TG Telegram Group Link
Channel: ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Back to Bottom
ክፍል 21

#የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፊያ መንገዶች
hottg.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ሁናችሁ ብቸኝነት ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እቤት በመክረማችሁ የብቸኝነት ስሜት እያጠቃችሁ ነው? እንግዲያውስ ይሄን ስሜተት የማሸነፊያ የሥነልቦና መፍትሔዎችንና ምክሮችን ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡
__
አዕምሮአችን የተፈ
ጠረው የተለያዩ አይነት ስሜቶችን እንዲረዳና እንዲያስተናግድ ነው ፡፡ እነዚህ ስሜቶች አወንታዊና አሉታዊ ሲሆኑ ለኛ ማንነትና አኗኗር ወሳኝነት አላቸው ፡፡ በውስጣችን የሚፈጠሩት አወንታዊ ስሜቶች የሚገነቡንን ያህል አሉታዊ ስሜቶች ደግሞ ከውስጥ እያፈረሱን ከውጭ ደግሞ በድካም ፣ በድብርት ፣ በጭንቀት ፣ ስለ ነገ ባለ ፍርሀት ያስሩናል ፡፡

በአዕምሮአችን ከሚፈጡሩ አሉታዊ ስሜቶች አንዱ ደግሞ የብቸኝነት ስሜት ነው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት እድሜና ፆታ ፣ ሀብትና ስልጣን ሳይለይ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ፣ ከደሀ እስከ ሀብታም  የሚያጠቃ አሉታዊ ስሜት ነው ፡፡

አዕምሮአችን " ማንም አይወደኝም ፣ እኔ ተሸናፊ ነኝ ፣ ሁሉም ሰው ጥሩ አይደለም ፣ ይሄ ወረርሽኝ እኔና ቤተሰቤን እንዳይጎዳ"  የሚሉ የተለያዩ ምክንያቶችን ሲያቀርብ በውስጣችን የብቸኝነት ስሜት እንዲያድግ ያሆናል ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የደረሱብንን የስነልቦና ፣ የስሜት ፣ የአካል ... ጥቃቶች ፣ ትችቶች መላልሶ ሲያሰላስል እንዲሁም በሌሎች የመገለል ነገር ሲኖር ወደዚህ ብቸኝነት ስሜት ልንመጣ ይችላል ፡፡

ከዚህ በታች የብቸኝነት ስሜትን ተረድተን እንዴት በጤነኛ መንገድ ማሸነፍ እንደምንችል 3 ሀሳቦችን እናያለን

1.ብቸኝነት ስሜት እንጂ እውነታ እንዳልሆነ መረዳት

ብቸኝነት ስሜት ሲሰማን በሕይወታችን  አንድ የተፈጠረ ነገር ይሄን ስሜት እንዳስነሳው መረዳት አለብን ፡፡ የብቸኝነት ስሜት የሚመጣው 'በመገለል ወይም ለብቻ በመሆን ' ብቻ አይደለም ስለዚህ ብቸኝነት ሲሰማን ቁጭ ብለን ጊዜ በመውሰድ ይህን ስሜት ያመጣብንን ምክኒያት ለማወቅ መሞከርና መንስኤውን ለማስወገድ ካልተቻለም ለመቀነስ እቅድ ማውጣት ተገቢ ነው ፡፡

2.በየቀኑ ትርጉም ያለው ስራ በመስራት ማሳለፍ

በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ባለንበት ቦታ ( በቤትም ሆንን በውጭ ) እያንዳንዱን ቀን ትርጉም ያለው ስራ ሰርተንበት እንለፍ ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀኑን ሙሉ ፊልም መመልከት ፣ ማሕበራዊ ሚዲያ ከአንዱ ወደአንዱ እየተሸጋገሩ ማየት ወደባሰ ድብርት ፣ ጭንቀትና ብቸኝነት ስሜት ስለሚመራ በየቀኑ አንድ አዲስ ነገር ለመስራት መሞከር ከብቸኝነት ስሜት ለመውጣት ይረዳል ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ማታ ስንተኛ ዛሬ ከነጋ ምን ሰራሁ ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ነገ ደግሞ ምን መስራት እንዳለብን ማቀድ መልካም ነው ፡፡


3. በጣም የምንወዳቸው ሰዎች ማግኘት ፣ የምንወዳቸውን ነገሮች መስራት

ይሄን ማድረግ በውስጣችን መልካም ሀሳብና ኢነርጂ እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡ ይሄም የተሻለ የስራ ተነሳሽነት ይፈጥርልናል ፡፡ ከሚወዱት ነገር ጋር ጊዜ ማሳለፍ በውስጣችን አወንታዊ ሀሳብ እንዲፈልቅ ፣ አሉታዊዉ ደግሞ እንዲቀንስ ይረዳል ፡፡ በተጨማሪም በዙሪያችን ለብቸኝነት መንስኤ ከሆኑ ሁኔታዎችና ሰዎች መሸሽ ተገቢ ነው፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጥቂጥ መፍትሔዎች ናቸው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት ሲሰማን ሊረዱን የሚችሉ ሌላ ብዙ መንገዶችን ከመጸሐፎች ፣ ከድህረ ገፆች፣ ከሰዎች ልናገኝ እንችላለን።


       ❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
                  
_____
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

                  የሳምንት ሰው ይበለን!
__❖

ሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ሀሙስ 18
ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ መጨነቅን ለማቆም ቀላል ዘዴዎች
Telegram hottg.com/psychoet

‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!

1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡- እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም አንችልም፡፡

2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::

3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:- እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡

4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን፡፡

5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው ”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን መረዳት ይጠበቅብናል::

6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡

7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ: ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::

8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ) በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡

9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም) ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን ልናጣ እንችላለንና፡፡

10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!

(በአለበል አዲስ)
©Zepsychologist
Telegram hottg.com/psychoet
ክፍል 22

#አራቱ የወላጅ አይነቶችና በልጆች አስተዳደግ ላይ ያላቸው ተፅዕኖ
hottg.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

የወላጆች አስተዳደግ ሁኔታ በልጆቻቸው ከአካላዊ እስከ ሥነልቦናዊ ውቅር ተፅዕኖ ያደርግባቸዋል ፡፡ በመሆኑም ወላጆች ምን አይነት አስተዳደግ ሁኔታ መምረጥ እንዳለባቸው ሊወስኑ ይገባልጠ፡፡ ይሄም ለጤነኛ ለልጆች አስተዳደግ ጉልህ ሚና አለው ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት 4 አይነት የወላጅ አይነቶች አሉ እነርሱም :-

Authoritarian ፦ ፈላጭ ቆራጭ

Authoritative ፦በልጆቻቸው እምነት የሚጥሉ

Permissive ፦ ልጆቻቸውን ሁሌ ነፃ የሚያረጉ (እሺ ባዮች)

Uninvolved ፦ ልጆቻቸው ህይወት ላይ በቂ ትኩረት የማያደርጉ (ዞር ብለው የማያዩ )

እያንዳንዱ የአስተዳደግ መንገድ የራሱ የሆነ መገለጫዎች ያሉት ሲሆን በልጆች ሁለንተናዊ ሕይወት ላይ የሚያመጣው አወንታዊና አሉታዊ ሚና አለው ፡፡

📌ፈላጭ ቆራጭ

እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸውን አብዝተው የሚጨቁኑ ሲሆኑ የልጆችን ስሜት የማይረዱ ፣ ሀሳብ አስተያየት የማይቀበሉ ናቸው ፡፡ እኔ ባልኩት መንገድ ብቻ ሂድ ብለው ልጆችን የሚያሳድጉ ናቸው ፡፡

የዚህ አይነት ወላጅ ያሳደጋቸው ልጆች ብዙ ጊዜ የተግባቦት መጠናቸው የቀነሰ ፣ ሰው በተሰበሰበበት ማውራት የሚፈሩ ፣ በራሳቸው መተማመን የሌላቸው ይሆናሉ ፡፡ ነገር ግን የተሻለ ስርአት ያላቸው ናቸው ፡፡

📌በልጆቻቸው እምነት የሚጥሉ
እነዚህ ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር የሚያስቀምጡት የጋራ ህግ ፣ ግብ ያላቸው ሲሆኑ ከልጆቻቸው ጋር ጥሩ ግንኙነት የሚፈጥሩ ናቸው ፡፡ የልጆቻቸውን ስሜት የሚረዱና ልጆቻቸውን በጥንቃቄ የሚጠብቁና ልጆቻቸው ያልተገባ ባህሪይ እንዳያዳብሩ ከጅምሩ የሚቆጣጠሩ ናቸው ፡፡ልጆቻቸውን በቅጣት ከማስተማር ይልቅ ጥሩ ነገር ሲሰሩ በመሸለምና በማበረታታት ለመቆጣጠር ይሞክራሉ ፡፡

በዚህ ቤተሰብ የሚያድጉ ልጆች ሀላፊነት የሚሰማቸውና ሀሳባቸውን የሚገልፁ ናቸው ፡፡

📌እሺ ባዮች

እነዚህ ወላጆች ልጆቻቸውን ከልክ በላይ አሞላቀው የሚያሳድጉ ፣ ልጆችን እንደ  ልጆች ብቻ የሚያዩ ናቸው ፡፡ በተጨማሪም ከወላጅነት ይልቅ የጓደኛነት ባህሪ ለልጆቻቸው የሚያሳዩና የልጆችን ሁሉን ጥያቄ እሺ የሚሉ ናቸው ፡፡

በዚህ ቤተሰብ ውስጥ ያደጉ ልጆች ብዙ ጊዜ በትምህርታቸው ዝቅተኛ የመሆን እድላቸው የጨመረ ነው ፡፡

📌ልጆቻቸው ህይወት ላይ በቂ ትኩረት የማያደርጉ

እነዚህ ወላጆች ደግሞ ልጆች ራሳቸውን እንዲያሳድጉ የሚጠብቁ ናቸው ፡፡ የልጆቻቸው ፍላጎት ላይ ጊዜና ጉልበት የማያባክኑ ልጆቻቸውን የማይቆጣጠሩ ናቸው ፡፡ ትኩረታቸው የግል ስራቸው ፣ ሕይወታቸው ላይ ያረጋሉ ፡፡

በዚህ ቤተሰብ ያደጉ ልጆች ለራስ ያላቸው ግምትና ክብር ዝቅተኛ ነው ፡፡

🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
ሁሉም የወላጅ (የአስተዳደግ) አይነቶች የራሳቸው የሆነ አወንታዊና አሉታዊ ጎን ቢኖራቸውም ከሁሉም ለልጆች አስተዳደግ ተመራጭ የሚሆነው ሁለተኛው ነው ፡፡ ይህን አይነት የወላጅነት ሚና በመወጣት ቤተሰብን ብሎም ሀገርን በመልካም መገንባት ይቻላል ፡፡


በዩቲዩብ የምንለቃቸውን ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን Subscribe አድርጉ
youtube.com/thenahusenaipsychology
_________❖
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
__________❖

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ክፍል 23

#የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፊያ መንገዶች
hottg.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ሁናችሁ ብቸኝነት ተሰምቷችሁ ያውቃል ? እቤት በመክረማችሁ የብቸኝነት ስሜት እያጠቃችሁ ነው? እንግዲያውስ ይሄን ስሜት የማሸነፊያ የሥነልቦና መፍትሔዎችንና ምክሮችን ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡
______
አዕምሮአችን የተፈጠረው የተለያ
ዩ አይነት ስሜቶችን እንዲረዳና እንዲያስተናግድ ነው ፡፡ እነዚህ ስሜቶች አወንታዊና አሉታዊ ሲሆኑ ለኛ ማንነትና አኗኗር ወሳኝነት አላቸው ፡፡ በውስጣችን የሚፈጠሩት አወንታዊ ስሜቶች የሚገነቡንን ያህል አሉታዊ ስሜቶች ደግሞ ከውስጥ እያፈረሱን ከውጭ ደግሞ በድካም ፣ በድብርት ፣ በጭንቀት ፣ ስለ ነገ ባለ ፍርሀት ያስሩናል ፡፡

በአዕምሮአችን ከሚፈጡሩ አሉታዊ ስሜቶች አንዱ ደግሞ የብቸኝነት ስሜት ነው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት እድሜና ፆታ ፣ ሀብትና ስልጣን ሳይለይ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ፣ ከደሀ እስከ ሀብታም  የሚያጠቃ አሉታዊ ስሜት ነው ፡፡

አዕምሮአችን " ማንም አይወደኝም ፣ እኔ ተሸናፊ ነኝ ፣ ሁሉም ሰው ጥሩ አይደለም ፣ ይሄ ወረርሽኝ እኔና ቤተሰቤን እንዳይጎዳ"  የሚሉ የተለያዩ ምክንያቶችን ሲያቀርብ በውስጣችን የብቸኝነት ስሜት እንዲያድግ ያሆናል ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የደረሱብንን የስነልቦና ፣ የስሜት ፣ የአካል ... ጥቃቶች ፣ ትችቶች መላልሶ ሲያሰላስል እንዲሁም በሌሎች የመገለል ነገር ሲኖር ወደዚህ ብቸኝነት ስሜት ልንመጣ ይችላል ፡፡

ከዚህ በታች የብቸኝነት ስሜትን ተረድተን እንዴት በጤነኛ መንገድ ማሸነፍ እንደምንችል 3 ሀሳቦችን እናያለን

1.ብቸኝነት ስሜት እንጂ እውነታ እንዳልሆነ መረዳት

ብቸኝነት ስሜት ሲሰማን በሕይወታችን  አንድ የተፈጠረ ነገር ይሄን ስሜት እንዳስነሳው መረዳት አለብን ፡፡ የብቸኝነት ስሜት የሚመጣው 'በመገለል ወይም ለብቻ በመሆን ' ብቻ አይደለም ስለዚህ ብቸኝነት ሲሰማን ቁጭ ብለን ጊዜ በመውሰድ ይህን ስሜት ያመጣብንን ምክኒያት ለማወቅ መሞከርና መንስኤውን ለማስወገድ ካልተቻለም ለመቀነስ እቅድ ማውጣት ተገቢ ነው ፡፡


2.በየቀኑ ትርጉም ያለው ስራ በመስራት ማሳለፍ

በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ባለንበት ቦታ ( በቤትም ሆንን በውጭ ) እያንዳንዱን ቀን ትርጉም ያለው ስራ ሰርተንበት እንለፍ ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀኑን ሙሉ ፊልም መመልከት ፣ ማሕበራዊ ሚዲያ ከአንዱ ወደአንዱ እየተሸጋገሩ ማየት ወደባሰ ድብርት ፣ ጭንቀትና ብቸኝነት ስሜት ስለሚመራ በየቀኑ አንድ አዲስ ነገር ለመስራት መሞከር ከብቸኝነት ስሜት ለመውጣት ይረዳል ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ማታ ስንተኛ ዛሬ ከነጋ ምን ሰራሁ ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ነገ ደግሞ ምን መስራት እንዳለብን ማቀድ መልካም ነው ፡፡


3. በጣም የምንወዳቸው ሰዎች ማግኘት ፣ የምንወዳቸውን ነገሮች መስራት

ይሄን ማድረግ በውስጣችን መልካም ሀሳብና ኢነርጂ እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡ ይሄም የተሻለ የስራ ተነሳሽነት ይፈጥርልናል ፡፡ ከሚወዱት ነገር ጋር ጊዜ ማሳለፍ በውስጣችን አወንታዊ ሀሳብ እንዲፈልቅ ፣ አሉታዊዉ ደግሞ እንዲቀንስ ይረዳል ፡፡ በተጨማሪም በዙሪያችን ለብቸኝነት መንስኤ ከሆኑ ሁኔታዎችና ሰዎች መሸሽ ተገቢ ነው፡፡


       ❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
              

_________❖
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

                  የሳምንት ሰው ይበለን!
__________❖

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ሀሙስ 19

እንደምን አላችሁ፣
የዛሬ የሀሙሱ ጽሑፋችን...
በጣም የምትጠሉትን የሰው ባህሪ Comment ላይ ጻፉልን?

ብዙ ሰው የጻፈው ባህሪ ላይ ሥነልቦናዊ ማብራሪያ እናቀርባለን፡፡

@psychoet
ክፍል 24
በቤተሰብ አባል ውስጥ የሥነ-ልቦና መታወክ ሲያጋጥም ምን እናድርግ?
#SHARE

የስነ-ልቦና ወይም የስነ-ባህሪ መታወክ በሀገራችን ትኩረት ካልተሰጠባቸውና የህክምና ዘዴው (psychotherapy) ካልተስፋፋባቸው ማኅበራዊ ችግሮች ውስጥ ዋንኞቹ ናቸው፡፡ ምንም እንኳን በባህላዊና በሃይማኖታዊ ድጋፎች ማኅበረሰባችን ከዚህ ችግር ጋር እየተጋፈጠ ቢሆንም፣ ዋናው ጫና የዚህ ችግር ተጠቂ ከሆኑ የቤተሰብ አባላት ላይ ነው፤ምክኒያቱም እንደሰለጠነው ዓለም የህክምና ፤ ድጋፍና እንክብካቤ ሰጪ  ቦታዎች ስለሌሉን ነው፡፡ ይህን ችግር ለማቃለል እየተንቀሳቀሱ ካሉት አገር በቀል ድርጅቶች ውስጥ አንዱ መቄዶኒያ ሲሆን በዚህ አጋጣሚ ስለሚሰሩት ስራ ያለኝን አድናቆት ሳልጠቅስ አላልፍም፡፡እናንተም የተቻላችሁን ድጋፍ አድርጉላቸው፡፡

ከዚህ በመቀጠል የስነ-ልቡና መታወክ ችግር ያጋጠማቸው የቤተሰብ አባላት ይህን ተግዳሮት ለመቋቋም ምን ማድረግ አለባቸው የሚለውን በዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽሐፍ መነሻነት ይጠቅማሉ ያልኳቸውን ነጥቦች አነሳለሁ፡፡ መልካም የንባብ ጊዜ!
___
#ለበሽታው_ያለንን_ግንዛቤ_ማሳደግ ፡-

ስለታመመብን ሰው የስነ-ልቡና መታወክ አይነት፣ መንስኤ፣ ምልክቶች፣ ስለሚያባብሱ ሁኔታዎችና ነገሮች እራስን ማስተማር፡፡ ስለታመመው ሰው የስነ-ልቡና ወይም የስነ-ባህሪ ችግር የተሳሳተ መረጃ ካለን ወይም ስለ ምልክቶቹና ስለሚያባብሱ ጉዳዮች ዝቅተኛ ግንዛቤ ካለን ግለሰቡንና ቤተሰቡን በአጠቃላይ ሊጎዳ የሚችል ተግባር ልንፈጽም እንችላለን፡፡

#ለምሳሌ እስኪዞፍሬኒያ (Schizophrenia) ያለባቸው ግለሰቦች ስለሚታያቸው አስፈሪ ግን በገሃዱ አለም የለለ ምስል (hallucination) ምንም ግንዛቤ ከሌለን፤ በተገቢው ተጠቂዎችን ላንረዳቸውና አግባብነት ያለው ምላሽ ላንሰጥ እንችላለን፡፡

#በለሌላ ምሳሌ በከፍተኛ ድባቴ (Depression) ውስጥ ያሉ ግለሰቦች አጥብቀው እራስን ስለማጥፋት (suicidal ideation) ሊያስቡ ይችላሉ፡፡ ይህ ሃሳብ በዝርዝር እራሳቸውን እንዴት፣በምን፣የትና እራሳቸውን እነደሚያጠፉና የመሳሰሉትን በዝርዝር ማሰላሰልና ሙከራ ማድረግን ሊያካትት ይችላል፡፡ ስለዚህ እድብታ ወደ እንደዚህ አይነቱ የስነ-ልቡናና የስነ-ባህሪ ዝንባሌ ሊወስድ እንደሚችል በቂ እውቀት ከሌለን፤ በዚህ የሚሰቃይ ቤተሰባችን፣ጓደኛችን፣ፍቅረኛችንን እንዲሁም የስራ ባልደረባችንን በተገቢው መንገድ መርዳት አንችልም፡፡ አንዳንዴም ለምን ስለማይጠቅም ነገር ታስባለህ እና የመሳሰሉትን ትችቶች በመስጠት ግለሰቡን እንኮንናለን፡፡ ስለሆነም በግለሰቡ ላይ የምናያቸው እንግዳ ባህሪያትና አስተሳሰቦች ከግለሰቡ ቁጥጥር ውጭ ስለመሆናቸው መረዳት ተገቢ ነው፡፡ ስለዚህ ስለ ግለሰቡ የስነ-ልቡና ችግር ያለን ግንዛቤ ለግለሰቡ ለምንሰተጠው እርደታ፣ግለሰቡን የምንረዳበትን እይታ፣እንዲሁም ለራሳችን ደህንነት ወሳኝ ሚና ይጫወታል ምክኒያቱም የቤተሰብ አካል ጓደኛ ወይም ፍቀረኛ የስነ-ልቡና ችግር ሲያጋጥም የኛ ደህንነት ላይም ተጽዕኖ ስለሚያደርስ፡፡

➋ትክክለኛ የመረጃ ምንጮችን ማፈላለግ፡-

ስለ ግለሰቡ የስነ ልቡና ችግር ሳይንሳዊ ግንዛቤ ለመጨበት ትክክለኛ ምንጮችን መከተል ይገባናል፡፡ ምንም እንኳን በሀገራችን ቋንቋንዎች የተጻፉ ሳይንሳዊ መሰረት ያላቸው መጽሀፍት ባይኖሩም፣ የእንግሊዚኛ ችሎታ ካለን በእንግሊዚኛ የተጻፉ ሳይንሳዊ መጽኃፍትን ወይም ታእማኝነት ያለቸውን ድህረ-ገጾች መጠቀም፡፡ እንዲህ ስል በእንግሊዚኛ ስለተጻፈ ብቻ ጠቃሚ ነው ማለቴ ሳይሆን እነደ ዕድል ሆኖ ሳይንሱ በምዕራቡ አለም ስለተስፋፋ ብዙ ሳይነሳዊ የሆኑ መጽሀፍት በእንግሊዚኛ ቋንቋ ስለተጻፉ ነው፡፡ ስለዚህ የሀገራችን ሳይኮሎጂስቶችና ሳይካቲሪስቶች ብዙ የቤት ስራ አለብን፡፡ ምርምር ከመመረቂያ ጽሁፍ በላይ መሆን አለበት፡፡ (እዚህ ጋር ላቋርጣችሁና… የኛ አላማ ይህን ክፍት መሙላት  የሚችል በስነ-ልቡና ችግሮችን፣ ትዳርን፣ ፍቅር፣ የልጅ አስተዳደግን፣ ትምህርት ነክና ለሌች የስነ-ልቡና ጉዳዮችን የሚዳስስ ሳይንሳዊ መሰረት ያለቸውን መረጃዎች ለናንተና በውጭ ሀገር ላሉ አዳማጭ ላጡ ወገኖቻችን አማራጭ ማቅረብ ነው፡፡ ስለዚህ ለወደፊት ስለተለያዩ የስነ-ልቡና ችግሮች መንስኤ፣ምልክት፣የመጀመሪያ እርዳታ እንዲሁም ዕርዳታ እንዴት ማግኘት እነደምትችሉ የተደራጀ መረጃ በዌብሳይታችን እናቀርባልን)፡፡ወደ ወናው ሃሳብ ስመለስ ስለስነ-ልቡና ችግሮችና መፍትሄዎች የተነገሩ ወይም የተጻፉ ነገሮች ሁሉ ትክክል ናቸው ማለት አይደለም፡፡ ለምሳሌ በጋዜጦችና መጽሄቶች የሚነገሩ ነገሮችን በባለሙያተኞች የሚነገሩ ከሆኑ እንደ ግብአት መውሰድ ይቻላል፡፡ በጥቅሉ ሳይንሳዊ ዳራ ያለቸውን ታማኝ ምንጮችን ተጠቀሙ ምክሬ ነው፡፡

➌የእርዳታ ምንጮችን መፈለግ፡-

የስነ-ልቡና ችግርን በሀገራችን ካሉ ሌሎች በሽታዎች ለየት የሚያደርገው የበሽታው ተጠቂዎች ላይ የሚደርሰው አድሎና መገለል አንዱ ነው፡፡ ስለዚህ በዚህ ምክኒያት ከማህበረሰቡ ከሚገኙ ድጋፍ ይልቅ አድሎው የሚያመዝንበት ሁኔታ አለ ምንም እንኳ የተለያዩ የሀይማኖት ተቃማት የራሳቸውን ድጋፍና እንክብካቤ ለተጠቂዎች የሚያደርጉ ቢኖሩም፡፡ በዚህም ምክኒያት የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ሰዎች ስለ በሽታቸው ከሌሎች ግለሰቦች የመወያየትና ድጋፍ የማግኘት እድላቸው ዝቅተኛ ነው፡፡ እናም የስነ-ልቡና ችግር ያለባቸው ግለሶቦች ቤተሰቦች ተመሳሳይ ችግር ያለባቸው ሌሎች ቤተሰቦች ጋር መወያየትና ሀሳብ መለዋወጥ ልምድ ከማካፈል በዘለለ ስለሚደርስባቸው ተግዳሮቶች ማውራታቸው የተወሰነም ቢሆን ስለጉዳዩ የሚሰማቸው ጭንቀት ቅልል ሊልላቸው ይችላል፡፡ ይህ እንግዲህ ፈረንጆቹ support group የሚሉት አይነት ነገር ነው፡፡ እዚህ ጋር ማንኛቸውም ሊጠቅሙ የሚችሉ ባህላዊና፣ ሀይማኖታዊ፣መንግስታዊ እንዲሁም መንግስታዊ ያልሆኑ ከስነ-ልቡና ችግር ጋር በተገኘ እርዳታ የሚሰጡ ተቋማትን ማፈላለግ፡፡


🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉


ቴሌግራም ሊንክ 🚙 hottg.com/Psychoet

ምንጭ ፦ Emotional survival guide for care givers ከሚለው የዶ/ር ቤሪ ያኮብስ መጽኃፍ መነሻነት የቀረቡ

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
ክፍል 25

በእራስ መተማመን

ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡
ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን ነው ??  በራስ መተማመንን የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ ፍቺዎች ሰጠውታል ሆኖም ጭብታቸው ተመሳሳይ ሆኖ ስላገኘሁት አንዱን ብቻ ልንገራችሁ፡፡ ጎልማን በራስ መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው ይለናል፡፡ በራስ መተማመን የራስ እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy)  ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣ አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡

ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው ነገሮች ለማውራት ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን አጠንክረን እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?? የሚከተሉትን ነጥቦች አብረን እንያቸው…… መልካም ንባብ ተመኘሁ፡-

1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡- በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡

2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች  ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡

3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡ ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡

4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ፡፡

5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡

6.በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡

7.ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ እራስህ ውሸት በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት አትሞክር፡፡

በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን  ያለው ሰው የሚመጣውን አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት ወይም ከመሞከር ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ እየሞከረ ራሱን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት ሚዛናዊ አድርጎ መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ……….
መልካም ቀን !
© (ቁምላቸው ደርሶ)
@psychoet
ሀሙስ 20

#ውሸት

ለምን እንዋሻለን ??? ውሸት ተናጋሪዎችን እንዴት እናውቃለን???
ለምን እንዋሻለን ??

ሀ. ግላዊ ጥቅም ለማግኘት፡–  ለምሳሌ ለስራ ስንወዳደር ቃለ መጠየቅ ላይ የተሻለ ደመወዝ እንዲከፈለን አሁን የሚከፈለንን የደመወዝ መጠን ከፍ አድርገን እንናገራለን፡፡

ለ.ቅጣትን ለማስቀረት፡– ህፃናት በወላጆቻቸው እንዳይቀጡ ያጠፉትን ነገር አይናገሩም ወይም አልሰራንም ይላሉ፡፡

ሐ. ሌሎች ስለኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ፡- ሰዎች ስለኛ ጥሩ የሆነ ግንዛቤ ይኖራቸው ዘንድ ያልሆነውን ሆንን፣ ያላደረግነውን አደረግን ብለን እንናገራለን፡፡

ከላይ የተጠቀሱት የውሸት ዓይነቶች  በእኛ ዙሪያ ያጠነጠኑ እና  እራሳችንን ለመጥቀም የታለሙ  (self oriented) ናቸው፡፡ ሆኖም ግን ለሌላ ሰው  ተብለው የሚዋሹ ውሸቶችም አሉ ለምሳሌ፡-

ሀ. ሌሎች ሰዎችን ለመጥቀም፡– እናት ልጇን ከፍርድ ቤት ቅጣት ለመጠበቅ ስትል ወንጀሉ በተፈፀመበት ሰዓት ልጄ እቤት ነው ብላ ልትመሰክር ትችላለች፡፡

ለ. ሰዎች ለማህበራዊ ግንኙነት ሲባልም ይዋሻሉ፡– ጎረቤት እራት ተጋብዘን እዚህ ግባ የማይባለውን  ምግብ ጣት ያስቆረጥማል ብለን የምንወጣው ቀጣይ የሚኖረንን ግንኙነት ከግምት ውስጥ በማሰገባት ነው፡፡

ሐ. ሰዎችን ለመጉዳት እንዋሻለን :- ይህ ደግሞ በሌሎች እንዲቀጡ ባልሰሩት ነገር ላይ በሀሰት በመመስከር የሚደረግ ውሸት ነው ፡፡

ሰዎች እንደሁኔታው ዓይነት ውሸቶችን ይዋሻሉ ለምሳሌ #ሮቢንሰን ባጠናው ጥናት ላይ ስራ ለማግኘት ተብሎ ቃለ ምልልስ ላይ የሚዋሽ ውሸትን #83% የሚሆኑ የጥናት ተሳታፊዎች የነበሩት የኮሌጅ ተማሪዎች እንደ ውሸት አይቆጥሩትም፡፡
#ሮዋት ባጠናው ጥናት ደግሞ #40% የሆኑት የጥናቱ ተሳታፊዎች ወደፊት የፍቅር አጋር ይሆናል ብለው ላሰቡት ሰው በመጀመሪያ ግንኙነት ላይ እንደሚዋሹ አረጋግጠዋል፡፡
ሆኖም ግን ምን ያህል የሚሆነው የተሳካ የፍቅር ግንኙነት ኖሮት እንደቀጠለ ጥናቱ የሚለው ነገር ባይኖርም ከላይ በተቀስነው የውሸት ዓይነት ማለትም ሰዎች ስለ እኛ መልካም እይታ እንዲኖራቸው ለማድረግ በሚዋሽ ውሸት ፍፃሜው ያማረ የፍቅር ግንኙነት ሊኖረን አይችልም፡፡

ሌላው በጥናቱ ላይ የተመለከተው ነጥብ ጾታን በተመለከተ የታየ ልዩነት የለም ይህም ማለት ሁለቱም ወንዶችም ሴቶችም በእኩል መጠን ይዋሻሉ፡፡ በእኛስ ሀገር የትኛው የበለጠ ይዋሻል?? #ወንድ ወይስ #ሴት?? መልሱን ለእናንተ ተውኩት፡፡ ተጨማሪ በሌሎች ጥናቶች ላይ እንደተመለከተው ተጫዋች (ማህበራዊ) (Extraverts) ግላዊ (Introvert) ከሆኑት በበለጠ ውሸት እንደሚያዋሹ አመልክተዋል፡፡

ውሸትን እና ውሸታሞኝችን ለመለየት ሰዎች በጥናት የተደገፉ ከቤተ ሙከራ እስከ ውሸትን የማወቂያ መሳሪያ (polygraph) ድረስ ያሉ የተለያዩ ዓይነት ዘዴዎችን ይጠቀማሉ፡፡ ፖሊግራፍን ውሸትን ለማወቅ የሚለካው እንደ ልብ ምትና የመሳሰሉትን አካለዊ ለውጦችን እንደመሆኑ መጠን እንደየ ግለሰቡ ባህሪ ትክክለኝነቱ ሊወሰን ይችላል፡፡ ስሜታቸውን በቀላሉ የሚቆጣጠሩ ሰዎች ውጤቱን ሊያሳስቱ ሲችሉ፤ ድንጉጥ፤ ስሜታዊና ለነገሩ አዲስ የሆኑ ግለሰቦች ደግሞ በተቃራኒው የቀጣፊነት ባህሪ ሊሰጣቸው ይችላል፡፡ አሁን አሁን ግን ከጎንዮሽ ጉዳቱና ከውጤቱ እርግጠኝነት ጋር በተያያዘ ፖሊግራፍ እየቀረ ያለ ቴክኖሎጂ ነው፡፡

ለጊዜው ግን ለእኛ ይሆነን ዘንድ የሰዎችን ባህርይ በማየት እንዴት ውሸታሞችን መለየት እንችላለን የሚለውን እንመለከት፡፡ የተደረጉት ጥናቶች በዋናነት መሰረት ያደረጉት
#ስሜታዊነትን (emotional state)፣
#የወሬያቸውን (የመልዕክቱን) ይዘት (content complexity)  እና
#ባህርይን ለመቆጣጠር ከሚደረግ ጥረት (attempted behavioral control) በመነሳት ነው፡፡ ስሜታዊነት ላይ ሰዎች ውሸት ሲያወሩ አንደኛ ውሸት እያወሩ ስለሆነ የጥፋተኝነት ስሜት ይሰማቸዋል፣ ሁለተኛ በውሸቱ ምክንያት ወደፊት በሚያገኙት ጥቅም ደስተኛ ይሆናሉ ወይም ደግሞ ይታወቅብኝ ይሆን በማለት ይፈራሉ፡፡ ከወሬያቸው ይዘት ጋር በተገናኘ ውሸት ተናጋሪዎችን ለመለየት ተናጋሪውን ተደጋጋሚ ጥያቄ በመጠየቅ ተመሳሳይ መልስ እንደመለሰልን ማረጋገጥ እና ለምላስ ወለምታዎች ትኩረት መስጠት እንደ ዘዴ ተቀምጠዋል፡፡

የሰዎችን ባህርይ በማየትም ውሸት ተናጋሪዎችን መለየት እንችላለን #ዲፓውሎ_እና_ሮዘንሀል በጥናታቸው እንዳረጋገጡት ከሆነ ውሸት የሚያወሩ ሰዎች በሚያውሩበት ጊዜ እነዚህን ባህሪዎች አሳይተዋል መረጃውን  የሚያስተላልፉለትን ወይም የሚነግሩትን ሰው ዓይን ላለማየት የተለያየ ጥረት ደርጋሉ፣ አላስፈላጊ በሆነ ቦታ ላይ ሊስቁ እና ፈገግ ሊሉ ይችላሉ፣ ተደጋጋሚ የሆነ መንገድ በእጅ ለማስረዳት የእጅ እንቅስቃሴ ያደርጋሉ (ውሸት የማይናገሩ ሰዎች በእጃቸው እንቅስቃሴ ለማስረዳት እንደሚሞክሩ ልብ ይሏል)፣ ፊታቸውን እና  ፀጉራቸውን ያካሉ ወይም ይነካሉ፣ በተለያዩ ፊት ለፊት በተቀመጡ ግዑዝ ነገሮች ይጫወታሉ፣ በፍጥነት ያወራሉ፣ ግንባራቸውን እና እጃቸውን ያልባቸዋል፣ ጥያቄ ሲጠየቁ እስኪመልሱ ድረስ ባንጻራዊነት ሰፊ ጊዜ ይወስዳሉ፣ በመሀል አ……ኧ….እም……ያበዛሉ፣ መንተባተብ (ቃላትን መደጋገም፣ ዐረፍተ-ነገሮችን አለመጨረስ፣ የምላስ ወለምታ)እንዲሁም  ድንገተኛ የሆነ የድምጽ መጨመርና መቀነስ ይታይባቸዋል፡፡

ሰዎች በተለያየ መንገድ ግንኙነት ፈጥረው ሲያወሩልን ወይም መልዕክት ሲያስተላልፉልን ከላይ ከጠቀስናቸው ምክንያቶች መካከል አንዳንድ ነገሮችን ካየን ውሸታም ብለን ከመፈረጃችን በፊት በእራሳችን መንገድ እና ለምን እንደዋሹን ደግሞ ማጣራት ይኖርብናል፡፡ በዚህች ባጭር ጽሁፍ መሸፈን አልችልም እንጂ ስለ Pathological liars (ህይወታቸው በሙሉ በውሸት ስለተሞላና ውሸት መናገርና ማቆም ስለማይችሉ ውሸት በሽታ ስለሆነባቸው ሰዎች) ጥቂት ባወራ ደስ ባለኝ ነበር፡፡ ነገር ግን ወደፊት ይዤላችሁ እንደምቀርብ ቃል በመግባት የዛሬውን በዚህ ልቋጨው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………..

©Zepsychologist
@psychoet
🏆🏆🏅🏅🎖🥇🎖🏅🏅🏆🏆
ንቃ ወንድሜ

♻️ኒዉ ዬርክ ከ ካሊፎርኒያ በ 3 ሰዓት ይቀድማል ነገር ግን ይኼ ካሊፎርኒያን ቀርፋፋ አያደርጋትም❗️

♻️አንዳንድ ሰዉ በ22 አመቱ ይመረቃል ነገር ግን አሪፍ ስራ ለመያዝ 5አመት ይፈጅበታል❗️

♻️አንዳንዱ በ25 አመቱ የድርጅት ሃላፊ ሁኖ በ50 አመቱ ሲምት ሌላዉ በ50 ዓመቱ ሃላፊ ሁኖ እስከ 90 ዓመት ይኖራል❗️

♻️ኦባማ በ55 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጨረሰ ነገር ግን ትራንፕ በ70 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጀመረ! ይሄ ትራንፕን ኅላ ቀር አያረገዉም❗️

〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️〽️
🎤🎤🎤ሳጠቃልለዉ ጊዜ የፈጣሪ አንዱ መሳሪያ ነዉ ፤ እሱ በጊዜዉ ሁሉን ነገር ዉብ ያደርጋል ፡፡፡

💫💫💫💫💫💫💫💫💫
🎨ስለዚህ ወደዚና ወደዛ እየተመለከትክ ከሁሉ በኅላ የቀረክ ወይም በፊት የቀደማክ አይምሰልህ❗️
ሁሉም ሰዉ የራሱ የሆነ የኑሮ ሩጫና የተፈጠረበት አላማ አለዉ❗️❗️❗️

💫💫💫💫💫💫💫💫💫
_
©©
©©©©©©©©©
ሁላችንም የራሳችን የሆነ የሆነ የጊዜ ክልል አለን::
ስለዚህ
ወደጎን🕺🕺🕺ከማየት
ወደፊት 🏃🏃እያየን
🏃🏃‍መንገዳችንን እንጓዝ!!!🏃🏃🏃

🎡🚧🎡መልካም ሳምንት
Nahu|ናሁሰናይ

@psychoet
ክፍል 26

ራስን በመቆጣጠር ድብርትን መከላከልና መጋፈጥ
ለሌሎችም #Share ይደረግ

የራስ ቁጥጥርና (self-regulation) የድብርት ስሜት ተዛማጅና ግንኙነት ያላቸው የስነ-ልቡና ክስተቶች ናቸው፡፡ ራስን መቆጣጠር ማለት አንድን ነገር ከግብ ለማድረስ ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብንና ጠባይን መግራት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ራስን መቆጣጠር ከግብ ወይም አላማችን ጋር የተቆራኘ ነው፡፡ ለምሳሌ ግባችን መማር፤ጥሩ ስራ መያዝ፤ የፍቅር ጓደኛ መያዝ፤ትዳር መመስረትና ልጆች ማፍራትና የመሳሰሉት ሊሆን ይችላል፡፡ እናም አላማችን ከትናንሽ የዕለተለት ግቦች እስከ ላቅ ያሉ ለህይወታችን ከፍተኛ ትርጉም ያላቸው ግቦች ድረስ ሊሆን ይችላል፡፡

ራስን መቆጣጠርና የድብርት ስሜትን ምን አገናኛቸው?

ራስን መቆጣጠር ውስጠ ስሜትን፣አስተሳሰብና፣ጠባይንና ከአላማነችን አንጻር መግራት ነው በሚለው ከተስማማን፤ የግባችን የስኬት መጠን ከድርጊታችን በኋላ ለሚሰማን ሰሜት ወሳኝ ሚና ይጫወታል፡፡ ያሰብነውና ያቀድነው ነገር በተሰካ ጊዜ ደስታ፣እርካታ፣ተሰፋና ለነገ የተነሳሽነት ስሜት ይፈጥርልናል፡፡ ያሰብነውና ያለምነው ነገር ሳይሳካ ሲቀር በተቃራኒው የድብርተና ተዛማጅ አሉታዊ ስሜቶች ሊፈራረቁ ይችላሉ፡፡ በዚህም ምክኒያት ራስን መቆታጠርና ድብርት የጠለቀ ግንኙነት አላቸው፡፡

የድብርት ስሜት ለራስ ቁጥጥር ያለው እንድምታ

ምንም እንኳን የድበርት ስሜት ምችት የማይሰጥ ቢሆንም ሳይንሳዊ መላምቶችና ምርምሮች እንደሚያመላክቱት ከሆነ እራሳችን ለመቆጣጠር የራሱ የሆነ አስተዋጽኦ አለው፡፡ ለምሳሌ ለፍቅረኛችን ታማኝ መሆን ሲገባን በስህተት ተማኝነታችንን ብናጎድል ከፈጸምነው በኋላ የድብርት ስሜት ሊፈጠርብን ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ነገ ተደጋጋሚ ስህተት ላለመፈጸም ለእራሳችን ግበረ-መልስ (feedback loop) ነው:: ስለዚህ አላማችን ያማረ የፍቅር ህይወት መመስረት ከሆነ ለዚህ አላማችን መሳካት የእራሳችንን ጠባይ እንድንቆጣጠር የድብርት ስሜቱ አስተዋጽኦ ያበረክታል ማለት ነው፡፡ በተቃራኒው ሁሌም ታማኝነታችንን እያጎደልን ከፈጸምነው በኋላ ፌሽታና ደስታ የሚሰማን ከሆነ በዛው እምነት አጉዳይነታችን የመቀጠላችን እድል የሰፋ ነው፡፡ በተመሳሳይም በትምህርታችን ጥሩ ውጤት የማስመዝገብ አላማ ቢኖረንና ጊዜያችንን በአግባቡ ሳንጠቀም የፈለግነው ውጤት ባይመጣ አሁንም የድበርት ስሜት ሊከስት ይችላል፡፡ ይህ የድብርት ስሜት ለእራሳችን ጠባይ ከሰነቅነው አላማ አንጻር ምን ያህል ውጤታማ እንደሆነ አእምሯችን እራሱን የሚገመግምበት ግብረ-መልስ ሲሆን፤ ለወደፊት ይህ እንዳይከሰት የማስጠንቀቂያ ደወል ነው፡፡ በአጭሩ በዚህ የአረዳድ ድባብ መሰረት የድብርት ስሜት መፈጸም በምንፈለግገውና በፈጸምነው መካከል ልዩነት ሲፈጠር የሚከሰት ነው ማለት ነው፡፡

ተደጋጋሚ ውድቀትና ድብርት

በተደጋጋሚ ያሰብነውና ያቀድነው ነግር በማይሳካ ጊዜ የድብርት ስሜቱም እየጠነከረ በተደጋጋሚ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት፣መንስኤና ውጤት አትኩሮት ሰጥተን እንድናሰላስል በር ይከፍታል፡፡ ይህም ክስተት rumination በመባል ይታወቀል፡፡ ይህ አጥብቆ ስለሚሰማን የድብርት ስሜት ማንሰላሰል ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን ይችላል፡፡ አብዛኞቹ በዚህ ዙሪያ የሚያጠኑ የስነ ልቡና ጠበብቶች አጥብቆ ከልክ በላይ ማሰቡ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ እንደሚያመዝን አጽኖት ሰጥተው ይናገራሉ፡፡

ስለዚህ ከድብርት እራሳችን ለመካከልና ለመቋቋም ምን እናደርግ?

❖ተግባራዊ ግብ

በተደጋጋሚ ነገሮች ሳይሳኩ ሲቀሩ የድበርት ስሜት የሚከሰት ከሆነ፣ በተደጋጋሚ ላለመውደቅ ሊተገበር የሚችል ግብ ማውጣት፡፡ የነገሮች አለመሳክት ሁልጊዜ የችሎታ ማነስ፣እድለቢስነትና የሌሎች ተዛማጅ ነገሮች እጥረት ሳይሆን፤ በህይወታችን የምንሰነቃቸው ግቦች ሊተገበሩ የማይችሉና የራስ ቁጥጥራችን ደካማ ስለሆነ ሊሆን ይችላል፡፡

❖ግባችን ለመምታት አስፈላጊ ግብዓቶቸን ማፈላለግ

ተግባራዊ እቅዶችን ከነደፍን በኋላ ወደዚያ ጎዳና ለመድረስ የሚያስችሉ ግብዓቶችን ከእራሳችንንና ከአካባቢያችን ማፈላለግ፡፡ ተሰጥኦቻችንን ማበልጸግ፤ ድክመታችንን ማሻሻልና የሚጎድለንን መሙላት፡፡

❖ጽናት

ተግባራዊ ግቦችን ካስቀምጥንና ወደ አላማችን የሚያደርሱንን ግብዓቶችንን ካመቻቸንን፤ ቀጣዩ የአላማ ጽናት (persistence) ነው፡፡ ሁሌም አዲስ ነገር ሲጀመር በወረትና በመነሳሳት መንፈስ ማደርግ የተለመደ ነው፡፡ ነገር ግን ወደ ድርግጊቱ መሃል ሲገባና ጫና ሲበዛ መፍረክረክ ግባችንን እንዳናሳካ ያደርገናል፡፡ ፈተና ሊበዛ ይችናል፡፡ ነገር ግን ካለ ተግዳሮትና ፈተና የሚገኝ የቤተሰብ ውርስ ብቻ ነው፡፡ የራሳችን ነገር፣ በእራሳችን ብርታት የምንፈልግ ከሆነ ፈተናና ተግዳሮት አይቀሬ ጉዳይ ነው፡፡ ስለሆነም ከፈተናና ተግዳሮት ልምድ መቅሰምና እራሳችንን እንዲጠቅመን መቀየር ነው፡፡ ለዚህም ራስን ማዘጋጀት፡፡ ሁሉም ነገር አልጋባልጋ ይሆናል ብለን ከተነሳን፤ በኋላ ተግዳሮቶች ሲከሰቱ የመንፈስ ስበራቱ ያለምነው ግባችን ላይ እንዳንደርስ መሰናክል ይሆናል፡፡ ስለዚህ ለተግዳሮቶችና ፈታናዎች ራስን በማዘጋጀት የአይበገሬነት መንፈስ መቀናጀት፡፡

❖አንዴ አልተሳካም ማለት ህይወት አከተመላት ማለት አይደለም

ህይወት መስመሯ አባ ጎርባጣ እነደመሆኑ መጠን ዛሬ ያቀድነው ነገር አልተሳካም ማለት አጠቃላይ ህይዎታችን አለቀላት ማለት አይደለም፡፡ እንደዚህ አይነቱ አስተሳሰብ ለድበርት ስሜትና ለሌች የስነ ልቡና ችገሮች መከሰት ከፍተኛ ሚና የሚጫወት ምክኒያታዊ ያልሆነ አስተሳሰብ (irrational belief) ነው፡፡ ዛሬ ያፈቀርካትን ልጅ ስላላገኘሀት አጠቃላይ የፍቀር ህይዎትህ ዜሮ ሆነ ማለት አይደለም፡፡ ዛሬ የፈለግኸውን ስራ ስላላገኘህ የነገ መንገድህ ተቆረጠ ማለት አይደለም፡፡ ያለተሳካው ከብዙ የህይወት ግብ ውስጥ እንዱ ወይም የተወሰኑት ናቸው፡፡ ህይወት ደግሞ በአንድና ሁለት እቅድ አትመዘነም፡፡ ይህም የህይወትንና የተፈጥሮን ታላቅንት ማሳነስ ነው፡፡

❖ራስን መቆጣጠር ልምምድ ይፈልጋል

እንግዲህ ተግባራዊ ግብ ማስቀመጥና አስተሳሰባችንን፤ውስጠ ስሜታችንንና ጠባይያችንን ከዚህ ግብ አንጻር መግራት የራስ ቁጥጥር አንኳር መገለጫዎች ናቸው፡፡ የማይተገበር ግብ ማስቀመጥም ለውድቀት ይዳርጋል፤ ተግባራዊ ግብ ቢኖረንም በጽናት ጠባይያችንንና nአስተሳሰባችንን ካልገዛነውም ለውድቀት እንዳረገልን፡፡ ስለዘህ እራሳችንን የመቆጣጠር ክህሎት ለመካን ከትናንሽ ነገሮች ጀምረን እንለማመደው፡፡ ያኔ የስብእናችን ዋነኛ ምሰሶ ይሆናል፡፡

@psychoet

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 hottg.com/Psychoet

ምንጭ ፦©Zepsychology

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
የማንበብ ልምድ ያላችሁ ሰዎች እንዴት ነው ያዳበራችሁት?
ሀሙስ 21

በእራስ መተማመን
ሼር ይደረግ ጠቃሚ ትምህርት ነው
በቴሌግራም hottg.com/psychoet

ለአንድ ግለሰብ ከሚያስፈልጉት መሠረታዊ የስነ-ልቦና እሴቶች መካከል አንዱና ዋነኛው በራስ መተማመን (self confidence) ነው፡፡ ብዙዎቻችን በራስ መተማመናችን አነስተኛ ወይም ከነጭራሹ ባለመኖሩ ምክንያት ያጣናቸው ብዙ ነገሮች አሉ፡፡

ለመሆኑ በራስ መተማመን ምንድን ነው ?? በራስ መተማመንን የተለያዩ ምሁራን የተለያዩ ፍቺዎች ሰጠውታል ሆኖም ጭብታቸው ተመሳሳይ ሆኖ ስላገኘሁት አንዱን ብቻ ልንገራችሁ፡፡ ጎልማን በራስ መተማመን ማለት ይለናል በራስ መተማመን ማለት ስለ ራሳችን ችሎታ በቂ የሆነ እውቀት እና እምነት ኖሮን ከዚህ በመነሳት ደግሞ በግፊት እና በጫና ውስጥ ስንሆን ጥሩ ውሳኔዎችን መስጠት ነው ይለናል፡፡

በራስ መተማመን የራስ እውቀት እና ክብር (self esteem) እና የራስን ችሎታን የማወቅና ውጤታማ በሆነ መልኩ ነገርን እፈጽማለሁ ብሎ በራስ ላይ እመነት መጣል (self efficacy) ድምር ውጤት ሲሆን፤ በራስ የሚተማመን ሰው መገለጫዎቹም…….. ስለ ነገ ሲያስብ መልካም መልካሙ ነው የሚታየው፣ በራሱ የሚተማመን ሰው ምክንያታዊ በመሆን ምን ይመጣልን ከግምት ውጥ በማስገባት እና አደጋን በመጋፈጥ (risk taker) ኢላማውን ለመምታት የሚታትር ነው ፣ በእራሱ የሚተማመን ሰው እራሱን በትክክለኛ ደረጃ የሚወድ ነው….. ወዘተ በአንጻሩ ደግሞ በራሱ የማይተማመን ሰው ደግሞ የሚሞክራቸው ነገሮች የሚሳኩለት የማይመስሉት፣ ነገን ሲያስብ መጥፎው ብቻ እና ውድቀቱ ፈጥኖ የሚታየው፣ አቅሙን አሟጦ ለመጠቀም የሚፈራ ወዘተ… መገለጫዎች ያሉት ነው፡፡

ዛሬ በራስ መተማመናችን አነስተኛ ስለሆነ ስላጣናቸው ነገሮች ለማውራት ሳይሆን የተነሳሁት እንዴት በራስ መተማመንን መገንባት እንችላለን ወይም ያለንን አጠንክረን እንሄዳለን የሚለውን ለማየት ነው፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመንን እንዴት መገንባት እንችላለን?? የሚከተሉትን ነጥቦች አብረን እንያቸው…… መልካም ንባብ ተመኘሁ፡-

1.በራስ መተማመንህን የሚሸረሽሩ ሃሳቦችን ነቅሰህ አውጣ፡- በአዕምሮህ ውስጥ ያሉትን አልችልም፣ አይሳካልኝም፣ እወድቃለሁ እና አይሆንልኝም የሚሉ አሉታዊ ሃሳቦችን ለያቸው፡፡ እነዚህ ሃሳቦች የጨለምተኛነትን ዘር በውስጥህ በመዝራት የራስ ዕውቀትህን በማሳነስ በእራስ መተማመንህን ይሸረሽሩታል፡፡

2.አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ አዎንታዊ ቀይራቸው፡- ከላይ የተጠቀሱትን አሉታዊውን ሃሳቦች ወደ ምክንያታዊ ወደ ሆኑ አዎንታዊ ሀሳቦች ቀይራቸው ለምሳሌ እችላለሁ፣ እሞክረዋለሁ ፣ አሳካዋለሁ ወደ ሚሉ ሃሳቦች ቀይራቸው እነዚህን እራስን የማበረታቻ እና ለራስ ዕውቅና መስጫ ሃሰቦች ቀስ በቀስ አዳብራቸው፡፡

3.አዎንታዊ ሃሳቦችህን ትኩረት ስጣቸው፡- አዕምሮህ አሉታዊውን ሃሳቦች ብዙ ትኩረት እንዳይሰጠቸው ለአዎንታዊው ሃሳቦች ሰፊ ቦታና ጊዜ ስጣቸው፡፡ ለማሳካት የምታልመው ን ጉዳይ ትኩረት በመስጠት ይህን ጉዳይ ወደ ትናኝሽ ሃሳቦች በመቀየር ወደ ተግባር ግባ፡፡

4.ዙሪያህን በጥንቃቄ ቃኘው፡- በዙሪያህ ላሉ አዎንታዊ ሀሳቦችን እንድታስብና መልካም ድርጊቶችን እንድታከናውን ለሚያደርጉህ እና ለሚያግዙህ ወዳጆችህ ሰፊ ጊዜ ስጥ፣ በአንጻሩ ስለ ራስህ መጥፎ እንድታስብና ምቾት የማጣት ስሜት እንዲሰማህ ከሚያደርጉ ሰዎች እና ድርጊቶች በተቻለህ መጠን እራቅ፡፡

5.ችሎታህን ለይተህ አውጣ፡- እያንዳንዱ ሰው ቢያንስ በአንድ ነገር ላይ ጎበዝ ነው፡፡ ስለዚሀም አንተም ጎበዝ የሆንክበትን ወይም ብሰራው አሳካዋለሁ የምትለውን ነገር ነቅሰህ በማውጣት ትኩረትህን ወደእዚህ አድርገው፡፡

6.በራስህ ኩራ፡- ባሉህ አዎንታዊ እና በጎ ጎኖች ምክንያት ተገቢ እና መጠነኛ የሆነ ኩራትን ኩራ፡፡

7.ሁሌም ራስህን ሁን፡- አዳዲስ ሰዎችን ስትተዋወቅ ስለ እራስህ ውሸት በመናገር ዕውቅናን ለማግኘት አትሞክር፡፡

በራስ መተማመን ሁሌም ሚዛናዊ ሊሆን የሚገባው እሴት ነው፡፡ ዝቅተኛ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን አስቀድሞ በመፍራት ነገሮችን ከመስራት ወይም ከመሞከር ይቆጠባል አልያም ደግሞ ከመጠን ያለፈ እና ጥግ የያዘ በራስ መተማመን ያለው ሰው የሚመጣውን ነገር ሁሉ እየሞከረ ራሱን አደጋ ውስጥ ይከታል፡፡ ስለዚህ በራስ መተማመን ሁለቱን በአመክንዮአዊ ልኬት ሚዛናዊ አድርጎ መጓዝን አብዝቶ ይጠይቃል፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ……….
መልካም ቀን !
© (ቁምላቸው ደርሶ)
ክፍል 28
የአሸናፊነት ሳይኮሎጂ (ክፍል 1)
በናሁሰናይ ፀዳሉ

አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡

10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ

1. Self Projection
ይህ ማለት ወደፊት ልንሆነው ፣ ልንደርስበት እና ሊኖረን ስለምንፈልገው ነገር ጥርት ያለ እይታ / አመለካከት መኖር ነው ፡፡ የመጨረሻ መዳረሻ ግባችንን አስበን ወደዛ ለመጓዝ የምናረገውን ሂደት በአይነ ሕሊናችን መሳል / መመልከት ነው ፡፡

2.Setting Goals

ይህ ደግሞ በአይነ ሕሊናች የሳልናቸው የመጨረሻ ውጤቶች ጋር ለመድረስ የምናበጀው ግብ ነው ፡፡ የምናዘጋጃቸው ግቦች ተግባራዊ የሚሆኑ ፣ በጊዜ የተወሰኑ ፣ ሊደረስባቸው የሚችሉ ፣ ሊለኩ የሚችሉ መሆን አለባቸው ፡፡ አለበለዚያ ግቡን ማሳካት አንችልም / እጅጉን ይከብደናል ፡፡

3.Focus positive side

ፍርሀት ጭንቀትንና ውጥረትን ይወልዳል ፡፡ ፍርሀት ደግሞ በአብዛኛው የሚመነጨው ከአሉታዊ አመለካከት ነው ይህ አመለካከት ደግሞ በሕይወታችን አሸናፊዎች እንዳንሆን ይይዘናል ፡፡ ስለዚህ አሸናፊዎች ሁልጊዜም ቀና / አወንታዊ አሳቢዎች ናቸው ፡፡

4.power of self determination

ቆራጥነት ሌላው የአሸናፊነት ሥነልቡና መነሻ ነው ፡፡ ብዙ ሰው ለሚሰራው ስራ ፣ ለሚወዳደረው ውድድር ፣ ለሚያጋጥመው ፍልሚያ ቆራጥ አይደለም ፡፡ የምንሰራውን ስራ የምንሰራው ግድ ስለሆነ ፣ ገንዘብ ለማግኛ ብቻ እንጂ በሕይወታችን ደስታን ለማግኚያ አይደለም ፡፡ ስለዚህ የአሸናፊነት ሥነልቡና ለማዳበር በስራችን ቋራጥና የምናረገውን ነገር ሁሉ ለሌላ ሰው ብለን ሳይሆን ለራሳችን ብለን ማድረግ አለብን ፡፡

5.Self Awareness

በዚህ ምድር አንድም ፍፁም ሰው የለም ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ ፍፁምነት / ሁሉን አዋቂነት ሳይሆን በምንወዳደርበት ነገር ተሽሎ (በልጦ) መገኘት ነው ፡፡ ለዚህ ደግሞ ራስን ማወቅ ( ደካማና ጠንካራ ጎናችንን) ወሳኝነት አለው፡፡

የሚቀጥሉትን 5 ባህሪያት በቀጣይ እንመለከታለን ፡፡

@psychoet

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 hottg.com/Psychoet

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
«እሺ ልጄ ልትጠይቀኝ የፈለግኸው ነገር ምን ይኾን?»
. .
«አባ አኹን ላለው የአገራችን ግጭት ተጠያቂው ሕዝቡ ነው ወይስ አስተዳዳሪዎች? ቅድም ሰላም በጦርነት አይመጣም ሲሉም ነበር፤ ታዲያ ጨቋኞችና ኹሉም ነገር የኔ የሚሉ ሰዎች ባሉበት ምድር ታግለን መብታችንን ካላገኘን መብታችንን ማን እንካችኹ ይለናል?"

አባ፣ በተለመደው ርጋታቸው ንግግራቸውን ቀጠሉ፡፡

«ልጄ ሆይ፤ ሕዝብ እንደ ሕዝብነቱ ተጠያቂ አይኾንም፡፡ ለጥሩም ኾነ መጥፎ ማኅበራዊ ለውጦች ተጠያቂዎች አስተዳዳሪዎች ናቸው።

“መቶ በሬዎች ያሉት ትጉሕና ከብቶቹን የሚወድ አንድ እረኛ ነበር። በሬዎቹ ግን እንደ እረኛው መልካም አልነበሩም፡፡ ቀኑን በመስክ አሠማርቶና አብልቶ ሌሊቱን እበረታቸው ሲያስገባቸው ሙሉ አዳራቸውን እርስ በእርስ ሲጋጩ ያድሩ ነበር፡፡ በተደጋጋሚ እንቅልፍ እየነሡ ሲያስቸግሩት የራሱም ኾነ የበሬዎቹ ሰላምና ጤና ያሳስበው ጀመር፡፡ ቀን ቀን ሰላም የሚውሉት ከብቶች ሌሊቱን እሱ ሲተኛ እየጠበቁ መበጣበጣቸው ያስደንቀዋል፡፡በአንዱ ቀን ግን እረኛው የመንደሩን ጠቢብ አማካሪ ሰው አፈላልጎ በሬዎቹን ወደ ቀድሞ ዕላማቸው እንዲመልስለት ይለምነው ጀመር፡፡

«ጠቢቡም ሰው ለቀናት ካሰበበት በኋላ ጓዙን ሸክፎ ወደ እረኛው ቤት መጣ፡፡ በሬዎቹን በእረኛቸው ፊት ሲመለከት ኹሉም ነገር ሰላም ይመስል ነበር ኋላ ግን ሌሊት በበረታቸው ሳሉ የማይቀረው ግጭት ይጀምራል። ጠቢቡም እረኛው በሬዎቹን ዐሥር ቦታ ከፋፍሎ እንዲያሳድራቸው መከረው፡፡ በሬዎቹም በዐሥር በዐሥር ተከፍለው ኑሯቸውን ጀመሩ፡፡ እረኛውም ለውጣቸውን ሲከታተል ከቀናት በኋላ ሰባቱ በረት ሰላም ሲኾን፣ በሦስቱ ግን የበሬዎቹ ግጭት ይበልጥ ጨመረ፡፡

«ስለዚኽ፣ በሦስቱ በረት የሚገኙትን ሠላሳ በሬዎች በድጋሚ ከፋፍሎ በመጨረሻ የሚረብሹትን ዐምስት በሬዎች ለየ፡፡ እረኛውም በጠቢቡ ምክርና ብልኀት ተደንቆ ዘጠና ዐምስቱን ከብቶች በአንድ ላይ እንደ ቀደመው ቀላቅሎ በሰላም ያኖራቸው ጀመር፡፡

«ጠቢቡም ለእረኛው፡- ‹እነዚኽ ዐምስት በሬዎች ቀሪዎቹን ዘጠና አምስት በሬዎች ሲያበጣብጡ ነበርና አርደኽ ለጐረቤቶችኽ አብላቸውን አለው ይባላል፡፡

‹‹ልጄ ይህን ታሪክ የነገርኹኽ ከጠየቅኸኝ ጥያቄ አንጻር የሕዝቡንና የመሪዎቹን ድርሻ ላስቀምጥልኽ ነው፡፡ በምድር ላይ እስካለን ድረስ ጥሩም ኾነ መጥፎ ለውጥ የሚመጣው በመንጋ ሳይኾን፣ በጥቂት ሰዎች አስጀማሪነትና በብዙኀኑ ተከታይነት ነው።

ሜሎሪና - ቴሎስ
@psychoet
ክፍል 29
የአሸናፊነት ሥነልቡና(ክፍል 2)
በናሁሰናይ ፀዳሉ

አሸናፊነት በራሱ ባህሪይ ነው ለዛውም የምንለማመደውና የምናሳድገው ፡፡ አሸናፊነት ደግሞ የሚጀምረው ከአስተሳሰብ እንጂ ከተግባር አይደለም ፡፡ በሀሳቡ ፣ በአዕምሮው የተሸነፈ ሰው በተግባር ቢያሸንፍም ውስጣዊ ደስታ እርካታ ድልን አያገኝም ፡፡ አሸናፊነት የሚለመድ የሚታይ ባህሪይ ነው ፡፡

10ሩ የአሸናፊዎች ባህሪ

ከተራ ቁጥር 1 - 5 ያሉትን ባለፈው በዝርዝር አይተናል፡፡ ዛሬ ከተራ ቁጥር 6-10 ያሉትን እናያለን ፡፡
__
1.ል
ንሆነው/ልንደርስበት ስለምንፈልገው ነገር የጠራ እይታ / አመለካከት
2.ግብ ማስቀመጥ
3.አወንታዊ አመለካከት
4.ቆራጥነት
5.ራስን ማወቅ
__

6.
Self Esteem / ራስን ማክበር

አሸናፊ ሰዎች ለራሳቸው ትልቅ ክብርና አድናቆት ያለቸው ናቸው ፡፡ስለራሳቸው ጥሩ አወንታዊ አመለካከት አላቸው ይህ ማለት ግን ሌሎችን ይንቃሉ / አያከብሩም ማለት አይደለም፡፡ ራስን ማክበርና ሌሎችን ማክበር መነጣጠል የሌለባቸው ጉዳዮች ናቸው ፡፡ አንዳንድ ተሳካልን ፣ ትልቅ ደረጃ ደረስን አሸነፍን የሚሉ ሰዎች ከታች ያሉ ሰዎቾን የመናቅ ያለማክበር ሁኔታ ይታያል ይህ ግን ትልቅ ችግርና ያልተሟላ አሸናፊነት ብሎም ለወደፊነቱ ወደ ተሸናፊነት የሚወስድ መንገድ ነው ፡፡ አሸናፊ እራሱን ያከብራል ደግሞም ያስከብራል ብሎም ደግሞ ሌሎችን አክብሮ ያስከብራል ፡፡

7.Self Discipline / ስርአት መኖር

ይህ በተግባር የሚገለፅ የአሸናፊነት ባህሪ ነው ። በዚህ ዘመን ብዙ ሰው የወሬ እንጂ የስርአትና የተገባር ሰው አይደለም ከላይ አመራር ጀምሮ እስከታች ድረስ ብዙ ጊዜ ወሬ እንጂ ስርአትና / ተግባር አይታይም ፡፡ ጠንካራ ልምምዶችን እንደ ልምድ አድርጎ በተግባር አለመግለፅ አሸናፊ እንዳንሆን ያረገናል ፡፡ ለምሳሌ እግር ኳስ ተጫዋቾችን ብንመለከት ልምምዳቸውን በየጊዜው በስርአት ካልሰሩ ብዙ ሽንፈት ሊገጥማቸው ይችላል ፡፡

8.Self Talk / ከራስ ጋር ማውራት (ጊዜ መውሰድ)

አሸናፊዎች ሁልጊዜ የሚራራጡ ፣ እረፍትና እርጋታ የሌላቸው ፣ ሁሌ ሳያቋርጡ የሚሰሩ አይደሉም ፡፡፡ይልቁንስ በቂ ሰአት ስራቸው ላይ የሚያጠፉ እንዲሁም ተመጣጣኝ ጊዜ ደግሞ ለራሳቸው የሚሰጡ ፣ ነገሮችን በትኩረት ረጋ ብለው የሚያስቡ (ሳይጨነቁ ነገሮችን የሚያወጡ የሚያወርዱ) ናቸው ፡፡ ከራሳቸው ጋር በቂ ጊዜ የሚወስዱ ሰዎች ሁሌ ከውጥረት ብሎም ከጭንቀት ራሳቸውን ያስመልጣሉ ፡፡

9.Complete person / ሙሉ ሰውነት

ትክክለኛ አሸናፊ ሰው አንድ ወገን ብቻ ያደገ ፣ ሌላው ጎኑ የጎደለ ሳይሆን በሙሉ ማንነቱ የሞላ ያሸነፈ ነው ፡፡ ሕይወት ትምህርት ጥሩ ውጤት ማምጣት / ሩጦ 1ኛ መውጣት ፣ ተዋግቶ ማሸነፍ ፣ በሀብት ትልቅ ደረጃ መድረስ ብቻ አይደለችም ፡፡ አንዳንድ ሰው በገንዘብ አቅሙ ትልቅ ደረጃ ይደርስና በማህበራዊ ሕይወቱ ደግሞ 0 ይሆናል ፡፡ እንደዚህ አይነት ሰው ሙሉ ሰው አንለውም ፡፡

#ሙሉ ሰውነት ላይ ወደፊት ሰፋ ያለ ማብራሪያ ይዤ እቀርባለሁ ፡፡

10.Live in the present/ አሁንን መኖር

ይሄ ብዙዎች አሸናፊ እንዳይሆኑ የሚያረግ የአመለካከት ችግር ነው ፡፡ ነገራችንን በሙሉ በነገ ተስፋና በትናንት ፀፀት / ወቀሳ ዛሬ ላይ በደንቡ ሳንኖር በሀዘን እንዘልቃለን ፡፡ አሁንን በአሸናፊነት ሀሳብ/ አመለካከት ሳንኖር የነገን ያልተጨበጠ ድል በማለም በተስፋ ብቻ እንደክማለን ፡፡ ስለዚህ አሸናፊ ለመሆን የሚያስብ ሰው አሸናፊነት ስለ ነገና ስለ ወደፊት ሳይሆን ስለ አሁን ነው ፡፡


አሸናፊነት የሚጀምረው ከአስተሳሰብ ነውና አስተሳሰባችሁን ቀና ፣ በጎ ፣ ጥሩ ጥሩውን ማድረግ ጀምሩ ፡፡ አሉታዊ አስተሳሰባችሁን በአወንታዊ ሀሳቦች ለውጡ ፡፡

ይቀጥላል...

#መልካም_ቀን!
@Psychoet

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 hottg.com/Psychoet

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
ክፍል 30
የአሸናፊነት ሕይወት (ክፍል 3)
በናሁሰናይ ፀዳሉ

በእርግጥ አሸናፊነት በዋነኛነት ከራሳችን ጋር የሚደረግ ውድድር ቢሆንም በሕይወት ዘመናችን ግን ብዙ ከሌሎች ሰዎች ጋር የሚደረጉ ውድድሮች ይኖሩናል ፡፡ ለምሳሌ ፦ በትራክ / በጎዳና የሚሮጡ እሯጮች የሚያሸንፋት ከሌሎች ተወዳድረው ቀድመው በመግባት እንጂ ከራሳቸው ጋር ተወዳድረው አይደለም ።
እግር ኳስ ተጫዎቾች አሸናፊ የሚባሉት ከሌሎች ተጋጥመው በሚያስቆጥሩት የበለጠ ጎል እንጂ ባላቸው የኮከብ ተጫዎች ብዛት አይሆንም ፡፡

በጦር ሜዳ ላይም የሚደረግ ፍልሚያ አሸናፊው ማን የበለጠ የጠላትን ድንበር / ወሰን ተቆጣጠረ / ብዙ ሰው ማረከ በሚል ነው ፡፡

በትምህርት ገበታችን 1 ኛ ወጣን የምንለው ከሌሎች በልጠን እንጂ 100 ስላመጣን አይደለም ፡፡

በንግድ ቦታ አሸናፊ የምንሆነው ከሌሎች ተመሳሳይ ነጋዴዎች የተሻለ ብዙ ደንበኛ ፣ ብዙ ሽያጭ ፣ ጥሩ ገቢ ስናገኝ ነው ፡፡

ስለዚህ አሸናፊነት ውድድርም መሆኑን መገንዘብ አለብን ስለዚህ በነዚህ ውድድር እንድናሸንፍ ማረግ ካለብን ዋነኛ ነገሮች ጥቂቱት እንመልከት

1. ራሳችንን እንወቅ፦

ይሄ ዋናውና መሰረታዊው ነገር ነው ፡፡ አብዛኞቻችን ራሳችንን ደካማና ጠንካራ ጎናችንን ምን መስራት ፣ የት መስራት እንዳለብን በደንብ ስለማናውቅ መወዳደር በሌለብን ዘርፍ ስንወዳደር እንገኛለን ፡፡ ከዛም ሁሌ የምንፈልገውን / ያሰብነውን ውጤት ሳናመጣ እንከርምና መጥፎ የተሸናፊነት ስሜት ይሰማናል ፡፡

ለምሳሌ ፦ ጥሩ እግር ኳስ ተጫዎች ሩጫ ቢወዳደር አይደለም ማሸነፍ ላይጨርሰው ይችላል ፡፡ ራሱንና ችሎታውን አውቆ እግሮ ኳስ ቢጫወት ጥሩ ውጤት ሊያመጣ ይችላል ፡፡

ራሳችንን ለማወቅ ማረግ ያለብን ነገሮች በጥቂቱ
ሀ.መጸሐፍቶችን ማንበብና ዕውቀትን ማሳደግ
ለ. በዚህ ጉዳይ ያተኮሩ ስልጠናዎችን መውሰድ
ሐ. ተረጋግቶ ስለ እራስ ማሰብና ለራስ በቂ ግዜ መስጠት
መ. ሌላ በዘርፉ የተሻሉ ሰዎችን ማማከር ...


ከዚህ ቀጥሎ ያሉትን በቀጣዩ ክፍል አብራራቸዋለሁ _
2. ተጋ
ጣሚያችንን እንወቅ፦
3.ራሳችንን እናሻሽል
3. ካለንበት ምቹ የሚመስል የተለመደ ቀጠና እንውጣ፦
4. አሸናፊነት ያማልና ራሳችንን ለሕመም እናዘጋጅ፦
_

ይቀ
ጥላል...

#መልካም_ቀን!
@Psychoet

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉

ቴሌግራም ሊንክ 🚙 hottg.com/Psychoet

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
#የሳምንት_ሰው_ይበለን !

🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊🎉🎀🎊
HTML Embed Code:
2024/04/20 01:31:22
Back to Top