TG Telegram Group Link
Channel: Teddy Afro
Back to Bottom
ቴዎድሮስ እስኪ-ነግሥ /የቴዲ አፍሮ የህይወት ጉዞ/

"የሰው ልጅ በኖረበት በየትኛውም የዓለም ስፍራ፥ ባለጸጋ ሆነ ድሃ፣ አለቃ ሆነ ምንዝር በምድር በቆየባቸው ዘመናት የፈጸመው መልካምም ሆነ መጥፎ ተግባር በትውልዶች የህይወት ገጽ ውስጥ በአንዳች መልኩ መስፈሩ አይቀሬ ነው። በዚህ የህይወት ፍሰት ውስጥ ያለፈ ሁሉም ሰው ደግሞ የኋላ ዳና፣ የዛሬ አሻራ፣ የነገም ራዕይ አለው።"

እነሆ የክቡር ዶክተር አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን /ቴዲ አፍሮ/ የትላንት፣ ዛሬና ነገ መልክ፡፡

መጽሐፉን ከነገ ጀምሮ በነዚህ በታች በተጠቀሱት መደብሮች ማግኘት ይችላሉ።

✔️ስታዲየም ነጃ መጽሐፍ መደብር 0910990259

✔️ለገሀር በጋሻው መጽሐፍ መደብር 0911656729

✔️ለገሀር ማድያ ያሬድ መጽሐፍ መደብር 0913094097

✔️ሜክሲኮ ኤልያስ አምደ መጽሐፍ መደብር

✔️መሳለሚያ ሆናልያት ህንፃ ቢሮ ቁጥር 156 ተኬ ማን ፕሮሞሽን 0911518012 ወይም 0921935862

✔️አራት ኪሎ 0901197837

✔️ካዛንቺስ መላ ህንጻ ጦቢያ መጽሐፍ መደብር 0913108312

✔️ፒያሳ አፒር ታረቀኝ መጽሐፍ መደብር 0983294565

እንዲሁም በሁሉም የመጻፍ መደብሮች ያገኛሉ
ለበለጠ መረጃ 0975550865 ይደውሉልን
የአክብሮት ሰላምታዬን በማስቀደም ከሰሞኑ በምድረ አሜሪካ ኦሪገን ግዛት ተካይዶ በነበረው 18ተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና በተቀዳጀነው አንፀባራቂ ድል የተሰማኝን ደስታ ስገልፅ በተለይም በአሁኑ ወቅት ሀገራችን ካለችበት ተጨባጭ ሁኔታ አንፃር ከመቼውም ጊዜ በላቀ ብሔራዊ ስሜታችን ሊጠናከር በሚገባበት በእዚህ ታሪካዊ እና ወሳኝ ሰዓት ይህን አኩሪ ድል ላስመዘገቡ ባለውለታ ውድ ጀግኖች አትሌቶቻችን እና እንዲሁም ይህ የተቀናጀ ውጤት እንዲመጣ ከፍተኛ አስተዎፆ ላደረጉ ጀግናዋ አትሌት ኮማንደር ደራርቱ ቱሉን ጨምሮ ለአሰልጣኞች እና ለመላው የሉካን ቡድኑ አባላት በሙሉ ከፍ ያለ የአክብሮት ምስጋናዬን እያቀረብኩ ነው::

በእዚህ አጋጣሚ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ወገኖቼ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክቴን ለማስተላለፍ እወዳለሁ::

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!
ፍቅር ያሸንፋል
ቴዎድሮስ ካሳሁን
(ቴዲ አፍሮ)
በአትሌቲክሱ ዘርፍ በአገሬ አሜሪካ ኦሪገን ግዛት ላይ ተካሂዶ በነበረው በ18ተኛው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና አራት /4/ ወርቅ፣ አራት /4/ ብር እና ሁለት /2/ ናህስ በጥቅሉ አስር /10/ ሜዳሊያዎችን በማንሳት አገራችን ኢትዮጵያ በዓለም የሁለተኛ ደረጃነትን እንድትይዝ እና ለዚህ አንጸባራቂ ድል እንድትበቃ ያስቻላችሁ መላው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን አባላት በሙሉ ከልብ ልናመሰግናችሁ እንወዳለን።

ኢትዮጵያ ስሟ በዓለም ከፍ ይል ዘንድ ብሎም ኢትዮጵያውያን ወደ ብሄራዊ ስሜታቸው ይመለሱ ዘንድ እንዲህ ያሉ አነቃቂ እና አርኪ ተግባሮች በሁሉም ዘርፎች ይደገሙ ዘንድ መልካም መሆኑን ለማስታወስ እወዳለሁ። ሁሉም ኢትዮጵያ ሲል ማየት ደስ ይላል።

4 🥇 4 🥈 2 🥉

#WorldAthleticsChamps

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
ቴዎድሮስ እስኪ ነግሥ
ቴዎድሮስ እስኪነግሥ ከተሰኘው መጽሐፍ ከገጽ 204-206 ካለው የተወሰደ።

የምትሰማውን ሳይሆን የሚሰማህን ተከተል,!

ኢትዮጵያ የጀብድና መስዋዕትነት እንዲሁም የአሸናፊነት ምልክት እንጂ በምርኮ የምትበዘበዝ የተሸናፊዎች መገለጫ አይደለችም፡፡ ጀግኖቿ በህይወት እያሉም ሆነ በሞታቸው ውድቀትና ባርነትን ድል ነስተው፣ ሀገርና ህዝብን በነጻነት ያቆዩ ናቸው፡፡ በዘመን መፈራረቅ ውስጥ እነዚህ ታላላቅ ሰዎች ለሚወዱት ሀገርና ህዝብ ራሳቸውን ዝቅ በማድረግ ኢትዮጵያና ህዝቦቿን ከፍ አድርገው ህይወታቸውን ያለስስት ገብረዋል፡፡ እኒህ ከሀገርና ከህዝብ በፊት ራስን መስዋዕት ማድረግ የሚቀድማቸው ቀደምት አባቶቻችን እንዳለመታደል ሆኖ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ እሳት አመድን ወለደ እንደሚባለው ከላይ እስከ ታች የተሰገሰጉ ባለጊዜ ሹመኞች ባላጠለቁት ሱሪ፣ ባልነበሩበት የጦር ግንባር፣ የድል አጥቢያ ሽለላና ፉከራቸውን እያቀለጡ ሀገርን ለባንዳ፣ ህዝባቸውን ለባርነት አሳልፈው ሲሰጡ ይስተዋላል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የመረማመጃ ምንጣፋቸውን አንስተው በባዶ እግር ጉዞ እሾህ ተጎዝጉዞ የሚኖሩ ኢትዮጵያ ከኔ ጀመረች ባይ ተራማጆችን መመልከት የተለመደ ነገር እየሆነ መጥቷል፡፡ በሰላም ተኝቶ ለማደር ቀርቶ ቆሞ ለመራመድ እንኳን ከእግር በፊት ዋስትና የሆናቸውን የቀደሙት አባቶቻችንን ደምና አጥንት እየከሰሱና እያንኳሰሱ የተያይዞ ገደል ጉዟቸውን ተያይዘውታል፡፡ ይህ ጊዜ የሰጠው ባለ ጠባብ ቅል አዕምሮ የሰፊዋንና ታላቋን ሀገር ነባር ርስት ሸንሽኖ ህዝብን ለመበታተን በመጣደፍ ለሰይጣን ወዶ ገብነቱን በመፍቀድ ሽምጥ የሚጋለብ ፈረስነቱን ተያይዞታል፡፡ ልዩነት እየዘራ የሰው አንገት ያጭዳል፤ ጎተራና ገበታውም የአቤል ስጋና ደም ከሆነ ሰንብቷል፡፡

በዚህ መርህ አልባ የህይወት አዙሪት ቅኝት ብዙኀኑ የውሸት ገናናዎች በእውነት ተፈትነው ይወድቃሉ፡፡ ባለራዕዩ የጥበብ ሰው በአባቶች ቅን አመለካከትና በመንፈሳዊ ጸጋ ከዘመነ መሳፍንት አዙሪት ወጥታ እያበበች የነበረችውን ሀገር ትንሽዬ መንደር ያደረጓትን ሹማምንት በአደባባይ መታገሉ ከሞት በታች የሆነ ብዙ ዋጋ አስከፍሎታል፡፡ ይሁን እንጂ ከራሱ ዝና የቀደምት ሀገሩን ክብርና የህዝብ ነጻነት ለማስከበር ሞትም ቢመጣ ጽዋውን ሊጋተው ወስኖ ጉዞውን በመጀመሩ ምንም ዓይነት ፈተና ከጉዞው ሊያስቆመው አልቻለም፡፡

በጥቂት የሚቆጠር እድሜ ውስጥ ዋጋው ተለክቶ የማይታወቅ ዕልፍ ዘርፈ-ብዙ ስራ የሰራው ጥበበኛ የወገኖቹ የጸብ ጠብመንጃ ላይ በፍቅር ቁሞ የፈሰሰውን ደም ለማድረቅ፣ የተደፋውን ለማቅናት፣ የደረቀውን ለማለምለም ደፋ ቀና እያለ ሲታትር ውቡን የወጣትነት እድሜውን ለሀገሩ ገብሯል፡፡ ቴዲ ከብዙዎቹ የሚለየው የሚሰማውን ውስጡ የሚለውን፣ የሚሰሙትን፣ ጆሯቸውን የሰጡትን እንጂ በየመንገዱ የሚሰማውን አልተከተለም፡፡ ጥላቻን ጆሮው ሲሰማ ውስጡን ፍቅር ገባው፤ መከፋፈልን ጆሮው ሲሰማ አንድ መሆን ውስጡን ገዛው፤ የወደፊቱን ጭንቅ በጆሮው ሲሰማ ልቡ የወደፊቱ ብርሃን አየው፤ ያንንም ሲከተልና ሲያቀነቅን የኖረ የመልካም መሆን አርአያ ጀግና አርቲስት ነው፡፡

መጽሐፉን ከዚህ በታች በተጠቀሱት መደብሮች ማግኘት ይችላሉ።

✔️ስታዲየም ነጃ መጽሐፍ መደብር 0910990259

✔️ለገሀር በጋሻው መጽሐፍ መደብር 0911656729

✔️ለገሀር ማድያ ያሬድ መጽሐፍ መደብር 0913094097

✔️መሳለሚያ ሆናልያት ህንፃ ቢሮ ቁጥር 156 ተኬ ማን ፕሮሞሽን 0911518012 ወይም 0921935862

✔️አራት ኪሎ 0901197837

✔️ፒያሳ አምፒር ታረቀኝ መጽሐፍ መደብር 0983294565

ለበለጠ መረጃ 0975550865 ይደውሉልን።
‹‹አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ ዕለት እዚያው ነበርኩ፡፡ መጀመሪያ በእጃቸው ይዘውት የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለውም በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ። የኪሳቸውንም ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከኪሳቸው ከተቱት። ወዲያው ወታደሮቸ በሩምታ ተኩሰው ገደሏቸው። ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ሕዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ። ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል› አለኝ። ‹እንዴት?› ብለው ‹አላየህም ሲያጨበጭብ?› አለኝ። ‹ባታውቀው ነው እንጂ የሕዝቡ ባሕል ሲናደድም ያጨበጭባል› አልኩት። ‹እንዴት?› ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት።››

አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ በቦታው ሆነው የተከታተሉት ሙሴ ፓይላክን የተባሉ ግለሰብ በወቅቱ የነበረውን ሁኔታ ለጳውሎስ ኞኞ ከነገሩት የተወሰደ።

ሀገራችን ኢትዮጵያ የቆየችው በዕልፍ መስዋዕትነት ነው። በትላንቱ መስዋዕትነት ያሁኑ ትውልድ በሰላም እና በተድላ ይኖር ዘንድ መብት ነበረው። ምክኒያቱም በቂ የሆነ መስዋዕትነት የተከፈለለት እድለኛ ትውልድ ስለሆነ። ዳሩ ግን ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ እንዲሉ ሆነና ነገሩ ዛሬም ከግማሽ በላይ በሆነው ልባችን መከራ አዝለን እንኖራለን። በአመት ሺ ጊዜ አዝነን አንድ ጊዜ ብቻ ደስ እንሰኛለን። እሱም ጣዕሙ እንደቀድሞ በሆነልን እያልን....

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

ስለከበረው መስዋዕትነታቸው አባቶቻችንን እናመሰግናለን።
Twitter ላይ በታዋቂ ሰዎች ስም በተከፈቱ ሀሰተኛ የTwitter ገጾች ላይ ቴዲ አፍሮን ጨምሮ በሌሎች የአገራችን ታዋቂ ሰዎች ላይ የሚደረጉ የጥላቻ ንግግሮች ተጠናክረው እየቀጠሉ ይገኛሉ። እነዚህ ነገሮች ሀሰት መሆናቸውን በስፋት ተደራሽ ለማድረግ እና እነዚህን የስም አጠልሺ ገጾችን ለማዘጋት ሁሉም ሰው የበኩሉን ሊወጣ ይገባል።

የኛን የTwitter ገጽ ይቀላቀሉ።

https://twitter.com/teddyafro_net
ለውዴ ውዱ ነሽ

በጎደለ ሞልተሽ፤ በጠፋው ተክተሽ፣
ሲዝል አበርትተሽ፤ ግራውን ደግፈሽ፣
የብቸኝነት ጉዞውን፤ በጥንድ ቀይረሽ፣
ባብሮነትሽ አጅበሽ፤
ሙሉ አደረግሽው፤ መልኩን አሳቅፈሽ
እራሱን ደግመሽ፣ እራስሽን ደግመሽ።

መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ሚካኤል እናት፣
መኑ ከመ ሄዋን፤ እንደ ብሩክቲ እናት?
ሁሌም አብራው ያለች፤ እየሆነች ብርታት፣
ለብላቴናው ክብሩ፤ ለልቡም ዘውድ ናት።

እንደ ግጥሜ ርዕስ፤ እንደ ስንኝ ቋጠሮ፣
እንደ ጠቢብ ቅኔ፤ እንደ ፀሐይ ኑሮ፣
ልብሽ ብሩህ ነው፤ ዘውትር የሚፈካ፣
መልክሽ በለስ ነው፤ ውዴ ባንቺ 'ረካ።

የሰጠሽው ፀጋ፤ የሰማይ ላይ መና፣
እንደ ምድር ሃመልማል፤ የፈካ ነውና፣
ልቡን ፍቅር ሞላው፤ ደስታውም አበበ፣
ለውዴ ውዱ ነሽ፤ በመልክሽ ተዋበ!

እንደ ከዋክብ ብዙ፤ እንደ ጀምበር ውብ፣
አንድ ሰው እልፍ ነው፤ ከተቸረው ልብ!!
አንድ ሳለሽ ብዝተሽ፤ ሁሉን የሆንሽለት፣
ጤና ይስጥሽ አምላክ፤ ዘላለም ኑሪለት!

እንደ ምድር አሸዋ፤ እንደ አባይ ጅረት፣
አንድ ሰው ብዙ ነው፤ ፍቅር ከሞላበት!
በዝተሽ አበዛሽው፤ በርተሽ አፈካሽው፣
ከፊትም ከኋላም፤ በሁሉም ከበሽው።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
MAYA MUZIKA

የፊልም ዳይሬክተር፣ ተዋናይት፣ ፕሮዲዩሰር፣ እስክሪብት ጸሐፊ እና የማያ ፊልም ድርጅት ባለቤት የሆነችው አርቲስት አምለሰት ሙጬ በሙዚቃው ዘርፍ ላይም Executive Producer በመሆን Maya Muzika የሚል ዲጂታል ሚዲያ አቋቁማ ወደ ስራ ገብታለች። በቀጣይነትም በኪነጥበቡ ዘርፍ በፊልም እና በሌሎች የሚዲያ ስርጭቶች ላይ በስፋት ለመሳተፍ ዝግጅቶቿን በማጠናቀቅ ላይ ትገኛለች።

Maya Muzika አዳዲስ ሙዚቃዎችን በማሰራጨት ለአድማጭ ማቅረቡን ጀምሯል።

የMaya Music You Tube Channel Subscribe በማድረግ አዳዲስ ሙዚቃዎችን ያድምጡ።

https://youtube.com/channel/UCwoELuj5NvoHsBV4Q394ASQ
ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ....!

2015 አመተ ምህረት!

በመላው ዓለም የምትገኙ ውድ ኢትዮጵያውያን ሆይ ኢትዮጵያ ሀገራችን ከጥንት ጀምሮ የራሷ የሆነ የዘመን አቆጣጠር ቀመር ያላት ሀያል አገር ነች። እነሆ ከክርስቶስ ልደት በፊት ዓክልበ. (ዓመቶች ከክርስቶስ ልደት በፊት) ወይም ክ.በ. (ከክርስቶስ በፊት) አልያም ቅ.ል.ክ. (ቅድመ ልደተ ክርስቶስ) ማለት ከ1ኛው ዓመተ ምሕረት (ዓ.ም.) አስቀድሞ የነበሩት ዓመቶችን የመቆጠሪያ ዘዴ በነዚህ መልኩ እንደነበር ይታወቃል። የነዚያን አመታቶች ቀኑን አስልታ ዘመኑን ፈጽማ ስታበቃ ከክርስቶስ ልደት ጀምሮ /ዓ.ም/ አመተ ምህረትን አንድ ብላ በመቁጠር ከዚህ ዘመን የደረሰች የጥበብም የእድሜም ባለጠጋ ነች።

እነሆ በኢትዮጵያ የዘመን አቆጣጠር መሰረት ዘመኖች በአራት ተከፍለው በዚሁ መደብ እየዞሩ ሲደግሙ ይገኛሉ። እነሱም በሐዋርያት ስሞች የተሰየሙ ናቸው። ዘመነ ማቴዎስ፣ ዘመነ ማርቆስ፣ ዘመነ ሉቃስ እና ዘመነ ዮሐንስ ይባላሉ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ባሳለፍናቸው ጢቂት አመታቶች ብዙ ፈተናን አሳልፈናል። በኢትዮጵያ ታሪክ ሊያውም በዚህ ዘመን በፍጹም ሊፈጸሙ የማይገቡ አሰቃቂ ግፎች በንጹሃን ወገኖቻችን ላይ በተደጋጋሚ ሲፈጸምና ፍትህ ሳይሰጥ፣ የደም ካሳ ሳይደረግ፣ በአገር ደረጃ የሀዘን ቀን ሳይታወጅ አልፎም ተርፎም ለአስክሬን ጥላ እናኖራለን በሚል ፌዝ ባላስፈላጊ እልቂቶች ታጅቦ ዘመኑ እንዳይልፍ ሆኖ አልፏል። በነዚህ አመታቶች ውስጥ የደረሰው ግፍ ሁሉ ሰው ሰራሽ ግፍ ነበር። ንጹሃን ወገኖቻችን ያለቁት በማንአለብኝነት አገሪቷ ላይ በሚፈነጩ አካላት እንጂ ተፈጥሯዊ በሆነ አደጋ አልነበረም። ለዚህም ተጠያቂው አካል ቃታ ሳቢው እና የአገሪቷን ህገመንግስት ማስከበር ያለበት አካል ነው።

ውድ ኢትዮጵያውያን እኛ በህይወት ያለን ቅዱስ እግዚአብሔርን የማመስገን ግዴታ አለብን። ልዑል እግዚአብሔር በወጀብ እና በማዕበል መኃል ጠብቆን ከዘመነ ማርቆስ ወደ ዘመነ ሉቃስ አሸጋግሮናል። ክብር እና ምስጋና ለቅዱስ ስሙ ይሁን። መጪው አዲስ አመት ከምንም በላይ የሠላም፣ የጤና፣ የፍቅር፣ የፍትህ እና የኢትዮጵያውያን ክብር የሚጸናበት ይሆንልን ዘንድ ከልብ እመኛለሁ። ከአመቱ ጅማሬ እስከ ፍጻሜው ድረስ እግዚአብሔር ይክበርበት። እግዚአብሔር ያልቀደመበት ዘመን አይደለም ሰዓታቶች እንኳን ከንቱዎች ናቸው።

ብሩህ ዘመን ለመላው ህዝባችን ይሁን።

#ታታ_አፍሮ /ነፃ ብዕር/
Forwarded from ሰኒ ባህላዊ አልባሳቶች አከፋፋይ
መልካም አዲስ አመት...!
🌼🌼🌼🌼

ሰኒ የአገር ባህል አልባሳት እና ቁሳቁስ አስመጪ!

ከኢትዮጵያ የአገር ባህል አልባሳቶችን እና የኢትዮጵያ ባህላዊ ቁሳቁሶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እናስመጣለን። የፈለጉበት አህጉር ሆነው ይዘዙን...!

የሚፈልጉትን የአገር ባህል ልብስ አልያም ቁስ ፎቶውን በውስጥ መስመር ይላኩልን እኛም ከጥራት ጋ ያሉበት አገር ድረስ በፍጥነት እንልክሎታለን።

በተጨማሪም ካሉበት አገር ሆነው ወደ ኢትዮጵያ ለወዳጅ ዘመድዎ መላክ የሚፈልጉትን ማንኛውንም አይነት እቃ በከተሞች እና ወደ ክፍለ አገሮች በፍጥነት እንልካለን።

እዚህ ይዘዙን👇
@mimiteshager
@seniclothesimporter
HTML Embed Code:
2025/06/28 08:02:11
Back to Top