TG Telegram Group Link
Channel: ሁለገብ
Back to Bottom
#Mekelle

የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ሀይል ዛሬ መቐለ ከተማ መግባቱን አሳወቀ።

ዛሬ መቐለ የገባው የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ልዩ ኮማንዶ እና የወንጀል ምርመራ ቡድን ነው።

የፌዴራል ፖሊስ ከ 'ሀገር መከላከያ ሰራዊት' ጋር በመቀናጀት በህግ የሚፈለጉ የህወሓት ተፈላጊ አባላትን ማደን መጀመሩን ገልጿል።

የኮማንዶ ቡድኑ በመቐለ ከተማ በሚያደርጋቸው አሰሳዎች እና የተለያዩ ኦፕሬሽኖች እንዲሁም በወንጀል ምርመራ ቡድኑ የሚገኙ ውጤቶችን በቀጣይ ለህዝቡ ይፋ ይደረጋል ተብሏል።

@livlav
በስፔን ቫሌንሺያ በተካሄደ የግማሽ ማራቶን ሩጫ ኢትዮጵያዊቷ ገንዘቤ ዲባባ 1:05:18 በመግባት አሸናፊ ሆናለች።

@livlav
🚑 አሊሰን, ቫንዳይክ, አርኖልድ, ጎሜዝ, ማቲፕ, ሚልነር, ፋቢኒሆ, ሄንደርሰን, ቲያጎ, ኬይታ, ቻምበርሊን ፣ ሻኪሪ።

እነዚህ ሁሉ ተጫዋቾች በዚህ የውድድር አመት ሊቨርፑል በጉዳት ያጣቸው ተጫዋቾች ናቸው። የተወሰኑ ተጫዋቾች ተመልሰዋል ነገር ግን አሁንም በጎል ተበልጠው 2ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።😮

@livlav
አብዛኞቹ የትግራይ ከተሞች እስከ እሁድ ድረስ መብራት እንዲያገኙ እየተሰራ ነው‼️

በትግራይ ክልል ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያዎችን ወደ ቀደመው አገልግሎታቸው እንዲመለሱ በማድረግ የክልሉ አብዛኞቹ ከተሞች እስከ መጪው እሁድ መብራት እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑ ተገለፀ።የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እንዳስታወቀው በህወሓት አማካኝነት ጉዳት ደርሶባቸው የነበሩ የኃይል ማስተላለፊያዎች በአፋጣኝ ጥገና እየተደረገላቸው እንደሆነ እና አንዳንድ አካባቢዎች ላይም በከፊል መጠናቀቁን ይፋ አድርጓል።

@livlav
@livlav
#Mekelle

ዛሬ መቐለ የደረሰው ደጋፍ 12 ሺህ 400 ኩንታል ስንዴ ነው።

በሌላ በኩል በዛሬው ዕለት የአስቸኳይ ጊዜ ድጋፍ የሚሆን 7 ሺህ ኩንታል ዱቄት ከአዳማ ከተማ እየተጫነ እንደሆነ የአደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን አሳውቋል።

በተጨማሪም 15 ሺህ ሜትሪክ ቶን የድጋፍ እህል ለመላክ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን አስታውቋል።

@livlav
@livlav
በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን የመከላከያ ሚኒስቴር አስታወቀ‼️

በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍትሻ ከ426 ሺህ በላይ የክላሽ ጥይት፣ ከ3500 በላይ የብሬን ጥይት፣ በርካታ ቁጥር ያላቸው ክላሽንኮቭና ሽጉጦች፣ ከ1100 በላይ ልዩ ልዩ የእጅ ቦንቦች መያዙን የመከላከያ ሚኒስቴር ለዋልታ በላከው መግለጫ አስታውቀል፡፡በዕዙ የ32ኛ ክፍለ ጦር 3ኛ ብርጌድ ዋና አዛዥ የሆኑት ኮሎኔል መላኩ ገላነህ እንዳሉት ከሃዲውን ሃይል ለማጥፋት ከተደረገው የህግ ማስከበት ዘመቻ መጠናቀቅ በኋላ በማይጨው ከተማ በተደረገ የቤት ለቤት ፍተሻ በርካታ ቁጥር ያላቸው የጦር መሳሪያዎች መገኘታቸውን አረጋግጠዋል።ከተማዎችን የጦርነት አውድማ ለማድርግና ዜጎችን ለከፋ ችግር ለመዳረግ በማለም ሰራዊት በህግ የሚከለከልባቸው ቦታዎች ተለይተው በእምነት ተቋማት፣ በመማሪያ ክፍሎች፣ በአገልግሎት መስጫ ተቋማትና በመንግስት መስሪያ ቤቶች በርካታ ቁጥር ያለው የጦር መሳሪያ ተከማችቶ መገኘቱንም ዋና አዛዡ አረጋግጠዋል።
@livlav
የ2013 ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ነገ በሚደረጉ ሁለት ጨዋታዎች ይጀምራል።

📆 ቅዳሜ ታህሳስ 3

ቀን 04:00 | ሰበታ ከነማ ከ ድሬደዋ ከነማ
ከሰዓት 09:00 | ቅዱስ ጊዮርጊስ ከ ፋሲል ከነማ

📆 እሁድ ታህሳስ 4

ቀን 04:00 | ኢትዮጵያ ቡና ከ ወልቂጤ ከተማ
ከሰዓት 09:00 | ጂማ አባጅፋር ከ አዳማ ከተማ

📆 ሰኞ ታህሳስ 5

ቀን 04:00 | ወላይታ ዲቻ ከ ሀዲያ ሆሳና
ከሰዓት 09:00 | ባህርዳር ከነማ ከ ሲዳማ ቡና

ጨዋታዎቹን በቀጥታ ስርጭት ለማስተላለፍ ሱፐርስፖርት ጊዚያዊ ስቱዲዮውን በአዲስ አበባ ስታዲየም ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል።

@livlav
@livlav
ነገር ተጀመረ ይሔን መስማት ከቻልክ እድለኛ ነክ ምክር ቢጤም ይመስላል እናንተዬ አድምጡኝ አየሁ አየሁ የጠላሁትን ለመተንፈስ ወደድኩ እባካቹን ሀገራችንን ለቀቅ አድርጉ በስሟ እየማላችሁ መቀመቅ አትክተቷት እኛ 2 ኢትዮጵያ አናውቅም አንዲት ኢትዮጵያ እያላቹ አታሰልቹን አንዳንዴ ኤርትራን እየቆጠሩ ነው እንዴ እንደዚ ሚሉት ብዬ አስባለሁ በስሟ እየማላችሁ አትግደሉዋት ለቀቅ አድርጓት ሀሜት አትወድም ስራን እንጂ አያቶቻችን እያልን እንጃጃላለን የተደፋ ውሃ ቀና ሳናደርግ ከንቱ ፉከራ ብቻ ከቻልክ የሚታይ ስራ ስራ እና እንደ አያቶችክ ታሪክ ሰርተክ እለፍ ይሔን ስል ሁሉም ሰው ወደ ፖለቲካ ይሮጣል ታሪክ የሰራ መስሎት ታሪክ እንደተሰራበት ሳያውቅ ይችን ብያለሁ ለምሽታችን በዚህ አይቆምም መልካሙን አበርትተን ክፉውን አውግዘን በስራ ታጅበን ለራሳችን ቅድሚያ ቀና ብለን ሀገር እናቀናለን


ሼር ይደረግ

መልካም ምሽት


@livlav
@livlav
👉 ፓኪስታናዊው ኻን ባባ የ24 አመት ወጣት ሲሆን 440 ኪ.ግ ይመዝናል ። ታዲያ ይህ ወጣት በቀን 5ሊትር ወተት 4 ዶሮዎች እና 36 እንቁላል ይበላል ። እርሶስ በቀን ምን ያህል ይመገባሉ ?

@livlav
የ3 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የቦንብ ፍንዳታ !

ጠዋቱ 2፡30 ሠዓት በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 6 ልዩ ቦታው ስልጤ መስኪድ ጀርባ ለልማት በፈረሰ ክፍት ቦታ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች ተጥሎ በተገኘ የእጅ ቦንብ የጎዳና ተዳዳሪ የሆኑ የ3 ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ በ5 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

ከፍንዳታው ጋር በተያያዘ ያለው የምርመራ ሂደት እየተጣራ መሆኑ ተገልጿል። የምርመራ ውጤቱ እንደተጠናቀቀ ለህብረተሰቡ ግልጽ ይደረጋል ተብሏል።

በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን የልዩ ልዩና የተደራጁ ወንጀሎች ምርመራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ኮማንደር አለማየሁ አያልቄ ባስተላለፉት በተለያዩ ቦታዎች እንደ አልባሌ በሚጣሉ ቦንቦችና ፈንጂዎች ንፁሀን ሰለባ መሆናቸውን አስታውሰው ህብረተሰቡ ምንነታቸው ያልታወቁ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት ከመነካካት በመቆጠብ ለሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጥቆማ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

Via Addis Ababa Police Commission
@livlav
በ4ኛ ሳምንት ጨዋታ

🎯 ማንቸስተር ዩናይትድ 1-6 ቶትንሃም

🎯 አስቶን ቪላ 7-2 ሊቨርፑል

በ14ኛ ሳምንት ጨዋታ

🎯 ማንቸስተር ዩናይትድ 6-2 ሊድስ ዩናይትድ

🎯 ክርስትያል ፓላስ 0-7 ሊቨርፑል

🏃‍♂

@livlav
ስራ ልትቀጠር #ለኢንተርቪው ሄደህ "ማክስህ ቆሻሻ ነው?" ሲልህ

አደለም ከወዳደቀ እቃ ስለሰራውት ነው


😆😂🤣
Join👉 @livlav
ሰላም የሁለገብ ቤተሰቦች እንዴት ናችሁ?? ቻናላችን ከዚህ በፊት ብዙም እየሰራ እንዳልሆነ ይታወቃል። አሁን ላይ ግን ትላልቅ ስራዎችን ለመጀመር ወስነናል በቅርቡ ወደ ስራ እንገባለን ይጠብቁን
እንዴት አደራችሁ የሀገሬ ልጆች??

በማለዳ መንቃት መልካም ነው ቀንን ብሩህ ያደርጋል ግን ለምን ይሆን አብዛኛው ሰው እያወቅን ይሔን ጠዋት መነሳት አንችልም?? መልሱን ለናንተ ልተው እና በጠዋት በመነሳት ቀናችንን ብሩህ እናድርግ መልካም ቀን❤️
ሰላም ሰላም እንዴት ናችሁ??

አንድ እያስከፋ ደስ የሚያሰኝ ዜና ሰማሁ በግፍ የተገደለው ልጃችን በአለም እጅግ ትልቁ የሆነው ግራሚ አዋርድ ላይ መነሳቱን እና ታሳቢ መደረጉ ደስ ብሎናል ትልቅም ድል ነው። ማን ያውቃል ባለ ትልቅ ተሰጥኦ ወጣት ነበር የተሻለ ሰርቶ ተወዳዳሪ መሆን ሚችል ታላቅ ሰው ነበር💔💔💔 ነብስ ይማር ጀግናው🕯🕯🕯



በሌላ በኩል ደግሞ በእግር ኳስ ተንታኝነት እና ጋዜጠኝነት የምንወደው እና ምናደንቀው መንሱር አብዱል ቃድር የፈረንሳይ ሚድያ በሆነው ካናል ፕላስ ቻናል ላይ ስራ ከሰሞኑን እንደ ሚጀምር ሰምተናል እኛም ጀግናው ይገባካል በርታልን ከነ ጋሽ ይድነቃቸው ተሰማ ተርታ ተሰልፈክ የሀገርክን ስም እንደ ምታስጠራ ተስፋ እናደርጋለን❤️🙏🙏


እኔም ለምሽት ይችን ልበላቹ ብዬ ነው ነገም ሌላ ቀን ነው በሌላ ዝግጅቶች የምንቀርብ ይሆናል እስከዛው ሰናይ ምሽት🙏🙏🙏🙏

@livlav
እንግዲ መችም ጀንበር ስታዘቀዝቅ ሀሳባችንም እንቅልፍ ወደሚሉት ብርሃን ያመራል የቀኑን የሀሳብ ብዛት ትቶ ወደ ብርሃን እንቅልፍ

ሸጋ ለሊት ተመኘን

@livlav
ሰላም ለናንተ ይሁን??

እሁድን ለሳምንታት የደከመ እኛነታችንን ለቀጣዩ ሳምንት እኛነታችን መስተካከል ልክ እንደ እጅ መንሻ የተሰጠችን ቀን ናት። እሁድን ሁሌም አዕምሮን በሚያድስ ነገር እናሳልፋት።

መልካም እለተ ሰንበት🙏

@livlav
ቀንን ቀን እየተካው በሔደ ቁጥር የኛም እድሜ እኩል ይነጉዳል ባለን ጊዜ በአግባቡ እንጠቀም እና የተሻለ ነገር እንስራ


መልካም ቀን❤️
መልቀም የማትችለውን አትዝራ ሁሉን ነገር ስትሰራ በሀላፊነት ይሁን

መልካም ቀን🙏🙏

@livlav
HTML Embed Code:
2024/04/27 11:24:08
Back to Top