Channel: መንፈሳዊ የህይወት ምክር
" ያዳነን በቅዱስም አጠራር የጠራን እግዚአብሔር ነውና፥ . . ." (2ኛ ጢሞ 1፥9)
መለኮታዊ የሆነውን ተልእኮ ለመፈጸም ከቶ የሰውን ፈቃድ መጠበቅ የለብንም። እግዚአብሔር ወደራሱ ሲጠራን ማንንም አላማከረም፤የእኛን የልብ ፈቃድ ከመመልከት ውጪ። ማንም ደግሞ እግዚአብሔር ወደራሱ እንዴት እንደሳበንና ልባችንን እንደነካው ፍጹም የሆነውን ሚስጥር አያውቅም፤ ከድንጋይ ይልቅ ጠጣራ፣ እንኳን የሰውን የአምላክን ማንነት ክዳ በምድረበዳ ልኖረችው ልባችን፡ እንዴት አድርጎ ክርስቶስ በፍቅሩ መዶሻ እንዳፈረከሳት የሚረዳም ሆነ የሚያውቅ ፈጽሞ የለም። እናም ሰውን ደስ ከማስኘት ይልቅ አምላክን መታዘዘ ብርቱ ከሆነ ኪሳራ አውጥቶ ዘላለማዊ ትርፍ የሚስገኝ ነገር መሆኑን ልብ ልንለው የሚገባ ነገር ነው።
በልብህም ይሁን በአእምሮ ጽላት ላይ የተጻፈውን መልኮታዊ አጀንድ፣ ለእግዚአብሔር ይህን በሕዝቤ መካከል አደርጋለው ብሎ ሲያመልክትክ ለልብህም ሲናገራት ማንን አማክሮ ነው? ባጠገብህስ ማንን ምስክር አስቀምጦ ነው? አምልካዊ እይታውን መንፈሳዊ አይኖችህን አብርቶ በመንግስቱ ውስጥ የድርሻህን እንድትወጣ ያየውን እንድታይ እና እንድትከውን ራዕይን ሲሰጥህ ማንን ተማምኖ ነው? ከዚያ ከውዳቂ ሰፈር እውጥቶ ወደ አላማ እና ግቡ ወደ ሚያደርሰው የከበረ ሰረገላ ላይ ሲያሳፍርክ እርሱን ለመታዘዝና ለመሄድ " አማላክ ሆይ ይህው እኔ ላከኝ" በሚል ልብ በፊት ከመሆን ይልቅ ስለምን በዙሪያ ያልውን ነገር ማይት አስፈለገ? ስለምንስ ካምላክ ይልቅ የሰውን ፍቃድ እንጠብቃልን?? አብርሃም አምላኩን እሺ ባይልና ባይታዘዝ ለዓለሙ መዳን ተስፋ የሆነው የክርስቶስ የኪዳን ዘር ምን ይመስል እንደነበረ ማሰብ ከባድ ነው። ዳዊት ስንቅን ሊያደርስ ሲሄደ ከአምላኩ ይልቅ፡ የሰማውንና የታዘዘው ውንድሞቹን ቢሆን ፍልስጤም በእስራኤል ላይ ምን ያደርግ ይሆን? ከደም መፍሰስ ነጻ ወጥታ የክርስቶስን እግር በሽቱ የጠበችው ማሪያም መቅደላዊት ያንን ለማደረግ ለቧ ከውሰነው ውሳኔ ይልቅ ለደቀመዛሙርቱና በቤቱ ለነበረው ማጉረምረም ታዛ ወደ ኋላ ብትል " ይህ ወንጌል በተነገረበት ስፍራ ሁሉ" የተባለው ስለ እርሷ የተነገረው ምስክርነት ይነገር ይሆን?።
እርግጥ ነው እንዳንድ ጊዜ ተመክሮዎችንም ይሁን ምክሮችን በመልካምነቱ ከሰዎች መቀበል ይሁን፣ መስማትና መተግበር አስፈላጊ ነው፤ ፍጹም በሆነ መንገድ ግን ሰምቶ መልኮታዊውን የአምላክ ትዕዛዝ ለመታዘዝ የሰውን ፍቃድ መጠበቅ ፈጽሞ ስህተት ነው። " ጴጥሮስና ሐዋርያትም መልሰው አሉ። ከሰው ይልቅ ለእግዚአብሔር ልንታዘዝ ይገባል።" ሐዋ 5፥29
ልንታዘዘው የተገባውን የመልኮትን እጀንዳ ጊዜና ውቅት ልንቀጥርለት አይገባም በፍጹም፤ ዘግይቶ መታዘዝ ካለመታዘዝ አይለይም። እርሱ ነውና ለአላማው የጠራችሁ እርሱን ታዘዙት።
" የሚጠራችሁ የታመነ ነው፥ እርሱም ደግሞ ያደርገዋል።" 1ተሰ 5፥24

ሰበር መረጃ
መንግሥት የቤተ ክርስቲያኗን የጥበቃ መሣሪያ እየነጠቀ ነው!
ከቅዱስ ሲኖዶስ መግለጫ በኋላ አዲስ መመሪያ ወጥቷል። መመሪያው በየአጥቢያው ለጥበቃ የሚያገለግሉ መሣሪያዎች በአስቸኳይ እንዲወረሱ የሚል ነው። በዚህም መሠረት የአዲስ አበባ ፖሊስ አዛዦች የአጥቢያ አስተዳዳሪዎችን እየደወሉ ባስቸኳይ አስረክቡ ማለት ጀምረዋል። በአስኮ ገብርኤል እና በአንዳንድ ቦታዎች ፖሊስ መሣሪያውን ሊረከብ ሲል ሕዝቡ ደርሶ አስቀርቶታል።
የጥበቃ መሣሪያ ፈቃድ ወጥቶለት ቤተ ክርስቲያኗ ለጥበቃ አገልግሎት የምትጠቀምበት ሲሆን ከረጅም ዓመታት በፊት ጀምሮ ጥቅም ላይ ያለ ነው።
በአበውና በባለሥልጣናት ውይይት መሠረት ሰላማዊ ሰልፉ ከተራዘመ በኋላ መሣሪያ መንጠቅ ለምን አስፈለገ? የሚለው የየአጥቢያውን አገልጋዮች አስደንግጧል።
ሁላችንም በየአጥቢያችን በመሄድ የመሣሪያ ነጠቃውን እናስቀር።
https://hottg.com/onesinod

Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA
መላው የኦርቶዶክስ ልጆች አዲሱን ዓመት በዘፈንና ዳንኪራ ሳይሆን በቤተክርስቲያናቸው በጸሎት ፣ በምህላ፣ የቻለም ደግሞ በመጾም፣ እግዚአብሔርን በመመለመን እንዲቀበሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ጥሪ አስተላለፈች።
ቤተክርስቲያን ይህን ጥሪ ያስተላለፈችው የአዲሱን ዓመት አቀባበል በተመለከተ በሰጠችው መግለጫ ነው።
በዚህም የጷጉሜን ወር ፮ ቀናት መላው ኦርቶዶክሳዊ በጸሎት እና በምህላ እንዲያሳልፍ ታውጇል።
ቤተክርስቲያን ፤ ዘመኑ ከደስታ እና የምስራች ይልቅ ሀዘንን የምንሰማበት ዘመን ስለሆነ ምዕመናን የተቸገሩትን የተራቡትን ፣ የተፈናቀሉትን እና የተጎዱትን እያሰቡ በጾምና በጸሎት እንዲያሳልፉ ስትል ጥሪዋን አቅርባለች።
ምዕመናን በዚህ ወቅት ከዘፈን እና ከዳንኪራ እንዲርቁ አሳስባለች።
ብፁህ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ እና የባህር ዳር ሀገረ ስብከት ሊቃ ጳጳስ ፤ " አንዳንድ የዘፈን ግብዣዎችን እየሰማን ነው ፤ ሀገር በሚያልቀስበት፣ የንፁሃን ደም በሚፈስበት ሰቆቃ በበዛበት ረሃብ ችግር በሰፈነበት የዳንኪራ ግብዣ እየሰማን ነው " ብለዋል።
" ለምንም የማይጠቅሙ ብዙ ነገሮች እየተስተጋቡ ነው " ያሉት ብፁዕነታቸው " ይህን እየሰማን ያለነው መደፋፈሩ በዝቶ ፣ ከመጠን በላይ ኑሮ፣ ንቀቱ በዝቶ፣ ማንአለብኝነቱ እንደልብ ተናጋሪው ፣ ፀብ አጫሪው ሃይ የሚለው ጠፍቶ ብዙ ነገሮች እየተደረጉ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።
ብፁዕነታቸው አለኝ ባሉት መረጃ " ቤተክርስቲያን ዘቅዝቆ እሳት ያያያዘ ፣ መስቀል ዘቅዝቆ አንገቱ ላይ ያጠለቀ ኢትዮጵያ ምድር ላይ ሊዘፍን ተዘጋጅቷል፤ ግብዣም ተደርጓል። " ብለዋል።
" የሰዎችን መብት መንካት ስለማንችል እንደ ኢትዮጵያውያን እገሌ እገሌ ሳይል ከእንዲህ አይነቱ ማንም ተካፋይ ሳይሆን እንደ ኦርቶዶክሳዊያን ዳግሞ የኦርቶዶክስ ልጆች ለፀሎት ታውጇል ፣ ለጾም ለጸሎት እራስን ከማዘጋጀት ውጭ ምንም ትርፍ የሌለው ከሳንቲም ውጭ ትርፍ ለሌለው የሀገርን ገፅታ የሚንድ ድርጊት ላይ ተሳታፊ ከመሆን #እንድትቆጠቡ " ብለዋል።
" አባቶቻችን ቅድሚያ የሚሰጡት ለጾም ፣ለጸሎት ለፍቅር፣ ለሰላም ነው ፤ ውሃ ሙላት እያሳሳቀ ይወስዳል እንደሚሉት አባቶች በዘፈን እና በዳንኪራ እያሳሳቀ ወደ ሞት፣ ወደ ማዕበሉ የሚገፋ ነገር ላይ ተሳታፊ እንድንሆን ቤተክርስቲያን አትፈቅድም ፣ የሃይማኖት ሰዎችም ድርሻ አይደለም " ሲሉ አስግዝበዋል።
ብፁዕነታቸው ፤ " እኔ ምን አገባኝ በሚል በዘመናዊ ስሜት እንደልብ ተካፋይ መሆን በእግዚአብሔር ዘንድ ነውር ነው ፤ ወንጀልም ነው " ያሉ ሲሆን " ፀብ አጫሪ መሆንም አስፈላጊ ስላልሆነ የኦርቶዶክስ ልጆች በቤታችሁ ሰብሰብ ብላችሁ ተቀመጡ፤ የሚመለከተው እንደፈለገ ይሁን ፤ ኦርቶዶክሳውያን ከቤተክርስቲያናችሁ ተገኝታችሁ ጸልዩ፣ እግዚአብሔርን ለምኑ አብረን ተያይዘን እንዳንጠፋ " ብለዋል።
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፤ በጳጉሜን 6 ቀናት ሁሉም ምዕመናን እግዚአብሔር መጪውን ዘመን የሰላም፣ የፍቅር፣ የመተሳሰብ የአንድነት፣ ብሶተኛ የማይኖርበት ተራብኩ ተጠማሁ ተፈናቀልኩ ተሰቃየሁ ተንገላታሁ የሚል የማይኖርበት ፣ ኢትዮጵያውያን በፍቅር በአንድነት የምንኖርበት ዘመን እንዲሰጠን ጸሎት በማድረግ እናሳልፍ ስትል አደራ ብላለች።
ጸሎት ለሁሉም የታወጀ ሲሆን ፤ ጾምን በተመለከተ የወደደ ይጹም ፤ ያልወደደም / ፕሮግራሞች ቀደሞ የያዘም እንዲጾም አይገደደም በነፃነቱ መጠቀም ይችላል ተብሏል።
@tikvahethiopia

👉ጸሎት ለማድረግ አታቅማማ፤ ሥጋ ከምግብ በተከለከለ መጠን ደካማ እንደሚሆን ነፍስም ከጸሎት ስትከለከል ደካማ ትሆናለች፡፡ (አቡነ ማቴዎስ ግብፃዊ)
ስለሁሉም ነገር ሳታቋርጥ ጸልይ፤ እንዲህ ካላደረግክ ምንም ነገር ያለ ልዑል እግዚአብሔር ፈቃድ የማታከናውን ትሆናለህ፡፡ ያለጸሎት ራሱን በማንኛውም ዓለማዊ ጉዳዮች የሚያደክም ሰው በመጨረሻ ውጤታማ ሊሆን አይችልም፡፡ ሰው ራሱን ኃጢአተኛ እንደሆነ እያሰበ ወደ እግዚአብሔር ካለየ ጸሎቱ ተቀባይነት አይኖረውም ፡፡ (አባ አጋቶን)
እግዚአብሔር ለሰው ምሕረትን ሲያድል አንድ ሰው እንዲጸልይለት ያነሣሣዋል፡፡ በዚህ ጸሎት አማካኝነትም ይረዳዋል፡፡ በመከራ ጊዜ ያለማቋረጥ መሓሪውን አምላክ በጸሎት ጥራው፡፡ ባለማቋረጥ የእግዚአብሔርን ስም መጥራት ለነፍስ ቁስል መድኃኒት ነው፡፡ ሰው በታመመ ጊዜ ዶክተሩ ፍቱን መድኃኒትን ፈልጎ ለበሽተኛው እንደሚሰጠው መድኃኒቱም ወደ ሰውነቱ ገብቶ ሥራ ሲሠራ እንጂ እንዴት እንደሚሰራ እንደማናውቀው በተመሳሳይ ሁኔታ የእግዚአብሔርን ስም አዘውትረን ስንጠራ እንዴት ጸሎታችን እንደሰራ ሳናውቅ የእግዚአብሔርን ፍቅር ምህረትና ርኅራኄ በእኛ ላይ ሲደረግ እንመለከታለን፡፡
(አቡነ ማቴዎስ ግብጻዊ)

በአንድ ወቅት አንድ መንፈሳዊ አባት ከነበሩበት ቦታ ወደ በረሃ መሰደድ ግድ ሆነባቸው። ከቅዱስ መጽሐፋቸው ሌላ ሦስት ነገሮች ነበሯቸው።
እነሱም፦ ቅዱስ መጽሐፉን በጨለማ ወቅት ለማንበብ የሚጠቅማቸው ኩራዝ ፣ጎህ ከመቅደዱ በፊት ከእንቅልፍ የሚቀሰቅሳቸው አንድ አውራ ዶሮ እና ለመጓጓዣነት የሚገለገሉበት አንድ አህያ ነበሩ።
አንድ ቀን ምሽት ከጉዞ የተነሣ በጣም ስለ ደከሙ እኚህ መንፈሳዊ አባት ወደ አንድ መንደር ቀርበው ማደሪያ ቢጠይቁም መንደርተኛው ፈቃደኛ ባለመሆኑ ማንም አላሳደራቸውም። ስለዚህም ከመንደሩ አቅራቢያ አንድ ጉድጓድ ያገኙና በዚያ ውስጥ ገብቶ ለማደር በመወሰን ገብተው አደሩ። እንደ ወትሮው ቅዱስ መጽሐፋቸውን ለማንበብ ኩራዛቸውን ቢለኩሱትም የነበረው ብርቱ ነፋስ አጠፋባቸው።
ስለዚህም ለመተኛት ጋደም እንዳሉ ተኩላ መጥቶ አውራ ዶሮዋቸውን፣ አንበሳም አህያቸውን በሉባቸው። የተደራረበ ጉዳት ስለደረሰባቸው ሽማግሌው እርዳታን በመሻት ወደዚያ መንደር ቢመለሱ ዘራፊ ሽፍታዎች የመንደሩን ነዋሪዎች በሙሉ ገድለው ንብረት ዘርፈው ዖና መንደር ሆኖ አገኙት።
ሽማግሌው ይህን ሁሉ ባጤኑ ጊዜ እግዚአብሔር ምን ያህል መልካም ነገርን እንዳደረገላቸው አስተዋሉ። በዚያች ምሽት በመንደርተኞቹ በአንዱ ቤት ቢያድሩ ኖሮ የዘራፊዎች ሰለባ ሆነው ሊገደሉ በቻሉ ነበር። ቀንዲላቸውንም ነፋስ ባያጠፋው የብርሃኑ ወጋገን እዚህ ጋር ሰው አለ በማለት ለሽፍታዎቹ ያሳብቅ ነበር። አውራ ዶሮአቸውና አህያቸውም ባይበሉ ኖሮ ከሽፍታዎቹ ተደብቀው ማደር ባልቻሉ ነበር።” እግዚአብሔር ከክፉ ነገሮች ውስጥ መልካም ነገር ማውጣት የሚችል አምላክ ነው።"
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
ስለዚህ እንዲህ በሉ፦ "የሚደርስብኝ ፤ የሚገጥመኝ ፈተናና መከራ ሁሉ አምላኬ ሆይ ለበጎ ታደርግልኛለህና አመሰግንሐለሁ" አሜን
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ

፨በጭንቀት ጊዜ የሚያፅናኑ ቃላት፨
።> እነሆም እኔ እስከ አለም ፍፃሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ። ማቴ28፥20
∞∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞
።> በአንቺ ላይ የተሰራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም። ኢሳ 53፥17
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >እኔ ነኝ አትፍሩ አላቸው።
ዮሐ 6፥20
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ፤ ሰዎች በእኛ ላይ በተነሱ ጊዜ ቁጣቸዉ በላያችን በነደደ ጊዜ ፤ በዚያን ጊዜ ሕያዋን ሳለን በዋጡን ነበር፤ ....ለጥርሳቸዉ ንክሻ ያላደረገን እግዚአብሔር ይባረክ ። ነፍሳችን እንደ ወፍ ከአዳኞች ወጥመድ አመለጠች፤ ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን ። ረድኤታችን ሰማይንና ምድርን በሠራ በእግዚአብሔር ነዉ። መዝ 123፥2፤3፤6-8
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> ፃድቃን እጃቸውን ወደ ክፋት እንዳይዘረጉ ፤ የኃጥአን በትር በፃድቃን ዕጣ ላይ አይኖርም። መዝ 124፥3
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >እነሆም እኔ ከአንተ ጋር ነኝ፤ በምትሄድባትም መንገድ ሁሉ እጠብቅሃለሁ ፤ ወደዚህችም ምድር እመልስልሃለሁ ፤ የነገርሁህን ሁሉ እስካደርግልህ ድረስ አልተውህምና።
ዘፍ 28፥15
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> ከአንተ ጋር ይዋጋሉ ፤ ነገር ግን አድንህ ዘንድ እኔ ከአንተ ጋር ነኝና ድል አይነሱህም ፤ ይላል እግዚአብሔር ኤር 1፥19
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> እኔ ከአንተ ጋር ነኛ ፤ ማንም ክፉ ሊያደርግብህ የሚነሳብህ የለምና አትፍራ፤
ሐዋ18፥9-10
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> በአለም ሳላችሁ መከራ አለባችሁ ፤ነገር ግን አይዟችሁ ፤ እኔ አለምን አሸንፌዋለሁ።
ዮሐ 16፥33
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> ከትንሽነቴ ጀምሮ ብዙ ጊዜ ተሰለፉብኝ ፤ ነገር ግን አላሸነፉኝም። ኃጢአተኞች በጀርባዬ ላይ መቱኝ ፤ኃጢአታቸዉንም አስረዘሟት ። እግዚአብሔር ፃድቅ ነው ፤ የኃጢአተኞችን አንገታቸውን ቆረጠ ።
መዝ 128፥2-4
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።>ገፉኝ ለመዉደቅም ተንገዳገድሁ ፤ እግዚአብሔር ግን አገዘኝ ። መዝ 117፥13
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ ፤አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም።
መዝ 22፥4
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> በአጠገብህ ሺህ በቀኝህም አስር ሺህ ይወድቃሉ፤ ወደአንተ ግን አይቀርብም ። በአይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ ፤ የኃጥአንን ብድራት ታያለህ። መዝ 90፥7-8
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
። >እግዚአብሔር ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል ፤ ነፍስህንም ይጠብቃታል ። ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለአለም እግዚአብሔር መዉጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል። መዝ 120፥7-8
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
።> እግዚአብሔር ብርሃኔና
መድሀኒቴ ነው ፤ የሚያስፈራኝ ማንነው ? እግዚአብሔር የህይወቴ መታመኛዋ ነው ፤የሚያስደነግጠኝ ማነው ? ሠራዊትም ቢሰፍርብኝ ልቤ አይፈራም ፤ ሰልፍም ቢነሳብኝ በዚህ እተማመናለሁ
መዝ 26፥1-3
∞∞∞∞∞✞∞∞∞∞∞
ሰላም ለኢትዮጵያ ሰላም ለሀገራችን ይላክልን ቸሩ አምላካችን!
📌➴📌➴📌➴📌➴📌➴📌
@Menfesawimeker
👆👆👆👆👆👆👆👆👆

+ የቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ ምክር +
☞ ተወዳጆች ሆይ ጊዜ ሳለልን ድኅነታችንን እንፈጽም፡፡ ጊዜ ሳለልን ለመብራታችን ዘይት የተባለ ምጽዋትን እንያዝ፡፡ ጊዜ ሳለልን መክሊታችንን ለማብዛት እንፍጨርጨር፡፡ በዚህ ዓለም ሳለን ይህን ለማከናወን ልል ዘሊል እና ሐኬተኞች ከኾንን በወዲያኛው ዓለም እልፍ ወትእልፊት ጊዜ ወዮ ብለን ብናለቅስ ብንጮህም እንኳን የሚረዳን የለምና፡፡ ያ ባለ አንድ መክሊት ሠራተኛ አንዲቷን መክሊት ሳይቀንስ ለጌታው ቢያስረክብም ከኩነኔ አላመለጠምና፡፡ አምስቱ ሰነፎች ደናግልም ጌታችንን ለምነውት ነበር፤ በሩን አንኳኩተው ነበር፡፡ ነገር ግን ልመናቸውም ማንኳኳታቸውም ከንቱ ነበር፥ ጥቅም አልባ ነበር፡፡
☞ስለዚህ እነዚህን ነገሮች ዐውቀን በሀብታችንም፣ በትጋታችንም፣ ለወንድማችን በምናደርገው ማናቸውም ጠቃሚ ነገርም የዓቅማችንን ያህል እንጣር፡፡ መክሊት የተባለው የእያንዳንዱ ሰው በእጁ ያለውና ማድረግ የሚችለው ነገር ማለት ነውና፡፡ ለአንዱ ወንድሙን መጠበቅ ሊኾን ይችላል፥ ለአንዱ በገንዘቡ ደግ ነገር ማድረግ ሊኾን ይችላል፥ ለሌላው ማስተማር ሊኾን ይችላል፥ ለሌላው ደግሞ ይህን በመሰለ ሌላ ነገር ሊኾን ይችላልና ጊዜ ሳለልን በሞተ ሥጋም ሳንወሰድ መክሊታችንን እናብዛ፡፡ አንድ ሰውስ እንኳን መክሊቴ አንዲት ናት አይበል፡፡ የተሰጠችህ መክሊት አንዲት ብትኾንም አንተ ንቁ ከኾንህ ንዑድ ክቡር ከመባል አትከለከልምና፡፡ ምንም ያህል ድኻ ብትኾንም ከዚያች ኹለት ሳንቲም ከሰጠችው ሴት በላይ ድኻ ልትኾን አትችልምና የተሰጠቺኝ ትንሽ ናት አትበለኝ፡፡ ከቅዱስ ጴጥሮስና ከቅዱስ ዮሐንስ በላይ ያልተማርክ ልትኾን አትችልምና እኔኮ አልተማርኩም አትበለኝ፡፡ እነርሱ ምንም ያልተማሩ ቢኾኑም ባሳዩት ትጋት ርስት መንግሥተ ሰማያትን መውረስ ተችሎዋቸዋልና እኔ አይቻለኝም አትበለኝ፡፡
☞ እግዚአብሔር አንደበትን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር እግርን የሰጠን ለዚህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ብርታትን፣ አእምሮን፣ ማሰብን የለገሰን ለዚህ ነው፡፡ እነዚህን ኹሉ የሰጠን ለራሳችን እንድናተርፍባቸውና ለባልጀሮቻችንም እንድንጠቅምባቸው ነውና ኹለት ወይም አምስት መክሊት አልተሰጠኝም አትበለኝ፡፡'
ተርጓሚ፦ ገብረ እግዚአብሔር ኪደ

✝እግዚአብሔር ተስፋ አድርግ
ለመንጋው ሁሉ በጎ እንደሚመኝ እንደ መልካም እረኛ እግዚአብሔር ለፍጥረቱ በሙሉ ያለምንም ጥርጥር #በዝምታ_ይሠራል ። ይሁን እንጂ ሰዎች በመከራ ውስጥ ሆነው የእግዚአብሔር መልስ ከዘገየባቸው እንደማይሠራ አድርገው ያስባሉ ። እነርሱ እግዚአብሔር አይሠራም ብለው በሚያስብበት ሰዓት ሁሉ እርሱ ግን ለእነርሱ #በጥልቅ_እየሠራ ነው ። ሰዎች ይህንን ስለማይገነዘቡ የእግዚአብሔርን ሥራና የሥራውን ውጤት ፈጥነው ለማየት ይፈልጋሉ ። እነዚህ ሰዎች ግን በእምነታቸው ያመኑትን በዓይናቸው እስኪመለከቱ ድረስ ሊቆዩ ይገባቸዋል ። " እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ፤ በርታ ልብህም ይጽና ፤ እግዚአብሔርን ተስፋ አድርግ ። " [መዝ 26*14 ] ።
እግዚአብሔርን እንዴት እንጠብቅ?
እግዚአብሔርን የሚጠብቅ ሰው እርሱን በተስፋ ፤ በእምነት ፤ በተሞላ ሙሉ ልብና ያለምንም ድካም ይጠብቀዋል ። ይህ በመሆኑም እንደዚህ ዓይነቱ ሰው እግዚአብሔር በመካከል ገብቶ እንደሚሰራና ሁሉም ነገር ለበጎ እንደሚሆን ያምናል ። " እግዚአብሔር ለሚወዱት እንደ አሳቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን ።" [ ሮሜ 8*28] ። " እግዚአብሔርን በመተማመን የሚጠባበቁ ግን ኃይላቸውን ያድሳሉ እንደ ንስር በክንፍ ይወጣሉ ፤ ይሮጣሉ አይታክቱም ይሄዳሉ አይደክሙም " [ኢሳ 40*31] ። ኃይላቸው በመከራ የተናወጠባቸው ሁሉ እግዚአብሔርን በተስፋ በመጠባበቅ ኃይላቸውን ያድሳሉ ማለት ነው ። " ጎልማስነትሽን እንደ ንስር ያድሳል " የሚል ቃል ተጽፋል [ መዝ 102*5] ። ስለሆነም ማንም ቢሆን እግዚአብሔር #እምነት በተሞላ ብርቱ ልብና በእርሱ ላይ በመተማመን ይጠብቀዋል ።
ነገር ግን አንድ ሰው እግዚአብሔር እርምጃ እንደሚወስድና እርምጃውም ግልጽና ኃያል እንደሆነ መተማመን አለበት ። ከዚሁ ጋር እርምጃው በተመቻቸ ሰዓት ፍሬያማ በሆነ መንገድ የሚከናወን ነው ። እግዚአብሔር አንድ የሆነ እርምጃ ለመውሰድ ከወደደ ምንም የሚጠባበቀው ሰዓት አይኖርም ። ኢየሱስ ክርስቶስ " ... አብ በገዛ ሥልጣኑ ያደረገውን ወራትንና ዘመናትን ታውቁ ዘንድ ለእናንተ አልተሰጣችሁም አላለምን ? /ሐዋ 1*7/ ። አንተ ችግርህን እግዚአብሔር እንደሚያቃልልህ በማመን መቼ ለችግርህ መፍትሔ እንደሚሰጥህ ሳታስብ በእርሱ እጅ ላይ ብቻ ጣለው ። ችግርህን እግዚአብሔር በጊዜው እንደሚያቃልለው መጠባበቅ የአንተ ሥራ አይደለም ።
አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ

አንድ ተማሪ በፈተና አዳራሽ ገብቶ ሁለት ጥያቄዎችን እንዲሠራ ተሰጠው። ጥያቄዎቹ እነዚህ ናቸው።
1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።
ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።
የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።
ወንድሜ ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ
1. ስለ እግዚአብሔር ጻፍ
2. ስለ ሰይጣን ጻፍ የሚሉ ነበሩ።
ጥያቄዎቹን ካነበበ በኋላ ስለእግዚአብሔር ጻፍ የሚለውን ይጽፍ ጀመረ። ነገር ግን የተሰጠው ጊዜ አንድ ሰዓት ብቻ ስለነበር ሙሉውን ሰዓት ስለ እግዚአብሔር ሲጽፍ ቆይቶ ሰዐቱን ጨረሰ።
የፈተናውን ወረቀት የሚሰበስበት ጊዜ ደርሶ ደውል ተደወለ ብልሁም ተማሪ ሁለተኛውን ጥያቄ አለመሥራቱን ተረድቶ "ለሰይጣን ጊዜ የለኝም" ብሎ በአንድ መስመር መልስ ሰጠ።
ወንድሜ ሆይ ለሰይጣን ጊዜ አይኑርህ።
@menfesawimeker
🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿🌿
አሁንም ለ ጥያቄያችሁ
@menfesawimekerbot ይጠቀሙ
Forwarded from መንፈሳዊ የህይወት ምክር
ጌታ ሆይ፥ ከአንተ የሆነውን ሰማያዊ ደስታ አትንፈገኝ።
ጌታ ሆይ፥ ከዘላለም ፍርድ አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ በአሳብም ሆነ በአእምሮ፥ በቃልም ሆነ በሥራ ብበድል ይቅር በለኝ።
ጌታ ሆይ፥ ከአላዋቂነት፥ ከዝንጉነት፥ ከፈሪነት፥ ከልብ ጥንካሬ አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ከማናቸውም ፈተና አድነኝ።
ጌታ ሆይ፥ ክፉ ምኞት ያጨለመውን ልቤን አብራልኝ።
ጌታ ሆይ፥ ሰው የሆንኩት እኔ በድያለሁ፥ ነገር ግን አንተ ባለጸጋው አምላክ፥ ምሕረት አድርግልኝ፤ የነፍሴን በሽታ ታውቃለህና።
ጌታ ሆይ፥ ቅዱሱ ስምህን አክብር ዘንድ ጸጋህ እንዲያግዘኝ ላክልኝ።
ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ እኔን ባሪያህን በሕይወት መጽሐፍ ጻፈኝ፤ መልካም ፍጻሜ ስጠኝ።
ጌታዬ አምላኬ፥ በፊትህ ምንም መልካም ሥራ ባይኖረኝም፥ ከጸጋህ የተነሣ መልካም ጅማሬ አድለኝ።
ጌታ ሆይ፥ የጸጋህን ጠል በልቤ ላይ እርጨው፤ የሰማይና የምድር ጌታ፥ እኔን ኃጢአተኛውን አገልጋይህን በመንግሥትህ አስበኝ። አሜን። ደህና አምሹልኝ🙏
@menfesawimeker
👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ለ አስተያየት ወይም መንፈሳዊ ጥያቄ ካሎት
@menfesawimekerbot ላይ የጻፍልን

✝የእግዚአብሔር ፍቅር በልብህ ውስጥ ጠልቆ ከገባ ድካምህ ይጠፋል ።
ከእግዚአብሔርና ከትእዛዛቱ የበለጠ ኃጢአትን የምትወድ ከሆነ ደካማ ትሆናለህ ። ነገር ግን ፍቅሩ ወደ ልብህ ከገባ በውስጥህ ያለውን የኃጢአት ፍቅር አውጥቶ ይጥለዋል ። ስለሆነም ማንኛውንም ዓይነት ፈተና ለመቃወም ብርቱ ትሆናለህ ።
"ንስሓ ማለት ፍላጎትን በፍላጎት መቀየር ማለት ነው ።" ይህ ማለት የእግዚአብሔር ፍቅር የአለምን ፍቅር ይተካል ማለት ነው ። ስለዚህ ወደ እግዚአብሔር ፍቅር የሚመሩህን ማንኛውም አይነት መንፈሳዊ መንገዶች ሁሉ ተከተል ። ከዚህ በተጨማሪ እግዚአብሔርን ከሚወዱት ጋር ተባበር ! እርሱን ስለ ወደዱት ሰዎች የተጻፈውንም አንብብ ! በመጨረሻም ምሳሌያቸውን ተከተል ።
አቡነ ሺኖዳ ሳልሳዊ

"ጌታዬ አምላኬ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ የውስጤን የሚረዳልኝ እንዳንተ ያለ ማንንም አላገኝም፤ ከአንተ ጋር ስሆን ብቻ ደህንነት ስለሚሰማኝ ለአንተ ለአምላኬ ልቤን ከፍቼ ምስጢሬን አዋይሃለሁ። ቃልህን የምሰማ ነገር ግን የማላስተውል ደካማ ነኝና፣ ናፍቆቴን ቢገልፅልኝ እንባዬን በፊትህ አፈሰዋለሁ።ልቤን ከሚያጸናውና በሃይሉ ከሚደግፈኝ ጋር እንደሆንኩ አውቃለሁና ከአንተ ጋር ብቻ ስሆን #ብቸኝነት አይሰማኝም። ያለ አንተ ግን ባዶነቴ ያስጨንቀኛል። ከእኔ ጋር የሆንክ አማኑኤል አምላኬ ሆይ ነፍሴ ከአለምና በአለም ካሉት ከቁሳዊ ነገሮች ይልቅ የአንተን ሁሉን ቻይነት ትናፍቃለች። ውስጤ የማትወሰን አንተን ተጠምቷል። ከአንተም በቀር ይህን የሚረዳኝልኝ ከቶ የለም።"
አቡነ ሽኖዳ
@menfesawimeker
አቡነ ሽኖዳ
@menfesawimeker
ማግባት ስትፈልጉ ይህን አስተውሉ፦
የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ #ጽድቅን #መፈጸም ነው፡፡ ሌሎቹ የትዳር ዓላማዎች ኹሉ በዚህ የሚጠቃለሉ ናቸውና፡፡ ስለዚህ አንድ ወጣት፡-
ልጅን ለመውለድ ብቻ አስቦ ማግባት የለበትም፤ የትዳር አንዱ ዓላማ ልጅ መውለድ ቢኾንም ቅሉ፥ ላይወልድም ይችላልና፡፡
“በየምግብ ቤቱ መብላት ወጪውን አልቻልኩትም” ብሎ ማግባት የለበትም፡፡ “በገንዘብ እንድንረዳዳ” ብሎ ማግባት የለበትም፡፡ ወጪ መቀነስ መልካም ቢኾንም፥ የትዳር ዋናው ዓላማ ግን ከዚህ ከፍ ያለ ነውና፡፡ እንዲያውም ሊቁ፡- “ክርስቲያን ኾነህ ሳለ ከትዳር አጋርህ ገንዘብ ለማግኘት ብለህ ወደ ትዳር ከምትገባ ምድር ተከፍታ ብትውጥህ ይሻላል” ይላል፡፡ ስለዚህ “ገንዘብን አትሹ፤ የወላጆቹን ባለጸግነት አትመልከቱ፡፡ የትውልድ ቀዬውን ታላቅነትም አትዩ፡፡ እነዚህ ኹሉ ዋና ነገሮች አይደሉምና፡፡ ከትዳር አጋራችሁ ጋር በተድላ በደስታ መኖርን ስትሹ ማየት የሚገባ’ችሁ ንጽሃ ነፍስን፣ ደግነትን፣ ልባምነትንና ፈሪሐ እግዚአብሔርን ነው፡፡”
አንድ ለአንድ መወሰን ጥሩ ነው በሚል ብቻ ማግባት የለበትም፡፡ ይህ በራሱ መልካም ቢኾንም በውስጡ ከዝሙት ተጠብቆ ጽድቅን ለመፈጸም ካልኾነ አንድ ለአንድ መወሰን ብቻውን የትዳር ተቀዳሚ ዓላማ አይደለምና፡፡ ከአሕዛብም የጽድቅ አሳብ ሳይኖራቸው አንድ ለአንድ የሚወሰኑ አሉና፡፡
ዕድሜዬ እንዳያልፍ ብሎም ኾነ ሰው አግባ ብሎ አስጨንቆት ማግባት የለበትም፡፡ ትዳር ከ “ለምን አታገባም?” ጭቅጭቅ ለማምለጥ የተሰጠ አይደለምና፡፡
“መልኳን ወደድኳት” ብሎ ማግባት አይገባም፡፡ ውበት ባይጠላም እርሱ ግን የትዳር ዓላማ አይደለምና፡፡ ይህን አድንቆ ወደ ትዳር ከገባ ያ የማረከው ውበት ከሃያ ወይም ከሠላሳ ቀናት በኋላ አይማርከውምና፤ ይለምደዋልና፡፡
ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
(ኦርቶዶክሳዊ ቤተሰብ መጽሐፍ በገብረ እግዚአብሔር ኪደ)

"ይህቺ ጥፊ የኔ ናት"
መነኮስ አባ አርሳንዮስ በገባበት ገዳም ዉስጥ፣ እግዚአብሔርን
እያገለገለ ሲኖር አንድ ቀን ከገዳሙ ሕግ ዉጭ የሆነ ነገር
ይፈጽማል፡፡ ጥፋቱ ከገዳሙ አበምኔት ይደርስና አበምኔቱ አስበዉ
ብገስጸዉ ያፍራል፣ ዝም ብል ጥፋቱ ጥፋት ሳይመስለዉ ሊቀር ነዉ
አሉና፡፡ የሱን ረድዕ ጠርተዉ እንዲህ አሉት፡፡ "አርሳንዮስ ያጠፋዉን
ጥፋት እኔ እያየሁህ በእርሱ ፊት አንተ አጥፋ ከዛ በጥፊ
እመታሃለሁ፡፡ ያኔ እርሱ በአንተ ጥፊ ይማራል አሉት፡፡"
እንደተመካከሩት በአርሳንዮስ ፊት ረድኡ የእርሱን ጥፋት አጠፋ
አበምኔቱም ተቆጥተዉ በጥፊ መቱት በዚህ ጊዜ ነገሩን የተከታተለዉ
አርሳንዮስም "ይህች ጥፊ የኔ ናት" ብሎ ተናገረ፡፡
እግዚአብሔር እኛን ባጠፋነዉ ቅጣት የግድ እስከሚቀጣን ቁጭ
ብለን መጠበቅ የለብንም ፣ከሌላዉ ጥፋት፣ ከሌላዉ ቅጣት መማር
አለብን፡፡ ከሌላዉ ጥፋት መማር ትልቅ ዕዉቀት፣ ታላቅ ማስተዋል
ነዉ፡፡ አርሳንዮስ ጓደኛዉ በጥፊ ሲመታ፣ ይች ጥፊ የኔ ናት አለ እንጂ
ባጠፋዉ ጥፋት ነዉ የተቀጣዉ ብሎ አልፈረደበትም፡፡ እኛም ቁጣ፣
መቅሰፍት፣ እኛ ጋር እስኪመጣ መጠበቅ የለብንም ከጓደኞቻችን
ከጎረቤቶቻችን በሌላም ሀገር ከምናየዉ ከምንሰማዉ ተምረን ንስሓ
መግባት አለብን ጾም ማለትም ይህ ነዉ፡፡ ንስሐ የምንገባዉም
ኃጢአታችንን ስናስተዉል ነዉ፡፡ ማስተዋል ከሌለን ኃጢአቱን እንደ
ጽድቅ ቆጥረን ለንስሐ አንበቃም፡፡
ማስተዋልን ገንዘብ ያደረገ ምዕመን በሌላ ላይ የተደረገ ቅጣት
በርሱ ላይ እንደመጣ ይጠነቀቃል፡፡ እንደ ርግብ የዋህ እንደ እባብ
ብልህ በመሆን የነገሮችን ሁኔታ በማስተዋል ይከታተላል፡፡ ከሰብአ
ትካት ከሰዶም ይማራል ሎጥ የዳነበትን መንገድ ይከተላል ቃሉን
በመስማት በኖህ መርከብ በተመሰለች ቅድስት ቤተክርስቲያን
ይገኛል እራሱን በንስሐ በሥጋ ወደሙ በጸሎት በእግዚአብሔር
ቸርነት ከሚመጣዉ መቅሰፍት ያድናል፡፡
የአባቶቻችን በረከታቸው ይደርብን አሜን፡፡
⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅⛅

🌻🌻🌻🌻🌻
ምጽዋት
የማትፈልገውን ሳይሆን ለአንተ ምርጥ የምትለውን መስጠት ልመድ፡፡ የአገልግሎት ዘመኑን የጨረሰ ልብስ፣ ለመመገብ አስቸጋሪ የሆነ፣ የሻገተ ወይንም የደረቀ ምግብ መስጠት የተለመደ በሆነበት ዘመን ላይ ስላለህ የምታደርገውን ሁሉ ተጠንቅቀህ አድርግ፡፡ አንተ የማትለብሰው ስለማይለበስልህ ነው፡፡ የማትበላው በጤናህ ላይ ችግር ስለሚያስከትልብህ ነው፡፡ ታድያ ወንድምህስ? የምትሰጠው ለሕመም የሚዳርገውን ነው? መሆን የለበትም፡፡ ማስቀመጫ እንዳጣ መጣያ አታርገው ይልቁንም ለወንድምህ ከምትበላው አካፍለው፡፡ ከምትለብሳቸው ሁለት ልብሶች አንዱን ስጠው፡፡ የሚጎዳውን ብዙ ነገር ከምትሰጠው የሚጠቅም ትንሽ ነገር ስጠው፡፡ ለአንተ የምትመኘውን ጥራት ለወንድምህም አድርግ፡፡ “ለእኔ እንዳደረጋችሁት ነው” ያለውን የእግዚአብሔር ቃል መለስ ብለህ አስብና፣ የምትሰጠውን ጎጂ ነገር ለክርስቶስ እንደምትሰጠው ተረዳ፡፡ ከዚሁ ጋር አቤልና ቃየል ለእግዚአብሔር ያቀረቡት መሥዋዕት እንዴት እንደነበረ አስብ፡፡ “አቤልም ደግሞ ከበጎቹ በኩራትን ከስቡ አቀረበ፡፡ እግዚአብሔርም ወደ አቤልና ወደ መሥዋዕቱ ተመለከተ፡፡” (ዘፍ 4፣4) ለምን መረጠለት? ብትል ፣ ካለው ሁሉ መርጦ የተሻለውን ስላቀረበ ነው፡፡ በሐዋርያት ሥራ 4፣34-35 ላይ ሠፍሮ የሚገኘውን የሐዋርያቱ ሕይወት ምን
ይመስል እንደነበረ የሚናገረውን ቃል አስተውለህ አንብበውና የአንተ ምጽዋት የአንተ ሥጦታ የትኛው ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ራስህን ጠይቅ፡፡ ክብርን ለመፈለግ አትስጥ በአንደበትህም ይሁን በልብህ፣ በስሜትህም ይሁን በሃሳብህ የራስህ ነገር ኖሮህ እንደሰጠህ አስበህ አትኩራራ፡፡ ለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ የተናገረውን እንደ ትልቅ ማስረጃ ተጠቀም፡፡ “አንተ እድትበልጥ ማን አድርጎሃል? ያልተቀበልኸውስ ምን አለህ? የተቀበልክ ከሆነ ግን እንዳልተቀበልክ የምትመካ ስለምንድር ነው?” (1 ቆሮ 4፣7) ስለዚህ ስጦታ ሁሉ ከእግዚአብሔር ተቀብለን የምንሠጠው እንጂ የራሳችን እንደሆነ በከንቱ የምንመካበት አይደለም፡፡
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊ
+++
ምንጭ:- መቅረዝ ዘተዋሕዶ
@menfeswimeker
ለ አስተያየት @menfesawimekerbot

HTML Embed Code: