TG Telegram Group Link
Channel: መንፈሳዊ ኪነ ጥበብ ብቻ
Back to Bottom
የልደትሽ ቀን ልደታችን ልጅሽ ደሞ ህይወታችን ነው🙏🙏🙏

እንኳን አደረሳችው ግንቦት 1
ዮም ፍስሐ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም

ሃና እና ኢያቄም ፣ ተግተው ቢማልዱ
የአምላክን እናት ድግልን ወለዱ
ጸሐይን የምትወልድ ፣ ጨረቃን አመጡ
ለጨለማው አለም ፣ ብርሃን አወጡ
በአንቺ የልደት ቀን ፣ እኛም ተወልደናል
ተጠምቆ ተሰቅሎ ፣ ልጅሽ አድኖናል
ካለአንቺ እማ ልደት ፣ ይሄ መች ይሆናል
እውነት በልደትሽ ፣ ልደት ተሰቶናል።

እንኳን ለእናታችን ለእመቤታችን ለአማላጃችን ለቅድስተ ቅዱሳን ለእመቤታችን የልደት በዓል አደረሰችሁ።

ፍቅሯን በልቦኖቻችን ውስጥ ታኑርብን ታጽናብን ❤️❤️

በልደቷ ለዓለም ሁሉ ድኅነትን ያስገኘች እናታችን በስደት በመከራ በጦርነት በርሃብ በስደት እና በእርዛት ላሉት ሁሉ የሰላም ፍቅርን እና አንድነትን ከልጇ አማልዳ ትላክልን። አሜን
@kinexebebe
ልደታ ለማርያም ፩🙏🙏
ከሀና ማህጸን የአዳም ተስፋ ታየች
በኀጢአት የደረቀው የሰው ህይወት በድንግል መወለድ በተስፋ ለመለመ
ጨለማው ዓለም በድንግል መወለድ ብርሃን ሆነ
የሊባኖስ ተራራ በብርሃን ተከበበ
ሊባኖስ የብርሃን መቀነት ታጠቀች
ሊባኖስ በብርሃን አጥር ታጠረች
ኢያቄም የደስታ ካባ ደረበ
ሀና የደስታ አክሊል ደፋች
የብርሃን እናት ድንግል ተወልዳለታለችናችና
የዓለም ሞት በህይወት ተቀየረ
ሰማይ ከሀና ማኅፀን ተወለደች
የሐና ማሕጸን የሰማዯ መውጫ ሆነ
የውርስ ኀጢአት ከድንግል ራቀ
ሰወች ሁሉ በውርስ ኀጢአት በሚወለዱበትን ያለውርስ ኀጢአት ንጹህ ሁና ወላዲተ አምላክ ተወለደች
ከኢያቄም አብራክ ነጭ እንቁ አበራች
ከሀና ማኅጸን ጸአዳ ርግብ ወጣች
የሀና ታሪክ ተቀየረ
ሀና የእግዚአብሔር ወልድ አያቱ ተባለች
ሰማያት ሰለሰማዯ መወለድ ዝማሬ ዘመሩ
ምድር ሰማይን በመሸከሟ እልል አለች
ሰማዯ በምድር ታየች
የአበው ተስፋ መሰረት ተጣለ
አይሁድ አፈሩ
ቤተ ክረርስቲያን የድንግልን መወለድ አበሰረች
በ5485 ዓመተ ዓለም ድንግል ተወለደች
ፀሐይ ሊወጣ ሰማይ ተገኘች
ሰማዯ ከሰው ተወልዳ ፀሐይን ወለደች
እመቤቴ በመወለድሽ የአበው ተስፋ እውን ሆነ።
የድንግል ማርያም አማላጅነት አይለያችሁ🙏🙏
@kinexebebe
ዳግም ሥራኝ

በሰጠኸኝ ሳላመሰግን ባጣሁት ያማረርኩህ
ዝቅ ብዬ ሳላይ በበላዬ ያስጨነቅኩህ
በሰው ላይ ጣቴን የምቀስር
ወንድሜን በግፍ የማሳስር
አስታራቂ መስዬ የአንዱን ለአንዱ የነገርኩ
በሰላም በፍቅር ፈንታ ፀብ ጥላቻን ያፋፋምኩ
ነጠላዬን አስረዝሜ ማለዳ ከማደሪያ
ማምሻ ከሰኬም የምገኝ
ገና ነው ስል የመሽብኝ
አሥራ አንደኛው ሰዓት ላይ ቆሜ ዛሬም ኃጢአት ያናወዘኝ ሥራዬ ተዘበራርቆ ስባዝን ውዬ ስባዝን ያደርኩኝ
አጎንብሼ የምማትር የኃጢአት ሽክም ያጎበጠኝ
ለኔ ስትል ሰው መሆንክን የረሳሁኝ
ውለታ ግርፋት ሞትህን እንኳን ያላሰብኩኝ
ለአፍታ ዳግም ምጽአትህን ቸል ያልኩህ
የአዳምን ጩኸት ጮኸህ ጎንህን በጦር ተወግተህ የከፈልከውን ዋጋ ከልብ ያላሰብኩኝ
በስም ብቻ የምኖር በደልን የካብኩኝ
ልቤ ከዓለም ሆኖ አገልጋይህ መስዬ
ከጠላት ጋር ውዬ ከእርሱ ጋር ተዋውዬ
በኃጢአት ደምቄ
በቂም አሽብርቄ
ለሰውማ አለሁ ለወጪ ለገቢ በዓይን እታያለሁ
በሰገነት ቆሜ ለክብርህ እዘምራለሁ
ነጠላ ቀሚሴን አስረዝሜዋለሁ ጠዋት እና ማታ እመላለሳለሁ
በጎ እንደሚሠራ ጎንበስ ቀና እላለሁ
የጽድቅ አበባዬ ጠውልጎ የኃጢአት ችግኜ አፈራ
አዝመራው ለምልሞ በለሱም የጎመራ
ለዓለም ሳጎበድድ ጊዜዬን የጨረስኩ
በኃጢአት ብል ተበልቼ ባዶ ሆኜ የቀረሁ
ክርስትናዬን በነጠላ የሽፈንኩ
የራሴ ምሶሶ እያለ ጉድፍ ለማውጣት የሮጥኩ
እኩይ ግብሬ ጸጽቶኝ በንስሐ ያልታጠብኩ
በተሰጠኝ የማልረካ ምስጋና የተሳነኝ
የራሴ ወርቅ ተቀምጦ የሰው ነሐስ የሚያምረኝ
ለሰዎች ያለሁ መስዬ ከእቅፍህ የወጣሁኝ
አካሌ ከመቅደስ ልቤ ከዓለም የሆነብኝ
ጠፋ ብዬ የምፈልግ ለራሴ ፈላጊ የሚያሻኝ
የተሰጠኝ መና ሰልችቶኝ የግብጽን ሽንኩርት የናፈቅኩኝ የሚጠቅመኝን ትቼ የማይጠቅመኝን የፈለግኩ
እንደ ዴማስ ተማርኬ ዓለም ያስቀረችኝ
በውበቷ ገመድ አስራ የሳበችኝ
በቤትህ ውስጥ የጠፋሁ
...ድሪምህን ዳግም ሥራኝ።
@kinexebebe
ልሂድ አደን

ልቤ ተነሳስቶ፣ ጽድቅህን ፍለጋ፣
ከማዳንህ ጋራ ፡ ስምህን ሊጠጋ፣
ልሂድ ወደ ዱሩ፣ ካ'ባቶች ማደሪያ፣
ከለምለሙ መስክህ ከጽድቅ መነኻርያ፣
ዓለምን 'ሚረግጡት፣ ሰማዩን ሚመኙት፣
እሳቸውን ጥለው፣ ...ሰዉን ከሚወዱት፣
ስለስምህ ብለው፡ .........ከዋሻ ከገቡት፣
ቀንና ሌት ተግተው፣ ወንጌሉን ከኖሩት፣
የምድሩን ንቀው ፣ ቃልህ ጣፍጧቸው፣
የማዳንህን ሥራ ማንም ላይቀማቸው፣
እንትፍ ዓለሚቱ፣ ከነማርሽ ጥፊ፣
እየጎመዘዘ ፣ዓለማቸው ሰፊ፣
ኬት ይገኛል ያንተ ፣ልቡን ላልከፈተ፣
በደልን ምኞቱን ፣ ጉድጓድ ካልከተተ፡
በወንጭፍ አይቀልቡት፣ በጦሩ አይወጉት፡
ጅማሬው ይጥላል ፣ ልቡናን ካልረቱት፤
አደን ልሂድ ልውጣ ልጀግን ልጠንክር ፣
እኔም እዛ ልሂድ ፣ ከቅዱሳን አጥር
ልጨክን ላምርረው፣ ጦሬን ልታጠቀው፣
ልቤን አሸንፌ፣ ዓለሙን ልስቀለው፤
@kinexebebe
Forwarded from የያሬድ ውብ ዜማ🕇🕆 (ይለይብኛል12 @webzema)
ሞክሩት መሞከሩ አይከፋም
https://hottg.com/tapswap_mirror_bot?start=r_394755665 🎁 +2.5k Shares as a first-time gift
የተፈተነ ህይወት ድራማ.pdf
86.3 KB
መንፈሳዊ ድራማ

🔴የተፈተነ ህይወት
የራሄል እንባ ያርግልሽ ! ተውኔት.docx
32.7 KB
መንፈሳዊ ተውኔት

🔴የራሄል እንባ ያርግልሽ
HTML Embed Code:
2024/06/05 13:55:32
Back to Top