TG Telegram Group Link
Channel: አንዲት እምነት ✟✟✟
Back to Bottom
ሊቀ ካህናቱ በትህትና ቆሞ የሚያገለግልባት ቅድስተ ቅዱሳንም ሰማያዊው እና መለኮታዊው ሊቀ ካህናት ቆሞ ሳይሆን ተቀምጦ ምሕረትን የሚያስገኝባት "የጸጋ ዙፋን" ሆነች። (ዕብ. 4፥16)
እንግዲህ ቀድሞ በምድር ላይ ኃጢኣት ስንሠራ የሚያስታርቁን፣ ጠላት ሲያይልብን ከእግዚአብሔር ረድኤት የሚያሰጡን የሚማልዱልን ነቢያትና ካህናት ነበሩን፤ አሁን ግን ያ ሁሉ ካለፈ ምን እንሆናለን? እግዚአብሔር ያለ አማላጅ እና መካከለኛ ትቶናል? ከእግዚአብሔር ጋር ማን ያገናኘናል? እንደ ነቢያቱ (ምሳሌ ሙሴ) እና እንደ ሊቃነ ካህነቱ መካከለኛ ማን ይሆነናል? ብሎ የሚጨነቅ እንዳይኖር በመዝሙሩ "ጠላቶችህን የእግርህ መረገጫ እስካደርግልህ ድረስ በቀኜ ተቀመጥ" ተብሎ የእግዚአብሔር አዳኝነት ተነገረ። በዚህም የክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጥ ጠላቶቹ (የምዕመናን ጠላቶች) ድል የሚሆኑበት፣ በመስቀሉ የተገለጠ ፍቅሩ እና ኃይሉ ያለማቋረጥ የሚሠራበት የረድኤት እና የጸጋ ዘመን እንጂ እግዚአብሔር ዝም ብሎ ቁጭ ብሎ (passively) የሚያይበት እንዳልሆነ ያመለክታል። በምዕመናን ላይ መከራ የሚያጸኑት ለክርስቶስ "ጠላቶቹ" መባላቸው እግዚአብሔር ምዕመናንን የሚጠብቀው ስለ ክርስቶስ (አካሉ ስለሆንን) እንደሆነ ያሳያል። "ይማልዳል" መባሉ ጸጋውን እና ረድኤቱን ሁሉ በእርሱ ምክንያት የምናገኘው በመሆኑ ነው። አብ በልጁ ፍቅር ይጠብቀናል፤ አካሉ ያደረገን የወልድ ፍቅርም የመለኮታዊ ረድኤት ምንጭ ነው። (ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
በዮሐንስ መልእክትም "በአብ ዘንድ ጠበቃ አለን" የሚለው በሌላ መንገድ ቢነገርም ያው ነው። "በአብ ዘንድ" ማለት "በአብ ቀኝ የተቀመጠ" ማለት ነው።
ቅዱሳት መጻሕፍት ስለ ክርስቶስ "ምልጃ" ሲናገሩ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡን ሁሌ የሚነግሩን እንደ ቅዱሳን ምልጃ ያለ ልመና አለመሆኑን፣ ይልቁንም አዳኛችን ክርስቶስ የእኛን ሥጋ ተዋሕዶ በዙፋኑ ላይ መቀመጡ ከእግዚአብሔር ዘንድ የጸጋ እና ረድኤት ምንጭ መሆኑን ጥልቅ በሆነ ዘይቤ (metaphor) የሚገልጽ ምስጢር ነው። ከፍቅሩ የተነሣ አካሉ ያደረገን እርሱ መድኃኒታችን ክርስቶስ በእግዚአብሔር ቀኝ መቀመጡ ምልጃ ሁሉ ሊያስገኘው የሚችለውን ጸጋ እና ረድኤት አስገኝቶአል፤ ያለማቋረጥም ያስገኛል።
ታዲያ ቅዱሳን ለምን ይማልዳሉ? የሚል ይኖራል። ይህ ከመነሻው የተሳሳተ ጥያቄ ነው። ቅዱሳን የሚማልዱት የክርስቶስ ተከታዮች ስለሆኑ ነው። በዙፋኑ ላይ ሆኖ ሁሉ መዳንን ይወርሱ ዘንድ የሚሻው እና የጸጋ ሁሉ ምንጭ የሆነው የእርሱ መንፈስ ጰራቅሊጦስ ስላደረባቸው ነው። (መንፈስ ራሱ "ይማልዳል" እንደተባለ አንርሳ) እሱ ሁሉን ስለሚወድ እና ሁሉን ስለሚሰጥ እኛ ለምን ሰውን እንወድዳለን? ለምንስ መልካም እናደርጋለን? ብሎ እንደመጠየቅ ነው። የክርስቶስ መካከለኝነት እና የቅዱሳን ምልጃ ለአንዳንዶች ቢጣላባቸውም ለታላቁ ሐዋርያ ለቅዱስ ጳውሎስ አልተጣላበትም፤ "በእግዚአብሔር እና በሰው መካከል ያለው 'መካከለኛ' አንድ ነው፤ እርሱም ሰው የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤" ባለበት ቦታ "ልመናና ጸሎት ምልጃም ምስጋናም ስለ ሰዎች ሁሉ ስለ ነገሥታትና ስለ መኳንንትም ሁሉ እንዲደረጉ ከሁሉ በፊት እመክራለሁ፤" ብሎ አስተምሮአልና። (1ኛ ጢሞ. 2፥1-2)
***
ለማጠቃለል ያህል በአዲስ ኪዳን መጻሕፍት የተነገረው ይህ ጉዳይ ከፊደል የሚያልፈው ድንቅ ምስጢሩን መረዳት ይገባል። ቀድሞ እነ አርዮስ ክርስቶስን ፍጡር ለማለት እነዚህን ጥቅሶች ይጠቅሷቸው ነበር። (St. Athanasius, Against the Arians, Discourse IV) ሌሎችም ሰውነቱን ነጥሎ ለማየት እና ሁለት ባሕርይ ለማለት ይጠቅሷቸዋል። የቅርቦቹ ደግሞ የቅዱሳንን ምልጃ እና ክህነትን ለመቃወም እንዲሁም ሌሎች ድብቅ የሆኑ ነገረ-ክርስቶሳዊ እሳቤዎችን (latent Arianism and Subordinationism) ለማንጸባረቅ ይጠቅሷቸዋል። ይህ ሁሉ ስለሆነ ግን ጤነኛ መልእክታቸውን አንጥልም። ከሐዋርያዊ ትምህርትም አንቀንስም። በትክክለኛ ዓውዳቸው መረዳት ይገባናል እንጂ። ሥጋ ባለበት አሞራዎች ይሰበሰባሉ እንደተባለው ብዙ ውዝግብ የሚበዛባቸው ጥቅሶች ጠለቅ ብለን ስናያቸው ድንቅ መልእክት ያላቸው ናቸው።
(እነዚህን ጥቅሶች መና*ፍ*ቃ*ን አብዝተው ስለሚጠቅሳቸው እንዳንጥላቸው እና እንዳንጠላቸው ይልቁንም ከፊደላቸው አልፈን መንፈሳቸውን በመረዳት እንድንጠቀምባቸው ይህ ተጻፈ።)

Dn Bereket Azmeraw
"ስለ አንተ ድክመት የሚነግርህን ጥሩ #ባልንጀራ አድርገህ ያዘው።"

•• ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
👆👆👆👆👆
ሃይማኖት እና እምነት
* ሃይማኖት ምንድን ነው?
* እምነት ምንድን ነው?
* የእምነት አይነቶች በመጽሀፍ ቅዱስ
ሃይማኖት አያስፈልግምን ?
* ክርስትና ሃይማኖት አይደለምን?
* ድህነት በሃይማኖት አይደለምን?
* በሞተልን ጌታ የምንገኘው እንዴት ነው?
* ወንጌል በየትኛውም ሃይማኖት ቢሰበክ ችግር የለውምን?
* ዶግማ ማለት ምን ማለት ነው?
* ኦርቶዶክስ ተዋህዶበሰው የተመሰረተች ነችን?
* የሃይማኖት ክፍልፋይ ስም ነው ችግራችን? ወይስ የመጽሀፍ ቅዱስ አረዳድ?
* የመጽሀፍ ቅዱስ ክርስትና እንደምን ያለ ነው?
* በሃይማኖቶች መካከል ያለው የአስተምህሮ ልዩነት ችግር የለውምን?

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
"God so loved you; for this reason He brought you into being. God so loved you, for this reason He created you in the best image; He created you in His image. He gave you understanding, wisdom, spirit, immortality, beauty in all things"

+ Pope Shenouda +

"እግዚአብሔር እንዲሁ ወዶሃልና፤ ስለዚህም ወደ መኖር አመጣህ። እግዚአብሔር እንዲሁ ወዶሃልና፤ ስለዚህም በመልካሙ መልክ (ምስል) ፈጠረህ፤ በመልኩ በአምሳሉ ፈጠረህ። ማስተዋልን፣ ጥበብን፣ መንፈስን፣ ዘላለማዊነትን፣ በሁሉም ነገር ውበትን ሰጠህ።"

+ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ሺኖዳ +
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
                        †                          



[ ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ! ]



         †              †               †
▬▬▬▬ ▬▬▬▬▬ ▬▬▬▬
ኑፋቄ (በዲያቆን ያረጋል አበጋዝ) (1).pdf
330.5 KB
ኑፋቄ

* ኑፋቄ ምንድን ነው?

በዘመናት የነበሩ ዋና ዋና መናፍቃንና ኑፋቄያቸው በአጭሩ

* ግኖስቲኮች/ ኖስቲኮች
* አርዮስ
* ንስጥሮስ
* ሄልቪዲየስ
* ጆቪኒያን
* ቪጂላንቲየስ
* አርዮስ ዘቴባስቴ
* ማርቲን ሉተር

#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
የአውስትራሊያው ታዋቂ የአሦሪያ ጳጳስ የግድያ ሙከራ፣ መ*ና*ፍ*ቁ ንስጥሮስ እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች (እንደወረደ)
++++++
(ቀሲስ ኤፍሬም እሸቴ)
ሀ/ መነሻ
የሰኞ የብዙዎች መነጋገሪያ ርዕሰ ጉዳይ የነበረው በአውስትራሊያ የሚገኙ የአሲሪያ ቤተ ክርስቲያን ጳጳስ ላይ በቤተ መቅደሳቸው እንዳሉ የተፈጸመባቸው የመግደል ሙከራ ነው። ጳጳሱ በቀጥታ ሥርጭት በሚተላለፈውና በመላው ዓለም ያሉ በሺህዎች የሚቆጠሩ ተመልካቾቻቸው በሚከታተሉት ዝግጅት ላይ ነው በስለት የመግደል ሙከራ የተደረገባቸው። አንድ በወጣትነት ዕድሜ ላይ የሚገኝ ሰው ጳጳሱን በስለት ደጋግሞ ሲወጋቸው በቪዲዮው ይታያል። ከእርሳቸውም በተጨማሪ በቤተ መቅደሱ የነበሩ ሌሎች ሰዎች አደጋ ደርሶባቸዋል::
እኒህጳጳስ በፌብርዋሪ ወር 2024ም ተመሳሳይ በስለት የመግደል መኩራ ተደርጎባቸው ተርፈዋል፡፡ በፊብሩዋሪ ወንጀሉን የፈጸመው የ 15 ዓመት ወጣት እንደነበር መገለጹ ይታወሳል።
ዛሬ የተፈጸመባቸው የመግደል ሙከራ በጣም አሳዝኖኛል፣ አስደንግጦኛልም:: በርግጥ ወንጀሉን የፈጸመው ሰው ማንነት ግልጽ ባይሆንልኝም ከሊበራሉ ዓለም እስከ አክራሪ ጽንፈኞች ድረስ ጥቃት ሊያደርሱባቸው የሚችሉ ሰዎች እንዳሉ መገመት ይቻላል። በትምህርታቸው ጠንካራነት ምክንያት። በቅርቡ እንኳን እሥራኤል በጋዛ ፍልስጥኤማውያን ላይ የምትፈጽመውን ጥቃት የተቃወሙበትን ንግግር ተመልክተናል። ይህንን ጽሑፍ እስከጻፍኩበት ሰዓት ድረስ የአውስትራሊያ ፖሊስ ወንጀሉን የፈጸመውን ሰው ማንነት እና ወንጀሉን ለመፈጸም የገፋፋውን ምክንያት አልገለጸም።
ለሁሉም ግን እንኳን እግዚአብሔር አተረፋቸው፡፡ አሁንም ቶሎ አገግመው ወደር ወደሚወዱት አገልግሎት እንዲመለሱ ምኞቴ ነው።
++++
ለ/ ጳጳሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል (Bishop Mar Mari Emmanuel) ማን ናቸው?
----------
ማር ማሪ ኢማኑኤል በአውስትራሊያ የሚገኘው የ"Assyrian Church" ሊቀ ጳጳስ ሲሆኑ መልካም እረኛ ቤተ ክርስቲያን (Christ The Good Shepherd Church) በተባለ ሥፍራ ያገለግላሉ። በ2009 (እ.አ.አ) ቅስናን፣ በ2011 ደግሞ ጵጵስና መቀበላቸውን ታሪካቸው ያሳያል።
ጳጳሱ ማር ማሪ ኢማኑኤል በስብከቶቻቸው የሚያነሧቸው ጉዳዮች በብዙ ሰው ዓይን ውስጥ እንዲገቡ ያደረጋቸው ይመስላል። በዘመነ ኮሺድ በመላው ዓለም የተጣለውን ከቤት ያለመውጣት እግድ በጽኑዕ በመቃወማቸው ይታወቃሉ። ከዚያም ቀጥሎ በአሜሪካ እና በሩሲያ ፖለቲካዊ ጉዳዮች ላይ የሚሰጧቸው ሐሳቦች በተለይም በሊበራሉ ዓለም "አክራሪ" አሰኝቷል። የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ባይደን "የተመረጡት በሕቡዕ ቡድኖች ይሁንታ ነው" ማለታቸው እንዲሁም "ግ*ብ*ረ ሰ*ዶ*ማ*ዊነት"ን በጽኑዕ መቃወማቸው ጠላት ያፈራባቸው ይመስላል።
ታዋቂነታቸው ከእንግሊዝኛ ተናጋሪው አልፎ ወደ ኢትዮጵያ እና ኤርትራ ኦርቶዶክሳውያን ዘንድም ደርሷል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ ስለ ጳጳሱ ያወቅኹት ስለ ቤተ ክርስቲያኒን ጠንካራ ትችት ያቀረቡበትን እና ቤተ ክርስቲያን "ንስሐ ግቢ" የሚል መንፈስ ያለው አጭር ቪዲዮ አይቼ ነው። "እንዴ!!! ቤተ ክርስቲያን ኃጢአት የማይስማማት የክርስቶስ አካሉ መሆኗን የደፈጠጠ የምዕራቡ ዓለም ፕሮ*ቴስ*ታን*ቲዝም ትምህርት የሚናገር ጳጳስ ከየት ተገኘ?" ብዬ ተገርሜ ነበር። የግብጽ/ቅብጥ ጳጳስ መስለውኝም ነበር። ኋላ ነው የአሦር ኦርቶዶክስ ጳጳስ መሆናቸውን የተረዳኹት። ብዙ ኦርቶክሳውያን የተዋሕዶ ልጆች ስብከቶቻቸውን ሼር ሲያደርጉ "የተዋሕዶ ጳጳስ መስለዋቸው ይሆን?" እል ነበር።
+++++
ሐ/ ስለ ምሥራቅ አሦሪያ ቤተ ክርስቲያን በመጠኑ
---------
1/ ሙሉ ስማቸው:-
## The Assyrian Church of the East (ACOE)፤
## የፓትርያርኩ መቀመጫ (መንበረ ፓትርያርኩ) ሰሜን ኢራቅ ኢርቢል (Erbil) ነው።
2ኛ/ ሌሎች ሰዎች "ንስጥሮሳዊት ቤተ ክርስቲያን" (the Nestorian Church) ይሏቸዋል። በኤፌሶን ጉባዔ የተወገዘውን የንስጥሮስን አስተምህሮ የሚቀበሉ ቢሆንም ንስጥሮሳውያን መባል አይፈልጉም። ከጽርፈት (ስድብ) ይቆጥሩታል።
3ኛ/ ራሳቸውን "ኦርቶዶክስ" ብለውም አይጠሩም:: በየትኛውም ጽሑፋቸው ላይ "ኦርቶዶክስ" የሚል ቃል አይጠቀሙም። ነገር ግን ብዙ ሰዎች የኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት በተለይም የተዋሕዶዎቹ "የኦሪየንታል አብያተ ክርስቲያናት" አካል አድርገው ይቆጥሯቸዋል። ስሕተት ነው።
4ኛ/ Assyrian Church of the East (branch of Syriac Christianity) ከሚባሉት ውስጥ በ1870 የተለዩት/ የተገነጠሉት "The Chaldean Catholic Church" ከሮማ ካቶሊክ ጋራ ውሕደት ፈጽመዋል። በ1994 ባደረጉት ውሳኔ በነገረ ክርስቶስ ላይ ያላቸውን አስተምህሮም ከሮማ ካቶሊክ ጋራ አንድ አድርገዋል። መንበረ ፓትርያርካቸውም ኢራቅ ባግድዳ ነው። የቅዳሴ ቋንቋቸው ግን ልክ እንደሌሎቹ የሲሪያክ ይትበሐል አብያተ ክርስቲያናት ሁሉ አሁንም "አራማይክ" ነው።
መ/ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎቹ የሦሪያ ክርስቲያኖች
—-------------
ሙሉ ስማቸው The Syriac Orthodox Church ይባላል፤
West Syriac Church ወይም West Syrian Church ይባላሉ፣
በመደበኛው (official) አጠራራቸው ደግሞ the Syriac Orthodox Patriarchate of Antioch and All the East ይባላሉ፤
በኢመደበኛ (informal) አነጋገርም ቢሆን (the Jacobite Church) ያዕቆባዊት ቤተ ክርስቲያን ይባላሉ። በትምህርቱ እና በተቀበለው ሰማዕትነት ቤተ ክርስቲያኗን በተዋሕዶ እምነቷ ባጸናት በሊቀ ጳጳሱ በቅዱስ ያዕቆብ ዘእልበረዲ (Jacob Baradaeus ወይም Jacob bar Addai) ስም ይጠራሉ።
የቅዳሴ ቋንቋቸው አራማይክ ሆኖ ይትበሐሉ ግን "የምዕራብ አራማይክ (West Syriac)" ነው።
ንስጥሮሳውያኑ "የምሥራቅ አራማይክ" ይትበሐል ተከታዮች መሆናቸውን ከላይ መግለጻችንን ልብ ይሏል።
የሕንድ ማላንካራ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶዎች የነዚሁ የያዕቆባውያን ኦርቶዶክሶች አካል ናቸው።
++++++
ሠ/ መ*ና*ፍ*ቁ ንስጥሮስ እና የኤፌሶን ጉባኤ (431 ዓ.ም)
—------
ጉባኤ ኤፌሶን በ431 ዓ.ም በኤፌሶን ከተማ በ200 ሊቃውንት የተካሄደ ታላቅ ጉባዔ ነው፡፡ የስብሰባው መሪ ቅዱስ ቄርሎስ ነበር፡፡
የስብሰባው ዋና ምክንያት የንስጥሮስ ክህደት ነው፡፡
የንስጥሮስ ክህደቱም "ቃል ከሥጋ ጋር አልተዋሐደም። ሰው አልኾነም። አምላክም ሰው የሆነው በኅድረት ነው፡፡ ኅድረት ማለትም እመቤታችን የወለደችው ሰውን ብቻ ነው፡፡ ማርያም በወለደችው ሰው ላይ የእግዚአብሔር ቃል አደረበት (ሕድረት)፤ ስለዚህ እርሷም ወላዲተ አምላክ አትባልም" የሚል ነው፡፡
ንስጥሮስን ተከራክሮ የረታውና መልስ ያሳጣው እስክንድርያዊው ሊቀ ጳጳስ ቅ/ቄርሎስ ነው፡፡
የንስጥሮስን የክህደት ትምህርት በመሠረዝ እመቤታችን "እመአምላክ ወላዲተ አምላክ፣ እመ እግዚአብሔር (Mother of God, Theotokos)" መሆኗን እናምናለን፣ እናሳምናለን፣ እናስተምራለን።
ንስጥሮሳውያን እና የነርሱን ትምህርት የሚከተሉ አንዳንድ ፕ*ሮ*ቴስ*ታንቶች ዛሬም ድረስ Mother of Jesus እንጂ Mother of God አይሉም።
* ቅዱስ ቄርሎስ ለንስጥሮስ ሲመልስ፦ "ወልድ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማይመረመር ተዋሕዶ ሰው የኾነ አምላክ ነውና ቀዳሚ ሲኾን ከዘመናት አስቀድሞ ከአብ የተወለደ ነው! ዳግመኛም ከድንግል ማርያም በሥጋ የተወለደ ነው" ብሏል /ሃይማኖተ አበው 73፣4 ገጽ 271)
+++++
ረ/ ቃል ሥጋ ሆነ፤ ዘእንበለ ሕድረት (ያለማደር)
==============
የንስጥሮስ ክህደት የሆነው "ሕድረት" የሚለው ነው።
ሕድረት ማለት አንድ አካል በሌላ አካል ውስጥ ገብቶ ማደር ማለት ነው። ለምሳሌ መጽሐፍ ማሕደር ውስጥ ያድራል፤ ሰይፍ ሰገባ ውስጥ ያድራል።
በሕድረት ጊዜ አዳሪውና ማደሪያው በባሕርይ አይዋሐዱም።
ቃል ሥጋ የሆነው ግን በሕድረት አይደለም። ቃል ሥጋ ውስጥ አደረ ከተባለ ሥጋ ለቃል ማሕደሩ፤ ልብሱ፤ መቅደሱ ሆነ እንደማለት ነው። ይህ ማለት ደግሞ ባሕርያዊ ተዋሕዶ አልተፈጸመም እንደማለት ነው።
ቃል ግን ሥጋ ሲሆን የቃል ገንዘቡ ሁሉ ለሥጋ፤ የሥጋም ገንዘብ ሁሉ ለቃል ሆኗል። ስለዚህም ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በፍጹም ተዋሕዶ ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ፍጹም ሰው ፍጹም አምላክ ሆነ እንላለን።
ሰ/ የኢንተርኔት ላይ ክርስትና
—-----
ኢንተርኔቱ በጠቅላላው በተለይ ማኅበራዊ ሚዲያው ሃይማኖታችንን ለማወቅ፣ ለመጠበቅና ለማስፋፋት ይረዳል። ነገር ግን በነባራዊው ዓለም እንዳለው ሕይወታችን ተመልካች፣ መሪ፣ ተቆጪ፣ ተጠያቂ ስለሌለበት ለሃይማኖታዊ ፈተና ሊያጋልጠን ይችላል። ኑ*ፋ*ቄዎች ትክክለኛ ትምህርት፣ የተሳሳቱ መምህራንም ቀና እምነት የሚያስተምሩ መስለው ብዙዎችን ሲያሳስቱ እናያለን። ስለዚህ ራሳችንን ከቀጥተኛዋ የተዋሕዶ ትምህርት ውጪ ሆነን እንዳናገኘው ጥንቃቄ እናድርግ።
ይቆየን!!!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ይሄን እያዬ የሚከራከር ካለ ጤንነቱ 😁ያሳስበኛል ይሄን ሰውዬ መናፍቅ አይደሉም የሚል
ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ህይወቱና_ትምህርቱ_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
214.8 KB
ወደ ቤተ ክርስቲያን ስላልመጡ ምዕመናን

የሚያስጨንቅህ የዚህ ዓለም ጉዳይ አለብህ? እዚህ በምታሳልፈው ጊዜ የእግዚአብሔርን ርዳታና ምሕረት ታገኝ ዘንድ፣ በመረጋጋትና በመጽናናት መንፈስ ሆነህ ትሄድ ዘንድ ስለዚህ ምክንያት ወደዚህ ና፡፡ እርሱ ኃይልሀና ጋሻህ ይሆን ዘንድ፣ በሰማያዊ ሥልጣን በመጠበቅ ለጠላቶችህ ለአጋንንት የማትሸነፍ ትሆን ዘንድ ወደዚህ ወደ ጸጋው ዙፋን ና፡፡ በአባቶች ከሚደርሰው ጸሎት ሱታፌ ካለህ፣ በማኅበር ጸሎት ከተሳተፍክ፣ ቅዱስ የሆነውን የእግዚአብሔርን ቃል ከሰማህ፣ የእግዚአብሔርን ርዳታ ካገኘህ፣ እነዚህን መሣሪያዎች ከታጠቅህ የትም ብትሄድ እንዳንተ ያሉ ሥጋ የለበሱ ጠላቶችህ ክፉዎች ሰዎች ይቅርና ዲያብሎስ ራሱ ፊትህን ማየት አይችልም፡፡ ነገር ግን ከቤትህ እንደ ተነሣህ ወደ ቤተ ክርስቲያን ሳትመጣ ወደ ገበያ፣ ወደ ሥራ፣ ወዘተ ብትሄድ ብቻህን ያለ ምንም መንፈሳዊ ትጥቅና ጸጋ እግዚአብሔር ስለምትሆን ሁሉም ነገር በአንተ ላይ ይበረታብሃል፤ ጠላቶችህም በቀላሉ ያጠቁሃል

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ_ህይወቱና_ትምህርቱ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
የእግዚአብሔር ምሕረት ያስደንቃል። ያደረግነውን ብቻ አይደለም ይቅር የሚለን። የማይገባንን ገነትም ይሰጠናል!!!
ሕይወት ሌሊት ሆና ጉዞዋ ሲከብደን እንደ ኒቆዲሞስ ወደ ጌታችን እንገስግስ፥ "ጨለማ በአንተ ዘንድ ከቶ አይጨልምምና" እንዳለ መዝሙረኛው ቅዱስ ዳዊት፥ እኛን ያስጨነቀን ጨለማ በእርሱ ፊት ምንም ብርታት የለውም። ሌሊታችንን ብሩህ የሚያደርግ ፀሐይ ክርስቶስ አለን።

ዲያቆን እስጢፋኖስ ግርማ
ሚያዝያ 14 | 2016 ዓ.ም.
ለካህን_መናዘዝና_ቀኖና_መቀበል_ለምን_በዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ.pdf
333.1 KB
ለካህን መናዘዝና ቀኖና መቀበል ለምን?

* የተሐድሶዎች ትምህርት ለካህን ስለመናዘዝና ቀኖና ስለመቀበል
* በዚህ ጉዳይ ላይ የተሐድሶዎች መሠረታዊ ስህተቶች
* ለንስሐ አባት መናዘዝና ቀኖና መቀበል በመፅሀፍ ቅዱስ ትምህርት
* ቀኖና የሚሰጥባቸው ምክኒያቶች
* ንስሐ አባትና ቀኖና በአበው ትምህርት

“ነቢዩ ናታን ንጉሥ ዳዊትን ኃጢአቱን ከነገረው በኋላ ወዲያውኑ ኃጢአቱን እንዳመነ አጽናንቶት ነበር፡፡ ሆኖም ብፁዕ ዳዊት ግን ምንም እንኳ እግዚአብሔር ደግሞ ኃጢአትህን አርቆልሃል፡ ኣትሞትም' (2 ሳሙ. 12፡13) የሚለውን የነቢዩን ቃል የሰማ ቢሆንም ንስሐ ከመግባት ግን አልተመሰለም፡፡ ንጉሥ የነበረ ቢሆንም በልብሰ መንግሥት ፋንታ አመድ ለበሰ በወርቅ ዙፋን ላይ በመቀመጥ ፋንታ በመሬት ላይ፣ ያውም በአመድ ላይ ተቀመጠ፡፡ በአመድ ላይ የተቀመጠ ብቻ ሳይሆን አመድንም ምግቡ አደረገ፤ እርሱ ራሱ “አመድን እንደ እህል ቅሜያለሁና፣ መጠጤንም ከእንባዬ ጋር ቀላቅያለሁና” (መዝ 101፡9) ብሏልና፡፡ ወደ ኃጢአት የተመለከተው ዓይኑ በዕንባ እስኪሟሟ ደረሰ፤ “ሌሊቱን ሁሉ አልጋዬን አጥባለሁ፣ በዕንባዬም መኝታዬን አርሳለሁ፤ ዓይኔ ከቍጡ ዕንባ የተነሣ ታወከች” እንዳለ፡፡ መዝ. 6፡6-7 መኳንንቱ እህል እንዲቀምስ በለመኑት ጊዜ እንኳ አልሰማቸውም፡፡ ጾሙን እስከ ሰባት ሙሉ ቀናት አራዘመ፡፡ ንጉሥ የነበረው እርሱ እንዲያ ባለ ሁኔታ ንስሐ ከገባ ተራ ግለሰብ የሆንከው አንተ ንስሐ ልትገባና ልትናዘዝ አይገባህምን?” (ቅዱስ ቄርሎስ ዘኢየሩሳሌም፣ ትምህርት 2 በእንተ ንስሐ ወሥርየተ ኀጢአት፣ ቁ 12)


#መድሎተ_ጽድቅ

#ዲያቆን_ያረጋል_አበጋዝ
🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ አንድ የሚገርም የ Forex  ቻናል ያውቃሉ

💶  𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶

@City_Forex_Ethiopia ይባላል ።
ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል !

    ☎️   +251977338586       🇪🇹
    ☎️   +251977338586       🇪🇹

ይህን ይጫኑ የ Telegram ቻናላቸውን ለማግኝት  👇👇


https://hottg.com/City_Forex_Ethiopia
https://hottg.com/City_Forex_Ethiopia
https://hottg.com/City_Forex_Ethiopia
https://hottg.com/City_Forex_Ethiopia

🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹
HTML Embed Code:
2024/04/27 08:15:39
Back to Top