Channel: የጅማ ሀገረ ስብከት መገናኛ ብዙኃን🇪🇹
"ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድን የሚዘክር ልዩ መርሐ ግብር በጅማ ፈ/ሰ/ቅ/ገብርኤል ቤ/ክ ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ት/ቤት አማካኝነት ተካሄደ"
ሕዳር 15 ቀን 2017 ዓ.ም በጅማ ፈለገ ሰላም ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን ፍኖተ ሎዛ ሰንበት ት/ቤት አማካኝነት "ዝክረ ቅዱስ ያሬድ" በሚል ርዕስ ኢትዮጵያዊው ሊቅ ቅዱስ ያሬድን የሚዘክር ልዩ መርሐ ግብር በሃኒላንድ ሆቴል ተካሄደ።
በዕለቱ የሊቁ ቅዱስ ያሬድን የሕይወት ታሪክ ጨምሮ ለኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እና ለሀገራችን ኢትዮጵያ ያበረከታቸውን አስተዋጽኦዎች በሙሉ የሚገልጽ ጥናታዊ ጽሑፍ በሊቀ ጠበብት ኢንጅነር ገብረ ማርያም አበበ የቀረበ ሲሆን ፥ ቅዱስ ያሬድ ለቤተ ክርስቲያን ባለውለታ አባት መሆኑን የሚያወሱ ልዩ ልዩ መርሐ ግብራት ቀርበዋል።
በመርሐ ግብሩ ላይ ክቡር መልዐከ ሠላም ተስፋ ሚካኤል አሰፋ የጅማ እና የየም አህጉረ ስብከት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ ክቡር ላዕከ ወንጌል መ/ር ባዬ የጅማ እና የየም አህጉረ ስብከት የሰንበት ት/ቤት ማደራጃ መምሪያ ኃላፊ ፣ የአድባራት አስተዳዳሪዎች ፣ የቅዱስ ያሬድ የመንፈስ ልጆች የሆኑ ሊቃውንተ ቤ/ክ መምህራን ፣ የሰንበት ት/ቤቶች ተወካዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በሙሉ ተገኝተዋል።

HTML Embed Code: