TG Telegram Group Link
Channel: ኡመተ ረሱል
Back to Bottom
ረመዳን 26

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

አላህ ሆይ የአይን ማረፊያ የሆኑ ልጆችን ስጠን! በእኛ መሞት ስራችን እንዳይቋረጥ የሚያደርጉ ደጋግ ልጆችን ወፍቀን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዳን 27

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

አላህ ሆይ ጤነኛ፣ ሰላም፣ አፊያ ሆነን ረመዳንን መላልስብን! ከበረከቱም በውስጡ ካለው መልካምም ሁሉ አጣቅመን በሉት!

እኛንም በደግ ዱዓችሁ አትርሱን!

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዷን - 28

ሰዓቱ ዱዓ ላይ ያመለክታል!

ሰው ዘንድ በአደራ ልናስቀምጣቸው ከምንችላቸው ነገሮች አንዱ ዱዓ ነው። አንዳንዴ በራስ አቅም መወጣት የማንችላቸውን ነገሮች የሰው ኃይል እንጨምርበታለን። እኛ አሳምረን አንፈጽመውም በለን የተጠራጠርነውን ጉዳይ መልካም ወንድም እህትን አግዙን እንላለን ።
ወዳጆቼ
በራሳችን ዱዓ ያላገኘነውን በረከት በደጋግ ወንድምና እህቶች ዱዓ ልናገኝ እንችላለን ። ለዚህ ነው ዱዓ አድርጉልን ማለት የምናበዛው።
እኔ ዘንድ ዱዓ ያኖራችሁ ሁሉ ቢስሚላህ አላህ የልባችሁን መሻት ይሙላው።

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
ረመዷን - 29

የቁርአን ኺትሚያ ምሽት።

ረመዷን ሊወጣ ነው። አቀባበሉ ያልሆነለት አሸኛኘቱን ያሳምር።

ዐፉ በሉን ወዳጆች ።

ጌታችሁ የለማኞችን ልመና እየተቀበለ ነው!
عيد مبارك እንኳን ለ1446ኛው የዒድ አል_ፊጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ 🌙

ዒድ ሙባረክ ❤️
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

የወንጀሌ ብዛት  ቁጥር ስፍር የለው
መልካም ስራ የለኝ  የምተማመነው

በማይጠቅምበት ቀን  ወዳጅ ከጓደኛ
በእዝነትህ ካልሆነ  የለኝም መዳኛ

ሰዎች ሲገምቱኝ  መልካም እውነተኛ
እኔ ግን ሌላ ነኝ  ምስኪን ወንጀለኛ

ጌታዬ ሆይ ማረኝ  ድክመቴን ዕይና
መዳኛው ተስፋዬ  ምህረትህ ነው


🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀
🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀

«ከመቃብር ግባ!!»
---------------------

መከራ ምን ቢከብድ ችግር ቢፈረጥም፡
በዱንያዊ ጥቅም ህሌና አይሸጥም፡
ምን ብታብለጨልጭ ይህች ጠፊዋ አለም፡
ለርሷ ባሪያ መሆን ትክክል አይደለም፡

ወርቅህን በብረት አልማዝክን በጠጠር፡
የምትለውጥ እርኩስ ሆነህ አትፈጠር፡
ነቄ ሁን እባክህ በህይወትህ ሰጠር፡

ለስልጣን ለዝና ሁሌ ከመጓጓት፡
ዋጋ ክፈሉና ሐቅን ከፍ አድርጓት፡
ከወተት በስተፊት አይገኝም አጓት፡

ሁለት ፊት አታሳይ ወዳጄ ልምከርህ፡
የእንሰሳ ሳይሆን የሰው ልብ ይኑርህ፡
የምትኖረው ህይወት ይሁን ንግግርህ፡

ነፍስህን አጥግበህ ስጋህ ግን ተርባ፡
ውስጥህ ሰላም ሰፍኖ ፈክተህ እንደ አበባ፡
ሰው ሰው እየሸተትክ ከመቃብር ግባ!!!

🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀🌸🥀
🟡 በዩንቨርስቲው ቅጥር ግቢ ውስጥ የህክምና አስተማሪ ነው። ከእጁ የማትለይ፣ ሲበዛ የሚወዳት ሰዓት አለችው። መልኳም ሆነ ይዘቷ የሴት ነው። ሊያስተምር እጁን ሲያወራጭ ተማሪዎች ይጠቋቆሙበታል። ከዕለታት በአንዱ ቀን ታዲያ በአደጋ ምክንያት የተለየችው የልጁ ሰዓት መሆኑን ከጓደኛው አንደበት ሰሙ። ለእሷ ካለው የገዘፈ ውዴታ የተነሳ ሰዓቷን ከእጁ ሊያወልቅ አልተቻለውም።

(ሊያወሩላቸው የሚደክሙ፣ ሊገልጿቸው የሚከብዱ ንፁህ ልቦች)

🟡 ረጅም ርቀት በእግሯ ከአባቷ ጋር ተጉዛ የምትወደውን አይስክሬም አባት ገዝቶ ሲሰጣት በግንባሯ ሱጁድ ወረደች። አይስክሬም ሻጩ በአግራሞት እየተመለከታት እስክትነሳ ጠብቆ ጠየቃት። ሱጁድ የወረድሽበት ምክንያት ምንድነው?! አላት። እናቷ ስትደሰት እንዲህ እንደምታረግ ነገረችው::

(የመልካም ተርቢያ ውጤት ይሉሀል ይህ ነው)

🟡 በአረጋውያን መጦርያ ማዕከል የምትገኘውን ሚስታቸውን ለመዘየር ኪሎ ሜትሮችን አቆራርጠው እርሷ ዘንድ ይሰየማሉ። ከጎኗ ተቀምጠው የሆድ ሆዳቸውን ያወጋሉ። ከአስር ዓመታት በፊት የማስታወስ ችሎታዋን አጥታ ባሏንም ሆነ ልጆቿን አታስታውስም ነበርና
"እየተመላለሱ ለምን ይለፋሉ?! ማንነትዎን ለማታውቅ ሴት ስለምን ብለው ይቸገራሉ?!" በማለት ጠየቋቸው። አዛውንቱም ፈገግ አሉና "እኔ ግን ባለቤቴ የህይወት አጋሬና ጓደኛዬ እንደሆነች አውቃለሁ" በማለት መለሱ።

(ከዚህ ወዲያ ስለየትኛው ንፁህ ፍቅር ነው የምታወሩት)

🟡 በቤትህና በሥራ ቦታህ መካከል ያለው ርቀት ምን ያህል ነው ተብሎ ተጠየቀ
"በመኪና ከሆነ 500 ተስቢህና ተህሊል። በእግሬ ከሆነ ደግሞ 1200 ተህሚድና ኢስቲግፋር የሚያዘክር ወቅት ያደርሰኛል" ሲል መለሰ።

(አላህን ሳያስታውሱ የማያመሹ ልቦች)

🟡  አንድ አዛውንት ተጠየቁ "ንፁህ የመጠጥ ውሀ በቤትዎ ኖሮ ለምን ወቅፍ የተደረገ የመስጂድን የቧንቧ ውሃ መጎንጨት ፈለጉ?!" ተባሉ።
"ለመስጂዱ የወቀፉት ሰዎች አጅር ያገኙ ዘንድ" ሲሉ መለሱ።

(መልካም ነገርን ለራሳቸው እንደሚወዱት ለሌሎችም የሚወዱ ንፁህ ልቦች)

የምተርክላችሁ ስለ ቅን ልቦች
የማወጋችሁም ስለ እነርሱ ነው
{وَعَدَ اللَّهُ الْمُؤْمِنِينَ وَالْمُؤْمِنَاتِ جَنَّاتٍ تَجْرِي مِنْ تَحْتِهَا الْأَنْهَارُ خَالِدِينَ فِيهَا وَمَسَاكِنَ طَيِّبَةً فِي جَنَّاتِ عَدْنٍ وَرِضْوَانٌ مِنَ اللَّهِ أَكْبَرُ ذَلِكَ هُوَ الْفَوْزُ الْعَظِيمُ}
أصبحنا وأصبح الملك لله والحمد لله ، لا إله إلا الله وحده لا شريك له ، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير . ربي أسألك خير ما في هذا اليوم وخير ما بعده . وأعوذ بك من شر ما في هذا اليوم وشر ما بعده ربي أعوذ بك من الكسل وسوء الكبر ، ربي أعوذ بك من عذاب في النار وعذاب في القبر
{ أَوَلَا یَرَوۡنَ أَنَّهُمۡ یُفۡتَنُونَ فِی كُلِّ عَامࣲ مَّرَّةً أَوۡ مَرَّتَیۡنِ ثُمَّ لَا یَتُوبُونَ وَلَا هُمۡ یَذَّكَّرُونَ }

በየዓመቱ አንድ ወይም ሁለት ጊዜ እነርሱ የሚሞከሩ መኾናቸውን አያዩምን ከዚያም አይጸጸቱምን እነሱም አይገሰጹምን
[Surah At-Tawbah: 126]
{ إِنَّ ٱلَّذِینَ لَا یَرۡجُونَ لِقَاۤءَنَا وَرَضُوا۟ بِٱلۡحَیَوٰةِ ٱلدُّنۡیَا وَٱطۡمَأَنُّوا۟ بِهَا وَٱلَّذِینَ هُمۡ عَنۡ ءَایَـٰتِنَا غَـٰفِلُونَ }
እነዚያ መገናኘታችንን የማይፈሩ ቅርቢቱንም ሕይወት የወደዱ በእሷም የረኩ እነዚያም እነሱ ከአንቀጾቻችን ዘንጊዎች የኾኑ፡፡

{ أُو۟لَـٰۤىِٕكَ مَأۡوَىٰهُمُ ٱلنَّارُ بِمَا كَانُوا۟ یَكۡسِبُونَ }

እነዚያ ይሠሩት በነበሩት ምክንያት መኖሪያቸው በእሳት ውስጥ ነው፡፡

{ إِنَّ ٱلَّذِینَ ءَامَنُوا۟ وَعَمِلُوا۟ ٱلصَّـٰلِحَـٰتِ یَهۡدِیهِمۡ رَبُّهُم بِإِیمَـٰنِهِمۡۖ تَجۡرِی مِن تَحۡتِهِمُ ٱلۡأَنۡهَـٰرُ فِی جَنَّـٰتِ ٱلنَّعِیمِ }
እነዚያ ያመኑና መልካም ሥራዎችን የሠሩ ጌታቸው በእምነታቸው ምክንያት (የገነትን መንገድ) ይመራቸዋል፡፡ ከሥራቸው ወንዞች ይፈስሳሉ፡፡ በመጠቀሚያ ገነቶች ውስጥ ይኖራሉ፡፡

{ دَعۡوَىٰهُمۡ فِیهَا سُبۡحَـٰنَكَ ٱللَّهُمَّ وَتَحِیَّتُهُمۡ فِیهَا سَلَـٰمࣱۚ وَءَاخِرُ دَعۡوَاهُمۡ أَنِ ٱلۡحَمۡدُ لِلَّهِ رَبِّ ٱلۡعَـٰلَمِینَ }
በእርሷም ውስጥ ጸሎታቸው ጌታችን ሆይ! ጥራት ይገባህ (ማለት) ነው፡፡ በእርሷ ውስጥ መከባበሪያቸውም ሰላም መባባል ነው፤ የመጨረሻ ጸሎታቸውም ምስጋና ለዓለማት ጌታ ይሁን (ማለት) ነው፡፡


[Surah Yūnus: 7-10]
ለሴቶች!
~
ሰበብ እየፈለጉ ያለ ቤተሰብ እውቅና በየመንደሩ የድብቅ ኒካሕ ከሚያስሩ ጎረምሶች፣ ደረሳዎች፣ የዱዓት ጭንብል ካጠለቁ ዱርየዎች ተጠንቀቁ! ጋብቻችሁም አይሰምሩም። መለያየታችሁም አያምርም። የአላህ መልእክተኛ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም እንዲህ ብለዋል፦
«لا نِكَاحَ إِلّا بِوَليٍّ»
"ያለ ወሊይ ኒካሕ የለም።"

አልባኒይ ሶሒሕ ብለውታል። [ሶሒሕ ኢብኒ ማጀህ፡ 1537]

በሆነ ሸሪዐዊ ምክንያት አባትን መጠቀም ካልተቻለ ቅደም ተከተሉን ጠብቆ ሌሎችን መጠቀም እንጂ ሰበብ እየፈለጉ ከወሊይ እውቅና ውጭ የድብቅ ጋብቻ መፈፀም ተቀባይነት የለውም። በዲንና በደዕዋ ስም ስማቸውን ከተከሉ፣ ታማኝነትን ካገኙ በኋላ ብዙ ጥፋት የሚፈፅሙ አሉ።
{ ۞ وَسَارِعُوۤا۟ إِلَىٰ مَغۡفِرَةࣲ مِّن رَّبِّكُمۡ وَجَنَّةٍ عَرۡضُهَا ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تُ وَٱلۡأَرۡضُ أُعِدَّتۡ لِلۡمُتَّقِینَ }
ከጌታችሁ ወደ ኾነችም ምሕረትና ስፋትዋ እንደ ሰማያትና ምድር ወደ ኾነች ገነት አላህን ለሚፈሩ የተዘጋጀች ስትኾን ተቻኮሉ፡፡

{ ٱلَّذِینَ یُنفِقُونَ فِی ٱلسَّرَّاۤءِ وَٱلضَّرَّاۤءِ وَٱلۡكَـٰظِمِینَ ٱلۡغَیۡظَ وَٱلۡعَافِینَ عَنِ ٱلنَّاسِۗ وَٱللَّهُ یُحِبُّ ٱلۡمُحۡسِنِینَ }
ለእነዚያ በድሎትም ኾነ በችግር ለሚለግሱት፣ ቁጭትንም ገቺዎች ከሰዎችም ይቅርታ አድራጊዎች ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡ አላህም በጎ ሠሪዎችን ይወዳል፡፡

وَٱلَّذِینَ إِذَا فَعَلُوا۟ فَـٰحِشَةً أَوۡ ظَلَمُوۤا۟ أَنفُسَهُمۡ ذَكَرُوا۟ ٱللَّهَ فَٱسۡتَغۡفَرُوا۟ لِذُنُوبِهِمۡ وَمَن یَغۡفِرُ ٱلذُّنُوبَ إِلَّا ٱللَّهُ وَلَمۡ یُصِرُّوا۟ عَلَىٰ مَا فَعَلُوا۟ وَهُمۡ یَعۡلَمُونَ }
ለእነዚያም መጥፎ ሥራን በሠሩ ወይም ነፍሶቻቸውን በበደሉ ጊዜ አላህን የሚያስታውሱና ለኀጢአቶቻቸው ምሕረትን የሚለምኑ ለኾኑት ከአላህም ሌላ ኀጢአቶችን የሚምር አንድም የለ፡፡ (በስሕተት) በሠሩትም ላይ እነርሱ የሚያውቁ ሲኾኑ የማይዘወትሩ ለኾኑት (ተደግሳለች)፡፡

{ أُو۟لَـٰۤىِٕكَ جَزَاۤؤُهُم مَّغۡفِرَةࣱ مِّن رَّبِّهِمۡ وَجَنَّـٰتࣱ تَجۡرِی مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَـٰرُ خَـٰلِدِینَ فِیهَاۚ وَنِعۡمَ أَجۡرُ ٱلۡعَـٰمِلِینَ }
እነዚያ ምንዳቸው ከጌታቸው ምሕረትና በውስጣቸው ዘውታሪዎች ሲኾኑ በሥሮቻቸው ወንዞች የሚፈሱባቸው ገነቶችም ናቸው፡፡ የሠሪዎችም ምንዳ (ገነት) ምንኛ አማረች!፡፡


[Surah Āli-ʿImrān: 133-136]
ሰለዋት እናብዛ‼️
🌴🌴🌴

ምን ያህሎቻችን ነን ጁምዓ ተጠባብቀን በረሱል [ሰለላሁ ዐለይሂ ወሰለም] ላይ ሰለዋት የምናወርደው
ለምንድን ነው ከዚህ ትልቅ ስራ የምንዘናጋው

📚እስኪ አላህና መልዕክተኛውን ምን እንደ ሚሉን እንመልከት
👇👇👇

🌴💥🕋🌴💥🕋

قال الله تعالى ﴿إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلّونَ عَلَى النَّبِيِّ يا أَيُّهَا الَّذينَ آمَنوا صَلّوا عَلَيهِ وَسَلِّموا تَسليمًا﴾
[الأحزاب: ٥٦]
አላህ እንዲህ ይላል፦
{አላህና መላዒካዎቹ በነብዩ ላይ ሰለዋት ያወርዳሉ; እናንተ ያመናችሁ ሆይ በእሱ (በነብዩ) ላይ ሰለዋትና ሰላምን አውርዱ}


📖የአላህ መልዕክተኛም እንዲህ ይሉናል👇👇

"أكثروا الصلاة علي يوم الجمعة وليلة الجمعة فمن صلى علي صلاة صلى الله عليه عشرا "
و حـسـنه الألباني في السلسلة الصحيحة 1407
{ጁምዓ ቀንና ጁምዓ ሌሊት በእኔ ላይ ሰለዋት አብዙ። በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው በእሱ ላይ አላህ አስር ጊዜ ሰለዋት ያወርድበታል}

"من صلى علي مرة كتب الله له بها عشر حسنات"
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة (٣٣٥٩)
{በእኔ ላይ አንድ ጊዜ ሰለዋት ያወረደ ሰው አላህ ለእሱ በዚህ ምክንያት አስር ምንዳ ይፅፍለታል}

" من صلى علي من أمتي صلاة مخلصا من قلبه صلى الله عليه بها عشر صلوات ورفعه بها عشر درجات وكتب له بها عشر حسنات ومحا عنه عشر سيئات "
وصـحــحه العلامة الألباني رحمه الله في السلسلة الصحيحة ( ٣٣٦٠)
{ከኡመቶቼ ውስጥ ከቀልቡ ጥርት አድርጎ በእኔ ላይ ሰለዋት ያወረደ የሆነ ሰው; አላህ በእሷ ምክንያት አስር ሰለዋት ያወርድበታል፣ አስር ደረጃም ከፍ ያደርግለታል፣ አስር ምንዳም ይፅፍለታል፣ አስር ወንጀልም ይሰርዝለታል}

" من صلى علي واحدة صلى الله عليه عشرا "
رواه أبو داود في سننه (١٥٣٠)
وصححه الألباني رحمه الله
{በእኔ ላይ አንድ ሰለዋት ያወረደ በእሱ ላይ አላህ አስር ያወርድበታል}

🌴🌱🌴🌱🌴🌱
"اللهم صل على محمد وعلى آل محمد كما صليت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد، اللهم بارك على محمد وعلى آل محمد كما باركت على إبراهيم وعلى آل إبراهيم إنك حميد مجيد"


"ወደ መልካም ያመላከተ እንደ ሰሪው ነው"
{ كُلُّ نَفۡسࣲ ذَاۤىِٕقَةُ ٱلۡمَوۡتِۗ وَإِنَّمَا تُوَفَّوۡنَ أُجُورَكُمۡ یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۖ فَمَن زُحۡزِحَ عَنِ ٱلنَّارِ وَأُدۡخِلَ ٱلۡجَنَّةَ فَقَدۡ فَازَۗ وَمَا ٱلۡحَیَوٰةُ ٱلدُّنۡیَاۤ إِلَّا مَتَـٰعُ ٱلۡغُرُورِ }
ነፍስ ሁሉ ሞትን ቀማሽ ናት፡፡ ምንዳዎቻችሁንም የምትሞሉት በትንሣኤ ቀን ብቻ ነው፡፡ ከእሳትም የተራቀና ገነትን የተገባ ሰው በእርግጥ ምኞቱን አገኘ፡፡ ቅርቢቱም ሕይወት የመታለያ መሳሪያ እንጅ ሌላ አይደለችም፡፡


[Surah Āli-ʿImrān: 185]
{ وَلِلَّهِ مُلۡكُ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِۗ وَٱللَّهُ عَلَىٰ كُلِّ شَیۡءࣲ قَدِیرٌ }
የሰማያትና የምድር ንግሥና ለአላህ ብቻ ነው፡፡ አላህም በነገሩ ሁሉ ላይ ቻይ ነው፡፡

{ إِنَّ فِی خَلۡقِ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ وَٱخۡتِلَـٰفِ ٱلَّیۡلِ وَٱلنَّهَارِ لَـَٔایَـٰتࣲ لِّأُو۟لِی ٱلۡأَلۡبَـٰبِ }
ሰማያትንና ምድርን በመፍጠር ሌሊትና ቀንንም በመተካካት ለባለ አእምሮዎች በእርግጥ ምልክቶች አሉ፡፡

{ ٱلَّذِینَ یَذۡكُرُونَ ٱللَّهَ قِیَـٰمࣰا وَقُعُودࣰا وَعَلَىٰ جُنُوبِهِمۡ وَیَتَفَكَّرُونَ فِی خَلۡقِ ٱلسَّمَـٰوَ ٰ⁠تِ وَٱلۡأَرۡضِ رَبَّنَا مَا خَلَقۡتَ هَـٰذَا بَـٰطِلࣰا سُبۡحَـٰنَكَ فَقِنَا عَذَابَ ٱلنَّارِ }
(እነርሱም) እነዚያ ቆመው፣ ተቀምጠውም፣ በጎኖቻቸው ተጋድመውም አላህን የሚያወሱ በሰማያትና በምድር አፈጣጠርም የሚያስተነትኑ፡- «ጌታችን ሆይ! ይኸን በከንቱ አልፈጠርከውም፤ ጥራት ይገባህ፤ ከእሳትም ቅጣት ጠብቀን» የሚሉ ናቸው፡፡

{ رَبَّنَاۤ إِنَّكَ مَن تُدۡخِلِ ٱلنَّارَ فَقَدۡ أَخۡزَیۡتَهُۥۖ وَمَا لِلظَّـٰلِمِینَ مِنۡ أَنصَارࣲ }
«ጌታችን ሆይ! አንተ እሳት የምታገባውን ሰው በእርግጥ አዋረድከው፤ ለበደለኞችም ምንም ረዳቶች የሉዋቸውም፡፡»

{ رَّبَّنَاۤ إِنَّنَا سَمِعۡنَا مُنَادِیࣰا یُنَادِی لِلۡإِیمَـٰنِ أَنۡ ءَامِنُوا۟ بِرَبِّكُمۡ فَـَٔامَنَّاۚ رَبَّنَا فَٱغۡفِرۡ لَنَا ذُنُوبَنَا وَكَفِّرۡ عَنَّا سَیِّـَٔاتِنَا وَتَوَفَّنَا مَعَ ٱلۡأَبۡرَارِ }
«ጌታችን ሆይ! እኛ በጌታችሁ እመኑ በማለት ወደ እምነት የሚጠራን ጠሪ ሰማን፡፡ አመንም፡፡ ጌታችን ሆይ! ኃጢአቶቻችንንም ለኛ ማር፡፡ ክፉ ሥራዎቻችንንም ከኛ አብስ፡፡ ከንጹሖቹም ሰዎች ጋር ግደለን፤»

{ رَبَّنَا وَءَاتِنَا مَا وَعَدتَّنَا عَلَىٰ رُسُلِكَ وَلَا تُخۡزِنَا یَوۡمَ ٱلۡقِیَـٰمَةِۖ إِنَّكَ لَا تُخۡلِفُ ٱلۡمِیعَادَ }
«ጌታችን ሆይ! በመልክተኞችህም ላይ ተስፋ ቃል ያደረግክልንን ስጠን፡፡ በትንሣኤ ቀንም አታዋርደን፡፡ አንተ ቀጠሮን አታፈርስምና» (የሚሉ ናቸው)፡፡

{ فَٱسۡتَجَابَ لَهُمۡ رَبُّهُمۡ أَنِّی لَاۤ أُضِیعُ عَمَلَ عَـٰمِلࣲ مِّنكُم مِّن ذَكَرٍ أَوۡ أُنثَىٰۖ بَعۡضُكُم مِّنۢ بَعۡضࣲۖ فَٱلَّذِینَ هَاجَرُوا۟ وَأُخۡرِجُوا۟ مِن دِیَـٰرِهِمۡ وَأُوذُوا۟ فِی سَبِیلِی وَقَـٰتَلُوا۟ وَقُتِلُوا۟ لَأُكَفِّرَنَّ عَنۡهُمۡ سَیِّـَٔاتِهِمۡ وَلَأُدۡخِلَنَّهُمۡ جَنَّـٰتࣲ تَجۡرِی مِن تَحۡتِهَا ٱلۡأَنۡهَـٰرُ ثَوَابࣰا مِّنۡ عِندِ ٱللَّهِۚ وَٱللَّهُ عِندَهُۥ حُسۡنُ ٱلثَّوَابِ }
ጌታቸውም «እኔ ከእናንተ ከወንድ ወይም ከሴት የሠሪን ሥራ አላጠፋም፡፡ ከፊላችሁ ከከፊሉ ነው፤ በማለት ለነርሱ ልመናቸውን ተቀበለ፡፡ እነዚያም የተሰደዱ ከአገሮቻቸውም የተባረሩ በመንገዴም የተጠቁ የተጋደሉም የተገደሉም ክፉ ሥራዎቻቸውን ከእነርሱ በእርግጥ አብሳለሁ፡፡ በሥሮቻቸውም ወንዞች የሚፈሱባቸውን ገነቶች በእርግጥ አገባቸዋለሁ፡፡ ከአላህ ዘንድ የኾነን ምንዳ (ይመነዳሉ)፡፡ አላህም እርሱ ዘንድ መልካም ምንዳ አልለ፡፡ »


[Surah Āli-ʿImrān: 189-195]
የጓደኛው ቤት ደጃፍ እንደቆመ ሲፈራ ሲቸር እያመነታ በሩን በቀስታ አንኳኳ። ተከፈተለት አይኑን ከመሬቱ እንደተከለ ለጓደኛው እንዲህ አለ፡-
"ብዙ ጊዜ የሆነኝ ዕዳ ሰላም ነሳኝ ጧት ማታ አበዳሪዬ ሲጠይቀኝ የምከፍለው ገንዘብ አጣሁ። የማደርገው ግራ ቢገባኝ ችግሬን ላካፍልህ ወዳንተ መጣሁ"

ወደ ውስጥ ተመለሰና አራት መቶ ዲርሀም ቆጥሮ ሰጠው። በደስታ ሲፍለቀለቅ ተሰናብቶት እያለቀሰ ወደቤት ዘለቀ።

ይህን ሁሉ ተደብቃ ስትከታተል የነበረችው ሚስት የባሏን ለቅሶ ስታይ "ለምን ታለቅሳለህ? ብሩን መስጠት ከብዶህ ከሆነ ይቅርታ የለኝም ብለህ ምክኒያት ፈጥረህ አትመልሰውም ነበር?" አለችው
"ያስለቀሰኝስ ያለበትን ሁኔታ ሳልከታተል በመቅረቴ ተቸግሮ እስኪጠይቀኝ ድረስ ቸልተኛ መሆኔ ነው" አላት።

ኡኹዋ!!!
የሐጅ ትዕይንት፣ ጥበብና አስተምህሮው

ሐጅ የትንሳኤን ቀን ክስተት በመጠኑም ቢሆን በዐይናችን ለመቃኘትና  እንዲሰማን ለማድረግ ትልቅ የዓለማችን ትዕይንት ነው፡፡ የቂያማ ቀን የሚኖረው በአንድ ቦታ ላይ መሰባሰብ፣ መጨናነቅ፣ ዕርቃን መሆንና የመሳሰሉትን ክስተቶች ያስተውሰናል፡፡ ያኔ በነቢዩ ኢብራሂም ዐ.ሰ. ለሐጅ የተደረገው ጥሪ ለቂያም ቀን መቅቀስቀስ በቀንዱ ዉስጥ ከሚነፋው ጥሪ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ሁሉም በአላህ ፍራቻ ስሜት ዉስጥ ሆኖ፣ እዝነቱንም በእጅጉ ከጅሎ፣ ምህረቱን፣ ይቅርታውንና ምንዳውን አስቦ ይቀርባል፡፡

ሌላው የሐጅ አስተምህሮ በአላህ መንገድ መታገልን የጂሃድን ውጣ ውረድ እንድናስታውስ ማድረጉ ነው፡፡ በሐጅ አንድ አማኝ ትግልን፣ ብርታትን፣ ድካምና ትዕግስትን መማሩ ነው፡፡ ዒባዳውን ለማከናወን ጭምር ውጣ ውረድን፣ እንግልትን፣ ችግርና መከራ መሸከምን ይሠለጥናል፡፡ ከዓለም የተለያየ አካባቢ የተውጣጡ፣ በተለያየ የዕውቀትና የኑሮ ደረጃ ላይ ከሚገኙ ከተለያዩ ሰዎች ባህሪ ጋር እንዴት ሰክኖ እና ተረጋግቶ መኖር እንደሚገባ ልምድ ይገኝበታል፡፡

 የሐጅ ሥርዓት ብዙው የሚፈፀመው እልም ባለ በረሃ ሜዳ ላይ ነው፡፡ ጥላና አረንጓዴ ነገር በሞላው ግቢውና ቤቱ ዉስጥ አይደለም፡፡  የአየር ፀባዩ ከባድ ነው፡፡ ሐሩሩ ትንፋሽ ያሳጥራል፡፡ ግፍያውና መጨናነቁ ሶብር ይፈትናል፡፡ ሐጅ እንግዳነትና መንገደኝነት ነው፡፡  እንደፈለጉት ዕረፍትና የመዝናናት ዕድል የሚገኝ አይደለም፡፡ በዚህ ሁሉ መካከል ነው አላህ ዘንድ ተቀባይነት ያለው የተሟላ የሐጅ ሥራ የሚፈለገው፡፡

ሌላው ሐጅ ቅንነትንና አምልኮን ለአላህ ብቻ ማጥራትን ያስተምራል፡፡ በዚያ በረሃ ዉስጥ የአማኝ መመኪያው እና መጠጊያው አላህ (ሱ.ወ.) ብቻ ነው፡፡

ሐጅ በባሪያው እና በአላህ መካከል የሚኖረውን ግንኙነት ያጠናክራል፡፡ ምክንያቱም ሐጃጆች የአላህ እንግዶች ሆነው በርሱ ቤት አርፈዋልና፡፡

ሌላው ጥበቡ ሐጅ በሙስሊሞች መካከል የሚኖረውን ግንኙነት ለማጠናከር ይረዳል፡፡ አላስተዋልንም እንጂ አላህ (ሱ.ወ.) በሐጅ የሚያስተላልፈው መልዕክት ያለ ይመስላል፡፡ መበታተን፣ መራራቅ፣ ጀርባ መሠጣጠት ከናንተ አንድ አላህን ከምታመልኩ ባሮች አይጠበቅም የሚል መልዕክት፡፡

ሌላው ለአስተውሎት የሚገባው ነጥብ - ሑጃጆች የሐጅ ተግባር ለመፈፀም ሲሄዱ የተለመደውን የአኗኗር ዘይቤያቸውን ሁሉ እርግፍ አድርገው በመተው በተለየ የአለባበስ ሥርዓት (የኢሕራም ልብስ) ራሳቸውን ይቀይራሉ፡፡ ይህ ልብስ የሚያስታውሳቸው ዕለተ ሞታቸው ሲደርስና ጌታቸው ጋር ለመገናኘት ወደ መቃብሮቻቸው ሲወሰዱ የሚጠቀለሉበት የከፈን ጨርቅ ነው፡፡

ሞት እንደሚታወቀው ሁሉንም በተራ በተመሳሳይ ሁኔታ ወደ አፈር እንደሚመልሰው ሁሉ የኢሕራም ልብስም የሀብት፣ የክብር፣ የሥልጣንና የዘር ልዩነቶችን አስወግዶ ሁሉንም ሰው አንድ ዓይነት ያደርገዋል፡፡ እነሆ እዚያ የተገኘ ሁሉ ንጹሕና ተራ ባሪያ በመሆን የሐጅ ሥርዓቱን ይፈጽማል፡፡ ይህን በመሰለ የቅድስናና የንሰሀ ሁኔታ የሚጓዝ ተጓዥ በዚያ አካባቢ የሚገኝን ማንኛውም ሕይወት ያለው ፍጡር መጉዳት ይቅርና ጥፍርንና ጸጉርን መቁረጥና መነቃቀል ጭምር የተከለከለ ነው፡፡

በሐጅ ወቅት በሰዎች መካከል የሚኖር ልዩነት ሁሉ ይከስማል፡፡ የሰው ልጆች እኩልነት በተግባር ይሰፍናል፡፡ ሥልጣን፣ ዝናና ክብር ያላቸው ከዝቅተኛና  ከማይታወቁ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር እኩል ይሆናሉ፡፡ ሁሉም የአላህን ምሕረት ከመከጀል ውጭ ሌላ ሐሳብ የላቸውም፡፡ ትልቁ ግባቸው የአል-ረሕማንን ውዴታና ጀነት ነው፡፡ እንዱ ሌላውን በአላህ ፍራቻ ካልሆነ በስተቀር በምንም ሊበልጥ አይችልም፡፡

ሐጅ አድራጊ የገንዘቡንና የጤነኛ አካሉን ምስጋና (ሹክር) እንዲያደርስ የሐጅ ክንውን አጋጣሚውን ይፈጥርለታል፡፡ እነኝህ ሁለት ፀጋዎች የሰው ልጅ በዚህች ዓለም ከሚያገኟቸው ፀጋዎች ሁሉ ዋንኞቹ ናቸው፡፡

ሐጅ ለአላህ የመዋረድ፣ የመተናነስና የታዛዥነት ስሜት የሚጎላበት ክንውን ነው፡፡ ምክንያቱም ሐጅ አድራጊ፣ ነቢዩ ኢብራህም የአላህን ትእዛዝ ለመፈፀም ሲሉ ቤተሰቦቻቸውን በባዶ በረሃ ላይ ጥለው የመሄዳቸውን ታሪክ እንዲያስታውስ አጋጣሚውን ይፈጥርለታልና፡፡
በአላህ እምላለሁ ዑመር ቢያያቸው በንዴት እንደ አንበሳ እያገሳ በላያቸው ላይ በሰፈረባቸው "አላሁ አክበር" በሚል መፈክር ግዙፍ ሰራዊትን ባነቃነቀ ከስፍራቸው።

ሰላሐዲንስ ይህን ቢመለከት ምን ሊውጣቸው? ሠይፉን እያንቀለቀለ ሰልፉን እየተቀላቀለ እየደለቀ አጥንታቸውን ባደቀቀ።

አቅሷ ሆይ ይቅር በይን!
ውርደትን በተከናነቡ ገዥዎች መሐል ነው ኑሯችን። በምቾት ያጌጠ መቀመጫ ዙፋናቸውን ማጣት የሚፈሩ ግብዞች መሐል ሆነን ምንም ማድረግ አልተቻለንም። አዝነናል የሚል መግለጫ እንኳ ለመስጠት አልተንቀሳቀሱም። በምላሳችን እናወግዛለን ለማለትም አልደፈሩም።
ተበን ለሁም
ወወይሉን ሊመን ዋላሁም
HTML Embed Code:
2025/06/24 20:30:37
Back to Top