TG Telegram Group Link
Channel: Orthodox Patristic Writings.
Back to Bottom
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
+++እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ክብርት፣ውድስት በዓለ መስቀል በሰላም አደረሳችሁ++++

የጌታ ኢየሱስ መስቀል፣አዲስ ኪዳን ተመርቆ የተከፈተበት ነው።
አዳም እስከ ልጆቹ የዳነበት፤ እና ናፍቆቱን ሁሉ ያየበት ነው።
ነብያት የናፈቁትን ድኅነት፤ያዩበት እና የተሳለሙት ነው።
እርሱ(ጌታ ኢየሱስ) ወደ ላይ ከፍከፍ ባለ ጊዜ እኛን ከእርሱ 'ርቀን የነበርነውን ወደ በረቱ ያስገባበት ነው።

የጌታ የኢየሱስ መስቀል ትኅትናን የተማርንበት፣ነው።
ኃያሉ ደካማ የሆነበት፤ደግሞም ኃይሉን የገለጠበት ነው።
ፍቅር የተገለጠበት እና የፍቅርን ትርጉም የተረዳንበት ነው።
ሞት እና ሲዖል ድል የተደረጉበት፣ኃይላቸው የደቀቀበት፣ የግዛታቸው ጊዜ ያበቃበት ነው።

የጌታ ኢየሱስ መስቀል ተአምር እና ድንቅ ነው።
ኃይልን አድሎናል፣ዋጅቶናል፣ ባርኮናል።
በጌታ ኢየሱስ መስቀል ፀጋ ተሰጥቶናል።
መንፈስቅዱስ ቀርቦናል፣አብ ልጅነትን ሰጥቶናል።

ጌታ ኢየሱስ እርሱ ደቆ እኛኝ አከበረን፣
እርሱ ደኽይቶ እኛን አበለፀገን፣
እርሱ ቆስሎ እኛን አከመን፣
እርሱ ተጠምቶ እኛን ከጥማችን አረካን።

ለዘላለም እንዳንጠማ፣እንጠጣው ዘንድ ራሱን ሰጠን።
እርሱ ተርቦ፣እኛን አጠገበን፥ለዘላለም እንዳንራብ መና ሆነን።
እርሱ ሞቶ ለእኛ ሕይወት ሆነን።
በሞቱም ሙስናን፣ጉስቅልናን አጠፋ።

የእርሱ ሞት ኃይል ነው፣ሞተን ለነበርን ጠቅሞናል።
ሔኖክ ብቻ ሲቀር የብሉይ ሰዎች በሞት ቁጥጥር ስር ነበሩ፣
ሔኖክ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋር ስላደረገ በሞት ሳይያዝ ቀረ፣
ረሱን ጠቀመ፣ ወገኖቹን ግን አልታደጋቸውም።

የጌታ ሞት ግን ዓለሙን ሁሉ ታደገ፣
ሞትን ዘልፎ ማሰሪያውን ቆረጠ፣
የሥግው ቃል ሞቱ የሞት መጨረሻው ሆነ፣
ሞት ከእርሱ ሞት በኋላ ድል ማድረጉ ቀረ።

የወልድ ዋኅድ ሞቱ የእግዚአብሔር ፍርድ የታየበት ነው።
መንፈስቅዱስ ይህን ሚስጢር እንረዳ ዘንድ ያግዘን!
በጌታ ሞት ሚስጢራት ተገኙ!
በሚስጢራቱም ዘወትር ከእርሱ ጋር ኅብረት አድርገን እንኖራለን።

አስቀድሞ በእርሱ መሠረትነት ዓለማት ተፈጠሩ፣
ስለሆነም ዓለማት በሁለንታቸው(Macrocosm)በአዳም አደፉ፣
ስለዚህ መሠረታቸው ቃል ሥጋ ለብሶ ሁለንታቸው ሆኖ መጣ፣
በአዲስ ተፈጥሮ ፈጠራቸው፣አጠባቸው፥ስለዚህ ዘወትር ፋሲካን ያደርጋሉ።

ለዚህች እለት ስግደት፣ዝማሬ፣እልልታ፣ግርግርታ ይገባል።
የጌታ ሕማም ኃይላችን ነው።
የጌታ ሕማም ምልክታችን ነው።
የጌታ ሕማም ድኅነታችን ነው።
የጌታ ሕማም ልብሳችን ነው።
የጌታ ሕማም ውበታችን ነው።
የጌታ ሕማም እድፈታችንን የሚያነጻልን ነው።
ንጹሕ በግ፣በቀበሮዎች መኻል ቆመ።
Jacob_of_Sarug's_Homily_on_Christ's_Entrance_to_Sheol_Daniel_McConaughy.pdf
1.6 MB
ቅዱስ ያዕቆብ በዚህ ድርሳኑ ስለ ጌታ የመስቀሉ ማዳን አብዝቶ የተናገረበት እና ሞት እና ሲዖልን ድል ስለማድረጉ በብዙ የተናገረበት ነው። አንብቡት 😍 ይህን ሊቅ ግን በምን ቃል ልግለጠው? ያለው የመንፈሳዊ ዕውቀት፣ልእልና እንዲሁም መጽሐፍትን የሚፅፍበት ተማኅልሎአዊ መንገድ ብቻ ሊቁ የምርም ሊቅ ነው። በአማን እንዚራ መንፈስቅዱስ፣ በአማን እንዚራ ቤተክርስቲያን አክሲዮስ!አክሲዮስ!አክሲዮስ ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ😍 እንኳንም የኛ ሆንኽ🤗(የOriental Orthodox አባት እንደሆነ ልብ ይሏል)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Jacob_of_Sarug's_Homilies_on_the_Resurrection_Metrical_Jacobus,.pdf
633.7 KB
ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ ስለ ትንሣኤ በዓል የደረሰው ድርሳን እነሆ😍 ከዚህ ከማይነጥፈው ምንጭ፣ከእንዚራ መንፈስቅዱስ፣ከእንዚራ ቤተክርስቲያን ከቅዱስ ያዕቆብ አንብባችሁ እርኩ!
Orthodox Patristic Writings.
Video
አበው ቅዱሳንን ሐኪም(Doctor) ማለት በቤተክርስቲያናችን በስፋትየተለመደ ትውፊት ነው። በተለይም፤ በመካከለኛው ክፍለ ዘመን በአባቶቻችን ጽሑፎች በስፋት የምናገኘው ገላጭ ቃል ነው። በተለይም ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘታቴቭ በስፋት ሲጠቀምበት እናያለን።

አበው በቤተክርስቲያን ውስጥ ትልቅ ድርሻ አላቸው። ያልተበረዘው ትምህርተ ክርስቶስ በእነርሱ በኩል ነው የደረሰን፣ሐዋርያት ቃላቸውንም፤ትምህርታቸውን እና መጽሐፍቶቻቸውን በእነርሱ በኩል ነው ያስተላለፉት።
ሐዋርያት የኖሩትን ኑሮ በእነርሱ በኩል ይደገማል፥ለእኛም አስተላልፈውልናል። (ኦርቶዶክሳዊነት ማለት ኅሊና አበውን ገንዘብ ማድረግ እንደሆነ ልብ ይሏል።) እንዲሁም የእነርሱ ታሪክ ሕያው ነው። ምክንያቱም ሁሌም አሁን በምትለው(ቤተክርስቲያን በስርአተ-አምልኮቷ ጊዜ ኃላፊ እና መጻኢ ጊዜ የሌለውን Kyros የተባለውን ጊዜ ትጠቀማለች። ) በቤተክርስቲያን ውስጥ ይታወሳሉ እንዲሁም የእነርሱን ሕይወት እኛም ለመኖር እንጥራለን፤እንቃትታለን።
እንዲሁም ሁሌ ከእነርሱ ጋር በስርአተ-አምልኮታችን እና በቅዱስ ቁርባን ኅብረት እናደርጋለን።

ለዚህም ነው አበው አዲስ ትምህርት በመናፍቃን ሲመጣ፥ማሩ እንደተነካበት ንብ በመናፍቃን ላይ የሚነሱት፣በሰላው እና በተጠረበው ትምህርታቸው የመናፍቃንን የዶለዶመ ትምህርት ለማቃናት የሚጋደሉት። ለትምህርታችን ምስክር የምናደርጋቸው ቅዱሱን የጌታን ትምህርት ሳይበርዙ በማቆየታቸው ነው።

በእኛ ቤተክርስቲያን(ኦሬንታል ኦርቶዶክስ ማለቴን ልብ ይሏል።) ልክ እንደ ካቶሊኮች እና ምስራቅ ኦርቶዶክሳውያን የተወሰኑ አበውን ብቻ Doctor የማለት ትውፊት ያለን አይመስለኝም።ነገርግን ቅዱስ አትናቴዎስን፣ቀጶዶቅያውያን አበውን፣ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅን፣ቅዱስ ቄርሎስ ዘእስክንድርያን፣ቅዱስ ሳዊሮስ ዘአንፆኪያን እና ቅዱስ ፊሎክሲኖስ ዘማንቡግን እና ቅዱስ ዶዮናስዮስ ዘአርዮስፋጎስን (በእርግጥ የእርሱ ድርሳናት የሊቁ ትክክለኛ ድርሳናት አይደሉም የሚሉ አካላት ቢኖሩም የኛ አበውግን አስቀድመው ነው የእርሱን ድርሳናት መጠቀም የጀመሩት እንዳውም ቅዱስ ሳዊሮስ ቀዳሚው ነው። ከምስራቃውያን እና ከካቶሊኮች በፊት ከእርሱም በኋላ የኛ አበው በስፋት ተጠቅመውበታል። በተለይ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘታቴቭ የእርሱን የነገረ መለኮት አስተምህሮ የሚተነትን ጽሑፍም አለው። )ይበልጡን በብዛት በነገረ-መለኮታዊ ጉዳዮች የመጥቀስ ትውፊት ግን አለን።

ይህን ጣፋጭ እና ነፍስ የሚያድስ በሶርያ ባለችን ቤተክርስቲያን ውስጥ የሚገኘውን ማኅሌት ስሰማ ጊዜ፥አበውን ማንሳት ሻትኹ።😍
ለእግዚአብሔር የገባሁት ቃል ኪዳን የመረጋጋት እና የዝምታ ሕይወት ነበር ::እንደ ቃሌ ይህንን ሕይወት እየተለማመድኩ ሕሊናየ ከፍ ያለውን ነገር በሚመለከትበትና የሕይወት ፍልስፍናዬ ትክክል እንደሆነ እያመንኩ በመጣሁበት በዚህ ወራት ባልጠበቅኩት ጊዜና አጋጣሚ የተጫነብኝን ቀንበር ልሸከምበት የምችለውትከሻ አልነበረኝም :: ለእኔ አስፈላጊ የነበረው ነገር የስሜት ሕዋሳቶቼን በር ዘግቼ ከሥጋዊ እና ዓለማዊ ነገር ሁሉ ሸሽቼ ከራሴ ጋር ብቻ መሆንን ነው ::  ከራስ ጋ ከመነጋገር የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ምን ነገር አለና ከማውቀው ከራሴ ጋር መወሰንን ወደድኩ :: ለራሴ እና ለእግዚአብሔር ነገርን እየተናገርኩ ከሚታይ እና ከሚዳሰሱ ነገሮች ሁሉ በላይ ትልቅ የሆነ ሕይወትን መኖርን ወደድኩ በልቡናዬ ውስጥ የምጫረውን ሰማያዊ ነገር ::

ከምድራዊ ሐሳብ ጋር ሳልቀላቅል መንፈሳዊ የሆነ ነገር በውስጤ እንዲያድር ማድረግ የዘወትር ፍላጎቴ ነበር  ይህ ሐሳብ ንጹሕ መስታወት የሰውን መልክ እንዲያሳይ እግዚአብሔርን እንድንመለከት የሚያደርግ የልቡና መስታወት ነው ::በብርሃን ላይ ብርሃንን የሚጨምር በእውቀት ላይ እውቀትን የሚጨምር በተስፋ የሚጠብቁት የሚደሰቱበት ከቅዱሳን መላእክት ጋር ሆነው እግዚአብሔርን የሚያመሰግኑበት ስሜት ነው ::

"ከራስ ጋ ከመነጋገር የበለጠ ደስታን የሚሰጥ ምን ነገር አለና ከማውቀው ከራሴ ጋር መወሰንን ወደድኩ ::"

(ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘእንዚናዙ ትምህርቱ እና ሕይወቱ ከገጽ 43-44 )
Orthodox Patristic Writings.
the life of saint Macrina the younger.pdf
ሴቶች በጥንቷ ቤተክርስቲያን ሚና አልባ አይደሉም። የትንሣኤው ምስክሮች ሴቶች ነበሩ፣ጌታን የሚያገለግሉ ብዙኃን ሴቶች ነበሩ፣ጌታ መንፈስቅዱስ ሲወርድ በዚያው ብዙ ቅዱሳን አንስት ነበሩ፣ሐዋርያት ብቻም ሳይሆኑ ቅዱሳን ሴቶችም የጌታ ትንሣኤ ምስክሮች ነበሩ ለአብነት ያህል የቅድስት ማርያም መግደላዊትን እና የቅድስት ቴክላን ሐዋርያዊ ሥራዎች ማየት ይቻላል።ሐዋርያትን በመላላክ እና በመርዳት ረገድም እነ ቅደስት ፌበንን ማንሳታችን የግድ ነው። የዲያቆናዊነት ስልጣንም ነበራቸው፣በዚህ ስልጣን ለሴቶች ትምህርትን ይሰጡ ነበር።

በተለይም ቅዱሳን ሴቶች ልጆቻቸውን፥በቅድስት ሃይማኖት አንጾ በማሳደግ አይነተኛ ሚናን ተጫውተዋል። እንግዲህ ከእኒህ ሁሉ ቅዱሳን ቅድስት ማክሪና አንዷ ናት። ይህች ቅደስት ከቂሳርያ ከበጎ፣ደገኛ ቤተሰቦች ከቅዱስ ባስልዮስ ታላቁ እና ከቅደስት ኤሚሊያ የተገኘች ስትሆን። ይህም ቤተሰብ በቅድስና የሚታወቅ፥በሐብታቸውም የከበሩ ሲሆኑ ልጆቻቸውን ግን በቅድስና እና በምግባር ያሳደጉ ናቸው።

ቅደስት ማክሪናናን ጨምሮ ቅዱስ ባስልዮስ ዘቂሳርያ፣ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ እና ቅዱስ ጴጥሮስ ዘሰባስቴ ከዚህ ቅዱስ ቤተሰብ ነው የተገኙት።ነገርግን እነዚህ ቅዱሳን ሊቃውንትን በማብቃት ረገድ የቅድስት ማክሪና ድርሻ እጅጉን የላቀ ነበር። ይህች ቅደስት ዓለማዊ ትምህርትም ሆነ መንፈሳዊውን የተማረች ስትሆን፤ ከልጅነቷ ጀምሮ ራሷን በቅድስና ያስጌጠች ነች። መዝሙረ ዳዊትን አብዝታ ትጸልይም የነበረ ሲሆን ወንድሞቿ ከመንፈሳዊ ሕይወት ሲነጥፉ የመለሰች እና የገሰጸች ብሎም የቤቱ የመጀመሪያ ልጅ ስለሆነች እንደ እናትም የሆነች ናት።

ቅድስቷ የኋለኛውን ሕይወቷን ከእናቷ ጋር በመሆን በድንግልና እና በምንኩስና ሕይወት ነበር ያሳለፈችው። ነድያንን በመምሰል፣ለነድያን በመመጽወት ራሷን ድኃ ያደረገች ናት። የሕይወት ታሪኳ በወንድሟ በቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘኑሲስ የተጻፈ ሲሆን በነፍስና በትንሣኤሙታን ላይ የነበራትንም አስተምህሮ "On The Soul And Resurrection" ብሎ ጽፎላታል።የሕይወት ታሪኳን ከማይነጥፈው ምንጭ አንብባችሁ ትረኩ ዘንድ፣ጋበዝዃችሁ።በረከቷ ይደርብን!
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በግብጽ ያለችው ቤተክርስቲያናችን ስለ እናታችን ልደት እንዲህ ትዘምራለች፦

"የኢያቄም ልጅ ድንግል ማርያም ሆይ አንቺ ፅዮን ነሽ፣የኢየሩሳሌምም ከተማ ነሽ...ዛሬ ሁሉም ደስታ እና ፍስሀ ስለ አማኑኤል እናት ስለ ንግሥት ማርያም ወደ እኛ መጣ...ሁሉም ክርስቲያን ሕዝቦች ከመምህራን ጋር እና ከጳጳሳት ጋር በማርያም ልደት በቤተክርስቲያን ተሰበሰቡ።"

(Psali adam for birth of the virgin,psali watos for birth of the virgin)

የመድኃኒት እናት፣በሁለት ወገን ድንግል የሆንሽ፣ማርያም ሆይ በበዓልሽ ቀን እኛን ባርኪን እናታችን ሆይ እንወድሻለን እንኳንም ተወለድሽልን።
ለአቋቋም ትምህርት ፈላጊዎች እንኳን ደስ አላችሁ

አቋቋምን  በነጻ የሚስተምር ቻናል አለ ዝግጅት ጨርሰዋል ሁሉም እኩል እንዲጀመር እናንተን ነው የሚጠብቁት

ትምህርቱ መማር ለሚፈልግ ለሁሉም ነው  

የሚሰጠው ትምህርት
አጠቃላይ አቋቋም ከነ ሥረዩ[ምልክቱ]
👉አጠቃላይ ዚቅ አቋቋም ከነ ሥረዩ
👉እስመ ለዓለም፣መዝሙር ከነ ሥረያቸው
👉አመላለስ ፈጠራ ከእነ ሸብሻቦ
👉የቅኔ ምራታ እና የቅኔ አቋቋም
👉ላይ ቤት አቋቋም የአቀያየር
👉ወረብ እና ሌሎችም......

(አቋቋሙ---የጎንደር አቋቋም ነው)

ትምህርቱ የሚፈጀው ጊዜ🌼
✔️1 ዓመት   (በጣም ከገፋ ደግሞ 1 ዓመት ተኩል)

ቻናሉ 👉 @akuakuambet
              @akuakuambet
              @akuakuambet


https://hottg.com/akuakuambet


https://hottg.com/+y5meoeP9oIA3ZWY8
Orthodox Patristic Writings.
https://paulosmargregorios.in/wp-content/uploads/2015/12/act_of_love.html
እግዚአብሔር ጋር ያለን ግንኙነት አጋፔያዊ ግንኙነት(Agapeic Relationship)ነው። ታዲያ ይህ ግንኙነት በቅዱስ ቁርባን ወቅዳሴ ነው እውን የሚሆነው። በዘመናችን በህንድ ባለችው ቤተክርስቲያናችን የኒው-ዴልሂ ሀገረ-ስብከት ጳጳስ የነበሩት ብጹእነታቸው ጳውሎስ ማር ጎርጎርዮስ ስለዚህ አጋፔያዊ አንድነት፤ኅብረት በጻፉት Article በማይነጥፈው ብእራቸው ተራቀውበታል። በዚህች አጭር ጽሑፍ ውስጥEcclesiology,Sacramental theology እንዲሁም መለኮታዊ ፍቅርን ይገልጡልናል። እኝህ አባት ከTheology ባሻገር Philosophyም ያጠኑ ናቸው። ፍልሱፍ እንዲሁም የSocio-political thinkerም ነበሩ፥በሕይወት ዘመናቸው በTheology,Philosophy,Politics,Law,Sociology እና ሌሎች Socio-economic issues ላይ ያነጣጠሩ Articles ጽፈዋል።
የብርሃን መንገድ.docx
12.5 KB
አንዳንዴ ሀሳብን ለመግለጥ ስነ-ጽሑፍ በእጅጉ ያግዛል ሀሳብን እንደው በደፈናው ከመጻፍ በልብ-ወለድ መልክ መጻፍ ደግሞ እጅጉን የሚመች የሆነ መንገድ ይመስለኛል።(ግላዊ ሀሳብ😁) ስነ-ጽሑፍ ሀሴት ያላት መንገድ ነች ስለሆነም ስለመኖር ያለኝን ምልከታ እንዲህ በእጅጉ በጣሙን አጠር ባለች መንፈሳዊ ልብ-ወለድ ውስጥ ለማስቀመጥ ሞክሬያለሁ፣በጥሞና አንብቡልኝ መቼስ ባይጠቅም እንኳ Atleast አይጎዳም። ጽሑፉ የተጻፈበት መንገድ Metaphorical ነው።
HTML Embed Code:
2025/06/28 18:23:58
Back to Top