TG Telegram Group Link
Channel: NidaTube -ኒዳ ቲዩብ
Back to Bottom
በኢስላም ንጉስም ብትሆን ስትሞት ነጭ ከፈን እንጂ ሌላ ለብሰህ አትቀበርም!

ዛሬ በ 73 አመታቸው መሞታቸው የተገለፀው እና በህዝባቸው ዘንድ እጅግ ተወዳጅ እንደነበሩ የሚነገርላቸው የተባበሩት አረብ ኢምሬትሶች ፕሬዝደንት ሼይኽ ከሊፋ ቢን ዛይድ (አላህ ይዘንላቸው) ሰርዓተ ቀብራቸው ተፈፅሟል::

እጅግ የሃብታም ሃገር መሪ ሆነው ቢቆዩም ሲሞቱ ግን እንደማንኛውም ተራ ሰው ባለ ሶስት ነጭ ከፈን ተጠቅልለው ሰላተል ጀናዛ ተሰግዶባቸው አፈር ውስጥ ተቀብረዋል::

በኢስላም ሁሉም ሰው እኩል ነው:: ንጉስም ሁን፣ የሃገር መሪ፣ ባለስልጣን፣ ባለሃብት ፣ምሁር ፣ደሃ፣ጥቁር ሁን ነጭ ስትሞት የአቀባበርህ ሁኔታ ላይ የምትበላለጥበት መንገድ የለም:: ሃብታም ግድግዳ ውስጥ ደሃ አፈር ውስጥ የሚቀበርበት የቀብር ስነ ስርዓት በኢስላም የለም::

በኢስላም ስትሞት ሃብታም ወይንም መሪ ስለሆንክ ዘመናዊ ሙሉ ሱፍ አልያ የተሽቀረቀረ ሙሉ ልብስ ፣እጅግ ውድ እና ዘመናዊ የሬሳ ሳጥን፣እና ሌሎች አጀባዎች ወዘተ.... እንዲኖርህ አይጠበቅም::

የሃገር መሪ ስለሆንክ ታላላቅ የሃገራት መሪዎች እስኪመጡ ፣ ህዝብ አስክሬኑን እስኪሰናበተው፣ የቀብር ስነ ስርዓቱ ለማከናወን የአደባባይ ድግስ እና የሽኝት ፕሮግራም እስኪካሄድ አስክሬኑ ሳይቀበር ይቆይ የሚባል መርህ በኢስላም የለም::

ማንም ሰው ከሞተ ቶሎ አጥቦ፣በነጭ ከፈን ሸፍኖ እና ገንዞ ሰላተል ጀናዛ በመስገድ ወደ ቀብር ወስዶ መቅበር በኢስላም የተደነገገ ነው::

"የሰው ልጆች ሁሉ እንደማበጠሪያ ጥርስ እኩል ናቸው" የሚለው የነብያችን (ሰዓወ) የእኩልነት አስተምህሮ በህይወት እያሉ ብቻ ሳይሆን ሞተንም ቢሆን በቀብር ስርዓታችን ላይ አንዱ ከአንዱ የሚበላለጥበት መንገድ የዘጋ ነው::
ለሞቱት አላህ እዝነቱን ይላክላቸው

abu dawd

@nidatube
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"ይቺ ሀገር የሁላችንም ናት፣ ሁላችንም በእኩል የምንኖርባት የጋራ ሀገር ናት" ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

ይቺ ሀገር የሁላችንም ናት ፣ ኦርቶዶክሱም ፣አይሁዱም ከመካከለኛው ምሰራቅ ነው የመጡት ግን ይቺ የሁላችንም ሀገር ናት ፣እዚች ሀገር ላይ የበቀሉ ክርሰቲያኖች የአረብ ክርቲያኖች ወይም የግሪክ ክርሰቲያኖች አይደለም የሚባሉት፣እንዲሁም እዚህ ምድር ላይ የበቀሉ ሙሰሊሞች ኢትዮዺያዊ እንጂ የሳኡዲ ፣ የሶሪያ ወይም የኢራቅ ሙሰሊሞች አይደሉም፣ኢትዮዺያዊ ሙሰሊሞች ናቸው።

ሁላችንም በእኩል የምንኖርባት የጋራ ሀገር ናት

ተወዳጁ ኡስታዝ አቡበከር አህመድ

@nidatube
‏ጎንደር ታላቅ አሊም አጣች።
‏ ሸህ ጀማል አደም ሀገር ውስጥም በሰፈር ቂራዓት በውጭም በሱዳን አፍሪካ ዩንቨርስቲ በቂርዓት አቀባበላቸው ፈጣንና ሀፊዝ ነበሩ። የጎንደር ከተማ ዑለማ ም/ቤትን በዘመናዊ አሰራር የተሻለ ሀሳብ በማምጣት ጥሩ እቅስቃሴ ሲያደርጉ የነበሩና የጎንደር ሙስሊሞችን ግፍ በአደባባይ የተጋፈጡ ታላቅ አሊም ነበሩ። አባ-ሼህ ጀማል አደም - ከላቁ የእኛ-ዘመን ዑለሞች መካከል ተጠቃሽ ነበሩ።
‏በጎንደር-ከተማ ሚና መስጂድ፣ ኢማም፣ ኸጢብና ዋዒዝ ነበሩ።

‏የጎ/ከ/ዑለ/ም/ቤትን በነጻ፣ ለሁለት ዓመታት በፀሀፊነት አገልግለዋል። ለአምስት ዓመታት የስራ አስፈጻሚ አባል ኾነው ቆይተዋል። ለውጥ ፈጥረዋል። ‹ሼህ ጀማል አደም› ቢኾንም ስማቸው፣ በ“ሼህ ጀማል ገበሬው” ነው የሚታወቁ። በእርግጥም! የነህው፣ የሶርፍ፣ የመንጢቅ፣ የሉጛ ገበሬ ነበሩ። የዲን ገበሬ ነበሩ። በወሎና በጎንደር፣ እንዲሁም በሱዳን ሀገር ተዟዙረው ሰፊ ዒልም ያካበቱ ታላቅ ዓሊም ነበሩ።

‏ሼህ ጀማል ከወራት በፊት ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ህክምና ሲደረግላቸው ቆይተው በትናንትናው ዕለት ለህልፈት በቅተዋል። መልካም ስራቸውን አላህ ይቀበላቸው። ለወዳጅ ዘመድ፣ ለእኛም መፅናናት ይኹን። አላህ መልካሙን ተተኪ ይስጠን!!!
اللَّهُمَّ اغْفِرْ لَهُ وَارْحَمْهُ، وَعَافِهِ، وَاعْفُ عَنْهُ، وَأَكْرِمْ نُزُلَهُ، وَوَسِّعْ مُدْخَلَهُ، وَاغْسِلْهُ بِالْمَاءِ وَالثَّلْجِ وَالْبَرَدْ، وَنَقِّهِ مِنَ الْخَطَايَا كَما نَقَّيْتَ الثَّوْب الأَبْيَضَ مِنَ الدَّنَسِ، وَأَدْخِلْهُ الْجَنَّةَ، وَأَعِذْهُ مِنْ عَذَابِ الْقَبْرِ وَعَذَابِ النَّارِ
🛑 ለአዲስ አበባ ሙስሊም ማህበረሰብና ለመስጂድ ጀመዓዎቸ ከአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የተላለፈ ጥሪ

ነገ እሁድ መጋቢት 3 | 2015 ከጠዋቱ 12:30 ሰዐት ጀምሮ ጉለሌ በሚገኘው የሙስሊሞች መካነ መቃብር ቅጥር ግቢ የማይቀርበት ቀጠሮ ተይዟል።

ቀጠሮው ወጣት ወንዶችን ይመለከታል።

ስራው ወደ ጫካነት ተለውጦ የጅቦች መራቢያ፣ የሌቦች መደበቂያ፣ የሱሰኞች መነሀሪያ የሆነውን ጉለሌ መካነ መቃብርን ጫካውን በመመንጠር ምቹ የቀብር ስፍራ ማድረግ ነው።

በዚህ ትልቅ አጅር በሚያስገኘው በጉልበታችን ብቻ በሚሰራው ኸይር ስራ ላይ ወላጆች እና ሴቶች ወንድ ልጆቻችሁን እና ወንድሞቻችሁን በመላክ እና በማበረታታት የአጅሩ ተካፋይ ይሁኑ።

ይህ ስፍራ የነገው የእያንዳንዳችን ማረፊያ ነው ቤታችንን እናፅዳ ቤታችንን ምቹ እናድርግ።

📌 ነገ በፍፁም አይቀርም ጠዋት 12:30 ሰዐት ላይ እንገናኝ።

የጉለሌ ሙስሊም መካነ መቃብር አድራሻውን ለማታውቁ

🛑 ከፒያሳና አካባቢው ለምትመጡ:-

እንቁላል ፋብሪካ አደባባዩን አልፋችሁ ወደ ጎጃም በረንዳ በሚወስደው መንገድ በስተ ግራ በኩል

🛑 ከአለም ባንክ፣ ጦርሀይሎችና አካባበከው ለምትመጡ:- ከአውቶብስተራ ወደ ፓስተር ስትሄዱ በስተቀኝ በኩል ሁለተኛ አስፓልት ቂያስ ወደ ሀግቤስ በሚወስደው መንገድ ላይ ወደ ግራ በሚወስደው በመታጠፍ በስተቀኝ በኩል ቀብሩን ታገኙታላችሁ

🛑 ከአስኮ እና አከባቢ ለምትመጡ:- ከፓስተር አደባባይ እንዳለፋችሁ ኖክ ማዲያ ፊት በስተቀኝ በኩል ወደ ጨው በረንዳ ስትታጠፉ ቀብሩን በግራ በኩል ታገኙታላችሁ

🛑 ከጥቁር አንበሳ ለምትመጡ ደግሞ አንዋር መስጂድን አልፋችሁ በቀኝ በኩል ወደ አዲሱ ገበያ የሚወስደውን አስፓልት አልፋችሁ ወለጋ ሆቴል በሚገኝበት አስፓልት ወደቀኝ በመግባት ውሀ ልማቱ ፊት ታገኙታላችሁ
@nidatube
🌙ነገ ጨረቃ ከታየች ሮብ ረመዳን 1 ብሎ ይጀምራል፣ ነገ ካለታየች ሀሙስ የመጀመሪየውን የረመዳን ፆም እንጀምራለን።
አላህ ያድርሰን🙏
@nidatube
መልካም የረመዷን ወር ይሁንልን
ከ48 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎ የተገነባው የዳሩል ሂጅረተይን መስጂድ የምረቃ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ነው።
በምረቃው ስነ ስርዓት ላይ በርካታ እንግዶች ተገኝተዋል።
HTML Embed Code:
2024/05/11 06:12:29
Back to Top