TG Telegram Group Link
Channel: Neshida And menzuma Lyrics
Back to Bottom
~በጀሊል ቁድራ~

{ሰላም አለይካ ነቢ ሰላም አለይካ ነቢ(2×)}
{በጀሊል ቁድራ በኩኑ የተሰራ}>>አዝማች (4×)

ፈለከል ሀምዱ ረቢ ያደረክልን ያነቢ
የኡመቱ ሰብሳቢ ጠባቂ ከመከራ
መቼም ለኛ ደግ ነው በጣም እናመስግነው
የመሳኪን ስንቅ ነው መሸሻ የፉከራ

{አዝማች}

የመደዱ ዘበኛ ከዘለቀ ወደኛ
እናውራው በአማርኛ ቢገባው የእጅ ስራ
ያአላሁ ያካፊ የባሮቹ ደጋፊ
ነብሲያን አሸናፊ ጠብቀን ከመከራ

{አዝማች}

አልፏል ባለመዘራ የስጦታው አዝመራ
በኢናያው መስከሪያ ሲያድለው ለዛ ሁላ
በቁርአን ተፍሲር ማዕና ተናገረ መውላና
ፊት በነኑ ከስምና በኢሻችን ተወራ

{አዝማች}

የመዲናው ሙሽራ ከአስሀቦቹ ጋራ
ግቡልን በኛ ሀድራ ስማችሁን ስንጠራ
መርቀም በነቢ ሀድራ በነሻጣን አደራ
ረሱለላህን ጥራ እንድታገኝ መግፊራ

{አዝማች}

ሲወለዱ በመካ ተዘረጋ በረካ
የደረቀው ዛፍ እንኳ ለመለመና አፈራ
ኑሩን እያፈለቀው ሲሩን እያተለቀው
ሙሂቡን አስደነቀው ኸበሮ ቢወራ

{አዝማች}

ጌታችን የኸለቀው ለራህመት አዘለቀው
በኑር እየተወቀው አስችል ባንተው ባንዲራ
ሙንተሀ ላይ ቢዘልቅ ካለበና ቡራቀ
ኑሮዎ እየደመቀ በአለሙን አበራ

{አዝማች}

የረፍረፍ ከተማ ዘለቀው በጎፍ ጫማ
ኸበሮው ቢሰማ መላኢካው ተጣራ
በመላኢካ ጁንዲ በረፍረፍ ሲራመድ
አብሽር አለው ሰመዲ ድል ቡንዛ ከጎተራ

{አዝማች}

በረፍረፍ ላይ ቢዘልቅ ጫማን እንዳጠለቀ
ጎንበስ ሳልል ያውልቅ ሀያእ አርጎ ቢፈራ
አብሽር የኔ አይናማ ሂድበት በጎፍ ጫማ
ተንቧለል በከተማ እንጫወት እናውራ

{አዝማች}

መቃሙን እያሰፋ እያበጃጀ ስርፋ
በረሱል እየደፋ የሀይባውን ጡሩራ
ወጣና በሱለመ በኑር ገላጠመ
ሄዶ ጉዳይ ፈፀመ ገብቶ በጌታ ሀድራ

{አዝማች}

50 ነበር ሰላቱ ወረደ ወደ 5ቱ
ከጌታችን እንደ ፀንቶ ለኡመቱ ሊያጋራ
ለምነው ተባሲጡ 5 አርገውት መጡ
50 ነበር በሸርጡ በዋጂቡ ሲሰራ

{አዝማች}

ለመዲናው ሙርሰል ስልኬን ልደውል በቀልቤ ሲዋልል እንደሰማኝ ስጣራ
ወዳጁን የከመለው በፈይድ እያባበለው
ስንቱን አስኮበለለው መዲና ለዚያራ

{አዝማች}

እየዋለለ ልቤ ረዘመ ሀሳቤ
ልድረስ ጠይባ ጋር ልቤ በምፅዋ ባስመራ
የሻላቸው ተዋቡ በጣያራ ጋለቡ
መካ ተሳፍረው ገቡ በሰማይ እንዳሞራ

{አዝማች}

በሶፋ እየተነሱ ነቢን እያወደሱ
መዲናን ገሰገሱ ኒያቸው እየጠራ
የሻላቸው ለጢፉ በይቱላህን ጠወፉ
ገጠማቸው ኡኩፉ ከሀጅ እና ከኡምራ

{አዝማች}

በሁቡ እየጋለቡ እያስገቡ ከድልቡ
ተክለው እየጀረቡ አብቦ እየፈራ
የሙሀባ ኩረቲ ለኩሰው በደረቴ
ለዚህ ነው መጎትጎቴ ቢያቃጥለኝ ሀረራ

{አዝማች}... (3×)

__~{ተፈፀመ}~___
ጀማላቸው መጥቶ፡ ቀልቤን ተ‘መጠነው
በዓጀም እንዝርቴን፡ እስቲ ልወጥነው
የውዱ‘ሳት ላንቃ፡ ሆዴን አቃጠለው
ናፋቂው ሚሻለው ሙራዱን ማየት ነው
የሙራዱ ዓይነታ፡ እንደምነው ጦይባ።
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
እንግዲህ ምን አለ ተነውሬ ብነጠል
በወስፋቹሁ ገመድ ቀልቤ ሲንጠለጠል
በወርያቹሁ ብራቅ ልቤ ሲጎነጠል
ምን ይተርፋችኋል ዘላለም ብቃጠል
ክፍሌን ግለጡልኝ በሐድራችሁ ልግባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
ምንነው ያንን ጀማል እኔም ባስተውለው
መሃባው ለቀልቤ ደርሶ ታበሰለው
የመደዱን ግባት እያስተካከለው
ልቤን አቃጠለው ወስፋን ብኸይለው
ሰይፋ ተለተለው ቀልቤን እንደ ዱባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
ሰማይ ሲያጉረመርም፡ መደዱ እንደ ዝናብ
በክፍያም አይደል ፡ ሊያጎርፍ በጥጋብ
የሱ ቅልብተኛ ፡ የለበትም ራህብ
ጀዝቡ ይጎትታል ፡ ወዳጁን ለመሳብ
በከውኑ ይጮሃል ፡ የውዱ ለለባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
ዘላለም ለቅሶ‘ነው ዳኢም እንጉርጉሩ
የወዳጁህ ደረት ፡ ባንቱ ተጎርጉሮ
የቀልብ እድምተኛ ፡ ጦይባ ላይ ጨፍሮ
አቤት! አቤት! ይላል ፡ ቆሞ ተደርድሮ
አንዳንዱ እዛ መሃል ይባላል ና ግባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
የገባማ ጊዜ ፡ ሁሉም ይገለጣል
ያንን ጀማል ማየት ፡ ለዳኢም ይሰጣል
የኛ ቢጤ ደግሞ፡ ቆሞ ያዳምጣል
ተራ‘ኢስቲ‘መርቀው፡ በደጃፍ ይቀልጣል
ምን ይፈረድ ይሆን ?! ለሚስኪን ገገባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
.
አሏሁመ ሶልሊ ዓላ ሙሀመዴ
ሸምሱከ ጧሊዑ ፤ ፊ‘ነዋሂ ጦይባ
ቀድ ኧም፝ ሸርቀን ወገርባ
🍀 🍀 🍀
Channel photo updated
ሠለላ አላ ዘይኑል አለሚን
ጀሊሉ በኑር የመረጠው
አርሹን የረጋገጠው


አልሀምዱሊላሂ ያማረ መጓዜ
ደረሠልን አሉ በጣምጥሩ ግዜ
በፊት ግልፅ ነበር ልጓምም መያዜ
ተሠማማ አሉ መዳኒቴ ሂፍዜ
ለሀሢድ መጋዜን ጨርሰህ አትቁረጠው
ሠለላ አላ x2
ይኑር በነቢ ላይ ሠላትና ሠላም
በነሱም ቤተሰብ ባስሀቦቹም በጣም
ይጉረፍ ላህባቦቹም ልቀቁለት ገዳም
እሺበል ለመንኩህ በሩህም በገላም
ደረሰ አሉ መቃም ፍቅር ያቀለጠው
ሠለላ አላ
ያሚና ልጅ ዘይኔ ሙሃመድ ተሰማ
ባገሩ በመካ በዋናው ከተማ
ኑር ይዞ ቢወለድ ታየለት ከራማ
በትከሻው ነበር የንቤዋ አላማ
ኩፍርና ጨለማ ገደል አሰመጠው
ሠለላ አላ
4አመት ሙሉ ኖሮ ከአሊማ
ለናቱለአሚና መልሳ ተሸክማ
ከእድሜው እስኪሆን 6 አመትማ
2አመት ኑሮ እያላት እማማ
ትውልዱ ቢሰማ ሁሉ አሽቆጠቆጠው
ሠለላ አላ
ደግሞ 8አመት ከእድሜው እስኪቀርብ
ኖሮ ከአያቱ ከአብድል ሙጠሊብ
በኋላ ከአጎቱ ስሙ አባጣሊብ
ያስተኛው ነበረ ከሱኮ አጠገብ
እንዲያድግ በአደብ ኢራን አስቀመጠው
ሠለላ አላ
ነበር አሉ ታማኝ ሰዎች እሚያምኑት
ሙሀመዱል አሚን ብለው እሚጠሩት
ለሱነበር አሉ አደራ ሚሰጡት
ስለዚሀጁንም ቢያሸንፍ ዳሩት
እሱን የሚጠሉት ጨርሶ ይዳጠው
ሠለላ አላ
ከሞላው በኋላ ከእድሜው 40አመት
ነብይነህ ብሎ ጅብሪልን ላከበት
እየደጋገመ ወህዩንም መጣለት
የሚእራጅን ለሊት ቡራቅ ተጫነለት
አጎነበሰለት እያንቀጠቀጠው
ሠለላ አላ
ኢማምሆኖ አሰገደ በበይተል መቅዲስ
ደሞም ወደሰማይ ሙንተሃ ድረስ
ከጅብሪል ጋር ሆኖ ሄደ ገሰገሰ
መለኮች ጀመሩ እሱን ማወደስ
ከአላህ ጋር መጅሊስ ረፍረፍ አስቀመጠው
ሠለላ አላ
ሱጁድ አደረገ ቢንቀጠቀጥ ልቡ
አታህያቱ ሊላህ አለኮ ለረቡ
አሰላም አለይካ አዩሀል ሙሂቡ
ብሎ ቢለው አላህ መልሶ ጀዋቡ
ለኢብነጣሊቡ ለእስልምና አሮጠው
ሠለላ አላ

🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
ሙሳኮ መከረው ጠቃሚ ምክሩ
ከ50 ሰላቶች 5ተሰጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ለአርሽ በጫማ መላልሶ ቢረግጠው
ተርበተበተ አሉ እያስደነገጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
የጀላላውም ኑር በአይኑ ቢያበራ
ፊየዲሂል ቁድራ ትከሻውን ጨበጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ሠጥቶ ተመለሰ በአርዋሁ መፍቻ
በኑሩ ኮርቻ እያቆናጠጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ሰጥቶት ተመለሰ በኑሩ ኮርቻ
በአርዋሁ መፍቻ እያፈናጠጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ሀይለኛነው ክፉ አለው ብዙ ዛቻ
በበድር ዘመቻ ኩፋር የወቀጠዉ
🙏🙏🙏🙏🙏
ላለም በመሀባ ጨርሶ አዋከበው
ለእስልምና ሳበው እያቆናጠጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ወረደለት አሉ ተገምሶ ጨረቃ
የጠራው ወሊቃ የተበጠበጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
አለም እንዲያምነው አሳየውመድህኑ
አቀናው በአይኑ እየገላመጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ከሰይፍ ጠማማ ጨርሶ ወሰደው
መሀባ መረጠው ጨለማ አቀለጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
መውላዬነው ሹሙ የአለም ጠቅላላ
እንደማር ወለላ ዚክሩ የጣፈጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ነቃ ነቃ በሉ ደረሰልን ኑሩ
ልፈንድቅ በዚክሩ
ይፈንዳ ያበጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
መሀባው በልቤ የተጠቀለለው
የተወለወለው
ልሳመው ልምጠጠው

🙏🙏🙏🙏🙏
ለብሼ ልንሸርሸር የጌታየን ካባ
በሆዴ መሀባው የሚገላበጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ከወደደው ሰፊ ከፍያለውን ዋጋ
በመሀባ አለንጋ ልቤን የለጠጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ክፋት የሆነውን ጣለልና ሲሩ
አሁን አሁን ኑሩ የሚለዋወጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
የአለሙ ዳኛ የድሆች መሸሻ
በፍቅር መዶሻ ጀግናን ቀጠቀጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ነቃ ነቃ በሉ ደረሰልን ኑሩ
ልፈንድቅ በዚክሩ
ይፈንዳ ያበጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
እንቅፋትን ጨርስ ከዚህም በኋላ
ዚክርህን ሚጠላ በርዛህን ይዋጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ይውረድ ሰላት ሰላም ላላህ ሙቀረቡ
ወደ አላህ በልቡ ዘውትር ያፈጠጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ወአላ አሊሂ ወሳህቢሂ ዞላም
ደግሞም እጁን ልሳም
ይስጠኝ እንደሰጠው
🙏🙏🙏🙏🙏
ወአላአሊሂ ወሳህቢሂ ዞላም
ደግሞም እጁን ልሳም
ይስጠኝ እንደሰጠው
ያረቢ ሶሊ ወሰሊም አላ
ያ ረቢ ሶሊ ወሰሊም አላ
ሙስጠፋ ሸራቢ ሶፋ
💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚💚
ማልዶ ቢያነሳኝ እንቅልፍ ነሳኝ
ናፍቆቱ አከሳኝ እንዴት ልፋፋ
💚💚
አሁን ምን ነበር ተከፍቶልኝ በር
ያን የኑር ጀምበር ባየሁት ኢፋ
💚💚
አደራ ዘይኔ አልጣው ካይኔ
ያላንቱኮኔ የለኝም ሶፋ
💚💚
ስጋዬ ደሜ ተቃጥሎ አዝሜ
ጠንቶ ህመሜ ይታያል ኢፋ
💚💚
ሌት ቀን መባከን እንደው መብከንከን
ታድያ እንዴት ልስከን ሳላይ ያን ስርፋ
💚💚
እንድሆን ብርቱ እርዱኝ በወቅቱ
ክብረቴን ባንቱ አርጉት የሰፋ
💚💚
ደካማው አቅሜ ስጋዬ ደሜ
ጠንቶ ህመሜ ይላል ሙስጠፋ
💚💚💚
ሌት ቀን ይሰክራል ጉድ ይፎክራል
አንቱን ይጣራል በሁሉም ስርፋ
💚💚
ተነስቶ ማልዶ በሸውቁ ነዶ
ይጣራል አብዶ ልጅሁ በኢፋ
💚💚
ጉድ ነው ተው ጉድ በል የፈይዱ ማዕበል
በከውኑ ዘምበል ብሏል በኢፋ
💚💚
ፈይዱ ሊፈጋ ዳምኖ ተንጋጋ
መጠጫው ዋጋ ሀድራ ነው ሶፋ
💚💚
ይከፈት ባቡ ያጥግብ ዝናቡ
ይደሳ አህባቡ ይመንዳ ኢፋ
💚💚
ይዋላል ልቡ ይጎርፋል እምቡ
ነብዬ ግቡ እሳቱ ይጥፋ
💚💚
ዋለልኩ አልቻልኩም በጣም ሰከርኩም
ሰላም አለይኩም በሉኝ ሙስጠፋ
💚💚
አበደ ልጅሁ ጋቱት ከሀውድሁ
በሰፊው እጅሁ አርገሁ የሰፋ
💚💚
ከዱንያ ጣጣ ና በሉኝ ውጣ
እንድቀናጣ በሀድራሁ ኢፋ

ኑሩን ቢያፈጋው ከውኑን አነጋው
ከፍ ያለው አልጋው የኔ ጎንታፋ
💚💚
ጅብሪል ለለበ እየጋለበ
ሀቁ ገለበ ባጢል ተደፋ
💚💚💚
ከውድሁ ጠጣው ናፍቆት ተቀጣሁ
ስጠራሁ መጣው በሉኝ ሙስጠፋ
💚💚
አድርገው ወረት የሰፋ ክብረት
ያድናል ክፍረትመላ ሲጠፋ
💚💚💚
በኩሌው አይኑ ስንቱ መነኑ
በየ ዘመኑ አህባብመች ጠፋ
💚💚
የሱማ ሸውቅ መድፍ ነው ትጥቅ
በህር ነው ገርቅ በጣም የሰፋ
💚💚
ወዳጄ ዘይኔ ዝለቁ ባይኔ
ገልጧል ሊሳኔ የልቤን ተስፋ
💚💚
ፈጠረው ጀሊል ከ እብራሂም ኸሊል
ዚሉን ሙዘሊል አርጎ የሰፋ
💚💚
ሸራቤ ጠጄ ሶላቴ ሀጄ
ሱለም ሚዕራጄ ሀድራዬም ሶፋ
💚💚
ልበለው ውዴ የዳኢም እዴ
ጋሻዬ ክንዴ የኔ ሙስጠፋ
💚💚
ሶብዩ መንገድ ጀመረ መሄድ
አብሸር ተራመድ በሉት ሙስጦፋ
💚💚
ለመሄድ ርቆት እንዳይቀር ጨንቆት
ውዴዋ አትራቁት ና በሉት ግፋ
💚💚
የኑሩ ገላ የአለም ጥላ
ያረገው መውላ የሁሉም ተስፋ
💚💚
ካንቱ ፈይድ ጋት ሲጎርፍ ልጋት
ሳይገለኝ ውጋት ደም እያስተፋ
💚💚💚
ከፈይዱ መጠጥ ተግቼው ልፍጠጥ
ልገረም ልስመጥ በህሩ እንደሰፋ
💚💚
አለበት ሂጄ ሲል ጠርቶኝ ልጄ
ይዤ እጆን በጄ እዛው ልደፋ
❤️💚❤️💚
ቀለቤ ኩቴ ሸራብ ሚለቴ
ናልኝ ናፍቆቴ ጭንቀቴ ይጥፋ
💚💚
ሩሄ ነህ ጅስሜ ለስጋ ደሜ
ያላንተ ህመሜ በምን ሊጠፋ
💚💚❤️❤️
ናፈቀኝ ኩሌሁ ልይሁ ና ብለሁ
ጉንጭሁን ስሜሁ ናፍቆቴ ይጥፋ
💚💚
ለሚንሀት ለኔ ቁሙልን ዘይኔ
እንደ ጀይላኔ ማዳችን ይስፋ
💚💚
የጀነቱ ለም ራህመተል አለም
አምሳያው የለም ክብረቱ ሰፋ
💚💚
ያ ረሱሉሏህ የኔ ዘንፋላ
ሁኑኝ ከለላ አለም ሲጠፋ
💚💚
ሀድራው ነደደ ኩሌው ተጣደ
አህባብ አበደ ቢታየው ኢፋ
💚💚💚
💚💚
ጩኬ ካንቱ ቤት ብያለው አቤት
ይኸው 40 ቤት ቀለሜ ገፋ
ቀኜም ከዳኝ ላንቱ ግራ ገባኝ ዘይኔ
አንቱን ማዳነቂያ አጣሁሎት ቅኔ
መዴም ለገመብኝ እኮ ምነው ለኔ
በጀርባዬ አርግዤሁ እራቀኝ ብያኔ.
በዘውቅ ሞሽሩኝ ይታይሁ ማዘኔ
በመደድ ልውለድሁ አረፍ እንዲል ጎኔ



በሸውቁ ሰፊና ኬላውን ያለፈ
ከመደዱ ባህር ገብቶ የቀዘፈ
አንድ ሁለት የለለው እልፍ እየአለፈ
በጀዝሙ ሰልፎ ደሞ እየለፈፈ.
በሀድራ ጠያራ ሀዋኡን ሠፈፈ
ጀዝሙን ሸረብ አርጎ ነውሩን ሁሉ አለፈ
🌟🌟🌟🌟🌟
🌟🌟🌟🌟🌟

ምን ቢፈነጭበት ቢበር እንዳሞራ
ቢነሳ ቢቀመጥ ደሞ እንደሰያራ
ሀድራ እያኸመረ ጠጥቶ ቢያጉራራ
ሀዱ አይደረስም ያልፋል በየተራ
💫💫💫💫💫
💫💫💫💫💫

ደግሞ እንደሸማኔ ቀጭን ቢያስፈትለው
ሀድራን ጃኖ ኩታ አርጎ ቢሸምነው
የጀመረው እንጂ የለም የጨረሰው
ነጋ እየጀደደ ይባስ አስለቀሰው
ሸውቁ ሆዱ ገብቶ አንጀቱን አመሰው
ሀበሻ ላይ ዘልቆ መሙን ረፈረፈው
በመጅት በገታ የለም የተረፈው



ወጅት ላይ ቢከትም የመሀባው ሎጋ
ሸዕር እያበጃጀ ስንቱ ጠርቶሁ ፈጋ
ሌት ቀን አሸርግዶ በሸውቁ ቢወጋ
ሀሰን ኢብኑ ኸሊል ጠለመ ካንቱጋ
💗💗💗💗💗
💗💗💗💗💗

ጉድ ነው የሸህ መጂት ስንቱን አሳደጉ
የሀድራውን ገበር አበጁት በወጉ
እስካሉ በሀያት ነጋ አደገደጉ
አሁንም ይጎርፋል በኢብራሂም ደጉ
ደግሞ ባማን አምባ ጉድ በል አስረገደው
በንጉስ በሶቃ ለሱ አስደገደገው
ፊት ተላይ ጀምሮ የለም ያመለጠዉ
ኢብራሂም ያሲንን ስቦ ለመጠጠው
ጌታው ሲራጁዲን መሀባ ቢያገርቀው
ባይተዋር አድርጎ ነጋ አስረቀረቀው
ባብሬት በቃጥባሬ ቆጥሬም አልዘልቀው
በዳና በከረም ለጉድ አጎረፈው
ወረባቦ ዘልቆ ነጋ አስለፈለፈው
ሁሉም ጥጉን እንጂ አንድ የለም ያለፈው
💝💝💝💝💝
💝💝💝💝💝

መሀባ የሚሉት መልክ የለውም አሉ
ሲያስለቅስ ሲያስቀው ቅጥ የለው መግደሉ
እንደ እምቦሳ ጥጃ ሲሻው ማዘለሉ
እንደ ሶብይ ልጅ ያልፍል ነውሩን ሁሉ
በኢሽቅ አንበልብሎ ከቶ ማዋለሉ
ዳኢም በሸሽ ነው ለታየው ጀማሉ
💞💞💞💞💞
💞💞💞💞💞

እኩሉ ሲያነባ እኩሉ ይስቃል
አንዱን በሸሽ አርጎ አንዱን ያስለቅሳል
አንቱን እየሰየ ሌላውን ይረሳል
ከሀድራሁ ሲገባ ይወድቃል ይነሳል
💚💚💚💚💚
💛💛💛💛💛
❤️❤️❤️❤️❤️

እህልም አይሻ አንቱን ካየ ሗላ
ሩሁ ከጀሰዱ ሸሽታ ተነጥላ
ጧት ማታ ጦይባ ላይ ቀልቡ ተንጠልጥላ
አንቱን ሲል ያኸትማል ሀያቱን በሙላ



ሶለላህ አላ ሙሀመድ
ሶለላህ አላ ሙሀመድ
ሙስጠፋ እንዳንቱ የለም ባለም
🌟🌟🌟🌟🌟

ለሶለዋቱ ላፍዶሉ ነገር
ለመሀባዬ ለምነቴ ማገር
ሸርቀን ወገርባ አድርገኝ ገበር
ለይለን ወንሀር ሀድራሁን ልኽደም
ሙስጦፍ እንዳንቱ የለም
💫💫💫💫💫

ሶለዋት እንጂ ትልቁ ግምጃ
ባንድ ኢባራ አስር ነቲጃ
አይበጅም ላለ ሞልቶናል ሁጃ
ኢሽረብ ያ አሂ ከቶም ነው ዘምዘም
ሙስጠፋ እንዳንቱ የለም
⭐️⭐️⭐️⭐️⭐️

✿ከሳር ቅጠሉ እጅጉን በዝቶ
✿ካባይ ጣናም ጎርፎ በርክቶ
✿ምድር ሰማዩን ሀዋዑን ሞልቶ
✿አውርደው በኛ በሆኑት ቅመም
✿ሙስጠፋ እንዳንቱ የለም


ሀድራ አርሂብ ብሎት ሰው የሆነ ሰው
የሸውቁረመጥ ያጥመሰመሰው
ፈይዱን አዝልቆ ገሎ አነገሰው
ግምድል ነው እጣው የዋዛ አይደለም
ሀቢቢ እንዳንቱ የለም
🖤🖤🖤🖤🖤

ከቶ አይገኝም የሀድራ ጥሪ
መሽኡም አባሮ ሀያት ዘዋሪ
ጀሰድ ከምሎ ሩህ አብጠርጣሪ
ከዚህ እድያ ና በሉኝ ታደም
ወርቄዋ እንዳንቱ የለም
💝💝💝💝💝

እድያውማ ትርፍ አለው አሉ
አንቱን ላለ ሰው ሀያቱን ሁሉ
ሩሁን ለሰጠ አልፎ ካካሉ
እንዲህ ነው ሸርጡ ሙቶ መሸለም
ሀያቴ እንዳንቱ የለም
💞💞💞💞💞

✿ከስብ ወንድሜ ነቃ በልማ
✿አትዘንጋ በቀን አትበል ጨለማ
✿ እነ አባ ሙራን እለፍ ሳትሰማ
✿ግባ በል በሩህ በወዳጅ አለም
ሙስጠፋ እንዳንቱ የለም
💓💓💓💓💓

ና ብለሁ ጊዜ በህሩ ንከሩኝ
ባንቱ ልኬት ልክ መድሁን አሽርቡኝ
በኑር እጃችሁ ዳብሱኝ ከምሉኝ
ከቶ እስከ መቼ ዳር ለይ መስለምለም
ወላሂ እንዳንቱ የለም
💗💗💗💗💗

የሳቡህ እንደው ወደ ሀድራቸው
ሩህ ያዋልላል ሲፋ ለዛቸው
ሌት ቀን ሀድረህ ከቶ አጠግባቸው
በለቅሶ ኑረህ በለቅሶ ማኽተም
ሙስጠፋ እንዳንቱ የለም


✿አይሻም ደሞ ሳቢ ደላላ
✿አህባቤ ንቃ ለዚ ሶለላ
✿ጠበቅ አድርህ አብሽር አትላላ
✿በሶለዋቱ ገብተህ ተጠቀም
ሙስጠፋ እንዳንቱ የለም
🧡🧡🧡🧡🧡

ካንቱ ወዳጆች ስላንቱ ሰማን
ታውቃለሁ አሉን ማከም የደማን
ምነው በኛ ላይ መደድሁ ጠናን
ሳቡን ከገፍላ አንሻም መጥለም
ሙስጠፋ እንዳንቱ የለም
💕💕💕💕💕

✿ገላፍ ቡዘና ዝንጋት ተውና
✿በዐደብ ሁነህ ተሸመርና
✿ልገማ መሽኡም ወዲያ ጣልና
✿አውርድ ለውዱ ሶሊ ወሰለም
ሙስጠፋ እንዳንቱ የለም
💜💜💜💜💜

ከቶም በኔ ላ ይ ቢዳምንብኝ
ዶፉን በላዬ አዘነበብኝ
ገፍላ የሚሉት አጎረፈብኝ
አንሳው ጀባሩ የኸይሩን ሸክም
አህመዴ እንዳንቱ የለም
💙💙💙💙💙

ዝንጋት እርሳናን ካነሳህ ሗላ
ኢጅማዑል ሙዕሚን ወንድሙን ሁላ
ኢልሚን ወተምኪን አርን ከማላ
ሙስተኢድ አርገን ዲን ለመኸደም
ሀቢቢ እንዳንቱ የለም፡፡
💚💚💚💚💚
💛💛💛💛💛
❤️❤️❤️❤️❤️

🌼🌼ወላሂ
🌻🌻ናፍቆቴ
🌹🌹አባቴ
💐💐ጀነቴ
🌺🌺ሀቢቢ
☀️☀️ጠቢቢ
⭐️⭐️ውዴዋ
🍀🍀🍀ጀነቴ
🌴🌴🌴🌴ጥላዬ
🍀🍀ጀነቴ


💚💚💛 እንዳንቱ የለም በአለም💚💚💛
👳‍♀️ ገለታ ዬድረስዉ                 አአአ  ከተዉሂድ ጅረት ላይ
                    ሩሁን ላነገሰዉ                             ለኛ አንዳፈሰሰዉ

👳‍♀️ከዉኑን ለርሳ ላንቱ                     ሩሁን አልፎ ዘልቆት
                        በልፍኙ ደገሰዉ                         ለኛዉ አወረሰዉ

👳‍♀️ራህመቱ መርጊያ                         የነቢ ዙፋኑ
                       ከዉናቱ ያረጋዉ                  የ ራህመት መፍለቂያዉ

👳‍♀️ለሱ የሻማቸዉ                   አሄሄሄ   ለስሙ ሸኽረዉ
                    ሰታቸዉ ካደጋዉ                                ተገኙ ከሊቃዉ

👳‍♀️አሀሀ  ጨለማዉን                                 ጉልበታቸዉ አልቆ
                      አራት ሽበት እስኪያፈጋዉ             መሬት እስኪያደሀዉ

👳‍♀️ፈርጣማዉ ከንዳቸዉ                              የአርጅና ጉተት
                            ከአለት የጠናዉ                             እስኪሸበሽበዉ

👳‍♀️እእእየኡምራቸዉን ጠጅ                            የኡምራቸዉን ጠጅ
                         ላህዱ እስኪጠጣዉ               ላህዱ እስኪጠጣው   

👳‍♀️በሁቡ አልቅሰዉ                         እናቱን እንዳጣ
                     እንባቸዉን ጨርሰዉ                          ህፃን ተንፈቅፍቀዉ     
      
👳‍♀️ሀዘን ፊታቸዉን                               በትካዜ መርከብ
                    ዳምኖ እስኪያጣቅረዉ                     እንዳሉ ተጭነዉ

👳‍♀️ቀናት በነሱ ላዬ                     አሀሀ  ደሞ ሲያስደሳቸዉ
                    ያልፋሉ ተቆጥረዉ                           ደርሳ ጀምልሆ

👳‍♀️የፊታቸዉ ጀንበር                       ሳቀቸዉ ይነጋል
                       ግርዳዉን ጥሰዉ                      ሸሽቶ ጨለማዉ

👳‍♀️ደሞቃ ትሞታለች                በየደረሱበት 
                     ሀዘኑን ግፋዉ                             ነቢን ሚከርሩ

👳‍♀️ጠልፎ ያዛቸዉ ነዉ የፈዬዱ ዘሩ           ሲያደምጡ
                           በነቢ መንገድ ነዉ                      ሲያወሩ

👳‍♀️ዚክሮን ሲያጎርፉ                       ከነሱ እስኪያልቅ
                         አንዴም ሳያባሩ                      ተንጠፈጥፎ ኡምሩ

👳‍♀️አሀሀ በቀብሩ አዳራሽ                  ዘልቆ አስኪጠራቸዉ
                             ድግስ ተደግሳ                  መለከል መዉት ደርሳ

👳‍♀️በሩሀቸዉ ሜዳ                  ነቢን እየጠሩ
                    ዱንካን ተቀልሶ                    አለቁ በ ለቅሶ
👳‍♀️                           አለቁ በለቅሶ
- አልፊ ሰላት ወሰላም አላ ነቢ አልፊ ሰላት ወሰላም አላ ነቢ  ሰይዲ       ያረሱለላህ                       *(2)
ኦሆዬ በዉበቱ ግርማ ከላይ ዉስጡን ታንጣ
ሁሉንም በለጠዉ መጨረሻ መቶ
ሽርኩን ገለባብጣ በተዉሂድ አንጣ
አበራዉ አለሙን በኑር እየቀባ 
                   ሰይዲ       ያረሱለላህ           
መፈጋፈግ እንጂ ምን ሊችለዉ እዉነቱን
እንቅጩን ለማስፈር የርሳማ ሲፈቱን
ማን በነገረልኝ ሆዴ መባባቱን
ጀማል ሰቶታል የሙስጠፋ ሀይባ
                   ሰይዲ       ያረሱለላህ     
ገና ፈትም ሆና ከናቶት መሀጠን
ጫልዩ ቢታጩ መድሁን ለማጠንጠን
ስንቱን ምት አነቁት ሰላዋት በማጠን
ለኛዉም ይሰጠን የነሱ ሙሀባ
                    ሰይዲ       ያረሱለላህ
የርሱ ስም አይደል ወይ ሲድቅን ያላቀው
ኡመሩል ፋሩቅን በከሽፍ ያደመቀዉ
ኡስማንን የሀያ ዝናን ያስታጠቀዉ
አሊን ያሳደገዉ ሂዳያ ያጠባ
                      ሰይዲ       ያረሱለላህ
የሙህሲሪን ፈሊጅ ሲሩን ያፈለሰዉ
የቡራኢን ሀዘን ጠራርጎ ያበሰዉ
የዘቡራን ልጃ ልሳን ያቀመሰዉ
አንዩን ዳንዩን መቃም ያደረሰዉ
አብደርዬን በኢልም ጅህልናን ያስገረፈዉ
ሸ አሊ ጎንደርን ሞት ያስቀሰቀሰዉ
ስንቱን አነገሰዉ ከ ኸልዋ ያስባ
                      ሰይዲ       ያረሱለላህ
በልቼ እየጠጣዉ ያርብ ይጠምኛል
መድሀኒት ወስጄም አጥብቆ ዬጠማኛል
መከዳ ታቅፌ አንቅልፍ እንቅልፍ ይርቀኛል
መነመነ ጅስሜ በናፈቅት እየሰባ
                       ሰይዲ       ያረሱለላህሀ
ጀሊሉን የርሳን ስም በክብር ሲያኖጋዉ
በተጠራ ቁጥበዠር ባንድነት ያሰጠራዉ
እርሱ ነዉ አማላጅ እሱ ነዉ ባላልጋዉ
ከዉኑን ያረጋጋዉ መስመር እያስገባ
                   ሰይዲ       ያረሱለላህ           
አልፉ ሰላት የፍቅርሆ ንጋት
የኔ ጌታ በላዩ ላይ ዘልቆ
አልፉ ሰላት የሰራ አካላቱ
የኔ ጌታ ያልቃል እምባ አፍልቆ
አልፉ ሰላት ከዉስጡ አየገባ
የኔ ጌታ ትንፋሹን ሰንጥቆ
አልፉ ሰላት ያስወተዉተዋል
የኔ ጌታ ያን ጨረቃ ናፍቆ
የኔ ነቢ ይወድቃል ተንጋሎ
ወላዬ አረፋዉን ደፍቆ
ጌታዬዋ ነብሱን ያስተዋል
የኔ ጌታ ልብን ተሰንጥቆ
አልፉ ሰላት ይዛ ያነፈለዉ
አልፉ ሰላት ዉስጡን አማሙቆ
የኔ ጌታ ፍጥረት የተባለ
አልፉ ሰላት ይተወዉ አልቆ
አልፉ ሰላት ጀምበር ከመዲና
የኔ ጌታ እየታየዉ ዘልቆ
      ሰይዲ       ያረሱለላህ
አልፉ ሰላት አንቺ የ ህይር ንፋስ
የኔ ጌታ ገልጠሽዉ ልቤን
አልፉ ሰላት ብለሽ ንገሪልኝ
ወለላዬ ለዛ መካንን
እህህህ ዛሬስ አዳረሰዉ
አልፉ ሰላት የሰራ ቃሉን
የኔ ጌታ ጉበቱ ነደደ
አልፉ ሰላት አፈላዉ ደሙን
የኔ ጌታ ስጋዉን ጨርሳ
አልፉ ሰላት አወራዉ ጅስሙን
የኔ ጌታ አበደ ጨርሳ
የኔ ጌታ ወሰደዉ ልቡን
አልፉ ሰላት አካላቱ አለቀ
የኔ ጌታ ተፍቆ አንዳንጀት
የኔ ጌታ ሰጋዉን አክስቶ
የኔ ጌታ ይሄዳል ባጥንት
የኔ ነቢ ጉበቱ ሁላ ሳስቶ
አልፉ ሰላት እንደ ወረቀት
የኔ ጌታ ሲቆም ደና መሳይ
አልፉ ሰላት ልብስ ሸፍኖት
የኔ ጌታ ነዉ እንጂ እስከ ቀኑ
አልፉ ሰላት ነዉ እንጂ እስከ ቀኑ
አልፉ ሰላት አይተርፍም ከሞት
ወለላዬ ያደረጉልኝ ዘንድ
አልፉ ሰላት የቡርሀን እልፍኝ
የኔ ጌታ አካሀኔን ሁላ
የኔ ጌታ አንድትነግርልኝ
አልፉ ሰላት አካላቴ አለቀ
አልፉ ሰላት ጉልበቴም ከዳኝ
የኔ ጌታ አጥንቴም አለቀ
የኔ ጌታደሜ አቃጠለኝ
አልፉ ሰላት ቀኑም ተራዘመ
ጌታዬዋ እኔንም ጎዳኝ
                   ሰይዲ       ያረሱለላህ
ጌታዬዋ ምን መክሳት ቢቻ ነዉ
አልፉ ሰላት ከቶም አለቀ እንጂ
የኔ ጌታ አጣድፎት ማበሉ
አልፉ ሰላት የናፍቆቱ መዉጅ
የኔ ጌታ እዋኛለዉ ብሎ
አልፉ ሰላት አንጋ ሳያበጅ
የኔ ጌታ ተሻግሮ ሊጠለም
የኔ ጌታ የመዲናን ጀንበር
አልፉ ሰላት የ አሽራፎቹን በርጂ
የኔ ጌታ ጠጣዉና ሁሉም
የኔ ጌታ የፍቅህን ጠጂ
5=�  �💛ነቢ ሰላም አላ💛💚
   💚💛ሰላም አላ💛💚
💚💛ረሱል ሰላም አላ💛💚
💚💛ሰላም አላ

🎼ቢስሚላሂ ብዬ      መድሁን ጀመርኩት
🎼ጌታዬን ላመስግን     ላረገኝ ኡመት
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼ያ ሀቢበሏሒ የአለሙ ራህመት
🎼አንቱን እየጠራሁ ብሞትም ልሙት
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼ጀሊሉ ጀምሮት እኛን ያዘዘዉ
🎼ሰሉ አለ ነቢ በሉ ነዉ ያለዉ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼እኔስ የገረመኝ የኻሊቁ ነዉ
🎼ፈጥሮት ሲያበቃ ወዳጄ ያለዉ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼እወድሃወለውኝ አፍቅሮዋለውኝ
🎼አንቱን እላለውኝ ፀንቼ በቃሌ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼መዲናን ዘየርን ሰዎቹ ቢሉኝ
🎼ናፍቆት አቃጠለኝ ሆዴን አባባኝ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼አንድ ሺ ዓመት የበራው እሳት
🎼በነቢ ውልደት አለ ጭልም ድርጋም
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼እንኳን አደረሰን ለነቢ መውሊድ
🎼ለታላቁ ነቢ ለአህመድ ሙሐመድ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼የሚለው አያጣም ሰው ያለውን ይበል
🎼እኛ በሀድራችን ነቢ ነቢ      እንበል
             🌟🌟🌟🌟🌟
🎼ነቢ ያንቱን ነገር ቢከትበዉ ቢፅፈዉ
🎼የጀመረዉ እንጂ የለም የጨረሰዉ
             🌟🌟🌟🌟🌟
🎼የአለሙ መብራት የአለሙ ዘዉድ
🎼የሚያምረዉ ነብዬ ዘይኔ ሙሐመድ
             🌟🌟🌟🌟🌟
🎼አህመድ ኸይረል ወራ እወድሗለሁ
🎼አንቱን የመሠለ ፍፁም አላየሁም
             🌟🌟🌟🌟🌟
🎼አዋጅ ይሰማኛል ከላይ ይመስለኛል
🎼አብሽሩ የሚለው ከሀድራው ቀበሌ
             🌟🌟🌟🌟🌟
🎼የሙርሶሎች አውራ የኛ ሙሐመድ
🎼አበደን አዲስ ነው ያንቱ መውሊድ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼ያረሱለሏህ አሁንም አሁን
🎼ያለንበት ሀገር አያስተማምንም
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼የዘይኔ ሙሀባ በቀልቡ የገባ
🎼እንቅልፋ አይፈልግም ያድራል እያነባ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼ይሄ ሁሉ አህባብ ሀቢቢ ሚለዉ
🎼ቢወዱህ ነዉ እንጂ ሌላ ምን አለዉ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼አበዱ አበዱ አበዱ ይሉናል
🎼እኛስ አላበድንም ሙሀባ ይዞናል
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼ያሙናል በወንጀል በለለብን ጥፋት
🎼ነቢ ነቢ ብዬ ሰሞት ሲጠራ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼አሪፎች ቢተክሉት የሙሀባን ዛፍ
🎼ዘላለም ያፈራል ቂያማ ድረስ
              🌟🌟🌟🌟🌟
🎼የመውሊዱን ጠላት ልምታው እንደ ድቤ
🎼እኔ እንደወዝወዝ እርሱን አንገብገቤ
17…መርሀባ ነቢ መርሀባ             መርሀባ
መርሀቤ ነቢ መርሀባ             መርሀባ

ሲወለድ ነቢ ጁሀሩ
አበራ ሰማይ ምድሩ 
👏👏👏👏👏👏👏
ሲወለድ ነቢ ሙስጠፋ
ያ ወስዋስ ድራሹ ጠፋ 
👏👏👏👏👏👏👏
ሲወለድ አይኑን ተኩሎ
አነሳው ጅብሪል ቸኩሎ 
👏👏👏👏👏👏👏
ሰይዲ የኛ ነው የኛ
አንሰጥም ለወንጀለኛ 
👏👏👏👏👏👏
ሰይዲ ተጣራ እኮ
ሀቢቢ ሩሂ ፊዳኩ 
👏👏👏👏👏👏
አንቱ የጠይባው ነጋዴ
ሰላም በልልኝ አህመዴ
👏👏👏👏👏👏
ናፈቁኝ ሩሄ ባባ
ውሰዱኝ ሀገሮ ጠይባ 
👏👏👏👏👏
ያለ ዘይንዬ ሙሀባ
አንድ የለም ጀነት የገባ
👏👏👏👏👏👏
የቆላም ሆነ የደጋ
ውሰደኝ ይላል ነቢ ጋ
👏👏👏👏👏
እሸት ነው ሁሌ እሸት
የለሌላው በጋ ክረምት
👏👏👏👏👏👏
ሰይዲ የኛ በሻሻ
ለተጨነቀ መሸሻ 
👏👏👏👏👏👏
🎼ያነቢ ሰለ ማለይካ
🎼ሰለዋቱላ አለይካ

👏👏👏👏👏👏
መርሀባ ያ ኑረል አይኔ
መርሀባ ጀደል ሁሴኔ 
👏👏👏👏👏👏
🎼ለጀነት ሀገር መክፈቻ
🎼መረጠ ሙስጠፋን ብቻ
👏👏👏👏👏👏
ነቢ ኖት ለወንጀሌማ
ሳሙናዬ ማጠብያዬ
👏👏👏👏👏👏
መዲና ሀገር ልሂድ
ካሉበት የኔ ሙራድ
👏👏👏👏👏👏
🎼አንቱን ከይዛን አንሸሽም
🎼ጀብረ እያለች ብመሽም
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼አይቀርም ሸድድ መውደዱ
🎼ሂም ሂም ሲሉ መውሊዱ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼ካልሆነ በቀር ነው ለአሏህ
🎼የለም መውሊዱን ሚጠላ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼አንተዬ ሚትለው ለሱ
🎼ማር ለመረራው ምላሱ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼እንደ ጫሎች ይንደድ
🎼ሂም ሂም ይበል መደድ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼የዙበራ ልጅ ወንድ ወዱ
🎼ፍትሁን ካላዩ ማይበርዱ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼ያማረው ሞላ የደነው
🎼ሙስጠፋል ወራ ባንቱ ነው
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼ሙስጠፋ የከወኑ ማሕድ
🎼የሙሂቦች ሙራድ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼አሚናት ወልዳ ጨረቃ
🎼አበቃ ኑርና ሀይባ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼እስማኤል ማር ወለላ
🎼አንገቱ ሰጠ ለብላ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼የኔ አብሬት ወዳጅ
🎼አኛንም ወደዱን እንጅ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼የኔ ሾንክይ ወዳጅ
🎼እኛንም ውደዱን እንጅ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼የበነ ሀሻም ጨረቃ
🎼አበቃ በነቢ ሀይባ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼የጀነት ሀገር ሙሽራ
🎼አንቱ ኖት ይኸይረል ወራ
👏👏👏👏👏👏👏👏👏👏
🎼አንቱ ኑር አንተ በድሩ
🎼አንቱ ኑራ ፉቁ ኑሮ
👏👏👏👏👏👏👏
🎼መርሀባ በለን ሰይድ
🎼ጠራኖት እኛም እንግድ
HTML Embed Code:
2024/06/11 21:44:44
Back to Top