትን በተመለከተ ባሳለፍነው ሳምንት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትውልድ የተሸጋገሩ የአብዩቱ ትሩፋቶችና ዕዳዎች በተመለከተ በተደረገ ውይይት ላይ፣ የመሬት ጥያቄ አብዮቱን ካቀጠጣለው የመሬት ላራሹ ጥያቄ ተነስቶ አሁን ተመልሶ ገንዘብ ያላቸው ሰዎች መሬት እንዳሻቸው የሚሰበስቡበት ሁኔታ ላይ ደርሷል፡፡ እዚህ ላይ አስተያየታችሁ ምንድነው በሚል ከታዳሚዎች ለተነሳ ጥያቄ የአገራዊ ምክክር ኮሚሽነር አቶ ዘገዬ አስፋው ምላሽ ሰጥተዋል።

አቶ ዘገዬ በቀዳማዊ አፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመን በመሬት ይዞታ ሚኒስቴር ውስጥ ያገለገሉ ሲሆን፣ የመሬት አዋጅ በሚወጣበት ጊዜ አዋጁን በማረም በኃላፊነት ተሳትፈዋል። የ1983 ዓ.ም. ለውጥ ተከትሎ በተቋቋመው የሽግግር መንግሥት የሕገ መንግሥት ማርቀቅ ሒደት ላይም ተሳትፈዋል።

የመሬት ጉዳይን በተመለከተ ላለፉት 50 ዓመታት በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ያገለገሉት አቶ ዘገዬ፣ ከታዳሚ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በአሁን ወቅት ከመሬት ጋር ተያይዞ የተነሳው ሙሰኝነት በዚህ ብቻ የተወሰነ ሳይሆን አገሪቷን ካጥለቀለቀው ሙሰኝነት ጋር የተያያዘ ነው ብለዋል።

በገጠር መሬት አዋጅ መሬት አይሸጥም አይለወጥም ተብሎ የተደነገገው በአዋጁ መሠረት ራሱን እንደ ባለርስት ከሚቆጥረው አርሶ አደር ላይ ባለሀብት በማታለል መሬትን እንዳይሰበስብ ለማድረግ የተካተተ ነበር፡፡ ይህ ደግሞ አልተለወጠም ብለዋል።

ነገር ግን በመሬት ላይ ሙስና መስፋፋቱን ድርጊቱም በድብቅ ብቻ ሳይሆን በይፋ እየተደረገ የሚገኝ እየታየ የሚያስቆም ኃይል መጥፋቱ እንደሚያሳዝናቸው ገልጸዋል።

አቶ ዘገዬ ‹‹የመሬት ጉዳይ ላይ የሚታይ ሙስና በአጠቃላይ አሳሳቢና ማንም ደፍሮ የማይነካውም ስለሆነ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ደፍሮ አንድ ትልቅ ውይይት የሚያካሂድበት ካልሆነ
በስተቀር አገራችን እየጠፋት ያለች ይመስለኛል፤›› ብለዋል።

ከመሬት ጋር በተያያዘ ስላለ የሕግ ክፍተት ሲያብራሩም፣ ከ1983 ዓ.ም. በኋላ በነበረው የሽግግር መንግሥት የቀረበው የሕገ መንግሥት ረቂቅ የመንግሥት አስተዳደር ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የአንድ ግለሰብ ንብረት የሆነ መሬት ለመውሰድ ሲያስብ የሚወስነው በራሱ ሳይሆን ፍርድ ቤት ቀርቦ እንዲሆን የሚያዝ፣ የካሳ ክፍያ መጠኑም እንዲሁ በችሎት የሚወሰን እንደሚሆን የሚገልጽ እንደነበር ጠቅሰዋል።

ኢሕእዴግ ሥልጣን ከያዘ ጊዜ ጀምሮ በሥራ ላይ ባለው በፀደቀው ሕገ መንግሥት ግን ይህ እንዳልተካተተ ይልቁንም የመንግሥት አስተዳደር መሬት ከሕዝብ ላይ ሲወስድ ካሳ ብቻ እንደሚከፍል እንደሚገልጽ አስታውሰዋል።

አቶ ዘገዬ ‹‹በዚህ ምክንያት ነው በየቀበሌውና በንዑስ ወረዳዎች ውስጥ ያሉ ሰዎች ሁሉ መሬት ያስፈልጋል ብለው ሰው የሚያስነሱበት ሁኔታ የተፈጠረው›› ብለዋል።

አያይዘውም ወደፊት ይህ አንቀጽ የሚሻሻል ከሆነ ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚያመች ገልጸዋል።

በሌላ በኩል ለመሬት ሙስናው መባባስ አንዱ ምክንያት መሬት የሚያስተዳድረው የመንግሥት አካል የተማከለ አለመሆን እንደሆነ ገልጸዋል።

‹‹በአንድ ክልል እንኳን ብንወስድ ብዙ የመንግሥት የስራ ክፍሎች እጃቸውን በመሬት አስተዳደር ውስጥ ያስገባሉ። የመሬት አስተዳደርን የተማከለ ብናደርግ በአንድ አመራር ቢመራ፣ ጡንቻ ያለው የወረዳ አስተዳዳሪ ሁሉ ለከተማው ስፋት ያስፈልጋል ተብሎ ሕዝብን የሚበድልበት ምክንያት አይኖርም›› ሲሉ ተናግረዋል።

ብዙ ማጭበርበርና የመሳሰለው ነገር የሚከሰተው ከዚሁ ጋር ተያይዞ እንደሆነ አብራርተዋል።

አያይዘውም ‹‹የመሬት ጉዳይ እንደ ተራ የኢኮኖሚ ፖሊሲ ተቆጥሮ ግራና ቀኝ መሸጥ የለበትም ያሉ ሲሆን፣ በሥራ ላይ ያለውን አዋጅ ለማስከበርም ይሁን ወደፊትም የመሬት ነጠቃውን ለማስቆም በአንድ አካል መሬት ቢተዳደር በጣሙን ከፍተኛ ጥቅም የሚሰጥ ይመስለኛል›› ብለዋል።

The post ለፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ትግል መቀዛቀዝ ምክንያቱ የጠራ ርዕዮተ ዓለም አለመኖር ወይስ የምሁራን መዳከም? first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by ናርዶስ ዮሴፍ
የአገራችን ክፍሎች በተለያዩ ምክንያቶች ማኅበረሰብ ለችግሮች ሲጋለጥ እንረዳለን፡፡ ጦርነት፣ ድርቅ፣ ጎርፍና በተለያዩ ምክንያቶች ለተለያዩ ችግሮች የሚጋለጡ ቤተቦች አስቸኳይ ዕርዳታ በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ከመንግሥትና ከሌሎች አጋር ድርጀቶች ጋር በመሆንና በመተባበር የአጭርና የመካከለኛ ጊዜ የድጋፍ መስጫ ፕሮግራሞችን እንተገብራለን፡፡   

ጥያቄ፡- በትምሕርት ዙሪያ ያላችሁን ተሳትፎ ቢያብራሩልን ?

አቶ ሳህለማርያም፡- በትምህርት ሥራዎች ሰፊ ተሳትፎ አለን፡፡ በትምህርት ተቋማታችን ውስጥ የሚሠሩ ሥራዎች እንዳሉ ሆነው፣ ከመንግሥት ትምህርት ተቋማት ጋር በጋራ በመሆን ዘርፈ ብዙ ፕሮጀክቶች እንተገብራለን፡፡ የትምህርት ቤት አቅም ግንባታ፣ ትምህርት ቤቶችን መገንባት፣ የመምህራንንና የትምህርት አስተዳደር አካላትን አቅም እንገነባለን፡፡ የትምህርት መርጃ መሣሪያዎችን እንሰጣለን፡፡ ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑ ልጆችና ወጣቶች እንዲመለሱ የማድረግ ሥራዎች እንሠራለን፡፡ በጤና በኩል በጤና ተቋማት ከምንሠራው ባለፈ የጤና ፕሮግራሞችን ቀርፀን እንተገብራለን፡፡ በተለያዩ ምክንያቶች የአካል ጉዳት የገጠማቸውን የሚያሳትፉ ፕሮግራሞችን እንተገብራለን፡፡ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት የሚያገኙበትና በልማት የሚሳተፉበትን የምናጠናክርበት ፕሮጀክቶች አሉን፡፡ በእነኚህና በሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶቻችን አማካይነት በርካታ ወጣቶችን፣ ልጆችንና ቤተሰቦችን መድረስ ችለናል፡፡ ዘንድሮ ብቻ 700 ሺሕ የሚጠጉ ሕፃናት፣ ወጣቶችና ቤተሰቦችን እያገዝን እንገኛለን፡፡ ባለፉት 50 ዓመታት 8.1 ሚሊዮን የሚሆኑ ልጆች፣ ወጣቶችና ቤተሰቦች የፕሮግራም ተጠቃሚ ማድረግ ችለናል፡፡

ጥያቄ፡- በሰሜን ኢትዮጵያ በነበረው ጦርነት ለተጎዱት ምን ዓይነት ምላሽ መስጫ ፕሮጀክቶችን ተግብራችኋል?

አቶ ሳህለማርያም፡- የገንዘብ አቅርቦቱና ተደራሽነቱ በፈቀደልን መሠረት ለመሥራት ሞክረናል፡፡ ከሠራናቸው የአደጋ ጊዜ ምላሽ መስጫ ፕሮግራሞች አንዱ ሰሜን ሸዋ ላይ የሠራነው ነው፡፡ ሰሜን ወሎ፣ መቀሌና ሳምሪ ላይ ሠርተናል፡፡ እየተተገበሩ ያሉ ፕሮጀክቶችም አሉ፡፡ ሰሜን ወሎ ላይ የተሠራው ሰፊ ሥራ በብዙ አቅጣጫ ለችግር ተጋላጭ ለሆኑ ቤተሰቦችና ማኅበረሰብ ምላሽ የሰጠንበት፣ የዕለት ተዕለት ድጋፍ ያደረግንበት፣ መልሶ የማቋቋም ሥራ የሠራንበት ነው፡፡ በእነዚህ ፕሮጀክቶች በአጠቃላይ ከአሥር ሚሊዮን በላይ ዩሮ ኢንቨስት አድርገናል፡፡ በተጨማሪም በምሥራቅ፣ በደቡብ ኢትዮጵያና በኦሮሚያ የአደጋ ጊዜ ምላሽ መስጫ ፕሮጀክቶችን እየተገበርን እንገኛለን፡፡ በአሁኑ ሰዓት በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ቀውስ ያለ መሆኑ እኛም ላይ ተፅዕኖ አሳድሯል፡፡ አውሮፓና አሜሪካ አካባቢ ያለውን ሀብት የሚቀራመት ብዙ ችግር አለ፡፡ ዩክሬን ላይ ያለው ችግር ከፍተኛ ገንዘብ እየወሰደ ነው፡፡ ጋዛ አካባቢና አፍሪካ በየቦታው ያሉ ችግሮች ብዙ ገንዘብ ስለሚፈልጉ ያለውን ሀብት ይቀራመቱታል፡፡ ስለዚህ ወደ አገራችን የሚመጣው ሀብት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየቀነሰ ነው፡፡ ሆኖም አቅማችን በፈቀደ የረጂዎችን ልብ ሊገዙ የሚችሉ ፕሮፖዛልና ኮንሰፕት ኖት እያዘጋጀን ለአጋሮች እየላክን ነው፡፡ ተጨማሪ ድጋፍ ይመጣል ብለንም ተስፋ እናደርጋለን፡፡

ጥያቄ፡- ወደፊት ምን ለመሥራት አቅዳችኋል?

አቶ ሳህለማርያም፡- እ.ኤ.አ. ከ2023 እስከ 2027 ድረስ የሚዘልቅ የድርጊት መርሐ ግብር ቀርፀን ወደ ሥራ ገብተናል፡፡ በቀጣይ ሦስት ዓመታት ያሉንን የማስተባበሪያ ጣቢያዎች ከሰባት ወደ 11 የማሳደግ ዕቅድ አለን፡፡ በዚህ መሠረት አራት የክልል ከተሞች ውስጥ ተጨማሪ የማስተባበሪያ ጣቢያዎችን እንገነባለን ብለን አቅደናል፡፡ ትግራይ ክልል ውስጥ አክሱም ከተማ አንድ፣ በአማራ ክልል ከባህር ዳር በተጨማሪ ደሴ ውስጥ አንድ የማስተባበሪያ ጣቢያ እንገነባለን፡፡ አፋር ሰመራ ተጨማሪ የማስተባበሪያ ጣቢያ ይኖረናል፡፡ አርባ ምንጭ ውስጥ ሁለት ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ ሲሆን፣ የማስተባበሪያ ጣቢያ ግንባታም ተጀምሯል፡፡ እስከ 2027 ባለው ያሉንን ተደራሾች ቁጥር ከ700 ሺሕ ወደ 4.5 ሚሊዮን ለማሳደግ ዕቅድ አለን፡፡ ይህንን ለማድረግ 210 ሚሊዮን ዶላር ያስፈልገናል፡፡ ይህ ማለት አሁን ያለንን ዓመታዊ ገቢ በ30 በመቶ ማሳደግ ይጠበቅብናል፡፡ ዓመታዊ ገቢያችንን በ30 በመቶ ለማሳደግ የተጠናከረ ሥራ መሥራት ይጠበቅብናል፡፡ ለዚህም ከውጭ ዕርዳታ ለማግኘት ከምንሠራው በተጨማሪ አገር ውስጥ ሥራዎች እየሠራን ገቢ የምናገኝባቸውን አመቻችተናል፡፡ ከእነዚህ መካከል አንዱ የአገር ውስጥ ስፖንሰርሺፕ ነው፡፡ ብዙዎቹ ልጆቻችን የሚታገዙት በውጭ ዜጎች ነው፡፡ ዘር ቀለም ሳይሉ ምንም የማያውቋቸውን የውጪዎቹ ከረዱ፣ እኛ ይህ ያቅተናል ብለን አናምንም፡፡ በራሳችን ሀብት ለችግር ተጋላጭ የሆኑ ሕፃናትን ማገዝ እንችላለን ብለን ስለምናምን የስፖንሰርሺፕ ፕሮግራም ዘርግተናል፡፡ ለአንድ ልጅ ስፖንሰርሺፕ የሚያስፈልገውን በወር 500 ብር ነው፡፡ በርካታ ይህንን ማድረግ የሚፈልጉ ኢትዮጵያውያንም አሉ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የድርጅታችንን ዓላማ ለመደገፍ በንግድ ሚኒስቴር የተመዘገበ ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት የሚያደርግ ተቋም አቋቁመናል፡፡ በስድስት ክልሎች ውስጥ የትምህርት ተቋማት አሉን፡፡ ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ አዲስ አበባ ውስጥ የትምህርት ተቋም ይኖረናል፡፡ ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች እየሰጠን በሚገኘው ትርፍ በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ያሉ ቤተሰቦችና ልጆችን እንደግፋለን፡፡ የፈርኒቸር ምርት ሥራ ውስጥ ለመግባትም ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ የወተት ሀብት ልማት ውስጥ ለመግባት ጥናት እያስጠናን ነው፡፡

ጥያቄ፡- ፕሮግራሞቻችሁን ስትተገብሩ የተባበሯችሁ አካላት ማን ናቸው?

አቶ ሳህለማርያም፡- ከተለያዩ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጋር በጋራ ሠርተናል፡፡ ከኛ ሥራ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በቅርበት እንሠራለን፡፡ ከትምህርት፣ ከጤና፣ ከገንዘብ ሚኒስቴሮች ጋር አብረን እንሠራለን፡፡ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን በፈለግናቸው ጊዜ ሁሉ አብረውን ናቸው፣ ሥራችንንም ይከታተላሉ፣ ቴክኒካዊ ድጋፍ ያደርጋሉ እንዲሁም ግብረ መልስ ይሰጣሉ፡፡ በእነኚህ እየታገዝን ፕሮግራሞቻችንን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያጠናከርን ለዜጎቻችን እየደረስን ነው፡፡ ለመንግሥትም ጠንካራ የልማት አጋር የመሆን ዕድል አግኝተናል፡፡ ከእነዚህ በተጨማሪ በገንዘብና በቴክኒክ እያገዙን ያሉ ረጂ ድርጅቶች አሉ፡፡ አብዛኛዎቹ አውሮፓ ውስጥ የሚገኙ ናቸው፡፡ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ ከአሜሪካ የገንዘብ አጋር አግኝተናል፡፡ እነዚህ ናቸው እስካሁን እንድንሠራ ያደረጉን፡፡ የኤስኦኤስ ሕፃናት መንደሮች ኢትዮጵያ ሠራተኞች የዚህ ሁሉ ውጤት ባለቤቶች ናቸው፡፡ ከዚህ ድርጅት ወጥተው ራሳቸውን ችለው መልሰው የሚያገለግሉንና የሚያግዙንም ውለታቸው ከፍተኛ ነው፡፡

The post ኤስ ኦ ኤስ እና ወርቅ ኢዮቤልዩ first appear on ሪፖርተር - Ethiopian Reporter - #1 Best and reliable news source in Ethiopia and is written by ምሕረት ሞገስ
በ83 አመታቸው የዶክትሬት ዲግሪያቸውን ያገኙት አዛውንት “ለመማር አይረፍድም” ይላሉ
جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS)

ከአንድ ሴሚስተር በላይ እንደማይዘልቁ ስጋት ገብቷቸው የነበረው አሜሪካዊት ምኞታቸውን አሳክተዋል
ቱርክ በእስራኤል ላይ የቀረበውን የዘር ማጥፋት ክስ ደግፋ ለመከራከር በይፋ ጥያቄ ለማቅረብ ወሰነች
جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS)

ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በጋዛ የዘርማጥፋት ወንጀል ፈጽማለች በማለት በአይሲጄ እስራኤልን መክሰሷ ይታወሳል
ብሪታኒያ “ቻይና ትልቅ የሳይበር ስጋት ደቅናብኛለች” አለች
جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS)

የብሪታኒያ የደህንነት ኃላፊ በሳይበር ምህዳር ቀጣዩ ጥቂት ዓመታት በጣም አደገኛ ይሆናል ብለዋል
እስራኤል በሀማስ ላይ "ሙሉ ድል" ትቀዳጃለች ብለው እንደማያምኑ ከፍተኛ የአሜሪካ ባለስልጣን ተናገሩ
جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS)

የባይደን አስተዳደር እስራኤል በሀማስ ላይ "ሙሉ ድል" ብሎ እንደማያስብ የአሜሪካ ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኩርት ካምቤል ተናግረዋል
ሰባት የአፍሪካ ሀገራት በፕሬስ ነጻነት ደረጃ ከአሜሪካ እንደሚሻሉ ያውቃሉ?
جديد አል ዐይን ኒውስ (RSS)

ኢትዮጵያ ካለፈው አመት 11 ደረጃዎች ዝቅ ብላ 141ኛ ደረጃን ይዛለች
HTML Embed Code:
2024/05/15 22:28:34
Back to Top