TG Telegram Group Link
Channel: ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
Back to Bottom
የጥያቄዎቻችን ትክክለኛ መላሾች
  ከስር ተዘርዝሯል
፩ኛ / @Magdalinamary1324
፪ኛ/ Atamu
፫ኛ/ Ye@b
፬ኛ/ Being Human
፭ኛ/ Kal Lingerh
፮ኛ/Fre
፯ኛ/ Dawit Yizengaw
፰ኛ/ Yordi 12
፱ኛ/ Hareg Tar

የመግቢያ ትኬታችሁን ለመቀበል በውስጥ አናግሩን ለተሳትፎ እናመሰግናለን ።
#ዝክረ_ዓድዋ
#ጦቢያ
የተከበራችሁ የጦቢያ ቤተሰቦች
ቀጣዩ የጥበብ መድረካችን እሁድ
የካቲት 17/2016 ከቀኑ ከ9:00 ጀምሮ ካዛንችስ በሚገኘው ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል አዳራሽ #ዓድዋ በድምቀት ይከበራል።

የመግቢያ ዋጋ 300 ብቻ

በኪነ ጥበብ ትውልድ ይታነፃል!
በኪነ ጥበብ ሀገር ይገነባል!
#በነፃ_ሀሳብና_በሰከነ_መንፈስ_ኢትዮጵያንና_ኢትዮጵያዊነትን_እናድምቅ!!
Forwarded from ጦቢያ ግጥምን በጃዝ (ሄኖክ ጦቢያ)
#ዝክረ_ዓድዋ
#ጦቢያ
የተከበራችሁ የጦቢያ ቤተሰቦች
ቀጣዩ የጥበብ መድረካችን እሁድ
የካቲት 17/2016 ከቀኑ ከ9:00 ጀምሮ ካዛንችስ በሚገኘው ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል አዳራሽ #ዓድዋ በድምቀት ይከበራል።

የመግቢያ ዋጋ 300 ብቻ

በኪነ ጥበብ ትውልድ ይታነፃል!
በኪነ ጥበብ ሀገር ይገነባል!
#በነፃ_ሀሳብና_በሰከነ_መንፈስ_ኢትዮጵያንና_ኢትዮጵያዊነትን_እናድምቅ!!
ጦቢያ ግጥምን በጃዝ በለንደን ለመጀመሪያ ጊዜ

የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 23 (March 2) የለንደን ጎዳና አድዋን ሆኖ ይውላል በፍፁም እንዳትቀሩ ብትቀሩ ማርያምን ቀረባቹ...... 💚💛❤️
...
ዝክረ ዓድዋ በለንደን ከስር ባለው ሊንክ ትኬቱን ማግኘት ይችላሉ።
https://www.eventbrite.com/e/bete-adwa-tickets-777915244437?aff=oddtdtcreator
ቀድመው ከቆረጡ £30 በእለቱ የመግቢያ ዎጋ ይጨምራል
የእግር ጉዞ መነሻ king’s cross station 13፡30
የአዳራሽ ፕሮግራም ላይ ባለው የወንበር ልክ ብቻ
ቀድመው ይቁረጡ። ቤተ ዓድዋ
07837864359
07585231830
07427133335

ልጅ ብሩክ ተዋነይ ዘጎንጂ
እንኳን ለመላው የአፍሪካውያን ኩራት ለሆነው ለ128ኛው የአድዋ ድል በዓል በሰላም አደረሰን!!!
ፎቶ ከለንደን
#ጦቢያ
የተከበራችሁ የጦቢያ ቤተሰቦች
ቀጣዩ መደበኛ ወርሃዊ የጥበብ መድረካችን አርብ
ሚያዚያ 4/2016 ከቀኑ ከ1130 ጀምሮ ካዛንችስ በሚገኘው ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል አዳራሽ ይካሄዳል።

የመግቢያ ዋጋ 300 ብቻ

በኪነ ጥበብ ትውልድ ይታነፃል!
በኪነ ጥበብ ሀገር ይገነባል!
#በነፃ_ሀሳብና_በሰከነ_መንፈስ_ኢትዮጵያንና_ኢትዮጵያዊነትን_እናድምቅ!!
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
#ጦቢያ
የተከበራችሁ የጦቢያ ቤተሰቦች
ቀጣዩ መደበኛ ወርሃዊ የጥበብ መድረካችን አርብ
ሚያዚያ 4/2016 ከቀኑ ከ1130 ጀምሮ  ካዛንችስ በሚገኘው ኢንተርኮንትኔንታል ሆቴል አዳራሽ ይካሄዳል።

የመግቢያ ዋጋ 300 ብቻ

በኪነ ጥበብ ትውልድ ይታነፃል!
በኪነ ጥበብ ሀገር ይገነባል!
#በነፃ_ሀሳብና_በሰከነ_መንፈስ_ኢትዮጵያንና_ኢትዮጵያዊነትን_እናድምቅ!!
Eid Al-fitr
ለመላው የእስልምና እምነት
ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለዒድ አልፈጥር በዓል
በሰላም አደረሳችሁ።

ዒድ ሙባረክ
ለተከበራችሁ የጦቢያ ቤተሰቦች በድጋሚ ይቅርታ እንጠይቃለን!
የነገዉ መድረካችን ተራዝሟል!።

ዛሬ ከሰአት በኋላ ለሆቴሉ ከወረዳዉ የሰላምና ፀጥታ ቢሮ መመሪያ እንደመጣላቸው መመሪያም ከአዲስ አበባ መስተዳደር የሰላምና ፀጥታ ቢሮ "ዝግጅት የማቅረብና የመሰብሰብ ፈቃድ" የሚል ሲሆን የተጠየቅነው የፈቃድ ደብዳቤ ለማቅረብ ያለን ጊዜ አጭር በመሆኑ ዝግጅቱን ማከናወን ስለማንችል ላልተወሰነ ቀናት ተራዝሟል ።

ከሀዋሳ ለመጣችሁ ምሁራን እና ለመላው የጦቢያ ታዳሚያንና አቅራቢያዎች ይቅርታ እንጠይቃለን! ትኬቱን ለገዛችሁ በቀጣዩ መድረካች ትጠቀሙበታላችሁ።

ቸር እንሰንብት
“ ጦቢያ” ለ2024 የሲድ ሽልማት ተመረጠ !!!

በሀገረ አሜሪካ የተመሰረተ እና ለ31 ዓመታት ለሀገራቸዉ በተለያየ ዘርፍ አገልግለዋል ያላቸዉን ተቋማትና ግለሰብ በመሸለም የሚታወቀዉ ማህበረ ግዩራን ዘረ ኢትዮዽያ / SEED / የሽልማት ድርጅት ዘንድሮ ለምርጫ ከቀረቡልን ኦርጋናይዜሽን መሀከል ጦቢያ ለ12 ዓመታት በመድረኩ ባለሙያዎችን፣የሀገር ሽማግሌዎች፣ የዕምነት አባቶች ምሁራንገጣሚያን፣ደራሲያን፣ተዋንያን፣ሙዚቀኞች
እና የተለያዩ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ኢትዮጵያዊ
አንድነትን አድማቂ ስራዎቻቸውን እንዲያቀርቡ
መድረክ በማመቻቸት ሀገርን በሚገነባና ትውልድን በሚያንፅ ተግባር ባደረገው አስተዋፅኦ የዘንድሮ ተመራጭ ተሸላሚያችን ሆኗል ሲሉ የሽልማት ድርጅቱ መስራችና ፕሬዘደንት አቶ አክሊሉ ደምሴ ለአርትስ ቲቪ ዜና ጋር በነበራቸዉ ቆይታ አስታዉቀዋል ።

ከሁሉ በፊት የመኖርን ፣ የመከበርን ፣ የመሸለምን እድል ፈንታ ለሚሰጥ ፈጣሪያችን ክብር ይግባዉ ።

እኛም ሀገራችንን በልቀቷ ፣ በታሪኳ ፣ በቀደምትነቷ በዝናዋ ፣ በጀግኖች ልጆቿ ክብር ፣ ተፈጥሮ ባደላት ዉበት ፣ በህዝቧ ህብረቀለም እሴትና ባህል ልክ ባንሰራም ፡ መድረካችን በቻለዉ አቅም በገባን በተረዳነዉ መጠን ነገር ግን በሙሉ መሰጠትና ትጋት ያደረግነዉ ኢምንት ተሳትፎአችንን በማጤን ወደፊት ለምናልመዉ ራዕይ ጉልበት ልትሆኑን ስለመረጣችሁን ከልብ እናመሰግናችኋለን ።

በረጅሙ የጦቢያ አመታት በስራችን ተስፋ ያደረጋችሁ ፣ የመረቃችሁ የደገፋችሁን እናመሰግናለን።

በስህተታችን ያሳዘናችሁ ፣ ባቅም ዉስንነት ምክንያት ከተደራሽነት ያጎደልናችሁ ሁሉ ልባዊ ይቅርታ እንጠይቃለን ፡ እንክሳለን ።

ጦቢያን የመሰረታችሁ ፣ ያመከራችሁ በመድረኩ ስራዎቻችሁን ያቀረባችሁ ታዳጊ፣ ወጣት፣ አንጋፋ ባለሙያ ፣ ምሁራን ፣ የእምነት አባቶች ፣ተቋማትና ድርጅቶች ፣ በመድረክና ከመድረክ ጀርባ ጠቅሰን በማንዘልቀዉ እገዛችሁ ለጦቢያ ጕዞ ሀሳብ ፣ እዉቀት ፣ ጉልበት ፣ ገንዘብ አዋጥታችኋልና እነሆ ምስጋና ።

የተከበራችሁ የተወደዳችሁ ልዩ ተመስጋኛቻችን የጦቢያ ታዳሚያን ፣ ቤተሰቦቻችን እና የቴሌቭዥን ተመልካችቻችን ውለታችሁ አይዘነጋም ።

ከሀገር ዉጭ ያላችሁ ኢትዮዽያዉያን የጦቢያ ቤተሰቦች ፡ እየደወላችሁ ለምታበረቱን ፣ በቤታችሁ ክብር ያለዉ አቀባበልና መስተግዶ ላደረጋችሁልን ሁሉ ምስጋና ይድረሳችሁ ።

አርትስ ቴሌቭዠን ጦቢያ በመላዉ አለም ተደራሽ እንዲሆን ላደረገዉ የላቀ ተግባር እናመሰግናለን ።

በቀጣይ የጦቢያን አመሰራረት ሂደት ለመማሪያነትን ለጥናት ይረዳ ዘንድ ዉሉን ያልሳተ መረጃና የጎዞ ታሪክ በባለሙያ ተሰንዶ ይቀርባል ።

ሽልማትም ጌጥም ወርቅም የሚያምረዉ የሚደምቀዉ በሀገር ነዉና

ሀገራችን “ኢትዮዽያን “ ሰላም ያድርግልን።

ማጠቃለያዬ …
የታላቁ ባለቅኔ ፣ገጣሚ ፣ ፀሀፊ ተዉኔት ሎሬት ፀጋዬ ገብረመድህን ቃል ተዋስኩት ..

ካደረግነዉ ይልቅ ያላደረግነዉ ይቇጨኛል !!!!!
"ጦቢያ የክብር ሽልማት የዓመቱ ምርጥ 5 የመዝናኛ የቴሌቭዥን መርሀግብሮች ውስጥ በዕጩነት ተመረጠ ።

በቃል መልቲሚዲያ አማካይነት ‹‹ክብር ሽልማት›› በሚል ሀሳብ ለደራሲዎችና ለሚዲያ ባለሙያዎች ፣ በግጥምና ወግ ፣ ለጋዜጠኞች ፣ ለመዝናኛ ዝግጅት አቅራቢ ፣ ለቴሌቭዥን መዝናኛ መርሀግብር ዕውቅና ለመስጠትና ለመሸለም በ16 ዘርፎች በባለሙያና በህዝብ ድምፅ ሲሰጥባቸው የቆየ ሲሆን ከእያንዳንዱ ዘርፍ ከተጠቆሙ ውስጥ “ጦቢያ“ በምርጥ የቴሌቪዥን መዝናኛ ፕሮግራም ምርጥ 5ቱ ውስጥ ተካትቷል።
የጦቢያ ቤተሰቦች አድናቂዎችና መላው ውድ ተመልካቾቻችን ከታች የተቀመጠው ሊንክ በመጫን ድምፃችሁን እንድትሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን።

https://kibershilemat.com
ሊንኩን በመጫን ድምፅዎን ይስጡ!።
Forwarded from ጦቢያ ግጥምን በጃዝ (🅢🅞🅛🅰🅺🅸🅰 Tsebaot)
.....ህማማት
.....
አባ አይኮንኑኝ
የጦም በመብላቴ
እንቁላል በልቼ
ብትቆይ ህይወቴ
ሌሎቹን ሳያዩ
እኔን አይገዝቱ
ሰው እየቦጨቁ
በለተ ህማማቱ
ምን ነው ግን አባቴ
በኔ ላይ በረቱ???
ቀለል አርገው አይተው
አባቴ ይፍቱኛ
የጣለችው ዶሮ
ነበረች ጦመኛ
በህይወት ዘመኗ
ስትጭር ስትለቃቅም
ከጥሬ በስተቀር
አንዳች በልታ አታውቅም

ፀባዖት ሶልአኪያ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
“እርሱ ግን፦ አትደንግጡ፤ የተሰቀለውን የናዝሬቱን ኢየሱስን ትፈልጋላችሁ፤ ተነሥቶአል፥ በዚህ የለም፤ እነሆ እርሱን ያኖሩበት ስፍራ።”
  — ማርቆስ 16፥6

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሳኤ በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን 🙏

መልካም በዓል!!
HTML Embed Code:
2024/06/03 07:24:01
Back to Top