TG Telegram Group Link
Channel: ✝ መምህረ ዜማ ማኅሌታይ ያሬድ✝ ‍
Back to Bottom
🔊 ♡ ㅤ ❍ㅤ YAHWEH PROOTION ♡ ㅤ ❍ㅤ
~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~~
♡ ㅤ ❍ㅤ YAHWEH PROOTION ♡ ㅤ ❍ እንደሚታወቀው በርከት ያሉ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስትያን ሥርዓትㅤ ጠብቀው መንፈሳዊ ትምህርትን ለምእመናን የሚያድርሱ ቻናሎች መስግቦ እያሳደገ ይገኛል። 500 members ካለው 5ሺ members ያሉ በጣም ብዙ ናቸው ። በአሁኑ ሰዓት ደግሞ #ከ5ሺ እስከ 50ሺ members የያዙ እና ከዛ በላይ አባሎች የያዙ ቻናሎችን እያሳደግን እንገኛለን እና ያለን ቦታ የተወሰነ ሰለሆነ ሁላችሁም የቻናል ባሌቤቶች (Owners ) በተሎ እንድታስመዘግቡ በትሕትና እናሳውቃለን ።
በፍጥነት ለማሳደግ አሁኑኑ ያስመዝግቡ
= @YEmeAmlak_DnglMaryam_Ljoch_Bot
= ♡@Azaheill
Tel :-+251943686155 📞 ያገኙናል !!
Forwarded from ያሬዳውያን (Aron)
🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵🏵
ሥርዓተ ማኅሌት ዘየካቲት ኪዳነ ምሕረት
🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊🕊
የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፣ በአሐቲ ቃል።
@EOTCmahlet
መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤ ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣህል፤ እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፣ ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤ ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ዚቅ
ወታስተሥርዪ ኃጢአተ ሕዝብኪ ተበውሐ ለኪ፤ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ፤ ከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውልደ ስብእ፤ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለኪ ይደሉ ከመ ትኩኒ መድኃኒቶሙ ለመሐይምናን ሕዝብኪ፤ ኦ መድኃኒተ ኵሉ ዓለም፤ ወልድኪ ሣህሎ ይክፍለነ ሰአሊ ለነ ቅድስት።
@EOTCmahlet
ዘጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤ ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤ መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤ ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤ እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ፤ እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን፤ ዘእንበለ ትብጻሕ ግብተ አሠንዶ ፍኖተ፤ ይፈኑ ለክሙ እመቅደሱ ረድኤተ፤ መድኃኒተ መቤዛዊተ እሞ ቅድስተ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
ቅንዑ ለእንተ ተዓቢ ጸጋ መድኃኒት ለነፍስ ወሥጋ ማርያም ድንግል/፪/
እስመ ርቱዓት ፍናዊሃ ጻድቃን የሐውርዎን ወኃጥአን ይስዕንዎን/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘአስተማሰልዎ በኮከብ፤ ሶበ ብርሃኖ ተከድኑ ጽልሙታነ ራእይ ሕዝብ፤ ኪዳነ አምላክ ማርያም ወተስፋ መድኃኒት ዘዐርብ፤ ተናዘዘ ብኪ አኮኑ ኅሊና ቀዳማይ አብ፤ አመ እምገነቱ ተሰደ በኀዘን ዕፁብ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም፤ አመ ይሰደድ እምገነት።
@EOTCmahlet
ወረብ
አንቲ ውእቱ ተስፋሁ ለአዳም አንቲ ውእቱ/፪/
አመ ይሰደድ እምገነት/፬/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለአዕዛንኪ እለ ተበስራ ኪዳነ፤ እምአፈ ፈጣሪ ወልድኪ ዘባሕርየኪ ተከድነ፤ አምሕለኪ ማርያም ከመ ኢታርእይኒ ደይነ፤ እንበለ ምግባር ባሕቱ እመ ኢይጸድቅ አነ፤ ቦኑ ለከንቱ ኪዳንኪ ኮነ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ኪዳንኪ ኮነ ለኃጥአን ቤዛነ፤ ኪዳንኪ ኮነ ኪዳንኪ ኮነ፤ ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ።
@EOTCmahlet
ወረብ
ኪዳንኪ ኮነ/፮/
ለኃጥአን ቤዛነ ኪዳንኪ ኮነ/፬/
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለመዛርዕኪ ወለኲርናዕኪ ምፅንጋዕ፤ እለ ሐቀፋሁ ለክርስቶስ ባሕርየ መለኮት ኅቡዕ፤ ማርያም ኅሪት እምነ መላእክት ወሰብእ፤ ተዝካረኪ ለእመ ገብረ በተአምኖ ጽኑዕ፤ በመንግሥት ሰማይ ምስሌኪ ይነግሥ ኃጥእ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
አመ ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን፤ ክፍልኒ ድንግል ዕቁም በየማን፤ ምስለ አባግዕ ቡሩካን።
@EOTCmahlet
ወረብ
ይነግሥ ወልድ በደብረ ጽዮን አመ ይነግሥ ወልድ/፪/
ክፍልኒ ድንግል ዕቁም በየማን/፪/
@EOTCmahlet
ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
መፍትው እንከ ንወድሳ ወንግበር ተዝካራ፤ ለቅድስት ድንግል ዓፀደ ወይን፤ መሶበ ወርቅ እንተ መና።
@EOTCmahlet
መልክዐ ኪዳነ ምሕረት፦
ሰላም ለድንግልናኪ መክብበ ሕዋሳት ሐምስ፤ወለአቊያጽኪ ክልኤ አዕማደ ነባቢት መቅደስ፤ማርያም ታቦት ወጽላተ ኪዳን ሐዲስ፤ቅብዕኒ ርጢነ ጾም እስከ ሰኰና እግር ወርእስ፤እስመ ጾም ትፌውስ ሕማማ ለነፍስ፡፡
@EOTCmahlet
ዚቅ
ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ፤ወታጸምም ኵሎ ፍትወታተ ዘሥጋ፤ ትሜሕሮሙ ለወራዙት ጽሙና፤እስመ ሙሴኒ ጾመ በደብረሲና፡፡
@EOTCmahlet
ወረብ፦
ጾም ትፌውስ ቊስለ ነፍስ ወታጸምም ኵሎ ዘሥጋ ፍትወታ/፪/
ትሜሕሮሙ ጽሙና ጽሙና ለወራዙት/፪/
@EOTCmahlet
መልክአ ኪዳነ ምሕረት
ሰላም ለመልክዕኪ እመልክዐ ሐና ወኤልሳቤጥ፤ ዘብዑድ ስኑ ወልምላሜሁ ፍሉጥ፤ ማርያም ድንግል ድንግልተ፧ አፍአ ወውስጥ፤ ቤዛ ይኩነኒ ኪዳንኪ በገጸ ፈጣሪ ሥሉጥ፤ አመ ወርኀ ነጊድ የኃልቅ ወይጸራዕ ሤጥ።
@EOTCmahlet
ዚቅ
ቃለ እግዚአብሔር እምድንግል አስተርአየ፤ ኤልሳቤጥ ኮነት ዓባየ፤ እስመ ወለደት ነቢየ።
@EOTCmahlet
@EOTCmahlet
ወረብ
እምድንግል አስተርአየ ቃለ ቃለ እግዚአብሔር/፪/
ኤልሳቤጥ ኮነት ዓባየ"እስመ ወለደት ነቢየ"/፪/ /፪/
@EOTCmahlet
አንገርጋሪ
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር፤ ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ፤ አንቲ ምስራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ፤ አማን፤ ኪዳንኪ ኢየኃልቅ።
@EOTCmahlet
አመላለስ
'አማን በአማን'/፪/ ኪዳንኪ 'አማን በአማን'/፪//፩/
ኪዳንኪ ኢየኃልቅ/፬/
@EOTCmahlet
ወረብ
ክነፈ ርግብ በብሩር ዘግቡር ወገበዋቲሃኒ በሐመልማለ ወርቅ/፪/
አንቲ ምሥራቅ ወወልድኪ ፀሐየ ጽድቅ ምሥራቅ ደብረ ሕይወት/፪/
@EOTCmahlet
እስመ ለአለም


  👇👇👇👇👇🇪🇹
     👉@EOTCmahlet👈                 
     👉@EOTCmahlet👈
     👉@EOTCmahlet👈
    🇪🇹👆👆👆👆👆👆🇪🇹

      @EOTCmahlet
    #Join & share
Forwarded from የብርሃን እናት (@with z ፩)
++ ሥርዓተ ማኅሌት ዘመጋቢት መድኃኔዓለም ++

የማንኛውም ወርኃ በዓልና ክብረ በዓል ሥርዓተ ማኅሌት መጀመሪያ "ሥርዓተ ነግሥ"....
ስምዓኒ እግዚኦ ጸሎትየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወይብጻሕ ቅድሜከ ገዓርየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ወኢትሚጥ ገፀከ እምኔየ፤ በዕለተ ምንዳቤየ አጽምእ ዕዝነከ ኀቤየ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ አመ ዕለተ እጼውአከ ፍጡነ ስምዓኒ ሃሌ ሉያ፤ ሃሌ ሉያ ለዓለም ወለዓለመ ዓለም፤ ሃሌ ሉያ ዘውእቱ ብሂል፤ ንወድሶ ለዘሃሎ እግዚአብሔር ልዑል፤ ስቡሕ ወውዱስ ዘሣረረ ኲሎ ዓለመ፤ በአሐቲ ቃል።

+ መልክአ ሥላሴ
ሰላም ለኲልያቲክሙ እለ ዕሩያን በአካል፤
ዓለመክሙ ሥላሴ አመ ሐወጸ በሣሕል፤
እምኔክሙ አሐዱ እግዚአብሔር ቃል፤
ተፈጸመ ተስፋ አበው በማርያም ድንግል፤
ወበቀራንዮ ተተክለ መድኃኒት መስቀል።

+ ዚቅ
ሃሌ ሉያ ለአብ በመስቀሉ አተበነ፤ ሃሌ ሉያ ለወልድ በመስቀሉ ቤዘወነ፤ ሃሌ ሉያ ወለመንፈስ ቅዱስ፤ በመስቀሉ ኮነ ሕይወትነ።

+ ዘመንክር ጣዕሙ
ሰላም ለዝክረ ስምኪ ዘመንክር ጣዕሙ፤
ለወልድኪ አምሳለ ደሙ፤
መሠረተ ሕይወት ማርያም ወጥንተ መድኃኒት ዘእምቀዲሙ፤
ኪያኪ ሠናይተ ዘፈጠረ ለቤዛ ዓለሙ፤
እግዚአብሔር ይትባረክ ወይትአኮት ስሙ።

+ ዚቅ
መድኃኔዓለም ወልድኪ ሥጋ ዚአኪ ዘለብሰ፤
ሐፃውንተ መስቀል ተአገሰ፤
በዓውደ ጲላጦስ ተወቅሰ አማዑትኪ ተካወሰ።

+ መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለዝክረ ስምከ ዘኢረከቡ ተፍጻሚተ፤
መላእክተ ሰማይ ወምድር እለ ለመዱ ስብሐተ፤
መድኃኔዓለም ተወከፍ እንተ አቅረብኩ ንስቲተ፤
ዘሰተይከ በእንቲአነ ከርቤ ወሐሞተ፤
በሞተ ዚአከ ከመ ትቅትል ሞተ።

+ ዚቅ
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ፤
ወአስተዩኒ ብሂዓ ለጽምዕየ፤
ወወደዩ ሐሞተ ውስተ መብልዕየ።

ዓዲ (ወይም)
ዚቅ
ወአቅደምከ ጸግዎ መንፈሰከ ቅዱሰ ለሥርየተ ኃጢዓት፤ አክሊል ዘሦክ አስተቀጸሉከ ዘበሰማያት ለነ አክሊለ ጽድቅ አስተዳሎከ፤ ሰቀሉከ ዲበ ዕፅ፤ ብሂዓ ዘምስለ ሐሞት አስተዩከ፤ ከመ ለነ ታስትየነ ወይነ ትፍሥሕት ወሐሤት፤ ረገዙከ በኲናት ወተርኅወ ገቦከ፤ ከመ ለነ ተሀበነ ሥጋከ ቅዱሰ ወደምከ ክቡረ፤ ከመ ትጸግወነ።

+ ወረብ
ወአቅደምከ 'ጸግዎ'/፪/ መንፈሰከ/፪/
አክሊለ ጽድቅ አስተዳሎከ በሰማያት አክሊለ ጽድቅ/፪/

+ መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለጒርዔከ ክቡር ወልዑል፤
ወለክሣድከ ዓዲ ዘሰሐብዎ በሐብል፤
መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቀራንዮ ስቁል፤
በለኒ መሐርኩከ በእንተ ማርያም ድንግል፤
እስመ ኄር አልቦ እንበሌከ ቃል።

+ ወረብ
'በለኒ መሐርኩከ'/፪/ በእንተ ማርያም ድንግል/፪/
እስመ ኄር አልቦ እንበሌከ ዘይሜሕር ቃል መድኃኔዓለም /፪/

+ ዚቅ
በእንተ ማርያም ወላዲትከ፤
ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ፤
ወበእንተ ኲሎሙ ቅዱሳኒከ፤
ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ፤
ኢታስተኃፍረነ እግዚኦ በቅድሜከ።

+ ወረብ
በእንተ ማርያም ወላዲትከ ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ/፪/
ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ/፪/

ዓዲ (ወይም)
+ ዚቅ
በአማን ቃልከ አዳም፤ ዘተሰቀልከ በእንተ ኃጥዓን ከመ ትቤዙ ነፍሰ ጻድቃን፤ በአማን ቃልከ አዳም፤ በአማን ቃልከ አዳም።

+ መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለልብከ እግዚአብሔር ናዝራዊ፤
ነቢይ ወመንፈሳዊ፤
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ሕፃን ወአረጋዊ፤
እፎ ቀሰፉከ ካህናተ ይሁዳ ወሌዊ፤
በዐውደ ጲላጦስ መስፍን ከመ ገብር ዓላዊ።

+ ዚቅ
ወጸሐፈ ጲላጦስ መጽሐፈ፤ ወይብል መጽሐፉ ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ።

+ ወረብ
ወጸሐፈ መጽሐፈ ጲላጦስ ወይብል መጽሐፉ ጲላጦስ ዘጸሐፈ/፪/
ኢየሱስ ናዝራዊ ንጉሥ ናዝራዊ ንጉሠ አይሁድ/፪/

+ መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለጸዓተ ነፍስከ አመ ዲበ መስቀል ቆመ፤
ወለበድነ ሥጋከ ምዑዝ እንተ ያጥዒ ሕሙመ፤
መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከመ ትቤዙ ዓለመ፤
አሜሃ እግዚእየ ፀሐይ ጸልመ፤
ወወርኅኒ ተመሰለ ደመ።

+ ዚቅ
ምድር አድለቅለቀት ወሰማይ ተሀውከ ሶበ ትወጽእ መንፈሱ ለኢየሱስ።

+ ወረብ
ምድር አድለቅለቀት ወሰማይ ተሐውከ/፪/
ሶበ ትወጽእ መንፈሱ ለኢየሱስ/፪/

ዓዲ (ወይም)
+ ዚቅ
ሶበ ሰቀልዎ ሶበ ሰቀልዎ፤ ሶበ ሰቀልዎ ለእግዚእነ ፀሐይ ጸልመ ወወርኅ ደመ ኮነ፤ ዬ ዬ ዬ፤ አድለቅለቀት ምድር ወተከሥቱ መቃብራት።

+ መልክአ መድኃኔዓለም
ሰላም ለግንዘተ ሥጋከ ዘመዓዛሁ ጽጌረዳ፤
ወለመቃብሪከ ዘኮነ ለኢየሩሳሌም በዓውዳ፤
መድኃኔዓለም ክርስቶስ በቅንዓተ ሰይጣን ዘይሁዳ፤
ሞተ ወተቀብረ በመቃብረ ሐዲስ እንግዳ፤ ኀበ
ኢተቀብሩ ለሔዋን ውሉዳ።

+ ዚቅ
አውረድዎ እምዕፅ ዕደው ጻድቃን፤ ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውስ ወልብሰ ገርዜን ንጹሕ ለግንዘተ ሥጋሁ።

+ ወረብ
'አውረድዎ'/፫/ እምዕፅ/፬/
ወአምጽኡ አፈዋተ ከርቤ ሕውስ/፪/

+ ምልጣን፦
መርሕ በፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን፤ ዝንቱ ውእቱ መስቀል፤ ለአዳም ዘአግብዖ ውስተ ገነት፤ ወለፈያታዊ ኃረዮ በቅጽበት፤ መድኃኒት ዕፀ ሕይወት፤ ዝንቱ ውእቱ መስቀል።

+ አመላለስ፦
መድኃኒት ዕፀ ሕይወት፤
ዝንቱ ውእቱ መስቀል

+ ወረብ፦
ሃሌሉያ መርሕ በፍኖት ሞገሶሙ ለጻድቃን ሞገሶሙ/፪
ዝንቱ ውእቱ መስቀል ለአዳም ዘአግብዖ ውስተ ገነት/፪

+ እስመ ለዓለም
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት፤ በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ዲቤሁ ቃለአብ፤ ወበስምከ ናኃሥሮሙ ለእለ ቆሙ ላዕሌነ፤ ወካዕበ ይቤ ወወሃብኮሙ ትዕምርተ ለእለ ይፈርሁከ፤ ከመ ያምሥጡ እምገጸ ቅስት፤ ወይድኃኑ ፍቁራኒከ፤ ወንሕነኒ ንትፈሣሕ ዮም ወንግበር በዓለ፤ በዛቲ ዕለት በዓለ እግዚእነ።

+ ወረብ፦
ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ብከ ንወግዖሙ ለኲሎሙ ፀርነ ይቤ ዳዊት በመንፈሰ ትንቢት/ ፪/
በእንተ ዕፀ መስቀል ዘተሰቅለ ተሰቅለ ዲቤሁ ቃለአብ/፪/

© ያሬዳውያን

@etsemeaza
Forwarded from የብርሃን እናት (@with z ፩)
+ ያልተናገረችው አህያ +

ነቢዩ በለዓም በአህያ ላይ ተጭኖ ሲሔድ አህያው የእግዚአብሔርን መልአክ አይታ ወደ ቅጥሩ ተጠጋች፡፡ በለዓም ተናድዶ መታት፡፡ ጥቂት እንደተጓዙ አህያይቱ ድጋሚ መልአኩን አየች፡፡ ከበለዓም በታችም ተኛች፡፡ በለዓም ተበሳጭቶ አህያይቱን በበትሩ ደበደባት፡፡

እግዚአብሔርም የአህያይቱን አፍ ከፈተ ፦ ሦስት ጊዜ የመታኸኝ ምን አድርጌብህ ነው? አለችው፡፡ በለዓምም አህያይቱን ፦ ስላላገጥሽብኝ ነው ሰይፍ በእጄ ቢኖር ኖሮ እገድልሽ ነበር አላት፡፡ አህያይቱም በለዓምን ፦ ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን? አለችው። እርሱም፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም አላት’’ /ዘኁ 22፡27-30/

ይህንን ታሪክ ባነበብሁ ቁጥር ሁልጊዜም የሚያስደንቀኝ የአህያይቱ መናገር ሳይሆን የበለዓም መልስ መሥጠት ነው፡፡

እግዚአብሔር ያሳያችሁ፡፡ በለዓም መልስ የሠጠው ከሎሌዎቹ ለአንዱ አይደለም፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ ‘ቃል የሌለው አህያ በሰው ቃል ተናግሮ የነቢዩን ዕብደት አገደ’ /2ጴጥ 2፡16/ እንዳለው አህያ ስትናገር ታይቶ ተሰምቶ አያውቅም፡፡

መንገድ ላይ እየሔድህ ከሰፈርህ ውሾች አንዱ ‘እንዴት አደርህ?’ ቢልህ እግዚአብሔር ይመስገን ትላለህ? እርግጠኛ ነኝ ራስህን ስተህ ልትወድቅ ትችላለህ፡፡ ከተረጋጋህ በኋላም አእምሮህ ተነክቶ ‘ውሻው ተናገረ እኮ’ እያልክ ትኖራለህ፡፡

በለዓም ግን ተናግራ የማታውቀው አህያ አፍ አውጥታ ስትናገር ሲያይ ትንሽ ደንገጥ እንኳን አላለም፡፡ ሌላ ቀን ሲያናግራት እንደኖረ ሰው ኮስተር ብሎ መመላለስ ጀመረ፡፡ አህያዋ አብረው ስለኖሩበት ዘመን የሥራ ልምድዋና የሥራ አፈጻጸምዋ ‘ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን?’ ብላ ስትነግረው በለዓም ሠራተኛውን እንደሚያናግር አለቃ ተረጋግቶ ያለ ምንም መደንገጥ ራሱን እየነቀነቀ ከሰማ በኋላ ፦ እንዲህ አላደረግሽብኝም ብሎ ግምገማዋን ተቀብሎ ኂሱን ዋጠ፡፡

የበለዓምን ነገር እንተወውና የተናጋሪዋ አህያውንም ነገር እንርሳውና አንዲት መናገር ሲኖርባት ያልተናገረች አህያ ነገር ግን የበለጠ ይቆጫል፡፡

ይህች አህያ በሆሳዕና ዕለት ጌታችን የተጫነባት አህያ ናት፡፡ ይህች አህያ እንደ በለዓም አህያ ጌታዋ በበትሩ የሚደበድባት ሳይሆን ‘ለጌታ ያስፈልጉታል’ ብሎ ከነ ልጅዋ ያስፈታት አህያ ናት፡፡ የእርስዋ ጌታ በተኛችበት በበትር የሚቀጠቅጣት ሳትሆን እግርዋ መሬት እንዳይረግጥ ጌታዋ ያስነጠፈላት አህያ ናት፡፡

የእርስዋ ጌታ እንደ በለዓም መልአክ መንገድ የሚዘጋበት ሳይሆን መላእክት በፊቱ እየሰገዱ እንደ ሻሽ የሚነጠፉለት ነው፡፡ የበለዓምን አህያ አንደበት የከፈተ ጌታ ምነው የዚህችን አህያ አንደበት በከፈተው ኖሮ! ስንት ነገር በተናገረች ነበር?

የሆሳዕናዋ አህያ አንደበትዋ ቢከፈት እንደ በለዓም አህያ ጌታዋን ከማማረር ይልቅ ከሕዝቡ ጋር አብራ ትዘምር ነበር፡፡ እንደ በለዓም አህያ ‘ብዙ ዘመን ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ የምትቀመጥብኝ አህያህ አይደለሁምን? በውኑ እንዲህ አደርግ ዘንድ ልማዴ ነበረን?’ በማለት ፋንታ ‘ከብዙ ዘመን ጀምሮ ሰው ሲቀመጥብኝ የኖርሁ አህያ ነበርሁ፡፡ በውኑ ንጉሥን እሸከም ዘንድ ልማዴ ነበርን?’ ብላ ታመሰግን ነበር፡፡

ጌታ ሆይ እኛስ ስንት በለዓሞችን ተሸክመን ኖርን? ስንት በለዓሞች በተሸከምናቸው በታግስናቸው ልክ በማመስገን ፈንታ በበትር ደበደቡን? በብሶት በምሬት አፍ አውጥተን ስንናገር እንኳን ትንሽ አይደንቃቸውም፡፡

አንተው መጥተህ ገላግለን፡፡ ለምስጋና ቢስ በለዓሞች ‘ለጌታ ያስፈልጉታል’ ብለህ እንዲፈቱን ንገራቸው፡፡ አንተው ዙፋንህ አድርገን፡፡ አንተን መሸከም አይከብደንም፡፡ አንተን የያዝን እንደሆን መንገዳችን በዝማሬ የተሞላ ይሆናል፡፡ የሚንቁን ሁሉ አንተን ብለው ያከብሩናል፡፡ ምንም እንኳን አንተን ሊይዝህ የሚችል ባይኖርም በደስታ እንሸከምሃለን፡፡

ራስህ እንዲህ ብለሃልና ፦

‘እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ ወደ እኔ ኑ
እኔም አሳርፋችኋለሁ ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ
ከእኔም ተማሩ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና
ለነፍሳችሁም ዕረፍትን ታገኛላችሁ
ቀንበሬ ልዝብ ሸክሜም ቀሊል ነውና’ /ማቴ 11፡28/

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
HTML Embed Code:
2025/06/27 21:54:10
Back to Top