TG Telegram Group Link
Channel: መዓዛ ሠናይ
Back to Bottom
"ቁጡ ሰው ከመኾን ገር ሰው ወደ መኾን ከተለወጥህ፣ ጨካኝ ሰው ከመኾን ቸር ሰው ወደ መኾን ከተቀየርህ በተግባር አሳየኝ እንጂ 'ለአያሌ ቀናት ጾምሁ፤ ይህን ወይም ያን አልበላሁም፤ ወይን አልቀመስሁም፤ መሻቴን ገትቻለሁ' እያልህ አትንገረኝ፡፡ እስከ አሁን ቁጣን የተሞላህ ከኾነ ለምን ሥጋህን ታስጨንቃለህ?  ቂምና በቀል በልቡናህ ውስጥ ካሉ፥ ወይንን ሳይኾን ውኃ የምትጠጣው ለምንድን ነው?  ረብ ጥቅም የሌለውን ጾም አትጹም፤ ጾም ብቻዋን ወደ ላይ አታርግምና፡፡"

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
​​​​ምኩራብ (የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት)🌹

🍂ምኩራብ ማለት፦ ቤተ-ጸሎት ሲሆን፤ ኢየሱስ በሰንበት ቀን ከአይሁድ ምኩራብ ገብቶ ምኩራቡን ገበያ አድርገው ሲገበያዩበት አገኛቸው።

ቤቴ የጸሎት ቤት ይባላል ያለውን አላነበባችሁምን? ትዕንቢተ ኢሳይያስ ፭፮፥፯ እናንተ ግን ገበያ አደረጋችሁት በማለት በተናቸው እቃውንም ገለባበጠባቸው በሮቹንም፤በጎቹንም በገመድ አየገረፈ አባረራቸው። የዮሐንስ ወንጌል ም. ፪፥፩፯ (ማቴዮስ ፪፩፣፩፫) ደቀ መዛሙርቱም የቤትሕ ቅንዓት በላኝ ተብሎ የተጻፈው ለካ ኣሁን ተፈጸመ
ብለው አስተዋሉ። መዝ. ዳዊት ፮፰፤፱
"ቤተክርስትያንን መርዳት ከፈለክ ሌሎችን ለማረም ከማሰብ በፊት በቅድሚያ እራስን ማስተካከል ይበጃል። እራስህን ካስተካከልክ አንድ የቤተክርስትያን ክፍል ዳነ ወይም ተስተካከለ ማለት ነው። ሁሉም ሰው ይህን ማድረግ ከቻለ ቤተክርስትያን ጤናማ ትሆናለች። ስለዚህ ላስተዋለው ሰው ሌሎች ላይ መፍረድ እጅግ በጣም ቀላል ነው እራስን ማስተካከል ግን ጥረት ይጠይቃል።"

#ቅዱስ_ፓሲዮስ
"ትህትናን ውደዷት ኃጢአታችሁን የምትሸፍን ናትና፡፡ ሁሉም ኃጢአት በእግዚአብሔር ፊት የተጠላ ቢሆንም ከኃጢአቶች ሁሉ መጥፎ የሆነው ግን የልብ ትዕቢት ነው:: ራሳችሁን አዋቂ አድርጋችሁ ከፍ ከፍ አታድርጉ፡፡ ይህን ምታድረጉ ከሆነ ጥረታችሁ ሁሉ ፍሬ አልባ ይሆናል፡፡"

#አባ_እንጦንስ
በውጊያ ላይ የቆሰለ ወታደር ቁስሉ ይድንለት ዘንድ ለሐኪም ማሳየትን አያፍርም፡፡ ንጉሡም ቢሆን ከቁስሉ የዳነን ወታደር ወደ ሰራዊቱ መልሶ ይቆጥረዋል እንጂ አይተወውም፡፡ እንደዚሁ ሁሉ ጠላታችን ሰይጣን ያገኘው፣ በኃጢአት የጣለው ሰውም ኃጢአቱን በመናዘዝ የንስሐን መድኃኒት ተቀብሎ መዳንን ማፈር የለበትም፡፡

ቆስሎ ቁስሉን መናገር ያፈረና በቶሎ መድኃኒት ያልተደረገለት ወታደር ቁስሉ ወደ ካንሰር ይለወጥና አመርቅዞ መላ ሰውነቱን በመምታት ይጎዳዋል፡፡ ጉዳቱን ቶሎ የተናገረ ታማሚ ግን ታክሞ በመዳን ወደ ጦር ሜዳው ይመለሳል፡፡ ቁስሉን ባለመታከሙ ወደ ካንሰር የተለወጠበትና ያመረቀዘበት ሰው ግን ሊድን አይችልምና ወደ ጦር ሜዳው ሊመለስ አይችልም፡፡

እንደዚሁ ሁሉ በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው እንደ ወታደር ነው። በተጋድሎ ውስጥ ያለ ሰው በኃጢአት ወድቆ "በኃጢአት ወድቄአለሁ" ብሎ የተናዘዘ የንስሓን መድኃኒት ያገኛል፡፡ ኃጢአቱን የደበቀ ግን ሊድን አይችልም፡፡ ምክንያቱም ታማሚው መድኃኒት አግኝቶ ከቍስሉ ሁሉ ይድን ዘንድ በሽታውን ሁለት ዲናር ወስዶ ለሚያክመው ባለ መድኃኒት አልተናገረምና።"

(ቅዱስ አፍርሐት ዘሶርያ - በእንተ ንስሐ ገጽ 52)
"አንድ ሰው በጣም የሚወደው ወዳጁ ኅዘንና ጭንቀት ሲገጥመው ሌላ ሰውን ሳይልክ እርሱ ራሱ እንደሚሔድለት ኹሉ እግዚአብሔርም ከቀናይቱ መንገድ ወጥቶ የወደቀውን የሰው ልጅን ያነሣው ዘንድ ሌላ ሦስተኛ አካል ሳያስፈልግው እርሱ ራሱ ይቀርበው ዘንድ ሽቶ ወረደ እንጂ መልአክ ወይም የመላእክት አለቃ ወይም ከአገልጋዮቹ አንዱን እንዳልላከለት አስተውል፡፡"

(ትምህርት በእንተ ምክንያት ሐውልታት፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፥ ገጽ 161)
"የቂመኛ ሰው ጸሎት፣ በእሾህ መካከል እንደ ወደቀ ዘር ነው"

#ማር_ይስሐቅ
ሕሊናህ ኃጢአትን ከማሰብ ይጡም፡ አእምሮህም ኃጢአትን ከማስታወስ ይከልከል፡፡ ክፉን ከመመኘት ሁሉ ጡም፡፡ ዐይኖችህ ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ከመመልከት፣ ጆሮህም ከንቱ ከሆኑ ዘፈኖችና ከሐሜተኞች ሹክሹክታዎች ጠብቅ፡፡ አንደበትህ ከሐሜት፣ በሌላው ላይ ከመፍረድ ፣ከስድብ፣ ከውሸት፣ ከማታለል፣ ከሽንገላ ንግግሮች እንዲሁም ከማይጠቅሙና አጸያፊ ከሆኑ ቃላት ይጡሙ፡፡ እጆችህም ሰውን ከመግደልና የሌላውን ንብረት ከመዝረፍ ይጡሙ፡፡ እግሮችህም ኃጢአትን ለመፈጸም ከመሄድ ይጡሙ፡፡ ከክፉ ተመለስ መልካምንም ፈጽም፡፡

ቅዱስ ኤፍሬም
#የጌታ_ስቅለት_በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››  #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ
🌼ከአንደበትህ መውጣት የሌለባቸው ቃላቶች

አልችልም አትበል

ኃይልን በሚሰጠህ በክርስቶስ ሁሉን ትችላለህ
— ፊልጵስዩስ 4፥13
•••
የለኝም አትበል
አምላክህ እንደ ባለ ጠግነቱ መጠን በክብር በክርስቶስ ኢየሱስ የሚያስፈልግህን ሁሉ ይሞላብኋል
— ፊልጵስዩስ 4፥19
•••
ፍርሃትህን አትናገር
እግዚአብሔር የኃይልና የፍቅር ራስንም የመግዛት መንፈስ እንጂ የፍርሃት መንፈስ አልሰጠኽምና
— 2ኛ ጢሞቴዎስ 1፥7
•••
ጥርጣሬህንና እምነት ማጣትህን አታውጅ
እግዚአብሔር ለእያንዳንዱ የእምነትን መጠን አካፍሎታል
— ሮሜ 12፥3
•••
ድካምህን አታውጅ
እግዚአብሔር ብርሃንህና መድኃኒትህ ነው፤ የሚያስፈራህስ ማን ነው? እግዚአብሔር የሕይወትህ መታመኛዋ ነው፤ የሚያስደነግጠህስ ማን ነው?
— መዝሙር 27፥1
•••
በህይወትህ የሴጣንን የበላይነት አታውጅ
በዓለም ካለው ይልቅ በአናንተ ያለው ታላቅ ነውና።
—1ኛ ዮሐንስ 4፥4
•••
ሽንፈትን አታውጅ
በክርስቶስ ሁልጊዜ ድል በመንሣቱ ለሚያዞረን በእኛም በየስፍራው ሁሉ የእውቀቱን ሽታ ለሚገልጥ ለአምላክ ምስጋና ይሁን
— 2ኛ ቆሮ 2፥14
•••
እንኳን በሰላም አደረሳችሁ

መጋቢት 27 በዚች ቀን ጥንተ ስቅለቱ  ለጌታችን ለአምላካችን ለመድኃኒታችን ለኢየሱሰ ክርሰቶሰ  ዓመታዊ ክብረ በዓል ነው ።
ዳግመኛም በዚች ቀን የመነኮሳት አለቃ የአባ መቃርስ የእረፍታቸው መታሰቢያ ነው

ፉያታዊ ዘየማንን በምህረቱ የተመለከተ አምላክ እኛንም በምህረቱ ይጎቭኝን  ከእመቤታችን ና ከቅዱሳን ረድኤት በረከት ያካፍለን፡፡
#የጌታ_ስቅለት_በአበው

"አደምን የፈጠሩ እጆቹ በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ በገነት የተመላለሱ እግሮች በመስቀል ቀኖች ተቸነከሩ ወዮ የማይሞተው ሞተ ሞትን ይሽረው ዘንድ ሞተ ሙታንን ያድናቸው ዘንድ ሞተ የምትወዱት ሰዎች ፈጽሞ አልቅሱለት፡፡" #ቅዳሴ_ዮሐንስ_አፈወርቅ

“እጆቹን እግሮቹን በተቸነከረባቸው ችንካሮች መወጋቱንም እናምናለን፡፡ ነቢዩ ኢሳይያስ እርሱ ደዌያችንን ወሰደ ሕማማችንንም ተሸከመ፤ እኛን ለማዳን ኃጢአታችንንም ለማሥተሥረይ መከራ ተቀበለ እንዳለ፣ በባሕርዩ ሕማም የሌለበት ሲሆን በሥጋ የታመመ ነው፤ በእርሱ ከመከራ ሥጋ ከመከራ ነፍስ ድነናል አለ፡፡ በተገረፈና በተቸነከረም ጊዜ በመከራው ሁሉ መለኮትን ሕማም ተሰማው የሚል ሰው ቢኖር የተለየ የተወገዘ ይሁን፡፡” #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ሊቀ_ጳጳስ

‹‹የሚሠዋ በግ እርሱ ነው፤ የሚሠዋ ካህን እርሱ ነው፡፡ ከባሕርይ አባቱ ከአብ ከባሕርይ ሕይወቱ ከመንፈስ ቅዱስ ጋርም መሥዋዕት የሚቀበል እርሱ ነው፡፡ በፈቃዱ መከራን በሥጋው የተቀበለ መከራንም ሁሉ የታገሠ እርሱ ነው፡፡ እንደ በግ ሊሠዋ መጣ፤ በግ በሚሸልተው ሰው ፊት እንዳይናገር አልተናገረም፤ በአንደበቱ ሐሰት አልተገኘበትም፡፡›› #ቅዱስ_ጎርጎርዮስ_ዘኑሲስ

‹‹ታመመ ሞትን ከተቀበለበት ከሥጋ ጋር ተዋሕዶ በመስቀል ላይ በፈቃዱ ለሥጋውያን ሞተ፤ ባሕርየ መለኮት ሥጋን ተዋሕዶ በማኅፀን ካደረ ጀምሮ ሥጋ ገንዘቡ እንደመሆኑ በሥጋ ይኸንን ሥርዐት ፈጸመ፡፡ ለማይመረመር ለመለኮቱ ባሕርይ እንደሚገባ ደግሞ እርሱ ኅብስት አበርክቶ ሁሉን ያጠግባል፤ አይራብም፤ አይጠማም፤ አይደክምም፤ አያንቀላፋም፤ አይታመምም፤ አይሞትም፤ ሕይወትን ለሁሉ ይሰጣል፡፡ ዳግመኛ በዛ በሲኦል ተገዝተው ያሉ ነፍሳትን ያድን ዘንድ በአካለ ነፍስ ወደ ሲኦል ወረደ በመለኮቱም ሲኦልን በዘበዘ›› #ቅዱስ_ቄርሎስ_ዘእስክንድርያ
    
‹‹ሙሴም ሞትን ያጠፋ ዘንድ አልቻለም፤ እርሱንም ይዞ ገዛው እንጂ፤ ከእርሱም በኋላ የተነሡ ነቢያትንም ሁሉ ሞት ገዛቸው እንጂ፡፡ ክርስቶስ ግን በቸርነቱ ለሁሉ ሕይወትን ሰጠ››  #ቅዱስ_አቡሊዲስ_ዘሮም

‹‹ምትሐት ያይደለ በእውነት ተራበ፣ ተጠማ እንጂ፡፡ ዳግመኛም ከኃጥአን ከመጸብሐን ጋር በላ ጠጣ፤ ያቀረቡለትንም በላ፡፡ ራሱን አሳልፎ ለመስቀል ሰጠ፤ እጁን እግሩን ተቸነከረ፤ ጎኑን በጦር ተወጋ፤ ከእርሱም ቅዱስ ምሥጢር የተገለጠበት ደምና ውኃ ፈሰሰ /ወጣ/፡፡›› #ቅዱስ_ባስልዮስ_ዘቂሳሪያ
👆🏽አቤቱ ክቡር መድኃኔዓለም...

እኛ በኃጢአት እና በበደል የጨቀየን ልጆችህ ምህረትህን እንሻለንና ቶሎ ድረስልን! እኛን እንደሚያገሳ አስፈሪ አንበሳ ሊውጠን የሚያንዣብበው ዲያብሎስ በእሳት ክንድህ ድል አድርግልን:: ከአንተ ጋር ለመዋቀስ የሚያስችል ብርታት የለንም ፤ ኃጢአታችንን አምነን ተቀብለናልና:: አቤቱ በነጭ ልብስ ላይ እንደፈሰሰ ደም ቀልታ እና ደምቃ የምታየውን ኃጢአታችንን ደምስስልን!

አቤቱ... በደሉኝ ብለህ ቅዱስ መንፈስህን አትውሰድብን!  አንተ ጋሻችንም ጦራችንም ነህና ፤ በከንቱ ምድራዊ መመካት እንዳንመካ በመንፈሳዊ ጥበብህ አስተምረን:: ለአንተ ቅድስት እናትህ ፣ ለእኛ ደግሞ የተወደደች እመቤታችን ስለምትሆን ቅድስት ድንግል ማርያም ብለህ ሁሌም ምህረትህን አስቀድምልን!

እንኳን ለቅዱስ ክቡር መድኃኔዓለም በዓል በሰላም አደረሰን!

ኦርቶዶክሳዊ ወጣት
#የፍቅር_ሥራ_ይህች_ናት

ባልንጀራውን የሚረዳውን ክብር ይግባውና እግዚአብሔር ይረዳዋል፡፡ ለወንድሙ የሚነቀፍበትን ስም የሚያወጣውን ፈታሒ በርትዕ እግዚአብሔር እንዲሰደብ ያደርገዋል፡፡ ክፉ ስለ ሠራ ወንድሙን በቤቱ ለብቻው ሆኖ የሚመክረው ሰው ግን በምክሩ ዐዋቂ ይሆናል፡፡ ወንድሙን በዐደባባይ የነቀፈ ግን ኀዘን ያጸናበታል፡፡ ከሰው ተለይቶ ወንድሙን የሚመክር ሰው እነሆ የፍቅሩን ብዛት ያስረዳል፤ በባልንጀሮቹ ፊት የሚነቅፈው ግን የቅናቱን ጽናት ያስረዳል፣ የምቀኝነቱን ጽናት አስረዳ፡፡ 

ወዳጁን ተሠውሮ የሚመክር ሰው ብልህ ባለመድኃኒት ነው:: ያ እንዳዳነው መክሮ አስተምሮ ያድነዋልና፡፡ ወንድሙን በብዙ ሰው ፊት የሚያመሰግነው ሰው እሱ እውነተኛ ጠላቱ ነው፣ በውዳሴ ከንቱ ይጎዳ ብሎ ነውና።

ኀዘን ያለበት የርሕራሄ ምልክቱ የበደሉትን ሁሉ ይቅር ማለት ነው። የጠማማ ምልክቱ ጸብ ክርክር ነው፡፡ ወደ ክብር የሚያደርስ ረብህ ጥቅም ያግኝ ብሎ የሚመክር፣ የሚያስተምር በፍቅር ይመክረዋል፣ ያስተምረዋል፡፡ ቂም በቀል የሚሻ ሰው ፍቅር የለውም፡፡ አንድም እበቀለዋለሁ ብሎ የሚመክር ከፍቅር የተለየ ነው፡፡

ስሙ ይክበርና እግዚአብሔር በፍቅር ይመክራል፣ ያስተምራል፣ እበቀላለሁ ብሎ ያይደል፡፡ እሱስ በምሳሌው የተፈጠረው ሰውን ለማዳን ይገሥጻል፡፡ አንድ ጊዜስ እንኳን ቂም አይዝም፣ መዓትን አያዘጋጅም፡፡ የፍቅር ሥራ ይህች ናት፣ በቅንነት ትገኛለች፡፡ ቂም ለመያዝ እበቀላለሁ አትልም፣ በፍቅር ሰውን መናገር ነው።

ብልህ የሚሆን ቅን ሰው ክብር ይግባውና እግዚአብሔርን ይመስለዋል፡፡ ሰውን ክፉ ስላደረገ እበቀለዋለሁ ብሎ አይገሥጸውም፣ ሊመክረው ወዶ ነው እንጂ ሌሎችንም ለማስፈራት ነው እንጂ። ተግሣጽስ በፍቅር ካልሆነ ተግሣጽ አይባልም፡፡ በጎ ነገር ያደርግልኛል ብሎ በጎ የሚሠራ ኋላ ፈጥኖ ይተዋል፡፡

(#ምክር_ወተግሣጽ_ዘማር_ይስሐቅ - በዲ/ን ሞገስ)
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ይህን ያህል ቀን ጾምኩ አትበሉኝ፡፡ ይህን አልበላሁም ወይም ያንን አልበላሁም፣ የወይን ጠጅ አልጠጣሁም አትበሉኝ።

ይልቁንስ ከግልፍተኝነት ወደ ገርነት፣ ከጭካኔ ወደ ደግነት የተሸጋገርኽ እንደሆነ አሳየኝ፡፡ በአንተ ውስጥ ጥላቻና ቂም ቢኖሩ፣ በወይን ፋንታ ውኃ ብትጠጣ ምን ይጠቅማል? ጾም ብቻውን ስማያዊ ምንዳ አያስገኝምና፤ ትርጉም በሌለው በባዶ የፆም ሥርአት ራስህን አታስገዛ።

#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
#እግዚአብሔርን_መፍራት

ከፍርሃታችን የሚመጡትን ጥቅሞች ታያላችሁ? ፍርሃት ባይጠቅም ኖሮ አባቶች ለልጆቻቸው ሞግዚቶችን አይቀጥሩም፤ ሕግ አውጪዎችም በከተሞች ላይ ዳኞችን አይሾሙም ነበር። ከገሃነም የበለጠ የሚያስፈራስ ምን አለ? እናም ገሃነምን ከመፍራት የበለጠ የሚጠቅም ነገር የለም:: ገሃነምን መፍራት ወደ እግዚአብሔር መንግሥት ይመራናልና፡፡ ይህ ፍርሃት ባለበት ምቀኝነት ቦታ የለውም፤ ይህ ፍርሃት ባለበት የገንዘብ ፍቅር ቦታ የለውም፤ ቁጣ ይጠፋል፣ ክፉ ምኞቶች ይወገዳሉ፡፡

አንድ ዘብ ሁልጊዜ ነቅቶ በሚጠብቅበት ቤት ውስጥ ሌባ፣ ዘራፊ ወይም ክፉ አድራጊ ሊመጣ እንደማይችል ኹሉ ፍርሃት አዕምሯችንን ሲይዝ፣ ልቅ ምኞቶች በቀላሉ አያጠቁንም፡፡ ይልቁንም ሸሽተው በየአቅጣጫው፣ በፍርሀት ምክንያት ይባረራሉ፡፡

ነገር ግን ፍርሃት ማባረር ብቻ አይደለም ጥቅሙ፤ ክፉ ፍላጎቶቻችንን ማስወገድ ብቻ ሳይሆን፣ እያንዳንዱን በጎነት ወደ ነፍሳችን ለማምጣትም ይጠቅማል፡፡ ፍርሃት ባለበት ለጋስ መሆን አለ፤ የጸሎት ብርታት፣ ትኩስ የሚደጋገም እንባ እና ለንስሃ የነቃች ነፍስ አለች። ኃጢአትን የሚሸፍን በጎነትን የሚያብበው በማያቋርጥ የፍርሃት ሁኔታ ውስጥ ስንሆን ነው:: ስለዚህ በፍርሃት የማይኖር ሰው ልቡ ደንድኖ የሰይጣን ባርያ እንደሚሆን ኹሉ፣ በፍርሃት የሚኖር ሰው በማያውቀው ጎዳና እንደማይጓዝ ኹሉ፣ እግዚአብሔርን መፍራት በትክክለኛው የጥበብ መንገድ ይወስደናል፡፡

(#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ - #የነፍስ_ምግብ ገጽ 20 #በፍሉይ_ዓለም_የተተረጎመ)
Audio
በሰማይ ደመና ይመጣል
                         
Size 27MB
Length 1:17:39

  በርዕሰ ሊቃውንት አባ ገብረ ኪዳን ግርማ
"እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እናንተም የምትወዱት ልጆቼ ሆይ! ወርሐ ጾሙ ሲያልቅ ባዶ እጃችንን እንዳንገኝ በኹሉም ረገድ እንበርታ ብዬ እማልዳችኋለሁ፡፡ በጾም እየደከሙ ሳለ የጾምን ዋጋ ሳያገኙ መቅረት አለና፡፡ "ይህስ እንደምን ነው?" ያላችሁኝ እንደኾነም፦"ከምግበ ሥጋ እየጾምን ሳለ የኃጢአትን መብል ስንመገብ፣ሥጋን ከመብላት ተከልክለን ሳለ የድኻውን ቤት ስንበረብር፣ ወይንን ከመጠጣት ታቅበን ሳለ በክፉ መሻቶች ስንሰክር፣ ቀን ሙሉ ምግብ ሳንበላ ውለን ሳለ ዓይናችን ግን ክፉ ነገሮችን ሲመለከት ነዋ" ብዬ እመልስላችኋለሁ፡፡"
(ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ)
HTML Embed Code:
2024/06/12 16:59:49
Back to Top