Create: Update:
ግንቦት ፳፯ /27/
@Mekre_Abew_Orthodox
በዚችም ዕለት የማርያና የማርታ ወንድም ጻድቅ አልዓዛር አረፈ። ይህንንም ጻድቅ ሰው በአራተኛ ቀን ከመቃብር ከአስነሣው በኋላ በዚሁ ሳምንት ውስጥ መድኃኒታችን መከራ ተቀብሎ ተሰቅሎ ሞተ። ከትንሣኤውም በኋላ አልዓዛር ከሐዋርያት ጋራ አንድ ሆነ።
አጽናኝ መንፈስ ቅዱስም በወረደ ጊዜ ከሐዋርያት ጋራ ጸጋውን ተቀበለ። ሐዋርያትም በቆጵሮስ አገር ላይ በአንብሮተ እድ ኤጲስቆጶስነት ሾሙት። መንጋውንም በመልካም አጠባበቅ ጠበቀ። በሹመቱም አርባ ዓመት ኑሮ በሰላም በፍቅር አረፈ።
ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን እኛንም በዚህ ጻድቅ አባት ጸሎት ይማረን በረከቱም ከእኛ ጋራ ትኑር ለዘላለሙ አሜን።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ምንጭ:- መጽሐፈ ስንክሳር
>>Click here to continue<<
መንፈሳዊ ኪነ-ጥበብ💒
