TG Telegram Group Link
Channel: Al-risaala tube
Back to Bottom
የሰዓት መቁጠሪያ ሲበላሽ
ጊዜ እንደማይቆመው
"ሁሉ" ሁኔታዎች ሲበላሹብክ
አንተም ዝም ብለክ አትቁም
   #ሰበቡን____አድርስ::
@risaalaatube
🍃๑﹏﹏๑﹏﹏๑﹏﹏๑﹏﹏๑🍃
       
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
😍😍
Utuba hiree muslimaa
Hundee jijjiirama uumaa
Talaallii ciraa dinagdee
Numatu furmaata cimaa...
Wal-cimsuu tibbu waloo
Hawaasa jabaa ijaaruu
Hirkoo dhugaan gumboobuu
Ol koru jedhee  baraaruu
https://youtu.be/OX_VAUCNRYI
@risaalaatube
ከሂጅራ ባንክ የሞባይል ባንኪንግ በ*827# ወደ ቴሌብር ገንዘብ የማስተላለፍ አገልግሎት መጀመሩን በደስታ እንገልጻለን!

ቴሌብር - ቀላል፣ ፈጣን፣ ምቹ እና አስተማማኝ!
Deebisaa?
መልሱት?
Anonymous Quiz
0%
3
13%
4
13%
17
38%
25
25%
2
13%
5
❤️……
የስልካቸውን የጥሪ ድምፅ
ስለሚወዱት ሲደወልላቸው ዘግይተው
የሚያነሱ ሰዎች አጋጥመዉኛል።
አላህም ዱዓህን በቶሎ
የማይመልስልህ ያንተን ጥሪ ደጋግሞ
መስማት ፈልጎ እንደሆነ አስብ !!
በጣም ወደምትፈልገው ሰው ስትደውል
ስልኩ ዝግ ቢሆንብህና ጥሪ ባይቀበልም
... ኔትዎርክ ቢያስቸግርህም ተስፋ
ባለመቁረጥ ደጋግመህ ትሞክራለህ!
እንደዚሁ ሁሉም ከምንም ከማንም በላይ
ለሚያስፈልግህ ጌታህ ተደጋጋሚ የጥሪ
ሙከራህን አታቁም
ምክነያቱም አላህ ጠያቂዎችን ይወዳል
ተስፋ ቆራጮች ተነሱ ሳትሰላቹ ደጋግማችሁ ለምኑት እሱ ጠያቂዎችን
አይመልስምና።
•Al-risaala tube»
ወላሂ! ትልቅ ሱናህ!!!
ያላፈዝነው እናፍዘው፡፡ ያፈዝነው እንተግብረው፡፡
5 የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚባል ዋጋው የገዘፈ አንድ ትልቅ
ዚክር!!
[ ﺳﺒْﺤﺎﻧَﻚ ﺍﻟﻠَّﻬُﻢّ ﻭﺑﺤَﻤْﺪﻙَ ﺃﺷْﻬﺪُ ﺃﻥْ ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺃﻧْﺖ
ﺃﺳْﺘﻐْﻔِﺮﻙَ ﻭَﺃﺗَﻮﺏُ ﺇﻟﻴْﻚَ ]
[ሱብሓነከልሏሁመ ወቢሐምዲከ አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢላ አንተ
አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይከ]
1. ከዚክር ቆይታ በኋላ ይህንን ያለ ልክ እንደ ማሸጊያ፣ ጥሩ
መቋጫ ይሆነዋል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 81]
2. ከዛዛታና ቀልድ በኋላ ይህንን ያለ ከቦታው የተፈፀሙ
ወንጀሎቸን አላህ ያብስለታል፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 2651]
3. ከውዱእ በኋላ ይህንን ዚክር ያለ እስከ እለተ ቂያማ ምንዳው
ባስተማማኝ መቀመጫ ታሽጎ ይቀመጥለታል፡፡ [ሶሒሑትተርጊብ፡
225]
4. ይህንኑ ዚክር ነብዩ ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም ከሶላት በኋላም
ይሉት ነበር፡፡ [አስሶሒሐህ፡ 3164]
5. ቁርኣን ከቀሩ በኋላም ይሉት ነበር ሶለላሁ ዐለይሂ ወሰለም፡፡
[ነሳኢይ]
እንዲህ አይነት ትልቅ ሀብት ይዘው ዝም አይበሉ፡፡ ለወዳጅ
ዘመዶችዎ ያድርሱ፡፡ ተጨማሪ አጅረዎን ይፈሱ

#SHARE
https://hottg.com/risaalaatube
https://hottg.com/risaalaatube
Al-risaala tube pinned «ወላሂ! ትልቅ ሱናህ!!! ያላፈዝነው እናፍዘው፡፡ ያፈዝነው እንተግብረው፡፡ 5 የተለያዩ ቦታዎች ላይ የሚባል ዋጋው የገዘፈ አንድ ትልቅ ዚክር!! [ ﺳﺒْﺤﺎﻧَﻚ ﺍﻟﻠَّﻬُﻢّ ﻭﺑﺤَﻤْﺪﻙَ ﺃﺷْﻬﺪُ ﺃﻥْ ﻻ ﺇﻟﻪ ﺇﻻ ﺃﻧْﺖ ﺃﺳْﺘﻐْﻔِﺮﻙَ ﻭَﺃﺗَﻮﺏُ ﺇﻟﻴْﻚَ ] [ሱብሓነከልሏሁመ ወቢሐምዲከ አሽሀዱ አንላኢላሀ ኢላ አንተ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይከ] 1. ከዚክር ቆይታ በኋላ ይህንን ያለ…»
በሀገረ አሜሪካ በሚገኝ ትልቅ ሆስፒታል ውስጥ ጫጫታ ነግሷል። ሁለት እናቶች በተመሳሳይ ሰዓት በሰላም ተገላግለው "ሴቷ ያንቺ ናት እኔ የወለድኩት ወንድ ነው" እየተባባሉ ሲጨቃጨቁ ሆስፒታሉ በጩኸታቸው ተናውጧል።

ሀኪሞቹ ልጆቹ ተምታቶባቸው ግራ ተጋብተዋል። ማንኛዋ ሴት የትኛዋስ ወንድ እንደወለደች ማወቅ ተስኗቸው መፍትሄ ሊያበጁ ከመሐል ገብተዋል።

  በዲ ኤን ኤ ምርመራ ለማረጋገጥ ውጤት መጠባበቅ ጀመሩ። አሁንም ግራ አጋቢ ነገር ተፈጠረ። ተቀራራቢ ውጤት በመታየቱ ጉዳዩ ከአቅማችን በላይ ሆኗል በማለት ለሆስፒታሉ ሃላፊዎች አሳወቁ።

ኃላፊዎቹም ረጅም ሰዓት ከተወያዩ በኋላ ይህንን ችግር መፍታት የሚችሉት ሙስሊም ዓሊሞች ናቸው በሚል ከመግባባት ላይ ደረሱ። ወደ አንድ ሙስሊም ሊቃውንትም አቀኑ። የተፈጠውን ሁሉ በዝርዝር አስረዱ። ምናልባት በሃይማኖታችሁ መፍትሄ ካለው ብለን እዚህ መጣን አሉ።

እሱም ክስተቱን አዳምጦ እንዳበቃ "መፍትሄው በጣም ቀላል ነው" አለ።ዶክተሮቹ እርስ በእርስ ተያዩ ንግግሩን ቀጠከ "አላህ በልጆቻችሁ ያዛችኋል፡፡

ለወንዱ የሁለት ሴቶች ድርሻ ብጤ አለው" የሚለውን የቁርአን አንቀፅ ከነትርጉሙ አነበበላቸው "ከሁለቱም እናቶች የወተት ጠብታዎችን ውሰዱና መርምሩ። በጣም የበለጸገና ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን የያዘችው የወተት ጡት ወንድ ልጅን የወለደችው እርሷ ናት" አለ። ንግግሩን ሰምተው እንዳበቁ አመስግነው ወደ ሐኪም ቤት አመሩ።

ከሁለቱም እንስቶች የወተቱን ናሙና ወስደው ላብራቶሪ አስገብተው መረመሩ። በመካከላቸው ያለውን ልዩነትም ተመለከቱ። ወንድና ሴት ልጅ የወለደው ማን እንደሆነ በዚህ መንገድ አወቁ። 

"(ይኽም) ከአላህ የተደነገገ ነው፤ አላህ ዐዋቂ ጥበበኛ ነውና" [ሱረቱ ኒሳእ]
ክብርና ምስጋና ለዓለማቱ ጌታ ለአላህ ተገባ

@risaalaatube
@risaalaatube
ዱባይ፣ የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ (ሲ.ኤን.ኤን) በሳውዲ አረቢያ ኪንግደም የሚገኘው የኪንግ አብዱላዚዝ ዩኒቨርስቲ የስነ ፈለክ ጥናት ባለሙያ ማልሃም ሂንዲ ሃሙስ አመሻሽ ላይ የሸዋልን ወር ጨረቃ ማየት በአይን እንደማይቻል ጠቁመዋል። በሥነ ፈለክ ጥናት መሠረት አርብ የ2023 የኢድ አል-ፊጥር የመጀመሪያ ቀን ነው።
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ኢትዮ_ቴሌኮም

በነዳጅ ማደያዎች በፍጥነት መስተናገድ ይችሉ ዘንድ ማድረግ ያለብዎትን ቅድመ-ዝግጅቶች እናስታውስዎ

⛽️ የቴሌብር አገልግሎት ተጠቃሚ ካልሆኑ ቴሌብር ሱፐርአፕን ከ onelink.to/75zfa5 በማውረድ ወይም በ*127# የቴሌብር አካውንት መክፈት

⛽️ ከቴሌብር ጋር ከተሳሰሩ 20 ባንኮች በሞባይል ባንኪንግ፣ በቴሌብር ወኪሎች እና በኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ማዕከሎች ገንዘብ ወደ ቴሌብር አካውንትዎ ያስተላልፉ፡፡

⛽️ ቴሌብር ሱፐርአፕን ሲጠቀሙ ቪ.ፒ.ኤን (VPN) እየተተቀሙ ከነበረ ያጥፉ

⛽️ ለተጨማሪ ድጋፍ ወደ 127 ይደውሉ ወይም በጽሁፍ ወደ 126 ወይም የቴሌብር ማህበራዊ ገጾቻችን ጥያቄዎን ይላኩ

ማስታወሻ: የነዳጅ ክፍያ በቴሌብር በመፈጸምዎ ምንም አይነት ተጨማሪ የአገልግሎት ክፍያ አይጠየቁም።

ለተጨማሪ መረጃ bit.ly/3V3wjPF
የአምላክ ዝምታ እና ሹመት ከታደለ፤
የሰው ልጅ በጭፍን አያደርገው የለ!
አምላክ ቤትህ ፈርሶ. . .
ቂም ቋጥረህ እንደኾን፣
ታውቅ እንደሁ በቀል፤
መዘዙ ብዙ ነው አንተን ማፈናቀል!
.
(#ፈይሠል_አሚን)©
.
@risaalaatube
@risaalaatube
የረሱትን ነገር ለማስታወስ ሰላት አለ ነቢይ  ስለማውረድ የተደረገ ውይይት

አዚዝ :-ቅድም የሆነ ነገር ረስተህ በመሀል ሰለዋት ስታወረድ ሰማውህ ልበል? ? ለማስታወስ ነው አይደል?

ዘኪ:-አዎ  የሆነ ነገር ረስቼ ለማስታወስ ነው ሰላት አለንነበይ ሰለሏሁ አለይሂ ወሰለም   ያወረድኩት።

አዚዝ :-ይህ ነገር ግን ቢድዓ ነው ፣ ምንም አይነት ማስረጃ የለውም ፣   ጃሂሎች ከየት  እንዳመጡት የማይታወቅ  ነገር ነው።

ዘኪ:-ነገራቶች ላይ ቶሎ ፍርድ ላይ መድረስ ከባድ ነው፣  በተለይ የዲን ጉዳይ ሲሆን በደንብ ማጣራት ፣ ማበጠር፣  ማድቀቅ  ይፈልጋል ምክንያቱም አደጋው በጣም ከባድ ነው።

አዚዝ :- ማስረጃ ካልለህ ማስረጃ የሚባሉትን  የእውቀት ማዕድ ላይ አቅርበናቸው ብንወያይባቸው ደስ ይለኛል።

ዘኪ :-እሺ የመጀመሪያው ደሊላቸን በጣም ሊገርምህ ይችላል ቁርአን ነው ።

አዚዝ:- ቁርአንን?

ዘኪ :- አዎ አሏህ እንዲህ ይላል:—
" وَاذْكُر رَّبَّكَ إِذَا نَسِيتَ"
"  ጌታህንም የረሳህ ጊዜ አስታውስ "
ይህ አንቀፅ ነገራቶችን በምንረሳ ጊዜ አሏህን  እንድናስታውስ ያዘናል፣ ይህን አንቀፅ በዚህ መልኩ የተረዱ ብዙ ሙፈሲሮች አሉ ከነዚያም ውስጥ ኢብኑ ከሲር ፣ በይዳዊ ፣  አሉሲ፣  ዘመኽሸሪ ፣ ሺንቂጢ ሌሎችም......... ይገኙበታል ።

* ስትረሳ  አሏህን የማስታወስ ጥቅሙ የመርሳት  ምንጭ የሆነው ሸይጣን ዚክር ሲሰማ ስለሚወገድ የዛን ጊዜ ስለምታስታውስ ነው አሏህ የሙሳን ዐለይሂስሰላም ባሪያ ታሪክ ሲያወሳ  እንዲህ ይላል:—

" وَمَا أَنسَانِيهُ إِلَّا الشَّيْطَانُ أَنْ أَذْكُرَهُ ۚ"
"ከማስታወስም አላስረሳኝም ሸይጧን ቢሆን እንጂ"

💢 የሚያስረሳህ ሸይጣን ከሆነ ሸይጣን የሚያባርር ነገር የለም ዚክር ቢሆን እንጂ።

አዚዝ:- አንቀፁ ሚያወራው ስለ ዚክር ነው ዚክር ደግሞ ሰለዋት አይደለም እኛ የምንወያየው ደግሞ ስለ ሰለዋት ነው ፣ ለምን የማይገባኝ ነገር ታገናኛለህ ።

ዘኪ :-ዚክር በሸሪአ  እይታ ዱዓእ ፣ አሏህን ማላቅ፣  ማስታወስ ፣ በተጨማሪም ማንኛውም መልካም ነገር ዚክር ይባላል ።

* ኢብኑ ዐላን በደሊሉል ፋሊሂን ላይ እንደጠቀሱት   ይህ አንቀፅ የዚክሩን አይነት ሳይለይ በደፈናው " በረሳህ ጊዜ ጌታህን አስታውስ " ስላለ ሰላዋት ከዚክር እንደሚመደብና የአንቀፁ ማስረጃነት  ምንም ጥርጥር የለውም።

❇️ ሁለተኛ  ሰሂህ በሆን ሀዲስ ነብዩ ዐለይሂስሰላም  እንዲህ ይላሉ: —
عَنْ أُبَيِّ بْنِ كَعْبٍ رضي الله عنه قَالَ : قُلْتُ : يَا رَسُولَ اللَّهِ إِنِّي أُكْثِرُ الصَّلَاةَ عَلَيْكَ فَكَمْ أَجْعَلُ لَكَ مِنْ صَلَاتِي ؟ فَقَالَ : مَا شِئْتَ . قَالَ قُلْتُ الرُبُعَ ؟ قَالَ : مَا شِئْتَ فَإِنْ زِدْتَ فَهُوَ خَيْرٌ لَكَ . قُلْتُ النِّصْفَ ؟ قَالَ : مَا شِئْتَ فَإِنْ زِدْتَ فَهُوَ خَيْرٌ لَكَ . قَالَ قُلْتُ فَالثُّلُثَيْنِ ؟ قَالَ : مَا شِئْتَ فَإِنْ زِدْتَ فَهُوَ خَيْرٌ لَكَ . قُلْتُ أَجْعَلُ لَكَ صَلَاتِي كُلَّهَا ؟ قَالَ : إِذًا تُكْفَى هَمَّكَ وَيُغْفَرُ لَكَ ذَنْبُكَ .
قال الترمذي : حَدِيثٌ حَسَنٌ صَحِيحٌ . وحسنه المنذري في (الترغيب والترهيب) ، وكذا حسنه الحافظ في "الفتح" (11/168) ، وأشار البيهقي في "الشعب" (2/215) إلى تقويته ، وصححه الألباني في "صحيح الترغيب" (1670)
* ይህ ታዋቂ ሀዲስ ላይ ሰሀብዩ ሰላት አለ ነቢ በማድረጉ የአላህ መልክተኛ ሰዐወ  ሁለት ነገራቶችን እንደሚያገኝ ነግረውታል ፣  እሱም 1 ኛ)  ከሚያስጨንቅህ ነገር ትበቃለህ 2ኛ)  ወንጀልህ ይማራል። ሰለዚህ ሰለዋት ማድረግ የሆነ ነገር ጠፍቶበት ያንን ነገር ለማስታወስ  ከሚደርገው ጭንቀት ይገላግለዋል።

🔰  ሶስተኛ ከሰይዱና አቢ ሁረይራ፣  ከሰይዱና ከኡስማን ኢብኑ ሀርብ፣  ከአነስ ኢብኑ ማሊክ የተዘገቡ ሀዲሶች የመርሳት ችግር በሚገጥም ጊዜ ሰላት አለ ነቢይ ማለት የተወደደ መሆኑን ይገልፃሉ: —
منها ما رواه الحافظ أبو موسى المديني من طريق محمد بن عتاب المروزي، حدثنا سعدان بن عبدة أبو سعيد المروزي، حدثنا عبيد الله بن عبد الله العتكي، أنبانا أنس بن مالك رضي الله عنه قال: قال رسول الله صلى الله عليه وسلم : (إذا نسيتم شيئا فصلوا علي تذكروه إن شاء الله) قال الحافظ أبو موسى: وقد ذكرناه من غير هذا الطريق في كتاب الحفظ والنسيان .
ذكره الإمام ابن القيم في جلاء الأفهام (239) .

👉 ይህ ሀዲስ እንደሚገል ፀው የአሏህ መልዕክተኛ ሰላሏሁ አለይሂ ወሰለም  እንዲህ ይላሉ "አንድን ነገር  በረሳችሁ ጊዜ በእኔ ላይ ሰለዋት አውርዱ በአላህ ፍቃድ ታስታውሱታላችሁ "  

    ኢብኑል ቀይም ጀላኡል አፍሃም ላይ ጠቅሰውታል

♻️ ብዙ የሰለዋት ጥቅሞችን  የሚገልፁ ድርሳናት እንደሚሉት ሰለዋት ከሚወደድባቸው ቦታዎች  ውስጥ አንደኛው  አንዳች ነገር ረስተን ለማስታወስ እንደሆነ ገልፀዋል ፣ ከነዚህም ኡለማዎች  ውስጥ በጥቂቱ የኢብኑ ተይምያህ  ተማሪ የሆኑት ኢብኑል ቀይም ጀላኡል አፍሀም በተባለ ኪታባቸው ላይ ይገኙበታል ፣  ሌሎችም ሰኻዊ  አልቀውሉል በዲዕ እንዲሁም ቀስጠላኒ በመዋሂብ መፀሀፍቶቻቸው ላይ በግልፅ ጠቅሰውት እናገኛለን።

አዚ :-ለሰጠሀኝ ማብራሪያ በጣም አመሰግናለሁ።

ዘኪ:-በትግስት ስላዳመጥከኝ እኔም አመሰግናለሁ።

https://hottg.com/risaalaatube
መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከሆነ የኤርዶጋን በቱርክመሪነት ለቱርክ ሙስሊሞች አስፈላጊ ነዉ። ኤርዶጋን የቱርክ መሪ ከመሆኑ በፊት የቱርክ ሙስሊሞች እጅግ በጣም ኢስላም ጠል የሆኑ አካላቶችን የሚከተሉና ሴቶች በአደባባይ ተገላልጠዉ ተሬቁተዉ የሚሄዱ ነበሩ። ሆኖም ኤርዶጋን ወደ ስልጣን ከመጣበት ሰአት ጀምሮ ቱርክ ዉስጥ የሚራቆቱ ሴቶች ወደ ሂጃቡ አለም ገብተዋል። በርካታ ኒቃቢስቶችም በነፃነት ኒቃባቸዉን መልበስ ችለዋል።

ቱርክ ላይ በሚካሄደው ምርጫ ከሙስሊሙ ዓለም አንፃር ኤርዶጋንና ፓርቲው ይሻላሉ። ተቀናቃኞቹ ሃገሪቱን በምዕራቡ ዓለም ሙስሊሙ የአይሁዶችን መንገድ እንዲከተል የሚፈልጉና ለሙስሊሞችም የባሰ ቆሻሻ ተግባር ፈፃሚ ናቸዉ።

ባባ ኤርዶጋን አሏህ ካንተ ጋር ይሁን።
ሙእሚን በትንፍሹ ልክ በረሱል (ሶለዋቱ ረቢ ወተስሊማቱ ዓለይሒ) ላይ ሶለዋት ቢያወርድ እንኳ የሳቸውን ሀቅ መወጣት አይችልም

ኢብኑል ቀይም🥰
ድንቅ ነው

ፋጢማህ ቢንት አብዱልመሊክ ስለባለቤቷ ዑመር ቢን አብድልአዚዝ ስትናገር...

"በህይወቴ እንደ ዑመር ጿሚና አላህን ፈሪ ሰው አላየሁም። ዒሻዕ ሰላት ይሰግዳል። ከዚያም ቁጭ ይልና ማልቀስ ይጀምራል እንቅልፍ ሲያሸንፈው ይተኛል ከጥቂት ሰአታት በኋላ ይነቃል። አሁንም በተሰበረ ቀልቡ የእንባ ዘለላዎችን ሲያወርድ አገኘዋለሁ። በድጋሚ ማንገላጃት ሲጀምር ይተኛል።
አንዳንዴ ከኔጋር ፍራሽ ላይ ሆኖ የመጭውን ዓለም ሁኔታ ሲያስታውስ ሰውነቱ ከውሃ ውስጥ ወጥታ ከላባዎቿ ላይ ውሃን እንደምታራግፍ ወፍ ይርገፈገፋል። ከዚያም ቁጭ ብሎ ማንባት ይጀምራል። እኔም እርሱ በተቀመጠበት ቦታ ብርድ ልብስ አለብሰዋለው።

እርሶስ ለነገ ቤትዎ ምን እየሰሩ ነው?
@risaalaatube
HTML Embed Code:
2024/05/21 10:28:50
Back to Top