Warning: mkdir(): No space left on device in /var/www/hottg/post.php on line 59

Warning: file_put_contents(aCache/aDaily/2025-07-22/post/orthodoxdigitallibrary/--): Failed to open stream: No such file or directory in /var/www/hottg/post.php on line 72
... የቀጠለ @Orthodox Patristic Writings.
TG Telegram Group & Channel
Orthodox Patristic Writings. | United States America (US)
Create: Update:

... የቀጠለ

                          የመጽሐፉ ፍሬ-ነገር

ሕዝበ አይሁድ እንዲነጹበት በተደነገገላቸው ሲነጹ ኑረው፣በጥላው ሲድኑ ከርመው፣ኋለኛው እውነተኛ አካሉ በመጣ ጊዜ ባለመቀበላቸው ቅዱሱ ይዘልፋቸዋል።

"ዕውራን ሕዝቦች ጥላውን ወስደው፥ነገርግን አካሉን ግን ከዱት።እንዲሁም ከዚህ በላይ መድኅን ለሆነው፤አካል እውቅና አልሰጡም።"¹

ከዚህም በላይ ደግሞ በኦሪት ዘኁልቊ የተሰጠው የመንጻት ሕግ ላይ እንደምናየው ሠዋኢው ሊቀ-ካኅን መሥዋዕቱን አሠናድቶ ከጨረሰ፣እና የትጥበት ስርአትን ከፈጸመ በኋላ እስከማታ ርኩስ እንደሚሆን እና ጊደሯን እስከ ሁለመናዋ፣ከቀይ-ግምጃው፣ከሂሶጱ እና ከዝግባ እንጨት ጋር ያቃጠሉት ሰዎችም የትጥበት ስርአት ከፈጸሙ በኋላ ርኩስ እንደሚሆኑ ይህ ስርአት ይደነግጋልና! ቅዱሱ ይህን በመያዝ ለሕዝበ አይሁድ እንዲህ ሲል ጥያቄ ያቀርባል፦
"የጌታን ሰቃልያን በምሳሌ ሊያሳይ ካልሆነ በቀር፥ንጹሕ መሥዋዕት ሠዋዒውን ስለምን ያረክሰዋል?"²

እርሱ(ካኅኑ) በሠዋው መሥዋዕት ሕዝበ እስራኤል ዘሥጋ ጥቅም አግኝተው ሳለ፣እርሱ ግን ለምን እንደረከሰ በቀጣዮቹ የመጽሐፉ ክፍሎች ያብራራል።

ይህ ካኅን ደገኛ ነው። ምክንያቱም ያልነጹትን ሌሎችን ሊያነጻ ይሻልና ነው። ነገርግን እርሱ ከሰዋ በኋላ ይረክሳል። ለምን እንደሆነ ሠዋዒው ካኅን መጥቶ ያነጋግረው ዘንድ ቅዱሱ ሊቅ "በልብወለዳዊ ንግግር"(Fictional dialogue)³ ይጣራል።ካኅኑም ሲመልስለት እንዲህ ይላል
"የኔ መሥዋዕት ማቅረብ ስለሚመጣው መጉደፌ(እርኩስነቴ) ምክንያት ነው።⁴

በዚህ ክፍል የምንረዳው ሊቁ በካኅኑ ወካይነት ሕዝበ እስራኤልን እየጠየቀ እንደሆነ  ነው።
"በመስቀል በኩል ሁሉም በእውነት ነጽቷል!አልወደዱትምምና ከሕዝብ(አይሁድ) ብቻ በእርሱ(በመስቀሉ) ረከሱ።"⁵

ብሎ እንዲተረጉምልን፥የካኅኑ ምሳሌ የሰቃልያነ ክርስቶስ የአይሁድ ምሳሌ ነው። ምክንያቱም አይሁድ አማናዊው መሥዋዕት ክርስቶስ በእነርሱ እጅ ነበር የተሠዋው(የተሰቀለው) ነገርግን እነርሱ አላመኑበትም፤ረከሱበት እንጂ። ስለዚህ በአሪት ዘኁልቊ ያለው መሥዋዕቱን ሠውቶ ሰዎችን አንጽቶበት ራሱ የረከሰበት መሥዋዕት ተምሳሌቱም፦ጌታን ሰቅለው እነርሱ ሳያምኑበት፥ነገርግን ዓለሙ ሁሉ የነጻበት ምሳሌ ነው። ሕዝበ አይሁድ ራሳቸው ያልተጠቀሙበትን መሥዋዕት ሠውተዋልና።(ጌታን የሰቀሉት አይሁድ እንደሆኑ ልብ ይሏል! እነርሱ ቢጠሉት እና ባይቀበሉት፥ለተቀበሉት ሁሉ መድኃኒት፣መንጽሔ አበሳ እና መንጽሔ ኃጢአት ሆኗል።)

የጊደሪቱ ቀለም ቀይ ነበር ይህም የክርስቶስ መከራ እና የደሙ ተምሳሌት ነው ይለናል ሊቁ፥
"እርሱ፦(ሙሴ) ጌታችን እየተሰቃየ እያለ ታላቅ ስዕልን ሳለ፣ምሳሌዋ ጊደር በስነ-ስነቅለቱ ቀለም ሆነች። ቀይ ነበረችና፣በገጽታዋ(በመልኩዋ) ሞትን ትገልጥ ነበር።⁶

ጌታችን በስቃዩ ጊዜ የፈሰሰውን ደም የመልኩዋ ቅላት ይገልጠዋል ማለቱ ሲሆን፥እንዲሁም የወልድ ዋኅድን ቁስል ይገልጣል።
ቀይ ጊደር መመረጧ በራሱ በተመረጠች ጊዜ በሙሴ የስነ-ስቅለቱ ቀለም እንደታየም ጭምር ሊቁ ይተረጉመዋል። ይቺ ቀይዋ ጊደር መንጽሔ እርኩሰት እንደሆነች ሁሉ የኢየሱስ ክርስቶስ ደምም ከኃጢአት ሁሉ የሚያነጻ ነው።

በነገራችን ላይ በዚህ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል(ኦሪት ዘኁልቊ 19) ብቻም ሳይሆን በሌላም የጥላው የብሉይ ኪዳን ክፍል በሆነው
በመሐልየ መሐልይ ዘሰሎሞን 5፡9ላይ ሙሽራይቱ ስለ ሙሽራዋ እንዲህ ትላለች፦"ወንድሜ ነጭና ቀይ ነው።"

ከአበው አንዱ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘናሬክ " ቀይ መባሉ ከቅድስት ድንግል ማርያም ፍጹም የሆነ የእኛን ሥጋ እና ደም እንደነሳ"አመላካች ነው ሲል ነጭ መባሉ ደግሞ "በንጽሕና መወለዱን ያመላክታል"⁷ ብሎ ይተረጉመዋል።

አንድም ቀይ መባሉ ደግሞ ቤተክርስቲያን ስለ መከራው እየዘመረች እንደምትኖር፣ ምክንያቱም የእርሱ መከራ ለእርሷ ድኅነቷ ነውና ስለ ድኅነቷ በፍስሀ ሆና ሙሽራዋን እየጠራች መሆኑን የሚያሳይ ነው ተብሎ ይተረጎማል።⁸
ስለሆነም፦
በራእየ ዮሐንስ 19:13 ላይ "በደም የታለለ ልብስ ለብሷል"

ተብሎ ከተነገረለት ከጌታችን ኢየሱስ ውጭ ይህ ቀይነት ለማን ይተረጎማል?

ከጊደሯ ጋር አብሮም ቀይ ግምጃ የመቃጠሉን ነገርም ሊቁ እንዲህ ሲል ይተረጉመዋል፦
"ቀይ የሆነችው ጊደር ለእርሱ በቂ አልሆነችም ነበር ፥ነገርግን በቀዩ ግምጃ ደምን አሳየ፤እርሱ በጥበብ የደምን ቀለም አንዱን ከአንዱ አደበላለቀ፤በዚህም የስነ-ስቅለት ስዕል ውበቱ ይበልጡን እንዲጠናከር!"⁹

ስለሆነም የጊደሯ ቀይነት እና ቀዩ ግምጃ ለክርስቶስ መከራ እና ደም መፍሰስ ተምሳሌት ናቸው።የዝግባ እንጨቱም ክርስቶስ የተሰቀለበትን ዕቀ-መስቀል የሚወክል እንደሆነ ይናገራል። እንዲህ በማለት፦
"አንተ የምትፈርድ ሆይ¹⁰ ተመልከት! ምሳሌው ሁሉንም ይገልጣል! እርሱ መስቀሉን አቆመ፤ነገርግን ያለዕፅ አይቆምም። ይህ ሙሴ የዝግባውን እንጨት በያዘጊዜግን የመስቀሉ ሥራ በሁሉም ነገር ተፈጸመ።"¹¹

እኒህ ሁሉ ተምሳሌቶች የሚያሳዩን፣የሚተነብዩልን ዘለዓለማዊ ኪዳን የሆነውን፤ መንጽሔ ኃጢአት የሆነውን የክርስቶስ የመስቀሉን ሥራ ሲሆን፥ ሚስጢረ ክርስቶስን  እንድንረዳ በሚታየው ነገር፣ድብቁን ነገር እንድንረዳ፣እንደሆነ ሲያትት ሊቁ እንዲህ ይላል፦
"በእነዚህ በተሠዉት መሥዋዕቶች መሠረት፣ዓለምን ያዳነውን እርድ እንረዳ ነበር"¹²

እንዲህ ማለቱም ሊቁ የምሳሌያትን አስፈላጊነት ሊያሳየን ሽቶ፤ አንድም ለተማኅልሎአዊ ነገረ-መለኮት(Mystical Theology) አጽንኦት ይሰጣል።
ምክንያቱም በተማኅልሎአዊ ነገረ-መለኮት ስለ ነገረ-መለኮት የምንረዳው አንድም በምሳሌያት እንደሆነ የመካከለኛው ክፍለዘመን የቤተክርስቲያን ጌጥ ቅዱስ ጎርጎርዮስ ዘታቴቭ ያስተምራል። ሊቁ ጎርጎርዮስም ምሳሌያትን እና ምልክቶችን "ምልክታዊ ነገረ-መለኮት" (Symbolic Theology) ብሎ ይጠራቸዋል¹³። ስለ እግዚአብሔር ስንናገርም ልንጠቀምባቸው እንደምንችልም አክሎ ይናገራል።

ይቀጥላል........

                    ማጣቀሻዎች
1. Homily on concerning the red heifer and crucifixion of our lord:110
2. ዝኒ ከማሁ፡115
3. ቅዱስ ያዕቆብ ዘስሩግ እንዲህ ያለ የአጻጻፍ ስልትን በብዛት ይጠቀማል። ለምሳሌ Homily on the nativity ላይም ይህን አጻጻፉን እናየዋለን። በእርግጥ ይህ አጻጻፍ በቅዱስ ኤፍሬምም ጽሑፎች በደንብ ጎልቶ ይታያል። የሶርያውያን አበው አንዱ የአጻጻፋቸው መለያ፤ውበት ነው ማለት እንችላለን።
4. Homily on concerning the red heifer and crucifixion of our lord:135
5. ዝኒ ከማሁ፡140
6. ዝኒ ከማሁ፡150
7. Commentary on blessing of blessings 5:9
8. F.r Tadros Y.Malaty,Patristic commentary on the song of songs,Page 105
9. Homily on concerning the red heifer and crucifixion of our lord:185
10.ለአንባቢ ፍርድ እየሰጠ እንዳለ ልብ ይሏል።
11.Homily on concerning the red heifer and crucifixion of our lord:190
12. ዝኒ ከማሁ፡205
13. Book of Questions Volume፡3 Chapter፡8 Section፡8

10

>>Click here to continue<<

Orthodox Patristic Writings.

Share with your best friend
VIEW MORE

United States America Popular Telegram Group (US)

Warning: Undefined array key 3 in /var/www/hottg/function.php on line 115

Fatal error: Uncaught mysqli_sql_exception: Too many connections in /var/www/db.php:16 Stack trace: #0 /var/www/db.php(16): mysqli_connect() #1 /var/www/hottg/function.php(212): db() #2 /var/www/hottg/function.php(115): select() #3 /var/www/hottg/post.php(351): daCache() #4 /var/www/hottg/route.php(63): include_once('...') #5 {main} thrown in /var/www/db.php on line 16