TG Telegram Group Link
Channel: Walta Tv ዋልታ ቲቪ
Back to Bottom
በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ 70 ሺሕ ዜጎች ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

ሚያዚያ 4/2016 (አዲስ ዋልታ) በ3ኛው ምዕራፍ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ 70 ሺሕ የሚጠጉ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው የመመለሱ ስራ በይፋ ተጀምሯል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በ3ኛው ምዕራፍ ዜጋ ተኮር ዲፕሎማሲ በውጭ አገራት በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎችን ወደ ሀገር ቤት መመለስ የሚያስችል ብሔራዊ ኮሚቴ ተቋቁም ወደ ስራ መግባቱ ይታወቃል።

በሳምንት 12 በረራዎች በማድረግ በሚቀጥሉት አራት ወራት በሳዑዲ ዓረቢያ ሽሜሲ ማቆያ ማዕከል በአስቸጋሪ ሁኔታ የሚገኙ ዜጎች የመመለሱ ስራ በዛሬው ዕለት በይፋ ተጀምሯል።

ተመላሾቹ አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ የደረሱ ሲሆን በዕለቱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ነብዩ ተድላ፣ የዓለም አቀፉ ፍልሰተኞች ድርጅት ጨምሮ የሌሎች ተቋማት የሥራ ኃላፊዎች በስፍራው ተገኝተው አቀባበል ማድረጋቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ የተመራና ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ልዑካን ቡድን በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ የሳኡዲ ዓረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የመካ ግዛት ኃላፊ አምባሳደር መአዚን ቢን ሀማድ አል-ሐምሊ ጋር በሽሜሲ የማቆያ ማዕከል የሚገኙ በ10 ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎችን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ በሚቻልበት ሁኔታ ውይይት ማድረጋቸው ይታወሳል።

የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን ዜጎችን ወደ ሀገራቸው መመለስ ከሚቻልባቸው ጉዳዮች ባሻገር የኢትዮ-ሳኡዲ ዲፕሎማሲያዊ ወዳጅችነትን በንግድና ኢንቨስትመንት ዘርፎች ለማስቀጠል ስኬታማ ምክክር ማድረጋቸውም ተገልጿል።
569 የሸኔ አባላት እጃቸውን መስጠታቸው ተገለጸ

ሚያዝያ 5/2016 (አዲስ ዋልታ) በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ሸዋ ዞን 569 የሽብር ቡድኑ ሸኔ አባላት መንግስት ያቀረበውን የሰላም ጥሪ ተቀብለው እጃቸውን ሰጡ፡፡

የሽብር ቡድኑ አባላት በሕዝብ ላይ ሲያደርሱት በነበረው ዘርፈ ብዙ በደል ተጸጽተው በሰላም እጃቸውን መስጠታቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ያገኘነው መረጃ አመላክቷል።
🔥የምንሰጠው ኮርስ ከወረቀት በላይ ነው!
 AICE ኮርስን በነፃ በመማር አፍሪወርክ ላይ ለሚወጡ ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኙ ስራዎች ብቁ ሆነው ይገኙ።የሶስተኛው ዙር ምዝገባ ተጀምሯል።
ቦታዎች ውስን ናቸው፣ እንዳያመልጣችሁ!
ኢራን ከ200 በላይ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል አስወነጨፈች

ለሊቱን ኢራን ከ200 በላይ ገዳይ ድሮኖች፣ ባለስቲክ ሚሳኤሎች እና የክሩዝ ሚሳኤሎችን ወደ እስራኤል ስታስወነጭፍ ማደሯ ተሰምቷል፡፡

ጥቃቱ ከቀናት በፊት በኢራን ቆንስላ ጽ/ቤት ላይ በተፈፀመ የአየር ጥቃት ከፍተኛ የኢራን ጄኔራልን ጨምሮ 13 ሰዎች በመገደላቸው የበቀል እርምጃ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

ለሊቱን የእስራኤል ጦር በሰጠው መግለጫ ኢራን ካስወነጨፈቻቸው ሚሳኤሎች ውስጥ አብዛኛውን ማክሸፍ ተችሏል ተብሏል፡፡ ወታደሮች በሁሉም ግንባሮች ተሰማርተውና ተዘጋጅተው የእስራኤልን ግዛት መከላከላቸውን ይቀጥላሉ ሲሉም አስታውቋል፡፡
 
የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታንያሁ የኢራንን ጥቃት የመከላከል እርምጃዋን እንደምትቀጥል አስገንዝበው የማጥቃት ምላሽ እንደሚሰጡም ተናግረዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ቢሆኑም ለእስራኤል ያላቸውን ቁርጠኛ ድጋፍ ገልጸው የጂ7 አገራት ቡድን መሪዎችን አስቸኳይ ስብሰባ እንዲቀመጡ ጠይቀዋል፡፡ ይህም የተባበረ ዲፕሎማሲያዊ ምላሽ ለማስተባበር እንደሆነ የኤን ዲቲቪ ዘገባ አመላክቷል፡፡


እንደ እንግሊዝ፣ ፈረንሳይ፣ ሜክሲኮ፣ እና ኔዘርላንድ ያሉ መሰል  የአውሮፓ ሀገራትም የኢራንን ጥቃት አውግዘዋል። 

የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት ኢራን በእስራኤል ላይ ያደረሰችውን ጥቃት አስመልክቶ ዛሬ አስቸኳይ ስብሰባ ያካሂዳል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በዚሁ ዙሪያ አዳዲስ መረጃዎች ሲኖሩ ተከታትለን የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡
ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሀደ ነው

ሚያዚያ 7/2016 (አዲስ ዋልታ) ሁለተኛው ዓለም አቀፍ የሃይማኖት ተቋማት የምክክር ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

በጉባዔው የሃይማኖት መሪዎች፣ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ ሚንስትሮች ፣ አምባሳደሮች፣የአፍሪካና የዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች ተገኝተዋል።

ኮንፈረንሱ በአፍሪካ ውስጥ የሃይማኖቶች የጋራ ተግባርን ለማስከበር እና ለማበረታታት፣ ሰላምን፣ ሰብአዊ ክብርን፣ ልማትን እና አካባቢን መጠበቅ እና የጥላቻ ንግግርን ፣ ጥቃትን እና የውጭ ዜጋ ጥላቻን መከላከል በሚል መሪቃል እየተካሄደ ነው ።

በአህጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ ሠላምና ልማትን ማረጋገጥ፣ ሰብዓዊ ክብርን መጠበቅ፣አካባቢን መጠበቅ፣ የጥላቻ ንግግርንና መጤ ጠልነትን በጋራ መከላከል የሚያስችል ምክክር ማድረግ የጉባኤው ዋና ዓላማ መሆኑም ተገልጿል።

ጉባዔው የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመተባበር በኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የበላይ ጠባቂነት የተዘጋጀ ሲሆን ዛሬ እና ነገ ለሁለት ቀናት ይካሄዳል።

በሰማኸኝ ንጋቱ
🔥የምንሰጠው ኮርስ ከወረቀት በላይ ነው!
 AICE ኮርስን በነፃ በመማር አፍሪወርክ ላይ ለሚወጡ ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኙ ስራዎች ብቁ ሆነው ይገኙ።የሶስተኛው ዙር ምዝገባ ተጀምሯል።
ቦታዎች ውስን ናቸው፣ እንዳያመልጣችሁ!
ሻሸመኔ
#ከተሞቻችን

የምዕራብ አርሲ ዞን ዋና መቀመጫ የሆነችው የሻሸመኔ ከተማ ከአዲስ አበባ በስተደቡብ አቅጣጫ 255 ኪ.ሜ ርቀት ላይ የምትገኝ ሲሆን በ1913 እንደተቆረቆረች ይነገርላታል።

ከከተማዋ ስያሜ ጋር በተያያዘ እንደ አፈታሪክ የምትነሳ አንዲት "ሻሼ" የምትባል እንግዳ ተቀባይ ሴት በአካባቢው ትኖር እንደነበር እና የሻሼ ቤት ወይም በኦሮምኛ "መነ-ሻሼ" የሚለው የስፍራው ስያሜ በጊዜ ሂደት ተቀይሮ ሻሸመኔ እንደተባለ በታሪክ ይወሳል።

ወይና ደጋ የአየር ንብረት ያላት የሻሸመኔ ከተማ ከባህር ጠለል በላይ 1937 ሜትር ከፍታ ላይ ትገኛለች።

ጀምበር የማይጠልቅባት የሻሸመኔ ከተማ የዞኑ ዋና የንግድ እና የትራንስፖርት ማዕከል ስትሆን ሐዋሳን ጨምሮ ወላይታ እና ዲላን የምታገናኝ ባለ5 በር ኮሪደር ከተማ ነች።

የተለያዩ ብሄረሰቦችን በጉያዋ ያቀፈችው ሻሸመኔ በ12 ወረዳ እና 4 ክፍለ ከተማዎች የተዋቀረች ስትሆን አቦስቶ፣ ጎፋ፣ አዋሾ፣ ኩዬራ እና አራዳ ከሰፈር ስያሜዎቹ መካከል ተጠቃሾች ናቸው።

ከበሀማስ፣ ከኮቤኮ፣ ከካሪቢያን እና ከጃማይካ የመጡ ዜጎች ለበርካታ ዓመታት ከትመው የሚኖሩባት ከተማ እንደሆነችም ይነገርላታል።

በከተማዋ ሻሸመኔ ሙዚየምና የተለያዩ የትምህርት ተቋማት የሚገኙ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ ሊድ ስታር ኢንተርናሽናል አካዳሚ፣ ሉሲ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሚሊኒየም ሻሸመኔ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ እናት ኮሌጅ እና የሻሸመኔ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ይገኙበታል።
በኮሪደር ልማት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት ሆኑ

ሚያዝያ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) በአዲስ አበባ ከተማ በተወሰኑ አካባቢዎች እየተከናወኑ በሚገኙ የኮሪደር ልማት ሥራዎች ምክንያት ዝግ ሆነው የቆዩ መንገዶች ለተሽከርካሪ ክፍት መደረጋቸውን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

በዚህም መሰረት፡-

•  ከደጃች ውቤ  በአፍንጮ በር ወደ ራስ መኮንን ድልድይ

•  ከባሻወልዴ ችሎት በቱሪስት ሆቴል ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

•  ከዳኑ ሆስፒታል እስከ  ቱሪስት ሆቴል በመውጣት ወደ ራስ መኮንን ድልድይ አፍንጮ በር

•  ከአራዳ መስተዳደር ወደ ዳኑ ሆስፒታል መውረጃ በአንድ አቅጣጫ ብቻ አሽከርካሪዎች መጠቀም እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ እየተከናወኑ ባሉ የልማት ሥራዎች ምክንያት ለአጭር ሆነ ለረጅም ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ በጥብቅ መከልከሉንም ነው ፖሊስ ያሳሰበው፡፡
ፌዴሬሽኑ በአወዛጋቢው የማራቶን ውጤት ላይ ምርመራ እንደሚያከናውን አስታወቀ

ሚያዝያ 8/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን በአወዛጋቢው የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውጤት ላይ ምርመራ እንደሚያከናውን አስታወቀ።

ባለፈው እሁድ በተደረገው የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውድድር ላይ ሦስት አፍሪካዊያን አትሌቶች ሆን ብለው ሄ ጂ የተባለው ቻይናዊ አትሌት እንዲያሸንፍ ማድረጋቸውን የተለያዩ መገናኛ ብዙኃን መዘገባቸው ይታወሳል፡፡

ጉዳዩን በተመለከተ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ዮሐንስ እንግዳ ከአዲስ ዋልታ ጋር በነበራቸው ቆይታ በዕለቱ ውድድር ላይ የተሳተፈው ኢትዮጵያዊ አትሌት ጀደኔ ኃይሉ ከፌዴሬሽኑ እውቅና ውጭ ወደ ውድድሩ ስፍራ ማቅናቱን ገልጸው ያደረገውን ተግባር እንደሚያጣራ አስታውቀዋል።

የውድድሩ አዘጋጆች በምን መስፈርት ተወዳዳሪውን እንዳሳተፉት ፌዴሬሽኑ እንደማያውቅ አመልክተዋል። አትሌቱ ወደ ሀገር ሲመለስ ፌዴሬሽኑ ስለሁኔታው እንደሚያነጋግርም አንስተዋል።

በቤይጂንግ ግማሽ ማራቶን ላይ የተሳተፉት ኬኒያዊያኑ ሮበርት ኬተር፣ ዊሊ ምናንጋት እና ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ኃይሉ ከስፖርታዊ ስነ ምግባር ባፈነገጠ መልኩ ሆን ብለው ሌላ ተወዳዳሪ እንዲያሸንፍ ፍጥነታቸውን በመቀነስ እንዲሁም በማበረታታት እንዲያሸንፍ ማድረጋቸው በተንቀሳቃሽ ምስል ይፋ መሆኑ ይታወሳል።

በሐብታሙ ገደቤ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከተወሰደው ገንዘብ 95 በመቶ ማስመለሱን ገለጸ

ሚያዝያ 9/2016 (አዲስ ዋልታ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ከተከሰተው የሲስተም ችግር ጋር በተገናኘ ያለአግባብ ተወስዶ ከነበረው ገንዘብ 95 በመቶ የሚሆነውን ማስመለሱን አስታወቀ።

ባንኩ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ በተጠቀሰው ዕለት በተፈጠረ ችግር ምክንያት ብር 801 ሚሊዮን 417 ሺሕ 747.81 ያለአግባብ ተወስዶ እንደ ነበር መገለጹ ይታወሳል።

ከተወሰደው ገንዘብ 762 ሚሊዮን 941 ሺሕ 341 ብር ማስመለስ መቻሉን ባንኩ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ላይ ባወጣው መረጃ አመልክቷል።

ይህም መሰብሰብ ከነበረበት ገንዘብ ውስጥ 95 በመቶ የሚሸፍን ሲሆን ቀሪውን 38 ሚሊዮን 474 ሺሕ 938 ብር የማስመለስ ስራ እንደሚቀጥልም ገልጿል።
አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ በዲያመንድ ሊግ 1 ሺሕ 500 ሜትር ውድድር አሸነፈች

ሚያዚያ 12/2016 (አዲስ ዋልታ) በቻይና ዝያሜን እየተካሄደ ባለው ዲያመንድ ሊግ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3:50:30 በሆነ ሰዓት በመግባት ውድድሩን ማሸነፍ ችላለች።

በተያያዘ የ2024 የዲያመንድ ሊግ ውድድር አትሌት ለሜቻ ግርማ በ5 ሺሕ ሜትር የሩጫ ውድድር አሸንፏል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ በውድድሩ ርቀቱን በቀዳሚነት ለማጠናቀቅ 12:58.96 ስዓት ፈጅቶበታል።

ውድድሩ ለ6 ወራት የሚቆይ ሲሆን አራት አህጉራት በ15 ከተሞች የሚካሄድ ይሆናል።
በኬንያ በተካሄደው የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች አሸነፉ

ሚያዝያ 13/2016 (አዲስ ዋልታ) ትላንት ማምሻውን በኬኒያ በተካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ኮንቲኔንታል ቱር ጎልድ ውድድር  በ5 ሺሕ ሜትር በሁለቱም ፆታዎች  ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች አሸንፈዋል።

በሴቶች የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አትሌት ማርታ አለማየው ርቀቱን 15 ደቂቃ ከ14 ሰከንድ ከ54 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በአንደኝነት ስትጨርስ፣ ለምለም ንብረት  15 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ ከ99 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት ውድድሩን በመጨረስ 3ኛ ሆና አጠናቃለች። ሌላዋ አትሌት ሽቶ ጉሚ ውድድሩን በአራተኝነት አጠናቃለች።
 
በሌላ በኩል በወንዶች የ5 ሺሕ ሜትር ውድድር አብዲሳ ፈፍሳ ርቀቱን 13 ደቂቃ ከ34 ሰከንድ ከ77 ማይክሮ ሰከንድ በሆነ ሰዓት በማጠናቀቅ አሸናፊ መሆኑን ከኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌደሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ጀጎል የምስራቅ አፍሪካው አውራ ግንብ
#ሀገሬ

ሀገራችን ድንቅና ውብ የተፈጥሮና ሰው ሠራሽ መስህቦች እንዲሁም ታሪካዊ ቅርሶችና ባህላዊ እሴቶች ባለቤት ናት። እነዚህ የሚዳሰሱና የማይዳሰሱ ቅርሶች የውስጥና የውጭ ጎብኚዎችን ቀልብ በመግዛት ይታወቃሉ። ምርጥ የቱሪዝም መዳረሻ ከመሆን ባሻገርም የዓለም ቅርስ ሆነው የተመዘገቡ ብዙ ናቸው፡፡

ከእነዚህ የሀገራችን ውብ ቅርሶች በምሥራቁ የሀገራችን ክፍል የሚገኘው የጀጎል ግንብ አንዱ ሲሆን የግንባታው መሀንዲሶች በወቅቱ የነበሩ አባቶች ናቸው። የጀጎል ግንብ የሀረሪ ህዝብ የኪነ ህንፃ ችሎታውን የሚያስመሰክር የታሪክ እና የጥበብ ውጤትም ነው፡፡

የሀረር ከተማ መለያና የዓለም ቅርስ የሆነው የጀጎል ግንብ የተገነባው በ16ኛው ክፍለ ዘመን በአሚር ኑር ቢን ሙጃሂድ መሆኑን ታሪክ ያስረዳል።

ጀጎል በሀገር በቀል ዕውቅ የፈጠራ ባለቤቶች የተገነባ የሀገረሰብ ጥበብ ውጤት መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን በዘመኑ አባቶች ያለምንም ቴክኖሎጂ እገዛ ነበር ግንቡን ያበጃጁት። ከፋብሪካ ውጤቶች ነፃ የሆነና በአካባቢያቸው የሚገኘውን ጥሬ ዕቃ በመጠቀም የገነቡት የዚህ ግንብ ቆይታው ደግሞ የአባቶችን የጥበብ ከፍታን ያሳየ ነው። በዘመኑ በምስራቅ አፍሪካ በግንብ የታጠረች የመጀመሪያዋ ድንቅ ከተማ ሀረር እንደሆነች መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ የግንባታው ዓላማም ከተማዋን ከጠላት ለመከላከል እንደሆነ ይነገራል፡፡
  🎉ጓደኞቾን ይጋብዙ፤ እንዲሁም ሽልማት ያግኙ!

አስደሳች የኬኖ መድረክ እንዲቀላቀሉ  ጓደኞችዎን ይጋብዙ! !

ወዳጆን ይጋብዙ:
 
👇👇👇👇👇👇👇
https://hottg.com/Fetabet_bot?start=7171110553895571456
🔥የምንሰጠው ኮርስ ከወረቀት በላይ ነው!
 AICE ኮርስን በነፃ በመማር አፍሪወርክ ላይ ለሚወጡ ከፍተኛ ክፍያ የሚያስገኙ ስራዎች ብቁ ሆነው ይገኙ።የሶስተኛው ዙር ምዝገባ ተጀምሯል።
ቦታዎች ውስን ናቸው፣ እንዳያመልጣችሁ!
እስከ 20ሺሕ ብር የሚሸጡ የሐረሪዎች የእጅ ሥራ

መጠናቸው አነስተኛ፣ ያጌጡ፣ ለዓይን የሚማርኩ እና አሰራራቸው በራሱ ብዙ ትርጉም ያለው የአለላ ስፌት ውጤቶች ከ5ሺሕ ብር እስከ 20ሺሕ ብር ድረስ ይሸጣሉ። ይህን የተመለከትነው ለሹዋሊድ ክብረ በዓል በሐረር ከተማ በዓሉን ምክንያት በማድረግ በተዘጋጀ የባህል ዐውደ ርዕይ ላይ ነው።

የአለላ ስፌት ውጤት በሐረሪዎች መንደር ትርጉሙ ብዙ ነው፡፡ ሐረሪዎች በአለላ ስፌት ውጤቶች ያሸበርቃሉ፣ ይዋባሉ፣ ይገለገላሉ፡፡ በሐረሪ የአለላ ስፌት ስራዎች ለተለያዩ አገልግሎት ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ የሐረሪ ሕዝብ እደ ጥበብ ውጤት የሆነው እና በክልሉ በሰፊው የሚመረተው አለላ ስፌት ምርት በዓለም አቀፍ ምድብ የንግድ ምልክት (ብራንድ) ሆኖ መመዝገብ የቻለ ልዩ ጥበብ ነው፡፡

የሐረሪ ክልል መንግስትም ለዘርፉ ልዩ ትኩረት በመስጠት ነዋሪዎች በማኅበር ተደራጅተው ታሪካዊ ትስስሩን በጠበቀ መልኩ ባህላዊ የአለላ ስፌቶች እና አልባሳቶችን እንዲያመርቱ ሁኔታዎችን አመቻችቷል፡፡

የሹዋሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀ የባህል ዐውደ ርዕይና ፌስቲቫል በሐረር ከተማ ሲከፈት የዕደ ጥበብ ውጤት ሥራዎቿን ለእይታ አቅርባ ያገኘናት የማኅበሩ አባል ሰኣዳ በርከሌ እንደገለጸችልን ሐረሪዎች ለሀዘን፣ ለደስታ፣ ለሰርግ፣ ለጌጥ፣ ለውበት እና ለሁሉም ማኅበራዊ ክዋኔዎቻቸው እነዚህን የእደ ጥበብ ውጤቶች ይጠቀማሉ፡፡ ሐረሪዎች እንደየሁኔታው ለሙሽራ፣ ለአማች እና ለቤተዘመድ የሚሰጥ ታሪካዊ ዳራ ያላቸው ልዩ ልዩ የአለላ ስፌቶችን ያዘጋጃሉ፡፡

በሐረሪዎች መኖሪያ ቤት የገባ ሰው በቀላሉ በግድግዳ ላይ የተሰቀሉ የአለላ ስፌቶችን በመመልከት አንዲት እናት ወንድ ልጅ ወይም ደግሞ ሴት ልጅ መዳሯን በቀላሉ ለማወቅ ይችላል፡፡
#news#
በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ አርሰናል ከቼልሲ ዛሬ ምሽት ይጫወታሉ

ሚያዚያ 15/2016 (አዲስ ዋልታ) በእንግሊዝ ፕሪሚዬር ሊግ ዛሬ ምሽት 4 ሰዓት ላይ አርሰናል በኤምሬትስ ስታዲዬም ከቼልሲ ጋር ወሳን ጨዋታ ያካሂዳሉ።

አርሰናል በ33 ጨዋታዎች በሊጉ የደረጃ ሰንጠረዥ በ74 ነጥብ አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን በተመሳሳይ 74 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘነው ሊቨርፑል በጎል ክፍያ ነው የሚለያዩት።

ለአርሰናል የዛሬ ምሽቱ ጨዋታ የዋንጫ ፉክክሩን ለማጠናከር በጥንቃቄ እንደሚጫወት ሲጠበቅ በጥሩ መነቃቃት ላይ የሚገኘው ቸልሲ ዘንድሮ ከታላላቆቹ የሊጉ ቡድኖች ጋር ጠንክሮ በመታየቱ የምሽቱን ጨዋታ አጓጊ ያደርገዋል።

ቼልሲ 31 ጨዋታዎችን አድርጎ በ47 ነጥብ 9ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠ ሲሆን የዛሬ ምሽቱን ጨዋታ ካሸነፈ ደረጃውን ወደ 7ኛ ከፍ ሊያደርግ የሚችልበት እድል ያገኛል።
መንግስት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከርና ለአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው - ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

ሚያዚያ 15/2016 (አዲስ ዋልታ) መንግስት ለህብረ ብሔራዊ አንድነት መጠናከርና ለአሰባሳቢ ትርክት ግንባታ በቁርጠኝነት እየሰራ መሆኑን የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዶክተር ለገሰ ቱሉ በኢትዮጵያ ለዘመናት ስር ሰደው የቆዩና ያለመግባባት መነሻ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት በርካታ የሪፎርም እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል።

ፖለቲካዊ ልዩነቶች በውይይት እንዲፈቱ መንግስት በፅኑ ይሰራል ያሉት ሚኒስትሩ የተፈጸሙ በደሎችን በእርቅ በይቅርታ እና በፍትሕ ለመሻገርም የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ መጽደቁን አንስተዋል።

በሀገራዊ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ ብሔራዊ መግባባት ለመፍጠርም ህዝብ በአጀንዳዎቹ ላይ ምክክር አድርጎ መፍትሔ የሚያቀርብበት ሀገራዊ ምክክር ለማካሄድ የዝግጅት ስራዎች እየተጠናቀቁ መሆኑንም ተናግረዋል።

መንግስት ኢትዮጵያዊ ህብረ ብሔራዊ አንድነት እንዲጎለብት ልዩ ትኩረት መስጠቱን በማንሳት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ትስስርን ማጠናከር እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያን አንድነት ለማፅናትና የህዝቦችን የዘመናት አብሮነት በጠንካራ መሰረት ለማዝለቅ አሰባሳቢ ትርክት ሚናው የላቀ እንደሆነም ነው ሚኒስትሩ የገለጹት።

ለዚህም መንግስት በብሔራዊነት ላይ የተመሰረተ አሰባሳቢ የጋራ ትርክትን መገንባት ላይ በቁርጠኝነት እየሰራ ነው ብለዋል።

የጋራ ትርክቱ የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ለማረጋገጥ፣ ብሔራዊ ጥቅሟን እና ክብሯን ለማስጠበቅ፣ እንዲሁም የህዝቡን አንድነት ለማጎልበት ወሳኝ በመሆኑ ሁሉም ሚናውን ሊወጣ እንደሚገባ ጠቅሰዋል።
HTML Embed Code:
2024/04/25 15:03:29
Back to Top