Channel: ደብዳቤዎች ❤💖
የቅዳሜ ቀደዳ-28(፳፰)
እንደም ነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? ወደ ቅዳሜያችን መጥተናል!
ምን መሰለህ?
.
.
.
አንድ ፀዴ መፅሃፍ እያነበብኩ ነው! የመፅሃፉ ርዕስ "Leaders Eat Last" ይላል! "...መሪዎች መጨረሻ ላይ ይመገባሉ/
ይበላሉ!..." እንደማለት ነው። የመፅሃፉ ፀሃፊ "Simon Sinek" ይባላል። ወጣት፣ ፀዴ፣ አንባቢ እና የተከበረ ምሁር ነው። በእድሜ የሚበልጡትን የዓለም መሪዎች "...እንዴት ህዝባቸውን መምራት እንዳለባቸው!..." ያስተምራቸዋል! እርሱ ብቻ ሳይሆን ተቋማትን የሚመሩ ግለሰቦች ".....በምን ማመን እንዳለባቸው? የአመራር ጥበብ ምን እንደሆነ? እና ለምን ግብ(ዓላማ) መስራት እንደሚገባቸው?..." ይናገራል! "Simon Sinek" ታላላቅ የዓለም መሪዎችን እና ግዙፍ ኩባንያዎችን የሚያማክር፣ "World Government summit" ላይ ተጋብዞ የአለም መሪዎችን እና የቢዝነስ ሰዎችን ስለ አመራርነት ብቃት ፊደል የሚያስቆጥር፣ "Tedtalk" ላይ በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ግለሰቦች የሚከታተሉት እና ትልልቅ ዩኒቨርስቲዎች እና የቢዝነስ ፎረሞች ላይ ረብጣ ገንዘብ ተከፍሎት ንግግር የሚያደርግ "ወሳኝ" ሰው ነው።
ከሁሉም የገረመኝ "Leaders Eat Last" የተሰኘው መፅሃፍ መግቢያ ላይ ያስቀመጠው መንደርደርያ ታሪክ ነው!
ከዚያ በፊት እኔ መንደርደሪያ ልስጥህ!
እ.ኤ.አ መስከረም 11, 2001 ላይ አሜሪካ በታሪኳ ታይቶ የማይታወቅ የሽብር ጥቃት ተፈፅሞባታል። ለሽብር ጥቃቱ አልቃይዳ (Al-Qaeda) እና የቡድኑ መሪ የሆነው ኦሳማ ቢን ላደን (Osama bin Laden) ሃላፊነቱን ወስደዋል! የወቅቱ የአፍጋኒስታን መንግስት ታሊባን (Taliban) ለዚህ ቡድን ድጋፍ እና ከለላን እያደረገ ነው በማለት አሜሪካ አፍጋኒስታንን የሽብር ጥቃቱ ከተፈፀመባት አንድ ወር እንኳን ሳይሞላ የዛሬ 20 ዓመት ገደማ ወራለች!
የመፅሃፉ መንደርደሪያ ታሪክ!
ግዜው እ.ኤ.አ ነሃሴ 16, 2002 አፍጋኒስታን ውስጥ ነው። ሰማዩ ጉም ለብሷል፣ ጭጋጋማ ደመና እና ምሽቱ ተጨማምሮ ቀኑን ደባሪ እና አስፈሪ አድርጎታል፣ ዝናብ ሊዘንብ እያጎበደደ ነው። ከጉሙ በላይ ምን እንዳለ ለማየት ከባድ ነው! ጨረቃም ሆነች ከዋክብት አይታዩም! ቦታው አንድ የአፍጋኒስታን ገጠራማ መንደር ውስጥ ነው! 22 የአሜሪካ ልዩ ሃይሎች (special forces) አንድ በጥብቅ የሚፈለግ ግለሰብን ይዘው እያጓጓዙ ነው! መሽቷል! አፍጋኒስታን እጅግ ሰንሰለታማ ተራሮች፣ ሸለቆዎች እና ገደሎች ያሉባት ሃገር ናት! በዛ ላይ አቧራው ቆሞ ይሄዳል! እነዚህ ልዩ ሃይሎች በነዚህ ሰንሰላታማ ተራሮች እና ገደላ ገደሎች መሃል ሲያቋርጡ የ "Taliban" ታጣቂዎች ጥቃት ሊሰነዝሩባቸው ይችላሉ! በተመሳሳይ ሰዓት አደጋ ቢደርስባቸው እነሱን ለመጠበቅ በተጠንቀቅ ከደመናው በላይ ሁለት "A-10 Warthog" የሚሰኙ ተዋጊ ጀቶች አሉ። የአንዱ ተዋጊ ጀት አብራሪ "Captain Mike Drowley" ይባላል!
"A-10 Warthog" የሚባሉ ተዋጊ ጀቶቹን ይዘው ከደማና በላይ ላሉት ሁለቱ ሽፋን ሰጪ ፓይለቶች ሁሉም ነገር ምቹ ነው። ጨረቃ ፈክታ ትታይቸዋለች። ከዋክብቶቹ በርተዋል። ሁሉ ሰላም ነው! ከደመናው በታች ግን 22 የአሜሪካ ልዩ ሃይሎች ህይወታቸውን አደጋ ላይ ጥለው በአስፈሪዎቹ የአፍጋኒስታን ገደላ ገደሎች መሃል እያቋረጡ ነው!
"Captain Mike Drowley" በመገናኛ ሬድዮ ውስጥ የባልደረቦቹን መረበሽ ይሰማል! ከድምፃቸው የሆነ የተጨነቁት ነገር እንዳለ ይረዳል! አደጋ ላይ እንደሆኑ እስካልተነገረው ድረስ ሽፋን ለመስጠት ጀቱን ይዞ ወደ ታች መብረር አይጠበቅበትም! ነገር ግን የድምፃቸውን መረበሽ በማስተዋል አብሮት ያለውን ሌላ አብራሪ "እዚው እንዲጠብቀው" ይነግረውና ከነበረበት ከፍታ ተዋጊ ጀቱን ይዞ ወደ ምድር ዝቅ ማለት ይጀምራል! በሚገርም መገጣጠው "Captain Mike Drowley" ባልደረቦቹን ለማየት ወደ ምድር እየበረረ ባለበት ቅፅበት በሬድዮ መገናኛው አንድ መልዕክት ይደርሰዋል! "Troops in contact!" የሚል ነበር! ይህ ማለት ደግሞ "....የአደጋ ላይ ነን! ድረሱልን!..." ጥሪ ነው!
በህይወቱ ለመጀመርያ ግዜ ከስልጠና እና ከፊልም ውጪ "troops in contact" የሚለውን የእርዳታ ድምፅ ጥሪ የሰማው ያኔ ነው።
ሃይለኛ ንፋስ ይነፍሳል፣ አቧራው አደገኛ ነበር! "Captain Mike" በሬድዮ ውስጥ ይህንን መልዕክት ሲሰማ የቦንብ ፍንዳታዎች እና የተኩስ ሩምታዎች ይሰሙት ነበር። በግዜው አሁን ላይ የደረስንበት ቴክኖሎጂ ላይ አልደረስንም! አካባቢውን እንኳን በደንብ ለመረዳት የሚያበቃ ካርታ የለም! የነበረው እ.ኤ.አ 1980 ላይ የቀድሞዋ ሶቭየት(ራሽያ) አፍጋኒስራንን በወረረችበት ወቅት ስትጠቀምበት የነበረን ያረጀ ካርታ ነበር! ካርታው ላይም ቦታዎቹ የተፃፉት በራሽያ ቋንቋ ነው።
የያዘውን "A-10 Warthog" ከአንድ ሺህ ጫማ በታች እያበረረ ባልደርቦቹ ላይ ተኩስ ከከፈቱት ታጣቂዎች ጋር ውጊያን ገጠመ! ይህንን የሚያደርገው ለመሬት እጅግ ቀርቦ በሁለት ትልልቅ ገደሎች መሃል እየገባ እና እየወጣ ነው! የመከስከስ እድሉ ሰፊ ነው። ስልጠና ላይ አይደለም! ፊልም ቀረፃ ላይ አይደለም! የያዘውን ካርታ አይቶ ከፊት ለፊቱ የሚደቀኑ ተራሮች ላይ ላለመላተም የራሱን ግምት በዘፈቀደ ሰርቶ ጠላት ላይ ከተኮሰ በኃላ ወደ ላይ ይወጣል! እንደገና ተመልሶ ይወርድና ጠላት ላይ ተኩሶ ተራሮች ከፊቱ ሲደቀኑ ወደ ላይ ይወጣል! አባዬ! "A-10 Warthog" ተዋጊ ጀቶች ወደ መሬት በጣም ከመቅረባቸው የተነሳ ጠላት ከቅርብ ርቀት በመሳርያ መትቶ መጣል የሚችላቸው አደገኛ ጀቶች ናቸው።
በዚህ ውጊያ መካከል ከ 22ቱ የአሜሪካ ልዩ ሃይሎች ይቀበል የነበረው የሬድዮ መልዕክት ተቋረጠ! ይህ ዝምታ ለእርሱ አስደንጋጭ ነበር! "... የገዛ ባልደረቦቼን አድናለሁ ብዬ ሳላውቅ ቦንብ ጣልኩባቸው እንዴ? ወይስ ታጣቂዎቹ ገደሏቸው? ምን ተፈጥሮ ነው?..." እያለ በሃሳብ ሲኳትን ከ 22ቱ አንዱ "... ጥሩ እያጠቃህ ነው! በርታ! ቀጥልበት!.." የሚል መልእክት በሬድዮው አስተላለፈለት!
ሌላ አስደንጋጭ ነገር!
በዚህ አደገኛ ሰዓት እያበረረ ያለው ተዋጊ ጀት መሳርያ ጨረሰ! በፍጥነት ወደ ሰማይ ከፍታ ወጥቶ "እዚሁ ጠብቀኝ!" ብሎት ወደነበረው ሌላኛው ባልደረባው አቅንቶ መሳርያ እንደጨረሰ እና እርሱ ወርዶ እንዲታደጋቸው ነገረው! ነገር ግን መሳርያ ጨርሻለው ብሎ ባልደረባውን ብቻውን አላከውም! መሳርያ የጨረሰውን ጀቱን ይዞ ከባልደረባው ጎን ለጎን እየበረረ እና ሞራል እየሰጠው እንዲዋጋ አደረገ!
በመጨረሻም በጠላት ጥቃት ስር ወድቀው የነበሩት 22ቱ የአሜሪካ ልዩ ሃይሎች አንዳችም ቦታ ሳይጫሩ በሰላም ከነዛ ሰንሰለታማ፣ አስፈሪ እና አደገኛ ተራሮች እና ሸለቆዎች መውጣት እንዲችሉ አደረገ!
ይህንን ጀብድ ፈፅሞ ሁሉም ነገር ካለፈ በኃላ "Captain Mike" "...ለምን እንደዛ አደረክ?...." ተብሎ ሲጠየቅ "....እነርሱ በእኔ ቦታ ቢሆኑ ተመሳሳይ ነገር ለኔ ለማድረግ ዝግጁ እንደሆኑ ስለማውቅ!..." ነበር ያለው!

አሁን ላይ በ ብርጋዴል ጀነራልነት ማዕረግ እያገለገለ ያለው "Captain Mike Drowley" ስለ አመራርነት እና ስለሌሎች መኖርን ለተተኪ አብራሪዎች እያስተማረ ይገኛል!
ጌታዬ! በዚህ ታሪክ የሚጀምረው የ "Simon Sinek" መፅሃፍ "በመሪዎች (leaders)" እና "በአስተዳዳሪዎች(managers)" መካከል ያለው ልዩነት ምን እንደሆነ፣ ተቋማዊ መዋቅሮች ምን መምሰል እንዳለባቸው እና ተቋማትን እንዴት መመራት እንደሚገባ በሰፊው ያስቃኛል!
የሚገርመው አመራርነትን "Endorphin", "dopamine", "Serotonin" እና "oxytocin" ከሚባሉት የሰውነታችን ሆሮሞኖች ጋር ሳይቀር እያገናኘ እንዴት እነዚህን ሆርሞኖች አመጣጥነን የተሻለ መሪ መሆን እንደምንችል ሳይቀር ያወራል!
እረፍትህን ይህንን መፅሃፍ በማንበብ እንድታሳልፍ ጋበዝኩህ! ያለማጋነን ታተርፍበታለህ! ማንበብ የማትወድ ከሆነ ደግሞ "Simon Sinek" ብለህ "google" ላይ ብትፈልግ ሰውየው የተለያዩ መድረኮች ላይ ያደረጋቸውን ንግግሮች እና ቃለ መጠይቆች ታገኛለህ! እሱን ተመልከት!
ማጠቃለያ!
ፀሃፊው "leaders eat last" እንዳለው ታትረው፣ ሰርተው፣ ጥረው፣ ግረው፣ በስራቸው ያሉ ሰዎችን አብቅተው፣ ሃገር የሚመሩ ከሆነ ህዝባቸው፣ ተቋማትን የሚመሩ ከሆነ ደግሞ ሰራተኞቻቸው ጠቅመው ከጨረሱ በኃላ መጨረሻ ላይ ለመጠቀም የሚያስቡ መሪዎችን ይስጠን!
መልካም ቅዳሜ! ፍክት ብላችሁ አምሹ!!
(በወንድዬ እንግዳ)
@monhappy
@BINCJ90

፡ ምነው ታዲያ?
መርሳት ቀላል ነው እንዴ?… ሁሉንም ነገር መተውስ?… አዲስ ነገር ለመጀመር ያለፈውን ማርሳት ያስፈልጋል እንዴ?…ምነው ታድያ?… ይሄ ለአንተ ቀለለህ… እኔ እመቤቴን አላውቅም…
🌼 @monhappy 🌼
🍃 @itsmehappy 🍂

የፊሊሞን ደብዳቤዋች ♥️🌷
እነዛ ቀኖቶች እኮ አልፈዋል…እማያልፉ እሚመስሉት…ነገ የሌላቸው እሚመስሉት ቀናቶች ተከናንበው ሄደዋል…
🍃 @monhappy 🍃
🌼 @itsmehappy 🌼

የቅዳሜ ቀደዳ 29-(፳፱)
እንደምነህ ጌታዬ? እንዴት ነሽ እናቴ? ወደ ቅዳሜያችን ተመልሰናል! እስቲ አንድ ፅድት ያለ ነገር ላጫውትህ!
.
.
.
ምን መሰለህ?
14 የአፍሪካ ሃገራት ለረጅም ዘመናት ተገደው ስለሚቀልቧት አውሮፓዊቷ ፈረንሳይ ሳስብ ይደንቀኛል!
እ.ኤ.አ ከ 1960ዎቹ በኃላ አውሮፓውያኑ አፍሪካን ተገደውም ሆነ ወደው መልቀቅ የጀመሩበት ግዜ ነበር! ታድያ በዛን ወቅት እንግሊዝን በቅኝ ግዛት ትገዳደራት የነበረችው ፈረንሳይ መካከለኛው እና ምዕራብ አፍሪካ እና አንዳንድ የሰሜን አፍሪካ ሃገራት የግሏ ነበሩ!
ፈረንሳይ የምዕራብ አፍሪካ ሃገራትን ለቃ ስትሄድ ሃገራቱን "PACT: for the continuation of colonization" የሚባል ስምምነት እንዳስፈረመቻቸው ይነገራል!
ስምምነቱ በአጭሩ እንዲህ ይላል!
"....በቀኝ ግዛት በያዝኳቹ ግዜ ፈረንሳይ ለእያንዳንዳችሁ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይን አፍስሳለች! ትምህርት ቤቶችን ሰርተናል፣ መንገድ እና ሆስፒታሎችን ገንብተናል፣ ብዙ የመሰረተ ልማት አውታሮችንም ዘርግትናል! ስለዚህ ነፃነታችሁን የምትፈልጉ ከሆነ በግዴታም ይሁን በውዴታ ይህንን ስምምነት መፈረም ይኖርባችኃል! ለእያንዳንዳችሁ ሃገራት ፈረንሳይ "CFA franc" የሚባል የመገበያያ ገንዘብ ትሰጣችኃለች! የምትገበያዩት በዚህ ገንዘብ ብቻ ይሆናል! የገንዘቡን ህትመት የምትቆጣጠረው ፈረንሳይ ብቻ ናት! እያንዳንዳችሁ የሃገራችሁን 85% የሚሆነውን ገንዘብ(reserve) የምታስቀምጡት የፈረንሳይ ማዕከላዊ ባንክ ይሆናል! እናንተ ጋር መቀመጥ የሚችለው 15% የሚሆነውን ብቻ ነው! ከዚህ የበለጠ ገንዘብ የምትፈልጉ ከሆነ የፈረንሳይን ፍቃድ መጠየቅ ይኖርባችኃል! 85% የሚሆነውን የሃገራችሁን "reserve" የፈረንሳይ የገንዘብ ሚንስትር ያስተዳድራል!...."
ይቀጥላል!
"....ምንም አይነት የጦር መሳርያ የምትፈልጉ ከሆነ መግዛት የምትችሉት ከፈረንሳይ እና ፈረንሳይ ብቻ ነው! የሃገራችሁን መከላከያ ማሰልጠን የምትችለው ፈረንሳይ ብቻ ናት! ከፈረንሳይ ፍቃድ ውጪ ከየትኛውም ሃገር ጋር የጦር(ወታደራዊ) ስምምነት መፈፀም አትችሉም! የፈረንሳይ ጦር እንደፈለገው ሃገራችሁ ውስጥ መንቀሳቀስ ይችላል!
በሃገራችሁ ውስጥ የሚካሄድ ማንኛውም ጉዳይ የፈረንሳይ መንግስትን ጥቅም አደጋ ላይ የጣለ መስሎ ከተሰማን ፈረንሳይ ወታደሮቿን ልካ አስፈላጊውን እርምጃ መውሰድ ትችላለች! የእያንዳንዳችሁ ሃገራት የስራ ቋንቋ ፈረንሳይኛ መሆን አለበት! ሃገራችሁ ውስጥ ተቆፍሮ የወጣው ብቻ ሳይሆን ለወደፊት ተቆፍሮ የሚወጣውም የተፈጥሮ ሃብት በቀደምትነት መሸጥ ያለበት ለፈረንሳይ ነው! የሃገሮቻችሁ የውጪም ሆነ የንግድ ፖሊሲ ለፈረንሳይ መንግስት በሚስማማ መልኩ መቀረፅ አለበት!..."
ጌታዬ! ይህ ስምምነት ፈረንሳይ 14 በቀኝ የገዛቻቸውን የምዕራብ እና መካከለኛው አፍሪካ ሃገራትን ለቃ ስትሄድ ያስፈረመቻቸው ነው! ሃገራቱ ቤኒን፣ ቡርኪና ፋሶ፣ ሴኔጋል፣ ኮትዲቯር፣ ማሊ፣ ኒጀር ፣ ቶጎ፣ ካሜሩን፣ ማዕከላዊ አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ጊኒ ቢሳኡ፣ ቻድ፣ ኮንጎ፣ ኢኳቶርያል ጊኒ እና ጋቦን ናቸው!
ይህ ስምምነት እውነት እንደሆነ ደግሞ የቀድሞዋ የአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር "Arikana Chihombori" ትናገራለች።
አባዬ! ፈረንሳይ "colonial Tax" ትለዋለች! በሌላ አጠራሩ "Monetary colonialism" ይባላል!
ገራሚ ሃቅ አንድ!
እነዚህ 14 ሃገራት ፈረንሳይ በሰጠቻቸው እና በምትቆጣጠረው "CFA franc" የሚባል የመገበያያ ገንዘብ እንዲጠቀሙ ተደርጓል!
ገራሚ ሃቅ ሁለት!
የእነዚህ ሃገራት 85% የሚሆነው የገንዘብ ክምችት ፈረንሳይ ማዕከላዊ ባንክ ይቀመጣል! ሃገራቱ መጠቀም የሚችሉት 15% የሚሆነውን ብቻ ሲሆን ከዛ ያለፈ ካስፈለጋቸው ፈረንሳይ መፍቀድ አለባት! እንደ አምባሳደሯ ገለፃ ፈረንሳይ ይህንን ገንዘብ ወደ "Stock market" በራሷ በማስገባት በአመት ወደ 500 ቢልዮን ዶላር ታገኝበታለች! ይህንን ገንዘብ ደግሞ መልሳ ለነዚህ ሃገራት በወለድ ታበድረዋለች! (በአጭሩ እነዚህ 14 ሃገራት በየአመቱ ለፈረንሳይ 500 ቢልዮን ዶላር ያስገባሉ!)
በነገራችን ላይ የነዚህ ሃገራት ነዳጅ፣ ጋዝ፣ ወርቅ፣ ዳይመንድ ወ.ዘ.ተ የሚጋዘው ወደ ፈረንሳይ ነው!
"Areva" የሚባለው የፈረንሳይ የኑዩክለር አምራች ኩባንያ ግብዓት የሚሆነውን "Uranium" 100% የሚወስደው ከ "Gabon" ነው!
"Total" የሚባለው የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያም የሚሰራው ተመሳሳይ ነገር ነው! በአንድ ወቅት የ "Gabon" ፕሬዝዳንት የነበሩት "Omar Bongo"
"....ጋቦን ከፈረንሳይ ውጪ ሹፌር የሌለው መኪና ስትሆን፣ ፈረንሳይ ያለ ጋቦን ደግሞ ነዳጅ የሌለው መኪና ናት!..." ማለታቸው ይታወሳል!
የፈረንሳይን ተዘዋዋሪ ቀኝ ግዛት የተቃወሙ የነዚህ ሃገራት መሪዎች ታሪካቸው ግድያ ወይ መፈንቅለ መንግስት ነው!
ፈረንሳይ እ.ኤ.አ ከ 1962 እስከ 1995 ባሉት 33 አመታት 19 ጊዜ በአፍሪካ ሃገራት የፖለቲካ ጉዳይ ጣልቃ በግልፅ ገብታለች!
እ.ኤ.አ ከ 1960 ጀምሮ ደግሞ 40 ግዜ በአፍሪካ ጉዳይ ወታደሮቿን ጣልቃ አስገብታለች!
እ.ኤ.አ ከ 2010 ጀምሮ ብቻ ብትቆጥር ሊብያ፣ ማሊ፣ መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ፣ ቻድ እና ኮትዲቯር የመሳሰሉ ሃገራት ውስጥ የተካሄዱ የመንግስት ግልበጣዎች ላይ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ተሳትፋለች!
ግልፅ ምሳሌዎች!
"Mali" ነፃነት ባገኘች ማግስት የመጀመርያው የሃገረቱ ፕሬዝዳንት የነበሩት "Madibo keita" ሃገሩ ከፈረንሳይ ጫና እንድትወጣ እና የፈረንሳይን ተፅህኖ ለማስቆም ሲያስቡ መፈንቅለ መንግስት እንዲደረግባቸው እና ከዛም በእስር እያሉ እንዲሞቱ ፈረንሳይ አድርጋለች!
"Tomas Sankara" ሃገሩ "Burkina Faso" ከፈረንሳይ ጫና እንድትወጣ ጥረት ማድረግ ሲጀምር እና አዝማሚያው አላምር ሲላቸው መፈንቅለ መንግስት ተደርጎበት እ.ኤ.አ 1987 ላይ እንዲገደል ሆኗል!
እ.ኤ.አ 1963 ላይ የቀድሞው የ "Togo" ፕሬዝዳንት "Sylvanus Olympio" አዲስ የመገበያያ ገንዘብ ለሃገሪቱ ህዝብ ለማስተዋወቅ ሲሰናዳ መፈንቅለ መንግስት ተደርጎበት፣ በንጋታው በአሰቃቂ ሁኔታ ተገሎ ሬሳው "Togo" የሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ አጠገብ እንዲጣል ተደርጓል!
የ "Benin" ፕሬዝዳንት የነበሩት "Hubert maga" እና የ"Libya"ው "Gadafi" መወገድ ጀርባም ፈረንሳይ አለች!
አሁን እንኳን የኮትዲቯር መንግስትን ደግፋ ስልጣን ላይ ያስቀመጠችው ፈረንሳይ ናት! አባዬ! እንደምታውቀው ደግሞ ፈረንሳይ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ "ቡና" እና ለቸኮሌት ግብዓት የሚሆናትን "Cocoa" የምትገዛው ከኮትዲቯር ነው።
ጌታዬ! የቀድሞው የፈረንሳይ ፕሬዝድንት "Jacques Chirac" ያሉትን ታስታውሳለህ?
"....We have to be honest and acknowledge that a big part of the money in our banks comes precisely from the exploitation of the African continent!... "

የጣልያኑ የውጭ ጉዳይ ሚንስትር "Luigi Di Maio" ስለ ፈረንሳይ እንዲህ ይላል!
"....ፈረንሳይ አፍሪካ ውስጥ ያሏት ቅኝ የተገዙ ሃገራትን ባትይዝ ኖሮ የዓለማችን ምናልባትም 30ኛው ኢኮኖሚ ትሆን ነበር! ነገር ግን የአፍሪካ ሃገራትን በመያዟ እና ከቅኝ ግዛት በኃላም በተዘዋዋሪ በቀኝ ግዛቷ ስር እነዚህ ሃገራት እንዲቆዩ በማድረጓ ምክንያት አሁን ላይ ኢኮኖሚዋ የዓለማችን 7ተኛ መሆን ችሏል! ፈረንሳይ ካለ አፍሪካ ተራ ሃገር ናት!..."
በአጭሩ እነዚህ የአፍሪካ ሃገራትን የሚመሩ ግለሰቦች የፈረንሳይን ጥቅም ማስጠበቅ ካልቻሉ በዚህም በዚያም ይወገዳሉ! ጥቅሟን የሚያስጠብቁ ከሆነ ደግሞ አንደላቃ ታኖራቸዋለች!
ማሳያ!
"Elf" የተባለው የፈረንሳይ የነዳጅ ኩባንያ ታማኝ ለሆኑ የአፍሪካ መሪዎች ረብጣ ጉቦ እና ቆነጃጂት ቅምጦችን ይሰጥ እንደነበር እ.ኤ.አ 1994 ላይ ተጋልጧል! ስለ "Elf scandal" ማንበብ ትችላለህ! በየዓመቱ ለነዚህ መሪዎች 15 ሚልዮን ይሮ ወጪ ይደረግ ነበር!
ሴኔጋላዊው ሙዚቀኛ "Akon" አንድ ቃለ መጠይቁ ላይ "....ፈረንሳይ ሁሉንም ነገር መውሰድ ትወዳለች! መስጠት የሚባል ነገር ግን አታውቅም! የዛሬ ሶስት እና አራት መቶ አመታት መጥተው የዘረፏቸው የአፍሪካ ሃገራት አሁንም ድረስ አንድ ኢንች ወደፊት ፈቅ ማለት አልቻሉም!...." ይላል!
ማጠቃለያ!
ይህንን የፈረንሳይ "Monetary colonization" እና "Colonial tax" ያጋለጠችሁ የአፍሪካ ህብረት የአሜሪካ አምባሳደር "Arikana Chihombori" ምን እንደተደረገች ታውቃለህ?
ገምት?
.
.
.
"የዛሬ ሁለት አመት በአፍሪካ ህብረት ቀጭን ደብዳቤ ተባራለች!"
ያባርራት ማን እንደሆነ ታውቃለህ?
የቀድሞው የቻድ ጠቅላይ ሚንስትር እና አዲስ አበባ ያስቀመጥነው የአሁኑ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር "Musa Faki Mahamat"!
በነገራችን ላይ 26 የሚሆኑ የአፍሪካ ሃገራት ውስጥ ፈረንሳይኛ ይነገራል! ከዚህ ውስጥ 20 የሚሆኑት የስራ ቋንቋቸው ፈረንሳይኛ ነው! በ 2050 ከዓለማችን የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች ውስጥ 80% የሚሆነው የሚገኘው አፍሪካ ውስጥ ይሆናል! (Projection ነው! የቀኝ ግዛት projection)
መልካም ቅዳሜ! ፈካ፣ ዘና፣ፀዳ ያለ ቅዳሜ ይሁንላችሁ!

"ናፊባ"
ክፍል ~ አንድ
#አዲስ አበባ ፒያሳ
..ኦልድ ታውን(Old Town Bar & Restaurant)
የጣራው ስር መናፈሻ ነፋሻማነቱ ደስ ይላል። ጨረቃዋ በግማሽ ለመድመቅ ከኮከቦቹ ጋር የፅሐይን መጥለቅ ብቻ አሰፍስፋ ትጠብቃለች። ፍም የመሰሉት የምዕራብ ሰማዮች የምድርን አተካራ ለጥቃ የምትሰናበተውን ፅሐይ ለማስገባት አጅበዋታል። ይሄን ሁሉ ትዕይንት ፊትለፊቱ ካለ የቤት መስታወት ነው የሚመለከተው። "ምነው ወዳጄ ፍዝዝ ብለህ ቀረህ ምን እያየህ ነው?"አለ ዮዳሄ የጓደኛውን የመስፍንን አይን የሳበውን ትዕይንት ለመመልከት እየዞረ። መስፍን አንገቱን ነቀነቀና "ምንም ዝም ብዬ ፊት ለፊት ስመለከት በመስታውቱ ውስጥ ሰማዩን እየቃኘሁ ነበር"አለና የሚጠጣውን የሐበሻ ጃምቦ አንስቶ ችርስ አለው" ጠርሙሶቻቸውን ከፍ አድርገው"ችርስ ችርስ "ተባባለው ጠጡ።
ማዶ ጃንጥላው ስር በከፊል ጡቶቿን አጋልጦ ያሰጣ ልብስ ለብሳ የጭኖቿን ብርቱካናማነት የሚያሳይ አጭር ቀሚስ ለብሳ ከሎሚ የነጡ ተረከዞቿና በአንደኛው እግሯ ላይ አሳርፋ አራዳዋን የምትልፍ አንዲት ሴት ፊት ለፊታቸው ተቀምጣ መስፍንና ዮዳሔን ትገላምጣለች። ነገር ግን አንዳቸውም ሊያይዋት አልቻሉም።
"ሁለታችንም የሚያመሳስለን ነገር አለ። ግን እስከመቼ ድረስ ነው በዚህ ኮንዲሽን የምንቀጥለው?"አለ ዮዳሔ ሁለቱንም እጆቹን አገጩ ላይ አስደግፎ " አላውቅም ዮዳሔ አታስጨንቀኝ ውስጤ ላይ የሚላወሰው ጥያቄ ይበቃኛል። አንተ ደግሞ አትጨምርብኝ እንጅ"አለና መስፍን ጃምቦውን ጭልጥ አድርጎ ጠጥቶ አስተናጋጇን ጠርቶ እንድትደግመው አዘዛት። ዮዳሔ ዝም ብሎ ተመለከተውና "ግን በእውነት ምንም ሊገባኝ አልቻለም ምን ሆነህ ነው ከእኔ የተለዬ እንደዚህ ያደረገህ ከቀን ወደቀን እየተቀየርክብኝ ነውኮ" "አንተ ላይ ብቻ አይደለም የተቀየርኩት ወዳጄ ራሴም ጭምር ላይ ነው የተለወጥኩት። አሁን ዝም ብለህ ጥያቄህን መጠየቅ አቁምና ጠጣ። ቀኑ ቅዳሜ ነው የቤቱ ቫይቭ ደግሞ ደስ ይላል። እዚህ እንስከርና ወርደን እንጨፍራለን"አለ መስፍን ፊቱ እንደተኮሳተረ "እሺ በቃ ጓደኛዬ "አለና ዮዳሔ ከፍ አደረገለትና ጠጥቶ "ሽንት ቤት ደርሼ መጣሁ"ብሎ ሄደ። መስፍን ዙሪያ ገባውን እያማተረ ሳለ ፊት ለፊት ከተቀመጠችው ልጅ ጋር ተፋጠጠ፡። ጠቀሳት ጠቀሰችው ሄዶ እንድትቀላቀላቸው ጠየቃት ተስማምታ ሶስተኛ ወንበር ስባ ተቀመጠች። ዮዳሔ ሲመጣ ደንግጦም ደስ ብሎትም "ከየት አገኘኻት ባክህ ብሎ ተቀመጠ። "ያው ብቻዋን ስለሆነች እኛም ብቻችንን ስለሆንን ከሁለት ሶስት መሆን ይሻላል ብዬ ጋበዝኳት እሷም ተስማማች"አለ መስፍን። "ጥሩ ነው ያደረከው "አለና ዮዳሄ ወደ ልጅቷ ፈገግ ብሎ ጠጋ ብሎ" እንተዋወቅ ዮዳሔ እባላለሁ። እሱ ደግሞ ብሎ ወደ መስፍን ሲዞር ገላመጠው በዚህ ጊዜ አንድ ነገር አስታወሰ"በፍፁም መጠጥ ቤት ላገኘኸው ሰው ሙሉ ራስህን ማስተዋወቅ የለብህም። የመጠጥ ቤት ስም ሊኖርህ ይገባል። እኔ ለምሳሌ በረከት በሚል ስም ነው የምተዋወቀው። የሚፈጠረው አይታወቅም አንተን የሚያጠቃህ ሰው ሰው የሚልክብህ ስምህን ነግሮ ነው ስለዚህ አንተም ስም ሊኖርህ ይገባል! ኧረ አሻፈረኝ ካልክ አይመለከተኝም ነገር ግን እኔን ለሰው ከማስተዋወቅህ በፊት ለማላቀው ሰው የምተዋወቅበትን ፌክ ስሜን መዘንጋት የለብህም"እንዳለው አስታውሶ " እ እሱ ደግሞ በረከት ይባላል "አለ ና የእሷን ስም ጠየቃት። "እኔ ሒወት እባላለሁ!" "ጥሩ ስም ነው በቃ እንጫወት ቆንጆ" ብሎ ብርጭቆውን ከብርጭቆዋ ጋር አጋጭቶ ፉት አለ። ጨዋታቸውን እያደሩ መጠጡም እየበዛ ሄደ።ጣራው ያለውን ነፋሻማነት እንደ እርጎ ከሚገመጠው ጃምቦ ጋር እያጣጣሙ እያለ ጃምቦ አልቋል ተብለው ታች ወርደው ክለቡን ተቀላቀሉ። ቆሞ የሚጠጣ ሞልቷል። የዘፈኑ ድምፅ ከቤቱ አልፎ ውጭ ላይ ይሰማል። የጨፋሪው ተከታይ ዜማ ለጉድ ነው።መስፍን ሒወትና ዮዳሔ እየጨፈሩ ባለበት ሽንት ቤት ደርሶ ሲመለስ ነፍሳቸውን አያውቁም። የሒወትና የዮዳሔ በፍጥነት መግባባትና መመቻቸት እያስገረመው ሙዳቸውን ላለመረበሽ ሒሳብ ከፍሎ ትቷቸው ወጣ።
ሒዎትዮዳሔ ለብዙ ጊዚያት የሚተዋወቁ ጓደኛሞች እንጅ ከስአታት በፊት የሚተዋወቁ አይመስሉም። ሰውነታቸው በላብ እስኪጠመቅ ድረስ ሲጨፍሩ ቆይተው ሲመለሱ መስፍንን ከቦታው አጡት። "እንዴ በረከት የት ሄደ?"አለች ሒዎት ቀድማ "አላውቅም። ምንም አልነገረኝም" "እንዴት ሳይነግርህ ይሄዳል? ነው ብቻውን ስለሆነ ደብሮት ነው?"አለች ሒዎት። "አይ እይደዛ አይደለም። ብቻውን ሆነ አልሆነ ግድ የለውም።በቃ ተይው እኛ እንዝናና አለና በጆሮዋ የሆነ ነገር አንሾካሾከላት፣ ከት ከት ብላ ሳቀችና ቶርክ መቶረክ ጀመረች። ዮዳሔ ወገቧን ይዞ ኤግለስ ያስጨፍራት ጀመር። "የአጨፋፈር አይነትና ጭፈራ ግን አንተ ጋር ነው ያሉት"አለችው ጆሮው ስር ተደግፋ "አመሰግናለሁ አንቺም በጣም ጎበዝ ጨፋሪ ነሽ ተመችተሽኛል"አላት "እኔም አመሰግናለሁ ሒሳብ እንክፈልና እንውጣ?!"አለች ሒወት "እሺ "አለና አስተናጋጇን ጠራት። ሒሳብ ለመክፈል እርስ በእርስ እየተገላገሉ ሳለ አስተናጋጇ "ሒሳብ ተከፍሏል። ጓደኛችሁ ነው ከፍሎ የሄደው እና ይቺን ወረቀት ደግሞ ለአንተ እንድሰጥህ ሰጥቶኛል "ብላ የተጠቀለለችውን ወረቀት ሰጠችው። ዮዳሔ ጥቅሏን ቀስ አድርጎ ፈታና አነበባት "ወዳጄ ራስህን ጠብቅ ጥንቃቄ ማድረግህን እንዳትረሳ። አገኘሁ ብለህ ዝም ብለህ ዘው እንዳትል ነግሬሀለሁ!"የሚል ማስጠንቀቂያ አዘል መልዕክት ነበር። ዮዳሔ ሳቅ አለና ወረቀቷን ጨምደድ አድርጎ ወደ ኪሱ አስገባት። "ምን ብሎህ ነው?" "ተይው ባክሽ ዝም ብሎ ነው"አለ እየሳቀ "ገብቶኛል።ተወው"አለች ሕሊና ፈገግ ብላ። "እሺ ከገባሽ ጥሩ እና "መሀል ሆቴል" ጋር አልጋ ብንይዝ አይሻልም ትያለሽ?" "አዎ ደስ ይለኛል ግን እስካሁን አያልቅም?" "እንጃ የሚያልቅ አይመስለኝም።ቸክ አድርገን እዛው አካባቢም መያዝ እንችላለን"አላትና ወጡ። በሲኒማ አምፒር ታጥፈው የግሪክ ቤተክርስቲያንን በግራ ትተው ተሻግረው መሀል ሆቴል ጋ ደረሱ። የእንግዳ ተቀባይዋም በስነስርዓት ከተቀበለቻቸው በኋላ አንድ አልጋ ብቻ እንደቀረ ነግራቸው ከፍለው ቁልፍ ይዘው ገቡ።
****
<በሄደበት ሁሉ እየተከተሉ በጣለው ሲያተርፉ
ራሱን ሲጥል ግን - አይተውት አለፉ››
የሚል የቀዬ እርዚቅ
የሚል የሰው ግጥም የሚል የአበሽ ቅኔ
ልብ አውቃዬ ሆኖ
ልክ እንደ አገር መዝሙር እንዳልዘመርኩ እኔ
ከአፍታ ዕድሜ በኋላ
የሆነውን ሁሉ ታሪኬን ቀየርሽው
ከትናኝ ከልለሽ
ከብናኝ አራግፈሽ ወስደሽ ልትፈውሽው
ሰው አይቶ ያለፈውን
የጣልኩት ራሴን - አየሁ ስታነሽው!!
ይህን እኔ ያየሁ
ሰርክ እንዲህ እላለሁ፤
እንኳ ራስን ጥሎ - ገፍቶ ጣይ ባለበት
ሰው በሰው ላይ ሊያሴር - በሚማስንበት
በዚህ ከይሲ ዘመን - በዚህ የክፋት ዓለም
ሰው ራሱን ሲጥል
እያለፉ መሄድ - የሚገርም አይደለም፤
፡
እልፎች ራስ ጥለው - ተስፋ ሲቆልፉ
እልፎቹም ገፍተረው - እየጣሉ ሲያልፉ
ነገር ግን
ከአመድና አቧራ - ከደይን የሚያነሱ
ድንገት ተወርውረው - ለጭንቅ የሚደርሱ
ጥቂት ሰዎች አሉ
አንቺን የመሰሉ !!
ጥቂት ሰዎች አሉ
አንቺን የመሰሉ!!"ብሎ በውብ አነባበብ ግጥሙን አነበበላት ተሕሚድ
ሼር
@monhappy
@monhappy
የደራሲው ቀደምት ስራዎች
✍️#መቅደላዊት
✍️#ኤሴቅ

HTML Embed Code: