TG Telegram Group Link
Channel: ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከል
Back to Bottom
ማኅበረ ቅዱሳን በሚዛን ደብረ በረከት አቡነ ተ/ሃይማኖት እና ቅ/ዑራኤል የእናቶች ገዳም ያስተማራቸውን ደቀ መዛሙርት አስመረቀ።

ሰኔ ፲፯/፳፻፲፯  ዓ.ም  

ማኅበረ ቅዱሳን በገዳሙ በሚገኘው የአቡነ ሕዝቅኤል አብነት ት/ቤት ሰኔ 16/2017 ዓ/ም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ በተገኙበት ለ4 ወራት ያስተማራቸውን ዲያቆናት አስመርቋል።

አጠቃላይ 24ተመራቂ ተማሪዎች ሲሆኑ ዘጠኝ የተለያዩ ቋንቋዎች ተናጋሪ ናቸው ተብሏል።

ይህም የካህናት እጥረት ባለባቸው አካባቢዎች በራሳቸው ቋንቋ ለማገልገል ጉልህ አስተዋጽኦ እንዳለው ተጠቁሟል።

ዲያቆናቱ ከካፋ ሸካ ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕ/ኦሞ ሀገረ ስብከት ስር ከሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ተመልምለው ወደ አብነት ት/ቤቱ የገቡ ሲሆን በጎ አድራጊ ምእመናንን በማስተባበር አስፈላጊውን ወጪ በመሸፈን ለአራት ወራት መሠረታዊ የክህነት ትምህርትና የትምህረተ ሃይማኖት ኮርሶችን ማስተማር የተቻለ ሲሆን ከነዚህም መካከል ሁለቱ ማእረገ ቅስና ተቀብለዋል።

ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል የካፋና ሸካ፣ ቤንች ሸኮ እና ምዕራብ ኦሞ  አህጉረ  ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና የሰዋሰወ ብርሃን ቅ/ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ በምርቃት መርሐ ግብሩ እንደተናገሩት "ማኅበረ ቅዱሳን ዋናው ማእከልና የሚዛን ማእከል በጋራ በመሆን ሀገረ ስብከቱ መሥራት የነበረበትን ሥራ ሠርቷል ሲሉ ተናግረዋል።

ብፁዕነታቸው አክለውም አገልጋይ ካህናትን የማፍራት ሥራው ተጠናክሮ ይቀጥል ያሉ ሲሆን ተመራቂዎች መማራችሁ ጥሩ ነው የነፍስ ዋጋን ይዛችኋልና ሕዝባችሁን በቅንነት አገልግሉ " ሲሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት አስተላልፈዋል።
"የጉባኤቤትቆይታችሁስኬት የሚለካውባገኛችሁት ዕውቀት ብቻ ሳይሆን በምትሰማሩበት መንፈሳዊ አገልግሎት የድካምና የመሰልቸት መንፈስ ሳይሰማችሁ ቃለ እግዚአብሔር ለተጠማውና በጠረፍ ላለው ሕዝባችሁ በመድረስ ወደ ቅድስና ሕይወት ስትመሩ ነው" ያሉት ደግሞ በማኅበረ ቅዱሳን የቤ/ን ሁለንተናዊ እድገትና መንፈሳዊ ት/ቤቶች አገልግሎት ዳይሬክተር የሆኑት ዲ/ን ደረጀ ጋረደው እንደሆኑ ተመላክቷል።

ዳይሬክተሩ ጨምረው እንደተናገሩት በዚህ ዓመት ከተለያዩ አህጉረ ስብከት ለተመረጡ 169 የአብነት ት/ቤቶች፣ ለ229 መምህራንና 2000 የአብነት ደቀ መዛሙርት  ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ዕቅድ ይዞ ድጋፍ  እያደረገ የሚገኝ ሲሆን ለዛሬዎቹ ተመራቂዎች ለሕክምና ፣ለትምህርት፣ ለቀለብና ለመሳሰሉት ድጋፍ አድራጊዎችን በማስተባበር 842,650.00 ብር ወጪ በማድረግ እንዲማሩ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል።

የሚዛን ተፈሪ ማእከል ሰብሳቢ የሆኑት መ/ር ጥላሁን ታደሰ በበኩላቸው የአገልጋይ ካህናት እጥረትን ለመቅረፍ በሚደረገው ጥረት ብዙ ፈተናዎች ቢኖሩም ዛሬ ለአራት ወራት ያስተማርናቸው አገልጋይ ካህናትን በማስመረቃችን ደስ ብሎናል ብለዋል።

በሸካ ፣ ቤንቺ ሸኮ እና ምዕ/ ኦሞ ሀገረ ስብከት 197 አብያተ ክርስቲያናት መካከል 5ቱ ገዳማት ሲሆኑ በአገልጋይ እጥረት ምክንያት አንድ ቤተ ክርስቲያን ሙሉ በሙሉ የተዘጋ፣ 25ቱ አብያተ ክርስቲያናት በአመት የሚቀደስባቸው፣ 5ቱ ወርሐዊ በዓላትን በመጠበቅ የሚቀደስባቸው፣ ከ100 በላይ የሚሆኑት ደግሞ ሰንበት ት/ቤት የሌላቸውና ሰርክ ጉባኤ የማይሰጥባቸው እንደሆኑ መረጃዎች ይጠቁማሉ።

መሠረታዊ የክህነት ት/ት የትምህርተ ሃይማኖት ኮርሶች የተማሩትና ለምርቃት የበቁት ደቀ መዛሙርቱ በአካባቢያቸው ቋንቋ በማስተማር እና የክህነት አገልግሎቱን በመስጠት የተዘጉ አብያተ ክርስቲያናትን ይከፍታሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ማኅበረ ቅዱሳን በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የመልሶ ማቋቋሚያ ግብዓቶች ድጋፍ አደረገ

ባለፈው ዓመት ሐምሌ አጋማሽ በጎፋ ዞን በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ባጋጠመው የመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ሰኔ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በቦታው በመገኘት የአልባሳትና የቤት ውስጥ መገልገያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።

በድጋፍ ማድረጊያ ቦታ የተገኙት የገዜ ጎፋ ወረዳ ዋና አፈ-ጉባኤ እና የወረዳው አስተዳደር ተወካይ አቶ ዓለምነህ ነጋሽ ፣የገዜ ጎፋ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዮሐንስ በየነ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ የሰንበት ትምህርት ቤቶች ማ/መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን ተወካይ ዲያቆን ፍጹም መሪነህ እና ሌሎች አባላትም ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል።

የገዜ ጎፋ ወረዳ ዋና አፈ-ጉባኤ እና የወረዳው አስተዳደር ተወካይ አቶ ዓለምነህ ነጋሽ እንደገለጸት በሐምሌ 15 ቀን 2016 ዓ.ም በማኅበረሰባችን ላይ የደረሰውን ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት በማድረግ ከሀገር ውስጥና ከሀገር ውጪ ያሉ ወገኖች ድጋፋቸውን እያደረጉ በመሆኑ ህዝባችን እየተጽናኑ ይገኛል ብለዋል።

ማኅበረ ቅዱሳን ችግሩ ባጋጠመበት ባለፈው ዓመትም፣ ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም በቦታው በመገኘት 1.2 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ የሆነበት የቤት መሥሪያ ቆርቆሮና ለተማሪዎች የሚሆን የትምህርት ቁሳቁስ ግብዓቶችን ድጋፍ ማድረጉ የሚታወስ ነው።

ድጋፉ የተደረገው ማኅበረ ወልድ ዘሰሜን አሜሪካ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ ሲሆን ለዚሁ ድጋፍ በጠቅላላው ከ700 ሺህ ብር በላይ ወጭ መሆኑ ተገልጿል።
የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ባለፉት 7 ወራት ብቻ በመጠለያዎች ጣቢያዎች ለሚገኙ ተፈናቃዮች፣ በድርቅና መሰል ማኅበራዊ ቀውስ ለተጎዱ ወገኖች፣ ለገዳማትና አብነት ት/ቤቶች ከ10 በላይ የሚሆኑ ተመሳሳይ ማኅበራዊ ድጋፎችን አድርጓል። በቀጣይ ጊዜም መሰል የነፍስ አድን ድጋፎችን ለማድረስ በሚደረገው የሰብአዊነት ሥራ ምእመናን የተለመደ ድጋፍ እንድታደርጉልን ማኅበሩ ጥሪውን ያቀርባል።
ድጋፍ ለማድረግ፡-
#በማኅበረ ቅዱሳን የማኅበራዊ ድጋፍና መልሶ ማቋቋም ሒሳብ ቁጥሮች፡-
1. በአሐዱ ባንክ - 0025393810901
2. በአቢሲንያ ባንክ - 37235458
3. በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ - 1000309803648
4. በወጋገን ባንክ - 0837331610101
5. በአዋሽ ባንክ 01329817420400
6. በጎ ፈንድ ሚ፡- https://gofund.me/f4c1b82e
6. በወገን ፈንድ፡- https://Www.wegenfund.com/mknu መጠቀም የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።
የማኅበረ ቅዱሳን ላሊበላ ወረዳ ማእከል የጤና ቡድን ለተከዜ ኃይላ ለጥበብ ወምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም  ገዳማውያን ነጻ የሕክምና አገልግሎት ሰጠ

ሰኔ ፲፱/፳፻፲፯ ዓ.ም

የማኅበረ ቅዱሳን ሙያ፣ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ኦርቶዶክሳዊያን ሙያተኞች በሙያቸው ተገቢውን አገልግሎት ለቤተ ክርስቲያን መስጠት ይችሉ ዘንድ በሁሉም ማእከላት ተገቢውን ድጋፍና ክትትል የማድረግ ሥራዎችን እየሠራ እንዳለ ይታወቃል። 

በዚሁ መሠረት በማኅበረ ቅዱሳን ላሊበላ ወረዳ ማእከል ሙያ ገዳማትና አብነት ት/ቤቶች አገልግሎት ክፍል የጤና ባለሙያዎች ኅብረት በላስታ ወረዳ ቤተ ክህነት ስር ለሚገኘው ለተከዜ ኃይላ ለጥበብ ወምእራፈ ቅዱሳን አቡነ ሐዋርያ ክርስቶስ አንድነት ገዳም 46 መናንያን ነጻ የሕክምና አገልግሎት  መስጠቱን  የጤና ባለሙያዎች ኅብረት አስተባባሪው ዲ/ን ዶ/ር ፈንታ ሲሳይ ገልጸዋል።

ወቅቱ ወረሽኝ የሚበዛበት  በመሆኑ የሕክምና አገልግሎቱን መስጠት አስፈልጓል ያሉት ዲ/ን ዶ/ር ፈንታ በሙያችን  ገዳማውያንን በማገልገላችን የእኛም ነፍስ ታክማለች፤  በቀጣይም አገሎግሎቱን ለማስፋት  የዳሰሳ ጥናት በመሥራት ወደ ሌሎች ገዳማት ለመድረስ እንሠራለን ብለዋል።

ዲ/ን ዶ/ር ፈንታ አክለውም  ለሥራቸው  መሳካት ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉትን አካላት አመስግነው ለቀጣይ መሰል ተግባራትም በጎ አድራጊዎች፣  አጋርና ባለድርሻ አካላት  መድኃኒትና መሰል ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የገዳሙ መጋቢ  አባ ገብረ ጻድቅ ከፍያለ በበኩላቸው "የገዳሙን ሕግና ሥርዓት በጠበቀ እንዲሁም የመናንያኑን መንፈሳዊ ሕይወት ባከበረ መልኩ  ይህ አገልግሎት መሰጠቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸው የሕክምና አገልግሎቱ  በተጠናከረ መንገድ ቀጣይነት እንዲኖረው" አባታዊ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ለሕክምናው የወጣው ወጭ በገንዘብ ሲተመን 51,050.90 ብር እንደሚሆንና የላስታ ወረዳ  ጤና ጽ/ቤትና ሌሎች በጎ አድራጊዎች ባደረጉት ድጋፍ የተሸፈነ መሆኑ ተገልጿል።

በሕክምና አገልግሎቱ 3 ሐኪሞች፣  3 ነርሶች፣  2 የላብራቶሪ  ባለሙያዎች  እንዲሁም 1 ፋርማሲ በአጠቃላይ 9 የጤና ባለሙያዎች ተሳታፊ መሆናቸውን የተገኘው መረጃ ያመልክታል።
HTML Embed Code:
2025/06/29 10:51:10
Back to Top