TG Telegram Group Link
Channel: የፍትህ መንገድ
Back to Bottom
እዉነተኛ ታሪክ
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

      🌀 #Part 2⃣2⃣

    እኔም እናት እና አባቴ በዚህ ጉዳይ ሲጣሉ ሲቸካቸኩ አባቴ አይሆንም እያለ ሲጮህ ይህ ችክችክ ወደ ሌላ ወደ ቤተሰብ ፀብ እንዳይዞር እኔዉ እራሴ መፍታት ማስታረቅ አለብኝ ብየ ወሰንኩ ግን አባቴን ማሳመኑ አደራዉ እኔ ጋር እንደሆነ ተገነዘብኩኝ ...በራስ መተማመን ይዤ አባቴ የተናገረኝን ቢናገረኝ ላልቀየም ላላለቅስ የአላህ ቀድር ከሆነ በእኔ ምንም መለወጥ አልችልም ብየ አስቤ.. እራሴን አሳምኜ በሩን ስከፍተዉ እናት እና አባቴ መቸካቸካቸዉን አቁመዉ ሁለቱም ወደ እኔ ትኩረታቸዉን አደረጉ፡፡

ቤቱ ፀጥ አለ ማን ወሬ እንደሚጀምር አስፈራኝ ግን እኔ መጀመር እንዳለብኝ ተረዳሁ ...ወደ አባቴ ጎን ሂጄ ቁጭ አልኩኝ
    አባቴ ምነዉ እናቴ ጋር አለመግባባት ምን ተፈጠረ??? አልኩት ነገሮችን እንዳልሰማሁ ሁኜ
.....እሱም የምሰማዉ ነገር እዉነት ነዉ እንዴ??? አለኝ
.....እኔም እዉነት ቢሆን ለአንተ ደስ አይልህም እንዴ?? አልኩት
.....እሱም የጠየኩልሽን አጭር መልስ ንገሪኝ ከአፍሽ ልስማዉ አለኝ
...እኔም ከእኔ መነገሩ ጥቅም የለዉም እናቴም ነግረሀለች አዎ እዉነት ባቢ ዙበይርን ነገ እናንተን ላስተዋዉቅ ምሳ ጠርተነዋል ከነ እህቱ አልኩት
....አባቴም እኔ አባትሽ አይደለሁ?? እስከ አሁን እንዴት ሳትነግሪኝ እኔ የልጄን ሂወት መወሰን አልችልም ማለት ነዉ?? ቢሆንም ባይሆን እንዴት አንድ ቀን ሲቀረዉ ትነግሪኛለሽ ?? እኔ ከእናተ እርቄ የመንግስት መስሪያ ቤት የምሰራዉ አስተካክየ ቁርስ በልቼ ምሳ በቅጡ የማልበላዉ ለማን ብየ መሰለሽ ለአንድ ፍሬ ልጄ ለአንቺ ብየ እኮ ነዉ፡፡ በጣም ጥፋተኞች ናችሁ አዝናለሁ አለኝ፡፡
 አባቴ እዉነቱን ነዉ የቤተሰብ ፍቅር እርቆ  በአገኘዉ የወር ደመወዝ ነዉ የሚያስተዳድረን ግን ዙበይር ጋር እዚህ ደረጃ ለትዳር እንደርሳለን ብየ ትዝም ብሎኝ አያቅም..... ደግሞ ቀድሜ ብነግራቸዉ ይሆናል ብየ ባይሳካ ቤተሰቦቼ እኔን ምን ይጠረጥሩኛል ?? አጃጅሎ ተዋት ብለዉ ወይ እኔን አያምኑኝም ወይ እሱ ጋር ፀብ እንደሚኖር መዘንጋት የለብኝም፡፡
   አሁን ያለኝ አማራጭ አባቴ ያለኝን የጠየቀኝን ከመመለስ እኔ ይቅርታ ብለዉ የተሻለ መሰለኝ፡፡

ከአባቴ ጎን ተነስቼ  ከእግሩ ስር ተደፍቼ አባቴ ጥፋተኛ ነኝ ይቅር በለኝ እኔ እንደዚህ ይከፋሀል ብየ ትዝም አላለኝ ሰርፕራይዝ ላረግህ ነበር ሀሳቤ ይቅር በለኝ እኔ ይሄ ትዳር ይሆናል ብየ አላሰብኩትም ፡፡ ለእናቴ እንኳ የነገርኳት ከሶስት ቀን በፊት ነዉ እኔ ዙበይር የሂወት አጋሬ ይሆናል ብየ አስቤዉም አላቅ አዉፍ በለኝ ብየ አለቀስኩኝ አባቴ እግር ላይ ተደፍቼ፡፡
    አረ ልጄዋ አታልቅሺ እኔ የአንቺን ለቅሶ አልፈልግም ሀገር ለሀገር የምዞረዉ አንቺ ደስተኛ እንድትሆኝ ነዉ አዉፍ ብየሻለሁ ብሎ ግንባሬን ሳመኝ
.....እኔም በደስታ እሺ የነገዉን ምሳ ፕሮግራም እዚሁ ልትገኝ ተስማማህ?? አልኩት
   አንዴ ጥያቄ ልጠይቅሽ ??አለኝ
..... ስለዙበይር ብዙ ነገር ጠየቀኝ መለስኩለት የጓደኛየ ወንድምም እንደሆነ..እናቴ እንደጠየቀችኝ
..... ሀብቱን አይተሽ እንዳይሆን አለኝ፡፡ እኔም በጭራሽ ይሄ እንዳለዉ ያወኩት ቅርብ ቀን ነዉ እኔ መስፈርቴ ብር አይደለም ነበር እኔ ማንነቴን አዉቆ ስለተቀበለ ነዉ የመረጥኩት አልኩት
    አባቴም ግን ልጄ እኔ የጠየቁኝ አሉ እሺ ከህመሟ ይሻላት እያልኩ መልሻለሁ  የነገዉን ምሳ ችግር የለም እንተዋወቃለን ፡፡ ግን ብትረጋጊ እና እኔ የጠየቁኝን ሰዎች አጥንተሽ ለምን መርጠሽ አታገቢም??? አለኝ
......እኔም ሳቅ እያልኩ አባቴ የመጡልኝ እኮ ማንነታቸዉን አላዉቅም ፀባያቸዉን ከኔ ምን እንደሚፈልጉ የማቀዉ የለኝም ዙበይር እኮ ከኔ የሚፈልገዉ ፍቅሩን እና የትዳር አጋሩ እንድሆን ነዉ፡፡ አንተን የጠየቁህ ለክብራቸዉ ለዘራቸዉ ሊጨነቁ ይችላሉ ደግሞ መቀራረብ እንጠናና በሚለዉ እኔም የእሱን ፀባይ ልወቅ ስል እሱም የኔን ፀባይ ልወቅ ሲል መቀራረብ አላህ ብዙ የከለከሉ ወንጀሎችን ልንሰራ እንችላለን ፡፡አንተ አስተዋወከን  ቀርባችሁ ተዋወቁ ነዉ የምትለን ..ቀርባችሁ ተዋወቁ  ማለት ከዚህ የባሰ ምን ይፈጠራል?? አባቴ አልኩት
   እሱም ይሄ ቂርአት ብዙ አስተምሮሻል ብሎ እየሳቀ እሺ ይሁና ልጄ እኔ የምፈልገዉ አግብተሽም ደስታሽን ነዉ አለኝ ቤቱ በደስታ አባቴም እናቴም እኔም ተቃቀፍን የቅድሙ ጭቅጭቅ በጠረንቤዛ ዙሪያ ዉይይት በመሰለ አጀንዳ በሰላም በፍቅር ተፈታ ቤታችን በአንዴ ወደ ቤተሰብ ፍቅር ዞረ ፡፡
    ቤተሰብም ጋር ሳያለቅሱ ሳይናደዱ ተረጋግቶ ማዉራት ጥቅም አለዉ፡፡ ግን አንዳንድ እህቶቼ ይዘሀኝ ጥፋ...እሱን ካልዳራችሁኝ እታነቃለሁ በሂወት አታገኙኝም የሚሉ አሉ፡፡ ይሄ አግባብ አይደለም ማንኛዉም ቤተሰብ ለልጆቹ ክፉ አይደለም ብቻ የትዳር ሂወት ማለት ሁለተኛ ሂወት ስለሆነ ቤተሰብም በትንሹም ቢሆን ጣልቃ መግባቱ አይቀሬ ነዉ፡፡ ትዳር ጋር አለመስማማት ቢኖር ተመልሰን የምንመጣዉ ወደ ቤተሰብ ነዉ፡፡
   
እሷ እና ጠቢቡ

#እሷ👇
አምላክ ልጠይቅህ ፍቅር ግን ምንድነው
ያኛውም ይሄኛውም ወደድኩሽ የሚለው
የቱ ነው የወደደኝ የቱ ነው ያፈቀረኝ
አንተው መልስልኝ እኔስ ግራ ገባኝ

#ጠቢቡ👇
ልጄ ተባረኪ ጥሩ ጥያቄ ነው
መውደድ በጣም ብዙ ማፍቀር ግን 1 ነው
አንቺን የሚወዱሽ ተቆጥረው አያልቁም
ያፈቀረሽ ሰው ግን ከ 1 እንኳን አይበልጥም

#እሷ👇
እንዲ ከሆነማ አፈቀርኩሽ ያሉኝ
ከ 1 እኮ ይበልጣሉ መጥተው የጠየቁኝ
ከነዛ ሰው ሁሉ ተድያ እንዴት ልለየው
የእውነት እፍቃሪ ምልክት ምንድነው

#ጠቢቡ👇
በማስመሠል ዘመን ማመኑ ቢከብድም
የእውነት ፍቅርን ግን መለየት አያቅትም
ተወኝ ብትይውም ሊተውሽ ቢፈልግ
ልቡ ግን አይፈቅድም ይሄንን ለማድረግ

አንቺን እንዲተውሽ ፊት አንኳን ብትነሺው
ፊትሽን ይተውና ልብሽን ነው የሚያየው
አፈቀርኩሽ ብሎ ፅናቱ ካልታየ
የውሸት ፍቅር ነው እለፊው ባላየ
#ምንጭ_anu

 ቅዳሜ ተሻግረን እሁድን የወፎች ጫጫታ አስተጋባ ትናንት ጀምሮ እናቴ ጋር አብሬ ደፋ ቀና እያልን ነዉ ስድስት ሰአት ላይ ስራዉን አጠቃለልን ስድስት ተኩል ሲል ከፊርዶስ ስልክ ተደወለ.... ስልኩን አነሳሁት ..ፊርዶስም ማመን የማልችለዉን በስልክ ነገረችኝ.....
ምን ተፈጥሮ ይሆን ?? የሂክማ ነገር አንዱን ፈተና ስጨርስ ሌላ የማትወጣዉ ፈተና ይመጣባታል ...

ክፍል 2⃣3⃣ ይቀጥላል.........


   የሂክማ ታሪክ በመጨረሻዉ ክፍል እና በማጠቃለያ ፁሁፋችን ይጠብቁን ...

https://hottg.com/mahbubil
#በ ጁመአው ለይል ሹክ ልበላችሁ

አዘጋጅና ፀሀፊ ፦ ካሊድ (kalido ye umi)

ሁሌም በልባችን ውስጥ ኖት! 😍

#የመሰናበቻው_ሐጅ

<<ሙዓዝ ሆይ፡ ከዚህ አመት በኋላ ላታገኘኝ ትችላለህ። ምንአልባትም በዚህ መስጂድና በቀብሬ አጠገብ ታልፍ ይሆናል።>>

የጥሪው ተግባር፣ መልእክት የማድረሱ ስራ፣በአላህ ብቸኛ አምላክነት እና በነብዩ ሙሐመድ ﷺ መልእክተኛነት መሰረት ላይ አዲስ ሕብረተሰብ የማነፁ እንቅስቃሴ ከተጠናቀቀ በኋላ የአላህ መልእክተኛ ﷺ ምድራዊ ህይወታቸው ወደ መጨረሻው መቃረቡን የሚገልጽ አንዳች ሚስጥራዊ መልእክት ከልቦናቸው ውስጥ ሰፈረ። እናም በ 10ኛው ዓመተ ሂጅራ ሙዓዝን ወደ የመን ሲልኩ እንዲህ ነበር ያሉት።

ሙዓዝም ያንን ሲሰማ ከእርሳቸው የመለየቱ ነገር ታሰበውና ስቅስቅ ብሎ አለቀሰ።

በዙሪያቸው 124 ሺህ ወይም 144 ሺህ ሰዎች በተሰበሰቡበት ከመሀከላቸው ተነሱና የሚከተለውን ሁለንተናዊ ንግግር ከዓረፋ ጋራ ላይ ሆኖ ረቢአህ ቢን ኡመያህ ቢን አልኸለፍ በማስተጋባት አሰሙ።

<< ሰዎች ሆይ ንግግሬን ስሙ። ምን አልባትም ከዚህ አመት በኋላ በዚህ ቦታ ላይ ዳግም ላላገኛችሁ እችላለሁ። ይህ ቀናችሁ በዚህ ወራችሁ እና በዚህ ሃገራችሁ ላይ የተከበረ እና እርም እንደሆነ ሁሉ ደማችሁም እና ገንዘባችሁም በእናንተ ላይ እርም ነው። #አዋጅ የመሐይምነት ዘመን ድርጊቶች ሁሉ ከእግሮቼ ስር ውድቅ ሆነዋል። የቅድመ ኢስላም(የጃሂልያ) የደም ብቀላ ሁሉ ውድቅ ሆኗል። ከደሞቻችን መካከል መጀመሪያ ውድቅ የተደረገው የቢን ረቢእሀ ቢን ሐሪስ ደም ነው። የመሐይምነት ዘመን አራጣ ውድቅ ነው። ከአራጣዎቻችን መካከል በመጀመሪያ ውድቅ የተደረገው የአባስ ቢን አብድልሙጦሊብ አራጣ ነው። እርሱ ሙሉ በሙሉ ውድቅ ሆኗል።

በሴቶች ጉዳይ አላህን ፍሩ። ምክንያቱም በአላህ አደራ ያዛችኋቸው። በአላህ ቃል ብልቶቻቸውን የተፈቀዱ አደረጋችሁ። እናንተ በእነርሱ ላይ ያላችሁ መብት የማትፈልጉት ሰው ፍራሻችሁን እንዳይረግጥ ሊያደርጉ ሲሆን ፣ይህን ካልፈፀሙ ለስሙ ያህል መታ አድርጓቸው። እነርሱ በእናንተ ላይ ያላቸው መብት ደግሞ ቀለባቸውንና አልባሳቶቻቸውን ተገቢ በሆነ ሁኔታ ልታመቻቹላቸው ነው።

የአላህን መፅሐፍ ትቼላችኋለሁ። በርሱ ከተመራችሁ መንገድ አትስቱም። ሰዎች ሆይ፣ ከኔ በኋላ ነብይ የለም። ከእናንተ በኋላም ኡማም የለም። #አዋጅ ፣የጌታችሁን ጀነት ትገቡ ዘንድ ጌታችሁን አምልኩ። አምስት ወቅት ሰላታችሁን ስገዱ። የረመዷን ወር ፆማችሁን ፁሙ። የገንዘባችሁን ዘካ፣ ወዳችሁና ፈቅዳችሁ አድርሱ። የአምላካችሁን ቤት ሐጅ አድርጉ። መሪዎቻችሁንም ታዘዙ።

ይህን ከተናገሩ በኋላ እንዲህ ሲሉ ጠየቁ?

<ስለእኔ ብትጠየቁ ምን ትላላችሁ?>

ሰዎችም < እርስዎ መልእክቱን በታማኝነት እንዳደረሱን እንመሰክራለን።> አሉ።

💚{ፊዳከ ነፍሲ ኡሚ ወ አቢ ያረሱለላህ}💚

ሳምንት በአላህ ፍቃድ በሌላ ፅሁፍ እመለሳለሁ !

መልካም የጁመዓ ለይል (ኸሚስ) ውዶቼ 🙏

join👉 @mahbubil
ሁል ጊዜ በሐሳብህ ሀቀኛ ሁን !

©Armala Charity
@Armala_charity2
 😢 #አስለቃሽ #የቴሌግራም
              #ፕሮፋይል

#የመጨረሻዉ #ክፍል

ክፍል 2⃣3⃣

   ፊርዶስ ደወለች ስልኩን አነሳሁት ...ምንም አልተፈጠረም ለወሬ አቸኩሉ 😊
  .....ፊርዶስ ጋር ሰላምታ ከተለዋወጥን ቡሀላ  አንድ ነገር ልጠይቅሽ ነበር አለችኝ
......እኔም ምን ነበር ፊርዱ ??አልኳት
........እሷም ምሳ የጠራችሁን ሁለታችን ነበር ግን አንድ ሰዉ አብሬ እናንተ ጋር ካልሄድኩ አለን ምን ትያለሽ ሂኩ??? አለችኝ
.....እኔም ችግር የለም እሄዳለሁ ያለዉን አብራችሁ ይዛችሁ ኑ አልኳት
....ፊርዱም የዛሬዉ ቀን እኮ ለ ዙበይር
 ታላቅ ቀን ነዉ ትናንት ቅዳሜ አዳር እንቅልፍ ሳይወስደዉ ነዉ ያደረዉ በደስታ ተባብለን ተሳስቀን ፊርዶስ አሁን ከቤት እየመጣን ነዉ ብላ ነገረችኝ፡፡ እኛም ተዘጋጅተን ነዉ እየጠበቅናቸዉ ያለነዉ...
      ከ30 ደቂቃ ቡሀላ እቤት ደረሱ ፡፡ ወደ ቤት ሲገቡ ያየሁትን ማመን አቃተኝ የፊርዶስ እናት አብረዉ መጥተዋል ቅድም ደዉላ አንድ ሰዉ ይዤ ልምጣ ያለችዉ እናታቸዉን እንደሆነ ተገለፀልኝ ፡፡ የእኔ እናት እና አባት ብድግ ብለዉ ተቀበሉ ፊርዶስ የእኔን እናት ከእሷ እናት አስተዋወቀች አባቴንም ..የፊርዶስ እናት  እና የእኔ ቤተሰቦች ሲያወሩ ዛሬ አዲስ የተገናኙ አይመስሉም ነበር በጣም ደስ አለኝ ፡፡
     ዙበይር ግን ፈርቶ ዝም ብሏን አባቴ አብሽር ተጨዋት አትፍራ እንጂ እያለዉ ነዉ፡፡
 ከዛም ምሳችንን በልተን ጨረስን ቡናዉ ተፈልቶ ተመራርቀዉ ቡናዉን ተጠጥቶ ከጨረሱ ቡሀላ የዙበይር እናት እስኪ የመጀመሪያ ስለሆነ ማስታወሻ  ብለዉ የተጠቀለለ ስጦታ ሰጡን ስጦታዉ ለእናቴ የሚያምር ድርኢና ጎጎራ እና የሚያምር ጫማ ሲሆን ለአባቴ ደግሞ ሽቶ የዙበይር እናት አበረክተዉ ለምሳዉ ፕሮግራም አመስግነዉ ተመራርቀዉ ተለያዩ  ፡፡ እናቴም አባቴም በጣም ተደስተዉ ከአሁን ቡሀላ ምን ቀረ እንግዲህ ልጄ ያሰብሽዉን አላህ ያሳካልሽ ብለዉ አባቴም እናቴም መረቁኝ፡፡
    ማታ ላይ ዙበይር ደወለልኝ ብዙ ነገሮችን አዉርተን ሂኩ መኖሪያ ቤቴን ያከራየሁትን ሰዎቹን ቤት እንዲፈልጉ ደዉየ ነግሪያቸዉ እሺ በቅርብ ቀን ለቀዉ እንደሚወጡ ነግረዉኛል ስለሆነም ተዘጋጂ ብሎ ነገረኝ፡፡
....እኔም እሺ  አልኩት
ዙበይርም ሂክማ እወድሻለሁ አላህ ሀላሌ ስላረገኝ የአንቺ በጣም ደስተኛ ነኝ አለኝ፡፡
እኔም እወድሀለሁ ዙበይር አንተ ማለት የሂወቴ ብሩህ ተስፋየ ነህ ጥሩ ልጅ ወልደን በዲነል ኢስላም ገንብተን እንደምናሳድግ ይታየኛል ኢንሻ አላህ አልኩት፡፡ ብዙ ደቂቃዎች አዉርተን ተሰነባብተን ወደ መኝታየ አመራሁ፡፡ የእኔ እናት እና የዙበይር እናት በስልክ ማዉራት መቀራረብ ጀምረዋል በጣም ደስተኛ ነኝ
 
  ፊርዶስም እቤት መቼ ሽምግልና እንላክ ??ብላ ጠየቀችኝ ...ቤተሰቦቼን ጠይቄ የሚመችባቸዉን ቀን ቤተሰቦቼን ጠይቄ ለፊርዶስ ነገርኳት
ዙበይርም መኖሪያ ቤቱ አስለቅቆ የቤት እቃ እያሟላ ነዉ ፡፡ በስልክ ቀን በቀን እያወራን ነዉ አልፎ አልፎ በአካል እንገናኛለን ግን ተሳስመን አናቅም የወደፊት መሆን ያለባቸዉን ተወያይተን እንለያያለን....
   ሸምግልና የሚልኩበትን ቀን ቤተሰብ የሚመችባቸዉን ጠይቄ ለዙበይር ነገርኩት.....

አስታዉሳለሁ ቅዳሜ ቀን የዙበይር አባትን አብሮ በመምጣት እስከ 10 የሚደርሱ ሽማግሌዎች መጥተዉ ልጅህን ለልጄ ተባብለዉ ለዙበይር ታጨሁ ...በዛዉም የሰርጉን ቀን ተቆርጦ ሽማግሌዎቹ ተመለሱ ....በጣም በሂወቴ ደስተኛ እየሆንኩ ነዉ የዙበይር የሰራዉ የመኖሪያ ቤት ሸጎሌ መንገድ 7 አካባቢ  ነዉ፡፡ ምን የራሱ ለወደፊት አብረን ልጅ ወልደን የምናሳድግበት ቤት ነዉ እንጂ
  

የሰርጉ ቀን ደረሰ ሰርጋችንንም ..
ሁለታችንም ተነጋግረን ጦር ሀይሎች አካባቢ በሚገኘዉ  በኡማ ሆቴል ነበር ፡፡ ፊርዶስ ለኔ የመጀመሪያ ሚዜ ሆነች ሁለቱ ሚዜዎቼ ደሴ ከተማ ካሉት የአጎቴ ልጆች አረኩኝ  ..ፊርዶስ ለዙበይር መጀመሪያ የሱን ደስታ ያስቀደመች እህቱ ለእኔ ደግሞ የዲን እህቴም ጓደኛየም ..የወንድሟ ባለቤት(አይቷ)  ነኝ፡፡ ሰርጉ በሚያምር ዘመድ ጓደኛቼ በተገኙበት በአማረ ሁኔታ በኡማ ሆቴል ተፈፀመ፡፡ ፊርዶስ ጋር ከበፊቱ በበለጠ ከአገባሁም ቡሀላ ተቀራርበናል ደስ የሚል ሂወት እየመራሁ ነዉ፡፡

 አንተን ያወቅኩ ለታ
የዛን እለት ማታ
ትዝ ይልሀል ያኔ
ያወራሀኝ አንተ የወደድኩህ እኔ
ያን ምገዛውን ፈጣሪዬን ትቼ
ህጉን ተላልፌ ራሴን ሰዉቼ
      ትዝ ይልሀል ያኔ🤔
መዉደድህ ሲያሰክረኝ
ፍቅርህ እንዲያ ሲያንገላታኝ
መውደድህ የእውነት
ማፍቀርህ የእውነት
ማውራትህ የእውነት
ሁሉም ነገር እውነት መስሎ ያዘናጋኝ
ትዝ ይልሀል ያኔ
ከቤት  ተደብቄ ምክንያት ፈጥሬ
የውሸት  ጋጋታ  አውርቼ ደርድሬ
አንተ ጋር ለመምጣት ብዙ ቀባጥሬ
  ትዝ ይልሃል ያኔ
አሁን  አስብና ያን ሁሉ መሆኔ
ፈገግ  እላለሁ አወይ ስልጣኔ
  ለካ
ፍቅር የሚሰምረው
ፈክቶ  የሚጠነክረው
ከአላህ  ጋር ሁኖ የተመሰረተ ነው
በትላንቴ አፍራለሁ በዛኛው ዘመኔ
     ግና
መሀሪው ጌታዬ እስኪ ተቀበለኝ ፀፀት  ፍራቻዬን
አዲሱን ህይወቴን ካንተ ጋ ልጀምር
አንተ የገባህበት አያውቅም  ድንግርግር

    ፊርዶስ ከእኛ ሰርግ አራት ወር ቡሀላ ስለታጨች  የምታገባበት ቀን ደርሷል ......እኔም ዙበይር ጋር ጥሩ የትዳር ሂወት መኖር ጀመርኩ፡፡ ሁሉም ወንድ አንድ አይደለም ለምን ሁሉም ሴት አንድ ስላላይደል...አንድ ሰዉ የምንቀርበዉ የምንወደዉ ሰዉ ሲሸዉደን መጥፎ ስራ ሲሰራብን ጥሩ ሰዉን ማመን ስለሚያቅተን ሂወታችን ህልማችን ዳግም  አይሳካም በሚል እኔ ዙበይርን ላጣዉ ነበር፡፡ የሰዉ ልጅ ነን እና እንሸወዳለን ግን ከተሸወድን ቡሀላ በዛ ነገር ላይ ቋሚ ወንጀለኛ መሆን የለብንም ወደ አላህ መመለስ መቻል አለብን፡፡ ዙበይር ጋር በደስታ በፍቅር እየኖርኩ ነዉ .. በቅርብ ቀን ደግሞ ፊርዶስ ልታገባ ነዉ እኔም የመጀመሪያ ሚዜየ አንቺ ነሽ ተዘጋጂ ብላኝ ዝግጅት ላይ ነኝ፡፡

እህቶቼ  ብዙ ሴቶች በቻት የሚያወሩ አሉ ቻት እና የተለያዩ group እንደ እኔ እንደሚጎዱ ከመቶ አንድ የሚቆጠሩ እንደዙበይር ያሉ ወንዶችን ለማግኘት በቻት ሳይሆን በዱአ ነዉ እንጂ በቻት አይደለም ቻት የዚና መስመር ነዉ እንጂ የትዳር መስመር የሚጀመረዉ በኒካህ ነዉ፡፡ አንዴ በራስሽ ፍቃድ ሂወትሽን አበላሽተሽ ፈጣሪሽን አታማሪ ወንድንም አታማሪ መጀመሪያ ብልጥ መሆን ያለብሽ አንቺ ነሽ ሴት ልጅ ክብር ነሽ ..ክብርሽን በማያቁ ወንዶች ክብርሽን አትነፈጊ

ነግሬሽ ነበረ በአጥር ተንጠልጥዬ
የTelegram ወንድ ዉሽማ እንጂ
ባል አይሆንም ብዬ
  ታሪኬን እዚህ ላይ ጨረስኩኝ፡፡

#ተ........ #ፈ....... #ፀ....... #መ

🌹ዉድ የቻናል ምርጥ ቤተሰቦችይህን እዉነተኛ ታሪኩን ጨርሰናል ማመስገን የምፈልገዉ ሁላችሁንም የቻናል ቤተሰቦች ነዉ ታግሳችሁ አብራችሁ ስለጨረሳችሁ ከልብ አመሰግናለሁ

https://hottg.com/mahbubil
As wr wb ወዳጆቼ ነብያችን ሰ.አ.ወ የዙልሒጃ 9ኝን የጾመ ሠው የ ሁለት አመት ወንጀሉ እንደሚማርለት ተናግረዋል ። ቀኑም ነገ አርብ ነው !
ከቻልን እንፁም ካልቻልን ደግሞ እናስታውስ !
ወዳጆቼ የዚህ ኸይር ተካፋይ እንሁን!
ለሌሎችም ያጋሩ!!!
📿إن شاء الله📿
@mahbubil
አያመ ተሸሪቅ - ከዒድ ቀን በኋላ ያሉ ሦስቱ የደስታ ቀናት ናቸው። በነኚህ ቀናት ዉስጥ መፆም የተከለከለ ነው። መብላት፣ መጠጣት፣ መዝናናትና አላህን ማወደስና ማላቅ ነው የሚገባው፡፡ ትናንት ከትናንት ወዲያ ያላረደ ዛሬም ማረድ ይችላል።
ዒዱ እንደቀጠለ ነው

ፍቅር፣ አብሮ መብላትና መተዛዘናችን ሁሌም አይለየን!

#Share
#Like
Telegram:
https://hottg.com/mahbubil
https://hottg.com/mahbubil
ሁሌም ዋጋቸው ትልቅ ነው!

ሁል ግዜም ቢሆን አጠገባችን ያሉ ሰዎች ለእኛ ያሉልን ሰዎች በሙሉ ጀግናዎቻችን ናቸው! የትዳር አጋሮቻችን ቤተሰቦቻችን ጓደኞቻችን ብቻ በህይወታችን በመኖራቸው ብዙ ዋጋ ያገኘንባቸው ሁሉ ከሩቅ አይተን ከምናደንቃቸው ሰዎች በላይ ለእኛ ድንቆች ናቸው እና ዎጋቸው ከልባችን ገብቶን ልናከብራቸው ፣ ልናደንቃቸው እና ልናከብራቸው ይገባናል ከእኛ በላይ ዋጋቸውን ሊያውቅላቸው የሚችል ሌላ ማንም ሰው አይኖርም እና ያስፈልጋቸዋል !

የተባረከ ቀን ተመኘን 🙏
@mahbubil
🖤❤️ዋሪዳ

ነብያችንﷺ እና ሰሓባዎቻቸው በእስልምና የመጀመሪያው የሆነውን ሒጅራ ከመካ ወደ መዲና ባደረጉ ግዜ ሠይደል ውጁድﷺ እና ረፊቃቸው ሠይዲና አቡበከር(ረ.ዐ) በቀናት ወደሁዋላ ዘግይተው ነበር::

ቀድመው መዲና የገቡት ሙሓጂሮች እና አንሳሮች በነብዩﷺ ናፍቆት ልባቸው ተንጠልጥሎ ህፃን አዋቂው፣ሴት ወንዱ ከቤቱ ወጥቶ መጠባበቅ ሆነ ስራው:: የካኢናቱ ሁሉ ኢማምﷺ በደረሱ ግዜ በዛ ሁሉ ኸልቅ ልብ ላይ ዋሪዳው ወረደ ሁሉም በአንድነት:-(ከሠይዲ እንደሰማሁት ከዛ በፊት ተብሎ የማያውቅ የሆነ አዲስ መድህ)
"ጠለዓል በድሩ ዓለይና ሚን ሠኒየቲል ወዳዕ
ወጀበ ሹክሩ ዓለይና ማዳዓ ሊላሂ ዳዕ" እያሉ ነብዬንﷺ እየመደሁ ድቤ እየደለቁ እያጨበጨቡ ሐቢቢን ተቀበሏቸው:: አሊይሂ አፍደሉ ሰላት ወልሰላም🤍🤍🤍
በሀገራችን እንዲሁም ከሀበሻ ውጪ ያሉ አካቢር አውሊያዎች ነቢንﷺ የመደሁት ልመድህ ብለው አስበው ግጥም ገጥመው ሳይሆን ግጥሙ እራሱ መጥቶ በሉኝ ነው የሚላቸው:: ለምሳሌ ያክል ሸምሰዲነል አብሬትይ ክብሪተል አሕመር የሰለዋት ኪታባቸው መግቢያ ላይ እንዲህ ብለዋል:-በሸዋል ወር ከዙሁር ሶላት ተርቲብ አዝካሬ(ኢባዳ)ዬ በሁዋላ ምንም አይነት ሌላ ንግግር ሳላስከትል ተኛሁ...የዚህ ሰለዋት ዋሪዳ በመናሜ ሐርፈን ሐርፍ ተከትቦ መጣ...እኔ አፍደል (የተሻልኩ) (ምርጥ) የሆንኩ ሶለዋት ነኝ, ክብሪተል አሕመር እባላለው ቅራኝ አለኝ እኔም ቀራሁት... ብዙ እንግዳ እና ግሩም የሆኑ ብዙ አስራሮችን አየሁባት ይላሉ ጌቱዋ:: ለእኛ አይነቱ የሚገባ ጉድ አይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሐርፍ በዋንጫ ሆኖ በልዩ ልዩ መጠጥ ተመስሎ መጣ ይላሉ... ኧረ እንደው ከለሩንም ይናገራሉ::
ሌሎችንም እጅግ ብዙ ብዙ አብሬትይ ከመድሆቻቸ እና የሰለዋት ኪታቦቻቸው መግቢያ ወይንም መጨረሻ ላይ የፃፉዋቸውን መጥቀስ ይቻላል::

@mahbubil
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ኸሚስ ሙባረክ🥰🥰
ጀግኖቹን የመሻይኮቹን ልጆች ታስረው ነቢን ሰለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም በማወደስ እስር ቤት ሳይሆን ኸልዋ ያሉ ያስመሰሉትን ጀግኖች ሀድራ ተጋበዙልኝማ🥰

ክብር ለመሻይኮቻችን እንዲሁም ለልጆቻ😘

hottg.com//mahbubil
hottg.com//mahbubil
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ሀቁን የሚፈልግ ይስማ ልቡን ከፍቶ አሏህ ሀቁን እንዲያወጣውም ዱዓ ያድርግ።

#ፍትህለሙስሊሞች
#ፍትህለዑለሞቻችን
#ፍትህለአስሱናቲቪ
@mahbubil
የአለም መንግስታት የትናንትናውን የወንበዴዎችን ስራ በማውገዝ ላይ ይገኛል!!

ኤርዶጋን በዚህ መልክ አውግዘዋሉ☝️☝️

ይቀላቀሉን👇👇
@mahbubil
የእድሜ ልክ መሪያችንን! 🥰

hottg.com//mahbubil
ኸሚስ ሙባረክ
KEMIS MUBAREK
ዛሬማ ወሏሂ አንላቀቅም
በሙሂቦች አፍ የተረገመው
ነብዬም አይወዱት የጠመመ ነው
ሙሂቦችዬ ሴት ወንድ ትልቅ ሽ
ሳትሉ ለሀገራችን ለስልምና
የማይበጀውን ወገባችሁን ታጥቃችሁ በዱአ በርቱ
አሏህ ምንግዜም ከእውነተኞች ጋር ነው አብሽሩ
ሼር......
ሼር.....
https://hottg.com/limugenet
https://hottg.com/mahbubil
ፉአድ መሀመድ ከ አሙዋ ሪከርድስ ጋር ባደረገው ቆይታ መንዙማ ስለምትለቅ ምን እያሉ ይተቹካል
ተብሎ ለተጠየቀው ጥያቄ የሠጠው አሳዛኝ ምላሽ😔😔😔
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
Join & Share
👇👇👇👇👇👇👇👇
hottg.com//mahbubil
on YouTube
https://youtu.be/pHQQj0fxSZoአዲሱን የሁሉ እስትንፋስ ስለወደዱት አመሰግናለሁ አሁንም ገብተዝ ይመልከቱ
hottg.com//mahbubil
hottg.com//mahbubil
HTML Embed Code:
2024/05/21 19:08:47
Back to Top