TG Telegram Group Link
Channel: NidaTube -ኒዳ ቲዩብ
Back to Bottom
‏ጎንደር ታላቅ አሊም አጣች።
‏ ሸህ ጀማል አደም ሀገር ውስጥም በሰፈር ቂራዓት በውጭም በሱዳን አፍሪካ ዩንቨርስቲ በቂርዓት አቀባበላቸው ፈጣንና ሀፊዝ ነበሩ። የጎንደር ከተማ ዑለማ ም/ቤትን በዘመናዊ አሰራር የተሻለ ሀሳብ በማምጣት ጥሩ እቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩና የጎንደር ሙስሊሞችን ግፍ በአደባባይ የተጋፈጡ ታላቅ አሊም ነበሩ። አባ-ሼህ ጀማል አደም - ከላቁ የእኛ-ዘመን ዑለሞች መካከል ተጠቃሽ ነበሩ።
‏በጎንደር-ከተማ ሚና መስጂድ፣ ኢማም፣ ኸጢብና ዋዒዝ ነበሩ።

‏የጎ/ከ/ዑለ/ም/ቤትን በነጻ፣ ለሁለት ዓመታት በፀሀፊነት አገልግለዋል። ለአምስት ዓመታት የስራ አስፈጻሚ አባል ኾነው ቆይተዋል። ለውጥ ፈጥረዋል። ‹ሼህ ጀማል አደም› ቢኾንም ስማቸው፣ በ“ሼህ ጀማል ገበሬው” ነው የሚታወቁ። በእርግጥም! የነህው፣ የሶርፍ፣ የመንጢቅ፣ የሉጛ ገበሬ ነበሩ። የዲን ገበሬ ነበሩ። በወሎና በጎንደር፣ እንዲሁም በሱዳን ሀገር ተዟዙረው ሰፊ ዒልም ያካበቱ ታላቅ ዓሊም ነበሩ።

‏ሼህ ጀማል ከወራት በፊት ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው በትናንትናው ዕለት ለህልፈት በቅተዋል። መልካም ስራቸውን አላህ ይቀበላቸው። ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእኛም መፅናናት ይኹን። አላህ መልካሙን ተተኪ ይስጠን!!!
اللَّهُمَّ اغْفِرْ لَهُ وَارْحَمْهُ، وَعَافِهِ، وَاعْفُ عَنْهُ، وَأَكْرِمْ نُزُلَهُ، وَوَسِّعْ مُدْخَلَهُ، وَاغْسِلْهُ بِالْمَاءِ وَالثَّلْجِ وَالْبَرَدْ، وَنَقِّهِ مِنَ الْخَطَايَا كَما نَقَّيْتَ الثَّوْب الأَبْيَضَ مِنَ الدَّنَسِ، وَأَدْخِلْهُ الْجَنَّةَ، وَأَعِذْهُ مِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ وَعَذَابِ النَّارِ
🛑 ለአዲስ አበባ ሙስሊም ማህበረሰብና ለመስጂድ ጀመዓዎቸ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተላለፈ ጥሪ

ነገ እሁድ መጋቢት 3 | 2015 ከጠዋቱ 12:30 ሰዐት ጀምሮ ጉለሌ በሚገኘው የሙስሊሞች መካነ መቃብር ቅጥር ግቢ የማይቀርበት ቀጠሮ ተይዟል።

ቀጠሮው ወጣት ወንዶችን ይመለከታል።

ስራው ወደ ጫካነት ተለውጦ የጅቦች መራቢያ፣ የሌቦች መደበቂያ፣ የሱሰኞች መነሀሪያ የሆነውን ጉለሌ መካነ መቃብርን ጫካውን በመመንጠር ምቹ የቀብር ስፍራ ማድረግ ነው።

በዚህ ትልቅ አጅር በሚያስገኘው በጉልበታችን ብቻ በሚሰራው ኸይር ስራ ላይ ወላጆች እና ሴቶች ወንድ ልጆቻችሁን እና ወንድሞቻችሁን በመላክ እና በማበረታታት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።

ይህ ስፍራ የነገው የእያንዳንዳችን ማረፊያ ነው ቤታችንን እናፅዳ ቤታችንን ምቹ እናድርግ።

📌 ነገ በፍፁም አይቀርም ጠዋት 12:30 ሰዐት ላይ እንገናኝ።

የጉለሌ ሙስሊም መካነ መቃብር አድራሻውን ለማታውቁ

🛑 ከፒያሳና አካባቢው ለምትመጡ:-

እንቁላል ፋብሪካ አደባባዩን አልፋችሁ ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ በስተ ግራ በኩል

🛑 ከአለም ባንክ፣ ጦርሀይሎችና አካባበከው ለምትመጡ:- ከአውቶብስተራ ወደ ፓስተር ስትሄዱ በስተቀኝ በኩል ሁለተኛ አስፓልት ቂያስ ወደ ሀግቤስ በሚወስደው መንገድ ላይ ወደ ግራ በሚወስደው በመታጠፍ በስተቀኝ በኩል ቀብሩን ታገኙታላችሁ

🛑 ከአስኮ እና አከባቢ ለምትመጡ:- ከፓስተር አደባባይ እንዳለፋችሁ ኖክ ማዲያ ፊት በስተቀኝ በኩል ወደ ጨው በረንዳ ስትታጠፉ ቀብሩን በግራ በኩል ታገኙታላችሁ

🛑 ከጥቁር አንበሳ ለምትመጡ ደግሞ አንዋር መስጂድን አልፋችሁ በቀኝ በኩል ወደ አዲሱ ገበያ የሚወስደውን አስፓልት አልፋችሁ ወለጋ ሆቴል በሚገኝበት አስፓልት ወደቀኝ በመግባት ውሀ ልማቱ ፊት ታገኙታላችሁ
@nidatube
🌙ነገ ጨረቃ ከታየች ሮብ ረመዳን 1 ብሎ ይጀምራል፣ ነገ ካለታየች ሀሙስ የመጀመሪየውን የረመዳን ፆም እንጀምራለን።
አላህ ያድርሰን🙏
@nidatube
መልካም የረመዷን ወር ይሁንልን
ከ48 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተገነባው የዳሩል ሂጅረተይን መስጂድ የምረቃ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።
በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
#ጥቆማ #የኢትዮጵያአየርመንገድ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ በTRAINEE CABIN CREW ፣ በSENIOR ACCOUNTANT I እንዲሁም በሌሎች ዘርፎች ማስታወቂያ አውጥቷል።

ለTRAINEE CABIN CREW በኢትዮጵያ ሀገር አቀፍ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ቢያንስ (ዝቅተኛው) 200 ነጥብ ያስመዘገበ ለማመልከት ብቁ ነው።

የዕድሜ ገደቡ ከ19 እስከ 30 ዓመት ነው።

ቁመት ቢያንስ 1.58 ሜትር እና 212 ሴ.ሜ የሆነ ክንድ ለሴት እንዲሁም ለወንድ ቢያንስ 1.70 ሜትር ቁመት መሆን አለበት።

የምዝገባ ጊዜው ከህዳር 08/2017 ዓ/ም እስከ ህዳር 12/2017 ዓ/ም ነው።

ምዝገባው ፦
- በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ (አዳማ)
- አዲስ አበባ (በኦንላይን ልክ ማመልከቻው ሲከፈት ይፋ ይደረጋል)
- አምቦ ዩኒቨርሲቲ (አምቦ)
- አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ (አርባ ምንጭ)
- አሶሳ ዩኒቨርሲቲ (አሶሳ)
- ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ (ባህር ዳር)
- ወሎ ዩኒቨርሲቲ (ደሴ)
- ድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ (ድሬዳዋ)
- ጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ( ጋምቤላ)
- ጎንደር ዩኒቨርሲቲ (ጎንደር)
- ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ (ሀዋሳ)
- ጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ (ጅግጅጋ)
- ጅማ ዩኒቨርሲቲ (ጅማ)
- መቐለ ዩኒቨርሲቲ (መቐለ)
- ወለጋ ዩኒቨርሲቲ (ነቀምቴ)
- መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ (ሮቤ)
- ሰመራ ዩኒቨርሲቲ (ሰመራ)
- ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ (ወልቂጤ) ይከናወናል።

ተጨማሪ መረጃዎች፣ የሚያስፈልጉ መስፈርቶች፣ ዝርዝር ጉዳዮች እንዲሁም ሌሎችም የወጡ ማስታወቂያዎች በዚህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድረገጽ ላይ ሰፍሮ ይገኛል ይመልከቱ 👇
https://corporate.ethiopianairlines.com/AboutEthiopian/careers/vacancies

@tikvahethiopia
report አደራረግ tiktok account ለማዘጋት.pdf
2.7 MB
አካውንቱን በህብረት Report የማድረግ ዘመቻ
=================================
(ግለሰቡ በየቀኑ እኩይ የጥላቻ ሰበካውን የሚያሰራጭበትን አካውንት report አድርገን ከማዘጋት እንጀምር!
ሁሉም ይህን ዘመቻ ይቀላቀል ዘንድ ሁላችንም ጉዳዩን እናሰራጭ!)
||
Report የማድረግ መርሃ ግብራችን ተጠናክሮ ይቀጥል።
አንዳንዶች በማወቅም ይሁን ባለማወቅ Live ላይ የምትከታተሉና አለፍ ሲልም እዛው ገብታችሁ መልስ ለመስጠት የምትሞክሩ አላችሁ። በቂ ዕውቀት በሌላችሁና በተገቢው መልክ መግለፅ የማትችሉ ዱዳዎች መድረኩን ለሚችሉበት ወንድሞች ለቃችሁ ሪፖርት አድርጋችሁ ብቻ ውጡ። ነጥብ ታስጥላላችሁ!


Report አደራረግን በተመለከተ ይህ ሶፍት ኮፒ ሁሉንም ቅደም ተከተሎች በግልፅ ስለሚያሳይ፤ ወደ ግለሰቡ የቲክቶክ አካውንት በዚህ ሊንክ ግቡና ሪፖርት አድርጉ።

ሪፖርት ማድረጋችን ውጤት የሚኖረው ደጋግመን ስናደርግና ብዛት ሲኖረው ነው። የርሱን እኩይ ተግባር በድብቅና በይፋ የደገፉ መንጋዎቹ ኮፒ ሊንክ እያደረጉና በዘመቻ መልክ ፎሎወሩን እያበዙ ስለሆነ፤ የቱንም ያክል ሚሊዮን ፎሎወር ቢኖረው ሪፖርት ማድረጋችንን ካጠናከርን በአንድ ጊዜ አካውንቱ ሙሉ በሙሉ ይዘጋል።

ሪፖርት ለማድረግ የግድ የቲክቶክ አካውንት ሊኖራችሁ አይገባም። ሪፖርት ከማድረግ በፊት አካውንቱን ፎሎው ማድረግ አይጠበቅባችሁም። ተሳስታችሁ ፎሎው ያደረጋችሁ ካላችሁም ፎሎውን አንሱት። ዝም ብላችሁ በዚህ ሊንክ (https://www.tiktok.com/@effoyyy?_t=ZM-8uZBPeh00RB&_r=1) ወደ ግለሰቡ አካውንት ግቡና በተቀመጠው ጋይድላይን መሠረት ስቴፑን ተከትላችሁ ሪፖርት አድርጉ።


ከናንተ በተጨማሪ በዙሪያችሁ ያሉ ሰዎችንም ሪፖርት አስደርጉ። ከአንድ በላይ ደጋግሞ ሪፖርት ማድረግ ስለሚቻል እናንተም ደጋግማችሁ ሪፖርት አድርጉ። ዘመቻውን ሁሉም እንዲቀላቀል መልዕክቱን ለሁሉም አሰራጩ።

በተለይ በዛው በቲክቶክ ሰፈር ያላችሁ ወንድሞችም በዚህ ላይ ኮንተንቶችን እየሠራችሁ ዘመቻው በአጭር ጊዜ ለውጥ እንዲያመጣ እናድርግ። ግለሰቡን ተጠያቂ ከማድረግ ባሻገር ይህንንም ጎን ለጎን እንሥራ።

ሪፖርት አደራረግን ከዚህ PDF በተጨማሪ በጽሑፍና በምስል እንዲሁም በቪድዮ የሚያሳይ ከፈለጋችሁ በነዚህ ሊንኮች አለላችሁ።
√ ጽሑፍና ምስል፦ https://hottg.com/MuradTadesse/40353
https://hottg.com/MuradTadesse/40363
በነዚህ ሊንኮች ላይ ይገኛል።
HTML Embed Code:
2025/06/27 12:29:09
Back to Top