TG Telegram Group Link
Channel: መሐርኒ ድንግል
Back to Bottom
መሐርኒ ድንግል

የወር አበባ ሴት ልጅ ፈጣሪ ለመደበላት ዕጥፍ የሕይወት ሚና ማለትም ሚስት እና እናት ለመሆን መድረሷን የሚያመለክት በመሆኑ ሳትከፍ በጸጋ ትቀበለው ዘንድ ይገባታል ። (ሕይወተ ወራዙት)

https://hottg.com/mehereni_dngl
ስጋችን ምግብ ሲያጣ እደ ሚደክም ሁሉ
ነፍስም ምግቡን የእግዚአብሔር ቃል ስታጣ ትደክማለች

ሰዉ ሀጢአት ጨርሶ ሲጠላ ሀጢአትንም ሁሉ ሲተዉና ከልቦናዉ ፈፅሞ ሲያጠፋዉ የልብ ንፅህና ያገኛል

በንሰሀ ሕይወት ለመኖር የምንሻ ከሆነ ለወደቅንበት ሀጢአት ምክንያት መደርደር እና ለራሳችን ይቅርታን ለመስጠት መሞከር የለብን

ጨዋ ሰው በሌሎች ሰወች መጐሳቆል ላይ የራሱን ምቾት አይገነባም እርሱ የሌሎችን ሰዎች ምቾት ለማደላደል የራሱን ምቾት ይረሳል። "ብጹዕ አቡነ ሺኖዳ"
ፆመ ሁዳዴ (የዓብይ ፆም) የመጀመሪያ ሳምንት ዘወረደ በማለት ነገ በይፋ ይጀምራል።

ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች እንኳን አደረሳቹ መልካም የፆም ወቅት እንዲሆንላቹ ቻናላችን ከልብ ይመኛል !

@mehereni_dngl
Forwarded from 👑 All wallpaper 👑
የተለያዩ ለኳስ ወይም ወይም የተለያዩ wallpaper & profile picture ከፈለጉ
ከዚህ በታች ሊንኩን ተጭነው ማግኘት ይችላሉ !
👇👇👇👇👇👇
@all_wallpaper_1
"ንጽሕት በኲሉ"

ዲያቆን ሚክያስ አስረስ

ከሰው ወገን እንደ እመቤታችን ማን አለ? እንደ እርሷ ለእግዚአብሔር የቀረበ፤ የእርሷን ያህል ዘመድ የኾነውስ ማን አለ? ልዑል እግዚአብሔር ሰውን ያዘዘውን ሁሉ ሆና እና ፈጽማ የተገኘች እርሷን ማን ይመስላታል። ቤተ ክርስቲያን፣ ቅድስና፣ ንጽሕና፣ ማመን፣ መታዘዝ፣ የዋህነት በምልዓት በፍጥረታዊው ሰው ይገለጹ ቢባል እመቤታችን ናት። ሌላ ሰው ቢቀደስ የእርሷን ያህል አይቀደስም፤ ቢነጻ የእርሷን ያህል አይነጻም። ንጽሕናዋን አይቶ አምላክ ከእርሷ ሊወለድ በጥበቡ ወደ እርሷ መጣ። የሰው ዘር እርሷን በድንግልና ንጽሕት አድርጎ ለእግዚአብሔር አቀረበ፤ እግዚአብሔርም እርሷን በድንግልና እናቱ አድርጎ ለሰውም እናት ትሆን ዘንድ ሰጣት። ቀድሞ ለወለዷት ጸጋ ሆና የተሰጠች፤ ለእግዚአብሔር እናት ሆና ከቀረበች በኋላ ለሰው ሁሉ ጸጋ ሆና ዳግም ተሰጠች። ለእርሱ በንጽሕናዋ ምክንያት እናት ሆነችው፤ ለእኛ በርኅራኄዋ እናት ሆነችን። እርሱን መውለዷ ታላቅ ተአምር ሆነ። ልጇን በእውነት የሚወደውን በደግነቷ ትጠብቀዋለች። ታንጻን፤ ታጽናን፤ ትውደደን፤ ትጠብቀንም። አሜን።


#መሐርኒ_ድንግል
@mehereni_dngl
ሰው በሰውነቱ መኖር እንዳይችል እንስሳዊነት ማንነቱን የሸፈነበት ዘመን ።

እንደተፈጠርንበት እንኖር ዘንድ ማስተዋል ያድለን ፈጣሪ ። !!! 🙏

#ኦርቶዶክሳዊ #አእምሮ
#ለሰይጣን_ጊዜ_የለኝም

መምህሩ ተማሪዎችን ሊፈትን በአንድ ሰዓት ውስጥ የሚመለሱ ሁለት ጥያቄዎችን አዘጋጀ። ተማሪዎች ራሳቸውን አዘጋጅተው ወደ ፈተና ክፍል ገበተው ወንበር ወንበራቸውን ይዘው ይጠብቃሉ። መምህሩ የፈተና ወረቀቱን ይዞ ገባ። የፈተናውን መመሪያ ተናግሮ የፈተና ወረቀቱን አደለና ሰዓት ይዞ "መጀመር ትችላላችሁ" አላቸው።

የመጀመሪያው ጥያቄ ስለ እግዚአብሔር የምታውቀውን ጻፍ የሚል ነው። ሁለተኛው ጥያቄ ደግሞ ስለ ሰይጣን የምታውቀውን ጻፍ ይላል፡፡ "ለአንዱ ጥያቄ 30 ደቂቃ ነው የተሰጠው ማለት ነው" ብለው ሰዓት ሳያልቅባቸው ሁለቱንም ጥያቄዎች ለመጨረስ ተሎ ተሎ ይጽፋሉ። ፈተና ከተጀመረ 30 ደቂቃ መሙላቱ ሰዓት ያዩ ተማሪዎች ከአንደኛው ጥያቄ ወደ ሁለተኛው አልፈው መስራት ጀምረዋል፡፡ በአእምሮአቸው የመጣላቸውን ሐሳብ በቻሉት ፍጥነት ይጽፋሉ፡፡ መምህሩም ሁሉም ተማሪ የየራሱ መስራቱን እየዞረ ይከታተላል።

"ለማጠናቀቅ አስር ደቂቃ ይቀራችኋል" አለ መምህሩ። መልሰን ጨርሰናል ብለው ያሰቡ ተማሪዎች ግማሾቹ ፈተና ወረቀቱን ለመምህሩ ሰጥተው ሲወጡ፥ ሌሎቹም የመለሱትን ደግመው ያነባሉ፡፡ ያልጨረሱም የቀረችውን ደቂቃ ለመጠቀም ይጣደፋሉ። ከአስር ደቂቃ በኋላ "ሰዓት አልቋል ሁላችሁም መስራት አቁሙ" አለ መምህሩ፡፡ እየዞረም ፈተና ወረቀቱን መሰብሰብ ጀመረ፡፡ አንድ ተማሪ ጋር ሲደርስ ግን አሁንም መልስ እየጻፈ ያገኘውና "ሰዓት አልቋል ሲባል አትሰማም እንዴ?" ብሎ ወረቁትን ተቀበለው፡፡

ሁሉም ተማሪዎች ለሁለቱም ጥያቄ የሚያውቁትን የመለሱ ሲሆን አንዱ ተማሪ ግን ለጥያቄ ቍጥር አንድ (ስለ እግዚአብሔር የምታውቁትን ጻፉ ለሚለው) ብቻ ነው መልስ የሰጠው። መምህሩ በዚህ ተማሪ መልስ ተገርሞ "ለምንድ ነው ለሁለቱንም ጥያቄዎች መልስ ያልጻፍከው?" ብሎ ጠየቀው። እርሱም "#ለሰይጣን_ጊዜ_የለኝም" ስለ እግዚአብሔር ራሱ የማያልቅ ቢሆን እኮ ነው የተሰጠን ሰዓት አልቆ ገና እየጻፍኩ ያስቆምከኝ" አለው ይባላል፡፡

እውነት ነው ነገረ እግዚአብሔር ቢጽፉት፣ ቢናገሩት፣ ቢሰሙትና ቢያዜሙት የማያልቅና የማይሰለች ጥልቅ ምሥጢር ነው። የፈለግነው ያህል ጊዜ ብንሰጠው እንኳን በጅምር እያለን ጊዜው ያልቃል። በቃሉ ፍቅር፥ በምሥጢሩ ተመስጦ ውስጥ ሆነን ወደማያልፈው ዓለም እንሻገራለን፡፡

ይህንን ገንዘብ ለማድረግ ግን ለሰይጣንና ለጉዳዮቹ የሚሆን ጊዜ የለኝም ማለት ይገባል፡፡ ከጊዜ ውጭ የሚሰራ ነገር የለምና ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን ከኃጢአት ሁሉ መራቃችን አይደል? ለሰይጣን ጊዜ ላለመስጠት ደግሞ ከእርሱ ጋር መጣላት ነው። መቼም ሰው ለጠላው ነገር የሚሆን ጊዜ አይኖረውም። ምንም ስራ ባይኖረውም እንኳ ከጠላው ጋር ላለመገናኘት ምክንያት ፈጥሮ ይርቅ የለ? ስለዚህ ለሰይጣን ጊዜ እንዳይኖርህ ከእርሱ ጋር ተጣላ። የሚገርመው ከሰይጣን ጋር ስትጣላ ደግሞ ከሰው እና ከእግዚአብሔር ጋር በፍቅር መኖር ትችላለህ፡፡ ከ24ቱ ሰዓት ለሰይጣን የሚሆን ጊዜ ከሌለን መቼም ቢሆን ኃጢአት ሊያሰራን የሚችልበት ዕድል ወይም አጋጣሚ አይኖርም። የተሰጠን ጊዜ ለሰጪው አምላክ መልሰን እንሰጠው ዘንድ ማስተዋሉን ያድለን።

@MEHERENI_DNGL
ሆሳዕና ለዳዊት ልጅ በጌታ ስም የሚመጣ የተባረከ ነው ፤ ሆሳዕና በአርያም እያሉ ይጬኹ ነበር ፦ ማቴ 21 ÷ 9
    
ሆሳዕና ቃሉ ከሁለት አረማይክ ቃል የወጣ ሲሆን ትርጉሙም "እባክህ እርዳ አሁን አድን" ማለት ነው።

ለመላው ለክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለሆሳዕና በአል በሰላም አደረሳችሁ።

መሐርኒ ድንግል
@mehereni_dngl
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
መሐርኒ ድንግል

ቲክቶክ ቻናላችን ነው
follow & share
👇👇👇👇👇👇👇👇👇
http://tiktok.com/@mehereni_dngl
http://tiktok.com/@mehereni_dngl
http://tiktok.com/@mehereni_dngl
#በእንተ_ጸሎት_ሐሙስ

"ተራሮችን በኃይሉ የሚያስታጥቃቸው ለማገልገል ማበሻ ጨርቅ ታጠቀ፡፡ የባሕርን ውኃ እንደ አቁማዳ የሚሰበስበው በቀላያትም መዝገቦች የሚሾማቸው ርሱ ከወዳጁ ከአልዓዛር ቤት የውኃ ማድጋ አንሥቶ እግሮችን ለማጠብ ያገለግልባት ዘንድ ወደ  ኩስኩስት አፈሰሰ፡፡ እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን በሚታጠቡበት ገንዘብ የናስ ኩስኩስት ሠርቶ በደብተራ ኦሪት ደጃፍ እንዲያኖራት ሙሴን ያዘዘው ውኃውን በኩስኩስት ሞልቶ የደቀ መዛሙርቱን እግር ሊያጥብ ዠመረ፡፡ የተረከዞቻቸውንም እድፍ በታጠቀው ማበሻ ጨርቅ አሸ፡፡"  (አባ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ)

"በወገቡ የታጠቀውን ማድረቂያ አይተው መላእክት አደነቁ፤ ስሙ ከፀሓይና ከጨረቃ በፊት የነበረ ርሱ አገልጋይ ኾነ፤ ሕያው ጌታን ሱራፌል ያመሰግኑታል፤ ቦታውን ግን አያውቁም፤ ሱራፌልን የፈጠረ ርሱ በራት ጊዜ ወገቡን ዘርፍ ባለው ዝናር ታጠቀ፤ እንዳያቃጥል በመፍራት የማይታይ እሳት ለሐዋርያት አገልጋይ ኾኖ አብነት ይኾናቸው ዘንድ የትሕትና ሥራን የሚሠራበትን ውሃ በኩስኩስት ቀዳ የደቀ መዛሙርቱን አለቃ ጴጥሮስንም እግሩን ሊያጥበው ጠራው"
(ሃይማኖተ አበው ዘያዕቆብ ዘሥሩግ)

@mehereni_dengl
HTML Embed Code:
2024/05/04 10:16:43
Back to Top