TG Telegram Group Link
Channel: ✝️ስርዓተ ቤተክርስቲያን መመሪያ ✝️
Back to Bottom
እግዚአብሔርን አምናለሁ አከብራለሁ የሚል አንድ ሰው ነበር ከእለታት በአንደኛው ቀን አንድ እንግዳ ወደቤቱ ይመጣል እሱም እንደክርስትናው ሥርዓት ጓዙን ተቀብሎ 🍽የሚበላውንና የሚጠጣውንየሚተኛበትንም አዘጋጅቶ ሲያብቃ እግሩን ያጥበው ጀመር፡፡ ይህ ደግ ሰው የእንግዳውን እግር እያጠበ "ዛሬ አንተን ወደ ቤቴ ያመጣልኝ እግዚአብሔር ክብር ምስጋና ይግባው" ይላል:: እንግዳውም "እግዚርአብሔር ማነው?" ይለዋልእድሜህ በጥያቄው የደነገጠው እንግዳ ተቀባይ "ምን ማለትህ ነው እግዚአብሔርን አታውቀውምን?" ይለዋል "ኧረ በፍጹም ስሙንም ያለዛሬ ሰምቼ አላውቅም"ይላል እንግዳው፡፡ ለመሆኑ  ስንት ነው?ይላል የቤቱ ባለቤት። እንግዳውም ፷(ስልሳ) ይላል የቤቱ ባለቤት በጣም በመደነቅ በመናደድም ጭምር የእንግዳውን እግር ማጠብ አቋርጦ "60 ዓመትእንዴት ሙሉ እግዚአብሔርን የማያውቅ ሰውማ እቤቴ አያድርም" ብሎ ያባርረዋል። የቤቱ ባለቤት እኩለ ለሊት ላይ ራእይ ያያል ልኡል እግዚአብሔር ተገልጾ "ዛሬ  ውለህ አመሸህ?" ሲለው የቀኑን ውሎ ተናግሮ ሲያበቃ "60 ዓመት ሙሉ አንተን የማያውቅ እንግዳ በቤቴ ሊያድር ሲል እኔ ያንተ ባርያ አባርርኩት" አለ።እግዚአብሔርም ይህንን ስህተቱን ሊያርም ነበርና መምጣቱ "ወዳጄ ሆይ እኔ ፷(ስልሳ) ዓመት የታገስኩትን አንተ አንድ ሌሊት መታገስ አቃተህን?" .....ብሎ መክሮት ተለየው

ብዙውን ጊዜ ሰው ከእግዚአብሔር ቀድሞ ፍርድ ለመስጠት ሲደክም ይታያል። እሱ እኛን በታገሰን ልክና መጠን ባይሆንም ምሳሌነቱን ወስደን ሰዎችን ይቅር ማለትና መታገስ አለብን
https://hottg.com/sratebetkrstyane
አንዲት ሴት ወደ ንስሐ አባቷ ጋር በመሔድ ከዛሬ ጀምሮ ቃለ እግዚአብሔር ለመማር ወደ ቤተክርስቲያን አልመጣም አለቻቸው።
እኚህ አባትም ደንገጥ ብለው  ለምን ልጄ ብለው ጠየቋት

እሷም እንዲህ አለች" ለትምህርት የሚመጡ ሰዎች በስብከት ሰዓት ስልካቸው ላይ አፍጠው  ፌስቡክናሌሎች ሶሻል ሚዲያዎች እያዩ አንዳንዶች አፍ ለአፍ ገጥመው ያንሾካሽካሉ፣ ሰውን ያማሉ ሌሎቹ ደም በሀሳብ ሔደዋል ሁሉም አስመሳዮች ናቸው ስለዚህ ሁለተኛ አልመጣም" አለቻቸው።

አባም ዝም አሉ ፦ ከዚያ ትንሽ ቆይተው ውሳኔ ላይ ከመድረስሽ በፊት ለአንቺ የሚሆን አንድ ጥያቄ አለኝ አሉዋት

እሱዋም ጠይቁ አለቻቸው

አንድ ብርጭቆ ሙሉ ውሃ 💦 ይዘሽ በጉባኤው መሀል አቋርጠሽ መምጣት ትችያለሽ አሉዋት

እሱዋም በሚገባ እችላለሁ ብላ አንድ ጠብ ሳይልባት እንዳለችው አደረገች።

አባም ጥያቆውን አቀረቡላት  ውሀውን ስታመጪ  ጉባኤው ላይ ስልክ የሚመለከት ወይም የሚንሾካሸክ አይተሻል  ወይ  አሉዋት

ሴትዬዋም "አለ በፍጹም አላየሁም❗️ለሳቤ ሁሉ የብርጭቆው ውሃ💦 እንይፈስ ሀሳቤ ሁሉ እዛ ላይ አድርጌው ነበር" አለች

አባም እንዲህ አሉ፦ "አየሽ ሙሉ ትኩረትሽን ብርጭቆ ላይ ስለነበር ማንንም አላየሽም ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጪ ማድረግ ያለብሽ ነገር ይህ ነው ሙሉ ትኩረትሽ እግዚብሔር ላይ መሆን አለበት አለበለዚያ ትወድቂያለሽ። አይኖችሽን ከሰዎች ላይ አንስተሽ ክርስቶስ ላይ አድርጊ።

እግዚአብሔር እኔን ተከተሉኝ እንጂ ክርስቲያኖችን ተከተሉ አላለም። አእምሮአችን ክርስቶስ የተናገረውን፣ ያደረገውን፣ ያሰበው ምን እንደነበር እንዲያሰላስል እናድርግ ከሰዎች ላይ አይናችንን አንስተን መስቀሉ ላይ አይናችንን እንትከል።
https://hottg.com/DIYAKONAE
🛑🛑የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ የተዋህዶ ልጆች አክሊል ሚዲያ ተተኪ ዘማርያን የምናፈራበት መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ ተከፈተ አሁኑኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ለነፍስዎ ብዙ ነገር ያተርፋሉ@aklil media


https://youtu.be/-S_ZG86A9Bc?si=0HlMPv5UnuqJ9Vv4
ከተራ ምንድን ነው?

ከተራ 'ከበበ' ካለው የግእዝ ግሥ የወጣ ነው፡፡ ፍችው ውኃ መከተር፣ መገደብ ማለት ነው፡፡

በጥምቀት ዋዜማ ታቦተ ሕጉ ከቤተ መቅደስ ወጥቶ ውኃ ባለበት አካባቢ ስለሚያድር የየአጥቢያው ሕዝብ እየተሰበሰቡ በወንዝ ዳር ወይም በምንጭ አካባቢ ድንኳን ይተከላሉ፡፡ ድንኳንም ከሌለ ዳስ ሲጥሉ ይውላሉ፡፡ የምንጮች ውኃ እንዲጠራቀም ይከተራሉ (ይገድባሉ) ጉድጓድ እየተቆፈረ ውኃው እንዳይሄድ በመገደብ ለመጠመቂያ (ለጥር 11) ዝግጁ የሚያደርጉበት ዕለት ነው፡፡

በተጨማሪ  በአቅራቢያ የሚገኙት ቤተክርስቲያናት ተሰብስበው ከዚሁ ከተቆፈረው ገንዳ ወይም ከተገደበው ጅረት  አጠገብ ባለው ዳስ ወይም ድንኳን ታቦቶቻቸውን ያሳድራሉ ሊቃውንቱም በዚያው እግዚአብሔርን በማህሌት ሲያመሰግኑ ያድራሉ።

በበዓለ ጥምቀት የታቦታቱ ወደ ወንዝ መውረድ መድኃኔ ዓለም ክርስቶስ በእደ ዮሐንስ ለመጠመቅ ከገሊላ ወደ ዮርዳኖስ የመሄዱ ምሳሌ ነው፡፡ ታቦቱ የጌታችን፣ ምሳሌ ሲሆኑ ካህናቱ የመጥምቁ ዮሐንስ ምሳሌ ናቸው፡፡ መዘምራኑና ሕዝቡ ደግሞ ዮሐንስ ያጠመቃቸው ሕዝቦች ምሳሌዎች ናቸው፡፡

መልካም የከተራ በዓል....❤️

#ይቀላቀሉን!!
https://hottg.com/sratebetkrstyane
****

ቃና ዘገሊላ

ቃና' የሚለው ቃል በሃገራችን ልሳን (በአማርኛ)
የምግብን: የመጠጥን ጥፍጥና ወይም በጐ መዓዛን የሚያመለክት ነው:: ምንአልባትም ከዚህ በዓል ምሥጢር የተወሰደ ሳይሆን አይቀርም

በቤተ ክርስቲያን ታሪክ ግን ቃና ከገሊላ አውራጃዎች አንዷ ናት:: ለስም አጠራሩ ስግደት ይሁንና የክብር ባለቤት መድኃኒታችን ክርስቶስ በዚህች ሥፍራ ተገኝቶ በድንግል እናቱ ምልጃ ታላቅ ተአምርን በዚህች ዕለት ሠርቷል

ተአምር የሚለውን ቃል በቁሙ 'ምልክት' ብሎ
መተርጐም ይቻላል:: መሠረታዊ መልዕክቱ ግን ነጮቹ በልሳናቸው Miracle የሚሉት ዓይነት ነው:: ከተፈጥሮ ሕግ ውጪ (በላይ):
ከፍጡራንም ችሎታ የላቀ ነገር ሲሠራ (ሲፈጸም) ተአምር ይባላል:: ተአምር የእግዚአብሔር የባሕርይ ገንዘቡ ነው:: እርሱ ዓለምን ከመፍጠሩ ጀምሮ እያንዳንዷ ተግባሩ ለእኛ ተአምራት ናቸው

ስለዚህም ነው 'ኤልሻዳይ / ከሐሌ ኩሉ / ሁሉን
ቻይ' እያልን የምንጠራው:: እግዚአብሔር ፍጡራኑን ይወዳልና እርሱ ለወደዳቸውና ደስ ላሰኙት ተአምራት ማድረግን ሰጥቷል:: በብሉይ ኪዳን እነ ሙሴ ባሕር ሲከፍሉ: መና ሲያዘንሙ: ውሃ ሲያፈልቁ (ኦሪትን ተመልከት) እነ ኤልያስ ሰማይን ሲለጉሙ: እሳትን ሲያዘንሙ: ሙታንን ሲያስነሱ (1ነገሥትን ተመልከት) እንደ ነበር ይታወቃል


እንዲያውም በሙሉ መጽሐፍ ቅዱስ የተአምር መጽሐፍ ነው ብሎ ለመናገርም ያስደፍራል:: በሐዲስ ኪዳንም መድኃኒታችን ብዙ ተአምራትን ሠርቶ ለሐዋርያቱ የተአምራት ጸጋውን ሰጥቷቸዋል:: (ማቴ. 10:8, 17:20, ማር. 16:17, ሉቃ. 10:17, ዮሐ. 14:12) እነርሱም በተሰጣቸው ሥልጣን ብዙ ተአምራትን ሠርተዋል:: (ሐዋ. 3:6, 5:1, 5:12, 8:6, 9:33-43, 14:8, 19:11)

ቅዱስ ዮሐንስ ሐዋርያ በወንጌሉ ምዕራፍ 2 ላይ
እንዳስቀመጠው የቃና ዘገሊላው ተአምር የመጀመሪያው ነው:: "ወዝንቱ ቀዳሜ ተአምር ዘገብረ . . ." እንዲል:: (ዮሐ. 2:11) ያ ማለት ግን ጌታ ከዚያ በፊት ተአምራትን አልሠራም ማለት አይደለም

ይልቁኑ ራሱን ከገለጠና ከተጠመቀ በኋላ የሠራው
የመጀመሪያው ተአምር ነው ሲል ነው እንጂ:: ምክንያቱም መድኃኒታችን እንደ ተጠመቀ ዕለቱኑ ገዳመ ቆረንቶስ ገብቷልና:: (ማቴ. 4:1) አንድም በቃና ሌሎች ተአምራትን የሚሠራ ነውና ይህ ተአምር በቃና የመጀመሪያው ሆነ

+ትክክለኛው የቃና ዘገሊላ ቀን የካቲት 23 ነው:: ጥር 11 ተጠምቆ: የካቲት 21 ቀን ከጾም ተመልሷል:: ከዚያም የካቲት 23 ቀን ደቀ መዛሙርቱን ሰብስቦ ሒዷል:: ነገር ግን አበው መንፈስ ቅዱስ እንደ መራቸው የውሃ በዓል
ከውሃ በዓል ጋር ይስማማል ብለው ጥር 12 ቀን አድርገውታል

በቃና ዘገሊላ ሙሽራው ዶኪማስ ሲሆን ባለ ሠርጉ
ደግሞ አባቱ ዮአኪን ነው:: ይህም ለሐዋርያው ቅዱስ ናትናኤል አጐቱ ነው:: የልጁ ጋብቻ የተቀደሰ ይሆን ዘንድም ጌታ ክርስቶስን: ድንግል እናቱንና ባለሟሎቹ ሐዋርያትን ወደ ሠርጉ ጠራ

ምንም እንኳ መድኃኒታችንና እመቤታችን ከድግሱ
የማይበሉ ቢሆኑም (በትሕርምት ኗሪዎች ነበሩና)
ጠሪውን ደስ ለማሰኘት ሠርጉን (ብቻውን) ለመቀደስና የጋብቻን ክቡርነት ለማሳየት አብረው ታደሙ


የሠርጉ ሥነ ሥርዓት ሲጀመር በድንኳኑ ውስጥ ጌታ ከመካከል ተቀመጠ:: ድንግል በቀኙ: ዮሐንስ በግራው
ሲቀመጡ: ሌሎች ሐዋርያት ግራና ቀኝ ከበው ተቀመጡ:: ሲበላና ሲጠጣ ድንገት የተደገሰው ምግብና መጠጥ አለቀ:: ደጋሾቹ በጭንቅ ላይ ሳሉም አይጠና ሆዷ ድንግል እመ ብርሃን የሆነውን አወቀች:: እንዴት አወቀች ቢሉ:- በጸጋ: አንድም 'ከልጅሽ አማልጂን' ብለው ቢለምኗት ነው ይሏል:: እመቤታችን በዚያ ጊዜ ወደ ልጇ ቀርባ ቸር ልጇን "ወይንኬ አልቦሙ-ወይኑኮ አልቆባቸዋል" አለችው

+ለጊዜው ወይኑም: ምግቡም ስላለቀባቸው እንዲህ አለች:: በምሥጢሩ ግን ወይን ያለችው ፍቅርን: ቅዱስ ቃሉንና ክቡር ደሙን ነው:: ጌታም ይመልሳል:- "ምንት ብየ ምስሌኪ ኦ ብእሲቶ: ዓዲ ኢበጽሐ ጊዜየ-አንቺ ሆይ! (እናቴ ሆይ!) ያልሺኚን አላደርግ ዘንድ ካንቺ ጋር ምን ጠብ አለኝ? ነገር ግን ጊዜው ገና አልደረሰም ብየ ነው እንጂ " አላት::
ምክንያቱም ጌታ:-

የወይን ጋኖቹ እስኪያልቁ ይጠብቅ ነበር:: (አበረከተ ይሉታልና) አንድም ይሁዳ ወጥቶ ነበርና እርሱ እስኪመለስ ነው:: (እኔ ስወጣ ጠብቆ ተአምር ሠራ ብሎ ለክፋቱ ምክንያት እንዳያቀርብ) አንድም "ወይን (ቅዱስ ደሜን) የምሰጠው በቀራንዮ አንባ ነው" ሲል "ጊዜየ ገና ነው" ብሏታል:: አንዳንድ ልቡናቸው የጠፋ ወገኖቻችን ጌታ እመቤታችንን እንዳቃለላት (ሎቱ ስብሐት! ወላቲ ስብሐት!) አስመስለው ይናገራሉ:: ይህንን ስእንኅን ጌታ ባለጌዎቹ እነሱም አያደርጉት:: "አባትህንና እናትህን አክብር" (ዘጸ. 20) ያለ ጌታ እንዴት ለእናቱ ክብርን ይነፍጋል?ልቡና ይስጠን!

ወደ ጉዳያችን ስንመለስ መድኃኒታችን እንዲህ ሲል መለስላት:: ተግባብተዋልና እመ ብርሃን አሳላፊዎቹን "ኩሎ ዘይቤለክሙ ግበሩ-የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው:: (ዮሐ. 2:5) ጌታም በ6ቱ ጋኖች ውሃ አስሞልቶ በተአምራት ወይን አደረጋቸው

+እንጀራውን ወጡን በየሥፍራው ሞላው:: ታላቅ ደስታም ሆነ:: የአሳላፊዎቹ አለቃም (ለአባታችን አብርሃም ምሳሌ ነው) ከወይኑ ጥፍጥና የተነሳ አደነቀ:: በዚህም የድንግል ማርያም አማላጅነት: የመድኃኒታችን ከሃሊነት ታወቀ: ተገለጠ
https://hottg.com/sratebetkrstyane
🌿❤️  ጥር 21  በዓለ  አስተርእዮ  ማለት🌿❤️
《የእመቤታችን በዓለ ዕረፍት እንኳን ለዚህች ታላቅ ክብረ በዓሏ አደረሳችሁ አደረሰን!!!

🌿❤️ ወላዲተ አምላክ ምንም እንኳን የአምላክ እናት ብትሆንም ሞተ ሥጋ ለሁሉም ዕጣ ፈንታ በመሆኑ በስድሳ አራት አመቷ ከሞት ወደ ሕይወት ከመከራ ወደ ደስታ የተሸጋገረችበት ዕለት ነው፡፡

🌿❤️ ታላቁ የቤተክርስቲያን አባት ቅዱስ ያሬድም “ሞትሰ ለመዋቲ ይደሉ ሞታ ለማርያም የአጽብ ለኩሉ” ትርጉሙ ሞት ለማናኛቸውም ሰው ሁሉ የተገባ ነው የማርያም ሞት ግን ሁሉን ያስደንቃል፡፡ በማለት አደነቀ፡፡
🌿❤️ በመሆኑም በዓሉ የወላዲተ አምላክ በዓለ ዕረፍት ከመሆኑ የተነሳ ታላቅ በረከት የሚያስገኝ ስለሆነ በየዓመቱ ይከበራል፡፡
... 🌿❤️ የእረፍቷስ ነገር እንደምን ነው ቢሉስድሳ አራት ዓመት በዚህ ዓለም ኖራ ጥር 21 እሁድ ቀን ጌታ እልፍ አዕላፋት መላዕክቱን አስከትሎ መጥቶ እናቴ ሆይ ከዚህ ዓለም ድካም ላሳርፍሽ መጣሁ አላት፡፡
🌿❤️ ልጄ ሰማይና ምድር የማይወስኑ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በማህጸኔ ተሸክሜ በድንግልና ወልጄህ እሞታለሁミ አለችው፡፡
🌿❤️ በሲዖል የሚሰቃዩ ነፍሳትን አሳይቶ እናቴ ሆይ ሞትሽ ለእነዚህ ቤዛ ይሆንላቸዋል አላት፡፡ እኚህን ከማርክልኝስ ይሁን አለችው፡፡ ቅድስት ሥጋዋን ከቅስስት ነፍሷ ለይቶ በቃለ አቅርንት በዝማሬ መላእክት አሳረጋት፡፡
🌿❤️ ደቀመዛሙርቱንም ከያሉበት በደመና ጠቅሶ ካለችበት አድርሶ እመቤታችሁን ቅበሩ አላቸው፡፡ ባባ ይዘወት ወደ ጌሰማኒ ሲስደት አይተው ልጇን ተነሳ አረገ እያሉ ሲውኩን ይኖራሉ አሁን ደግሞ እሷን ተነሳች አረገች እያሉ ሊያውኩን አይደለም ብሎ ኑ እናቃጥላት ተባባሉ፡፡
🌿❤️ ከመካከላቸው አንዱ ታውፋንያ ዘሎ ያልጋውን ሸንኮር ያዘ፡፡ የታዘዘው መላእክት መጥቶ በሰይፍ ሁለት እጁን ቀጣው፡፡ በድያለሁ ማሪኝ ብሎ ቢማጸናት ድኖለታል፡፡ ከዚህ ቦሃላ ዮሐንስን ጨምሮ ከመካከላቸው ነጥቆ በእጸ ሕይወት ሥር አኑሯታል፡፡
🌿❤️ አንድም በዓሉ-፡ እግዚአብሔር ወልድ በሰውነት ተወልዶና ማንነቱ በይፋ ታውቆ በተገለጠበት በዘመነ አስተርእዮ ውስጥ ስለሚከበር የ
#አስተርእዮ__ማርያም ተብሏል፡፡
🌿❤️ አስቀድመው አሥራ ሁለቱም ሐዋርያት ለስብከተ ወንጌል ወደ ዓለም ሁሉ ተበትነው ነበርና በመንፈስ ቅዱስ ተነድተው ሁሉም ደመናን ጠቅሰው ወደ ኢየሩሳሌም መጡ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ መርቶ አመጣቸው እንጂ ለምን እንደመጡ አያውቁም ነበር፡፡ እመቤታችንም ለምን እንደመጡ ጠየቀቻቸው፡፡
🌿❤️ ቅዱስ ጴጥሮስም፡- “ጸጋን የተመላሽ ቅድስት ሆይ! የመምጣታችን ምሥጢርማ እኛ አንቺን እንጠይቅ እንጂ አንቺም እኛን ትጠይቃለሽን? ሁላችንም ለምን እንደመጣን አናውቅም፡፡
💟ለምሳሌ እኔ አስቀድሜ በአንጾክያ ነበርኩኝ አሁን ግን እነሆ እዚህ ነኝ፡፡ ለምን እንደመጣሁኝ ግን አላውቅም” አላት፡፡ እርሷም ሁሉም በአጠገቧ በተሰበሰቡ ጊዜ የሚሆነውን ነገር አስቀድማ ከልጇ ከወዳጇ አውቃ ተዘጋጅታ ነበርና ለምን እንደመጡ 《ዕረፍተ ሥጋዋን ለማየት እንደሆነ》ነገረቻቸው፡፡
💟ሌሊቱንም በሙሉ በጸሎትና በማኅሌት ደግሞም በዝማሬ ሲያመሰግኑ አደሩ፡፡ ከዚህ በኋላ የተወደደችው እናት በረከቷን አሳድራባቸው በሰላም አንቀላፋች፡፡ ነፍሷም በዐብይ ዕልልታና በታላቅ ምስጋና በመላእክት እጅ ወደ አምላኳ ሄደች፡፡
🌿❤️ ኋላ ሐዋርያቱ ዮሐንስን ሲያገኙት፡- “እመቤታችን እንደምን ሆነች?” አሉት፡፡ እርሱም “በገነት በዕጸ ሕይወት ሥር ዐርፋለች” አላቸው፡፡
🌿❤️ የቀሩት ሐዋርያት “ዮሐንስ ያን ድንቅ የእግዚአብሔርን ሥራ አይቶ እኛስ ሳናይ እንዴት እንቀራለን?! አቤቱ ለእኛም ቸርነትህን አድርግልን” ብለው በነሐሴ መባቻ በአንድነት ሆነው ወደ ፈጣሪያቸው የሚቀርብ የአንድ ሳምንት ጾምና ጸሎት ጀመሩ፡፡
🌿❤️ በሁለተኛው ሱባዔ ማብቂያ ዕለት ነሐሴ 14 ቀን እሑድ የእመቤታችንን ትኩስ ሥጋ መልአኩ ከገነት አምጥቶ ለሐዋርያቱ ሰጣቸው፡፡
💟እነርሱም ልመናቸው ስለ ተፈጸመላቸው ፈጣሪያቸውን በጸሎት አመስግነው በዚያችው ዕለተ እሑድ ቅዱስ ሥጋዋን ወስደው ቀብረውታል፡፡ እርሷም በሦስተኛው ቀን ነሐሴ 16 ቀን ማክሰኞ ተነሥታለች፡፡
🌿❤️ ትንሣኤዋ “ከመ ትንሣኤ ወልዳ- እንደ ልጇ ትንሣኤ” ያሰኘው ይህ በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተለይታ የመነሣቷ እውነታ ነው፡፡
🌿❤️ የአዛኚቱ ድንግል አማለጅነትና በረከት አይለየን አሜን ።
❤️💜💚💛💙❤️💙💚💜❤️
ወስብሓት ለእግዚአብሔር
ወለወላዲቱ ድንግል
ወለመስቀሉ ክብር አሜን
❤️💜💚💛💙❤️
https://hottg.com/sratebetkrstyane
#ይህንን_ያውቃሉ

የሦስቱ ዲያቆናት ምሳሌነት ምንድን ነው ?

ቅዳሴ ላይ እንደሚታወቀው ልዑካኑ  ከሁለት እስከ ሃያ አራት ድርስ ሊደርሱ ይችላሉ

አምስቱ ልዑካን  ማለት ሁለት ካህን ሦስት ዲያቆናት በአጠቃላይ የአምስቱ አማዕደ ምሥጢራት ምሳሌ ናቸው

ሦስቱ ዲያቆናት የየራሳቸው ምሳሌነት አላቸው

1. የዋና ዲያቆን (ሠራዒ )

ይህ ዲያቆን የቅዱስ እስጢፋኖስ ምሳሌ ነው

መጾር ወይም መስቀል ይዟ መቀደሱ ቅዱስ እስጢፋኖስ የተቀበለውን ሰማዕትነት ለማሰብ ነው

2. ተጨማሪ (ንፍቅ )

ዲያቆን ይህ ዲያቆን ደግሞ መጥመቀ መለኮት የቅዱስ ዮሐንስ ምሳሌ ነው

ከፊት ከፊት እየቀደመ  ካህናቱን መምራቱ ሊቀ ካህናት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከፊት ቀድሞ መጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ጥርጊያውን መንገድን የማዘጋጀቱ

ይህ ዲያቆን መብራት ወይም ጠፋፍ የሚያዙ ከመስዋዕት ከማቅርብ አልፎ በዚህ ይመሰላል

3. ፍሬ ሰሞን (መጽሐፍ ገላጽ )

  ይህ ዲያቆን የሐዋርያት አባቶቻችን ምሳሌ ነው እንዴት ቢሉ መጽሐፍ ይዞ በአራቱም አቅጣጫ ይዞራል ይህም
ሐዋርያት በአራቱ አቅጣጫ ወንጌልን የመስበካቸው ምሳሌ ነው።
https://hottg.com/sratebetkrstyane
የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና ግብረ ሰዶማዊነትን አስመልከቶ እየተደረጉ ያሉ ሁለገብ ተጽእኖዎችንና መመሪያ የማስለወጥ ማግባባቶችን አስመልክቶ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ መግለጫ፡፡


የካቲት 4 ቀን 2016 ዓ.ም (ተ.ሚ.ማ/አዲስ አበባ)
#ብዙ_እናቶች ስቃይ ካለበት የወሊድ ሰዓት በኋላ ልጆቻቸውን ሌሎች እንዲመግቡላቸው ለእንግዶች ይሰጣሉ። ክርስቶስ ግን እኛ ልጆቹን በብዙ መከራ እና ስቃይ በመስቀል ላይ ከወለደን በኋላ ሌሎች እስኪመገቡን ድረስ አይተወንም። በገዛ ሥጋ እና ደሙ እየመገበ ራሱ ያሳድገናል። በዚህ ሁሉ መንገድም ከራሱ ጋር አንድ ያደርገናል።”

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
https://hottg.com/sratebetkrstyane
"ወደ ቤተክርስቲያን ወጥተህ እግዚአብሔርን እንደ አምላክነቱ እንደሚገባ አምልከህ ከዚያ በኋላ ወደ ስራህ ብትሔድ የምትሠራው ሥራ የተባረከና የሠመረ እንደሚሆንልህ አታውቅምን?"
  
       
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
D#ነገረ #ክርስቶስ #ክፍል #፵
ጌታ ክርስቶስ በባሕርይው ፍቅር ነው። ይህ ማለት ጥላቻ አይስማማውም ማለት ነው። አይሁድ እርሱን ጌታን ከኃጢአተኞችና ከቀራጮች ጋር ሲበላ አይተውት ነቅፈውት ነበር። "የቀራጮችና የኃጢአተኛዎች ወዳጅ" ብለውታል (ማቴ. ፲፩፣፲፱)። ኢየሱስ ኃጢኣታችን እንደ ምድር አሸዋ የበዛ ቢሆን እንኳ ንስሓ ብንገባ ይቅር የሚል አምላክ ስለሆነ ኃጥአንን ከኃጢአታቸው እንዲመለሱ ምክንያት ለመሆን አብሯቸው ይበላ ይጠጣ ነበር። 

ጌታ ሰዎች ተአምራቱን አይተው፣ ትምህርቱን ሰምተው ከኃጢአታቸው ተመልሰው መልካም ሥራን ይሠሩ ዘንድ በከተማዎችና በመንደሮች እየተመላለሰ ያስተምር ነበር። ነገር ግን ይህ ሁሉ ተደርጎላቸው ከኃጢአታቸው ያልተመለሱ ሀገሮች ስለነበሩ ወዮልሽ ኮራዚ ወዮልሽ ቤተሳይዳ እያለ ወቅሷቸዋል። በፍርድ ቀን መከራ እንደሚበዛባቸውም ነግሯቸዋል (ማቴ. ፲፩፣፳-፳፭)። ጌታ ኃጥአንን እንጂ ኃጢአታቸውን አይወድም። ኃጥአንን ከኃጢአታቸው ለመለየት ብዙ ተአምራትን አሳይቷል። ነገር ግን በባሕርይው ፍቅር የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ በባሕርይው በትክክል የሚፈርድ (ፈታሒ በርትዕ) ስለሆነ ለሁሉም እንደየሥራው ይከፍለዋል። ፍቅሩና ፍርዱ የተስማማለት ጌታ ነው።

ስለዚህ ኢየሱስ የኃጢአተኞች ወዳጅ ነው እያልን ኃጥአን እንሁን ማለት ትልቅ በደል ነው። ጌታ ኃጥአንን በባሕርያቸው ይወዳቸዋል በግብራቸው ግን ይጠላቸዋል። ጻድቃንን ደግሞ በባሕርያቸውም በግብራቸውም ይወዳቸዋል። ስለዚህ እንደ ጻድቃን በግብርም ለመወደድ መልካም ሥራን መሥራት ይገባናል።
#የካቲት_16

#ኪዳነ_ምሕረት (#የሰባቱ_ኪዳናት_ማሕተም)

የካቲት ዐሥራ ስድስት በዚችም ዕለት የክርስቲያን ወገኖች ሁሉም አማላክን ለወለደች ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በዓልን ያደርጋሉ። በዚች ዕለት መታሰቢያዋን ለሚያደርግ ስሟን ለሚጠራ ለድኆችና ለችግረኞች እስከ ቀዝቃዛ ውኃ ለሚሰጥ የክብር ባለቤት ከሆነ ከተወደደ ልጅዋ ከጌታችንና ከመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳንን ተቀብላለችና።

ይህችም የከበረች እመቤታችን ልጅዋ ንጹሕ ሥጋዋን ተዋሕዶ ከብቻዋ ኃጢአት በቀር የሰውነትን ሥራ ፈጽሞ ስለእኛ መዳን ወዶ ያደረገውን መከራ ተቀብሎ ሙቶ ተነሥቶ ከዐረገና በአባቱ ዕሪና ከተቀመጠ በኋላ እርሷን እናቱን ማርያምን በደቀ መዝሙሩ ዮሐንስ ዘንድ ትቷት ነበር እነሆ ልጅሽ እርሱንም እነሆዋት እናትህ ብሎ አደራ እንዳስጠበቀው።

ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ማርያም ትጸልይ ዘንድ ያለ ማቋረጥ ወደ ልጅዋ መቃብር ሁል ጊዜ ስትሔድ ኖረች ይኸውም ጎልጎታ ነው።

አይሁድም በአዩዋት ጊዜ ቍጣንና ቅናትን ተመልተው በድንጊያ ሊወግሩዋት ወደዱ እግዚአብሔርም ከዓይናቸው ሠወራት ከዚህም በኋላ ዳግመኛ መጥታ በዚያ እንዳትጸልይ ተማክረው ከመቃብሩ ዘንድ ጠባቂዎችን አኖሩ እርሷ ግን በየዕለቱ መሔድን አላቋረጠችም ጠባቆችም አያይዋትም የልጅዋ የጌትነቱ መጋረጃ ሠውርዋታልና መላእክትም መጥተው ያገለግሏታል ጌታችንም ዘወትር ይጐበኛታል የምትሻውንም ይፈጽምላት ነበር።

ከዚህም በኋላ መላእክት ወደ ሰማይ አሳረጓትና የጻድቃንን ማደሪያዎች አሳዩዋት አብርሃም ይስሐቅ ያዕቆብም ወዳሉበት አደረሱዋት ከአዳም ጀምሮ እስከዚያ ዕለት በአካለ ነፍስ ያሉ አባቶች ሁሉ አንቺን ከሥጋችን ሥጋን ከዐፅማችን ዐፅምን ለፈጠረልን ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን የአምላክ ልጅ ከአንቺ ሰው በመሆኑ በአንቺ ድህነት አግኝተናል ከጥፋትም የሕይወት ወደብ ሆነሽልናልና እያሉ ሰገዱላት።

ከዚያም ወደ ተወደደ ልጅዋ የእሳት መጋረጃ ወደተተከለበት ወደ ጌትነቱ ዙፉን አደረሷት ጌታችንም እጇን ይዞ ወደ ውስጠኛው መጋረጃ አስገብቶ ከጌትነቱ ዙፋን ላይ አውጥቶ ከእርሱ ጋር አስቀመጣት ያዘጋጀላትንም ዐይን ያላየው ጆሮ ያልሰማው በሰው ልቡና ያልታሰበ ተድላ ደስታን ሁሉ ነገራት።

ከጌትነቱ ዙፋንም በታች የእስራኤል ንጉሥ አባቷ ዳዊትን የነቢያትና የመላእክት ማኀበር እንደ ግድግዳ ከበውት በመሰንቆ ሲያመሰግን አየችው እንዲህም ይላል ልጄ ስሚ በጆሮሽም አድምጪ ወገንሽን የአባትሽንም ወገን ርሺ ንጉሥ ደም ግባትሽን ወዷልና እርሱም ጌታሽ ነውና።

ዳግመኛም የሥቃይን ቦታ ያሳዩዋት ዘንድ መላእክት ከዚያ ውሰዷት ለሰይጣንና ለሠራዊቱ በእርሱ ጐዳና ለሚጓዙ ሁሉ ወደተዘጋጀ ወደጨለማው ዳርቻ አደረሷት እመቤታችን ማርያምም ወዮልኝ ወደዚያ እንዳይመጡ ለሰው ልጆች ማን በነገራቸው አለች መልአኩም አመቤቴ ቡርክት ማርያም ሆይ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይኖራልና ለአንቺም ከአንቺ በኋላም በቃል ኪዳንሽ ለሚታመኑ አትፍሪ አላት ከዚህም በኋላ ወደ ቦታዋ መለሷት።

ከዚያንም ጊዜ ጀምራ እመቤታችን ድንግል ማርያም ስለ ኋጥአን እጅግ እያዘነች ኖረች እንደ ዛሬይቱም የካቲት ዐሥራ ስድስ ቀን በጎልጎታ ቦታ ቁማ ወደ ልጇ እንዲህ ብላ ለመነች ልጄ ሆይ በእግዚአብሔር አባትህ በክርስቶስ ስምህ ከአንተ ጋርም ህልው በሆነ አጽናኝ መንፈስ ቅዱስ አማፅንሃለሁ ዓለም ሁሉ ሊሸከምህ የማይችል ሲሆን ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በተሸከመችህ ማሕፀኔ አማፅንሃለሁ ልጄ ሆይ ያለ ሕማም ያለ ድካም ከእኔ በመውጣትህ በመወለድህ በአሳደጉህ ጡቶቼ በሳሙህ ከንፈሮቼ በአቀፋህ እጆቼ ከአንተ ጋር በተመላለሱ እግሮቼ አማፅንሃለሁ ። በውስጡ በተኛህበት በረት በተጠቀለልክበት ጨርቅ አማፅንሃለሁ የምወድህ ልጄ ሆይ በልቡናዬ ያለውን ሁሉ ትፈጽም ዘንድ የልመናዬን ቃል ሰምተህ ወደእኔ ትመጣ ዘንድ ወዳንተ ፈጽሜ እማልድሃለሁ።

የብርሃን እናቱ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም እንዲህ ብላ በጸለየች ጊዜ እነሆ ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ወረደ ከእርሱም ጋር አእላፍት መላእክት አሉ በዙሪያውም ሁነው ያመሰግኑታል እርሱም እናቴ ማርያም ሆይ ምን ላድርግልሽ አላት እመቤታችንም ለተወዳጅ ልጅዋ እንዲህ ብላ መለሰችለት ልጄ ወዳጄ ሆይጌታዬና ፈጣሪዬ አለኝታዬና መጠጊያዬ በእናቴ ማሕፀንም ሳለሁ ባንተ ጸናሁ አንተም ጠበቅኸኝ ሁልጊዜም ስም አጠራሬ አንተ ነህ።

አሁንም ጸሎቴንና ልመናዬን ስማኝ ቃሌንም አድምጥ እኔ እናትህ እኔም አገልጋይህ የምለምንህ ይህ ነው መታሰቢያዬን ለሚያደርጉ በስሜ አቢያተ ክርስቲያን ለሚሠሩ ወይም የተራቆተውን ለሚያለብሱ የተራበውን ለሚያጠግቡ የተጠማውንም ለሚያጠጡ የታመመውን ለሚጐበኙ ያዘነውን ለሚያረጋጉ የተከዘውንም ደስ ለሚያሰኙ ወይም ምስጋናዬን ለሚጽፉ ልጆቹንም በስሜ ለሚሰይም በበዓሌም ቀን በማኅሌት ለሚያመሰግን አቤቱ ዐይን ያላየውን ጆሮ ያልሰማውን በሰውም ልቡና ያልታሰበውን በጎ ዋጋ ስጣቸው በአማላጅነቴም የሚታመነውን ሁሉ ከሲኦል ነጻ አድርገው ከአንተ ጋር የደረሰብኝን ረኃቡንና ጥማቱን መከራውን ሁሉ አስብ አለችው።

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስም እንዳልሽው ይሁንልሽ የሰጠሁሽም ቃል ኪዳን እንዳይታበል በራሴ ማልኩልሽ አላት።

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በእመቤታችን ድንግል ማርያም በጸሎቷ ይማረን በረከቷም ከእኛ ጋር ይኑር ለዘላለሙ አሜን።

(
#ስንክሳር_ዘወርኀ_የካቲት)
https://hottg.com/sratebetkrstyane
HTML Embed Code:
2024/05/09 12:10:56
Back to Top